Thursday, June 29, 2017

የቁልቁለት መንገድ አዲስ አበባ ገደል ስትገባ!! – አገሬ አዲስ

   

  
By ሳተናውJune 29, 2017 21:17



በየትኛውም ዓለም ከተማ ውስጥ የሌለና ያልታዬ ታሪክ በአገራችን ዋና ከተማ በሆነችው አደስ አበባ ውስጥ ለበለጠ የህዝብ ልዩነትና  አገራዊ ቀውስ የሚዳርግ እቅድ ሰሞኑን በወያኔ ካቢኔ በህግ ጸድቆ ይፋ ወጥቷል።ህጉን ምክርቤት ተብየው የወያኔ ሆድ አደር መንጋ ካሳለፈው ለዘመናት ኢትዮጵያውያን በደምና በአጥንታቸው፣በእውቀትና በሃብታቸው የገነቡትን የጋራ ከተማ የሚንድና የአዲስ አበባን ሁልንተናዊነት አጥፍቶና ንዶ የጠበበች፣ የግጭትና የልዩነት አውድማ አድርጎ የሚያደራጅ ነው።
የወያኔ ዘላቂ ዓላማ ኢትዮጵያን በታትኖ የራሱን ጠባብ ክልል አገር አድርጎ ለመፍጠር እንደሆነ ምርምር አያሻውም።በዚያው አኳያ በኢትዮጵያዊነት የተሰሩትንና የተገነቡትን እየናደ፣የሚያስተሳስረውን ድርና ክር እየመዘዘ ማዳከም ለዘላቂው ዓላማው መጀመሪያው እርምጃ ነው።ባይሆንልን ብትንትኗን አውጥተን እንመለሳለን ከሚለው ነባር ዓላማ ጋር የተያያዘ መሆኑ ሊዘነጋ አይገባውም።
የወያኔ መራሹ የጎሰኞች ስብስብ አገር አቀፍ ህዝባዊ ተቃውሞ ዓላማውን እንደሚያጨናግፍበት በመረዳት  የትግሉን ትስስር ለመበጠስና ለማዳከም የተካነበትን የማለያየት ስልት፣አንዱን የጠቀመና መብቱን ያስከበረለት በመምሰል ሁሉንም የሚጎዳና ለበለጠ ግጭት የሚዳርግ ስልቱን  ሰሞኑን በአዲስ አበባ አስተዳደር ዙሪያ በመጀመር ይፋ አድርጓል።በዚህ ይፋ ባደረገው አዲስ የህገመንግስት አንቀጹ አዲስ አበባ የሁሉም ከተማ መሆኗ ቀርቶ የአንድ ማህበረሰብ ከተማ እደሆነች በማመን ዘርና ጎሳን ተንተርሶ ያልወጣላት ስሟም የኦሮሞ ተገንጣዮች በሚጠሯት ስም  ፊንፊኔ በሚለው ጭማሪ እንድትጠራ(ይህ እራሱን የቻለ ውዥንብር የሚፈጥር ነው፤የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በየትኛው ለመጥራት ግራ ይጋባል፤ከተማዋም ለሚኖራት ግንኙነት ሁሉ እንቅፋት ይፈጥራል)።ሁሉም ነዋሪ የሚጠቀምበትና የሚግባባበት ቋንቋ ቀርቶ አንድ ማህበረሰብ ብቻ የሚናገረው የኦሮሞ ቋንቋ የአስተዳደሩ ተጨማሪ የስራ ቋንቋ  ለማድረግ የሚያስችል ቅድመ ዝግጅቱን ጨርሶ ህጋዊ ሽፋን ሰጥቶት መወሰኑን ባወጣው መንግስታዊ መግለጫ ይፋ አድርጓል።ይህ ተንኮል ግን ኦሮሞውን ለመጥቀም ሳይሆን የተነሳበትን ተቃውሞ ለጊዜው ለማብረድና በስፋት የያዘውን የዘረፋ ዕድሜ ለማራዘም ሆን ተብሎ የተተመነ ስልት ነው።የኦሮሞም ሆነ የሌላው ማህበረሰብ  ተወላጅ ጥያቄው ቋንቋየን እየተናገርኩ ከሌላው ተነጥዬ ልረገጥ ሳይሆን የሰብአዊና የዜግነት መብቴ ይጠበቅ፣ከድህነትና ከዃላቀርነት የሚገላግለኝ የጋራ ስርዓት ይመስረት፣የዴሞክራሲ መብቶች ይከበሩ፣በጎሳ ማንነት መጠቀምና መጎዳት ይቅር ለወደፊቱም አይኑር፣ከትውልድ የወረስኩት መሬቴን  እየተቀማሁ አልፈናቀል… የሚል ነው።
አዲስ አበባ የአገራችን የፖለቲካና የዓለም አቀፍ ግንኙነት መዲና ፣የአገሪቱም የኤኮኖሚ እምብርት መሆኗ እየታወቀ የአንድ ነጠላ ማህበረሰብ ጥቅም ብቻ የሚከበርበት አንቀጽ  ህጋዊ መመሪያ አድርጎ መደንገግ፣በከተማዋም ሁለገብ ህይወትና በነዋሪው እጣፈንታ ላይ የአንድ ማህበረሰብ የበላይነት ማስፈን  ፍትሃዊና ለሰላማዊ ኑሮና ለህዝብ ጤናማ ግንኙነት የሚረዳ አይደለም።የከተማዋ እድገትና ህይወት ሁሉም የኢትዮጵያ ክፍለሃገሮችና የተለያዩ ማህበረሰቦች ተወላጆች ያበረከቱት ድርሻ ውጤት ነው።ከተማዋ የተገነባችው ከሁሉም ያገሪቱ ክፍሎች በሚሰበሰበው የግብርና የእውቀት መዋጮ ነው።ስለሆነም ሁሉም እኩል የባለቤትነት ድርሻ ሊኖረው ይገባል።ኦሮሞኛ ለሚናገረው ቅድሚያና ብልጫ ጥቅም ይሰጠዋል፣መብቱም ይከበርለታል ማለት በዘረኛው አፓርታይድ ስር  እንደ ቀድሞዋ ደቡብ አፍሪካና ከሚሊዮን ህዝብ በላይ በጎሳ ውዝግብ እንደተጨፈጨፈባት ሩዋንዳ ከባሰ ቀውስ ውስጥ የሚከት ነው።ለመሆኑ ኦሮሞኛ የማይናገረው አዲስ አበባ ውስጥ ተወልዶ ያደገው የኦሮሞ ልጅ ምን ይውጠው ይሆን?ኦሮሞኛ የሚናገረውስ የሌላው ማህበረሰብ ተወላጅ የጥቅሙ ተካፋይ ይሆን ይሆን?ወይስ የጀርባ አጥንቱ እየታዬ ለጥቃቱ ሰለባ ይሆናል?
በሌሎቹስ ክፍላተ ሃገሮች ውስጥ የተቋቋሙትና የተፈጥሮ ሃብት ምንጭ የሆኑት አካባቢ ህዝብ ተመሳሳይ መብትና ጥቅም ያገኛልን? የኤሌክትሪክ ምንጭ፣የወርቅና የተለያዩ ማዕድኖች ቁፋሮ የሚካሄድባቸው አካባቢዎች ህዝብ የጥቅሙ ተካፋይ የሚሆንበት አሰራርና ህግ መቼ ተፈጠረለት?የበይ ተመልካች ከመሆን ያለፈ ዕድል መች አገኘ?
ይህ እንደ አዲስ የወጣ የማጠናከሪያ ደንብና መመሪያ ምናልባት የኦሮሞውን ማህበረሰብ የሚጠቅም ሊመስል ይችል ይሆናል።አርቆ ለሚያስብ የኦሮሞ ተወላጅ ግን ተቃውሞውን ለመግታትና አገራችንን ለመበታተኑ ሂደት የመጀመሪያው መንደርደሪያ እንደሆነ፤ ብቻውን ነጥሎ የሚያስመታውና የሚያስጠቃው የወያኔ ሰይጣናዊ ብልሃት መሆኑንም ሳይረዳው አይቀርም።
የዘፈን ዳርዳሩ እስክስታ ነው እንዲሉ ወያኔ ስልጣን ከመያዙ በፊት ከአጋሩ ከኦነግ ጋር ሆኖ በጀርመን አገር ውስጥ በተካሄደው ስብሰባ ላይ ከፈረንጆቹ በኩል « ኦነግ ተሳክቶለት ስልጣን ላይ ቢወጣ በአዲስ አበባ ውስጥ የሚኖረው ከሁሉም ክፍለሃገር የተውጣጣ ህዝብ ምን ዕድል ይገጥመዋል?» ተብሎ ለቀረበለት ጥያቄ የኦነጉ መሪ የዛን ጊዜው አቶ የአሁኑ ዶክተር ዲማ ነገዎ(ዩሃንስ ነገዎ) የሰጠው መልስ «ለኦሮሚያ የሚጠቅመው መኖሪያ ፈቃዱን እያሳደሰ ሲኖር የማይጠቅመው ደግሞ ወደ መጣበት እንዲመለስ ቀዳዳ መንገድ(safe corridor) ይከፈትለታል» ብሎ ነበር።ይህንን ባለ በስድስት ወሩ ሻእብያ፣ወያኔና ኦነግ ከሌሎቹ በአማራው ስም ከተደራጁት አሽከሮቹ ጋር ስልጣኑንc ጨበጡ።ይህንን የተናገረው ዲማ ነገዎ(ዩሃንስ ነገዎ)የማስታወቂያ ሚኒስቴር ሆነና በውጭ አገር በመዘዋወር ስለተመሰረተው አገዛዝ መብራሪያ ለመስጠት በውጭ አገር እየተዘዋወረ በየስብሰባው መድረክ ላይ ብቅ አለ። በስብሰባ ላይ ያንን ቀድሞ ጀርመን የተናገረውን በአካል ካዳመጥነው ውስጥ አንዱ ቢጠይቀው« አይኔን ግንባር ያድርገው!፣እንዲህ ያለ ቃል ካፌ ወጥቶ አያውቅም» ሲል ሸመጠጠ።ይባስ ብሎም በጠያቂው  ላይ በስብሰባው የተሳተፉት አብዛኛዎቹ የወያኔና የሻእብያ ደጋፊዎች እንዲዛበቱበት የግለሰቡን  አስተያየት አጣጥሎ ለማቅረብ ሞከረ።
እውነትና ጀንበር እያደር ይጠራል! ነውና የኸው ዛሬ ከሃያ ሰባት ዓመት በዃላ የዚያ አስተሳሰብ እንቁላል ተፈልፍሎ በአደባባይ ይፋ ወጣ።
የአዲስ አበባ ከተማ በሸዋ ክፍለሃገር የምትገኝ እንጂ ኦሮሞ የሚል ክፍለሃገር እንዳልነበረና በዚያ  ክፍለሃገር ውስጥ የምትገኝ ከተማ እንዳልነበረች ሁሉም ያውቃል።የሸዋ ክፍለሃገር ደግሞ ኦሮሞውን ብቻ ሳይሆን አማራውና  የተለያዩ ማህበረሰቦች የሚኖሩበት ክፍለሃገር ነው።ስለሆነም  የባለቤትነቱ ጥቅም ይከበርለት ቢባል እንኳን የዚያው የሸዋ ጠ/ግዛት ህዝብ ይሆናል እንጂ የአንዱ ማህበረሰብ ብቻ ሊሆን አይገባውም።
የከተማውንም አስተዳደር በሚመለከተው የአንድ ከተማ አስተዳደር የሚዋቀረው በነዋሪው ብዛትና አኳያ ሊሆን ይገባዋል።አዲስ አበባ በክፍለ ከተማ ና ወረዳ እንዲሁም ቀበሌና መንደር የተዋቀረች በመሆኗ፤በነዚህም የከተማዋ እርከኖች  ውስጥ ከተለያዩ ማህበረሰቦች የፈለቀና የተዋለደ ህዝብ ስለሚኖር አስተዳደሩም(ማዘጋጃቤቱም)የነዋሪውን ገጽና ስብጥር የሚያካትት ሊሆን ይገባዋል።የሚጠቀምበትም የስራ ቋንቋ የከተማው ህዝብ የሚግባባበትና በአገሪቱ ህግ የጸደቀው የአማርኛ ቋንቋ ሊሆን ይገባዋል።ይህ ማለት ግን በከተማዋ ውስጥ ብሎም በአገር አቀፍ ደረጃ ተጨማሪ ቋንቋዎች አይነገሩ ማለት አይደለም።ማንኛውም ዜጋ ከጎሳው አባል ጋር እርስ በርሱ ሊግባባበት የሚችለውን ቋንቋ መናገሩ በህግ ብቻ የሚጸድቅ ሳይሆን ከቤተሰብና  በትውልዱ ያገኘው ችሎታና መብቱ ነው።ኦሮሞው ከኦሮሞው ጋር ለመግባባት ኦሮምኛ ይቀለዋል፤እንደዚህም ያለው ግንኙነት ለዘመናት የቆየና ያለፉት ስርዓቶችም የከለከሉት አሰራር አልነበረም፤በወያኔ መራሹ ስርዓት  ብቻም እውቅና የተሰጠውም አይደለም።ሰው ከሌላው ጋር ለመግባባት የሚመርጠው ቋንቋ ከሁኔታው ጋር የሚያየውና በግላዊ ውሳኔው የሚወስደው እንጂ በህግ ተገዶ የሚከተለው መሆን የለበትም።ብዙ ማህበረሰብ በሚኖርበት አገር ውስጥ የአንድ ማህበረሰብ ተወላጅ የሆነ ዜጋ በራሱ የጎሳ ቋንቋ ቢናገር ከጎሳው ተወላጅ በስተቀር ከሌላው ጋር ሊግባባ አይችልም፤ስለሆነም የሚግባባበት የጋራ ቋንቋ መኖሩ ችግሩን ያቃልልለታል።በታሪክ አጋጣሚ የሁላችን ቋንቋ የሆነው አማርኛ በሌሎቹ ማህበረሰብ ተወላጆች ላይ በግድ የተጫነ ሳይሆን በህብረተሰቡ ቅልቅልና መስተጋብር ሂደት ቃላት እየወረሰ ያደገና የተስፋፋ ቋንቋ ነው።
በኦሮሞ ማህበረሰብ ውስጥ የተወለደ የየትኛውም ማህበረሰብ ተወላጅ ኦሮምኛ ለመናገር ዕድሉ ከፍ ያለ ነው።ይናገረዋልም።የሌላውም በሌላውም ቦታ እንዲሁ ነው።የሁሉም ቅልቅል በሚኖርባትም የአዲስ አበባ ከተማ ኑዋሪ በሚያግባባው የጋራ ቋንቋ በአማርኛ መናገሩ ሊሻርና ሊገደብ አይገባውም።በአዲስ አበባ ብቻም ሳይሆን በተቀሩት ክፍለሃገር ውስጥ የሚኖረው ህዝብ ከየማህበረሰቡ የተውጣጣ በመሆኑ አንድ ቋንቋ አማርኛ መናገራቸው ከነጠላ ጎሰኝነት አጥር ውስጥ ፈልቅቆ ሊያወጣቸው ችሏል ለወደፊቱም ይችላል።የከባቢ ቋንቋ ብቻ ይነገር ከተባለ ከሰማንያ በላይ የሚሆኑት የኢትዮጵያ ማህበረሰቦች ሳይግባቡ ይኑሩ ብሎም በቋንቋቸው ተዋረድ የየራሳቸውን ክልልና መንግስት አቋቁመው እርስ በርሳቸው እየተጋጩና እየተዋጉ ይለቁ ብሎ መፍረድ ይሆናል።አዲስ አበባም ውስጥ የሚኖሩት  አማራና ኦሮሞ ብቻ ስላልሆኑ ሁሉም የማህበረሰብ አባል የጎሳዬ ቋንቋ የአስተዳደሩ ቋንቋ ይሁንልኝ የማለት ጥያቄ እንዲያቀርብ በር ይከፍታል። ወያኔና ግብረአበሮቹም  የሚወጡት የሚወርዱት በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ብሎም በአጠቃላይ በአገራችን ኢትዮጵያ በዚህ አይነቱ ዘዴ ትርምስምስ እንዲመጣ ለማድረግ ነው።በትርምሱ የሚያልቀው የፈረደበት ህዝብ ነው።እነሱ ቤተሰባቸውን ይዘው ቀድሞ ወዳዘጋጁት አገር ይሾልካሉ፤ቀድመውም የሾለኩና ያሾለኩ ብዙ ናቸው።።የደርግ መሪዎች የመጨረሻው ታሪክ ትዝ ሊለን ይገባል።የወያኔና ተባባሪዎቹ ገንዘብና ንብረት በውጭ አገር ማካበታቸው የሚታበል አይደለም።ህዝቡን ኦሮምኛ፣ትግርኛ… ተማር፣ተናገር እያሉ ሲያስጨንቁት ልጆቻቸውን ግን በሚሸሹበት አገር ችግር እንዳይገጥማቸው በከፍተኛ ወጭ በቤትና በውጭ አገር ት/ቤቶች ቋንቋ ያስተምራሉ። ሁለትና ሶስት የውጭ አገር ቋንቋ የማይናገር የባለስልጣን ልጅ ተፈልጎ አይገኝም።
የኦሮሞን ተወላጅ ጥቅም ለማስከበርና ለተጎዳው ካሳ መክፈል የሚለው የማታለያ ስልት ዕድሜን ከማራዘም ሌላ ትርጉም የለውም።በአዲስ አበባ መሬቱን የተነጠቀውና የተፈናቀለው ኦሮሞው ብቻ አይደለም።ከተማዋ ከተቆረቆረችበት ጀምሮ ለብዙ ዓመታት ከአያት ቅድመአያት ሲወርስ ሲወራረስና ገዝቶ ቤት ሰርቶ የኖረውም ኦሮሞ ያልሆነው ዜጋ የጥቃቱ ሰለባ ሆኗል።ወያኔና የሱ ባለሟል የሆነው የከተማዋን አስተዳደር በመያዝ መሬቱን እየነጠቀ ለከበርቴዎች በመሸጥ የባለስልጣኖች የገቢ ምንጭ ያደረገው ኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት( ኦፒዲኦ) የተባለው በኦሮሞ ህዝብ ስም ስልጣን ይዞ መልሶ ኦሮሞውን የሚያጠቃውና የሚያስጠቃው ቡድን ነው።ካሳ መክፈልም ያለበት ይኸው ድርጅትና የገበያው ሸሪኮቹ ናቸው። ካሳ ይከፈል ከተባለ ደግሞ መሬቱን የተነጠቀውና ቤቱ የፈረሰበት፣መጠለያ አጥቶ ለመከራ የተጋለጠውንና ጥቂት የገንዘብ መደለያ እንዲቀበል ተገዶና ተታሎ መሬቱ ለከፍተኛ ዋጋ የተሸጠበት ያዲስ አበባ ኑዋሪ ሁሉ ይመለከተዋል።በሌሎቹም ያገሪቱ ከተማዎች ተመሳሳይ ግፍ የተፈጸመ ሲሆን የካሳ ጉዳይ ከተነሳ በተመሳሳይ መንገድ ተግባራዊ ሊሆን ይገባዋል።
ቋንቋን በተመለከተ  ኦሮምኛም ሆነ የሌሎቹ ቋንቋዎች ማደግ ተገቢ ነው ።ሌላው ቀርቶ የውጭ አገር ቋንቋዎች የሚሰጡበት ትምህርት ቤት በተከፈተበት ከተማ የኦሮምኛም ሆነ የሌሎቹ አገር በቀል ቋንቋዎች ትምህርት ቤት መክፈቱ ለቀና ዓላማ እስከሆነ ድረስ ጉዳት የለውም።የፈለገ ሰው  ጎሳው ሳይታይ  ሊከታተለው ይችላል።ለአማራውም ሆነ ለሌላው ኦሮሞ ላልሆነውም ቢሆን አማርኛ ከማይችለው ኦሮሞ ወገኑ ጋር የሚግባባበትን ዕድል ከፍ ያደርግለታል።ጥንቃቄ የሚያሻው ነገር የተገንጣዮች ዓላማ መሳሪያ እንዳይሆን መከላከሉ ነው።እውነት ለኦሮሞ ህዝብ የሚያስቡለትና የአፍላቂነት ችሎታ ቢኖራቸው ኖሮ ከነጮችም  ተጽእኖ እንዲድን ቢፈልጉ ኖሮ የላቲን ፊደላትን አምጥተው ባልጫኑበት ነበር። ለኦሮሞ ህዝብ አዲስ የፊደል ባለቤት ባደረጉትና ሁላችንም ኢትዮጵያኖች የምንኮራበት ተጨማሪ እሴት እንዲኖረን ባደረጉ ነበር።የጠባብ ጎሳ ምሁራን ግን ቆምንለት ያሉትን ወገናቸውን ለውጭ አገር ባዕዳን ተጽእኖ በቋንቋው ጀርባ አሳልፈው ሰጥተውታል።እነሱ ግን አማርኛን ከአማራው በላይ እየተናገሩ በስልጣኑ ላይ የተቀመጡ ነበሩ፤ናቸውም።የቀና ልብ ባለቤቶች ቢሆኑማ ኖሮ  ልዩነትን የሚፈጥሩ ነገሮችን እያጠፋ አንድነትን በሚያመጡት ላይ ማተኮር በቻሉ ነበር።የዓለም ህዝብ ሊግባባ የሚችልበትን ቋንቋ በፍላጎቱ እየተማረ ካገሩ ወጥቶ እየተግባባ ሲኖር የአንድ አገር ህዝብ የሚግባባበትን ቋንቋ  እንዲጠላና በጎሳው ቋንቋ እየተናገረ እንዳይግባባ ማድረግ ጸረ አገር  ብቻ ሳይሆን ጸረ ህዝብ አሰራር ነው።
የአዲስ አበባን አስተዳደር በሚመለከተው ዙሪያ የወጣውን መመሪያ ከሌሎቹ የሰለጠኑ የዓለም ከተማዎች አሰራር ጋር ሲነጻጸር የሌሎቹ በጎሳ ዙሪያ የተቀነባበረና የተዘጋጀ ሳይሆን የከተማው ነዋሪ የሚሳተፍበትና  ብሎም የአገሪቱ ዜጋ ሁሉ የሚጠቀምበት ሁኔታን ከግምት ውስጥ ያስገባ ነው።አስተዳደሩም የሚመሰረተው ከጎሳ አንጻር ሳይሆን የፖለቲካ ድርጅቶች በፍልስፍና ላይ በተመሰረተ መርሃ ግብር አኳያ በምርጫ ወቅት ባገኙት የህዝብ ድምጽ መጠን አንዱ ብቻውን  ወይም ከሌሎቹ ጋር በጥምር ሁሉም የሚካፈልበትና የሚጠቀምበት አስተዳደር ይቋቋማል እንጂ አንዱን ነጠላ የጎሳ ማህበረሰብ ብቻ በሚጠቅም ሌላውን  በሚጎዳ፣ባይተዋርና ባዳ በሚያደርግ  እኩይ ጽንሰሃሳብ የሚመራ አስተዳደር አይመሰረትም።
በጣም የሚያስፈራውና የሚያሳስበው ነገር አዲስ አበባ የኦሮሞም ዋና ከተማና የአገሪቱም ዋና ከተማ  እርስ በርሱ በሚቃረን በክልላዊነትና በአገር አቀፍነት መልክ ሆና መቅረቧ በሁለት የተለያዩ አስተዳደሮች በጥቅም ፍጥጫና ግጭት ለመፈራረስ በሚያስችል ተንኮል እንድትዋቀር ማድረጉ ነው። ይህንን አደገኛ በማር የተጠቀለለ መርዝ  በኢትዮጵያዊነቱ የሚያምነውና የሚኮራው፣ለኢትዮጵያም አንድነት ህይወቱን ለመስጠት ወደ ዃላ የማይለው፣የጎሳን ፖለቲካ አንቅሮ የተፋውና የሚቃወመው  የኦሮሞ ማህበረሰብ  ተወላጅ ከሌላው ማህበረሰብ ተወላጅ ጋር ተባብሮ ሊከላከለው ይገባል።በህብረት የመሰረታትን አገሩን ኢትዮጵያን ለማፈራረስ  በቅድሚያ ምሰሶ የሆነችው አዲስ አበባ በጎሰኞች የተቀነባበረ ሴራ ለመፈራረስ ስትዘጋጅ በዝምታ ሊያየውና ሊያልፈው አይገባም።አሁን በተለያዩት  በሰሜኑና መካከለኛው ያገሪቱ ክፍለሃገራት በተለይም በጎንደርና አካባቢው የተቀጣጠለውን ህዝባዊ ትግል ለመቅጨትና የአማራውን ማህበረሰብ ለማጥፋት የታቀደውን ዘመቻ ከኦሮሞው ኢትዮጵያዊው በኩል ተቃውሞና ከህዝቡ ትግል ጋር ተሳትፎ እንዳይኖረው ለማድረግ የተሸረበ ሴራ ነው።
«ከጠላት የጎረሱት በሶ ይወጣል ደም ጎርሶ» ነውና ወያኔና ግብረአበሮቹ የሚወረውሩት አሳሳች የጥቅም ፍርፋሪ የኦሮሞን ማህበረሰብ ከኢትዮጵያዊነት የሚነጥልና የሚያስጠቃ፣ተባብሮ በመታገል የእድገትና የእኩልነት  ባለቤት ሊሆኑ ከሚችሉበት ሰልፍ ውስጥ የሚነጥል ስለሆነ« እኛም  አውቀናል ጉድጓድ ምሰናል» እንዳለችው አስተዋይ ጥንቸል የማዘናጊያውን መርዝና አደጋውን ተባብሮ ማክሸፍ ይኖርበታል።
ሌላው የአዋጁ አስፈላጊነት ወያኔና ግብረአበሮቹ ለገጠማቸው ውጥረት ማስተንፈሻና ምናልባትም በውጩ ግፊት ለውይይት  ከተገደዱ ከጠንካራ አክራሪ አቋም(from a strong position) በመነሳት ቀድሞ ወደ ነበሩበት ቦታ ለመመለስ የሚረዳቸው ስልት አድርገው ሊጠቀሙበት በማሰብ ይሆናልና ከወያኔ ጋር ተደራድረን ለውጥ እናመጣለን ብለው የሚያስቡ ከወዲሁ ምኞታቸውን እንዲያጤኑት ያስፈልጋል።ወያኔ ቀለሙን እንጂ ውስጣዊ ምንነቱን የማይቀይር እስስት መሆኑን ሊያውቁት ይገባል።
በተቃዋሚውም ጎራ ከወያኔ ጋር ለመደራደር የሚሹ እንዳሉ አይካድም።ከነዚያም ውስጥ የኦነግ መሪዎች ለተመሳሳይ ዓላማ ስማቸውን ቀይረው በተመሳሳይ የጎሳ ስብስብ መልክ ተደራጅተው የመጡ ስለሆነ ለዳግመኛ የስቃይ ኑሮ ላለመዳረግ የኢትዮጵያ ህዝብ ከጸረ ወያኔ ከሚያደርገው ትግል ጋር የነዚህንም ስብስብ ሊታገለው ይገባል።ወያኔን ተሸክመው አምጥተው  ላለፉት 27 ዓመታት የስቃይና የመከራ ስርዓት እንዳሰፈኑት ሁሉ ለሌላ 27 ዓመታት ተመሳሳይ ስርዓት እንዳይጭኑበት  ተባብሮ  ወግዱ ሊላቸው ይገባል።የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው የሚሉት ፈሊጥ አሁን አገራችን ባለችበት ሁኔታ ላይ አይሰራም።ትግሉ አገር የማዳን ስለሆነ አደጋውም በጎሰኞች ምክንያት የመጣ ስለሆነ ከነሱ ጋር ምንም አይነት የዓላማ አንድነት አይኖርም። ዓላማችንና ተልእኳችን ኢትዮጵያዊነትንና ኢትዮጵያን የማዳን ሊሆን ይገባዋል።ያ ደግሞ በጎሳ  ለተደራጀ ድርጅት አለርጅኩ ነው። በኢትዮጵያዊነታቸው የማያወላውል አቋምና ታሪክ ያላቸው ብዙሃን ስለሆኑ ድሉ የማታ ማታ የነሱ ይሆናል። እንደዚያማ ባይሆን ኖሮ ኢትዮጵያ የምትባል አገር አትኖርም ነበር።
የወያኔንና የግብረአበሮቹን አደገኛ ስልት ተባብረን እናክሽፍ።
አገሬ አዲስ

