Thursday, August 31, 2017

ወያኔ እጁ ራጅም ነው በ ደቡብ ኮርያ በስደተኞች የተመሰረተውን መሐበረ ማሪያም አፍሪሶ በራሱ የበግ ለሚድ በለበሱ ሰዎች ልተካ ከጫፍ ለይ ደርሱዋል።


     |



“ሰውን ብትታገልና ብትዋጋ ታሸንፈዋለህ፤ወይም ያሸንፍሃል፤ ቤተክርስቲያንን ግን ማሸነፍ አይቻልም፡፡ ቤተክርስቲያን ሁልጊዜ ትዋጋለች፤ተሸንፋም አታውቅም፡፡ዲያብሎስ ዝናሩን አራገፈ ቀስቱን ጨረሰ ቤተክርስቲያንን ግን አልጎዳትም፡፡” ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
መሐበረ ማሪያም በ ደቡብ ኮርያ በስደተኞች ስመሰረት እጅግ በጣም ልብ በሚነካ አሳዛኝ ሁኔታ ነበር። መሐበሩን ከመሰረቱት ፩፪ ሰዎች አንዱዋ አህቸታው በስደት ባረፈችበት ወቅት ፈጣሪያቸው በስደት ሃገር አንዲያስባቸው አንዲያበረታቸው በመከራና በወጀብ ጊዜ ፈጣርይ ብሪታቱና ጉልበቱን አንዲሰጣቸው ስሙንም ለማሰብ በየቤታቸው በጸበል እና ጻዲቅ መልክ የጀመሩት መሃበር አድጎ ዛሬ ደቡብ ኮሪያ ዉሲጥ ለሚኖሩት ክርስቲያኖች መሰባሰብያቸው ሊሆን በቅቱዋል። መሃበሩ ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ እስክ ቅርብ ጊዜ ድረስ እጅግ በሚያስቀና እና በሚያስደምም ሁነታ በርካታ ተግባራትን ሲያከናዉን ቆይቱዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን የአይናችሁ ቀለም አላማረኝም የሚለው ወያኔ ለትምህርት ወደ ደቡብ ኮሪያ በምልካቸው አባላቱ በኩል መሃበሩ ግራ የተጋባና ያልተግባባ በማድረግ በራሱ ሰሪጎ ገቦች በኩል የመሃበሩን አካሄድ ጠምዝዞ ወደሚፈልግበት አቅጣጫ ለመምራት ኢንድሁም ሰው እንቅልፉን አቶ አካሉን አጉድለው መከራዉን እየበላ ለቤተክርሲቲያን ማሰርያና ሙዳዬ ሚጹዋት የሚሰጠዉን ገንዘብ ለመቀራመት ወኪሎቹን አስከ መሃበሩ አመራር በማስረግ ከቻለ ከኢምባስው ቀጥለው መሃበሩን ሁለታኛ ቆንጽላ ጺፈት ቤት ለማዲረግ ካልሆነ ፊርኪስኪሱን ለማውጣት ተግቶ እየሰራ ይገኛል።  ድሮ ሰው ስማርና ስመራመር ለሃገር ዋልታና ማገር ይሆናል በአሁን ሰዓት ግን ወያኔ በራሱ ልክ ሰፊቶ የምያስተምራቸው ተማርዎቹ እንደ ዕንቦጭ አረም የሚለመልመዉን የሚያምረዉን ሁሉ ማጥፋት ስራቸው አደርገዉታል።ይህን ግዜ መማሩስ ምን ይተጠቅማል ብለን ልንጠይቅ አንችላለን። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንደዚህ ቢሎ ይመክረናል ተወዳጆች ሆይ፦ ጥበባችሁ ለሥጋችሁም ለነፍሳችሁም የሚጠቅም እንጂ በዚህ ዓለምም ይኹን በሚመጣው ዓለም የሚጎዳችሁ አይኹን፡፡  ነገር ግን የወያኔ ተላላክ ምሁራኖች ዛሬን መኖር እንጅ ነገን ማሰብ ያልፈጠረባቸው ዱኩማን የተማሩትን ትምህርት ለተንኮል እና ለጉዳት ይጠቀሙታል። የሰማያዊ እሳቤያቸውን ከአፈቸው እንጂ ከልባቸው መንግለው ጥለዉታል። አንዳንዴ ሳስባቸው ወያኔ ሆይ በደደቢት የምትኖር ብለዉ ልማታዊ ጸሎት ሁላ የሚያደርጉ ይመስሉኛል። አሁን ጥያቄው በተለያየ አለም ላይ የምትኖሩ ኦርቶዶክስ ክርሲቲያኖች መሃበሩን የመታደግ ሃላፊነት አለባችሁ። ወያኔ መሃበሩን የደደቢት ክፊለ ጦር ለማድረግ የቀራት ጊዜ በጣም አጭር ነው። ስራ አስፈጻሚው ኮሚቴ ዉስጥ ህዝበ ክርስትያኑ ሳይመርጣቸው በራሳቸው ስልጣን ዋያኔዉያንን የሰገሰጉት ሳያንስ የማሃበር ደንብ አዘጋጅተናል በሚል ሺፋን ገና ህዝበ ክርስትያኑ ያልተወያየበተን ደንብ የስራ አስፈጻሚው ኮሚቴ በራሱ አጽድቁዋል በማለት  መሃበሩን ከመጀመሪያው የመሰረቱትን ነባር ኮሚቴ አባላት በማሰናበት በቁዋምነት የወያኔ አባላተን በመመደብ አስከዛሬ የተሰበሰበውን ገንዘብ እጃቸው ለማስገባትና ሃገር ቤት ልማት ይከናወንበታል በሚል ሰበብ ገንዘቡን የዉሃ ሽታ ለማድርግ ዝግጅታቸዉን ጨርሰው እነሱ እንደምሉት የይስሙላ ምርጫ ለማድረግ በመጠባበቅ ላይ ናቸው።
ንቁ መሃበሩን እንታደግ።
የ እግዚሃብሄር ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን።

Tuesday, August 29, 2017

በሚኢሶ በኦሮሞ አርሶ አደሮችና በሱማሌ ልዩ ታጣቂ ሃይል ውጊያ ተከፈተ-ቄሮዎች ለሀገር አቀፉ አድማ ዝግጁ ነን አሉ – በወንድወሰን ተክሉ


By ሳተናውAugust 29, 2017 07:59


 

በምስራቅ ኦሮሚያ ዞን በሀረርጌ ሚኤሶ ሁለት ቀበሌዎች ውስጥ በኦሮሞ አርሶ አደሮችና በሱማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ ሚሊሺያ መካከል ለሰዓት የዘለቀ ውጊያ መካሄዱን ኢሳት ከስፍራው የነበሩትን ተሳታፊዎች ድምጽ ጠቅሶ የዘገበ ሲሆን የግጭቱም መንስኤ የድንበር ውዝግብ እንደሆነ ለማወቅ ተችላል።
ባለፈው ሳምንት ከረቡእ እስከ ዓርብ ለሶስት ቀናት ዘልቆ የነበረውና በመላ ኦሮሚያ ተግባራዊ የሆነው የስራ ማቆም አድማ ካነሳቸው ሶስት ጥያቄዎች መካከል አንደኛው በሱማሌ ክልል በኩል እየተካሄደ ያለውን ድንበር ዘለል ጥቃትና የመሬት ወረራን መንግስት በአስቸካይ እንዲያቆም የሚጠይቅ ሲሆን በዚህ የመሬት ይገባኛል ውዝግ ላይ ከአካባቢው ነዋሪዎች የተውጣጡ ሽማግሌዎች የአቤቱት ማመልከቻ ይዘው ለጠ/ሚ/ሩ እና ለተወካዮች ምክር ቤት ለመስጠት አዲስ አበባ መሄዳቸው መገለጹ ይታወሳል።
መላው ኦሮሚያ ለሶስት ተከታታይ ቀናት የስራ ማቆም አድማ ከተጥለቀለቀበት አንዱ በሆነው የኦሮሚያና ሱማሌ ክልል የድንበር ግጭት ዳግም አገርሽቶ በሚኤሶ ባሉት ሁለት ቀበሌዎች ላይ ለማጥቃት ከመጣው የሱማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ ሃይል ጋር የአካባቢው አርሶ አደር ለሰዓት ያህል ለመዋጋት እንደተገደዱ ማወቅ የተቻለ ሲሆን በውጊያው ሶስት አርሶ አደሮች የመቁሰል አደጋ እንደገጠማቸውና አንደኛው በጸና በመቁሰሉ ለህክምና ወደ አዳማ እንደተወሰደ ኢሳት ዘግባል።
በእኛ በኩል የረባ መሳሪያ የለንም ያሉት የኦሮሞ አርሶ አደሮች የሱማሌው ልዩ ፖሊስ ግን መንግስት ባስታጠቀው ዘመናዊ መሳሪያ እራሱን ያስታጠቀ መሆንኑ ገልጸው ከፌዴራሉም ሆነ ከኦሮሚያ ክልል ፖሊስም ሆነ ሰራዊት እንዳልተገኘ ነዋሪዎቹ ገልጸዋል።
የሱማሌ ክልል ለረዥም ግዜ በምስራቃዊው የኦሮሚያ ግዛት ባቢሌ ጉርሱም አካባቢ ይገባኛል ያላቸውን የኦሮሚያን ግዛቶች በወረራ ለመቆጣጠር ተደጋጋሚ ውጊያዎች በመክፈት የሚታወቅ ሲሆን የኦጋዴንን ክልል ነዋሪዎችን በተለይም የስርዓቱ ደጋፊና አባል ባልሆኑት ላይ አሰቃቂ እርምጃ በመውሰድ ጭካኔው የሚታወቅ እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በኦሮሚያ ክልል ያሉ ወጣቶች በተለምዶ አጠራር ቄሮዎች እየደረሰብን ያለውን በደል በግላችን ብቻ በመታገል ሳይሆን ከሌሎችም ጋር ተባብሮ በመታገል እንፈተዋለን ብለው እንደሚያምኑ የገለጹ ሲሆን የፊታችን መስከረም የኢትዮጵያዊያን አዲስ ዓመት በታቀደው ሀገር አቀፍ የስራ ማቆም አድማ ላይ ተሳታፊ ለመሆን ተዘጋጅተናልም ሲሉ በተለይ ለኢሳት ገልጸዋል።
ቄሮዎቹ በአማራ ክልል ወጣቶች በተጠራው ሀገራዊ የስራ ማቆም አድማን በንቃት እንደሚሳተፉ ተናግረው ይህን ስርዓት በህብረት ትግል እንጂ በተናጥል ትግል ጥያቄያችንን እንዲመልስ ማድረግ አይቻልም ሲሉ ተደምጠዋል።
በአማራ ክልል ወጣቶች የተጠረው ሀገር አቀፍ የስራ ማቆም አድማ በመጪው መስከረም 2-3 እንደሚካሄድ ይጠበቃል።

