Tuesday, October 18, 2016

ስለሰንደቅ አላማ የተጨነቁ በመምሰል ማንንም ማታለል አይቻልም::


ከቀድሞ ገዢዎች ሲወራረስ የመጣው በአንድነትና በባንድራ ሽፋን ሕዝብን መጨቆን ሊቆም ይገባዋል። ስለሰንደቅ አላማ የተጨነቁ በመምሰል ማንንም ማታለል አይቻልም::ሰንደቅ አላማ የማንነት መገለጫ እንጂ የኢትዮጵያውያን መወንጀያ አይደለም:: ወያኔ ይውረድ!!!

ቅድሚያ ለሰብኣዊ መብት!!! በሰንደቅ አላማ ላይ ጥቃት ይቁም!!!የሰንደቅ አላማ ላይ ጥቃት (State structural terrorism against flag) በወያኔ ተፈጽሟል:: ሕዝብን ለብሄራዊ ውርደት የዳረገው ወያኔ ስልጣኑን በመልቀቅ ለሕዝብ ሊያስረክብ ይገባዋል።
ምንሊክ ሳልሳዊ Minilik Salsawi
ይህን ሰሞን ያቺ በአመት በየወረቱ ህዝብን ለማታለል ለፖለቲካ ፍጆታ ለማዋል የሚለፉባት ቀን መታለች:: መሰረታዊ የዲሞክራሲያዊ መብቶቻቸን የጠየቁ ኢትዮጵያውያንን ለመወንጀል ይኸው የሰንደቅ አላማ ላይ ጥቃት (State structural terrorism against flag) በወያኔ ተፈጽሟል:: ኢትዮጵያውያን ስርኣቱ የማይቀበሉ;የተቃወሙ; መሰረታዊ የዲሞክራሲያዊ መብቶቻቸውን የጠየቁ ሁሉ ጸረ-ሰንደቅ አላማ ናቸው;የአብዬን ወደ እምዬ!!..ትላንትና በአለም አደባባይ ሲንቁት እና ሲያዋርዱት የነበረው ሰንደቅ አላማ ዛሬ የተገላቢጦሽ አድርገውት የራሳቸውን ወንጀል በሃገር ወዳዱ ህዝብ ላይ ማላከክ ጀምረዋል::
ወያኔ በረሃ በነበረበት ወቅት ሰንደቅ አላማን(የኢትዮጵያን) ለተለያዩ አስቀያሚ ድርጊቶች ይጠቀምባቸው እንደነበር ደርግ በሚዲያዎቹ ነግሮናል :: በ1982 አ.ም. መጨረሻዎቹ ወደ አምቦ ተጉዠ የተገናኘኋቸው የዛሬ አንድ ከፍተኛ ሚኒስትር ሰንደቅ አላማን በተመለከተ ጠይቄቸው ቃል በቃል =” ሰንደቅ አላማው ብሄረሰቦችን ቅኝ ለመግዛት የተወከለ ነው::…” ብለውኝ ነበር :: በተመሳሳይ በበረሃው ትግል ወቅት ጋዜጠኛ የነበረው ሴክቱሬ ጋር በተለያየ ጊዜ በተደረገው የስልክ ግንኙነት ሰንደቅ አላማ ትርጉም አልባ እንደነበር ይነግረን ነበር::
ዛሬ የሰንደቅ አላማእና የሰንደቅ አላማ ባለቀኖች ሆነው በመታየት የሚመጻደቁት ትላንት ሰንደቅ አላማዉ ጨርቅ ነው አላማን ያዘናጋል የቅኝገዢዎች መሳሪያ ነው እንዳላሉ ዛሬ በየትኛው የሞራል አቅማቸው ባንድራን ለማክበር እንደሚንደፋደፉ ግልጽ ሊሆን አልቻለም::ይህን ሰሞን ደሞ ደርሶ ሃኪም የሚሆኑት ወያኔዎች የእኩልነት ፣ የሉአላዊነት እና የማንነት መገለጫ የሆነውን ሰንደቅ አላማ ክብር እና እሴት በሚሸረሽር መልኩ የሚጠቀሙ የአንዳንድ ወጣቶችን እንቅስቃሴ ወጣቱ እንዲያወግዝ ጥሪ አቅርበዋል።…ይህ ማለት ምን እንደሆነ አልገባንም … ሊገለጽልን ይገባል ትላንት በሱማሌ በረሃዎች አልሸባብን ለመወንጀል ራሳቸው ወያኔዎች ሰንደቅ አላማ ሲያቃጥሉ ነበር …እንዲሁም መሰረታዊ የዲሞክራሲያዊ መብቶቻቸን የጠየቁ ኢትዮጵያውያንን ለመወንጀል ይኸው የሰንደቅ አላማ ላይ ጥቃት (State structural terrorism against flag) በወያኔ ተፈጽሟል::
ትላንት ቀዳደው የጨው መቋጠሪያ እና ቁምጣ ሲሰፉበት እንዳልነበር ሰንደቅ አላማውን ዛሬ ላይ የተቀደደ የተቦጫጨቀ … እያሉ ስም እየሰጡ መቤቴን ያለውን ኢትዮጵያዊ ለመወንጀል መሯሯጥ የትም አያደርስም::ትላንት የተቀዳደደ ሰንደቅ አላማ ይዞ አደባባይ ወጣ የተባለ ግለሰብ ፊልሙ በወያኔ የቴሌቭዥን ጣቢያ እጅ ይገኛል:ለምንስ ተይዞ ለፍርድ የማይቀርበው? ሰንደቅ አላማ የማንነት መገለጫ እንጂ የኢትዮጵያውያን መወንጀያ አይደለም:: ህዝብ ከነሱ መቶ ርምጃ ቀድሞ እንደነቃ ያልነቁት ወያኔዎች አንድን ነገር ከመስራታቸው በፊት ስለ ንጹህ ሰንደቅ አላማችን ሁለት ጊዜ ወደፊት ራመድ ብለው ያስቡ ዘንድ እንመክራለን::ስለሰንደቅ አላማ የተጨነቁ በመምሰል ማንንም ማታለል አይቻልም::
በኢትዮጵያ ታሪክ እንደወያኔ በሰንደቅ አላማችን ላይ አስከፊ ወንጀል የፈጸመ የለም::ለረዥም ዘመናት ታፍራና ተከብራ የኖረችውን መከበሪያችንን ሰንደቅ አላማ በመሃሉ ላይ ሰይጣናዊ የኮከብ ምልክት በማድረግ እንዲሁም ይህንን ያላመለኩ ዜጎችን እንደወንጀለኛ በመቁጠር በህዝብ እና በሰንደቅ አላማችን ላይ ከባድ ሽብር እና የወረራ ጥቃት አድርጓል::በየቦታው ለፖለቲካ አጀንዳው ሽፋንነት ለማዋል ከማቃጠል አንስቶ እስከ መቅደድ ድረስ የተለያዩ ወንጀሎችን በሰንደቅ አላማችን ላይ ፈጽሟል:; ይህንን አስከፊ እና አሸባሪ መንግስይ የሆነው የወያኔን ጁንታ ለማስወገድ በጋራ ትግላችንን በመቀጠል ስር አቱን ላንዲእና ለመጨረቻ ጊዚእ እንደጉም እንዲተን እና እንዲጠፋ መስራት አለብን:: ሕዝብን ለብሄራዊ ውርደት የዳረገው ወያኔ ስልጣኑን በመልቀቅ ለሕዝብ ሊያስረክብ ይገባዋል። ወያኔ ይውረድ!!! #ምንሊክሳልሳዊ

No comments:

Post a Comment