በአማራ ሕዝብ ትግል ውስጥ የብሔርተኝነትና የጽንፈኝነት አቋም እጅግ አስፈላጊነት! – ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

 


  
By ሳተናውJune 28, 2017 23:39



ከዓመታት በፊት ጀምሬ ባቀረብኳቸው ጽሑፎች ሊያከራክር በማይችል መልኩ የምዕራቡን ዓለም ሐሳብ ላይ እንጅ የዘር ልዩነት ወይም ብሔረሰብና ጎሳ ላይ ያልተመሠረተን የሠለጠነ የፖለቲካ (የእምነተ አሥተዳደር) ተሞክሮ እንዲሁም የ26 ዓመታቱን የወያኔን አገዛዝ ተሞክሮዎችን በማነጻጸር ግልጥልጥ አድርጌ በማሳየት የዘር ልዩነት ላይ ወይም የጎሳና ብሔረሰብ ላይ የተመሠረተ አደረጃጀትን ተፈጥሯዊ ኢዲሞክራሲያዊነት (ኢመስፍነ ሕዝባዊነት) ፣ ኢሰብአዊነት፣ ኃላ ቀርና ጠባብነት፣ ፀረ የሀገርና የሕዝብ አንድነት መሆንን ሳስረዳ መቆየቴ፤ ከጊዜ በኋላም አማራ በማንነቱ የተደራጀው አማራነቱ እንደወንጀል ተቆጥሮበት የዘር ማጥፋት ዘመቻ ስለተዘመተበት ህልውናውን ለመታደግ እንጅ እንደሌሎቹ ጎሳና ብሔረሰብ ተኮር ጅርጅቶች ጠባብ ለመሆንና የሀገርን አንድነትና ህልውና አደጋ ላይ ለመጣል አለመሆኑን በሚገባ አስረድቻለሁና እዚህ ላይ ደግሜ ማብራራት አይጠበቅብኝም፡፡
አማራ በማንነቱ ስለመደራጀቱ፣ ስለ አማራ ብሔርተኝነት፣ ዛሬ ስለአስፈላጊነቱ ስለምገልጽላቹህ ስለ አማራ ጽንፈኝነት ቃላቶች (Terms) ስናሰማ በርካታ ሰዎች እነኝህን ቃላቶች ወይም ፅንሰ ሐሳቦች የሚረዱት የቃላቶችን ፅንሰ ሐሳብ ሌሎቹ የጎሳና ብሔረሰብ ድርጅቶች በሚያራምዱት አስተሳሰብና መረዳት እየታየብን የአማራ ሕዝብ ህልውናን የመታደግ ትግል ችግር ገጥሞታል፡፡ ይህ ችግርም እኛ የአማራን ህልውናውን ከፈጽሞ ጥፋት የመታደግ ትግልን ከማንኛውም ሰብአዊ ፍጡር እንደሚጠበቀው ሁሉ ከአማራ ውጭ ያሉ ሌሎች ኢትዮጵያውያንም እንዲደግፉት ስንጠብቅ ጭራሽ አማራ የሆኑትም ትግሉን እንዳይቀላቀሉ እያደረገብን ይገኛል፡፡
ይህ በአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል ላይ የተሳሳተ ግንዛቤ እንዲያዝና ትግሉ የሚጠበቀውን ያህል እንዳይጋጋል በማድረጉ እረገድ ሦስት አራት የሚሆኑ በአማራ ስም የተደራጁ የወያኔ ቅጥረኛ ድርጅቶች ሚና ከፍተኛውን ሚና ተጫውተዋል፡፡ እነኝህ ሐሰተኛ የአማራ ድርጅቶች የአማራ ብሔርተኝነትንና ጽንፈኝነትን ፅንሰ ሐሳቦች ሌሎች የጎሳተኮር ድርጅቶች በሚያራምዱት አስተሳሰብ ዓይነት እንዲታይበት አድርገዋል፡፡ እርግጥ ነው እነኝህ ቅጥረኛ ድርጅቶች የአማራ ሕዝብ በጥፋት ኃይሎች እየተወሰደበት ያለው እርምጃ አንሶት እራሱን በራሱ ሊያጠፋ በሚችልበት የተወሳሰበ ችግር ውስጥ ለማስመጥ የቅጥረኝነት ዓላማቸውን ለማስፈጸም አሳቢ ተቆርቋሪ መስለው እየሠሩት ያሉትን ዕኩይ የባንዳ ሥራ፣ ከአማራ ሥነልቡናና ማንነት ጋር ተቃርኖ ያለው አስተሳሰብ በአማራ ሕዝብ ዘንድ በመታወቁ የሕዝብ ተቀባይነትን ሊያገኙ ባለመቻላቸው ከእንግዲህ ማኅበራዊ የብዙኃን መገናኛ ላይ ሲወራጩ እናያቸው ካልሆነ በስተቀር በሕዝብ ልብ ላይ ቦታ የላቸውምና የሚያንፀባርቁት አስተሳሰብ ፈጽሞ ከአማራ ሕዝብ የፈለቀ ተደርጎ ሊቆጠር አይገባም፡፡
በዚህ ጽሑፍ ላይ የአማራ ሕዝብ ትግል እንዴትና ለምን በብሔርተኝነትና በጽንፈኝነት መመራት እንዳለበት፣ የአማራ ብሔርተኝነትና ጽንፈኝነት እንዴትና በምን ከሌሎቹ የጎሳ ብሔረሰብ ተኮር ድርጅቶች እንደሚለይ እናያለን፡፡ እያወራን ያለው አማራ በአማራነቱ ብቻ በጥፋት ኃይሎች እንዲጠፋ ታውጆበት ተፈጻሚ እየተደረገበት ካለው ኢሰብአዊ ጥቃት እራሱን መታደግ ስለሚችልበት ጉዳይ ነው፡፡ ልብ በሉ ለአማራ መጠቃት መንስኤ የሆነው ማንነቱ ወይም አማራነቱ ነው፡፡ ለአማራ መጠቃት መንስኤ የሆነው አማራነቱ ከሆነ እራሱን ለማዳን ከአጥቂዎቹ ሲከላከል የሚከላከለው አማራነቱን ማለትም ባሕሉን፣ ወጉን፣ ሥርዓቱን፣ ሃይማኖቱን፣ አስተሳሰቡን፣ ፍልስፍናውን፣ ሥልጣኔውን፣ ቅርሱን፣ ማንነቱን አጠቃላይ እሴቶቹን ነው ማለት ነው፡፡ ብሔርተኝነት ማለት ይሄ ነው ሌላ አይደለም፡፡ እርግጥ ነው ጤነኛ ያልሆነ ብሔርተኝነትም አለ፡፡ የአማራ ብሔርተኝነት እንደዚያ አይደለም፡፡ አማራ ብሔርተኛ ሳይሆን ለእነኝህ እሴቶቹ ሊቆጭ ሊቆረቆር ሊታገል አይችልም፡፡ የአማራ ብሔርተኝነት ማለት ለእነኝህ እሴቶች ተጠብቆ መኖር አስፈላጊውን ዋጋ ለመክፈል መነሣሣት ማለት ነው፡፡ አማራ ለመጠቃቱ ምክንያት ስለሆነው ስለአማራነቱ ሳይቆጭ ሳይንገበገብ (ብሔርተኝነት ሳይሰማው) ሊታገልና እራሱን ከጥፋት ሊታደግ አይችልም፡፡ የአማራን ብሔርተኝነት ከሌሎቹ የሚለዩት አምስት ዋና ዋና ነጥቦች አሉ፦
1ኛ. የአማራ ብሔርተኝነት እራሱን እየተፈጸመበት ባለው የዘር ማጥፋትና ማጽዳት ጥቃት ፈጽሞ ከመጥፋት ለመታደግ የግድ መደረግ ያለበት በመሆኑ፡፡
2ኛ. የሀገርንና የሕዝቧን አንድነትና ህልውናን አደጋ ላይ የሚጥል፣ ለድርድር የሚያቀርብ ባለመሆኑ፡፡
3ኛ. እንደሌሎች ብሔርተኛ ኃይሎች ለሌሎች ብሔረሰቦችና ጎሳዎች ይሄንን ወይም ያንን ብሔረሰብ ወይም ጎሳ በመሆናቸው ብቻ ምንም ዓይነት ጥላቻ የሌለው በመሆኑ (የጥፋት ኃይሎች የጥፋት ዓላማቸውን ለማሳካትና ለማስፈጸም አማራን በተመለከተ ብዙ እየፈጠሩ የሚያወሩት ነገር አለ፡፡ እውነታው ግን በእጅጉ ከዚህ የተለየ ነው፡፡ ከእኛ ጋር ተመሳሳይ የአሥተዳደር ሥርዓት በነበረባቸው በአውሮፓ፣ በእስያ፣ በመካከለኛው ምሥራቅ ሀገራት ያሉ የተለያዩ ብሔረሰቦችና ጎሳዎች ቋንቋቸው፣ ባሕላቸው፣ እምነታቸው፣ ማንነታቸው በገዥዎቻቸው በኃይል እንዲጠፋ ተደርጎ የገዥዎቻቸውን ቋንቋ፣ ባሕል፣ እምነት፣ ማንነት እንዲይዙ እንዲወርሱ ሲደረጉ ማንም ማየት እንደሚችለው ኢትዮጵያ ውስጥ ግን የትኛውም ብሔረሰብም ሆነ ጎሳ በኃይል እንዲጠፋ ሳይደረግበት ቋንቋውን፣ ባሕሉን፣ እምነቱን፣ ማንነቱን እንደያዘ ይገኛል፡፡ ይሄ ማለት ግን ብሔራዊ ቋንቋና ሃይማኖት ኢትዮጵያ ውስጥ አልነበረም፣ የመናቅ ችግርም አልነበረም ማለት አይደለም፡፡ መናቅ ወይም መናናቅ የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ባሕርይ ነውና የትም ሀገር ቢሆን እንኳን ጥንት ወደፊትም ይጠፋል ተብሎ አይጠበቅም፡፡ ምክንያቱ ይለይ ይሆናል እንጅ ይህ ችግር ሌላው ቀርቶ በአንድ ቤተሰብ አባላት መሀከል እንኳ ያለ ችግር ነውና፡፡ ብቸኛው የትግሬ ንጉሥ ዐፄ ዮሐንስ 4ኛ ለሚከተሉት ሃይማኖት ቀንተው ሳይሆን መጨረሻ ላይ የሚያጠፏቸው ወይም ለሕልፈት የሚዳርጓቸው እስላሞች እንደሆኑ የተነገረ ንግርት ወይም ትንቢት ስለነበረባቸው ይሄንን ንግርት ያስቀሩ መስሏቸው ወሎ ወርደው ግራኝ አሕመድ ያሰለማቸውን የወሎ እስላሞችን በኃይል ክርስቲያን ለማድረግ ከሞከሩት ድርጊት በስተቀር አንድም ንጉሥ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ብሔረሰቦችንና ጎሳዎችን በኃይል እምነታቸውን ብቻም ሳይሆን ቋንቋቸውንም፣ ባሕላቸውንም፣ ማንነታቸውንም እንዲቀይሩ አድርጎ አያውቅም፡፡ ስላልተደረገ ነው አሁን ድረስ ማንነታቸውን እንደያዙ ሊገኙ የቻሉት፡፡ ብሔረሰቦችና ጎሳዎች ቋንቋቸው፣ ባሕላቸው፣ እምነታቸው፣ ማንነታቸው በቅኝ ገዥ እንዳይጠፋና ያልተነካካ ማንነታቸውን እንደያዙ እንዲገኙ አማራ ተነግሮ የማያልቅ መራር መሥዋዕትነትን ነው ሲከፍል የኖረው፡፡ ከዚህም በላይ ጥንታዊ ርስቱን በተለያዩ ምክንያቶች ወደሀገር ለገቡ ብሔረሰቦችና ጎሳዎች አስረክቦ ተራራማ ሥፍራ የሰፈረ ቅን ሕዝብ ነው፡፡ ነገር ግን “የግፍ ግፍ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ!” እንዲሉ ለዚህና ለሌላው ተነግሮ ለማያልቀው ውለታው ሁሉ አማራ የተከፈለው ዋጋ በገዛ ሀገሩ ተሳዳጅ ተባራሪ ከመሆን አልፎ ዘሩ እንዲጠፋ ማድረግ ነው፡፡)
4ኛ. ጠባብነትንና ጭፍን ወገናዊነትን ለራሱ እሴቶች ሳያሳይ እሴቶቹን የሀገር እሴት አድርጎ በማስመረጡ ሒደት ዳኝነትን ለልኅቀትና ለምሑራዊ ተዋስኦ በመስጠቱ፡፡
5ኛ. የቅጣት እርምጃውን ተጠያቂ በሆኑ አካላት ላይ ብቻ ያነጣጠረ በመሆኑ ወይም ጅምላ ጨፍጫፊ ባለመሆኑ ነው፡፡
የአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል የጽንፈኝነትን መንገድ መከተሉን የግድ አስፈላጊ የሚያደርጉ አምስት ዋና ዋና ምክንያቶች አሉ፡፡ እነሱም የሚከተሉት ናቸው፦
ሀ.) ጠላቶቻችን እኛን ለማጥፋት የተነሡበት ቁርጠኝነት ጽንፈኛ በመሆኑና እሾህን በእሾህ እንዲሉ ጽንፈኛ ጥቃትን በጽንፈኛ የመከላከል እርምጃ ካልሆነ በስተቀር በልማዳዊ ወይም ለዘብተኛ አካሔድ መመከትና መከላከል ብሎም መቀልበስ ፈጽሞ የሚቻል ባለመሆኑ፡፡ ለዘብተኛው አኪያሔድ በጥይት አረር የሚፈጅን ጠላት በብትር ወይም በቆመጥ ለመመከት የመሞከርን ያህል ጅልነት ስለሆነ፡፡
ለ.) በአማራ ላይ ጽንፈኛ አቋም የያዙ የጥፋት ኃይሎች ካልጠፉ ካልተደመሰሱ በስተቀር ይሄንን ዕኩይና ጽንፈኛ አቋም ዓላማቸውን የሚተው ባለመሆናቸው፡፡ አቅም አንሷቸው ወይም ሁኔታው ሳይመቻቸው ቀርቶ የሆነ ወቅት ላይ የተዉ ቢመስሉ ምቹ ሁኔታ ባገኙ ጊዜ ይሄንን የጥፋት ጽንፈኛ ዓላማ አቋማቸውን መልሰው የሚያነሡ በመሆናቸው፡፡
ሐ.) አማራ በመሆናቸው ብቻ ከሕፃናት እስከ አረጋውያን በጥፋት ኃይሎች የተፈጁ ወይም እንዲጠፉ የተደረጉ ወገኖቻችን ደም መመለስ ስላለበት ወይም ደመከልብ ሆኖ መቅረት ስለሌለበት፡፡
መ.) አማራ በተለያየ ጊዜ በሆደሰፊነት ያጣውን የተነጠቀውን ጥቅሙን እውነትን ታሪክን መሠረት ባደረገ ፍትሐዊ አሠራር መልሶ ማግኘት እንዲችል የጥፋት ኃይሎቹና ደጋፊዎቻቸው ፈጽሞ የማይፈቅዱ በመሆናቸው፡፡
ሠ.) ጽንፈኛ አቋምና ፍጹም ግፈኛ የጥቅም ፍላጎት ያላቸውን የጥፋት ኃይሎች ከስር ነቅሎ በማጥፋት ሀገራችንን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከነዚህ የጥፋት ኃይሎችና ጠንቀኛ አስተሳሰባቸው ነጻ ማድረግ መገላገል አስፈላጊ በመሆኑ የሚሉት ናቸው፡፡
ወገን ሆይ! ወያኔንና ሌሎች የጥፋት ኃይሎችን መቃወምና አለመደገፍ ብቻ በቂ አይደለም፡፡ ለውጥ ለማምጣት ከተፈለገ ተደራጅቶ መታገል የግድ አስፈላጊ ነው፡፡ በዚህም በዚያም በየቦታው ብንንጫጫ ከመንጫጫት ባለፈ ምንም ጠብ የምናደርገው ነገር የለም፡፡ በዚህም በዚያም በየቦታው መንጫጫታችንን እንደትልቅ ግብ ቆጥረን እሱላይ ብቻ ማተኮራችን ለውጥ ሊመጣ የሚችልበትን መላ እንዳናይ አድርጎናል፡፡ ሲጀመር ጀምሮ የኢትዮጵያ ሕዝብ በወያኔና በሌሎች የጥፋት ኃይሎች ማንነት ላይ ለአንድም ቀን ቢሆን ብዥታ ኖሮበት አያውቅም፡፡ ከማንም በላይ አሳምሮ ያውቃቸዋል፡፡ ሲጀመር የማናስተውል ሆነን ካልሆነ በስተቀር ግፉ የሚፈጸሙ በራሱ በሕዝቡ ላይ ሆኖ እያለ ሕዝቡ እንዴት አያውቅም ተብሎ ይታሰባል? የማያውቅ የመሰለው ማወቁን ማሳወቁ የሚያስበላው ስለሆነ ነው እንጅ ሕዝብ ወያኔንም ሆነ ሌሎችንም የጥፋት ኃይሎች አብጠርጥሮ ነው የሚያውቃቸው፡፡ በየቦታው እንደመንጫጫታችን ቢሆን ኖሮ ወያኔ እስከአሁን ድራሹ ጠፍቶ በነበረ፡፡ አሁን ባለንበት ሁኔታ ለውጥ፣ ስኬት፣ ድል ልናገኝ የምንችለው በየቦታው በመንጫጫት ወይም ሕዝቡ የሚያውቀውን እውነት መልሰን ለራሱ በመንገር፣ በማስተጋባት ሳይሆን በኅቡዕ ወይም በስውርም በግልጽም እንደሁኔታው አመችነት ተደራጅተን የታገልን እንደሆነ ብቻና ብቻ ነው፡፡ ወያኔ ባይደራጅ፣ ሕዝቤ የሚለውን አደራጅቶ ባይታገልና ደርግን እያማረረ፣ እያወገዘ በመንጫጫት ብቻ ቢቀመጥ ኖሮ ዛሬ እዚህ የደረሰበት ደረጃ ላይ ባልደረሰ ነበር፡፡
ነባራዊ ሁኔታው ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ባካተተ መልኩ ውጤታማ ትግልን መታገል ባለመፍቀዱ ፈዘንና ደንዝዘን እጅግ ብንዘገይም ዛሬ ላይ ቢያንስ እንዴት መደራጀት እንዳለብን አውቀን የተደራጀንበት ደረጃ ላይ ደርሰናል፡፡ ከተደራጀን በኋላ ግን ወያኔ ለስኬት በምንበቃበት መንገድ ላይ እንደቆምን ተረድቶ ትግላችንን ለማክሸፍ እንደ ቤተአማራ ያሉ ቅጥረኛ ድርጅቶቹን በአማራ ሕዝብ ስም አደራጅቶ ማሠማራቱ ይታወቃል፡፡ እነኝህ ቅጥረኛ ድርጅቶች ዛሬ ላይ ባወቅናቸው ደረጃ ቀደም ሲል ስላልታወቁና “የያዙትን አማራን ከኢትዮጵያ የመገንጠል የጥፋት የድንቁርናና የቅጥረኝነት አቋም የያዙት ከየዋህነትና ካለመብሰል ከሆነ እስኪ ቀርበን እንለውጣቸው!” በሚል ቅንና ኃላፊነት የተሞላበት ሐሳብ የአማራ ሕዝብ መድኅን ንቅናቄ (አሕመን) ይሄንን ውዳቂና ከአማራ ማንነት ጋር ተቃርኖ ያለውን አቋም አስተሳሰባቸውን እንደሚተው ቃል ካስገባ በኋላ ከቤተ አማራ እና ከአዴሀን ጋር ውሕደት ፈጽሞ “ቤተ አማራ መድኅን” የሚል ውሕድ ድርጅት ፈጥሮ የነበረ ቢሆንም የወያኔ ቅጥረኞች ናቸውና “ትተናል!” ያሉትን የደነቆረ አስተሳሰብ እንደገና በማንሣታቸውና ለወያኔ በሰላይነት ላይ ተሠማርተው በመገኘታቸው
አደጋዎችን በመጋረጣቸው ምክንያት ዓመት እንኳ ሳይሞላ ውሕደቱ ሊፈርስ ችሏል፡፡ አሕመን ይሄንን ጉዳይ በተመለከተ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ ዝርዝር መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡ የተጠበቀም ያልተጠበቀም ችግርና ፈተና ቢያጋጥምም ፈተና ትግል ውስጥ ከሚያጋጥሙ እንቅፋቶች አንዱና ዋናው በመሆኑ እንዲህና እንዲያ ያሉ የተለያዩ ዓይነት ፈተናዎች ቢያጋጥማቸውም የያዙት ትግል መሆኑን ጠንቅቀው ያውቃሉና፣ ከመጋፈጥ ውጭ ሌላ አማራጭ እንደሌለ ጠንቅቀው ያውቃሉና ይሄና ያ ችግር ተከሰተ ወይም አለና ብለው አሕመኖች አልበረገጉም አልተፍረከረኩም፡፡ አሕመን አንድ የተጠናከረ የአማራ ኃይል እንዲፈጠር ይፈልጋል፡፡ የግድ አስፈላጊ ነውና፡፡ በመሆኑም በሒደት ላይ ያሉ የኢትዮጵያን አንድነትና ህልውና ለድርድር ከማያቀርቡ በአማራ ሕዝብ ስም ከተቋቋሙ የአማራ ድርጅቶች ጋር የመዋሐድ እንቅስቃሴውን አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
ስለ አሕመን ጥቂት መረጃ ለመስጠት ያህል ለአራት ዓመታት ያህል ጥልቅ ጥናት ከተደረገ በኋላ ከሁለት ዓመታት በፊት የተሟላ ሰብእና ያላቸው፣ በተቃውሞ ፖለቲካ ያለፉና ልምድ ያዳበሩ፣ ራሳቸውን ለትግሉ የሰጡና ዋጋ ለመክፈል የቆረጡ፣ በወገን ፍቅር የተቃጠሉ፣ የጠራና የበሰለ አቋም አስተሳሰብ የያዙ የተማሩና የጠነቀቁ ወጣቶች አሕመንን (የአማራ ሕዝብ መድኅን ንቅናቄን) መሥርተዋል፡፡ አሕመን ከተመሠረተ ጊዜ ጀምሮ አባላትን በኅቡዕ ሲያደራጅ ቆይቷል፡፡ ይሁንና እነኝህ የወያኔ ቅጥረኞች የያዙትን የቅጥረኝነት አቋም እንዴት የአማራን ሕዝብ ሊጠቅም እንደሚችል አብራርተው ሊያስረዱ ሊገልጹ የማይችሉትን የማይሆን፣ የማይበጅ፣ የደነቆረ የመገንጠልን ሐሳብ እየነዙ ሕዝባችን ላይ በፈጠሩት ብዥታ ምክንያት ሕዝባችንን በማንነቱ ወይም በአማራነቱ ለማደራጀት አሕመን በሚያደርገው ጥረት የሚፈለገውን ያህል የሕዝባችንን ንቁ ተሳትፎ ማግኘት ችሏል ማለት አይቻልም፡፡ በውጭ ያለውም እንቅስቃሴ ከዚህ የተለየ አይደለም፡፡ ወገን ሆይ! አሕመንን ተቀላቀሉ? ከምሁር እስካልተማረ፣ ከሴት እስከ ወንድ፣ ከሃይማኖት አባቶች እስከ ሕዝባዊ፣ ከተማሪ እስከ ሠራተኛ፣ ከነጋዴ እስከ ከያኔ ያላቹህ ሁላቹህም አማራና ኢትዮጵያዊነት ይበልጥብናል የምትሉ ኢትዮጵያውያን በሙሉ መቀላቀላቹህ ግድ ነውና ጊዜ ሳታጠፉ አሕመንን (የአማራ ሕዝብ መድኅን ንቅናቄን) ትቀላቀሉ ዘንድ በፈጣሪ ስም በአክብሮት ትጠየቃላቹህ???
አማራን በአማራነቱ እንዲደራጅ በመደረጉም የአንድነት ኃይል ነን ከሚሉ አካላትም የሚመጣ ተቃውሞ አለ፡፡ አንድ ነገር ግን ግልጽ መሆን ይኖርበታል፡፡ ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ የዘር ፖለቲካ ሰፍኖ ብሔረሰቦችና ጎሳዎች ኢትዮጵያዊነትን ከመጣል አልፈው ኢትዮጵያዊነትን እየተዋጉ ባሉበት፣ የሀገሪቱን አንድነትና ህልውና አደጋ ላይ በጣሉበት ወቅት፣ የሀገሪቱ አንድነትና ህልውና መሠረትና ዋልታ የሆነው የአማራ ሕዝብ እንዲጠፋ ተፈርዶበት በአራቱም አቅጣጫ ሰፊ ዘመቻ እየተወሰደበት ባለበት ወቅት የአማራ ሕዝብ ዘግይቶም ቢሆን ኢትዮጵያን ከጥፋት ለመታደግ አስቀድሞ እራሱን መታደግ ቁልፉና አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን ተረድቶ ህልውናውን ከፈጽሞ ጥፋት ለመታደግ በአማራነቱ ተደራጅቶ የሚያደርገውን ትግል መቃወም ወይም አለመደገፍ ማለት በእርግጠኝነት እነግራቹሀለሁ አማራ የሌለባት ወይም የጠፋባት ኢትዮጵያ እንድትኖር መስማማት ነው፡፡ አማራ በመጥፋቱ ውስጣቸው ደስተኛ ስለሆነ ካልሆነ በስተቀር ፖለቲከኞች (እምነተ አሥተዳደራውያን) ነን ካሉ በኋላ ይሄንን የዘር ማጥፋትና ማጽዳት ግፍ ሊያጋልጡ፣ ሊናገሩ፣ ሊያስተናግዱ የማይችሉበት ምን ምክንያት አለ?
አማራ በአማራነቱ ተደራጅቶ እያደረገው ያለውን የአማራን የህልውና ትግል እየተቃወማቹህ ያላቹህ ወገኖች አውቃቹህም ይሁን ሳታውቁ እያደረጋቹህ ያላቹህት ይሄንን እንደሆነ ጠንቅቃቹህ ልታውቁት ይገባል፡፡ አማራ ያልሆነው በዚህ ጉዳይ ላይ ቢስማማ ላያስደንቅ ይችላል፡፡ “አማራ ነኝ!” የሚሉ ሆነው እያለ ግን አማራ የጠፋባት፣ የተወገደባት ኢትዮጵያ እንድትፈጠር መስማማት ወይም መፍቀድ ግን እጅግ አሳፋሪ፣ አስገራሚና የሚያቅለሸልሽ ጉድ አይደለም???
ሲጀመር በአማራ ላይ በሰፊው እየተወሰደ ያለውን የዘር ማጥፋት ዘመቻ የሚቃወም፣ የሚያወግዝና የሚያንገበግበው የአንድነት ኃይል ቢኖር እኮ አማራ በአማራነቱ ተደራጅቶ እራሱን ከመጥፋት ለማዳን መታገሉ አስፈላጊ ባልሆነ ነበር፡፡ የሆነውና እየሆነ ያለው ግን የዚህን ተቃራኒ በመሆኑ ነው በአማራነቱ ለመደራጀት የተገደደው፡፡ “የአንድነት ኃይል ነን!” የሚሉ ኃይሎች ከፊሎቹ በአማራ ሕዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ከፈጸሙ እንደ ኦነግና ትሕዴን ካሉ የጥፋት ኃይሎች ጋር ጥምረትና አንድነት ሲፈጥሩ፤ ከፊሎቹ ደግሞ ይሄንን በአማራ ሕዝብ ላይ እየተወሰደ ያለውን በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸመውን የዘር ማጥፋትና ማጽዳት የመጨረሻ ወንጀል እንኳንና ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሊያጋልጡ ሊያስታውቁ ይቅርና ለገዛ ራሳቸው እንኳ ቢሆን ለአንድም ጊዜ ነግረውት የሚያውቁ አይደሉም፡፡ አፍነው ይዘው ነው ያስፈጁን፡፡ እጅግ የሚገርመው ነገር ደግሞ ጉዳዩ አሁንም እንደተዳፈነ ተፈጅተን እንድናልቅ ይፈልጋሉ፡፡
ያለው ሸፍጥ እንዲህ በሆነበት ሁኔታ የአማራ ሕዝብ እንዴት ሆኖ ነው ይሄንን ሸፍጥና ግፍ በጸጋ ተቀብሎ በዝምታ ሊመለከትና ድምፅ ሳይሰማ እንዲያልቅ የሚፈቅደው??? ወይ አጀንዳውን (ርእሰ ጉዳዩን) እናንተው በአግባቡ አልያዛቹህት! ይሄንን ማድረግ ካልቻላቹህ ደግሞ የአማራ ሕዝብ ተደራጅቶ የራሱን ጉዳይ እራሱ ይዞ መንቀሳቀሱን በምን ሞራላቹህ (ቅስማቹህ) ነው ልትነቅፉ፣ ልትቃወሙ፣ ልታወግዙ የምትችሉት??? ትንሽ እንኳን አታፍሩም??? ይሄ በደላቹህ ጠላት ካደረሰብን ግፍ የማይተናነስ እንደሆነ አታስተውሉም??? ኧረ ተው ተው ግፋቹህን በልክ አድርጉት??? ትንሽም ቢሆን እፍረት ይኑራቹህ???
እርግጠኛ ነኝ ዛሬ ላይ የአማራን አስገዳጅ ህልውናን የመታደግ ትግል እየተቃወሙ ካሉ አማሮች ሁሉም እንዲሁም ደግሞ ሰብአዊነትና ኢትዮጵያዊነት የሚሰማው ሌላው ዜጋ ዘግይታቹህም ቢሆን ነገሩ ይገባቹህና የኋላ ኋላ በሁኔታዎች አስገዳጅነት ይሄንን የአማራን ህልውናውን በመታደግ ኢትዮጵያን የመታደግ ትግል መቀላቀላቹህ ወይም መደገፋቹህ አይቀርም፡፡ ይሁንና ይሄንን መረዳት በምታገኙበት፣ በምትገነዘቡበት ወቅት ግን ወቅቱ በጣም የረፈደ ወይም የዘገየ ስለሚሆን ልትፈይዱ የምትችሉት ነገር ስለማይኖር እባካቹህ ነገ ነገሩ ሲገባቹህ መንቃታቹህና ለመቀላቀል መወሰናቹህ ላይቀር ነገር ለአዋቂ አንዲት ነገር ትበቃዋለችና በግልጽ ፈጠው የሚታዩ ሁኔታዎችን ግምት ውስጥ በማስገባት ነገ ሳይሆን ዛሬ እንንቃና በመዘግየታችን ሊደርስብን የሚችለውን አላስፈላጊ የሆነ ከፍተኛ ጉዳትና ኪሳራ በማስቀረት እንታገልና በንጹሐን ደም የሚታጠቡትን የጥፋት ኃይሎችን፣ የኢትዮጵያ ጠላቶችን ጠራርገን እናጥፋ! ህልውናችንንም እንታደግ፡፡
ግድ የላቹህም በኔ ይሁንባቹህ ሀገራችን ኢትዮጵያን ልንታደጋት የምንችለው በዚህ መንገድ ብቻ ነው፡፡ ሌላው ቢሆን ደስ የሚል ነገር ግን የማይጨበጥ ሕልምና ምኞት ብቻ ነው፡፡ ይሄንን አትጠራጠሩ! ሞኞችም አትሁኑ፡፡ ትሰሙኛላቹህ? እንክርዳድ ተዘርቶ እያለ ስንዴን ለማፈስ ከመጠበቅ በላይ ምን ሞኝነትና ጅልነት አለ? ብዙ የማታውቁት ነገር አለ እንዴት ብየ ልግለጽላቹህ? ሁሉም እኮ አይነገርም፡፡ ዓይናቹህ የሚያየውን ጆሯቹህ የሚሰማውን ልብ ብትሉት እኮ ይሄ ሁሉ ጉድ ለመንቃት ከበቂ በላይ አንቂ ነገር ነበረ እኮ!
ዛሬ ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ በአራቱም አቅጣጫ ከገጠር እስከ ከተማ ተዘዋውራቹህ ብትመለከቱ በአማራ ላይ በኢሰብአዊ ርምጃዎች ታጅቦ እየተፈጸመ ያለው ጥላቻ እጅግ አስደንጋጭ ሆኗል፡፡ ይህ ግፍ ከአማራም ተሻግሮ አልፎ አልፎ በሚታዩ ኢትዮጵያዊነትን በሚያቀነቅኑ የሌላ ብሔረሰብ ወይም ጎሳ አባላት ላይም እየተፈጸመ ነው ያለው፡፡ ከሀገር ውጭ ያሉ ኢትዮጵያን ወዳጅ ኢትዮጵያውያንና ወያኔ የአማራ ክልል ብሎ ከሚጠራው የሀገራችን ክፍል ወጥተው የማያውቁ አማሮች ምን እየተካሔደ እንዳለ ቢያውቁም በሆነ ተአምር ነገሮች ድሮ በነበሩበት እንዲገኙ ካላቸው የዋህ ምኞት የትግላችንን አቅጣጫ ለመቀበል እየተቸገሩብን ተቸግረናል፡፡ ነገሮች አሁን ያሉበትን ሁኔታ ለመረዳት ራሳቸውን ንቁ በሆነ የግንዛቤ ዐውድ ላይ ባለማስቀመጣቸውና ከነባራዊ ሁኔታዎች አንጻር እራስን በጊዜው ካለው ሁኔታ ጋር ማጣጣም (making self update) አለመቻል ካልሆነ በስተቀር በተለያየ መንገድ ከሚሰሙትና ከሚያዩት ነገር ዛሬ ያለው እውነታ እነሱ ከሚያስቡትና ከሚመኙት በእጅጉ የተለየ መሆኑን ለመረዳት ሳይችሉ ባልቀሩም ነበረ፡፡ ሁኔታው የዚህን ያህል እጅግ አሳሳቢ በሆነበት ሁኔታ ይሄንን ያህል መዘናጋትንና መጃጃልን ምን ይሉታል??? ነገሩ “ጥፊ ያላት ከተማ ነጋሪት ቢጎሰምባትም አትሰማ!” ሆኖብህ ይሆን ወገኔ??? ኧረ ከዚህ ያውጣን በሉ! በቃ እመኑንና አብረን እንታገል??? ተዉ በኋላ ይቆጫቹሀል ተዉ ተዉ ተዉ???
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
amsalugkidan@gmail.com