ከ50 ሺ ኩንታል በላይ ስኳር ወደ ኬንያ እየተጓጓዘ ነው


ኢሳት ዜና ነሃሴ 23 ፣ 2009 ዓም
ከ50 ሺ ኩንታል በላይ ስኳር ወደ ኬንያ እየተጓጓዘ ነው
በኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የስኳር እጥረት ተፈጥሮ ባለበት ሁኔታ፣ ከወንጂ ስኳር ፋብሪካ መጋዘን ስኳር የጫኑ 125 መኪኖች በኢትዮጵያና ኬንያ ጠረፍ ላይ በምትገኘው ሞያሌ ከተማ ላይ መቆማቸው ታውቛል። በስልጣን ላይ ያለው መንግስት የአገሪቱን የስኳር አቅርቦት መሸፈን ተስኖት፣ ስኳር ከው እያመጣ እንደሚያከፋፍል ቢታወቅም፣ 125 መኪኖች እያንዳንዳቸው 400 ኩንታል በድምሩ 50 ሺ ኩንታል ስኳር በመጫን ወደ ኬንያ እያመሩ ሲሆን፣ በገጠማቸው የቴክኒክ ችግር ምክንያት ላለፉት 25 ቀናት ለመቆም ተገደዋል።
ስኳሩ ከወንጂ ስኳር ፋብሪካ መጫኑና ወደ ኬንያ እንደሚጓዝ ይታወቅ እንጅ የማን ንብረት እንደሆነ ወይም ለአገር ውስጥ ገበያ ሳይቀርብ ለምን እ...ንደሚወጣ የታወቀ ነገር የለም።
እነዚህ በብራይት ድንበር ተሻጋሪ የደረቅ ጭነት አክሲዮን ማህበር ስር የታቀፉ ከ125 በላይ መኪኖች ወንጅ ፋብሪካ ላይ ለ12 ቀናት ሞያሌ ላይ ደግሞ ለ13 ቀናት ስኳሩን እንደያዙ የቆሙ ሲሆን፣ ወደ ኬንያ ለመግባት በመከልከላቸው ለከፍተኛ እንግልት ተዳርገዋል።
እያንዳንዱ መኪና በእቁብና በባንክ ብድር የተገዛ እንደመሆኑ እዳችንን መክፈል አልቻልንም የሚሉት ሹፌሮች፣ መኪኖቹ ላለፉት 25 ቀናት በመቆማቸው ስኳሩ በዝናብ ሊበላሽ እንደሚችል፣ እስካሁን ድረስ ለቆሙባቸው የካሳ ክፍያ ማን እንደሚከፍላቸው እንደማያውቁና ኬንያ ውስጥ ከገቡ በሁዋላ ስኳሩን ቶሎ አራግፈው የመመለስ እድላቸው አንስተኛ መሆኑን ይገልጻሉ። ሹፌሮቹ ስኳሩን ከወንጂ ፋብሪካ መጫናቸውን እንጅ የማን እንደሆነ እንደማያውቁ ይናገራሉ።
ጉዳዩን በማስመልከት ጥያቄ ያቀረብንለት የ ብራይት ድንበር ተሸጋሪ የደረቅ ጭነት አገልግሎት አንድ ሃላፊ መኪኖቹ ስኳር እንደጫኑ ለረጅም ጊዜ ወንጂና ሞያሌ ላይ መቆማቸውን አምነተው፣ ይህም የሆነው የኬንያ ህግ አንድ የጭነት መኪና ከ280 ኩንታል በላይ ጭኖ እንዳይጓዝ ስለሚከለክልና የእኛ መኪኖች ደግሞ እያንዳንዳቸው 400 ኩንታል የጫኑ በመሆኑ ወደ ኬንያ መግባት አትችሉም በመባላችን ነው ብለዋል። መኪኖች የያዙትን ጭነት እንደያዙ ወደ ኬንያ እንዲገቡ እንዲፈቀድላቸው የኬንያ ባለስልጣናትን ለማነጋገር ሙከራ እየተደረገ ሲሆን፣ ይህ ካልሆነ ግን ስኳሩ እየተቀናነሰ እንዲጫን ስለሚደረግ በቅርቡ መፍትሄ ያገኛል ብለዋል። ስኳሩ የማን ንብረት እንዲሆነና ለምን ከአገር እንደሚወጣ ግን የገለጹት ነገር የለም።
የኢትዮጵያ ወርኃዊ የስኳር ፍላጎት ወደ 600 ሺ ኩንታል የሚጠጋ ቢሆንም፣ በአገሪቱ ያሉ ፋብሪካዎች በቀን የማምረት አቅማቸው ከ20 ሺ አይበልጥም።

ልዩ ፖሊስ የሚባለው ቡድን በኦሮሚያ ጭፍጨፋ እያከሔደ መሆኑ ተጠቆመ


    |


 


ልዩ ፖሊስ በመባል የሚታወቀው ታጣቂ ቡድን ከፍተኛ ጭፍጨፋ እያካሔደ እንደሚገኝ ምንጮች ጠቆሙ፡፡ በዛሬው ዕለት ብቻ በኦሮሚያ ምስራቅ ሐረርጌ ሰባት ሰዎች መገደላቸውን የጠቆሙት ምንጮች፣ ጉዳዩ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እየደረሰ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡ በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ ሶማሊያ ክልል በሚገኘው ልዩ ኃይል በተከፈተው የተኩስ እሩምታ፣ ከሲቪል ነዋሪዎች በተጨማሪም ከኦሮሚያ ፖሊሶች መካከል የተገደሉ መኖራቸውን ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡

ያለ ማቋረጥ ግድያ እየፈጸመ የሚገኘው ልዩ ኃይል የተባለው ቡድን፣ ባለፉት ጊዜያት ያለ ማቋረጥ ግድያ ሲፈጽም ቆይቷል፡፡ በዛሬው ዕለት የተፈጸመው ግድያም የሰሞኑ ተከታይ መሆኑን ነው መረጃዎች የሚጠቁሙት፡፡ ልዩ ኃይሉ በሚፈጽመው ግድያ የአካባቢው ነዋሪ መንገሽገሹን የሚገልጹት መረጃዎች፣ ነዋሪው በተደጋጋሚ ለኦሮሚያ ክልል መንግስት አቤቱታ ቢያቀርብም፣ የረባ ምላሽ ማግኘት አልቻለም፡፡
በዚህም የተነሳ በህወሓት ልዩ ትዕዛዝ እና በኢትዮጵያው ሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት ተባባሪነት የሚመራው ልዩ ኃይል፣ ያለ ማቋረጥ ግድያ እየፈጸመ እንደሚገኝ ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡ የዛሬውን ሳይጨምር ባለፉት ጊዜያት በልዩ ኃይሉ የተገደሉ ንጹኃን ሰዎች ቁጥር 61 መድረሱን የገለጹት ምንጮች፣ በልዩ ኃይሉ የሚገደሉ የኦሮሚያ ፖሊሶች ቁጥርም ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ መምጣቱን ይገልጻሉ፡፡
ልዩ ኃይል የተባሉት እነዚሁ ፖሊሶች ከግድያ በተጨማሪ አስገድዶ መድፈር እና ዘረፋ ላይ መሰማራታቸውን የሚገልጹት መረጃዎች፣ በምስራቅ ሐረርጌ እያደረሱ ያሉት ግፍ እጅግ በዝቷል ይላሉ-መረጃዎቹ፡፡ በዛሬው ዕለት ጭፍጨፋ የተካሔደበት የምስራቅ ሐረርጌ ክፍል ሚኢሶ መሆኑን የጠቀሱት ምንጮች፣ ልዩ ኃይሉ ከኦሮሚያ ፖሊስ ጋር ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ ማድረጉንም ምንጮቹ አክለው ገልጸዋል፡፡ ከሞቱ የኦሮሚያ ፖሊሶች በተጨማሪም የቆሰሉ መኖራቸውንም ለማወቅ ተችሏል፡፡

Monday, August 28, 2017

ታላቋ ትግራይን እንድለማመድ የተለቀቀው ካርታና የኢቢሲ ይቅርታ | ቬሮኒካ መላኩ


Filed under     



1~የEBC ን ውሃ የማያነሳ ማስተባበያና ይቅርታ አነበብኩት ። ፈረንጅ ሲተርት እንደዚህ ይላል “Fool me once, shame on you; Fool me twice, shame on me”…( አንድዬ ካታለልከኝ በአንተ አፍራለሁኝ ። ለሁለተኛ ጊዜ ካታለልከኝ ግን በራሴ ቂልነት አፍራለሁኝ ።) ይላል።

በእኔ በኩል EBC የሚያታልለው ንቃተ ህሊና ባለቤት ስላልሆንኩኝ “ይቅርታው ” ይለፈኝ።

2 ~ EBC የሚባለው ተቋም የራሱ የህውሃት እንደሆነ የታወቀ ነው። እንደ ራሱ ንብረት ሲጠቀምበት ነበር ። ፖሊሲውን ያስፋፋበታል። ማኒፌስቶውን ያራምድበታል። አማራን ይኮንንበታል።
በሌላ በኩል EBC ን ማመስገን ይገባል እንደዚህ ያለ ስሜት ኮርኩሮ የሚያቃጥል ድብቅ ሴራ እያቀረበ የደነዘዙ አማሮችን ቀስቅሶ ወደ አማራነት ካምፕ እንድቀላቀሉ ስለአነቃልን መመስገን አለበት።
ለማንኛውም ስህተቱ የተሰራው በፌስቡክ ሳይሆን በቴሌቪዥን ስርጭት ላይ በመሆኑ ይቅርታውም መጠየቅ ያለበት በቴሌቪዥን እንጅ ከጠቅላላው ህዝብ 1% የማይሞላ ህዝብ በሚጠቀምበት በፌስቡክ አይደለም።

3~ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ተተክሎ አማራ ህዝብ ውስጥ የሚቀበር የ Time bomb ፋብሪካ ቶሎ ካልመከነ አማራ በአገሩ Homeless መሆኑ የማይቀር ነው ።
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የመምህርነትና የሰራተኝነት ጭምብል አጠልቆ አዲስ የፖለቲካ መልክአ ምድር ለመፍጠር ፕሮጄክት ቀርፆ አማራን ከባድና ሊወጣው የሚያስቸግር አደጋ ከመደቀኑ በፊት እንደት ማስቀረት እንደሚቻል ማሰብ አለብን።

4 ~የዚህ Time bomb ፋብሪካው ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሲሆን የቦምቡ ማፈንጃ እና መቆጣጠሪያ ሪሞት ኮንትሮል ደሞ የሚመረተው መቀሌ ነው።
አማራ አፍንጫህ ስር መሽጎ “የቦምቦች ሁሉ እናት ” እያመረተ የሚቀብርብህን “መርስኔሪ ” ቶሎ መፍትሄ ካልሰጠህው ማለቅህ ነው። እኛ አሁንም ተኝተናል እነሱ ግን 7ቱንም ቀናት እና 24 ሰአታት አማራን ለማጥፋት እየሰሩ ነው።

5~ አማራ ሆይ በየአመቱ ፣ በየወሩ ፣ በየሳምንቱ በየቀኑ ፣ በየሰአቱ ፣ በየደቂቃው እና በየሰከንዱ እየተሰረቀ እና እየተዘረፈ ያለውን ማንነታችንን ፣ መሬታችንና ርስታችንንርስታችንን ለማስመለስ በአንድ ላይ ካልቆምን መጥፋታችን ነው።

Thursday, August 24, 2017

የካናዳ ኢምባሲ በሐረርና ድሬደዋ እንዲሁም ከሆለታ እስከ አምቦ ዜጎቹ እንዳይሄዱ ማስጠንቀቂያ አስተላለፈ


       




አወዳይ ከተማ ለ2ኛ ቀን ዝግ ናት
(ዘ-ሐበሻ) በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች የተጀመረው የአምስት ቀናት አድማ በዛሬው እለትም በተለያዩ ከተሞች ለሁለተኛ ቀን እየተካሄደ ነው:: በተለያዩ ቦታዎች የስር ዓቱ ወታደሮችና ተላላኪዎች ሱቃቸውን ያልከፈቱትን እያሸጉ እንዲሁም የትራንስፖርት አገልግሎት ያልሰጡትን ደግሞ ታርጋቸውን እየነቀሉ ቢሆንም ውጥረቱ ተባባሰ እንጂ አልበረደም::
ይህን ተከትሎ የካናዳ ኢምባሲ በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚኖሩት ዜጎቹ ባስተላለፈው ማስጠንቀቂያ ክትናንት ጀምሮ ማንኛውም የካናዳ ዜጋ ወደ ሐረርና ድሬደዋ እንዲሁም ከሆለታ እስከ አምቦ ባሉት ከተሞች እንዳይንቀሳቀሱ አዟል::
በኦሮሚያ ከተሞች አሁንም ውጥረቱ እንዳየለ ነው
ጉዳዩን ተከታትለን እንዘግባለን::

በወላይታ አድማ መጀመሩን መረጃ ደርሶናል። ኢሳት -


መረጃ
በወላይታ አድማ መጀመሩን መረጃ ደርሶናል። ከአርባምንጭ ወደ አዲስ አበባ ይጓዝ የነበረው ሰላም ባስ አውቶቡስ ጉዞውን ሰርዞ እንዲመለስ ተገዷል። በአርባምንጭ ከተማ “ ከኦሮሞ ወገናችን ጎን እንቁም” የሚል ወረቀት ተበትኖ አድሯል።

