Saturday, October 1, 2016

የትግሬ ወያኔ ቡድን የአርማጭሆን አብድራፊ የምትባል ከተማ ለመውሰድ እያሰፈሰፈ ነው::


የትግሬ ወያኔ ቡድን ወልቃይትን : ጠገዴን : ጠለምትን እና ሁመራን ከጎንደር በመውሰድ ሳያቆም አሁን ደሞ በራሱ ህገ መንግስት የአማራ ክልል ነው ያለውን ቦታ ለመውሰድ እያሰፈሰፈ ነው::

ነገሩ እንዲህ ነው:: በሰሜን ጎንደር ዞን የምእራብ አርማጭሆ ወረዳ የምትገኝ #አብድራፊ የምትባል ከተማ አለች::

ከተማዋ ከዛሬ አምስት አመት በፊት #የምእራብ_አርማጭሆ ወረዳ ዋና ከተማ ነበረች::

ከተማዋ ለሱዳን ቅርብ የሆነች እና በሰሊጥ ምርት የታወቀች ከተማ ናት::

ወያኔ ይችን ከተማ ለራሱ ለማድረግ ስለፈለገ ከዛሬ አምስት አመት በፊት የምእራብ አርማጭሆ ወረዳ ዋና ከተማ ለሱዳን ቅርብ የሆነችው አብድራፊ መሆኗ ቀርቶ ከሱዳን ወደ ጎንደር 25ኪሜ ገባ ብላ የምትገኘው #አብርሃ ጂራ የምትባለው ከተማ እንድትሆን ወስኗል::

ከዚህ ውሳኔ በኋላም የአብድራፊ ከተማ የበለጠ ወደ ትግራይ ኢንተግሬት እንድታደርግ ለማድረግ ከሁመራ እና ዳንሻ ወደ አብድራፊ የሚወስድ አስፓልት መንገድ ገንብቷል::

የአማራው ተውካይ ነኝ የሚለው ብአዴን ግን ከተማዋን ወደ መተማ እና ጎንደር ለማስተሳሰር መንገድ አልገነባላትም:: የአብድራፊ ከተማ አንገረብ እና አዲስ አለም የሚባሉ ሰፈሮች አሏት:: የከተማዋ ሃላፊ (ትግሬ) ከትግራይ ክልል ትግራዮችን እየጠራ አዲስ አለም በሚባለው ሰፈር ቦታ እየሰጣቸው ነው:: በአንጻሩ ከተማዋ የአማራ ክልልም ብትሆንም አማራወች ከተማዋ ላይ ቦታ የማግኝት እድላቸው ተዘግቷል::
አማራው ታግሎ ሁሉንም የተወሰዱበትን መሬት ካላስመለሰ በቀር የትግሬ ወያኔ ወረራ መቸም አያቆምም::

No comments:

Post a Comment