Wednesday, June 28, 2017

ኢትዮጵያ የሁሉም ኢትዮጵያዉያን እኩል ሀገር መሆን እንዲችል:- አዲስ አበባን እንደ ማሳያ



     

ሸንቁጥ አየለ
————————————–
አዲስ አበባ ላይ እራሱ የወሰነዉን ዉሳኔ እና ረቂቅ ህግ እያለ የሚያሰራጨዉን ነገር በማራገብ በኢትዮጵያዉያን መካከል የጥላቻ መርዝ እንዲሰራጭ ወያኔ ደፋ ቀና እያለ ነዉ::

አዲስ አበባም ላይ ሆነ እሌሎች ጉዳዮች ላይ ወያኔ እየወሰነ ያለዉ ሆን ብሎ ህዝብን በሚያፋጅ እና ጸረ ኢትዮጵያዊነት በሆነ መልኩ ነዉ::ኢትዮጵያን ወያኔ በቅኝ ግዛት ስለያዛት ቅኝ ገዥነቱን በሚያጠናክር መልክ: ህዝቡን በሚለያይ መልክ እና በመጨረሻም ኢትዮጵያዉያንን እርስ በርሳቸዉ በሚያፋጅ መልክ ነገሮች እንዲሄዱ ይፈልጋል::
ምናልባት ኢትዮጵያ ከእጁ የምትወጣ ከሆነም በሚነሳዉ የርስ በርስ ጦርነት ድምጥማጧ እንዲጠፋ ወያኔ በደንብ አስልቶ የተነሳዉ ዛሬ አይደለም:: በተንኮል አማካሪዎቹ በኩል ወያኔ ህገ መንግስት ሲያረቅ ዛሬ የሚያናፍሰዉን ሁሉ አስልቶ እና አንሰላስሎ አስቀምጦታል::አሁን እያደረገ ያለዉ ነገሮችን ከተንኮል ጎተራዉ እየጎተተ ኢትዮጵያዉያን እርስ በርሳቸዉ እንዲጨራረሱ እና እንዲበጣጠሱ የጥላቻ ሊጡን ማጎብጎብ ነዉ::
ወያኔ ሌላዉ የመዘዘዉ ካርታ ኦህዴድ (ኦሮሞን ወክሎ) እና ብአዴን (አማራን ወክሎ) የአዲስ አበባን ጉዳይ በመወሰን ሂደት ዉስጥ እንዳሉበት ማስመሰል ነዉ:: እናም የወያኔ ካድሬዎች በደንብ አድርገዉ ይሄን ፕሮፖጋንዳ እያናፈሱት ሲሆን አንዳንድ የዋህ ሰዎች ደግሞ እዉነትም ኦህዴድ እና ብአዴን እዚህ ዉሳኔ ዉስጥ ያሉበት እየመሰላቸዉ የነዚህን ድርጅቶች ስም ሲያነሱ እና ሲጥሉ ይስተዋላል:: ሆኖም ኦህዴድ እና ብአዴን የሚባሉ የፈረስ እና የአጋሰስ ስብስቦች አዲስ አበባ እንዲህ ትሁን ወይም እንዲያ ትሁን እሚለዉ ዉሳኔዉ ዉስጥ እንዳሉ የሚመስላችሁ የዋህ ሰዎች እንዳትሸወዱ ማስገንዘብ እወዳለሁ:: ገና ኢትዮጵያን ከተቆጣጠረበት: ህገመንግስት እስከጻፈበት እንዲሁም እስካሁን ድረስ ሁሉንም ዉሳኔዉን እየሰጠ ያለዉ ብቸኛዉ ሀይል ወያኔ/ህዉሃት ብቻ ነዉ::
እናም ሁሉም ወገን ለዉጥ ከፈለገ እንዲሁም እዉነተኛ የህዝቦች ዘላቂ ሰላም ከፈለገ አንድ ነገር ላይ ብቻ ያተኩር::ወያኔን በማባረር እና ስሩን በመንቀል ላይ::ኢትዮጵያን ከወያኔ ቅኝ ተገዥነት ነጻ እማዉጣት ላይ::አዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን ሁሉም የኢትዮጵያ ምድር የሁሉም ኢትዮጵያዉያን እኩል ሀገር መሆን የሚችለዉ ወያኔ ሲነቀል ብቻ ነዉ:: ወያኔ በኢትዮጵያ ፍጅት እና የጎሳዎች እልቂት እንዲመጣ አንዱን አካባቢ የአንዱ ብቻ: አንዱን ቀብሌ የዚያ ንብረት ብቻ እያለ ተንኮል እየጎነጎነ የሚፈጥረዉን ተረት ተረት ተቀብለህ ማንኛህም ወገን አብረህ አትሩጥ:: የቱም አካባቢ የማንም ብቻ አይደለም::ኢትዮጵያ የሁሉም ኢትዮጵያዉያን እኩል ሀብት እና እኩል ሀገር ነች::
ወያኔ ሆን ብሎ ኢትዮጵያን በሰባት ክልል ከልሎ ሰባቱን ክልሎች ለሰባት ብሄረሰቦች አድሎ ሲያበቃ ሰማኒያ የሀገሪቱ ብሄረሰቦችን/ጎሳዎችን/ማህበረሰቦችን ሀገር አልባ አድርጓቸዋል::በወያኔ የሀገር ሽንሸና መሰረት አንድ ክልል ሲከለል ያክልል የአንድ ብሄረሰብ ሀብት እና ንብረት ይሆንን እና በዚያ ክልል የሚኖረዉ ሌላዉ ኢትዮጵያዊ ግን መጤ ወይም ሀገር አልባ ተደርጎ እንዲቆጠር ይደረጋል::በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ከሚገኙት ሰማኒያ ሰባት ብሄረሰቦች ዉስጥ ክልል ያላቸዉ ሰባት ብቻ ሲሆኑ ሰማኒያ የሚሆኑት የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች/ማህበረሰቦች/ጎሳዎች ክልል የላቸዉም::
ይሄም ማለት በወያኔ የደንቆሮ ፍች መሰረት እነዚህ ክልል የሌላቸዉ ሰማኒያ ብሄረሰቦች አገር የላቸዉም::ምክንያቱም በየትኛዉም ክልል ቢሄዱ የሚቆጠሩት መጤ ወይም ሀገር አልባ ተደርገዉ ነዉ::የወያኔ አስተሳሰብ በመሰረታዊነት ታላቅ የተስቦ በሽታ የተጠናወተዉ አስተሳሰብ ነዉ::በርካታ ኢትዮጵያዉያንን እየገደለ ያለ እና በመጨረሻም ኢትዮጵያዊነትን ስሩ እንዲነቀል ተግቶ የተቀመረ አስተሳሰብ ነዉ::
በመሆኑም የመጀመሪያ ተቃዉሞ የሚጀምረዉ የወያኔን ህገመንግስት ብሎም ህግጋት: የወያኔን ክልል: የወያኔን ዉሳኔ እና የወያኔን አስተሳሰብ በሙሉ ዉድቅ ማድረግ ነዉ::ወያኔ የሰራዉን እና የወሰነዉን ሁሉ በልብህ አፍርሰህ መነሳት አለብህ:: ተወደደም ተጠላም ወያኔ የሰራዉ እና የዘራዉ ሁሉ ይፈርሳልም: ይደመሰሳልም::የወያኔ መርዝ እና ካንሰራዊ አስተሳሰብ በሙሉ ይነቀላል::
ኢትዮጵያ የሁሉም ኢትዮጵያዉያን እኩል ሀገር መሆን የሚችለዉ መቼ ነዉ ብለህ መጠዬቅ ከቻልክ ብቻ ይሄን እዉነት ትደርስበታለህ:: ኢትዮጵያ የኢትዮጵያዉያን ሁሉ ሀገር እንድትሆን ወያኔን ንቀል::ከዚያም ሁሉም በጋራ አንዲት ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመስራት ወገብህን ጠበቅ አድርገህ ተነስ::ምርጫ የለም::ያለዉ ምርጫ አንድ ነዉ::ሁሉም እኩል አሸናፊ የሚሆንበትን ስልት እና ስትራቴጅ መንደፍ ነዉ::ይሄም ኢትዮጵያ የሁሉም ኢትዮጵያዉያን እኩል ሀገር መሆን እንዲችል ማድረግ::ለዚህም አንዲት ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመስራት በጋራ መነሳት::
ኢትዮጵያን እግዚአብሄር ይባርካት !

የሃገራችንን ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ በማስመልከት የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ መሪዎች ከማረምያ ቤት የላኩት መግለጫ እጃችን ገባ (ይዘነዋል)


Filed under: News Feature,የዕለቱ ዜናዎች |


 0  1520  1520

በአሮጌ አቁማዳ አዲስ የወይን ጠጅ አይጨመርም!

ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታት በህዝባችን ላይ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ረገጣ፣ የኢኮኖሚ ዘረፋና የፖለቲካ ጭቆና የተፈፀመ ሲሆን በተለይም ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ ትዕግስቱ በመሟጠጡ በአገዛዙ ላይ የተቃውሞ እንቅስቃሴ በማካሄድ ላይ የሚገኝ መሆኑ ከማንም የተሰወረ አይደለም፡፡ እኛ ይህን ኢፍትሀዊነት የተቃወምን ዜጎች ከተወረወረንበት እስር ቤት ሆነን አሁንም ያገራችን ጉዳይ እንደሚመለከተንና እንደሚያሳስበን በመግለጽ ባለፈው ዓመት መጨረሻ ላይ ለመንግስት ጠቋሚ ነው ብለን ያልነውን ምክረ-ሀሳብ መለገሳችን ይታወሳል፡፡ ነገር ግን ከድጡ ወደ ማጡ እንዲሉ ሁኔታዎችን ከመለወጥ ወይም ከማሻሻል ይልቅ በሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን በመጨፍጨፍና በማቃጠል ሺህዎችን በፌዴራልና በክልል እስር ቤቶች በመወርወር፣ አስር ሺህዎችን በፌዴራል ወታደራዊ ካምፖች በማጎር፣ ሺህዎችን ካገር በማሰደድ አገሪቱ በመበታተና በርስ በርስ ጦርነት መንታ መንገድ ላይ እንድትቆም አድርጓታል፡፡ በተለይም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀ ወዲህ ደግሞ ህዝባችን በቀደመት ሥርዓቶች ይቅርና ከጠላት ወረራ ጊዜ እንኳን በባሰ የነፃነት እጦት ውስጥ ለመኖር ተገዷል፡፡ ያን ሁሉ ግፍ በህዝብ ላይ እያደረሰ መልሶ ደግሞ “እንዲህና እንዲያ አደርግላችኋለው” ተብሎ በየማዕዘኑ መሠረት ድንጋይ እየተጣለ፣ የቁርጥ ቀን አርቲስቶችና አድርባይ ምሁራን ከየአፎታቶው እየተመዘዙ የማስመሰልና የማታለል ተግባራቸውን ለማከናወን እንደጥንግ በመወርወር ላይ ናቸው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሚያዚያ 11 ቀን 2009 ዓ.ም በቴሌቪዝን ብቅ ብለው በፓርቲያቸው የሚመራው መንግስት በጥልቀት መታደስ ስለመጀመሩ ሰፊ ትንተና ሰጥተዋል፡፡ መታደስ ለመጀመሩ ማሳያ ናቸው ያሏቸውን ነጥቦችም ዘርዝረዋል፡፡ ዋና ዋና ማሳያዎች ናቸው ብለው ያነሱት አዲስ የአመራር ምደባ መደረጉ፣ አስፈፃሚ አካላትን የሚቆጣጠሩ ተቋማትን ማጠናከር መጀመሩ፣ ዴሞክራሲን የማስፋትና የማጥለቅ ተግባርን ማጎልበት መጀመሩና ለወጣቶች ሥራ ፈጠራ አዲስ ስትራቴጂ ተቀይሶ ሥራ ላይ መዋል መጀመሩ ናቸው፡፡ እነዚህ እርምጃዎች ካሁኑ ውጤት እያስገኙ መሆናቸውንም ገልፀዋል፡፡ እኛም እሳቸው በሰጡት መግለጫና ከዚያ በኋላ በሁሉም አዳራሾች እየተስተጋባ ስላለው የጥልቅ ተሀድሶ ማደንዘዣ መርፌ ስህተተኝነት በማብራራት ሊሆን የሚገባውን ለመጠቆም እንፈልጋለን፡፡
አሁን በሥልጣን ላይ ያለውን ፓርቲና መንግስት የኋላ ታሪክ ጥቂት መለስ ብለን ብንቃኝ አገር ለመምራት ሞራላዊ ብቃት የሌለው መሆኑን የሚያሳዩና ጥልቅ ተሀድሶ ተብዬውን ማደናገሪያ እንዳንቀበል የሚያደርጉ በርካታ ድርጊቶቹን እንመለከታለን፡፡ ከ16 ዓመታት በፊት ይኼው ፓርቲ “የመበሰበስ አደጋ አጋጥሞኛልና የመታደስ ዕድል ስጡኝ” በማለት የተወሰኑ አባላቱን በማሰርና ከፓርቲው በማባረር ሁኔታው እንደማይደገም ቃል ገብቶ በአገዛዙ ቀጠለ፡፡ ነገር ግን ንቅዘቱና መበስበሱ ቃል በተገባው መሠረት ባለመታከሙና ባለመቀረፉ ህዝቡ ቁጣውንና ቅሬታውን በ1997ቱ ምርጫ ድምፁን ለተቃዋሚዎች በመሰጠት ገለፀ፡፡ ዳግም ምርጫና ማሟያ ምርጫ በማለት የህዝቡን ድምፅ ያለአግባብ መልሶ ከወሰደ በኃላ አብዛኛውን ተቃዋሚ እስር ቤት አስገባ፡፡ በሌላ ወገን ደግሞ መሸነፉን በማመን “ህዝብ ድምፅ የነፈገኝ በገጠሩ ላይ አትኩሬ ከተማውን በመዘንጋቴ ነው” በማለት ከተሞችን በማልማት ስም የከተሞችን መሬት ለአባሎቹና ደጋፊዎቹ በማከፋፈል ዘርፎ አዘረፈ፡፡ በየአደረጃጀቱና በሲቪል ሰርቪስ አመራር ላይ የተመደበው የፓርቲ አባላም በዘርፉ ለይ በመሠማራቱ ህዝብን ማገልገል ተዘነጋ፡፡ ህዝቡ በመልካም አስተዳደርና ነፃነት እጦት በያለበት መነሳሳት ሲጀምር ቢፒአር የተባለ ዘመናዊ የአሠራር ጥበብ ሥራ ላይ በማዋል “ዳግም እንድታደስ ይፈቀድልኝ” በማለት ወትውቶ ከላይ እስከታች አዲስ መዋቅር መዘርጋቱን አስተወቀ፡፡ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ግድግዳቸው ፈራርሶ በመስተዋት ተተካ፡፡ በማንኛውም የሥራ መስክ ፀንቶ የኖረው ለህሊናና ለሙያ ሥነምግባር የመገዛት እሴት በይፋ ተቀበረና በመስተዋት ውስጥ መጠባበቅ ተጀመረ፡፡ አመራሮች ያለችሎታቸው መመደባቸውም እውቅና በማግኘቱ በተሃድሶው መሠረት በቂ የትምህርት ዝግጅት ያላቸው ሰዎች በተገቢው ቦታ ይመደባሉ ተባለ፡፡ የሙሰኝነትና የመልካም አስተዳደር ችግርም እስከወዲያኛው ያከትምለታል በማለት ህዝቡ የተሰፋ እንጀራ በመመገብ እንዲረጋጋ ተደረገ፡፡ ነገር ግን የተባለው ቀርቶ ተቃራኒው ሥራ ላይ ይውል ጀመር፡፡ የአመለካከት ችግር አለባቸው የተባሉ ሰዎች ተጠራርገው እንዲወጡ በተደረገው ዘመቻ እንኳንና የኃላፊነት ቦታዎች በተራው የሥራ መደብ ላይ ያለፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ማንም እንዳይቀጠር ተደርጎ ሲቪል ሰርቪሱ በካድሬ ተጥለቀለቀ፡፡ ሌላው ዜጋ ለሥራ አጥነት ተዳረገ፡፡ በድብቅ ሲቀናቀን የነበረው አመለካከትም ይፋ ሆነ፡፡ ይህ አመለካከት ማንኛውም በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ አገልግሎትና የፖለቲካ ዘርፍ በፓርቲው ቁጥጥር ሥር መዋል አለበት የሚለው አስተሳሰብ ነው፡፡ በሌሎች አገሮች ተሞክረው ውጤት ያስገኙት ዘመናዊ የአሠራር ሪፎርሞች ለህዝብ ሳይሆን ለፓርቲ ወገንተኛ በሆኑ አመራሮችና ሠራተኞች ምክንያት መክነው የተዘመረለት መልካም አስተዳደርም የውሃ ሽታ ሆኖ ቀረ፡፡ ከዚያ በኋላ የተፈጠሩት አደራጃጀቶችና ቅጥሮች ሁሉ የሚከናወኑት ይህን አስተሳሰብ ከግብ ለማድረስ ነው፡፡