Wednesday, August 23, 2017

በኦሮሚያ የታወጀው የአምስት ቀን የስራ አድማ-በሻሸመኔና አምቦ መኪኖች እየተቃጠሉ ነው ተባለ – በወንድወሰን ተክሉ


By ሳተናውAugust 23, 2017 19:35




በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ ሁለት ሰዓት አከባቢ በሻሸመኔ እና በአምቦ ከፍተኛ የንበረት ቃጠሎ መከሰቱን ከስፍራው ከደረሰን የስልክ መረጃ መረዳት የተቻለ ሲሆን የተቃጠለውም ንብረት የስራ ማቆም አድማ የጣሱ ተሽከርካሪዎች ናቸው ብለዋል።
በመላ ኦሮሚያ ከዛሬ ጀምሮ እስከ እሁድ ድረስ የሚዘለቅ ጠቅላል የስራ ማቆም አድማ ተግባራዊ መሆን የጀመረው ዛሬ ሲሆን በዚህ ዙሪያ የተጠናቀረው ዘገባ እንደሚከተለው ቀርባል።
**ትግሉ ከአቅማችን በላይ በመሆን በህዝብ እጅ ገብታል-ተቃዋሚ ፓርቲዎች።
በመላ ኦሮሚያ ለ5 ቀናት የታወጀው የስራ ማቆም አድማ ዛሬ ተግባራዊ በሆነበት የመጀመሪያው ቀን አጠቃላይ የንግድ ተቃሞች እና የትራንስፖርት አገልግት ሙሉበሙሉ ማለት በሚቻልበት ሁኔታ ከተሞቹን በጸጥታ አጥለቅልቆ እንደዋለ መረዳት ተችላል።
በምስራቅ ኦሮሚያ ጨለንቆ፣ደደር፣አሰቦት፣በዴሳ፣አወዳይ፣ገለምሶ፣ጨርጨር ከተሞች በሙሉ ነዋሪው ቤቱን ዘግቶ እቤት መዋሉን የጀርመን ድምጽና የቪ.ኦ.ኤ ጋዜጠኞች እየደወሉ አረጋግጠዋል።የንግድ ተቃሞች፣የትራንስፖርት አገልግሎት እና እንዲሁም የግል ትላላቅ ድርጅቶችም ሳይቀሩ ተዘግተው እንደዋሉ ለማወቅ ተችላል።
እንደ የቪ.ኦ.ኤ ዘገባ በምስራቅ ኦሮሚያ ካለ ሰው ጋር በስልክ ንግግር ዘገባ ከሆነ በአምስቱ ቀን የስራ አድማ ጥያቄዎቻቸው ካልተመለሰ የመታገያ ስልታቸውን ቀይረው እስከመጨረሻ እንደሚታገሉ ገልጸዋል።
የአምስቱን ቀን የስራ አድማ ያስተባበሩ ሃይሎች አገላለጽ የስራ አድማው ሶስት መሰረታዊ ጥያቄዎችን መሰረት ያደረገ እንደሆነ ለማወቅ የተቻለ ሲሆን በእስር እየተሰቃዩ ያሉ የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱልን፣ኢ-ፍትሃዊ የሆነው የግብር ተመን ይነሳልን እና ያለአግባብ እየተዘረፈና ለሱማሌ ክልልም እየተሰጠ ያለው መሬት በአስቸካይ ይቁም የሚል ጥያቄ ሲሆን ስርዓቱ ግን አንድም የፖለቲካም ሆነ የህሊና እስረኛ የለኝም በሚለው አቃሙ ይታወቃል።
የቪ.ኦ.ኤ ጋዜጠኛ ካነጋገራቸው የተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል አቶ ሙላቱ ገመቹ የኦ.ፌ.ኮ ም/ል ሊቀመንበር “እኛ ይህ እንዳይመጣ መንግስትን በሰላም ተለማመጥን ለመንን ግን የሰማን አልሆነም። አሁን ጉዳይ ከፖለቲካ ድርጅቶች እጅ ወጥቶ በህዝቡ እጅ ገብታል።ከእኛ በላይ የሆነ ነው “ሲሉ ተናግረዋል።
የስራ ማቆም አድማው በሰሜን ፍቼ መስመር በምእራብ ከአስኮ ጀምሮ እስከ ደንቢ ዶሎ ድረስ በተዘረጋው አውራ መንገድ ላይ አንዳችም ትራንስፖርት እንዳልታየ ማወቅ ተችላል። ከአዲስ አበባ ቡራዪ የታክሲ አግልግሎት የሌለ ሲሆን በደቡብ ወሊሶ፣ሻሸመኔ፣አሩሲና በጅማ በስራ ማቆም አድማው ጸጥ እረጭ ብለዋል።
በመንግስት በኩል አድማውን ለማክሸፍ ሰራዎቱን በማሰማራት ነጋዴዎችን በግድ እንዲከፍቱ ሲያስገድድ የታየባቸው ከተሞች ቁጥር ትንሽ እንዳልሆነ መረዳት የተቻለ ሲሆን የማሸግ ተግባር መፈጸሙንም መረዳት ተችላል።
በአምቦ፣በሻሸመኔ፣በወሊሶ፣በነቀምት፣በምስራቅ ኦሮሚያ ወታደሮች በግድ ለማስከፈት የሞከሩባቸውና የማሸግ ተግባር የፈጸሙባቸው ከተሞች ናቸው።በሻሸመኔ የተሰማሩት የስርዓቱ ታጣቂዎች ህዝቡን እቤት መቀመጥ አይቻልም እያሉ ደግሞም ሁለት ሶስት ሆናችሁ መሄድ አይችልም በማለት እስርሰበርሱ የሚቃረን ህግ እንደሚያዙ ነዋሪዎች ይናገራሉ።
የኦሮሚያ ግዛት በኢ-ፍትሃዊነቱ የታወቀውን እና በጠ/ ሚ ሃይለማሪያም ደሳለኝ በሌቦች የተተመነና 40%ትክክል ያልሆነ በተባለው ግብር ተመን እንደ አቻው የአማራ ግዛት ያለአግባብ የተጫነበት ሲሆን መሬቱን ለሱማሌ ክልል እየተሰጠበት በአስር ሺህ የሚቆጠሩ ልጆቹ በእስር ቤት እየማቀቈበት ያለ ግዛትና ህዝብ እንደሆነ ይታወቃል።

በተለያዩ የኦሮምያ ክልል ከተሞች የተጠራው የ5 ቀን የስራ ማቆም አድማ ተጀምሯል።

ዜና
በተለያዩ የኦሮምያ ክልል ከተሞች የተጠራው የ5 ቀን የስራ ማቆም አድማ ተጀምሯል። የንግድ መደብሮች ተዘግተዋል። የትራንስፖራት አገልግሎት ተቋርጧል። አድማውን ለማሰናከል የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ ነጋዴዎችን ለማስፈራራት እየሞከረ ቢሆንም፣ እስካሁን በፍርሃት የንግድ ድርጅቱን የከፈተ ነጋዴ የለም።

የባህርዳር አውቶቡሶች አድማውን ተቀላቀሉ | ♦ከአማራ ክልል ወደ ኦሮምያ ክልል የሚሄድ መኪና አቁመዋል!


          
      


ሙሉነህ ዮሐንስ እንደዘገበው
ነሃሴ 16 2009 | በመላ የኦሮሞ ክልል የተጠራውን የመጓጓዣ የስራ ማቆም አድማ ጥሪ ለአማራው ክልልና ለሌሎችም መተላለፉ ይታወሳል። ይህን መሰረት አድርጎ ከባህርዳር ወደ ነቀምትና ወደ ተለያዩ ቦታወች የሚሄዱ መኪኖች ለመንገደኛች ትኬቱን መልሠዋል። አድማ ስለተጠራ መኪኖቻን ይመቱብናል ጥሪውን መሰረት አድርገን ከስራ ታቅበናል ብለዋል። ከአማራ ክልል ወደ ኦሮምያ ክልል የሚሄድ መኪና አቁመዋል። ይህ ለወያኔ እጅግ አስደንጋጭ ሲሆን ለነፃነት ናፋቂው የኢትዮጵያ ህዝብ ደግሞ ትግሉ ሃገራዊ ገፅታው እየተሳሰረና እያደገ መምጣቱን ያረጋግጣል።

Tuesday, August 22, 2017

ሙስና ገንዘብ መቀበል ወይም መስረቅ ብቻ ኣይደለም ፡፡ የመንግስት ስልጣንን በዝምድና መከፋፈልም አይን ያወጣ ሙስና ነው – ብርሃን ኪሮስ


By ሳተናውAugust 22, 2017 04:13



ጉዳዩ፡ በኢትዮጵያ አየተካሄደ ስላለው ሙስና ይመለከታል

የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አባይ ወልዱን እና ባለቤቱን ወ/ሮ ትርፉ ኪዳኔን እንደ ምሳሌ ብንወስድ ለባልና ለሚስት ከፍተኛ የመንግስት ስልጣንን ያንበሳውን ድርሻ መቸር ማለት ስልጣንን ተገን ኣድርጎ መጠቃቀም ኣና ሙስናዊ ኣድሎ ኣንዳለ ያሳያል፡፡
ወ/ሮ ትርፉ ኪዳን በኣምባሳደርነት እዚህ አውስትራሊያ ተሹማ ከመጣች ሁለት ዓመት ቢሆን ነው ሆኖም ወ/ሮ ትርፉ ከተመደበችበት ስራ በላይ ትኩረት ሰጥታ የምትስራው አውስትራሊያ ነዋሪ ከሆኑ ጥቂት ኢትዮጵያን ግለሰቦች ጋር  በመመሳጠር እና ብዙ ሚሊየን ዶላር ኢንቭስት በማድርግ ሪል ስቴት ንግድ ላይ ነው ፡፡ እዚሀ አውስትራሊያ ከመምጣትዋ በፊት የዘረፈችውን እና ኣንዲሁም በባለቤትዋ  እየተዘረፈ በኢምባሲ በኩል የሚሸሸውን የሀገር ሀብት የኣምባሳደርነትዋን ሹመትዋን ተገን በማድረግ በተለያየ ኣውስትራልያ ሰቴት በሚኖሩ ሶስት ግለሰቦች ሰም ከፍተኛ ንግድ እያካሄደች ነው ያለው፡፡
ከሶስቱ ኣንዱ የሆነው ሜልበርን ከተማ የሚገኘው አቶ ኬኔዲ ገብረየሱስ የተባለው  ግለስብ  ከጥቂት ዓመት በፊት ኣንደማንኛውም የሜልበርን ነዋሪ ኢትዮጵያዊ ኖርማል ህይወት ይኖር የነበረ ነው ፡፡  በአጭር ጊዜ ውስጥ ግን በሚሊዮን ዶላር የሚገመቱ የመኖርያ ቤቶችን ኣና የንግድ መደብሮችን በመግዛት እና በመገንባት ለምሳሌ በቅርቡ ሜልበርን የሚገኘውን ዳሽን ኢትዮጵያ ሬስቱራንት ህንፃን ግዝቶ በማከራየት መጠነ ስፊ ንግድ እያካሄደ ይግኛልልላው ። አቶ ኬኔዲ ከአምባሳደርዋ ጋር በጣም ቅርበት ያለው ከመሆኑም በላይ  በየቦታው የአምባሳደርዋ ዋና አጃቢ በመሆን የሚታየው አሱ ነው፡፡
ኣንዲሁም ከአምባሳደርዋ ጋር በመመሳጠር በስፋት ቢዝነስ እያካሄደ ያለው  ሌላው የሜልበርን ነዋሪ  የሆነው አቶ ማማየ ናቸው፡፡ እነዚህ ሁለት ግለሰቦች በአንድ ጊዜ ተስፈንጥረው ወደ ሚሊየነርንት የተሸጋገሩበት ኣና የሀብታችው የእደገት ፍጥነት በጣም አስገራሚ ስለሆነ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚያውቀውን መረጃ ሜልበርን ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ በመስጠት ያለ አግባብ ኣየተዘረፈ ያለውን የሀዝብ ሀብት ዝርፍያ ለማስቆም ሀገራዊ ግዴታችንን መወጣት አለበን።

