Tuesday, October 11, 2016

የአስቸኳይ ጊዜ ኣዋጁ በሚከተሉት መሰረት ሙልጭ ኣድርጎ የዜጎችን መብት ይገፋል።


የአስቸኳይ ጊዜ ኣዋጁ በሚከተሉት መሰረት ሙልጭ ኣድርጎ የዜጎችን መብት ይገፋል። (Minilik Salsawi)
– መደራጀት ፣መሰብሰብ እና ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ አይቻልም፡፡
– ተቃውሞን መግለፅ የተከለከለ ነው፡፡የተቃውሞ ሞልክቶችን ማሳየት አይቻልም፡፡
-ማንኛውም ተጠርጣሪ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ይያዛል ፡፡ይፈተሻል፡፡የመኖሪያ ቤት እና ተሽከርካሪ ያለምንም ቅድመሁኔታ ይፈተሻል ፡፡
-መገናኛ ዘዴዎች ይዘጋሉ፡፡
– የተቋውሞ ፁሁፍ ማፃፍ ብሎም ማባዛት አይቻልም፡፡
– አንዳንድ መንገዶች እና ተቋማት ሊዘጉ ይችላሉ፡፡
– ስለታማ ና የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ይከለከላል፡፡
– ሰዎች ነፃ ከቦታ ቦታ የመንቀሳቀስ መብት ከአንዳንድ አካባቢዎች ላይኖራቸው ይችላል፡፡
–  ዜጎች ለደህንነታቸው የሚያሰጋቸው ከሆነ አካባቢያቸውን እንዲለቁ ይደረጋል ፡፡
– ለፀጥታ አካላት ያልተባበረ ተጠያቂ ይሆናል ፡፡
በአጭሩ በህገመንግሥቱ በዲምክራሲያ መብቶች ስር የተዘረዘሩት ለጊዜው ይታገዳሉ፡፡እንደ ሁኔታው ግን ሊያጥርም፣ሊረዝምም ይችላል ፡፡አዋጁ ከመስከረም 28 ጀምሮ ፀንቷል ፡፡አዋጁ ጥቅል የሀገሪቱ ቢሆንም፣በተለየ መንገድ የሚተገበርባቸው አካባቢዎች ይኖራሉ ፡፡

No comments:

Post a Comment