ታዲያ አሁን ወደ አመራር መጡ የተባሉት አዳዲስ ባለሥልጣኖች ከየት የመጡ ናቸው? በዚሁ አመለካከትና የታማኝነት መስፈርት ውስጥ አልፈው በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ሲሠሩ የነበሩ አይደሉምን? ብዙዎች ኢህአዴግ “መቶ በመቶ አሸንፌ ይዣለሁ” ባለው ፓርላማ ውስጥ ታድመው እያየናቸው “ቴክኖክራቶች እንጂ ፖለቲከኞች አይደሉም” ብሎ ከመናገር የበለጠ ህዝብን መናቅ ከየት ሊመጣ ይችላል? የህዝቡን ድምፅ ዘርፈው ተፎካካሪዎቻቸውንና ታዛቢዎችን አስደብድበውና እስር ቤት አስወርውረው ሥልጣን ላይ የተቀመጡ ወንጀለኞችን የጥልቅ ተሀድሶ ማሳያ ናቸው ማለት ሊታገሱት የሚከብድ ስድብ ነው፡፡ እነዚህ “ቴክኖክራቶች” የተባሉት አዳዲስ አመራሮች ሥራ ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ የሚናገሩትንና የሚሠሩትን የተከታተለ ሰው ከኢህአዴግ በላይ ነባር ኢህአዴጋውያን መሆናቸውን ሊገነዘብ ይችላል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለጥልቅ ተሀድሶው እንደሁለተኛ ማሳያነት ያነሱት አስፈፃሚ አካላትን የሚቆጣጠሩ ተቋማት በመጠናከር ላይ መሆናቸውን ነው፡፡ አስፈፃሚውን አካል በዋናነት የሚቆጣጠረው የተወካዮች ምክር ቤት ሲሆን የዋና ኦዲተርን፣ የሰብአዊ መብት ኮሚሽንን፣ ፀረ ሙስናና የእንባ ጠባቂ ተቋማትን በማጠናከር እየተጠቀመባቸው እንደሆነ ገለፀዋል፡፡ የተጠቀሱት ተቋማት ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረጉ መሆናቸውን በመጠቆም ተስፋ ሰጭ ጅምር ነው ብለውታል፡፡ ለመሆኑ ተቆጣጣሪ ነው የተባለው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በምን ዓይነት ሁኔታ የመጣና እንዴት ያለ ስብሰብ ነው? እውን እነዚህ ሰዎች ህዝቡ ድምጹን የሰጣቸው እውነተኛ ተወካዮቹ ናቸው? እያንዳንዳችን ከየምንኖርበት አካባቢ እንዴት እንደመጡና ስንት ግፍ በእጃቸው እንደለ ስለምናውቅ ስለማንነታቸው ብዙ በማተት ጊዜ ማጥፈት አንፈልግም፡፡ አብዛኛዎቹ ህዝብ ይሁንታውን ሰጥቶ የላካቸው ባለመሆናቸው በራስ መተማመን የሌላቸው፣ ለፓርቲያቸው እንጂ ለህዝብ ወገንተኛ ያልሆኑ፣ ተጽፎ የተሰጣቸውን ጥያቄ የሚጠይቁ፣ አስቀድሞ ለሚሰጣቸው ጥያቄ “ስጡ” የተባሉትን መልስ ብቻ የሚሰጡ ‘ተቃወሙ’ ወይም ‘ደግፉ’ የተባሉትን ያለአንዳች ጥያቄ የሚቃወሙና የሚደግፉ፣ ተመርጠናል የሚሉበትን ክልል ህዝብ የማይወክሉ መሆናቸውን ብቻ መግለጽ በቂ ይሆናል፡፡ በምክር ቤት ውስጥ ያሉት ቋሚ ኮሚቴዎችም በአብዛኛው ላሉበት ቦታ የሚመጥን ብቃት እንደሌላቸው በሰፊው ይታወቃል፡፡ ለምሳሌ ያህል የውጪ ግንኙነት፣ የመከላከያና ደህንነት ቋሚ ኮሚቴ አባላት አገሪቱ ከየትኞቹ አገሮች ጋር ምን ዓይነት ግንኙነት እንዳላት፣ ምን ያህል የመከላከያ ሠራዊታችን አባላት በስንት አገሮች ተሰማርተው እንዳሉ፣ ስንቶች ተሰውተው ላገራቸው አፈር ሳይበቁ እንደቀሩና ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆዩ ያውቁ ይሆን? ለመሆኑ ከዓለም አቀፍ አበዳሪ አካላት በየጊዜው መጥቶ ባለሥልጣኖች ኪስ ሲገባ የኖረውና በአገሪቱ ደም በአናታችን ላይ የሚያናጥረው የብድር ዕዳ ስንት እንደሆነ የሚያውቁ አባላት ምን ያህል ይሆኑ? ባገራችን ፓርላማ ውስጥ በቴሌቪዥን እንደምንመለከተው አስፈፃሚ አካላት በተለይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀርበው ሪፖርት ሲያቀርቡ አባላት ጥያቄ ሲጠይቁ እንኳን እንደዚያ የሚሸቆጠቆጡት ተቆጣጣሪ መሆናቸውን በትክክል ስለሚያውቁ ነው ማለት ይችላል? ህገ መንግስቱ ላይ የተፃፈውን ለጊዜ እንርሳውና የፓርላማውን ገሀዳዊ እውነት ብንመለከት ተቆጣጣሪ የሚመስለው ምክር ቤቱ ነው ወይስ አስፈፃሚው ነው? ታዲያ “እኔ ተቆጣጣሪ ነኝ” ብሎ የሚያስብ ወይም መሆኑን የማያውቅ ወይም አቅም የሌላው አካል እንዴት አድርጎ ሥራውን ሊያከናውን ይችላል? በመንግስት ሚዲያዎች ብዙ ጊዜ እንደምንሰማው የቋሚ ኮሚቴ አባላት አንዳንድ አስፈፃሚ መ/ቤቶችን በመጎብኘት ኃላፊዎችን አነጋግረው ገለፃዎችን አዳምጠው ይመለሳሉ፡፡ ቁጥጥር ማለት ይህ ነው? ተወካዮች ምክር ቤት ተጠናክሮ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል ተብሎ የሚነገረን ይኼ ነው፡፡ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እውን ተቆጣጣሪ ቢሆንና አባላቱም በህዝብ የተመረጡ፣ ለህዝብ የሚቆረቆሩ፣ በራሳቸው የሚተማመኑና ነፃነት ያላቸው ቢሆኑ ኖሮ ባለፉት ሁለት ዓመታት በሶስት ክልሎች ህዝባዊ ተቃውሞ ተነስቶ በአስፈፃሚው ትዕዛዝ የዜጎች ህይወት ሲረግፍ አጀንዳ ለማሳያዝ የሚሞክር ሰው ባልጠፋ ነበር፡፡ ስለዚህ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ይህን ኃላፊነት ሊወጣ አይችልም፤ ሊጠናከር የሚችልም አይደለም፡፡ አስፈፃሚ መ/ቤቶችን ለመቆጣጠር ጥረት እያደረገ ስለመሆኑ ይሰማል፡፡ ነገር ግን ከተጣለበት ኃላፊነት አንፃር አቅሙ ደካማ ነው፡፡ በአገሪቱ ከ250 በላይ ግዙፍ የፌደራል መንግስት መ/ቤቶች ሲኖሩ ተቋሙ በዓመት የፋይናንስ ኦዲት ሊያደርግባቸው የሚችለው ከስድሳ አይበልጡም፡፡ እያንዳንዱን መ/ቤት ለማዳረስና አንዴ ኦዲት ተደርጎ ጉድለት የተገኘበት መ/ቤት ተሻሽሎ እንደሆነ በዳግም ኦዲት ለማረጋገጥ ስንት ዓመት እንደሚፈጅበት መገመት ቀላል ነው፡፡ ተቋሙን በጥቂት ሚሊዮኖች አቅሙን አጎልብቶ የቁጥጥር ሥራ በማካሄድ ብዙ ሚሊዮኖችን ከምዝበራ መታደግ ሲቻል ከፓለቲካ ቁርጠኝነት ማነስ የተነሳ የአገር ሀብት ለዘራፊ ተጋልጦ ጉዟችን የኋሊት ሆኗል፡፡ ይህንን ለማለት ያስቻለን ተቋሙ ካመጣቸው ሪፖርቶቸ ቀንጨብ ተደርጎ በሚዲያ ከተላለፈው በመስማት ካደረብን መጠነኛ እምነት ነው፡፡ ተቋሙ ከሙሉ ልቡ ሳይሆን ለይስሙላ ብቻ እንዲንቀሳቀስ መደረጉን ሌላው አመላካች ጉዳይ በኦዲት ጉድለት የተገኘባቸው መ/ቤቶችና እስከነአካቴው “ኦዲት አንደረግም” ባሉ መከላከያ ሚኒስቴርን በመሳሰሉ እጅግ ከፍተኛ ገንዘብ የሚያንቀሳቀሱ መ/ቤቶች ላይ እርምጃ አለመወሰዱ ነው፡፡ መንግስት ጉዳዩን አጥብቆ የሚሻው ሳይሆን የግብር ይውጣ እንቅስቃሴ እንዲያደርግ መፈለጉን ሌላኛው ማሳያ የተቋሙ ሪፖርት ለሚዲያ ተቋማት የማይሰጥ መሆኑና በዝርዝር ይፋ የማይደረግ መሆኑ ነው፡፡ ኦዲት የሚደረጉ መ/ቤት ንጽህናና ሌብነት ከህዝብ እንዲሰውር የሚፈለገው ለምን ይሆን? አስፈፃሚውን አካል ይቆጣጠራል ብለው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጠቀሱት ሁለተኛው ተቋም የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ነው፡፡ ይህ ተቋም የዜጎችን መብት ለማስጠበቅ ሳይሆን ሥርዓቱ ለሚፈጽማቸው የሰብአዊ መብት ጥሰቶች የህጋዊነት ሽፋን ለመስጠት የተቋቋመ ነው፡፡ ከተመሠረተ ጀምሮ በአገሪቱ ከተፈፀሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች መካከል የትኞቹን አጣርቶ እርምጃ እንዳሰወሰደ ከሠነዱ ማግኘት አይቻልም፡፡ ሌሎች የውጪ ተመሳሳይ ድርጅቶች ስለህዝባችን በርካታ ሪፖርቶችን ሲያወጡ ተቋሙ ግን ግፍን በዝምታ በማለፍ ይታወቃል፡፡ እንዲህ ዓይነት ተቋም ቢኖረንማ ኖሮ በያመቱ ሺሀዎች ሲታሠሩ፣ ሲገደሉ፣ ካገር ሲሰደዱ፣ ዜጎች በጥይት ተቆልተው ወደ እሳት ሲጣሉ፣ በዓል ለማክበር ቀጤማ ይዘው ወጥተው ከሰማይና ከምድር በተርከፈከፈባቸው ጥይት ሲረግፉ “አሁንስ በዛ” በማለት ጥፋተኛን ያጋልጥ ነበር፡፡ አሁን ግፉ በዝቶ የህዝብ ቁጣ ገንፍሎ የዓለም ሁሉ ዓይንና ጆሮ ወዳገራችን ሲዞር ሥርዓቱን ከውድቀት ለማዳን ሲውተረተር እንመለከታለን፡፡ የተቋሙ መሪ ኢህአዴግ “ሙሉ በሙሉ ቀናኝ” ባለበት 2007ንም ምርጫ ድምፅ ለእውነተኛ ባለቤቱ እንዳይሰጥ ወይም እንዳይቆጠር በማድረግ የመራጮችን ተስፋ በማጨለሙ ረገድ ዋናኛውን ሚና የተጨወቱ መሆናቸው የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡ በወቅቱ የፈፀሙት ድርጊት ትክክል አለመሆኑና ህዝቡም በሥልጣን ላይ ያለውን መንግስት አለመምረጡን “ተመራጩ መንግሥት” ሥራ በጀመረ በሁለተኛው ወር የህዝብ ተቃውሞ፡፡ መፈንዳቱ ያረጋግጥልናል፡፡ ስለዚህ የተቋሙ መሪ ከወራት በፊት በተጭበረበረ መንገድ ወደ ስልጣን ያመጡት መንግስት ግፍ ቢፈጽም በገልተኝነት አጣርተው ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ አይጠበቅም፡፡ ለዚህ ነው በምርጫው ጊዜ በነበራቸው ኃላፊነት ቁም ስቅላቸውን ያሳዩአቸውን ለዴሞክራሲያዊ እየታገሉ ያሉ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትን ባላቸው ኃላፊነት ተጠቅመው ዛሬም ተጠያቂ አድርገው ያቀረቡት፡፡ በኮሚሽነሩ አማካኝነት በተዘረፈ ድምፅ በምክር ቤት የታደመው ፓርላማም ኮሚሽኑ “ከተቃውሞው ጀርባ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አሉ” ሲል ያቀረበውን ሃሳብ ማጣራት ሳያስፈልገው ተቀብሎ አጽድቆ ቀደም ሲል ከተካሄደው የእስራት ዘመቻ የተረፉ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ካሉ ታድነው እንዲታሠሩ የወሰነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰብአዊ መብት ኮሚሽናቸውን አስመልክተው በተናገሩት ንግግር ውስጥ አስገራሚ ነገሮችን አሰምተውናል፡፡ “አቅሙን ማጎልበት ይኖርብናል” ያሉትን ተቋም መልሰው ደግሞ “ለዚች ለተፈጠረችው ጉዳይ ግን በቂ አቅም አለው” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ “ይቺ” ተብሎ ተንኳሶ የቀረበው ጉዳት በአንድ ቀን ጀንበር ስድስት መቶ ያህል ሰዎች የሞቱበትና የብሔራዊ ሀዘን የታወጀበት የእሬቻ እልቂት፣ በባህር ዳርና በጎንደር መቶዎች የተገደሉበት፣ በቂሊንጦ እስር ቤት ቁጥሩ ያልታወቀ እስረኛ ከነ ነፍሱ የተቃጠለበት፣ በጌዴኦ በርካታ ሰው የሞተበትና የተፈናቀለበት፣ በኮንሶ መጠነ ሰፊ ፍጅት የተካሄደበት ኢሰብአዊ ድርጊት ነው፡፡ እነዚህ ወደፊት ታሪክ ይፋ የሚያደርጋቸውን አሃዞች እንኳን ብንተው የሰብአዊ መብት ኮሚሽኑ “ቆጥሬ ደርሼባቸዋለሁ” ያለው የ495 ሰዎች ሞትና የ464 ሰዎች አካል ጉዳት እንዴት እንደአልባሌ ሊቆጠር ቻለ? ስንት ሰው ቢሞት ይሆን መንግስታችንን የሚያሳስበው? የዓለም ህዝብ ከጥቁር ደቡብ አፍሪካውያን ጎን እንዲቆም ካደረጉትና ለአፓርታይድ ስርዓት መውደቅ ምክንያት ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ 69 ሰዎች የተገደሉበት የሻርፕል እልቂት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትራችን አያውቁም ማለት አንችልም፡፡ በህዝብ የተመረጡ መንግስሥታት ባሉባቸው አገሮች እንዲህ ያለው ጉዳይ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከሥልጣን የሚያስወርድ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ”በብዙ የበለፀጉ አገሮች ግፍ እየተፈፀመ ማንም አይጠይቃቸውም” በማለት “እኛን ለምን ትጠይቁናላችሁ?” የሚል ምሬት ያለው ንግግርም ተናግረዋል፡፡ እንደኮሚሽነራቸው የሆነውን “አልሆነም” የተበደለውን “ተጠያቂ”፣ መቶውን “እስር” ነው ከሚሉ አንደኛውን “አትጠይቁን” ማለት ይሻላል፡፡

ለመሆኑ የሰብአዊ መብት ኮሚሽናችን ዓላማው የህዝብ መብት እንዳይጣስ ማድረግ፣ ተጥሶም ከተገኘ አጣርቶ እርምጃ ማስወሰድ ከሆነ ተመሳሳይ ዓለማቀፍ ድርጅቶች ልምዳቸውን እንዲያካፍሉትና በማጣራቱ ተግባር እንዲያግዙት የከለከለው ምንን ለመደበቅ ብሎ ነውን ትምህርት ቤትና ጤና ጣቢያ ለመሥራት እርዳታና ብድር ሲያጎርፉልን “ሉአላዊነታችንን ደፍራችኋል ንቃችሁናል” ያላልናቸውን አካላት ዛሬ “በማጣራቱ ሂደት እንተባበራችሁ” ቢሉ ሉአላዊነትን መድፈር የሚሆነው በምን ስሌት ነው? እንዳይገለጥ የምንፈልገው እውነት ይኖር ይሆን? በአጠቃላይ “ተጠናከሯል፣ አስፈፃሚውን እየተቆጣጠረ ነው፣ ተአማኒነው፤” ተብሎ የሚሞካሸውና እየታደስን ለመሆናችን እንደማሳያ የተወሰደው ተቋሞ እንዲህ ያለው ነው፡፡ አስፈፃሚውን ይቆጣጠራሉ የተባሉት ሌሎች ተቋማት የእንባ ጠባቂ ተቋሞና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ናቸው፡፡ የነዚህ ተቋማት መኖር የሚታወቀው በዓመት የተወሰነ ቀናት ፓርላማ ላይ ሲቀርቡ ወይም መንግስት ባስፈለገው ቀን መዝዞ ለሰው ሲያሳያቸው ነው፡፡ ፋይዳ ያለው ሥራ ሲፈጽሙ አይሰማም ከሶስት ዓመታት በፊት የመንግስት አስተዳደር ኮሚሽን “ከፍተኛ ባለሥልጣኖች የመንግስት ቤቶችን አለአግባብ ይዘው አንለቅም ብለውኛልና አንድ በሏቸው” በማለት ለፀረ ሙስና ኮሚሽን ቢያመለክት “በቅድሚያ ለኛ ቤት ስጡን” እንደተባለ ከመንግስት ሚዲያ ለመረዳት ችለናል፡፡ ህዝቡ የሙስና ኮሚሽን ብሎ ሲጠራው ስህተት መስሎን የነበረው ለካ ትክክል ነው፡፡ ስለዚህ ራሱ ሌላ ተቆጣጣሪ የሚያሻው ነው፡፡ በብዙ ሚሊዮን ብር የተሠራ ህንፃ ጠፋ በሚባልበት አገር፣ ተማሪዎች መሬት እየተኙ በሺህዎች የሚቆጠሩ የዩኒቨርስቲ አልጋዎች በሚከራዩበት ምድር አስተዳደራዊ በደል ደርሶባቸው ፍትህ የተነፈጉ መንገድ ላይ በሚንሰላወዱበት ስርዓት ውስጥ ፀረ ሙስና/እንባ ጠባቂ ተቋማት አሉ ማት ፌዝ ነው፡፡ የውጭ ለጋሾችን ለማታለል ካልሆነ ከህዝብ ጆሮ የሚገባ አይደለም፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጥልቅ ተሀድሶው ሌላኛው መገለጫ ዴሞክራሲን የማስፋትና የማጥለቅ እንቅስቃሴ መጀመር መሆኑ ገልፀዋል፡፡ ዴሞክራሲን ለማስፋት ወሳኝ ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ የመድበለ ፓርቲ ሥርዓትን መገንባት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይህም የሚገነባው ነፃ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ሲኖሩ፣ ድምፁ ዋጋ ያለው መሆኑን የሚያምን ህዝብ ሲኖር፣ የህግ የበላይነት ሲኖር፣ በነፃ የመደራጀት መብት ሲኖርና ገለልተኛ የምርጫ አስፈፃሚ ሲኖር ነው፡፡ ይህ ሊሆን የሚችለው ህዝቡ ከመረጠው ብቻ ሥልጣን መቆየት የሚፈልግ መንግስት ባለበት አገር ብቻ ነው፡፡ በዚህ ረገድ ስንመለከት የኢሀአዴግ መንግስት ለዚህ ዝግጁ አይደለም፣ ፍላጎትም የላቸውም፡፡ ከመድረክ ውጪ ከሚታወቅባቸው አባባሎች አንዱ “ደም ከፍለን የመጣነው በካርድ ለመውረድ አይደለም” የሚለው ነው፡፡ ለዚህ ባህሪይ አስተዋጽኦ ያደረገው ሥልጣንንና በሱ አማካኝነት የሚገኘውን ጥቅም አብዝቶ በመሻቱ ብቻ ሳይሆን ገና ሲመሠረት የተጠናወተውና የመድብለ ፓርቲ ሥርዓትን የማይፈቅደው የሶሻሊስ ርዕዮተ ዓለም አባዜ ነው፡፡ ድጋፋቸውን ለማግኘት ሲል በኃላ ላይ የምዕራቡን ዓለም አስተሳሰብ ተቀብያለሁ ቢልም በራሱ ውስጥ አስርጾ ሊጠቀምበት ባለመቻሉ አስተሳሰቡን እንደያዘ የማስመሰያ ሰልቶችን ለመቀየስ ተገደደ፡፡ ለማደናገሪያነት አብዮታዊ ዴሞክራሲ፣ ልማታዊ መንግሥት እና አውራ ፓርቲ የሚሉ ባዶ ቃላትን መሰበክ ጀመረ፡፡ በተግባርም ዴሞክራሲ ብሎም መድብለ ፓርቲ ስርዓት የሚመሠረትበትን መሠረት መናድ ተያያዘ፡፡ ነፃ ተፎካካሪ ፓርቲዎች እንዳይመሠረቱ አደረገ፡፡ በትግል የተመሠረቱትን በራሱ ሠርጎ ገቦች አማካኝነት አፈራርሶ ጥገኛ ፓርቲዎች እንደአሻን እንዲፈሉ አደረገ፡፡ በተለይ በ1997 ህዝቡ ተፎካካሪ ፓርቲዎችን ከመረጠ በኃላ በብዙ ቦታዎች ምርጫ እንዲደገም አድርጎ አብዛኛውን መልሶ ወሰደ፤ በቀጣይ ምርጫ አንድ ተቃዋሚ ብቻ ፓርላማ መግባት ሲችል፤ በ2007 ደግሞ ሁሉንም ጨርሶ በመጨፍለቅ በአንድ ፓርቲ አምባገነናዊ መንግስት አቋቋመ፡፡ አምባገነንነቱንና አይምሬነቱን ከወራት በኃላ በግድያ አስመረቀ በዚህም ድመፅ ዋጋ አለው ብሎ የሚያስብ ህዝብ እንዳይኖር የመጀመሪያውን መስፈርት አፈረሰ፡፡ የመድብለ ፓርቲ ሰርዓት ያለ ገለልተኛ የፍትህ ተቋማት የሚታሰብ አይደለም፡፡ ኢህአዴግ ፍ/ቤቶች፣ ፓሊስ፣ አቃቤ ህግ፣ ማረሚያ ቤቶች በራሱ ሰው ብቻ እንዲያዝ እንዳረገ የህግ የበላይነትን ገደለ፡፡ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት በራሱ ፓሊሶች ተይዘውና ተመርምረው፣ በራሱ አቃቤ ህጎች ተከሰውና ተመስክሮባቸው፣ በራሱ ዳኞች ተፈርዶባቸው፣ በራሱ ጠባቂዎች የእስር ቤት ህይወት እንዲገፉ ይደረጋል፡፡ እንግዲህ እንዴት ነው መድብለ ፓርቲ ሰርዓት በቅሎ ሊያድግ በሚችለው? በአገሪቱ ውስጥ በሽብርተኝነት ተከሰው እስር ቤቶችን ያጣበቡት እነዚህ የዴሞክራሲ ተሟጋች የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ናቸው፡፡ በአገሪቱ ህግ መሠረት በነፃነት የመደራጀት መብት ተጽፎ ያለ ሲሆን ይህን መብቱን ለመጠቀም የቆረጠ ሰው ይዋል ይደር እንጂ መጨረሻው ቢያንስ እስር ቤት ነው፡፡ ከእስር በመለስ ያለው ፈተናም ቀላል አይደለም፡፡ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አባል መሆን በሰበብ አስባቡ ሁሉንም የዜግነት መብቶች ያስገፍፋል፡፡ ከሥራ ያስባርራል፣ ዕድገትና ሹመት ያስከለክላል፣ መኖሪያ ቤት በአንድንድ ቦታ ደግሞ ቀባሪም ያሳጣል፤ ቤተሰብ ለአደጋ ያጋልጣል፣ በአጠቃላይ ይህ ነው የማይባል ዋጋ ያስከፍላል ኢህአዴግ እንደፓርቲ የመንግስትን ሀብትና ንብረት ያለምንም ከልካይ ሲጠቀምበት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ንብረት ማፍራት አይችሉም፣ ቤት የሚያከራያቸው የለም፣ ድጋፍ ማሰባሰብ አይችሉም፣ ጽ/ቤት መክፈት አይችሉም፣ አዳራሽ ማግኘት ሚዲያ መጠቀም አይችሉም፡፡ በማንኛውም መንገድ ሲተባበራቸው የተገኘ ሰው ማረፊያውን ያውቀዋል፡፡ እንዲህ እያደረገ ነው ኢህአዴግ መራሹ መንግስት በመድብለ ፓርቲ ስርዓት አማካኝነት ዴሞክራሲን ለማስፋትና ለማጥለቅ እንቅስቃሴ እያደረግሁ ነው የሚለው፡፡ አሁንም የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትን እስር ቤት አጉሮ፣ ጽ/ቤታቸውን ዘጋግቶ፣ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሁሉንም መብታቸውን ገፎ እየታደስኩ ነው ማለት የቀልዶች ሁሉ ቀልድ ነው፡፡