በባህርዳር ግብር ያልከፈሉ ነጋዴዎች በመታሰር ላይ መሆናቸው ታወቀ


By ሳተናውAugust 21, 2017 19:59



(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 15/2009)በባህርዳር ግብር ያልከፈሉ ነጋዴዎች በመታሰር ላይ መሆናቸው ታወቀ።
በተለያዩ ክፍለከተሞች በሚገኙ የቀበሌ እስር ቤቶች ከ500 በላይ ነጋዴዎች ታስረው እንደሚገኙ የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
የባህርዳር ፖሊስ ቦምብ ያፈነዱትን ይዣለሁ በማለት የጀመረው የቪዲዮ ቀረጻ የተጠናቀቀ ሲሆን በቅርቡ በክልሉና በብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ እንደሚቀርብ ታውቋል።
በሌላ በኩል በተለያዩ የአማራ ክልል አካባቢዎች ጥብቅ ፍተሻ ሲደርግ ውሏል። በባህርዳር ነዋሪው የሌሊት ጥበቃ ሮንድ በፈረቃ እንዲደርሰው ሊደረግ ነው።
ግብር መክፈል ያልቻሉ አንዳንድ ነጋዴዎች ሱቃቸውን ዘግተው እየተሰወሩንም ነው ተብሏል።
ባህርዳር አሁንም በውጥረት ላይ መሆኗ ይነገራል። ነጋዴዎች በጅምላ እየታሰሩ ናቸው። በመቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች እየታፈኑ ተወስደዋል።
የኢሳት የመረጃ ምንጮች እንዳረጋገጡት በባህርዳር በየቀበሌው በሚገኙ እስር ቤቶች በትንሹ 500 የሚሆኑ ነጋዴዎች ታስረዋል።
የተራዘመው የግብር መክፈያ ቀነ ገደብ ካበቃ በኋላ፡ በየሱቅና መደብሩ የሄዱት የመንግስት ታጣቂዎች ግብር አልከፈላችሁም በሚል ነጋዴዎቹን እያፈሱ መውሰዳቸው ታውቋል።
ነሀሴ 1 የተገደሉ ሰማዕታትን ለማሰብ ከተጠራው የስራ ማቆም ጋር በተያያዘ የታሰሩት ከፍተኛ ነጋዴዎች በዋስ መለቀቃቸው በተገለጸበት በዛሬው ዕለት ግብር ያልከፈሉ ነጋዴዎች በየእስር ቤቱ መግባታቸውን ለማወቅ ተችሏል።
በሌላ በኩል ጨለማን ተገን በማድረግ በተለያዩ የባህርዳር ክፍሎች የሚገኙ ወጣቶችን በማፈስ ወደአልታወቀ ቦታ መወሰዳቸውን ያገኘነው መረጃ አመልክቷል።
ወጣቶቹ አመጽ ታስተባብራላችሁ፡ በሚል የታፈሱ ሲሆን ከዚህ ቀደም በነበረው ህዝባዊ ንቅናቄ ምክንያት ታስረው በብር ሸለቆ ማሰልጠኛ ካምፕ ቆይተው የተፈቱትም በድጋሚ መታሰራቸው ታውቋል።
በሌላ በኩል በቅርቡ በተከታታይ የደረሱትን የቦምብ ፍንዳታዎች ፈጽመዋል በማለት 17 ግለሰቦችን ማሰሩን የባህርዳር ፖሊስ አስታውቋል።
አደጋውን እንዴት እንዳደረሱ የሚያስረዳ ዘጋቢ ፊልም እየተዘጋጀ መሆኑን የገለጹት የኢሳት ምንጮች አንደኛው ወጣት በዚህ ዓይነት ድራማ አልሳተፍም በማለቱ ለእስር እንደበቃ መገለጹ ይታወሳል።
ከግብር ጋር በተያያዘ በሌሎች የምስራቅ ጎጃም ከተሞች ፍጥጫው አሁንም የቀጠለ ሲሆን እስሩን በመሸሽ ነጋዴዎች ከአከባቢው የተሰወሩ መሆናቸውን ከደረሰን መረጃ ለማወቅ ተችሏል።
ሱቃቸውን ዘግተው ሀገር ጥለው የተሰደዱም እንዳሉ የኢሳት ምንጮች ያረጋገጡ ሲሆን በአብዛኛው የአማራ ክልል አካባቢዎች ግብር እንዳልተከፈለ መረጃዎች አመልክተዋል። በቅርቡ አንድ የደጀን ከተማ የመንግስት ሃላፊ ግብር የከፈለው ነጋዴ ከ4በመቶ አይበልጥም ማለታቸው ይታወሳል።
በሌላ በኩል በደጀን መንገድ፡ በዓባይ በረሃና ወደ ቤንሻንጉል ጉምዝ በሚወስዱ መንገዶች ላይ ጥብቅ ፍተሻ ዛሬ ሲካሄድ እንደነበረ የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።
ድንገተኛ ፍተሻው ታይተው በማይታወቁ ትግርኛ ቋንቋ ተናጋሪ በሆኑ ወታደሮች የተካሄደ ነው ተብሏል። ምክንያቱ ምን እንደሆነ አልታወቀም።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ በባህርዳር በየቀበሌው በሚገኙ እና በተለያየ ቦታ በየጊዜው በሚመደቡት የማህበረሰብ ፖሊሶች አማካኝነት ማንኛውም ሰው ሮንድ(የምሽት ጥበቃ) እንዲያደርግ በወረፉ ተመድቦ ግዴታ እንደተጣለበት ከምንጮች ዘገባ ለማወቅ ተችሏል። ይህን ግዴታ የማይወጣ የገንዘብ ቅጣትና በቀበሌ በኩፖን የሚገኙ ስኳርና ዘይት የሚከለከል እንደሚሆን ተገልጿል።
ምናልባትም ሮንድ ያልወጣ በፀረ ሰላም ሀይሎች ተባባሪ ተብሎ የእስር እርምጃ ሊወሰድበት ይችላልም ተብሏል።
በቀበሌ ካድሬዎች እና የኮሚኒቲ ፖሊሶች አማካኝነት አዲስ ዙር የቤት ለቤት ምዝገባ የተጀመረ ሲሆን የተከራዮች መታወቂያ ጨምሮ የቤተሰብ አድራሻ ተመዝግቧል።
እነዚህ ተከራዩችም ሮንድ እንዲወጡ ግዳጅ ተጥሏል። ሮንድ የሚወጡትን ደግሞ በየቀጠና የሴቶች ተጠሪዎች ከሚኒሻ እና ከፖሊሶች ፣ ልዩ ሃይል ጋር በሚደረግ የምሽት ጥበቃ እንዲሰልሉ እየተደረገ ይገኛል።
ባለፈው ሳምንት በጎንደር በተደረገው ስብሰባ የተለየ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ለጠየቁት የትግራይ ተወላጆች የአማራ ክልል ፖሊስ ፍቃደኛ አለመሆኑን ተከትሎ የአማራ ክልል ደህንነት ሰራተኞች ለስልጠና አዲስ አበባ መግባታቸውም ይነገራል።
የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ መንግስት በአማራ ክልል ደህንነት፡ ልዩ ሃይልና ፖሊስ ላይ እምነት ያጣ ሲሆን ተቃዋሚዎች የተሰገሰጉበት ሲልም በስጋት እንደሚመለከተው ታውቋል።
በባህርዳር፡ በጎንደርና በሌሎች ተቃውሞ ተለይቷቸው በማያውቁ የአማራ ክልል አካባቢዎች ትግርኛ ተናጋሪ የሆኑ ታጣቂዎች እንዲሰማሩ መደርጋቸው ስርዓቱ የገባበትን አጣብቂኝ ያሳያል ብለዋል ታዛቢዎች።

Friday, August 18, 2017

የሕዋሃት ታጋዮች አጥንታቸውን የከሰከሱት ትግራይ እንድትለማ ነው በማለት በአንድ ወቅት ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ መናገራቸውን የአዲስ አበባ ኢህአዴግ ጽሕፈት ቤት በድረገጹ አስታወቀ።


(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 11/2009) የሕዋሃት ታጋዮች አጥንታቸውን የከሰከሱት ትግራይ እንድትለማ ነው በማለት በአንድ ወቅት ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ መናገራቸውን የአዲስ አበባ ኢህአዴግ ጽሕፈት ቤት በድረገጹ አስታወቀ። ጽህፈት ቤቱ በፌስቡክ ድረገጹ እንደገለጸው በ1984 በትግራይ መቀሌ የሕወሃት ምስረታ በአል ሲከበር አቶ መለስ ለትግራይ ወጣቶች የተከሰከሰው አጥንት ለትግራይ ልማት ሲባል መሆኑን በይፋ ተናግረዋል። በዚያን ወቅት አቶ መለስ እኔ የተፈጠርኩት ከዚህ ወርቅ ህዝብ በመሆኑ እድለኛ ነኝ በማለት ከሌላው ኢትዮጵያዊ የተለየን ነን በሚል ንግግር ማድረጋቸው ይታወሳል። የአቶ መለስ ዜናዊን 5ኛ አመት የሙት አመት ዝክረ መለስ በሚል በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበረ ያለው የሕወሃት/ኢህአዴግ መንግስት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ያደረጓቸውን ንግግሮች እንዲታወሱ በማድረግ ላይ ይገኛል። በዚህ ሁኔታም የአዲስ አበባ ኢሕአዴግ ጽህፈት ቤት በድረገጹ አቶ መለስ የሕወሃት ታጋዮች አጥንታቸውን የከሰከሱት ትግራይን እንድትለማ ለማድረግ ነው ማለታቸውን አስታውሷል። አቶ መልስ በወቅቱ ያደረጉት ንግግር የሕወሃት ትግል ከትግራይ ልማት ውጪ ሌላ አጀንዳ እንዳልነበረው የሚያሳይ መሆኑን እንዳመላከተ ታዛቢዎች በመግለጽ ላይ ናቸው።

አብዛኞቹ የትግራይ ተወላጆች ባለሃብቶቹ የተበደሩትን ገንዘብ በመቀሌና በአዲስ አበባ ህንጻ ሰርተውበታል

(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 11/2009) በጋምቤላ ክልል መሬት ተነጥቀው የነበሩ 186 ባለሃብቶች በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት ትእዛዝ ተመለሰላቸው። በክልሉ ከነበሩ 6መቶ ያህል ኢንቬስተሮች የያዙትን መሬት በአግባቡ አላለሙም በሚል 296 ያህሉ ይዞታቸውን በጋምቤላ መስተዳድር ተነጥቀው ነበር። ባለሃብቶቹ ይህንኑ በመቃወም ቅሬታ በማቅረባቸው በአቶ አርከበ እቁባይ የተመራው አጣሪ ኮሚቴ በተለይ የትግራይ ባለሃብቶች ናቸው ለተባሉት 186 ባለሃብቶች መሬታቸው እንዲመለስ ተደርጓል። በኢትዮጵያ ባለው ህግ መሰረት የመሬት ሊዝ ኮንትራትን ማስተዳደር የሚችሉት ክልሎች ናቸው። በጋምቤላ ክልል መሬትን ለኢንቨስትመንት ወስደው አላለሙም የተባሉትን 296 ባለሃብቶች ይዞታቸውን የነጠቀውና እንደገና እንዲመለስ ያደረገው ግን የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት መሆኑ ታውቋል።–የክልሉ...ን ስልጣን በመንጠቅ። በጋምቤላ ካሉ 6መቶ የእርሻ ባለሃብቶች 296 የሚሆኑት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በተቋቋመውና በአቶ አለማየሁ ተገኑ ይመራ በነበረው አጥኚ ኮሚቴ መሬታቸው መነጠቁ ይታወሳል። ባለሃብቶቹ መሬታቸው ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ ልማት ባንክ የተፈቀደላቸው ብድርም ተሰርዞባቸው ነበር። አብዛኞቹ የትግራይ ተወላጆች የሆኑት እነዚሁ የጋምቤላ ባለሃብቶች ከፍተኛ ቅሬታ በጠቅላይ ሚኒስትሩና በአጥኚው ኮሚቴ ላይ በማቅረባቸው ሌላ አጥኚ ኮሚቴ በአቶ አርከበ እቁባይ እንዲመራ ተደርጎ ጉዳያቸው እንደገና እንዲታይ መደረጉ ታውቋል። በዚሁም መሰረት ቅሬታቸውን እንደገና ያቀረቡት ከ296ቱ መካከል 190ዎቹ ብቻ ነበሩ። የነዚሁ ቅሬታ አቅራቢዎች አቤቱታ ተቀባይነት አግኝቶ ከ4ቱ በስተቀር የ186ቱ ባለሃብቶች መሬት እንዲመለስ ተድርጓል። ይህም የተደረገው መሬቱን የተነጠቁት ያለአግባብ ነው በሚል እንደሆነ ፎርቹን ጋዜጣ ዘግቧል። በዘገባው እንደተመለከተውም ባለሃብቶቹ መሬቱን በአግባቡ ያላለሙት በመሬት መደራረብ፣በፍርድ ቤት እገዳና በመልካም አስተዳደር ችግሮች ነው። ይህም ሆኖ ግን በአቶ አለማየሁ ተገኑ የተመራው የጥናት ኮሚቴ ባለሃብቶቹ የተበደሩትን ገንዘብ በመቀሌና በአዲስ አበባ ህንጻ ሰርተውበታል ከታለመለት አላማ ውጭም አውለውታል ማለቱ ይታወሳል። ይህ ተዘንግቶ በአቶ አርከበ እቁባይ የተመራውና 13 አባላት ያሉት ኮሚቴ ባለሃብቶቹ ተበድረዋል በሚል መሬቱን የጋምቤላ ክልል ለባለሃብቶቹ እንዲመልስ በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት በኩል ትእዛዝ እንዲሰጥ አድርጓል። እስካሁንም የ27ቱ ባለሃብቶች መሬት ሲመለስ የቀሪዎቹም ይቀጥላል ተብሏል። በልማት ባንክ በኩል የታገደባቸው ብድር እንደገና እንዲለቀቅላቸውም ጥረት እየተደረገ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል።

