Monday, October 17, 2016

የአንድን ቡድን ብቻ የልብ ትርታ የሚያደምጥ ሥርዓት ለመፍጠር ጥረት ማድረግ ጥፋቱ ብዙ እየኾነ ይሄዳል፡፡


የአንድን ቡድን ብቻ የልብ ትርታ የሚያደምጥ ሥርዓት ለመፍጠር ጥረት ማድረግ ጥፋቱ ብዙ እየኾነ ይሄዳል፡፡ Akemel Negash
ኢሳትና ቪዥን ኢትዮጵያ አዘጋጁት ከተባለው ጉባዔ ጋር በተያያዘ እየተነሳ ባለው ቅራኔ ‹‹ሙስሊሞች አልተወከልንም አሉ›› የሚል ሐሳብ ብቻ ለምን ተንሟሎ እየቀረበ እንደኾነ አልገባኝም፡፡ ጉባዔውም ኾነ አጋፋሪዎቹ የአንድ ካምፕ (ዩኒየኒስት በሉትም ራይት ዊንግ) ሰዎች ናቸው፡፡ ስለ ኢትዮጵያ ሽግግር ጊዜ የራሴን ሰፈር ልጆች ብቻ ይዤ ልወያይ ማለት ተገቢ አይደለም፣ ብዙ ቡድኖች ባሉት የኢትዮጵያ ፖለቲካ መድረክ የአንድን ቡድን ብቻ የልብ ትርታ የሚያደምጥ ሥርዓት ለመፍጠር ጥቂት እንኳን ጥረት ማድረግ ጥፋቱ ብዙ እየኾነ ይሄዳል፡፡ ጫፍ የረገጡ፣ መሀል ሰፋሪ፣ ተራማጅ፣ ለዘብተኛ የኾኑ ቡድኖችን አካትቶ ውይይት በማድረግ ነው ለመጪው ዘመን መፍትሄ ይዞ መምጣት የሚቻለው፡፡
እኔ አንስቼ የነበረው ሐሳብ በጥቅሉ የአካታችነት ጉዳይን እንጂ፣ ሙስሊም ወይም ሌላ በስም ጠቅሼ ሊካተት ይገባል ያልኩት ቡድን ወይም ግለሰብ የለም፡፡ አሁን ባለው የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ ሚና ያላቸው ቡድኖችም ኾኑ ሌሎች ተዋናዮችን ያካተተ ውይይት ማድረግ ግን ይገባል፡፡ ይኼን ደግሞ ‹‹ኮል ፎር ፔፐር›› በሚል ጥሪ ሳይኾን በጋራ ተነጋግሮ በሚታለፍ ሂደት ነው የሚከናወነው፡፡ በፓስተሩ ላይ ያሉት ግለሰቦች እነ ፕሮፌሰር መሳይ በዚህ ሂደት ፔፐር አስገብተው፣ ተገምግሞ … አልፈው ነው ጉባዔው ላይ የሚሳተፉት ማለት አይናችሁን ጨፍኑና ላሞኛችኹ እንደማለት ነው፣ በሌላ በኩል ደግሞ የአካዳሚክ ፔፐር ሲያቀርቡ የማናውቃቸው ሰዎችም በፖስተሩ ላይ ይታያሉ፡፡ ይሄ ሐሳብ ማስታወቂው ላይ ያሉት ሰዎች በወረቀት አቅራቢነት ተመዝግበው ሳይኾን አዘጋጆቹ መርጠዋቸው የመጡ እንደኾኑ አመላካች ነው፡፡ ምን አልባት ጉባዔው የአማራ የሽግግር መንግሥት ጉባዔ 🙂 የሚል ርእስ ያለው ቢኾን ኖሮ፣ይኼን ያህል ውዝግብ አያስነሳም ነበር፡፡ ችግር የተፈጠረው የኢትዮጵያ የሽግግር ጉባዔ መባሉ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ካላችሁ ደግሞ ደፈር በሉና ሁሉንም ቡድኖች ድንበር አቋርጣቹሁ ጋብዙ፡፡ ለሀገራችን የሚጠቅመው ይሄ ብቻ ነው፡፡ ተለያይቶ መጓዝ ጎጂ ነው፤ በኢትዮጵያ ስም አንድን ማንንት ብቻ የፖለቲካ ገበያ ላይ ማውጣትም ፋሽን ያለፈበት ሊኾን ይገባል፡፡

No comments:

Post a Comment