ለመድብለ ፓርቲ ስርዓት መኖር የግድ መሟላት ከሚገባቸው ነገሮች አንዱና ዋነኛው የገለልተኛ ምርጫ አስፈፃሚ ተቋም መኖር ነው፡፡ በአገራችን ያለው የምርጫ አስፈፃሚ ከማዕከል ጀምሮ እስከ ምርጫ ጣቢያ ድረስ ያሉት በሙሉ የፓርቲ አባላት ናቸው፡፡ በምርጫ ጣቢያ ደረጃ አምስት አስፈፃሚዎችና አምስት የህዝብ ታዛቢዎች ገለልተኛ በሚል ስም የሚመድባቸው ኢህአዴግ ሲሆን በፓርቲው ስም አንድ ታዛቢ በመጨመር ተቃዋሚ ፓርቲ ከሚመድበው አንድ ሰው ጋር አደራ አንድ ለአንድ ይቀመጣሉ፡፡ በሁሉም ደረጃ ያለ የምርጫ አስፈፃሚ መዋቅር በዚሁ ዓይነት የተተበተበ በመሆኑ አንድ ቦታ የተዛነፈን ፍትህ የትም ማቃናት አይቻልም፡፡ ታዲያ የትኛውን የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት ምሰሶዎችን አስተካክሎ ነው መንግስት ዴሞክራሲን እያሳደኩ እያጠለቅሁነው የሚለው? ከላይ የጠቀስናቸውን ዘዴዎች በመጠቀም ሊቀናቀኑ የሚችሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን በማዳከምና በማጥፋት ጥገኛ ፓርቲዎች ከጎኑ አሰልፎ የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት ያለ በማስመሰል ድራማ ይሠራል፡፡ “ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ንግግር ጀምሬያለሁ” እያለ ቀለብተኞቹን በሰፊው ያስተዋውቃል፤ ተቃዋሚ እንዲመስሉ አንድንድ ጥያቄዎችንም አፋቸው ላይ አድርጎ ህዝቡ እንዲሰማቸው ያደርጋል፡፡ የግል ፕሬሶችንም አዳክሞ ከማጥፋት አልፎ ባህር ማዶ የሚገኙ አንድንድ የሚዲያ ተቋማት ላይም በቻይናውያን ቴክኖሎጂ እየተገዘ እንዳይደመጡ እስከማድረግ ደርሷል፡፡ በ1997 ምርጫ ዋዜማ ጥቂት የዲሞክራሲ ጭላንጭል የታየ በመሰለበት ወቅት ልዩ ልዩ ውይይቶችን በማዘጋጀት መንግስትና ተቃዋሚዎችን ለማከራከር ወሳኝ ሚና የተጫወቱ የሲቪክ ማህበራትም በአፋኝ አዋጅ ደብዛቸው እንዲጠፉ ተደርጓል፡፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ እንዴት ያለ ዴሞክራሲ ነው የሚገነባው? ባለፉት ሁለት ዓመታት ለተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ ቀዳሚ መንስኤ ነው ተብሎ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተገለፀው የሥራ አጥነት ችግር ነው፡፡ በእኛ እምነት ግን አብይ መንስኤው ህዝቡ አሮጌውን አስተሳሰብና ሥርዓት መሸከም የማይችልበት ደረጃ ላይ በመደረሱ ነው፡፡ አሮጌው አስተሳሰብ ልማታዊ መንግስት ከሚለው አንፀባራቂ ስም በስተጀርባ ያለው ሁሉን ነገር በኢህአዴግ ቁጥጥር ሥራ መሆን አለበት የሚለው አስተሳሰብ ነው፡፡ ይህ አስተሳሰብ ከኢሀአዴግ ወይም የሱ ተለጣፊዎች ውጪ ሌላ ፓርቲ እንዳይኖር፣ ከአባላቱ ውጭ ሌላ ሰው ባገሩ ሠርቶ እንዳይኖር፣ ሀብት እንዳያፈራ፣ ይህ እንዲሆን፣ በራሱ የማይተማመን፣ የኢህአዴግን ፈቃድ ጠብቆ የሚያድር ጥገኛ ሆኖ እንዲኖር የማድረግ አስተሳሰብ ነው፡፡ ይህ አስተሳሰብ ፀረ ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ ነው፡፡ ይህን ለማሳካት ለረጅም ጊዜ ሠርቷል፡፡ የትምህርት ሰርዓቱ ጥገኛና በራሱ የማይተማመን ዜጋ እንዲያፈራ አድርጓል፡፡ በአጭር ጊዜ ውስጥ ያገሪቱ ሀብት በሙሉ በጥቂት የፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች እጅ አስገብቷል፡፡ ጥገኛ ባለሀብቶችም ብዙ የሰው ኃይል ሊያሳትፉ በሚችሉ የማኑፋክቼሪንግ ኢንዱስትሪዎች ሳይሆን በጥቂት የቤተሰብ አባላት አማካኝነት ሀብት በሚዛቅባቸው የአገልግሎት ሰጪ ዘርፎች ላይ እንዲያተኩሩ በማድረግ ለሥራ አጥነት አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ ወጣቱ በተገኙት ጥቃቅን ዕድሎች እንኳን እንዳይጠቀም “የወጣት ሊግ አባላት፣ የነዋሪዎች ፎረም ድጋፍ ያስፈልጋል” በማለት በፖለቲካዊ አመለካከት አግልሎአቶዋል፡፡ ስለዚህ አብዛኛው ወጣት ጊዜያዊ ሥራ አጥነቱ ብቻ ሳይሆን ነፃነቱንም ተገፍፎ የመኖር ዘላቂ ተስፋውን ያጨለመውን ስርአት ሊታገለው ተነሳ፡፡ ሥራ አጥነቱንም ቢሆን አሁን መንግስት ሊፈታ እየሄደበት ያለው አካሄድ ጥገኛ ህብረተሰብ በመፍጠር አስተሳሰብ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ ሥራ አጥ የሚመዘግበው፣ በማህበር የሚያደራጀው፣ ገንዘብ የሚያበድረውና ገበያ ትስስር የሚፈጥረው አሁንም መንግስት ስለሆነ ከጥገኝነት መላቀቅ አይችልም፣ ዓላማውም ይኼው ነው፡፡

በአጠቃላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ መግለጫ ዋነኛ ማጠንጠኛ የሆነው መላው የኢህአዴግ ካድሬና ሚዲያ እየሰበከ ያለው በጥልቀት የመታደስ ጉዳይ በፍጹም ሊሆን የማይችልና ጊዜ ማባከኛ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡ ማሳያ ናቸው የተባሉ ድርጊቶችም ተሀድሶ ማምጣት የሚችሉ አይደሉም አዲስ የተባሉትም አዲስ አይደሉም፣ ቴክኖክራቶች አይደሉም፣ ለውጥ ለማምጣት የሚችሉም የሚፈልጉም አይደሉም፡፡ የሚመሩት በኢህአዴግ አስተሳሰብ ስለሆነ የሚታደስ ነገር የለም፡፡ አመራር አካሉን ለመቆጣጠር እየተጠናከሩ ናቸው የተባሉት የተወካዮች ም/ቤት፣ የዋና ኦዲተር፣ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን፣ የፀረ ሙስናና የእንባ ጠባቂ ተቋማት አፈጣጠራቸውና አደረጃጀታቸው በኢህአዴግ አሮጌ አስተሳሰብ የተቃኘ በመሆኑ ለጥልቅ ተሀድሶው አጋዥ ሳይሆኑ ስርዓቱን ከነአስተሳሰቡ ለማቆየት እየተፍጨረጨሩ ናቸው፡፡ ለማስፋት እየተሞከረ ነው የተባለው የዴሞክራሲ ምህዳርም ተቃዋሚዎችን በገፍ በማሰርና በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አማካኝነት ሁሉንም እንቅስቃሴ በማገድ እስከነአካቴው በመጥፋት ላይ ያለ መሆኑ እየታየ ነው፡፡ ለወጣቶች እየተፈጠረ ነው የሚባለው የሥራ ዕድል አሁንም ወገንተኛና አድልኦአዊ ከመሆን አልፎ ለተማረ ወጣት ሳቢ አይደለም፡፡ ሰርዓቱ አሁን በተያዘው መንገድ ሊታደስ የሚችልም የሚገባውም አይደለም፡፡ አንድ ነገር እንዲታደስ የሚፈለገው 1ኛ አገልግሎት ሊሰጥ የሚችለው አካሉ አገልግሎት ሊሰጥ ከማይችለው አካሉ በልጦ ሲገኝ 2ኛ የሚያስወጣው ወጪ አነስተኛ ሲሆን 3ኛ አዲሱን ማግኘት ያልተቻለ ከሆነ ነው፡፡ የዚህን መንግስት አካላት ብንፈትሽ አገልግሎት ሊሰጥ የሚችል አንድም አካል የለውም፡፡ ሁሉም የሚኒስቴር መ/ቤቶችና አደረጃጀቶቹ ከላይ እስከታች ያረጁ በመሆናቸው ለማደስ የሚፈጀው ጊዜና ሀብት እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡ አንድ ነገር ዘላለም ስታደስ አይኖርም፤ አገልግሎቱን ፈጽሞ ጨርሶ መታደስ የማይችልበት ደረጃ ይደርሳል፡፡ ከመወለድ፣ ከመጎልመስና ከመሞት ዲያሌክቲካዊ ህግ ውጪ መሆን የሚቻለው የለም፡፡ አገሪቷ ዘራፊ፣ ጉበኛ፣ ሙሰኛን በጥልቅ ተሀድሶ ስም ሥልጣን ላይ ትታ እሱን በዓይነቁራኛ ስትጠብቅ፣ ስትገመግም ዘመናት ልትቆጥር አትችልም፡፡ አሮጌ በአዲስ መተካት ግድ ነው፤ አገሪቱ አዲስ ሰርዓት አስፈልጓታል፡፡ መብት፣ ነፃነት፣ ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል፣ የመድብለ ፓርቲ ስርዓት፣ ዴሞክራሲ የሚሉ አስተሳሰቦች እንደ አዲስ ሀሳብ ሳይሆን አዲስ ህልውና ሊያገኙ ገፍተው እየመጡ ነው፡፡ እነዚህን አስተሳሰቦች ሲጋፉና ሲያቀጭጫቸው የኖረው የአብዮታዊ ዴሞክራሲ፣ የልማታዊ መንግስትና የአውራ ፓርቲ አስተሳሰቦች ቦታ መልቀቅ አለባቸው፣ ምክንያቱም በአሮጌ አቁማዳ አዲስ የወይን ጠጅ አይጨመር፡፡
ግንቦት 2009

Tuesday, June 27, 2017

አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ እና አቶ ሸፈራው ሽጉጤ በዘረጉት የሙስና ሰንሰለት ከፍተኛ ገንዘብ እየመዘበሩ መሆኑን መረጃዎች አመለከቱ


 

By ሳተናውJune 27, 2017 19:48 Updated
 0  471  472
አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ እና አቶ ሸፈራው ሽጉጤ
ሰኔ ፳ ( ሃያ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የቀድሞው የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት፣ የትምህርት ሚኒስትሩ ሸፈራው ሽጉጤ በዘረጉት ከፍተኛ የዝርፊያ ሰንሰለት በብዙ መቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ መዝረፋቸውን ከአስተማማኝ ምንጮች የተገኘው መረጃ አመልክቷል። የምንጮቻችንን ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል፣ ምረመራውን ያካሄደውን የኦዲት ክፍል ለመግለጽ ባንችልም፣ መርምራውን የካሂዶት ኦዲተሮች ግማሾቹ ማስፈራሪያ ደርሶአቸው ስራቸውን ለቀዋል።
አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከደቡብ ክልሉ ወንዶ ኢንዶውመንት ኩባንያዎች በየቀኑ ከ50 ሺ ብር በላይ ገንዘብ ይቀበላሉ። ወንዶ ድርጅት ከደቡብ ክልል ወደ አዲስ አበባ የሚሄደውን ጫት ቀረጥ እንዲሰበስብ ስልጣን የተሰጠው ሲሆን፣ በየኬላዎቹ ጫት ጭነው ከሚመጡ መኪኖች በኪሎ ግራም ለቀረጥ ለኮቴና ለተለያዩ ወጪዎች በሚል 11 ብር ይቀበላል። አንድ መኪና በአማካኝ እስከ 5 ሺ ኪሎ ግራም ጫት የሚጭን በመሆኑ፣ በመኪና እስከ 55 ሺ ብር ከፍያ ይፈጸማል።
ወንዶ ድርጅት ለመንግስት የሚያስገባው በቀን 60 ሺ ብር ሲሆን ይህም ከአንድ መኪና ጫት ከሚገኘው ገቢ ጋር ተመጣጣኝ ነው። በእየቀኑ እስከ 20 መኪና ጫት የሚቀረጽ ሲሆን፣ በቀን እስከ 1 ሚሊዮን 100 ሺ ብር ይሰበሰባል።
አዲተሮች በ2005 ዓም ባደረጉት ምርመራ ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ለመንግስት ገቢ አለመሆኑን ያረጋገጡ ሲሆን፣ ኦዲተሮቹ መቀሌ ለስልጠና ትፍለጋላችሁ ተብለው ከተጠሩ በሁዋላ ፣ በስፍራው በተገኙት የደህዴን ባለስልጣናት ከፍተኛ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል። የኦዲተሮች ሪፖርትም ይፋ እንዳይደረግ ተደርጓል። ከ2005 ዓም በሁዋላ ወንዶ ከጫት የሚሰበስበው ገንዘብ በቀን 110 ሺ ብር የደረሰ ሲሆን፣ ለእነ አቶ ሽፈራው የሚተላለፈውም ገንዘብ በዛው ልክ ከፍ ብሎአል። ስራውን የሰሩት ኦዲተሮች ከማስጠንቀቂያው በሁዋላ ስራቸውን በመልቀቃቸው ከ2005 ዓም ወዲህ ያለውን የገንዘብ መጠን ለማወቅ አይቻልም።
ኦዲተሮች ከአዋሳ ይልቅ መቀሌ ለምን እንደተጠሩ እስካሁን ባያውቁም፣ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውሩ ከደቡብ እስከ ትግራይ የተዘረጋ መሆኑን እንዳመላከታቸው ያምናሉ። አቶ ሽፈራው በራሳቸውና በዘመዶቻቸው በኩል የያዙዋቸው የንግድ ድርጅቶች ከፍተኛ ሲሆኑ፣ ከህወሃት ባለስልጣናት ጋር በፈጠሩት ከፍተኛ የጥቅም ቁርኝት አንድም ቀን ጥያቄ ቀርቦባቸው አያውቅም።
ሌላው የደቡብ ክልልን ሲመሩ የነበሩት ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝና ቤተሰቦቹ በታናሽ እህታቸው የተሰየመ ቤትሄሌም ሶሊዳሪቲ የሚባል የጤና ሙያተኞች ማሰልጠኛ ተቋም የመሰረቱ ሲሆን፣ ሃዋሳ የሚገኘው የኢትዮጵያ ጉምሩክ ባለስልጣን ኦዲት ባደረገበት ወቅት፣ 24 ሚሊዮን ብር ገንዘብ ተገኝቶበታል። የኦዲት ምርመራው ሃዋሳ በሚገኘው የጉምሩክ ሃላፊ ትእዛዝ ይፋ እንዳይሆን የተደረገ ሲሆን፣ ምርመራውን ያካሄዱት 3 ሰራተኞች ከስራ ተባረዋል።
በክልሉ የሚፈጸመው ሙስና ከፍተኛ ደረጃ መድረሱን የሚገልጹት ምንጮች፣ በተለይ በመሬት ሽያጭ ባለስልጣናቱ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ እየመዘበሩ ነው። ከላይ እስከታች ያሉ የክልሉ ባለስልጣናት የሙስና ሰንሰለት በመዘርጋታቸው አንዱ ሌላውን ለመጠየቅ አቅም እንደሌለው የመረጃው ምንጮች ገልጸዋል።

ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በየትኛውም የኢትዮጵያ ምድር ላይ ልዩ ጥቅም አለው! የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ የሕወሓት ሀገር ከፋፋይ ቀጣይ አጀንዳ አካል ነው


       




ጉዳያችን / Gudayacnhn
ሰኔ 21/2009 ዓም (ጁን 28፣2017)
++++++++++++++++++++
ዛሬ ሰኔ 20፣2009 ዓም የሕወሓት ሚኒስትሮች ምክር ቤት የኦሮምያ ክልል በአዲስ አበባ ላይ የሚኖራት ጥቅም በሚል ርዕስ ውሳኔ ማሳለፉ እና የሕወሓት ኢህአዴግ  99% አሸነፍኩ ወዳለበት ምክር ቤት እንደሚመራ ተነግሯል። ጉዳዩ ልዩ መብት የሰጠ የመሰለው ካለ እርሱ ከ26 አመታት በኃላም ገና ፖለቲካ ሀ ሁ እያለ እንደሆነ መረዳት ያለበት ይመስለኛል።
file photo
1/ ልዩ ጥቅም የሁሉም ኢትዮጵያዊ መብት አይደለም እንዴ?
 
ልዩ ጥቅም የሚለው አባባል በእራሱ የመከፋፈል አላማ ያነገበ አባባል ነው።አንድ ሰው ልዩ ጥቅም ለማግኘት ዋናው መሰረት ሊሆን የሚገባው በኢትዮጵያዊነቱ ነው እንጂ የታሪክ የበላይነት ወይንም የዘር መሰረቱ ወይንም የተለየ አነጋገር በመናገሩን መሰረት አድርጎ የሚሰጥ ከሆነ መከፋፈል ነው።ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በየትኛውም የኢትዮጵያ ምድር ላይ ልዩ ጥቅም ሊኖረው ይገባል። ልዩ የሚያደርገው ደግሞ ከኢትዮጵያ ምድር በመውጣቱ ነው።ከጃፓን ወይንም ብራዚል የመጣ ሰው የማይኖረው ልዩ ጥቅም ኢትዮጵያዊ ሊኖረው ይገባል።ይህ ማለት ኦሮሞው አዲስ አበባ ላይ በኢትዮጵያዊነቱ ልዩ ጥቅም እንደሚኖረው ሁሉ አዲስ አበቤውም በኦሮምያ ላይ ልዩ ጥቅም አለው።ኦሮሞው በመቀሌ ላይ ልዩ ጥቅም እንደሚኖረው ሁሉ የአክሱሙም ሰው በኦሮምያ ላይ ልዩ ጥቅም አለው።የወለጋው ገበሬ በጎንደር ላይ ልዩ ጥቅም እንዳለው የራስ ዳሽን ገበሬም በነቀምት ላይ ልዩ ጥቅም አለው።ይህ ሁሉ ልዩ ጥቅም የሚመነጨው እንደ ህወሓት የሚኒስትሮች ምክር ቤት በከፋፋይ አጀንዳ ላይ የተመሰረተ ሳይሆን በኢትዮጵያዊነት ሙሉ መብት ሁሉም የኢትዮጵያ ዜጋ እና መሬት በሁሉም የኢትዮጵያ መሬት ላይ ልዩ ጥቅም አለው።የኦሮምያ ልዩ ጥቅም በአዲስ አበባ የሚለው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ  በእራሱ ከፋፋይ የሆነው  የስርዓቱ አጀንዳ ቀጣይ ምዕራፍ ነው።
2/ የውሃ ፍሳሽ አገልግሎት ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚሰጥ አገልግሎት አይደለም እንዴ?
 “የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት በአዲስ አበባ ዙርያ ላሉ የኦሮምያ ክልሎች ያካተተ ይሆናል” ይላል ከአዋጁ አካል ውስጥ አንዱ።አሁንም ውሃ የማግኘት ልዩ መብት የሁሉም ኢትዮጵያዊ መብት ነው።ይህ አዋጅ ባይወጣ ኖሮ በኢትዮጵያዊነቱ በአዲስ አበባ ዙርያ ያሉ የኦሮምያ ክልሎች የውኃ አገልግሎት ላያገኙ ነበር? የውኃ ፍሳሽ አገልግሎት ለማግኘት የልዩ ጥቅም አዋጅ ባይወጣ ኖሮ በኢትዮጵያውነታቸው የማግኘት መብት የላቸውም ነበር? ይህ በእራሱ ከፋፋይ አቀራረብ ነው።በአዲስ አበባ ዙርያ ያለ የኦሮሞ ሕዝብ ውሃ ለማግኘት ልዩ አዋጅ መጠበቅ ነው ያለበት ወይንስ በኢትዮጵያዊነቱ የሚያገኘው መብት ነው መሆን ያለበት? ለአዲስ አበባ ውሃ ፍሳሽ አገልግሎት ወጪ የሚሸፈነው  ቀረጥ  ከኦሮምያ የሚመጣ ገንዘብም ጭምር መሆኑን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሊያረሳሳን ነው ? እናስ የአዲስ አበባ ዙርያ የኦሮሞ ማኅበረሰብ ገና ለገና ከአዲስ አበባ ሕዝብ ጋር አብሮ ይነሳብኛል ልከፋፍለው በሚል እሳቤ ውሃ በልዩ ጥቅም አዋጅ መሰረት ይዘረጋልሃል የሚል አዋጅ ረቂቅ አንድ ሐሙስ የቀረው እና የታመመ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ካልሆነ ማን ያወጣዋል?
3/ የጤና አገልግሎትስ የሁሉም ኢትዮጵያዊ መብት አይደለም እንዴ?
 
በአዋጁ ረቂቅ ላይ “አዲስ አበባ ወይም ፊንፊኔ የኦሮሚያ ክልል ዋና ከተማ በመሆኗ በከተማዋ የሚሰጠው የጤና አገልግሎት በከተማዋ ዙሪያ ያሉ የክልሉ ተወላጆችን ታሳቢ ያደረገ ይሆናል” ይላል። የጤና አገልግሎት የኢትዮጵያዊነት ልዩ ጥቅም ነው።ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍልል ቢኖር የጤና አገልግሎት የማግኘት መብቱ ነው።በእዚህ ረቂቅ ላይ አዲስ አበባ እና ኦሮምያ የተለያዩ ሀገሮች ይመስል በአዲስ አበባ የሚሰጠው የጤና አገልግሎት በከተማዋ ዙርያ ያሉ የክልሉ ተወላጆች ታሳቢ ያደርጋል ሲል ዛሬ ተነስቶ ልዩ ጥቅም የሰጠ አስመስሎ ሕዝብ የመከፋፈል አላማ ለማሳካት ብቻ የተገለፀ ነው።
4/ የአዲስ አበባ ሕዝብ እና የኦሮምያን ሕዝብ ከህወሓት በበለጠ ይተዋወቃል 
በእዚህ ረቂቅ አዋጅ ላይ የአዲስ አበባ ስም በፊንፊኔ፣የከተማዋ አንዳንድ ቦታዎች እና አደባባዮች በኦሮምያ ታሪክ ይቀየራሉ የሚል ሃሳብ የያዙ አረፍተ ነገሮች እንዲሁም ኦሮምኛ ከአማርኛ ጋር የስራ መጠቀምያ ይሆናል ይላል።ኦሮምኛ የስራ መጠቀምያ መሆኑ አማርኛ እስካልገባው ድረስ ኦሮምያ የተወለደ ኢትዮጵያዊ በኦሮምኛ አገልግሎት ማግኘቱ ሙሉ መብቱ ነው።ዛሬ ህወሓት እንደ ልዩ ጥቅም አድርጎ ማቅረቡ ነው የማይመቸው። ይህ እንዴት ልዩ ሆኖ ይቀርባል? ኢትዮጵያዊ መብቱ በሚለው ስር የሚገባ ነው።አንድ የጋምቤላ ተወላጅ አዲስ አበባ መጥቶ አማርኛ ካልገባው በጋምቤላ አነጋገር አገልግሎት የማግኘት መብቱ ኢትዮጵያዊነቱ ያጎናፀፈው መብት ነው እንጂ ልዩ መብት ሊባል ያችልም። ሕወሓት ለመከፋፈል ስትፈልግ ልዩ መብት ብላ ትርክት መጀመሯ አስቂኝ ነው። የአዲስ አበባ ስያሜ መቀየር እና የከተማዋን ታሪካዊ ቦታ ከመቀየር አንፃር የተነሳው አገላለጥ በእራሱ የተደናበሩ ሰዎች ያወጡት ረቂቅ አዋጅ ነው። በመጀመርያ ደረጃ በአዲስ አበባ ውስጥ የተሰጡት ስሞችም ሆኑ የአዲስ አበባ የእራሷ ስያሜ እውን ታሪካዊ አመጣጥ የሌለው ባዶ ትርክት ከነበረ የታሪክ ሰዎች ይንገሩን እና እንመን።በሐሰት ታሪክ ግን የትም ሀገር ስም አይቀየርም። ይህንን ልሞክር የሚል ካለ የመስቀል አደባባይ እና የአብዮት አደባባይ ስያሜን ማስታወስ ነው።በሕልም እና በስሜት ሕዝብ ያጋጭልኛል ከሚል እሳቤ ብቻ ሕወሓት ይህንን ማሰቧን እራሱ የኦሮሞ ሕዝብ እና የአዲስ አበባ ነዋሪ ጠንቅቆ ይረዳል።
ባጠቃላይ ልዩ ጥቅም በሚል ቡልኮ የተሸፈነው የህወሓት ሚኒስትሮች ምክር ቤት ረቂቅ አዋጅ አዲስ አበባ እና ኦሮምያን የተለያዩ ሀገር በማስመስል የአዲስ አበባ እና ዙርያዋን ያሉት የኦሮምኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን ግንኙነት ኢትዮጵያዊ የሆነ የጋራ እሴት ሳይሆን የጥቅም ግንኙነት ብቻ ያላቸው  አስመስሎ የማቅረብ ሙከራ ነው።መንግስት የተባለ አካል የመጀመርያ ስራው ዜጎቹን በእኩልነት የማስተዳደር፣ሕግ የማውጣት እና የማስፈፀም አቅሙን የማስመስከር  መሆን ይገባው ነበር።ከእዚህ ውጭ አንዱን አስነስቶ በእዚህ አካባቢ ልዩ ጥቅም አለህ።አንተኛው ግን በምትኖርበት ከተማ ከእርሱ ያነሰ ጥቅም ነው የምታገኘው የሚሉ አባባሎች በእራሳቸው ህዝብን ለመከፋፈል የሚደረጉ አጀንዳዎች የማስቀጠል ሥራ አካል ካልሆኑ ሌላ ሊሆኑ አይችሉም። አዲስ አበባ እና ኦሮምኛ ተናጋሪውን ኢትዮጵያዊ ለመከፋፈል አትሞክሩ።ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በየትኛውም የኢትዮጵያ ምድር ላይ ልዩ ጥቅም ሊኖረው ይገባል። ሕዝብ የምታገለውም ሁሉም ኢትዮጵያዊ በኢትዮጵያዊነቱ እኩል ልዩ ጥቅም እንዲኖረው ነው።
ይህንን ፅሁፍ የምደመድመው አንድ የኦሮሞ ማኅበረሰብ አክቲቪስት በተናገረው ንግግር ነው። አባበሉ አሁን ሕወሓት እየዳከረበት ካለው የመከፋፈል ከንቱ ሥራ ፍሬ እንደሌለው በሚገባ ያሳየ ነው። አክትቪስቱ ያለው እንዲህ ነበር
“ሕወሓት የኦሮሞ ማሕበረሰብ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ወገኑ ጋር ያለውን ማኅበራዊ፣ፖለቲካዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ትስስር በመቶዎች በሚቆጠሩ  ዓመታት ውስጥ ያለፈ እና ጠንካራ የደም ትስስር መሆኑን ህወሓት በደንብ ያወቀው አይመስለኝም።እነርሱ ራቅ ካለ አካባቢ ስለመጡ የእዚህ አይነቱ ጠንካራ ግንኙነት ታሪክ በደንብ የገባቸው አልመሰለኝም።የኦሮሞ ሕብረተስብ አሁን ሕወሓት እለያይበታለሁ እያለ የሚያቀርባቸው አጀንዳዎችን የመለያያ አጀንዳዎች እንደማይሆኑ ጥንት በሰራቸው ስርዓቶች ካፈረሳቸው ቆይቷል።ሕወሓት ትልቅ የመረጃ ክፍተት ላይ እንዳለ መረዳት አለብን” ነበር ያለው።