Wednesday, August 16, 2017

የአማራ ክልል ፖሊስ የህወሃት ደጋፊ የትግራይ ተወላጆች “ ልዩ ጥበቃ” እንዲደረግላቸው ያቀረቡትን ጥያቄ ውድቅ አደረገው


By ሳተናውAugust 16, 2017 09:00     



(ኢሳት ዜና ነሃሴ 9 ቀን 2009 ዓም)
በባህርዳር ከተማ የሚኖሩ የህወሃት ደጋፊ የሆኑ የትግራይ ተወላጆች በክልሉ ያለው የጸጥታ ሁኔታ በድጋሜ ስጋት ላይ የጣላቸው መሆኑን ለክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ባለስልጣናት በተወካዮቻቸው አማካኝነት ተናግረዋል። የህወሃት ደጋፊዎቹ በክልሉ የሚታየው ሁኔታ እያስፈራቸው እንደመጣ፣ ከዚህ በፊት የተከሰተው አደጋ በድጋሜ ሊከሰት የሚችልበት እድል እንዳለ በመግለጽ፣ ክልሉ እነሱን ለመጠበቅ የሚሰራው ስራ ባለመኖሩ ወቀሳ አቅርበዋል። የክልሉ የጸጥታ አካላት የተለዬ ጥበቃ ሊያደርጉላቸው እንደሚገባ ቢያሳስቡም፣ የክልሉ ፖሊስ ግን ማሳሰቢያውን ወደ ጎን በማለት ለእነሱ የተለዬ ጥበቃ እንደማያደርግ ገልጿል። የክልሉ ፖሊስ፣ በክልሉ ማንኛውንም የጸጥታ መደፍረስ ለመቆጣጠር እየሰራ መሆኑን ገልጾ፣ ጥበቃ ከተፈቀደለት ባለስልጣን እና ከመንግስት ተቋማት ውጭ በግለሰብ ደረጃ የሚደረግ ጥበቃ እንደማይኖር ገልጿል። የክልሉ ፖሊስ የሰጠው መልስ የህወሃት ደጋፊዎችን አላስደሰተም።
ከዚህ በፊት የህገ ወጥ መሳሪያዎች ቁጥጥር ቢመደረግበት ጊዜ ለከተማ ነዋሪዎች የተከለከሉ አውቶማቲክ ጠመንጃዎች ከበርካታ ጥይቶች ጋር በእነዚሁ የህወሃት ደጋፊ ወገኖች እጅ ቢያዙም፣ በአካባቢው ከሚገኘው መኮድ እየተባለ ከሚጠራው የመከላከያ ካምፕ የሚመጡ ወታደራዊ አዛዦች የሚያዙትን ጠመንጃዎች ለስራ ተብለው የተሰጡ የመንግስት መሳሪያዎች መሆናቸውን እየገለጹ መሳሪያዎቹ ለባለቤቶቹ እንዲመለሱ ሲያደርጉ ቆይተዋል። የክልሉ ፖሊስ ይህንን ድረጊት ጠንቅቆ ቢያውቅም እርምጃ ለመውሰድ ሲደፍር አልታየም።
የአሁኑ የልዩ ጥበቃ ጥያቄ ህወሃት፣ በጸጥታ መደፍረስ ስም ከዚህ ቀደም ሲወስዳቸው የነበሩትን ሁለቱን ህዝቦች የሚጋጩ ስራዎችን ለመስራት ማቀዱን እንደሚያመለክት ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ወገኖች ይገልጻሉ።
በተያያዘ ዜና ባለፈው እሁድ የክልሉ የመረጃ አካላት ከዞን ፖሊስ መምሪያ ሃላፊዎች ጋር ጎንደር ላይ ባደረጉት ስብሰባ፣ በአገዛዙ ላይ ስለተቃጣው አደጋና የጸጥታ መደፍረስ ተወያይተዋል። የክልሉ የደህንነት አካላት ስራቸውን በተገቢው ሁኔታ እየሰሩ አይደለም በሚል ወቀሳ ቀርቦባቸዋል። በባህርዳር ከተማ የሚደረሰውን የቦንብ ፍንዳታ ማስቆም አለመቻሉ የግምገማው ዋና አጀንዳ የሆነ ሲሆን፣ በአደባባይ እየተዛተ የሚደረገው ፍንዳታ በክልሉ ያለው ችግር ውስብስብና ሰፊ መሆኑ ተገልጿል። ኢሳት ቀደም ብሎ እንደዘገበው ፍንዳታውን አደረሱ ተብለው የተያዙ ሰዎች ከጉዳዩ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው ሰዎች መሆኑ በስብሰባው ላይ የተወሳ ሲሆን፣ ይህም በደህንነቱ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የመረጃ ክፍተት መኖሩን ያሳያል ተብሎአል።
በአዲስ መልክ የተዋቀረው የጸጥታ ስራ ምንም ለውጥ አለማምጣቱ በስብሰባው ላይ ተደጋግሞ ተነስቷል። በክልሉ ያሉት አብዛኞቹ የደህንነት ሰራተኞች እና የፖሊስ አባላት የህወሃትን የበላይነት እየተቃወሙ እንደሆኑ የሚደረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።

Tuesday, August 15, 2017

የኢሊሊ ሆቴል ባለቤት አቶ ገምሹ በየነ ተሰውረዋል


ዋዜማ ራዲዮ- በኢህአዴግ ታሪክ ሦስተኛው እንደሆነ የተነገረለት የጸረ ሙስና ዘመቻ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ አይነኬ የሚመስሉ ባለሐብቶችንና ድርጅቶችን በር ማንኳኳት የጀመረ ይመስላል፡፡ በአገሪቱ ግዙፍና ስመጥር የመንገድና የሕንጻ ተቋራጮች ሒሳባቸው እንዳይንቀሳቀስ በፍርድ ቤት እግድ መጣሉ ለዚህ እንደማስረጃ እየተጠቀሰ ነው፡፡
ከነዚህ ግዙፍ ተቋራጮች መካከል ስመጥሮቹ አሰር ኮንስትራክሽንና ገምሹ በየነ (Gemecon) ደረጃ አንድ ጠቅላላ ኮንትራክተር ይገኙበታል፡፡ የገመኮን መንገድ ተቋራጭ ድርጅቱ ባለቤት አቶ ገምሹ በየነ ከጥቂት ቀናት ጀምሮ የት እንደገቡ አልታወቀም ተብሏል፡፡ የዋዜማ ሁነኛ ምንጮች እኚህ ስመጥር ባለሀብት ከአገር ሾልከው ሳይወጡ እንዳልቀረ ይጠረጥራሉ፡፡ ምክንያታቸውን ሲያስረዱም ባለፉት ሰባት ቀናት ውስጥ ቢሯቸው አለመግባታቸውን ያነሳሉ፡፡

አንድ የኢሊሌ ሆቴል የጥበቃ ባልደረባ ከሁለት ሳምንት በፊት ጸጉራቸውን በራሳቸው ሆቴል ውስጥ በሚገኝ የውበት ሳሎን ሲስተካከሉ እንደተመለከቷቸውና ከዚያ ወዲህ ግን ወደ ሆቴላቸው ዝር እንዳላሉ ማረጋገጫ ሰጥተዋል፡፡ በስም መጠቀስ ያልፈለገ ሌላ የሆቴሉ ማኔጅመንት አባል ‹‹ለዕቃ ግዢ ከአገር መውጣታቸውን ነው የማውቀው፤ በእርግጠኝነት ይመለሳሉ›› ሲል ተናግሯል፡፤
በአገሪቱ ከሚገኙ በጣት ከሚቆጠሩ ባለ አምስት ኮከብ ሆቴሎች አንዱ የሆነውና በካዛንቺስ አካባቢ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (ኢሲኤ) ጀርባ የሚገኘው ኢሌሌ ኢንተርናሽናል ሆቴል በአቶ ገምሹ በየነ ባለቤትነት የተያዘ ግዙፍ ሆቴል ሲሆን ከአዲስ አበባ መስተዳደር በቅርብ አመታት ውስጥ ባገኘው 1690 ካሬ የማስፋፊያ ፕሮጀክት በአገሪቱ ታሪክ የመጀመርያውን ባለ አምስት ፎቅ የመኪና ማቆምያ በ258 ሚሊዮን ብር ገንብቶ በከፊል ለአገልግሎት ክፍት ማድረጉ ይታወሳል፡፡
ከዚህም ባሻገር በቡራዩና በቢሾፍቱ ግዙፍ ሪዞርቶችን ለመገንባት ላይ እንደነበር ይታወቃል፡፡ በመንገድ ግንባታ በአሁኑ ወቅት ከ3 ቢሊየን ብር የማያንሱ ፕሮጀክቶች በእጁ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡ በትግራይና አማራ ክልል ከማሃበሬ እስከ ዲማ፣ ከዲማ እስከ ፈየል ዉሀ፣ እንዲሁም ከአዘዞ እስከ ጎርጎራ፣ከድሬዳዋ እስከ ደዋሌ፣ በዚሁ የመንገድ ተቋራጭ የተገቡ ናቸው፡፡ ገመኮን የመንገድ ተቋራጭ እና የሆቴል ፕሮጀክቱን ጨምሮ አቶ ገምሹ በየነ በሥራቸው ከ7ሺ የማያንሱ ጊዝያዊና ቋሚ ሠራተኞችን ያስተዳድራሉ፡፡
አቶ ገምሹ በየነ የኦሮሚያ ክልል የወጣቶችን አመጽ ለማብረድ በተወጠነው የኦሮሚያ የኢኮኖሚ አብዮት ውስጥ ንቁ ተሳትፎ እያደረጉ ከሚገኙ ባለሐብቶች መካከል አንዱ ሲሆኑ የርሳቸው ድርጅት ከሙስና ጋር በተያያዘ ስሙ መነሳቱ የጸረ ሙስና ዘመቻው ውስጥ የኦህዴድ ከፍተኛ ባለሥልጣናት እጅ እንዳለበት አመላካች እንደሆነ የሚያምኑ በርካቶች ናቸው፡፡

‹‹ብሔራዊ ባንክ 60.5 ቢሊዩን ብር አሳትሞ፣በገበያው ውስጥ ወረቀቱን ሞቅ አድርጎ ዘርቶታል!!!››


ፀ/ት ፂዩን ዘማርያም
ኢትዩጵያ የብር ኖቶች ለማሳተም ጨረታ አወጣች
ሴፕቴምበር 18 ቀን 2011  – እንደ ኦል አፍሪካን ዶት ኮም ዘገባ መሠረት በሴፕቴንበር 14 ቀን 2011 እኤአ (2004ዓ/ም) ዴ ላአ ሩእ፣ፋራንሰስ ቻርልስ ኦበርቱር እና ጊሰኬና ዴቨርይንት ለኢትዩጵያ  ብሄራዊ ባንክ ገንዘብ ለማተም ጨረታ ማቅረባቸውን አስታውቀዋል፡፡  ጨረታው መሠረት 46 ቢሊዩን ብር ዋጋ ያለው ባለ 100ብር ኖቶችና 6 ቢሊዩን ብር ዋጋ የላቸው ባለ 50 ብር ኖቶች  ሲሆኑ የጨረታው አሸናፊ አዲሶቹን የብር ኖቶች በአራት ወራት ውስጥ አትሞ ማቅረብ አለበት፡፡ የብሮቹ ኖቶች አዲስ ዲዛይን ይኑራቸው አይኑራቸው አልተገለጸም፡፡
Ethiopia accepted bids to print more banknotesSep 18, 2011 09:51 AM Category: Africa
According to an article on allAfrica.com dated 14 September 2011, De La Rue, Francois-Charles Oberthur, and Giesecke & Devrient have submitted bids to the National Bank of Ethiopia for printing 46 billion birr worth of 100-birr notes and 6 billion birr worth of 50-birr notes. The winning bidder is expected to deliver the new notes within four months. No word on if the notes will be new designs.
Courtesy of Richard Miranda.

