
የኢትዮጵያ የለውጥ ፖለቲካ ኣብዛኛው የተከበበው በማግለል በመፈረጅ በኢሌ ኣውቅልሃለሁ በምቀኝነት በድብቅ የሴራ ፖለቲካና ተመሳሳይ ጉዳዮች ነው። ፖአቲካውን እንደ ግል ዘርፍ ኢንቨስትመት ለመቆጣጠር የሚፈልጉት ባለቅያሪ ማሊያዎች ለባሾች የሆኑ የስድሳዎቹ ፖለቲከኞችና በወያኔ የእሬት የዘር ፖለቲካ የተጋቱ የማያቅራቸው ዘረኞች የሆኑ የወያኔ ስርዓት ሹምባሾች ሲሆኑ እነዚህ ኣካላት ዘጠና ኣምስት በመቶ የዲያስፖራው ኣካል ሲሆኑ ትተውት የሄዱትን ሕዝብ በኣሁኑ ወቅት ያለውን ስነ ልቦና የማያውቁ ናቸው። ትንሹን ትልቅ ኣድርገው የሚጋግሩ የፖለቲካ ድሪቶ የሚያለብሱ ስለሆኡ ለኢትዮጵያ መፍትሔ ኣያመጡም። በስሜት እየተነዱ የኣምባገነኖችን እድሜ ማስረዘም ኣሊያም የርስ በርስ ጦርነት ለመፈብረክ መሮጥ ብቻ ስለሆነ ስራቸው ኣይረቡም።
ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን መፍትሄው በሕዝቦች የጋራ ትግል የሕዝቦች እኩልነት የተረጋገጠባት ኢትዮጵያን መመስረት ዋናው ግብ መሆን ኣለበት ለዚህ ደግሞ ከሕዝብ መሃል ከትግሉ ኣብራክ ውስጥ ያሉ ዜጎች እንጅ በፈረንጅ ኣገሩ የተመቸው ዲያስፖራ በፍጹም መፍትሄ ሊያመጣ ኣይችልም። የጋራ ሃገራዊ ኣጀንዳ ባሌለበት ኣብሮ ለመስራት በመዋዋል ብቻ ለውጥ ኣይመጣም። የጋራ ማኒፌስቶ ለሕዝብ ይፋ ባልሆነበት ውህደትና የትግል ፉጨት ለሕዝብ የሚፈይደው ነገር የለም። የሆያ ሆይ የቅፈላና የወረት ፖለቲካ ለኢትዮጵያ ኣይበጅም። #ምንሊክሳልሳዊ
No comments:
Post a Comment