Friday, June 23, 2017

የ34 ኢትዮጵያውያን ጉዳይ በኬንያ – ጥላየ ታረቀኝ


By ሳተናውJune 23, 2017 03:17



የ34 ኢትዮጵያውያን ጉዳይ በኬንያ – በሀገራችን ኢትዮጵያ ህገ-ወጥ የሰዋች ዝውውር ከፍተኛ የሆነ ጉዳት እያመጣና እያደረሰ መሆኑን ንፁሀንንና በእድሜ ያልጠነከሩ ለጋ ወጣቶችን እያረገፈ መሆኑን ለኢትዮጵያንና በዚህ ማህበራዊ ድህረ ገፅ ላይ ላላችሁ ወገኖቼ መንገር ለቀባሪ ማርዳት ይሆንብኛል ለምሳሌ በሊቢያ በግብፅ ሲና በርሃ በሜዲትራኒያ ባህር እንደጉድ የሚረግፉ ወገኖቻችን ቁጥር ቤት ይቁጠረው ይሄ ህገወጥ የሰዋች ዝውውር ጉዳዩ ያላንኳኳው ቤት የለምና ሁሉንም አንገት ያስደፋ ጉዳይ ነው።
ከኢትዮጵያ ደቡብ ክልል በዚህ ባሳለፍነው ሳምንት 34 ኢትዮጵያውያን በሞያሌ በኩል በማድረግ በህገወጥ የሰዋች አዝዋዋሪ ወይም ሰው በቁሙ በሚሸጡ የሰው ነጋዴዋች አማካኝነን ኬንያ ይገባሉነገሩን ከመነሻው ከሀገራቸው ኬንያ መግቢያ ቦርደር ጀምሮ ሲከታተል የነበረው የኬንያ ፓሊስ እነዚህን ወጣቶች ከናይሮቢ ወጣ ብሎ tika towen ተብላ በምትጠራ ትንሽ ከተማ ውስጥ በህገወጥ የሰዋች ዝውውር ላይ ተሳታፊ በሆኑ ሰው ሻጭ የእፍኚት ልጆች አማካይነት በተከራዬት ቤት ውስጥ እነዚህን ወጣቶችና በእድሜ አነስተኛ የሆኑ ለጋ ታዳጊዋች በአንድ ክፍል በማጎር ለተወሰነ ቀን ከዚህ ቀደም እንደሚያረጉት እንደልማዳቸው ወጣቶችን አፍነው በማቆየት ወደ ደቡብ አፊሪካ ለመላክ የተያዘው እቅድ ግን አልተሳካም
በአካባቢው ሰዋች ጥቆማና በኬንያ ፓሊሶች ክትትል እነዚህ ምንም የማያውቁ ነገ የተሻለ ኑሮ ትኖራላችሁ በሚል ስብከትና አጉል ተስፋ ተታለው ከፍተኛ ክፍያ በመክፈል ወደ ደቡብ አፊሪካ ለመሄድ የታቀደው እቅድ ሳይሳካ በኬንያ ፓሊስ እጅ ይወድቃሉ ሁኔታው በጥሞና ሲከታተል የነበረው የኬንያ ፓሊስ እነዚህ 34 ኢትዮጵያ በመያዝ እዛው ትንሽ ከተማ ውስጥ በሚገኘው juja police divisonal head quarters በሚባል ፓሊስ ጣቢያ ውስጥ ያስራቸዋል በተያዙ በማግስቱ እዛው ትንሽ ከተማ ፍርድ ቤት በመቀርብ ሰው ሀገር ላይ በህገወጥ መልኩ በመግባታቸውና ማንነታቸውን የሚገልፅ ምንም አይነት ማስረጃ ወረቀት እጃቸው ላይ አለመኖሩን ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን በማጣራት 27 ላይ የአራት ወር እስርና እስራቸውን ሲጨርሱ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱና ይወስናል ቀሪዋቹ ሰባት ወጣቶች እድሚያቸው ለፍርድ ያልደረሰ በመሆኑ በአስቸኮይ ወደ ኢትዮጵያ ይመለሱ የሚል ፍርድ በመፍረድ ፍርድ ቤቱ አማካኝነት ውሳኔው ይተላለፋል
ይሄ ፍርድ ቤት እነዚህ ኢትዮጵያውያን በቀረቡ በአንደኛው ቀን 27ቱ ወደ ከርቸሌ እንዲጎዙ ሲያረግ ሰባቱ ደግሞ እዛው ፓሊስ ጣቢያ ቆይተው ወደ ኢትዮጵያ ዲፖርት ወይም ይመለሱ ዘንድ ወስኖል ። እኔ ግን ወጣቶችን በዛች ጠባብ ክፍል በአካል አግኝቼ ሳዋራቸው በህገ-ወጥ ደላሎች ተታለው ከሀገራቸው ደቡብ ክልል ተነስተው ወደ ደቡብ አፊሪካ ለመሄድ ማሰባቸውንና አሁን ግን ሁሉም ነገር እንደጨለመባቸው ሲያጫውቱኝ እኔም እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ አይዞቹህ ከማለት ውጪና በእጄ የያዝኮትን ከወገን በመጠየቅ የእለት ውሃና ምግባቸውን በመግዛት ከዚህ ውጪ ሌላ ማድረግ እንደማልችል በማስረዳት ተሰነባብቼ መውጣቴን እናም በሁለተኛ ቀን አሻራ ሰጥተው ወደ ሀገራቸው ሊገቡ መሆናቸውን ሲነግሩኝ እጅግ ደስታዬ ብዙ ሆኖ ተመለስኩኝ የሚገርመው ግን እኔ ለማጣራት አስቤ እዛው ከተጠቂዋቹ ጋር በአካል ተገኝቼ የጠየኮቸው ጥያቄዋች አለ ወጣቶች ማን ሊረዳችሁ መጥቶ ነበር ብዬ ነበር በመጀመሪያ የወጣቶችም መልስ ማንም መጥቶ ጠይቆን አያውቅም ነው !!! #
የዋህ_ነህ_ወይ_አትበሉኝና ~~~ በዚህ ናይሮቢ ኬንያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤንባሲ ተብየው በዚሁ ናይሮቢ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ተብሎ EBS ላይ ኬክ ሲቆርሱ የነበሩ ግለሰቦች ወይም ልክ እንደ ዜጋ በናይሮቢ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሀይማኖት መድሀኔአለም ቤተክርስቲያን እንዲህ ስደተኛ ወገን ዜጎች ሲንገላቱ የሰው ልጅ እንደከብት ሲሸጥ ሌሎችም የሀይማኖት ተቆማት ድምፅ ሳያሰሙ ዝም ማለት ወይም ዝምታው እስከመቼ ነው ወገን እያለቀ: በተረፈ ግን @~~ ይህ ሁሉ ወገን ሲሰቃይ ሲንገላታ ሲጉላላ እንደሸቀጥ ሲሸጥ በቃ ልንል ይገባል ወገን በተቸገረና በተጨነቀ ሰአት ከጎን መቆም ካልቻለ ምኑን ነው ኢትዮጵያውያንን የሚወክለው ጠንከር አርጌ እነዚህ ኢትዮጵያውያንን እንወክላለን የሚሉ አካላትን መጠየቅ የምሻው እውን ይሄን ዜና አልሰሙ ይሆን ? ወይስ በዚህ የሰዋች ንግድ ላይ እጃቸው አለበት የሚለውን ጥያቄ ይመልሱልኝ ዘንድ ነው ? በዚህም የወገን ጉዳይ ላይ አይናቸውን ሳያሹ ዜናውን ሰምተው ድንገት ተርበው ይሆናል በማለት አቅማቸው የፈቀደውን ያደረጉ ትልቅ ምስጋና የሚገባቸው ሁለት ቅን ኢትዮጵያን habtamu tadege እና gelila legesse የተባሉ ድንቅ ኢትዮጵያውያን ለእነዚህ ወገኖች ምስጋና አቀርባለሁ ለአራት ቀን የሚሆን ምግባቸውንና ውሃ ገዝተው እንዲበሉ አድርገዋል ኢትዮጵያዊ ወገንተኝነታቸውን በተግባር አሳይተዋል እናም የኢትዮጵያ አምላክ ውለታችሁን ይመልሳላችሁ ከማለት ውጪ ሌላም የለኝ ። #ግን_እስከመቼ ??? #ኢትዮጵያ_ለዘላለም_በክብር_ትኑር

ጣራው ለሚያፈስ ቤት -የወለል እድሳት፣ – ይገረም አለሙ

By ሳተናውJune 23, 2017 01:56


መላ አከላቷን ዝንጀሮ እሾህ ወግቷት
መቆም መራድ መቀመጥ ተስኖአት
የትኛውን እንንቀልልሽ ብለው ቢጠይቋት፣
ብታስቀድሙልኝ የመቀመጫየን
እኔ እነቅለዋለሁ ቁጭ ብዬ ሌላውን ፣
በማለት መለሰች
ቅድሚያ የሚሰጠውን ነገር ስላወቀች ፡፡
ጣሪያው በሚያፈስ ቤት ውስት እየኖሩ ክረምት በመጣ ቁጥር እየተሰቃዩ በጋ  ሲሆን የወቅት መለዋወጥ የተፈጥሮ ባህርይ መሆኑ ተዘንግቶ ነገር አለሙን በመርሳት ወለሉን ቢያድሱት ግድግዳውን ቀለም ቢያብሱት አይቀሬ ነውና ክረምት ሲመጣ የሚሆነውን አስቡት፤ከንቱ ልፋት አጉል ብክነት፡፡
የቤቱ ወለል እድሳት ቢሻ፣ ግድግዳው ቀለም ቢያምረው፣ ጣራው ደህና እስከሆነ ድረስ መኖር አይከለክልምና ቅድሚያ መቀመጫየን እንዳለችው ዝንጀሮ መቀመጫን አስተካክሎ ሌላ ሌላውን በሂደት ቀን ሲፈቅድ አቅም ሲጎለብት ማደስ ይቻላል፡፡ ጣሪያው የሚያፈስ ቤት ውስጥ እየኖሩ ክረምቱ አልፏል ብሎ ወለል ማደስ ቅድግዳ ቀለም መቀባት ግን አንድም ሞኝነት ሁለትም አጭበርባሪነት ነው፡፡እንዲያም ሲል ከዛሬ ያለፈ አለማሰብ ይሆናል፡፡በአን ጎራ ካለነው እኛ ከምንባለው እነማን ከየትኛው ጎራ እንደሆኑ  እናንተው አስቡት፡፡
ሀገራችን ቤታችን ናት፤ ጣራዋ በብልሽትም በእርጅናም ተበለሻሽቶ በበጋ ለጸሀይ ሀሩር፣ በክረምት ለዝናም ዶፍ ብንዳረግም  ለምደን ተላማምደነው  እንኖራለን፡፡ገዢዎቻንም የእኛ ቻይነት፣ የፈረንጆቹም ጩኸት እንዴትነት ገብቷቸው ወለሉን እያደሱ፣ ግድገዳውን ቀለም እየቀባቡ  ለአላፊ አግዳሚውም ሆነ ለደርሶ ሀጅ ጎብኝው ችግሩ አንዳይታወቅ አንደውም ያማረ የሰመረ መስሎ አንዲታይ በማድረግና መኖሩን ችለውበታል፡፡ ያማረው ቤታችን ሞንዳላው ኑሮአችን እያሉ በሚያሰሙት ፕሮፓጋንዳም እኛን እያደነቆሩም አቀጣጫ እያሳቱም ከፈረንጆቹ ጋር እየተሞዳሞዱ ረብጣው ሳይነጥፍባቸው፣ ዲፕሎማሲያዊው ድጋፍ ሳይቋረጥባቸው፣ሲገድሉና ሲያስሩ የሚሰማው ተቃውሞም ከቃል ወደ ተግባር ሳይሸጋገርባቸው ሀያ ስድስት ዓመት እንደዋዛ ገዙን፡፡ ሁሉንም ነገር አይተው ገምተው ጠብ- መንጅቸውንም ተማምነው ገና አርባ አመት አንገዛችኋለን እያሉ ነው፡፡ ይበሉ! የታገሉት ለምንና ለማን ሆነና፡፡ ጥያቄው እኛ የምንባለው ከተቃውሞው ጎራ ያለነው ብዙ እኛዎች ያለፈውን የሰሩትን እያየን የወደፊት ምኞት ዝግጅታቸውን እየሰማን ምን አልን ምንስ አደረግን ነው ? ብዙዎቻችን ካለንበት ነቅነቅ ያላልነው  ከመማረር ወደ ማምረር ተሸጋግረን  ራሳችንን ከሰቀልንበት ከፍታ አውርደን ከመጯጫህ ወጥተን  አገዛዝ በቃን በማለት  የምንችለውን ጠጠርም ቢሆን ለማስቀመጥ ዝግጁ ነን ወይ? ነው ጥያቄው ይህ ካልሆነ ወያኔ ከምኞት ፍላጎቱም በላ ይገዛናል፡፡ አንደ አያያዛችን ከሆነ ብዙዎቻችን በአፋችን እንጮሀለን እንጂ በወያኔ የተፈጸመው ነገር ሁሉ ውስጣችን ዘልቆ አልተሰማንም ለዚህም ነው ከመማር ወደ ማምረር መሸጋገር ያልቻልነው፡፡ ይህ ባይሆንማ ኖሮ ወቅት እየጠበቀ ወያኔ በሚሰጠን መጫወቻ ከአንልፋችን እየባነንን በምናሰማው ውግዘት ጩኸት  ጣሪያው ለሚያፈስ ቤት የወለል እድሳት የምንጠይቅ ባልሆነ ነበር፡፡ በእኔ እምነት ጣራው ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ነው፡ እንደ አብርሀም ሊንከን አባባል የህዝብ፣ በህዝብ፣  ለህዝብ፣  የሆነ መንግሥት ፡፡ ስለሆነም ይህ በሌለበት/በተነፈግንበት/ ሀገራችን  ሌሎች የህግም በሉት የሰብአዊ መብት፣ የቋንቋም በሉት የሀይማኖት ጥያቄዎችን ማንሳት  ታሰርን ተሰደድን ተገደልን እያሉ መጮህ ከሂደቱ ለማትረፍ እንጂ ከግቡ ለመድረስ የማንታገል ያስመስላል፡፡
ዴሞክራሲ ቅንጦት ተደርጎ በሚታይበት አገዛዝ ውስጥ እየኖሩ ስለ ቋንቋ፣ስለ ሀይማኖት፣ስለ ብሄር ብሄረሰብ፤ስለ ህግ በላይነት፣ስለ ሰብአዊ መብት መከበር ስለ ነጻ ምርጫ ወዘተ ማሰብ፣  መጠየቅ፣ መጮህ ጣራው በሚያፈስ ቤት እየኖሩ ወለል ለመቀየር ግድግዳ ለማደስ የመንደፋደፍ ያህል ነው፡፡ እነዚህ ጥያቄዎች ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እውን ሲሆን ምላሽ የሚያገኙ ናቸው፡ ብቻ ሳይሆን ያለ እነዚህ ተግባራዊነት ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ሊኖር ስለማይችል ወያኔ በሥልጣን ለመቆየት ጠመንጃውን እንደሚተማመን ሁሉ በዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ውስጥ ለሥልጣን የሚበቃ ግለሰብም ይሁን ፓርቲ እነዚህን ነገሮች ማክበርና ማስከበር የህልውናው ጉዳይ ይሆናል፡፡ ስለሆነም ከፈረሱ ጋሪው የሆነውን መያዣ መጨበጫ ያጣውን ነገራችንን በማስወገድ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን እውን ማድረግ በሚያስችለው መንገድ አንደየአቅማችን እንራመድ፡፡ለዚህ ደግሞ ቀዳሚው ነገር ራስን መለወጥ ነው ፡፡ እዚህ ላይ አንድ ዘመን ተሸጋሪ አባባል ብጠቅስ ማለት የፈለኩትን ይበልጥ የሚያሳይልኝ መሰለኝና እነሆ!
የአሜሪካፕሬዝዳንት የነበሩት አብርሀም ሊንከን ለኮንግረስ ያስተላለፉት ሁለተኛው መልዕክታቸው ተብሎ በሚጠቀሰው ንግግራቸው «አንድ ትውልድ ያልፍና ሌላ ትወልድ ይተካል፣ ዓለም/መሬት ግን ለዘለአለም ትኖራለች፡፡ ጸጥ ረጭ ያለው ያለፈው ግዜ ፍልሰፍናዎች (ዶግማስ) አውሎ ነፋሳዊ ለሆነው ለዛሬው ችግር ለመፍትሄነት አይመጥኑም፡፡ ጊዜያችን ችግር ያዘለ ስለሆነ በአዲስ ሁኔታ ማሰብና በአዲስ ሁኔታም መንቀሳቀስ አለብን፡፡ ራሳችንን ከሰቀልንበት ከፍታ ማውረድ ይገባል፡፡ ያን ግዜ አገራችንን ለማዳን እንችላለን፡፡ ታሪክን ልናመልጥ አንችልም፣ልንሸሸው አይሆንልንም፣ ክፉም ሰራን ደግ እንዘከራለን፣ (እንታወሳለን) ግለሰባዊ መታወቅ ወይም አለመታወቅ አንዳችንንም ሆነ ሁላችንን አያተርፈንም፣የምናልፍበት እሳታዊ ፈተና (ፍርድ) በክብር ወይንም በውርደት ማለፋችንን ይመሰክራል»
ብዙዎች እኛ ፤ እነርሱ ወያኔዎች ምንም በሉዋቸው ምን ባነገቡት ዓላማ ሊደርሱበት በሚያስቡት ግብ አንድ ናቸው፡፡ በዚህ ጉዳይ አይደለም ሰው ነፋስ አያስገቡም፡፡እንዲህም በመሆናቸው ነው ታግለው ያሸነፉት፣ ሀያ ስድስት ዓመታትም በዙፋኑ ለመዝለቅ የበቁት፡፡ በተቃውሞው ሰፈር ያለነው እኛ ግን ብዙ እኛዎች ነን፡፡ ሰንደቅ ኣላማ ለብሶ ከሚፎክረው፣ ኢትዮጵያ እያለ ከሚዘምረው፣ የብሄር ኩታ ለብሶ ከሚያቀነቅነው ፖለቲከና አይደለሁም እያለ ከሚሸውደው  ወዘተ ብዙ እኛዎች መካከል  የቤታችን ጣራ ተቀይሮ ሁላችንም የጸሀዩ ሀሩር ሳጠብሰን፤ የክረምቱ ዝናም ሳያበሰብሰን መኖር የምችልበት ቤት እንዲኖረን ምን ያህሉ ነን ከምር የምንሻው ተብሎ ቢጠየቅ  ከብዙዎቹ ተግባር በማየት የምናገኘው ምላሽ አሉታዊ ነው የሚሆነው፡፡ ይህ ለወያኔ ግዞት ያመቻቸን መሰረት አልባው ልዩነታችን መሰረት የለሽ በመሆኑ ለገላጋይ ዳኛ ለመካሪ ሽማግሌም የሚመች አይደለም፡፡ ብዙዎች በቤታችን ጣራ መቀየር በየግላቸው ያምናሉ፣ነገር ግን ይህን እምነት የጋራ ለማድረግ ይቸገራሉ፣ለምክንያትነት የማይበቃው ሰበባቸው የሚያሳብቅባቸው ደግሞ ጣራው እኔ በምለውና በምፈልገው መንገድ ካልሆነ በስተቀር ባይለወጥ ይቅር የሚሉ ከራስ በላይ የማያስቡ መሆናቸው ነው፡፡ በግልጽ ቋንቋ ለመናገር እኔ አባዋራ የማልሆንበት ቤት አንኳን ጣራው ግድግዳውም ይደርመስ የሚሉ ነው የሚመስሉት፡፡
አንዳንዶቹ ደግሞ ለስሙ ከተቃውሞው ጎራ ከትመዋል እንጂ አድራጎት ንግግራቸው የተቃውሞ አይደለም፡፡ ጣራው እያፈሰሰም ለጸሀይ እየዳረገም ቢሆን ወለሉ ከታደሰ ግድጋዳው ቀለም ከተቀባ ርካታ የሚሰጣቸው አይነት ናቸው፡፡ ያ ባይሆን  ከሀያ ስድስት አመታት አገዛዝ በኋላ ዛሬ ስለ ህግ በላይነት፣ ስለ ሰብአዊ መብት መከበር፣ ስለ ሀብት እኩል ተጠቃሚነት፣ ስለ ፍትህ ወዘተ ለወያኔ  ማላዘኑ በቆመ ነበር፡፡ እነዚህ ከእባብ እንቁላል እርግብ የሚጠብቁ ሊባሉ የሚበቁ ይመስለኛል፡፡ ሌላው ሁሉ ቢቀርና ቢረሳን  የህዝቡ ጥያቄ ትክክል ነው፣ የሰጡትን ዝም ብሎ የማይቀበል ጠያቂ ትውልድ ፈጥረናል ወዘተ ብለው ተመጻድቀውና ተሳልቀው ለተቃውሞ መውጣቱም ሆነ ያነሳው ጥያቄ ትክክል ነው ያሉትን ህዝብ በገፍና በግፍ አስረው እያስተማርነው ነው ተሀድሶ እየሰጠነው ነው ከሚሉ ሰዎች ምን ሊገኝ ጥያቄ እንደሚቀርብ ጩኸት እንደሚሰማ አይገባኝም፡፡
እያዩያ አለማስተዋሉ፣እየሰሙ አለማዳመጡ፣ እያነበቡ አለመገንዘቡ በእኛ ሰፈር በመብዛቱ እንጂ ወያኔዎች ከጅምሩ በመቃብራችን ላይ ሲሉ በግልጽ ነግረውናል፡፡ጽፈው አስነብበውናል፣ በተለያየ መንገድ በዘፈንም በፊልም አሳይተውናል፡፡እኛ ሰፈር ግን በምኒልክ ዘመን የደነቆረ ምንይልክ ይሙት እንዳለ ይኖራል እንደሚባለው ሆነን በወያኔ ድል ማግስት የተጀመረው ጩኸት፣ልመና ተማጽኖ፣ ስድብ ዘለፋ የመግለጫ ተቃውሞ  ወይ መሻሻል ሳይሳይ ወይ አርጅቶ ገለል ሳይል እስካሁን አለ፡፡
ሎሬት ጸጋየ  ገብረ መድህን የአባቶቻችን ነገር ሳስታውሰው ትዝ የሚለኝ ከሞከርነው ነገር ይልቅ ያልሞከርነው ነው የሚቆጨኝ እንዳለው  እስከ ዛሬ የመጣንበት የፖለቲካ ጨዋታ አላዋጣም፣ የያዝነውም ተለይይቶ ጉዞ  ከምንለው ቦታ የሚያደርስ አልሆነም ስለዚህ ራሳችንን ፈትሸን፣ አመጣጣችንን ገምግምን ድክት ጥንካሬአችንን ለይተን፣ለዘመኑ የሚስማማውን አስተሳሰብ እንያዝ፣ ለትግሉ የሚመጥነው መንገድ እንከተል በማለት የሚታትሩ ብቅ ሲሉ ከወያኔ ሰፈር ባልተናነሰ ጩኸቱ የሚበዛውም ሆነ  ትንሽ ትንሽ መሰናክል ማስቀመጥ የሚጀመረው እኛ ከምንባለው ብዙዎቹ እኛዎች በኩል ነው፡፡
ቤቱ ጣራው ዝናብ ቢያፈስም፣ ጸሀይ ቢያስመታም ወለሉ ካማረ፣ ግድግዳው ቀለም ከተቀባባ ለእኔ ይመቸኛል፤ የጣራው ነገር አያስጨንቀኝም ማለት መብት ነው ምርጫ ነው፡፡ ለዴሞክራሲ ነው የምታገለው የሚል ሁሉ ይህን ምርጫ መቀበል የሰዎቹን መብት ማክበር ይገባዋል፡፡እነርሱ ደግሞ ጣራው መቀየር አለበት ብቻ ሳይሆን ካልተቀየረ በቤቱ ውስጥ መኖር አንችልም በሚለው ወገን እየተከለሉም እየተመሳሰሉም እያደናገሩም መኖሩን አቁመው አቋማቸው ጥቅም የሚያገኙበት ሳይሆን ከልብ የሚያምኑበት ከሆነ   መብታቸውን በይፋ መጠቀም እምነታቸውን በግልጽ ማራመድ ይኖርባቸዋል፡፡መሸፋፈን ለመኝታ ግዜ ብቻ ይሁን፡፡ ማለባበስ ይቁም!
በጣም አስቸጋሪው መፍትሄ አጥቶ የግዞት ዘመናችንን እያራዘመው ያለው በጣራው መቀየር ላይ ልዩነት ሳይኖር መቀየር ያለበት እኔ በምለው መንገድ ብቻ ነው የሚለው አስተሳሰብ ነው፡፡የነገሩ ክፋት የሚብሰው ደግሞ የዚህ አስተሳሰብ አራማጆች በሚሉት መንገድ ለመቀየር ስንዝር የተግባር እንቅስቃሴ የማያደርጉ መሆናቸው ነው፡፡ተግባሩ ቀርቶ እንዴት በምን ሁኔታ በማን ጣራው መለወጥ እንደሚችል ግልጽ አቋም የላቸውም፡፡ አቋማቸውን ገልጸው መንገዳቸውን አሳይተው ሊደርሱበት የሚያልሙትን ግብ ነግረው ደፋ ቀና በሚሉት ላይ ለመዝመት ግን እንቅልፍ የላቸውም ፡፡እንዲህ መሆን የለበትም፣ አንደዚህ ለምን ይደረጋል፣ በዚህ መንገድ ለምን ይኬዳል ከማለት በስተቀር እንዲህ ይሁን በዚህ መንገድ መሄድ ያዋጣል ወዘተ በተግባር ቀርቶ በቃል ደረጃ እንኳን አይናገሩም፡፡
ግልጽ አቋም በጣራው መለወጥ ላይ፣ የቤታችን ጣራ ከተለያየ አቅጣጫ ብዙ ስም የወጣለት ገዢዎቻችንም ሊያደናብሩንና አቅጣጫ ሊያስቱን በከጀሉ ቁጥር አዳዲስ ስም እያወጡ  በአንድ ያልረጉበት ሲሆን የምንሻው ግን ግልጽ ነው፡፡ዴሞክራሲያዊ ጣራ፡፡ ወራጅና ማገሩ ቆርቆሮና ምስማሩ በህዝብ ለህዝብ የህዝብ ሆኖ የሚሰራ ጣራ፡፡ይህን የሚጠላ ወይንም የማይፈልግ በአንደበቱ ባይናገረውም በተግባሩ እንለየዋልን፡፡የመጀመሪያው ወያኔና በዙሪያው ተኮልኩለው ተጠቃሚ የሆኑት ናቸው፡፡ለጥቆ የምናገኛቸው ሀያ ስድስት አመት ሙሉ ተቀዋሚ መባል ያልሰለቻቸው ምን አልባትም የሚያኖራቸው ወያኔ ተሰናብቶ ዴሞክራሲያዊ ሥርኣት ቢሰፍን ወለሉ ይታደስ ግድግዳው ቀለም ይቀባ አይነት የይስሙላ ተቃውሞ እያሰሙ መኖር አይችሉምና የጣራውን ለውጥ አይፈልጉትም፡፡ ሲስልስ ወያኔን ከማውገዝና ከማጥላላት ባለፈ የተጀመረም ሆነ የተሰነቀ ነገር የማይታይባቸው ነገር ግን ይህንኑ መኖሪያቸው ያደረጉ እናት ኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ብሉኮ ብትከናነብ ህዝባችን ተገደለ ታሰረ በዘራችን ብቻ ተጠቃን  እያሉ ነሸጥ ሲያደርጋቸውም በመገንጠል እያስፈራሩ፣ ሰከን ያሉ እለት ደግሞ ስለ አንድነት እየዘመሩ ያሉ፣ የሚኖሩ ወገኖች ያኔ ይህን ማድረግ አይችሉምና በአፋቸው የሚናገሩት/የሚነግዱበት  ዴሞክራሲያዊ ስርዓት በተግባር እውን ሲሆን ለማየት ይሻሉ ብሎ ማሰብ ይቸግራል፡፡
በድርድርም በሉት በግርግር፤በሰላማዊ ሰለፍም በሉት በጩኸት፣በጽሁፍም ይሁን በንግግር የሚቀርቡ ጣራውን በመለወጥ ላይ የማያተኩሩ ነሮች ሁሉ ጣራው ለሚያፈስ ቤት የወለል እድሳት የመፈልግ ያህል ነውና ሲብስም እቅጣጫ የሚያስት ትግል የሚያዘናጋ ለገዢዎች እፎይታ የሚሰጥ ወዘተ ነውና ይታሰብብት፡፡ በሁሉም መንገድ በየትኛውም መስመር ትግል ጣራውን ለመቀየር፡፤