Ethiopia new date (2015) 50-birr note (B333g) and 100-birr note (B334g) confirmed:-Nov 25, 2016
09:31 AM Category: Africa /Aug 30, 2016 08:29 AM Category: Africa
B333g: Like B333f, but new date (2007/2015). Prefix BV.
Courtesy of Kevin Warfel.
B333g: Like B333f, but new date (2007/2015). Prefix BV.
Courtesy of Kevin Warfel.
Ethiopia seeks to print its own banknotes
The websites allAfrica.com and addisfortune.net report that the National Bank of Ethiopia has issued a tender to, first, investigate if the country is capable to print its own banknotes and second, (if the answer is yes) to set up a national banknote printing facility.
The Bank announced a tender two weeks ago to hire an international consultancy firm to conduct a feasibility study for the printing plant on the state owned daily newspaper, The Ethiopian Herald. The main aim of planting the factory is to save the foreign currency that the country is spending to print banknotes in foreign countries. The other reason is to centralise the printing of banknotes in one place, according to a senior official from the Bank (…) Currently, NBE predominantly prints banknote in European countries, mainly in England and France. It has made an order for new banknote, as the notes that are in circulation have become worn out from use. The old notes will be collected and disposed of by burning.”  Steven Wednesday 17 December 2014 at 11:51 am | | news | No comments
B334g: Like B334f, but new date (2007/2015). Prefix EE.
Courtesy of Sejin Ahn.
B334g: Like B334f, but new date (2007/2015). Prefix EE.
Courtesy of Sejin Ahn.
የፈረንሳይ የገንዘብ ኖቶች ማተሚያ ካንፓኒ፤ ዴ ላአ ሩእ፣ፋራንሰስ ቻርልስ ኦበርቱር በፈረንሳይ አገር የሚገኝ የገንዘብ ኖቶች፣ ሚስጢራዊ ህትመት ሥራ ወዘተ የሚሠራ ሲሆን ከ1818 እኤአ ካንፓኒ ተመሠረተ፡፡  የካንፓኒውን የህትመት ሥራ ችሎታ ከካንፓኒው ድረ-ገፅ መረዳት ይቻላል፡፡ ካንፓኒው በሴፕቴምበር 18 ቀን 2011 እኤአ  የባለ 100ና የባለ 50 ኢትዩጵያ የብር ኖቶች ለማተም በወጣው ጫረታ ተወዳድሮ ነበር፡፡ 
François-Charles Oberthür — Wikipédia, https://fr.wikipedia.org/wiki/François-Charles_Oberthür
FrançoisCharles Oberthür (1818, Strasbourg – 1893, Paris VI) est un imprimeur français et le … Autour des bâtiments de la rue de Paris acquis en 1858, il installe ses usines de l’imprimerie Oberthur ( no 76 à 80) dont la construction remonte à …
የጀርመን የገንዘብ ኖቶች ማተሚያ ካንፓኒ፤ ጊሰኬና ዴቨርይንት የጀርመን ኮንፓኒ ሲሆን ዋና መሥሪያ ቤቱ ሙኒክ ይገኛል፣ ካንፓኒው የገንዘብ ኖቶች፣ ሚስጢራዊ ህትመት ሥራ፣ ስማርት ካርዶች፣የገንዘብ አያያዝ ስርዓት በመዘርጋት ወዘተ የሚሠራ ካንፓኒ ነው፡፡ ካንፓኒው በ1860 እኤአ ጀምሮ በዚህ የህትመት ሥራ ላይ የተሠማራ መሆኑንድረገፁ መረዳት ይቻላል፡፡ ካንፓኒው በሴፕቴምበር 18 ቀን 2011 እኤአ  የባለ 100 የባለ 50 ኢትዩጵያ የብር ኖቶች ለማተም በወጣው ጫረታ ተወዳድሮ ነበር፡፡
Giesecke & Devrient (G&D) is a German company headquartered in Munich that provides banknote and securities printing, smart cards, and cash handling systems. Old company advertisement of Giesecke & Devrient in Leipzig from the 1860s
ሱዳን ከረንሲ ፕሪንቲንግ ፕሬስ፤ Sudan Currency Printing Press (SCPP)
Sudan Currency Printing Press (SCPP) is a private enterprise of limited liability established in May 1994 in accordance with the 1925 company law. The Company had started the real production at the end of 1994. የሱዳን የገንዘብ ማተሚያ ፕሬስ፤ኃላፊነቱ ተወሰነ የግል ኢንተርፕራይዝ በግንቦት 1994 እኤአ መጨረሻ ላይ በሃገረ ሱዳን የተመሰረተ የገንዘብ ማተሚያ የግል ፋብሪካ ነው፡፡ በምን መለኪያና መሥፈርት የኢትዩጵያ ብሄራዊ ባንክ የብር ኖቶችና ቼክ እንዲሁም የአገር ግዛት ሚኒስትር መስሪያ ቤት (Ministry of Interior) ፓስፖርቶችና፣ከሃገር መውጫና መግቢያ ቪዛ፣ፓስፖርት ላይ የሚመታ የሚያብለጨልጭ የቪዛ ስቲከር ብሄራዊ ዶክመቶች፣ መታወቂያ ካርዶችና የተለያዩ የመታወቂያ ዶክመንቶች የህትመት ሥራ ለአዲስ ጀማሪው ካንፓኒ ተሠጠ፡፡ የሃገራችን ሉዓላዊነትና የህዝባችን ደህንነት በሱዳን የግል የገንዘብ ኖቶችና ፓስፖርት በሚያትም ካንፓኒ እግር ስር ወደቀ፡፡ የህወኃት የጦር አበጋዞች  መንግሥት በሃገሪቱ ታሪክ ሆኖ የማያውቅ ሚስጢራዊ የህትመት ሥራ ለሱዳን የግል ካንፓኒ መስጠት ውሎ አድሮ ከሱዳን በተጣሉ ጊዜ ሀገራችን ከፍተኛ ኪሣራ ያስከትላል፡፡  ወያኔ የኢትዩጵያ ተቃዋሚ ድርጅቶች በሱዳን ምድር እንዳይገቡ ለማድረግ የሃገሪቱን መሬት፣ የግብርና ምርትና የቁም እንሰሳት፣ የወርቅ ማዕድን ኃብት ወዘተ በህገወጥ የድንበር ንግድ ከሱዳን መንግሥት ጋር አብሮ ይዘርፋል፡፡ የሱዳን የግል ካንፓኒ የኢትዩጵያ ብር ኖቶች፣  ኤሌክትሮኒክ ፓስፖርትና ቼክ የማተም ሚስጢር ለምን ለህዝብ ይፋ አልሆነም፡፡ የኢትዩጵያ ብሄራዊ ባንክ፤ዋና ተግባራት ውስጥ፤ የብር ኖቶችንና ሣንቲሞችን ማሳተም፣ እንደ መንግሥት ወኪል ሆኖ መስራት፣ የውጭ ምንዛሪ ምጣኔን መወሰንና መቆጣጠር ሃላፊነት በህዝብ ቃል የገባበት ሙያዊ ሥነ-ምግባር በንዋይ ፍቅር ተሸጦ ቢያዩ እውቁ የብሄራዊ ባንክ ገዥ ክቡር አቶ ተፈራ ደግፌ እውቁ ኢኮኖሚስት ፕሮፊሰር እሸቱ ጮሌ ምን ይሎችሁ፡፡ ሞት አይቀር፣ስም አይቀበር!!!
Enterprise to Print Ethiopian Birr, Electronic Passport, Cheque:
The Ethiopian Herald (Addis Ababa), 6 March 2016፡ By Solomon Mekonnen
The Berhanena Selam Printing Enterprise (BSPE) Friday announced plan to cooperate with Sudanese Currency Printing Press to build capabilities to print Ethiopian Birr, electronic passport and cheque locally. Speaking at a Security Printing Technical Conference, Enterprise CEO Teka Abadi said: “We believe the printing of currency, electronics passport and cheque locally will have great role in saving hard currency that our country spends. It is also necessary to localize them for economic and security reasons.” According to him, the win- win relationship with Sudan Currency Printing Press and Koenig & Bauer AG (KBA) Notasys will help each party to achieve their goals. “The printing industry is rapidly growing and the world is continuously applying new technologies from time to time. This makes the competition fierce and puts our local printing houses in a very challenging situation. We need to work together with companies engaged in security printing area,” Teka said. Sudan Currency Printing Press General Manager Assistant Omer Ahmed Mokhtar on his part said that his company is committed to transfer know how through training, maintenance and development and other areas with BSPE. The two Enterprises have signed a Memorandum of Understanding to work together in the fields of technical support, training, capacity building and in areas that could help to build institutional capacities.
Copyright © 2016 The Ethiopian Herald.  Distributed by AllAfrica Global Media (allAfrica.com).
 