Thursday, June 22, 2017

ሰራዊቱን ዝም ለማሰኘት የታቀደ የመጀመሪያ ዙር ስራ የተቃዋሚ ደጋፊ የተባሉ ወታደሮችን ለማጥቃት የታቀደ ግምገማ ሊደረግ መሆኑ ታውቋል ቆንጂት ስጦታው



ቆንጂት ስጦታው – ከጦር ሃይሎች የተገኘው መረጃ እንደተመለከተው በመከላከያ ሰራዊቱ ሁሉም እዞች በወታደሮች ላይ ግምገማ ሊደረግ መሆኑ ታውቋል::የግምገማው ዋናው ሂደት በሰራዊቱ ውስጥ የተገኘው የኢሕአዴግ ድምጽ አነስተኛ መሆኑ እና ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል ከሚል አንጻር ተጠርጣሪ የተቃዋሚ ደጋፊ የተባሉ ወታደሮችን ለማጥቃት የታቀደ ግምገማ ሲሆን በግምገማው ላይ ሞባይሎች እንደሚፈተሹ እና ተቃዋሚዎችን በተመለከት ውስጥ ለውስጥ ፕሮፓጋንዳ ያራግባሉ እንዲሁም አለማቀፍ ጉዳዮችን በተመለከተ ከሚዲያ መረጃዎችን ይዘው መተው ያወራሉ የሚባሉ ወታደሮች የግምገማው ሰለባ እንደሚሆኑ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ተናግረዋል::የመከላከያ ሰራዊቱ ከሲቭል ደህንነት እና ከኢንሳ በተመደቡ እና የወታደሩን ካኪ ለብሰው በመመሳሰል በሚሰልሉ የሕወሓት አባላት አቅራቢነት ወንጀሎች ተቀነባብረው ግምገማውን እንደሚያጦዙት ይጠበቃል ሲሉ ምንጮቹ አክለው ገልጸዋል::
የለውጥ ፈላጊ ሃይሎችን ደግፋችሁሃል በሚል ለጥቃት የተዘጋጀው ይህ ግምገማ አለመተማመን እና ጥርጣሬ በሞላው የመከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ ልዩነቶችን በማስፋት በአንድ ብሄር የበላይነት የሚተዳደረውን አምባገነን ወታደራዊ አመራርን በማጠናከር ሌሎች ብሄሮች በፍርሃት እና በስጋት እንዲኖሩ ለማሸማቀቅ የሚያደርግ እንዲሁም ሰራዊቱን ለለውጥ ያነሳሳሉ የሚባሉ መኮንኖችን እና ወታደሮችን ሰብስቦ ለማሰር እና ደብዛቸውን ለማጥፋት የታቀደ እንደሆነ ታውቋል:ግምገማው የሚመራው በተለያዩ እና በጄነራልነት ማእረግ ባላቸው የሕወሓት መኮንኖች ሲሆን ሰራዊቱን ዝም ለማሰኘት የታቀደ የመጀመሪያ ዙር ስራ መሆኑን ምንጮቹ ገልጸዋል::
ይህ በእንዲህ እንዳለ 450 የሕወሓት አባላት ተመልምለው ለወታደራዊ ስልጠኛ በሚል በተለያዩ የምስራቅ አውሮፓ አገሮች ለትምሕርት ሊላኩ መሆኑ ሲታወቅ ከአንድ ብሄር ብቻ ለምን/እንዴት ይህ ሆነ የሚል ጥያቄ መነሳቱን እና ምንም አይነት ምላሽ እንዳልተሰጠው ታውቋል::ምንጮቹ አያይዘው እንዳሉት ልሰላም አስከባሪ ሃይል ከፍተኛ አመራር እንዲሆኑ ለስልጠና የታጩት የሕወሃት አባላት ጉዟቸው እንደማይሰረዝ እና ጉዞውን ለተቃወሙት መኮንኖች ከፍተኛ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል ሲሉ ገልጸዋል:: ቆንጂት ስጦታው

በአማራ ላይ የተሰለፉ አምስተኛ ረድፈኞች! (ቬሮኒካ መላኩ)

ሳተናው June 21, 2017 23:55      


የሰው ልጅ ታሪክ እንደሚያስረዳን አለም በመንታ ባህሪያት የተዋቀረች ትመስላለች። ሰማይ ስንል መሬት አለ። እሳት ስንል ውሃ አለ ፣ ብርሃን ብለን ጨለማ አለ ፣ አርበኛ ብለን ባንዳ አለ እንደዚህ እንደዚህ እያልን ብዙ ነገሮችን መጥቀስ እንችላለን።
እነዚህ ባህሪያት መገለጫ አንዱ ሰው ነው። የሰውም ባህሪ እንደዚሁ ለየቅል ነው። በሰው ውስጥም ክፋትና በጎነት ፣ታማኝነትና ክህዴት ፣ ሁሉም ተቃርኖ አለ። በአንድ ብሄር ፣ ማህበረሰብ ፣ እንድሁም ቤተሰብ ውስጥ የአስተሳሰብ ዝምድና ከሌለ የስጋ ዝምድና ብቻውን ሰዎችን ማወዳጄት ፣ በአንድ አላማ ስር ማሰባሰብ እንደማይችል ከአንድ ማህበረሰብ ብሎም ቤተሰብ የተገኙ ልጆች እርስ በርሳቸው ሲቆራቆሱ እና ሲጨራረሱ የአለም የትግል ታሪክ ያስተምረናል።
ሰሞኑን ከአማራው አብራክ እየወጡ ራሱን አማራውን ከጀርባ በጦር የሚወጉትን ቡድኖች ወዳጄ ዶ/ር GM Melaku “ዋለልኞች” ብሎ ስም አውጥቶላቸዋል። እኔ በበኩሌ ከስፔኖች ተውሼ “አምስተኛ ረድፈኞች ” በማለት ልሰይማቸው።
ዛሬ በወዳጄ በ GM Melaku ስያሜ መሰረት “ዋለልኞች” በእኔ አጠራር ደሞ ስለ አምስተኛ ረድፈኛ አጠር አድርጌ ልፅፍ ነው። ይችን አጠር ያለች ጦማር መፃፍ ያስፈለገኝ ከሁሉም በላይ የአማራ ብሄርተኝነትን ደንቃራ እና ጋሬጣ ሆኖ እየጎዳው ያለው ” አምስተኛ ረድፈኛ ” የሚባለው ቡድን ነው ብዬ ስላመንኩኝ ነው። አማራን የሚጎዳው በይፋ በጉያቸው ሾተል ፣በጭናቸው ክላሽንኮቭ በያዙ ጠላቶቹ ብቻ ሳይሆን ከጉያው በወጡ የወዳጅ ጠላትም ጭምር ነው።
አምስተኛ ረድፈኛ ማለት ፤ አንድ በሚስጥር የተደራጀ ቡድን ወይም ግለሰብ ሲሆን ፣ ለጠላት በመወገን የራሱን ሕዝብ ጥቅም በማንኛውም መልኩ ከመሀል ሆኖ የሚቦረቡር ማለት ነው።
እንደዚህ ዐይነቱ ጠላት ደግሞ ከለየለት የውጭ ጠላት የበለጠ አደገኛ ነው። ለዚህም ነው አማራ ሲተርት “ፈጣሪዬ እኔ ከጠላቶቼ እራሴን ስከላከል አንተ ከወዳጅ ጠላት ጠብቀኝ” ተብሎ የሚፀለየው።

አምስተኛ ረድፍ የሚለው ሀይለ ቃል በመጀመሪያ ለውስጥ ቦርቧሪዎችን ለመግለፅ የተጠቀመው ስፔናዊው የፋሽስት ጀኔራል ሞላ ነው። ከ1936 እስከ 1939 በተካሄደው የስፓኝ የርስ በርስ ጦርነት ጊዜ ማድሪድ ስትከበብ ፋሽስቱ ጀነራል ሞላ በውስጥ አርበኝነት ስለሚያገለግሉት ደጋፊዎቹ ሲናገር “እኛ ማድሪድን በአራት ረድፍ እያጠቃናት ነው። በከተማይቱ መሃል ደሞ 5ኛ ረድፍ አለን” በማለት ከገለፀው የተወሰደ ነው።
በኢትዮጵያ የረጅም ዘመን ታሪክም “አምስተኛ ረድፈኛ” አማራውን ፍዳ ሲያሳየው፣ ወገኖቹን ሲያስጨፈጭፍና ፣ ለጠላት አጋልጦ ሲሰጠው ታሪክ መዝግቦታል።
አረብ ፋቂህ የተባለው የኢማም አህመድ የግል ፀሃፊ በአረብኛ “Futuh al-habasha” በማለት ፅፎት “the conquest of Abyssinia” በሚል ርእስ ወደ እንግሊዚኛ የተመለሰው መፅሃፍ እንደሚከተለው ያለ “የአምስተኛ ረድፈኞች ” አሰቃቂ ድርጊት ተመዝግቦ አንብቤአለሁኝ … …
“ኢማም አህመድ ጠንካራውንና የማይደፈረውን የአምባ ግሸን ምሽግ ለመስበር ብዙ ሞከረ። እዚህ ምሽግ ውስጥ የሰለሞናዊ ስርዎ መንግስት የነጋሲ ልጆች፣ የልጅ ልጆች፣ ዘመዶች እና ብዙ ሀብት ይገኝ ነበር። ኢማሙ ከቱርክ እና ከፓኪስታን በመጡ መድፍ ተኳሾች ቢሞክርም የክርስቲያኖቹ አምባ የማይደፈር ሆነ። ወታደሮቹም አለቁበት። 3 ወር ሙሉ አምባ ግሸንን ለመስበር ሞከረ የማይቻል ሆነ። ወደ አምባው መውጫ ያለው ሁለት በር ብቻ ስለነበር በሩን ይዘው አልበገር አሉ። በመጨረሻ ኢማም አህመድ (ግራኝ) የአምባ ግሸንን ምሽግ ለመያዝ በውጊያ መሞከርን ትቶ አምባው ካሉ የክርስቲያን ተዋጎዎች መካከል አምባውን አሳልፎ የሚሰጠው ከሃድ መፈለግ ጀመረ። በወርቅ እና በገንዘብ የተደለለ ሰውም ተገኘ።በዚህም መሰረት የግራኝን ጦር በስርቆሽ በር በኩል እየመራ ወደ አምባው በድብቅ አስገባቸውና የክርስቲያኑን ጦር ከጀርባ በኩል አስጨፈጨፋቸው። የአምባ ግሸንም ጠንካራ ምሽግ ተሰበረ።” እያለ ይቀጥላል። The conquest of Abyssinia. Page. 345.
ይሄ ከመፅሃፉ የጠቀስኩት ቁራጭ ታሪክ የሰዎችን፣ የከሃድያንን እርቃነ ማንነት እና የሚያደርሱትን ወሰን የለሽ ጉዳት የሚያመለክት ነው። በአገራችን ውስጥ በታሪካችን ዘርዝረን መንዝረን ሳንመለከተው እየቀረን ይሆናል እንጅ የዚህ አይነት የትውልድ አራሙቻዎች ሲከሰቱ ተስተውሏልም እንማርበትም ዘንድ ተመዝግቧል።
አሁን ከአማራ ህዝብና የአማራን ብሄርተኝነት ለመገንባት በምናደርገው ትግል “የአማራ አምስተኛ ረድፈኞች ” ምን ማለት እንደሆነ የተግባባን መሰለኝ። ያልገባው ካለም አምስተኛ ረድፈኛ ” ማለት ከአማራ ህዝብ አብራክ ወጥተው አማራን ለጠላት አሳልፈው የሚሰጡ ፣ ከጀርባ የሚወጉ ( backstabbers) የአማራን ለምድ ለብሰው እንደ ተኩላ የሚተውኑ ማለት ነው።
አስተውላችሁ ከሆነ እነዚህ አጎብጓቢ ረድፈኞች ሲፅፉም ሆነ ንግግር ሲጀምሩ እንድህ በማለት ይጀምራል… “እኔ አማራ ነኝ ነገር ግን በብሄር መደራጀት አላምንም።” ይላሉ። ይች የአነጋገር ዜዬ መለያ ባህሪያቸው ናት። ለእኔ አደገኛው ይሄ ነው። እነዚህ ሰዎች “አማራ ነኝ” ብለው ይጀምሩና “በብሄርም መደራጀት አላምንም ” ብለው ድስኩራቸውን ቀጥለው የኦሮሞውን፣ የሱማሌውን፣ የትግሬውን፣ የወላይታውን፣ የ80 ውን ብሄር መደራጀት ችግር የለውም ብለውን እርፍ ይላሉ የአማራውን መደራጀት ግን በርበሬ እንዳጠኑት ልጅ ሲያስነጥሳቸው ይውላል።
ከ 500 አመታት በፊት ጠላቶቻችን ፈ ት ለፊት ተጋፍጠው ማሸነፍ ስለማይችሉ እየተጠቀሙ ያሉት በዚህ “በአምስተኛ ረድፈኛው” ቡድን በኩል ነው።
የአማራ አምስተኛ ረድፈኞች የሚሰሙኝ ከሆነ ጥቂት ምክር ቢጤ ጣል ላድርግና ፅሁፌን ልዝጋው። ረድፈኞች ከእናንተ ጋር የአንድ ቤተሰብ እና የአንድ ወገን ልጆች ብንሆንም በአስተሳሰብ አንገናኝም። የአንድ ክልል ፍሬ ብንሆንም ጎራችን ለየቅል ነው። የአንድ ወጥ ባህል ልምድና አካባቢ ውልዶች ብንሆንም ግባችን የተለያየ ነው። ባንድ መልክ ያደግን ብንሆንም በተዥጎረጎረ ባህሪይ ጎልምሰናል። ለእኔ የሚጣፍጠኝ ለአንተ ይመርሃል። ለእኔ የሚጥመኝ አንተን ያቅርሃል። ህዝባችን ያለበት አስከፊ ሁኔታ ቆራጥነትን የሚጠይቅ ሌላው ቀርቶ ከአንድ አብራክና ከአንድ መሀፀን የተገኙትን የአንድ አባትና የአንድ እናት ልጆች የሚያታግል ነው። ነፃነት የሚባለውን ክቡር ነገር ለማግኘት ጠላትን ብቻ ሳይሆን የወዳጅ ጠላትንም መፋለም የግድ ይላልና ትግላችን “ከአምስተኛ ረድፈኞች” እና “ዋለልኞች “ጋርም መሆኑ መታወቅ አለበት።

Monday, June 19, 2017

የኤፈርት ዳሪክተር ኣዜብ መስፍን ማጭበርበር ከትግራይ ህዘብ አይሰወርም – ከኣስገደ ገብረስላሴ ወሚካኤል


By ሳተናውJune 20, 2017 00:58



ባለፉት ቀናት ኣዜብ መስፍን ከዓይጋ ፎሮም ዌቭ ሳይት ጋር የኤፈርት ኩባንያዎች ማለት እንድስትሪዎች ፣ባንኮች ፣እንሽራንሾች ፣ የትራንስፓርትና ኮንስትራክሽን ኮፓንያዎች ፣ የንግድ ማእከላት ፣ የላኪና ኣሰመጭ ኩባንያዎች በሚመለከት ሁኔታቸው ለማወቅ ቃለመጠየቅ ሲደረግላት በጥሞና ሰምቸውኣለሁ።
ኣዜብ ለቀረበላት ጥያቄ የሰጠችው መልስ ከዛ በፊት ከነበሩት የኤፈርት ዳሪክቶሮች ስብሃት ነጋ ፣ ስዩም መስፍን ፣ ኣባዲ ዞሞ ልዩነቱ የነዛ የተራቀቀ ማጭበርበር ፣የኣዜብ መስፍን ያልበሰለ ግለጽ ማጭበርበር ነው የሚለያቸው ። በተረፈ የማጭበርበር ስልታቸው የኣንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ ነው ።
የነዛ ተንኮልና ማጭበርበር በኤፈርት ሃብት በለጸገ በላ ጠጣ ሃብታም ሆነ እተባለ 25 ኣመት መሉ የተነገደለት የትግራይ ህዝብ በተለይ በቅርብ በኣጠቃላይ ደግሞ የኢትዮጱያ ህዝብ እያወቀውና እየተቸው እየተቃወሞው ኖሮዋል ኣሁንም ተቃውሞው ኣልበረደም ።
ወደ ኣዜብ መስፍን ማጭበርበርና ሽወዳ ልግባ ፣
አዜብ ኤፈርት የማን ነው ተብላ ስትጠዬቅ የሰጠቹ መልስ ፣
** ኤፈርት የማንም እጅ ጣልቃ ሳይገባበት የትግራይ ህዝብ ነው ኣለች ። ይህ ኣባባል 25 ኣመት ሙሉ ኣደንዝዞን ነረዋል ። ኣዜብ መስፍን ህዝብ በየተኛው የባለቤትነት መብት ነው የህዝብ ነው የምትለን ያለች ? እነዚህ ኩባንያዎች ከመጀመሪያ ጀምረው በባለ ቤትነት የተመዘገቡ 32 የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ እና 4 የህወሓት ነባር ኣባላት የነበሩ በሽምግልና ኣእሙሯቸው የተዛቡ የትምህርት ቀለም ያልቆጠሩ ሁለት ከሽሬ ኣንድ ከኣድዋ ኣንድ ከእንደርታ ነበሩ ። ለምሳሌ ለመጥቀስ ወይዘሮ ነጅያ የተባሉ በዛን ወቅት ከ87 ኣመት እድሜ በላይ ነበሩ ።እኒህ እናት ልጆቻቸው በትግሉ ያለፉ ኣይናቸው ጭራሽ የደከሙ መስማት የተሳናቸው ነበሩ ።
እኒ ኣራት ሰዎች ወደዛ የባለቤትነት መብት ሲገቡ ሆን ተብሎ የህዝብ ነው ብሎ ለመጭበርበር ታሳቢ በማድረግ የተሰራ ነበር ።
ለዚሁ መራጋገጫ 32 ማ /ኮቴና ኣራቱ ኣርሶ ኣደሮች 36ቱ ማለት ነው እያንዳንዳቸው 500 ሚሊዮን ብር ሸር ተመዝገበው ሲያበቁ ፣እነዛ 4ቱ ኣርሶ ኣደሮች የተባሉት እኛ ሽማግሌዎች ስለሆን ለህወሓት ማ / ኮሚቴ ኣውርሰናል ብለው እንዲፈሩሙ ተደረገ ። ይህ ማጨበርበር ኣደለም ?
ሌላስ የትግራይ ህዝብ ለባለ ኣደራ ቦርድ በውክልና ሰጥቷል ብላለች ። መቸ ቀን ? በየተኛው ጉባኤ ? የተወከሉ እነማን ናቸው ? ለመሆኑ ከ5 ሚሊዮን የትግራይ ህዝብ ለምስክርነት የሚቀርብ ኣለን ? ሌላ ቀርቶ የህሓት ታማኝ ካድሬ የሚመሰክር ኣለ ? መልሱ የለም ነው ። ኤፈርት ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ የሸር ባለቤቶች ማ /ኮሚቴ ህወሓት ፣ቦርድ ዳሪክቶሮች ፖሊት ቢሮ ( ስራ ኣስፈጻሚዎች) ናቸው ። እስከኣሁንም የትግራይ ህዝብ ስለኤፈርት ምንም ግንዛቤም ተጠቃሚም ኣይደለም ። ኣሁን ሲመረው በተለይ ሙሁራን ተማሪዎች ወጣቶች ስለ የህወሓት ሸፍጥ በጥልቀት
እየተረዱ ሲሄዱ ጥያቄ ማንሳት ጀምረዋል ።
+++ አይጋ ፈሮም የኤፈርት ኩባንያዎች ሲጀምሩ የካፒታላቸው ምንጭ ከየትነው ሲላት ? በትግል ጊዜ ከሰተሰበሰበውና ከባንክ ብድር ነው ኣለች ። እዚህ ላይ ለጦርነት ማስፈጸምያ ተብሎ የተሰበሰበ ገንዘብ በብር ዶላር ፣ፓውንድ ፣ ደችማርክ ፣ የሱኡዲ ሩያል ፣ ነዳጅ ፣መድሃኒት ፣ የመኪና መለዋወጫ ወዘተ በቡዙ ቢሊዮን ነበረ ። እኔም በወቅቱ ስንቅና ትጥቅ ትራንስፓር ሃላፊ ስለነበርኩ በሚገባ ኣውቃለሁ ።
እኔ የማልቀበለው ከባንክ ተበድረናል ለሚለው በምክንያት ኣድርገው ለዛቁት ዶሏር ለመመዝበር ይመቻቸው ዘንዳ ሽፋን ሊሆናቸው የተሰራ ድራማ ነው እንጅ ለሁሉም ለተቋቋሙ ኩባንያዎች ማቋቋምያ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶሏርና ፓውንድ ነበር ።ብር ቢሆን በወቅቱ ከነበረ የመንግስት ገንዘብ የበለጠ ነበር ። ያከባንኪ ተበድረናል የሚል ድራማ ለወደፊት ዶሏር ለመመዝበር ኣርቀው በማሰብ የተሰራ ድራማ ነበር ። ምክንያቱም የኩባንያዎች ትርፍ የት ገባ ለሚል ጥያቄ ኣፍ መዝጊያ ብለው ኣዛጋጅተውት የቆዩ ነው ። በዛ የስርቆት እስትራተጃቸው መሰረት ደግሞ 25 ኣመት ሙሉ ለቀረበላቸው ጥያቄ ለማጭበርበር ተጠቅመውበታል ።
ሌላ ኣዜብ መስፍን ስትሸውድ ኤፈርት የገባሬሰናይ ስራ ይሰራል በመሆኑም ለኣካል ጉዳቶኞች ፣ ለታጋይ ቤቶሰዎች አግዘናል በዘለቄታም ለ12 000 ለተሰው ታጋዮች ቤተሰብ ኣግዘናል ፣ እናግዛለን በተጨማሪም በማህበራዊ ኣገልግሎት 12 ሁለተኛ ደረጃ ት /ቤቶች ኣሰርተናል ለገናም እና ሰራለን ኣለች ።
ኣዎን እኔም የምመሰክረው በዋጅራት ፣መሶቦ ፣ሳምረ ፣ኣግበ ፣ ኣጽቢ እያንዳቸው ከ17 ሚሊዮን በላይ ብር የፈጁ ወደ 90 ሚሊዮን ብር ጨርሰዋል ። በመቀሌ ሀጸይየውሀንስ ትቤት 70 ሚሊዮን ብር ወጭ ኣድርገው ሰርተዋል ። መቀሌ እና ኣዲስ ኣበባ የሚገኜው የኣካል ጉዳቶኞች ህንጻዎች በመቀሌ 80 ሚሊዮን ብር ፣በአዲስ ኣበባ 100 ሚሊዮን ብር በድምር 370 ሚሊዮን ብር ሰጥተዋል ። ለኣካል ጉዳቶኞች ለተሰው ታጋዮች ቤተሰዎች ኣግዘናል ለምትለው ኣምና ብቻ የትግራይ ህዝብ ስለጠላቸው ወደሁሉ ስራ ኣንሳተፍም ኣንሰበሰብ ብሎ ሲተፋቸው ለመላሳለስ ተብሎ ለ10 000 የ
ሰው የታጋዮች ወላጆች ድጋፍ ማማለጃ ተብሎ 30 ሚሊዮን ብር ለአንድ ሰው ለኣንድ ጊዜ ብቻ የተሰጠ 3000 ብር ሰጠናል ብለው ነበር ከዛበኃላ ኣልቀጠሉበትም። የተሰጠው ግን ለ10 000 ሰዎች ሳይሆን ለ7000 ሰዎች ብቻ ነው የተሰጠ ለዛው ያለውና የለለው(የመነጠ) የመነጠ ወይ ባዶ የሆነ እየተባለ ልዩነት የተፈጸመ ህዝብ ያጣላ ። አንድ ላም አንድ በሬ ወይ ኣንድ ፍየል ያለው አይሰጥም በማለት ተከልክለዋል ።በትግራይ ግን ቤተሰቦቻቸው ኣባቱ እናቱ ሚስቱ ለጆቹ ጨምሮ የታጋዮች የምልሻ የገጠር ካድሬና አደራጅ ፣ አስተዳዳሪዎች የነበሩ የተሰው ቤተሰዎች የደኸዩ ከ1000 000 በላይ ወገኖች ኣሉ ። በጠሩነቱ ባሎቻቸው ፣ ልጆቻቸው ከህወሓት ጋር ተሰልፈው መስዋእቲ የከፈሉ ከሰሜን ጎንደር ከሰሜን ወሎ የላስታን የሰቆጣ ኣገው ፣ ከሰሜን ሽዋ ፣ከኣፋር
ኣይጨምርም ። ኣዜብ መስፍን ስትዋሽ ግን ለ12 000 የታጋዮች ቤተሰዎች ቀጣይ በሆነ በየወሩ እርዳታ እየሰጠን እየጦርናቸው ነን ብላለች ።
*** ኤፈርት ግን በ2008 ዓ ም ከሱር ኮንስትራክሽን ፣መስፍን እንጅነር ፣ትራንስ ኢትየጱያ ፣ከሰሚንቶ ፋብሪካ በኣመታዊ ግምገማቸው በሃወልት ሰማኣታት ያቀረበቹ ሪፖርት የኣራቱ ኩባንያዎች ብቻ 8 . 6 ቢሊዮን ከወጭ ቀሪ ትርፊ በኣንድ ኣመት እንደ ተገኜ ፣ ኣስታውቃ ለሰራቶኞች በቦኖስ በገፍ ሰጥታ ነበር ።
በ2009 ዓ ም ኣሁንም የኣራቱ ኩባንያዎች የኣመቱ ሽያጭ 27 ቢሊየዮን ሆኖ ። የተጣራ ትርፍ 11 . 4 ቢሊዮን ትርፍ እንደተገኜ ከውስጧ ታማኝ ምንጮች ተናግረዋል እንደበፊቱ እንዳያውጁት የኢትዮጱያ ህዝብ በተለይ ደግሞ የትግራይ ህዝብ እንዳያውቀው ስለሰጉ ነው ።ይህ ሁሉ ትርፊ ሌሎች 28 ኩባንያዎችን ኣይጨምርም ። ታድያ ኣዜብ መስፍን 370 ሚሊዮን እርዳታ ሰጠናል ብላ ስታጭበረብር ኣታፍርም 370 ሚሌን ብር እኮ ለኣዜብ መስፍንና ልጆቻ የኣንድ ወር የመዝናኛ ወጭ ኣትሸፍንም ። በኣንድ ወቅት እኮ በውጭ ሚድያዎች እንደሰማነው መለስ ከመሞቱ በፊት በቡዙ ሚሊዮን ዶሏር የሚቆጠር በሁለት ትላልቅ ሻንጣዎች ሞልታ ይዛ ሎንደን ኣውሮፕላን ማረፍያ ተይዛ ነበር በመለስ ድጋፍ ወይ ከውስጥ የመጡ መረጃዎች እንደ ተናገሩት መለስ ከቶኒቢለር ተነጋግሮ ነው የተለቀቀች ወይ የዳነቹ ። ጥሩ ኣዜብ ባለቹ እንቀበላትና የ20 ኣመት ትርፍ የት ገባ የትግራይ ህዝብ እኮ ታጋሽ ሆኖዋል እንጂ ከናንተ በላይ ኣልፎ ሄደዋል ።ኣሁን ግን ትእግስቱ ሟጥጦ ጨርሰዋል ። ወገኖቼ ያትርፍ 28 ኩባንያዎች ኣይጨምርም ስላችሁ ቅርንጫፎችን ኣይጨምር ። ለምሳሌ ወጋገን ባንክ ፣ኣፍሪካ ኢንሽራንስ ፣ ጉና ፣ ሜጋ ህትመት ፣ በሀገር ደረጃ ተሰማርተው የሚሰሩ ናቸው ።
*** የኣዜብ መስፍን የኤፈርት ድርጅቶች የገባሬሰናይ የህዝብ ፣ የኣካል ጉዳተኞች ናቸው ብላ ማጭበርበር ቦሷ ብቻ የተጀመረ ሽወዳ ኣልነበረም ባለፉት 25 አመታት በትግራይ ህዝብ በኣስተማሪዎች ፣በዩንቨርሲቲዎች ፣ነዋሪ ህዝብ ፣ተቃዋሚ ፓርቲዎች በፓርላማ ፣በምርጫ ወድድር ስለኤፈርት የባለቤትነት ጉዳይ የህጋውነት ጉዳይ ጥያቄ ኣንስተው የህሓት ማ/ ኮሚቴ እነ ስብሀት ነጋ ኣባይ ጸሃዬ ፣ኣርከበ እቁባይ ፣ ኣለም ሰገድ ገኣምላክ ጸጋይ በርኸ መለስ ዜናዊ ፣ወዘተ ልክ እንደ ኣዜብ እየዋሹ ነው የነሩ ።
*** እነዚህ ሰዎች ሲዋሹ ለነገ እንኳን ኣይሉም ለመድረካ ማላቀቅያ ብቻ ትሁን ምን ግዳቸው ። በዛን ጊዜ ጥያቄ ሲመልሱ ኤፈርት የኣካል ጉዳቶኞች ነው ይሉ ነበር ።
እኒህ ሰዎች ይቅርና ኤፈርት ሊሰጡዋቸውስ በነሱ ስም የተቋቋመው በመቀሌና አዲስ ኣበባ የተሰራው ሰማይ ጠቀስ ህንጻ በየወሩ በሚሊዮኖች ብር የሚቆጠር ኪራይ የሚያስገባ ፣ ትልቅ የደረቅና ፈሳሽ መጓጓዣ ኩባንያ የበዙ መኪና በስሙ በባለቤትነት የሚነገድበት ፣ የከፍት ርቢ የውሃ መጣርያ ፋብሪካ ወዘተ ኣላቸው እነዚ ኩባንያዎች ኣካል ጉዳተኞች ከመጤፍም ኣይጠቀሙበትም ። በኣሁኑ ጊዜ የትግራይ የጦርነት ኣል ጉዳቶኞች ከ126 000 ውስጥ ትንሽ የጥሮታ ኣበል የምትሰጣቸው 4600 ሰዎች ብቻ ናቸው ። ኣብዛኞቹ በልመና ተሰማርተው የሚኖሩ ናቸው ። እነዚህ ሰዎች ታመው ህክምና ኣያገኙም እነ ኣዜብ መስፍን ግን ጉንፋን ይዙዋቸው በፈለጉት አገር ሚሊዮኖች ዶሏር ይከፈላቸዋል ።
*** ኣሁን ያለው የፓርቲዎች መቋቋምያ ህገመንግስትና ከዛ የመነጨ የፓርቲዎች መቋቋምያ ኣዋጅ ሲተነትን ፣ማንም ፓርቲ የኢህኣደግ ፓርቲም ጭምር 1ኛ በቀጥታ ይሁን በተዘዋዋሪ የንግድና የእንድስትሪ ስራ አይሰራም 2ኛ ማንም ፓርቲ የራሱ ሬድዮጣብያ ተለብዥን ኣይኖረውንም ። ከምልሳን የሚጠቀምበት መጽሄት ጋዜጣ ብቻ ይኖረዋል ይላል ።
ይህ በኣእላፍ የህዝቦች መስዋእት የጸደቀ ህገመንግስት በህወሓት መሪዎች ተንዷል ኣጋሮቹ ወይ ስሪቱ የሆኑ ፓርቲዎቹም ጭምር ንደውታል ።
ታድያ ኣዜብ መስ የኤፈርት ኩባንያዎች
የሀገራችን ህገመንግስት ኣክብረው የሚነግዱ ፣በሃገራችን ካሉ ባለሃብቶች እንደኛ ግብር የሚከፍል እንደ ኤፈርት የለም ብላ ስትናገር ለማያውቃቸው ሃቅ ይመስለዋል ።
ሚድያው ለኣዜብ መስፍን ሲጠይቃት የኤፈርት ኩባንያዎች በሃገሪቱ ያለው ባለሃብት ሊሰራው የሚችል እያለ ኤፈርት ግን በጥቃቅን ንግድ እየተሰማራችሁ ለድህነት ዳርጋችሁቷል ? ብሏታል ።
የኣዜብ መልስ በጠራራ ጸሃይ ስትዋሽ እኛ የተሰማራነው በሃገር ባለሃፍት ሊሰራው በማይችል እየሰራን ለሱ ለመደገፍ ነው የምንሰራ ያለን ኣለች ።
*** ሃቁ ግን እንገራቹሁ የህትመት ስራ ኣንስተኛ ኩባንያ ነው። በኢትዮጱያ በደርዘኖች የሚቆጠሩ ማተምያ ቤቶች ኣሉ ።በመቀሌ ብቻ ብንወስድ 10 ትላልቅ ማተሚያዎች ከ20 በላይ ትናንሽ ኣሉ ።ግን የመንግስት ስራ በሃገር ደረጃ የሚሰጠው ለሜጋ ህትመትና ኣሳታሚ ድርጅት ነው ። በመቀሌ ያሉ ማተምያቤቶች እየዘጉና እሸጡ ወደሌላ ክልሎች ሄደዋል ።ሌሎችም የሚገዛቸው ኣጥተዋል እንጅ ከስረዋል ። ትናንሾችም እየሞቱ ናቸው ።
*** መሰፍን እንጅነር ብንመለከትስ ፣ ከመስፍን መመስረቱ በፊት መኪና የሚገጣጥም የኤረክሽ ወይ ፋብሪካዎች የመገጣጠም ስራ የሚሰራ መቀሌ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ5000 ስኬር ሜትር ወይ ግማሽ ሄክታር መሬት ወስዶ በቡዙ ሚሊዮን ብር ወጭ በማድረግ እጅግ ዘመናዊ ዎርክ ሾብ ሰርቶ ስራ የጀመረ ፣ለመስፍን ለሌሎች ባለሃብቶች ያስተማረ ማሩ ተፈራ ነበር ያሁሉ ሃብት ወጭ ኣድርጎ ለመስፍን ያስተማረ ከመቀሌ ተባርሯል ሌሎች ትናንሽ የብረታ ብረት ስራ ፣ኤረክሽን የጀመሩም በመስፍን እንጅነር ተገፍተው እንዲወጡ ተደረጉ ። እንዲዋጡም ተደርገዋል ።የተራ የብረት መዝግያ ስራም በመስፍን ተይዞ ነበር ፣ የትግራይ ባለሃብቶች ሲጨንካቸው ማሩ ተፈራ ተከትለው ኣዲስ ኣበባ ደቡብ ሱዳን ሄደዋል ። ከነሱ ከሸሹ ውስጥ እነ ኣብይ ሃይሉ ፣ኣሸናፊ ሃይሉም ይጠቀሳሉ ።
*** ጉናስ ፣ ጉና በሙሉ የንግድ ስራ በሁሉም በኢትዮጱያ ክልል ያሉ ነጋዴዎች ሊሰሩት የሚችሉ ፣የላኪና ኣስመጭ ፣የችርቻሮ የጅምላ ንግድ ስራ በሞኖፓል በመያዝ በተለይ የሰሚንቶ ለከንስትራክሽን የሚያስልጉ ግብኣቶች ሁሉም ኣይነት ብረታብረት ቆርቆሮ ፣ HRS ፣ ሽኮር ጨው ፣ ወ ዘ ተ በሞኖፓል በመያዝ ፣ቡዙ ነጋዴ ኣፈናቅለዋለ በተለይ በጣም የወረደ የስስታም ስራ ከመሰቦ ስሚንቶ ፍብሪካ ማንም ነጋዴና ነዋሪ ህዝብ በቀጥታ ሊወስድ የሚገባው ስሚንቶ ለጉና ይሰጣልና ህዝቡና ኣከፋፋይ ነጋዴና ቸርቻሪ ለጉና ትርፍ ኣስገኝቶ ከጉና ይገዛል ።
*** ትራንስ ኢትዮጱያ የደረቅና የፈሳሽ ጭነት መማላለሻ ኩባንያም እንደሌሎች እህት ኩባንያዎች የሀገራችን ያገር ውስጥና ከውጭ ወደ ኣገር የሚገባ ሁሉም ኣይነት ጭነት የመንግስት ፣ የፓርቲ ኩባንያዎች ፣ የእርዳታ ጭነት ኣብዛኛው ጭነት ያለጨረታ በስምምነት በተጽእኖ ለትራንስ ይሰጠዋል ለዛው የእርዳታ ድርጅቶች የሚከፈለው በዶሏርና በፓውንድ ነው ወይ በከናዳ ዶላርና በደችማርክ ነው ። ሌሎች የግል የነጥረት ፣ የድንሾ እኩሉ ከትራንስ ኢትየጱያ የማጓጓዝ ኣቅም ቢኖራቸው የትራንስ ጌታ ኣዳሪነት ሳብ ኮንትራት ሆነው ኮምሽን እተቆረጠባቸው የሚሰሩ ናቸው ።
በኣጠቃላይ በኢትዮጱያ ያሉ ግለሰዎች በማህበር ተደራጅተው የትራንስ ኢትየጱያ እጥ ፍ
እጥፍ መኪኖች ቢኖሩዋቸውም የትራንስ ጥገኛ ሆነው መስራት የግድ የሏቸዋል ። ትራንስ ኢትየጱያ ሌላ ቀርቶ በክልሎች ያሉ ዞኖች ወረዳዎች ለሚደረግ መጓጓዣ ለትራንስ ኢትዮጱያ ነው የሚሰጠው።ለዚሁ ሀቅ በሀገራችን ያሉ የትራንስፓር ማህባራት ኩባንያዎችይመስክሩ በተለይ ደግሞ በመቀሌ የሚገኜው ሰላም የደረቅና የፈሳሽ ኩባንያ ማህበር ሊመሰክር ይችላል ።ኣባሎቹ መኪና የገዙበት የባንክ እዳ መክፈል ተስናቸው ከስረው እያለቀሱ ይኖሯለ ።
*** ሱር ኮንስትራክሽን ቢሆን ባገራችን ያለው የመሰረተልማት ስራዎች ኣብዛኛው ያለጨረታ በድርድር ይሰጠዋል ።ቡዙ ኣገር በቀል የኮንስትራክሽን ኩባንያዎች ከደረጃ ኣንድ እስከ ደረጃ ስምንት የስራ ፍቃድ ያላቸው ኮንትራክቶሮች እያሉ ። በደረጃ 5 እና 6 ገብቶ በመስራት ኣገር በቀል ኮንትራክተሮች እንዳያድጉ ወይ እንዲሞቱ ኣድርጓል ። ከሱ ጋር እኩል ደረጃ ያላቸው ኩባንያዎች ስራ የሚሰጣቸው ሱር ኮንስትራክሽ በቃኝ ካለ በኃላ ነው ስራ የሚሰጣቸው ።
*** የቀሩት 28 ግዙፍ ኩባንያዎችም በሙሉ በሌሎች ኣገር በቀል ኩባንያዎች ሊሰሩ እየቻሉ ስለህዝብ ተጠቃሚነት ደንታ የሌለው የህወሓት ኣማራር ግን አዜብ መስፍን እንዳለቹ ለባለሀብቶች የሚያሰለጥንና የሚደግፍ ሳይሆን የህወሓት ተላላኪ ያልሆኑ ባለሃብቶች ሆን ብሎ እንዲነቀሉ ነው እየተንቀሳቀሰ የቆየው ኣሁንም እየተገበረው ያለው ። የመለስ ረኣይ እኮ በሀገራችን ያሉ የንግድ እና የእንድስትሪ የእንጅነሪንግ ኩባንያዎች ከ10 ኣመት በኃላ 100% በኢህኣደግ ኣባል ፓርቲዎችና በመከላከያ ምኒስቴር ፣ ስር እንደሚሆን በግልጽ ኣስሙሮበት ኣልፈዋል ።ታድያ ኣዜብ መስፍን የምታዳናግረው እንዴት ብሎ ተቀባይነት ያገኛል ። እነዚህ ፍጡራን በበረሃ ኣለም የደረሰበት ስልጣኔ እንዳናውቅ ኣፍነውን የኖሩ ኣልበቃም ብሉዋቸው አሁንም ለዚሁ ኣዲስ ትውልድ አጭበርበረው ሊያልፉ ነው የሚፈልጉ ? ፍጹም ኣይሆንም ። ኣይቻልንም ።
*** ጠያቂው ለኣዜብ መስፍን ኤፈርት ግልጽነተ ይጎድለዋል ፣የኤፈርት ሃብት ኦዲት ኣይደረገም ብሎ ሲጠይቃት ?
ኣዜብ ኣይኑ ያፈጠጠ ውሼት ስትዋሽ ፣ሁሉም ኩባንያዎች የውስጥና የውጭ ሂሳብ የሚደርጉ ኣሉ ።የመንግስት ፋይናንስም ኦዲት ያደርጋሉ ብላ ዋሸች ።
ዋዋዋ ለኣዜብ እና ለህወሓት ኣማራር ህዝብ እንዲያውቃቸው የማውቀው እመሰክርላችሁ ኣለሁ ።
ኤፈርት ሲመሰረት ስልጣኑ በህወሓት እጅ በመሆኑ ኣብዛኞቹ ኩባንያዎች መዋቅራቸው ለስርቆትና ለማጭበርበር በሚመች ስለተዋቀሩ
ገቢና ወጭውም ለኦዲት በማይመች መልኩ ነው የተዋቀረው ።
ከ8 ኣመት በፊት በኢፈርት ደረጃ ተጠሪነቱ ለነስብሃት ነጋ የሆነ በኦዲተርነት ከፍተኛ ሙያ ያላቸው ምርጥ እዲተሮች ቀጥሮ የሁሉም የኤፈርት ኩባንያዎች የገቢና ወጭ ሰነዶች ወደ ኤፈርት እየተሰበሰበ ኦዲት ይደረግ ተብሎ ነበር ። ሙሁራኑ የኤፈርት ኣሰራር እጅጉን የተዝረከረከ ስለነበር ፣ ኦዲቶሮች ቡዙ ሃብት ገንዘብ እንደተጠፋፋ እና ወደ ህግ የሚያቀርብ ትልቅ ጉድለት እንዳለው ሪፓርት በማቅረባቸው ፣ እነዛ ቦርድ ዳሪክቶሮች ለኦዲተሮቹ ተጠፋፋ የምትሉት ሃብት ሰርዙት ብለዋቸው ፣ ኦዲቶሮችም ለሙያቸው የሚጻረር ኣሰራር በመሆኑ ኣመታት የጨረሰ የእዲት ስራ መሰረዝ ሂሊናቸው ስላልፈቀደላቸው ከሰራቸው በነስብሃት ነጋ ተገፍተው ተባረሩ ።
ስለዚህ ኣዜብ መስፍን እንደዚህ ኣይነት ኣሰራር የሚከተል ኤፈርት
በጥራት ኦዲት ይደረጋል ብላ ስትናገር ማን ይቀበላታል ?? ።
*** ኣዜብ በቢሊዮን የሚገመት የኢፈርት ብር የት ገባ በማን ቁጥጥርስ ይተዳደራል ሲላት ፣ ለመዋሼት ድንብርጭ የማይላት ኣዜብ ኤፈርት እስከኣሁን የተገኜ ገቢ ለባንክ እዳ ከፈልነው ኣለች ።
የተከበራቹ ኣንባብያን ኣዜብ ቀደም ሲል የኤፈርት ኩባንያዎች የተመሰረትበት ለጦርነት ማስፈጸምያ ተብሎ የተሰበሰበ ገንዘብ ጦርኖቱ ከተቃጨ በኃላ የቀረው በጦርነት ለተጎሳቆለውን የትግራይ ህዝብ ማቋቋማ የሚያክል ቡዙ ገንዝብ ነበረን ብላለች።
እኔም ጦርኖቱ ካለቀ በኃላ በወቅቱ እጅግ ቡዙ ቢሊዮን ብርና ዶላር ፓውንድ ፣ ወርቅ ነበር ። እንዲሁም ዋጋው በቢልዩን ብር የሚቆጠር የተሸጠ መድሃኒት ፣ የምግብ ዘይት ፣ ሽኮር ፣ ነዳጅ የሞተር ፣ዘይት ፣ የተሽከርካሪዎች መቀያየሪ እቃ ፣ ተሸከርካሪዎች ፣ ሌሎች ቁሳቁስ ተሽጠው ቡዙ ቢሌን ብር ነበር ፣ በሱኡዲ ኣረብያ ፣በኢጣልያን ፣ በእንግሊዝ የንግድ ኩባንያዎች ነበሩ ። እነሱም ቡዙ ገንዘብ ነበሩ ይህ ሃቅ እኔ የስንቅና ትጥቅ የትራንስፖርት ስልጣን ስለነበረችን የነበረን የገንዘብ መጠን በሚገባ ኣውቃለሁ ። በወቅቱ የኤፈርት የባለቤትነት ጉዳይ በመቃወም
እስከ በነፍጥ መማዘዝ ደርሸ ነበር ። በመሆኑ ኣዜብ የምትለው ያለች ሁሉ ለትግራይ ህዝብ ማታለል ነው ።
ኣዜብ መስፍን ብድር ነበረን ስትለን ግን የህወሓት ኣማራር ለረጅም ጊዜ የሚሰራ ያስቀመጡት የሸፍጥ እስትራተጂ ለመሸፈን ብላ እያታለለችን ያለች መሆኗ ነው ።
የኣዜብ ስለኤፈርት የባለ ቤትነት ጉዳይ ሌሎች የሸፍጥ ዘዴዎች የተናገረቹ መልስና ኣስተያየት እየቆራረጥኩ እቀጥልበት ኣለሁ ለዛሬ እዚሁ ላብቃ
ከኣስገደ ገብረስላሴ ወሚካኤል ፣
በ13 / 10 2009 ዓ ም

Friday, June 16, 2017

የፕ/ር አስራት ወልደየስ የመቃብር ቦታ ወደ ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ሊዘዋወር ነው



              

የቀኃስ ቀዳማዊ ገጽ እንደዘገበው የባለወልድ ቤተክርስቲያን እድሳትን ተከትሎ በቤተክርስትያኑ ፊት ለፊት ያሉ መቃብሮች በሙሉ የፈረሱ ሲሆን ዛሬ የ ፕ/ር አስራት ሀውልትም በመነሳት ለይ ይገኛል።
የ ፕ/ር አስራት መቃብር ወደ ቅድስት ሥላሴ በክብር ታጅቦ እንዲዘዋወር እያስተባበሩ ያሉ 9 ሰዎች መሀከል
1, ዶ/ር ያዕቆብ ሀይለማርያም
2, ኢ/ር ግዛቸው ሽፋራሁ
3, አቶ የሺዋስ አሰፋ( ከ ሰማያዊ ፓርቲ)
4, አቶ ሙሉጌታ አበበ ( ከ መኢአድ ፓርቲ)
5, ኢ/ር ጌታነህ ባልቻ ( ከ ሰማያዊ ፓርቲ)
6, አቶ ሸዋንግዛው (ከ መአህድ ፓርቲ)
7, አቶ አክሊሉ (ከ መአህድ ፓርቲ)
ይገኙበታል።

ምንጭ: የቀኅሥ ቀዳማዊ ገጽ