የኢትዩጵያ ብር ኖቶች ማተም፣ ኤሌክትሮኒክ ፓስፖርትና ቼክ የሚያትም ኢንተርፕራይዝ
ኢትጵያ ሄራልድ ጋዜጣ (አዲስ አበባ) 6 ማርች 2016 በሰሎሞን መኮንን
የብርሃነ ሰላም ማተሚያ ቤት ኢንተርፕራይዝ ከሱዳን ከረንሲ ፕሪንቲንግ ፕሬስ፤ Sudan Currency Printing Press (SCPP) ጋር በመተባበርና ችሎታ ለማዳበር ብሎም የኢትዩጵያ ብር ኖቶች ማተም፣ ኤሌክትሮኒክ ፓስፖርትና ቼክ በሃገር ውስጥ ለማተም ስምምነት ተደርጎል፡፡ የደህንነት ህትመትና የቴክኒካል ኮንፍረንስ ስብሰባ ላይ ቺፍ ኤክስኪዩቲፍ ኦፊሰር ተካ አባዲ በተናገሩት መሠረት ‹‹ የኢትዩጵያ ብር ኖቶች ማተም፣ ኤሌክትሮኒክ ፓስፖርትና ቼክ በሃገር ውስጥ ማተም ውጪ ምንዛሪ ወጪን ለማዳንና ለኢኮኖሚ እድገትና ለሃገር ሉዓላዊነት ደህንነት በጣም አስፈላጊ ምክንያት ናቸው፡፡›› ከሱዳን ከረንሲ ፕሪንቲንግ ፕሬስ እና ኮኒግና ባወር ኤጂ ኢንተርፕራዞች ጋር ተባብሮ መስራት ዓላማችንን ለማሳካት ይጠቅማል፡፡  የሱዳን ከረንሲ ፕሪንቲንግ ፕሬስ ምክትል ጀነራል ማነጀር ኡመር አህመድ ሙክታር የህትመት ካንፓኒያቸው ከብርሃነ ሰላም ማተሚያ ቤት ኢንተርፕራይዝ ጋር እውቀት ለማጋራት፣ በስልጠና ክህሎት ለማዳበር፣ ጥገናና የልማት ሥራዎች፣ የቴክኒክ ድጋፍ ለማድረግ፣ የሰው ኃይል ግንባታ ክህሎት ለማሳደግና በሌሎች የህትመት ዘርፎች አብሮ በጋራ ለመስራትና ግዳጃቸውን እንደሚወጡ በስምምነቱ ላይ ገልፀዋል፡፡
የኢኮኖሚ ፖሊሲ፣ የኢትዩጵያ መንግስት የኢኮኖሚ ፖሊሲ መሠረቱ በሃገሪቱ ልዩ ልዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች ማለትም በግብርና፣በኢንዱስትሪና የአገልግሎት ዘርፎች ውስጥ አስፈላጊውን የኢኮኖሚ ፖሊሲ በመተግበር ለህዝብ ብልፅግናና ለኢኮኖሚ እድገት የሚሆን ፖሊሲ መንደፍ ነው፡፡ የኢኮኖሚ ፖሊሲው ስርዓት በግብርና ታክስ፣  በመንግሥት በጀት፣ በገንዘብ አቅርቦት፣ የወለድ መጠን፣ እንዲሁም የሠራተኛ /የጉልበት ገበያ፣ ብሄራዊ ኃብትና  ሌሎች ኢኮኖሚ ዘርፎች በማበልፀግ እንዲሁም  የግሉ ዘርፍ ኢኮኖሚ ከፍተኛውን ሚና እንዲጫወት በማድረግ፣ የመንግስት ጣልቃ ገብነት በተወሰኑ የኢኮኖሚ ዘርፍ በተለይም  በማዕድን ዘርፍ (በወርቅ ፣ታንታለም፣ ፖታሽ ወዘተ) ውስጥ ብቻ እንዲወሰን ማድረግ አስፈላጊ ነበር፡፡ ሆኖም የህወኃት የጦር አበጋዞች መንግሥት በመንግሥታዊ ድርጅቶች (አየር መንገድ፣ ቴሌኮም፣ ባቡር፣ መርከብ፣ መብራት ኃይል፣ ስኮር ኮርፖሬሽን ወዘተ) በመፈልፈልና የፓርቲ የንግድ ካንፓኒዎችን (ኢፈርት፣ ሜቴክ፣ የመከላከያ ኮንስትራክሽን ወዘተ) የግሉ ዘርፍ ኢኮኖሚ እንዳይሰራ በሩን ዘግተውበታል፡፡ የአንድ አገር መንግሥት  የኢኮኖሚ ፖሊሲ፣ዘርፈ ብዙ ፈርጆች በሁለት ሊከፈሉ ይችላሉ፤ እነሱም ፊሲካል ፖሊሲና ሞኒተሪ ፖሊሲ በመባል ይታወቃሉ፡፡
ፊሲካል ፖሊሲ፤(Fiscal Policy) የህወኃት የጦር አበጋዞች መንግሥት የግብርና ታክስ እንዲሁም የመንግሥትን ወጪ ሥርዓትን አፈፃፀም ፖሊሲን ያሳያል፡፡ የመንግሥትን ገቢና ወጪና የበጀት ጉድለትና ትርፍ ያሰላል፡፡ የመንግስትና የታክስና የግብር ገቢ አሰባሰብ ሥርዓትና ፖሊሲን እንዲሁም የመንግሥታዊ ዘርፍ ወጪን ይቆጣጠራል፡፡  የህወኃት የጦር አበጋዞች መንግሥትና የብሄራዊ ባንክ ፊሲካል ፖሊሲ፤የግብርና ታክስ ስርዓት ፍትሃዊ ባለመሆኑ ምክንያት በሃገሪቱ ያስከተለውን ህዝባዊ አመፅ መመልከት ብቻ በቂ ነው፡፡
ሞኒተሪ ፖሊሲ፤(Monetary Policy) የህወኃት የጦር አበጋዞች መንግሥትና ብሄራዊ ባንክ በሃገሪቱ ውስጥ ያለውን የገንዘብ ዝውውር፣ገንዘብ ፍላጎትና አቅርቦት በመቆጣጠር የዋጋ ግሽበት መከላከልና የወለድ መጠን በመወሰን የገንዘብ ሥርዓት የሚቆጣጠርበት ሲሆን ከዓለም ዓቀፍ ኢንስቲቲውሽን ማለትም ከዓለም ዓቀፍ የገንዘብ ድርጅት፣ ከዓለም ባንክ እንዲሁም የሃገራቱን የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና የማህበረሰብ ልማት ፖሊሲዎች ጋር አዛምዶ መስራት ያካትታል፡፡ ሞኒተሪ ፖሊሲ ከሚያካትታቸው ውስጥ፤የገቢ ፖሊስ፣የሸቀጣ ሸቀጦችና ምርት የዋጋ ቁጥጥርና የውጪ ምንዛሪ መጠባበቂያ ገንዘብ ክምችትን ያካትታል፡፡
‹‹የዓለም ባንክ የኢትዩጵያን ብር የማርከስ እሰጥ አገባና የአሥራ አንደኛው ሰዓት ንስሐ››1 በሚለው ጥናታዊ ፁሁፉ አቶ ጌታቸው አሰፋው በሪፖርተር ጋዜጣ የብሄራዊ ባንክ ሥራና ሃላፊነትን ተንትኖ ከማስረጃ ጋር ያቀረበውን ፅሁፍ በመጥቀስ አንባቢዎች በቀላሉ መረዳት ይችላሉ፡፡ ‹‹የብሔራዊ ኢኮኖሚ ፖሊሲዎች የሚያጠነጥኑት በሁለት ዓይነት የፖሊሲ መሣሪያዎች በመንግሥት ገቢና ወጪ የበጀት ፖሊሲና በጥሬ ገንዘብ አቅርቦት ፖሊሲ ላይ ነው፡፡›› የጥሬ ገንዘብ ፖሊሲ ‹‹አስፋፊ የጥሬ ገንዘብ ፖሊሲ (Expansionary Monetary Policy) በሕግ ገደብ (By the Rule of the Law) ካልተገደበ፣በልክ ካልተመጠነና በዘፈቀደ (By Discreation) ካደገ በአጭር ግዜ ውስጥ ምርትንም ቢያሳድግ፣በረጅም ጊዜ ግን ውጤቱ ዋጋን ማናርና ጥሬ ገንዘቡን ዋጋ በማሳጣት የብራችንን የምንዛሪ መጣኝ ማርከስ ነው፡፡›› በባንክ ሁለት ዓይነት የገንዘብ ኃብቶች አሉ እነሱም አንደኛው የውጭ ምንዛሪ ኃብት ሲሆን ሁለተኛው የአገር ውስጥ ብድር ኃብት ናቸው፡፡

የበጀት አመት________የውጭ ምንዛሪ ኃብት(1)____________የአገር ውስጥ ብድር ኃብት(2) ____ በመቶኛ(1/2×100)      
2003ዓ/ም በጀት አመት፤ የውጭ ምንዛሪ ኃብት 55.5 ቢሊዩን ብር፣ የአገር ውስጥ ብድር ኃብት 135.5 ቢሊዩን ብር፣ በመቶኛ 41.0%
2004ዓ/ም በጀት አመት፤ የውጭ ምንዛሪ ኃብት 39.8 ቢሊዩን ብር፣ የአገር ውስጥ ብድር ኃብት 189.1 ቢሊዩን ብር፣ በመቶኛ 21.0%
2005ዓ/ምየበጀት አመት፤ የውጭ ምንዛሪ ኃብት 45.6 ቢሊዩን ብር፣ የአገር ውስጥ ብድር ኃብት 233.4 ቢሊዩን ብር፣ በመቶኛ 19.5%
2006ዓ/ምየበጀት አመት፤ የውጭ ምንዛሪ ኃብት 56.1 ቢሊዩን ብር፣ የአገር ውስጥ ብድር ኃብት 299.7 ቢሊዩን ብር፣ በመቶኛ 18.7%
2007ዓ/ምየበጀት አመት፤ የውጭ ምንዛሪ ኃብት 37.5 ቢሊዩን ብር፣ የአገር ውስጥ ብድር ኃብት 393.5 ቢሊዩን ብር፣ በመቶኛ  9.5%

‹‹ከ2003 እስከ  2007 ዓ/ም የባንክ የውጭ ምንዛሪ ሀብት ከአገር ውስጥ ብድር ሀብት ጋር ሲነፃፀር፣በ2003 ዓ/ም ከነበረበት 41 በመቶ በየዓመቱ ቀንሶ በ2007ዓ/ም ዘጠኝ ነጥብ አምስት በመቶ ብቻ ሆኖል፡፡››…
‹‹ይህ የውጭ ምንዛሪ ሃብትና የአገር ውስጥ ብድር ሀብት ንፅፅር ሁኔታ በብር የውጭ ምንዛሪ መጣኝ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ የአገሪቱ ቁልል የውጭ ዕዳ ክምችትም (Outstanding Debt Stock) ይጨምራል፡፡›› ብዙ ሰዎች ስለ ጥሬ ገንዘብ ሲነገር በገበያ ውስጥ የሚዘዋወርን ጥሬ ብር ማለት ሊመስላቸው ይችላል ነገር ግን በንግድ ባንኮች ቆጣቢዎች የሚያስቀምጡት ተቀማጭ ወይም ንግድ ባንኮች በተቀማጩ ላይ ተመርኩዘው ተቀማጩን አርብተው በማበደር የሚፈጥሩት ብድርም ጥሬ ገንዘቦች ናቸው፡፡
ብሔራዊ ባንክ ለመንግሥትና ለንግድ ባንኮች የሚሰጠውን ብድር ከመቆጣጠርም በላይ፣በጥሬ ገንዘብ አቅርቦት ከፍተኛ ሚና የሚጫወቱትን የንግድ ባንኮችን እንቅስቃሴ መቆጣጠር ይገባዋል፡፡ በኢትዩጵያ ለጥሬ ገንዘብ አቅርቦት መጠን ከፍተኛውን አስተዋፅኦ ያደረገው በብሔራዊ ባንክ የቀረበው በገበያ ውስጥ የሚዘዋወረው ጥሬ ብር መሆኑን በሚከተለው ቀላል አገላለጽ ማስተዋል ይቻላል፡፡
የንግድ ባንኮች ተቀማጭ
{1} 2003 ዓ/ም በጀት አመት፤ በብሔራዊ ባንክ አቅራቢነት በገበያ ውስጥ የሚዘዋወር 32.6 ቢሊዩን ብር+ የንግድ ባንኮች ተቀማጭ (ተንቀሳቃሽ፣የቁጠባና የጊዜ ተቀማጮች) 112.8 ቢሊዩን ብር = ጠቅላላ ለገበያ የቀረበ ጥሬ ገንዘብ 145.4 ቢሊዩን ብር፡፡ የጥሬ ብርና የተቀማጭ ንፅፅር በመቶኛ 32.6/112.8 X100=29.0%
{2} 2004 ዓ/ም በጀት አመት፤ በብሔራዊ ባንክ አቅራቢነት በገበያ ውስጥ የሚዘዋወር 38.5 ቢሊዩን ብር+ የንግድ ባንኮች ተቀማጭ (ተንቀሳቃሽ፣የቁጠባና የጊዜ ተቀማጮች) 151.0 ቢሊዩን ብር = ጠቅላላ ለገበያ የቀረበ ጥሬ ገንዘብ 189.5 ቢሊዩን ብር፡፡ የጥሬ ብርና የተቀማጭ ንፅፅር በመቶኛ 38.5/151.0 X100=26.0%
{3} 2005 ዓ/ም በጀት አመት፤ በብሔራዊ ባንክ አቅራቢነት በገበያ ውስጥ የሚዘዋወር 45.7 ቢሊዩን ብር+ የንግድ ባንኮች ተቀማጭ (ተንቀሳቃሽ፣የቁጠባና የጊዜ ተቀማጮች) 189.6 ቢሊዩን ብር = ጠቅላላ ለገበያ የቀረበ ጥሬ ገንዘብ 235.3 ቢሊዩን ብር፡፡ የጥሬ ብርና የተቀማጭ ንፅፅር በመቶኛ 45.7/189.6 X100=24.0%
{4} 2006 ዓ/ም በጀት አመት፤ በብሔራዊ ባንክ አቅራቢነት በገበያ ውስጥ የሚዘዋወር 53.2 ቢሊዩን ብር+ የንግድ ባንኮች ተቀማጭ (ተንቀሳቃሽ፣የቁጠባና የጊዜ ተቀማጮች) 244.5 ቢሊዩን ብር = ጠቅላላ ለገበያ የቀረበ ጥሬ ገንዘብ 297.7 ቢሊዩን ብር፡፡ የጥሬ ብርና የተቀማጭ ንፅፅር በመቶኛ 53.2/244.5 X100=22.0%
{5} 2007 ዓ/ም በጀት አመት፤ በብሔራዊ ባንክ አቅራቢነት በገበያ ውስጥ የሚዘዋወር 60.5 ቢሊዩን ብር+ የንግድ ባንኮች ተቀማጭ (ተንቀሳቃሽ፣የቁጠባና የጊዜ ተቀማጮች) 310.7 ቢሊዩን ብር = ጠቅላላ ለገበያ የቀረበ ጥሬ ገንዘብ 371.2 ቢሊዩን ብር፡፡ የጥሬ ብርና የተቀማጭ ንፅፅር በመቶኛ 60.5/310.7 X100=20.0%
  • በብሔራዊ ባንክ የጥሬ ገንዘብ ፖሊሲ የተዛባ በመሆኑ ምክንያት በሃገሪቱ የውጪ ምንዛሪ እጥረት ተከስቶል፡፡ ባንኩ በሃገሪቱ የጥሬ ገንዘብ አቅርቦት መጠን ከፍተኛ አስተዋፅዖ ማድረጉን ከገላጭ ሠንጠረዡ ላይ ማስተዋል ይቻላል፡፡ በብሔራዊ ባንክ አቅራቢነት በሃገሪቱ ገበያ ውስጥ የሚዘዋወር ጥሬ ብር በ2003 ዓ/ም 32.6 ቢሊዩን ብር ሲያቀርብ፣በ2007 ዓ/ም 60.5 ቢሊዩን ብር ማለትም 54 በመቶ ሞቅ አድርጎ በገበያው ውስጥ ዘርቶታል፡፡
  • በብሔራዊ ባንክ አቅራቢነት በገበያ ውስጥ የሚዘዋወር ጥሬ ብር አቅርቦት የምንዛሪ መጣኙን አዛብቶታል፡፡ በዓለም ታላላቅ ከተሞች እንካን ባልታየ ዓይነት በአዲስ አበባ የአንድ ካሬ ሜትር መሬት ዋጋ ሥስት መቶ ሃምሳ አምስት ሽህ ብር ደርሳል፡፡ በካንትሪ ክለብ፣ የአንድ ቪላ ቤት ዋጋ 10 ሚሊዩን ብር ደርሶል፡፡ የአንድ እንቁላል ዋጋ 3 ብር ከሰባ አምስት፣ አንድ ኪሎ ሙዝ፣ብርቱካን ዋጋ 25 ብር፣ አንድ ኪሎ ሥጋ ዋጋ 150 እስከ 300 ብር ወዘተ በአጠቃላይ ምርት ሳያድግ ብር ማተም፣ ብር ወረቀት እየሆነ እንዲሄድ ያደርጋል፡፡ ህዝቡ ለዳቦ፣ለዘይት፣ለስኳር ይሰለፋል!፣ ህዝቡ ለታክሲ፣ለባቡር፣ለነዳጅ ይሰለፋል! ህዝቡ ለስድት፣ ለሞት ይሰለፋል!!! የኢትዩጵያ ሕዝብ በአንድ ድምፅ ሁላችንንም ሁሌም ማታለል አይቻልም ይላል፡፡ በዚህም የተነሳ በሃገሪቱ ውስጥ ምን እንደተከተለ ለማወቅ ስለ ጥሬ ገንዘብ ፅንሰ-ሃሳብ እንመርምር ይለናል ጸሀፊው በመቀጠልም፡፡
{ሀ} ‹‹ጥሬ ገንዘብ የተፈጠረው የምርት ኢኮኖሚውን ለማገበያየትና ለመለካት እስከሆነ ድረስ የምርት ዋጋ አመልካች ከመሆን አልፎ የራሱ ዋጋ የለውም፡፡ የጥሬ ገንዘብ ዋጋ የሚተመነው ሊገዛ በሚችለው ምርት መጠን ነው፡፡ ስለዚህ ምርቱ ሳይኖር ጥሬ ገንዘቡን ማብዛት የምርቱን ዋጋ መጣል ነው፡፡ ለዚህ ነው በብሔራዊ ኢኮኖሚ ደረጃ የውጭ ሸቀጥ ለመግዛት ከሚያስችለው የውጭ ምንዛሪ በቀር የአገር ውስጥ ጥሬ ገንዘብ ለአገር ሀብትን ይለካል እንጂ ሀብት አይደለም የሚባለው፡፡››
Federal Democratic Republic of Ethiopian Passport
{ለ} ‹‹የአገር ውስጥ ምንዛሪ (currency) ከሌላ አገር ምንዛሪ ጋር በመገበያያ ዋጋ የሚለካው በእርግጠኛ መመነዛዘሪያ መጣኝ፣ የአንድ አገር ምንዛሪ ሸቀጦችን በመግዛት አቅሙ ከሌላ ተገበያይ አገር ምንዛሪ ሸቀጦችን በመግዛት አቅም ጋር ሲወዳደር፣ወይም ከጊዜ ወደ ጊዜ በተመናዛሪዎቹ አገሮች ውስጥ ያለውን የዋጋ ንረት ልዩነት ከግምት ባስገባ የመመነዛዘሪያ መጣኝ ነው፡፡›› በ2003 ዓ/ም አንድ የአሜሪካ ዶላር 14.06 ብር ነበር፣ 2004ዓ/ም (18.65ብር)፣ 2005ዓ/ም (18.65 ብር)፣ 2006ዓ/ም (19.65ብር)፣ 2007ዓ/ም (19.85 ብር)፣2008ዓ/ም (21.83ብር)፣በ2009ዓ/ም (23.23 ብር) የብር የመመንዘሪያ መጣኝ ከዓመት ዓመት እየረከሰ በመሄዱ ከውጭ ሸቀጣ ሸቆችና ኮፒታል ጉድስ መለትም (ማሽነሪዎች፣ መኪኖች፣ ትራንስፎርመር፣ ወዘተ) የመግዛት አቅማችን የመነመነ ለመሆን ችሎል፡፡ የሃገራችን የውጪ ንግድ ገቢ እያሽቆለቆለ በመሆዱ የታሰበው እድገት ውሃ በልቶታል፡፡
{ሐ} የብር ምንዛሪ ማርከስ( Devaluation of currency) የኢትዩጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ ምርቱ ሳይኖር ጥሬ ገንዘቡን በማብዛት በሃገር ውስጥ ገበያ ገንዘብ በማሰራጨቱ የምርቱን ዋጋ መጨመር አስከተለ፡፡  የሃገሪቱም የብር የመግዛት አቅም በመውደቁ ምክንያት የሃገር ውስጥ ምርቶችን የመግዛት አቅሙ ተዳከመ፡፡ ለዚህ ሁሉ ምክንያቱ ብሔራዊ ባንክ የጥሬ ገንዘብ አቅርቦቱን  ከልኩ በላይ በሃገሪቱ ገበያ ውስጥ በማሰራጨቱ ነው፡፡
ያለፉት ዓመታት የጥሬ ገንዘብ አቅርቦት ዕድገት
የበጀት አመት________ጠቅላላ ለገበያ የቀረበ ጥሬ ገንዘብ (በቢሊዩን ብር)____________የመጠን ልዩነት____ እድገት በመቶኛ      
2002ዓ/ም በጀት አመት፤ ጠቅላላ ለገበያ የቀረበ ጥሬ ገንዘብ 104.0 ቢሊዩን ብር፣ የመጠን ልዩነት  — ቢሊዩን ብር፣ እድገት በመቶኛ –%
2003ዓ/ም በጀት አመት፤ ጠቅላላ ለገበያ የቀረበ ጥሬ ገንዘብ 145.4 ቢሊዩን ብር፣ የመጠን ልዩነት 41 ቢሊዩን ብር፣ እድገት በመቶኛ 39.0%
2004ዓ/ም በጀት አመት፤ ጠቅላላ ለገበያ የቀረበ ጥሬ ገንዘብ 189.5 ቢሊዩን ብር፣ የመጠን ልዩነት 44 ቢሊዩን ብር፣ እድገት በመቶኛ 30.0%
2005ዓ/ምየበጀት አመት፤ ጠቅላላ ለገበያ የቀረበ ጥሬ ገንዘብ 235.3 ቢሊዩን ብር፣ የመጠን ልዩነት 46 ቢሊዩን ብር፣ እድገት በመቶኛ 24.0%
2006ዓ/ምየበጀት አመት፤ ጠቅላላ ለገበያ የቀረበ ጥሬ ገንዘብ 297.7 ቢሊዩን ብር፣ የመጠን ልዩነት 63 ቢሊዩን ብር፣ እድገት በመቶኛ 27.0%
2007ዓ/ምየበጀት አመት፤ ጠቅላላ ለገበያ የቀረበ ጥሬ ገንዘብ 371.2 ቢሊዩን ብር፣ የመጠን ልዩነት 73 ቢሊዩን ብር፣ እድገት በመቶኛ 25.0%
2002ዓ/ም እስከ 2007ዓ/ምየበጀት አመት፤የአምስት ኣመት እድገት አማካይ እድገት በመቶኛ 29.0%
‹‹የጥሬ ገንዘብ አቅርቦቱን   እድገት መጣኝ ቢመጣም በአካፋዩ መነሻ መተለቅ ምክንያት እንጂ፣የአቅርቦቱ መጠን እየጨመረ እንደመጣ እናያለን፡፡ የእርግጠኛ ጥቅል የአገር ውስጥ ምርት ዕድገትን በየአመቱ 11 በመቶ ይሁን ብለን ተቀብለን እንካ፣ ከአምስቱ አመት አማካይ የጥሬ ገንዘብ አቅርቦት እድገት 29 በመቶ ውስጥ 11 በመቶው ለምርት ዕድገት ዋለ ብንል ቀሪው 18 በመቶ የዋለው ለዋጋ ንረት ነው፡፡››

በ2008 ዓ/ም የመንግስትና የግል ባንኮች፣ በኢትዩጵያ የሚገኙ የመንግስትና የግል ባንኮች፣ በቁጠባ የሠበሰቡት ተቀማጭ ገንዘብ መጠን ከ670 ቢሊዩን ብር ሲሆን በአንጻሩ ለደንበኞች የሠጡት ብድር መጠን 480 ቢሊዩን ብር ነው፡፡ በሌላ በኩል የመንግሥትና የግል ባንኮች አጠቃላይ ተቀማጭ ካፒታል ደግሞ ወደ 30 ቢሊዩን ብር አካባቢ ነው ያላቸው፡፡ ከህዝብ በቁጠባ የሠበሰቡት ተቀማጭ ገንዘብን ከባንኮች ተቀማጭ ካፒታል ስናቀናንሰው (670 ሲቀነስ 30 ቢሊዩን ብር) 640 ቢሊዩን ብር ከህዝብ የተሠበሰበ ተቀማጭ ገንዘብ የህዝብ ኃብት ነው፡፡
  • የመንግስትና የግል ባንኮች፣ በቁጠባ የሠበሰቡት ተቀማጭ ገንዘብ መጠን ከ670 ቢሊዩን ብር
  • የመንግስትና የግል ባንኮች፣ ለደንበኞች የሠጡት ብድር መጠን 480 ቢሊዩን ብር
  • የግል ባንኮች፣ ባለ አክሲኖች ተቀማጭ ካፒታል ደግሞ ወደ 30 ቢሊዩን ብር
  • የመንግስትና የግል ባንኮች፣ በቁጠባ የሠበሰቡት ተቀማጭ ገንዘብ መጠን ከ670 ሲቀነስ ተቀማጭ ካፒታል ደግሞ ወደ 30 ቢሊዩን ብር 640 ቢሊዩን ብር ከህዝብ የተሠበሰበ ተቀማጭ ገንዘብ የህዝብ ኃብት ነው፡፡
  • በ2003 ዓ/ም 680 የቅርንጫፎች ባንኮች ቁጥር የነበረ ሲሆን፣ በዕቅድ ዘመኑ መጨረሻ ላይ 2800 ደርሶል፡፡ በአሁኑ ወቅት ደግሞ ወደ 3900 ደርሶል፡፡ የማይክሮ ፋይናንስ ተቆማትም 1600 ቅርንጫፎች መድረስ ችለዋል፡፡ ከባንክ ቅርንጫፎች ከ3900 ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆነው የግል ባንኮች ናቸው፡፡ 18 ሽህ የነበረው የባንክ ሠራተኛ አሁን ከ20 ሽህ በላይ ሆኖል፡፡
በአጠቃላይ ሃገሪቱ ያላት ሃብት ከግዜ ወደ ግዜ እየመነመነ፣ወደ ባህር ማዶ  የውጭ ምንዛሪያችን እየኮበለለ፣የገንዘባችን የመግዛት አቅም በዲቨሊዌሽን እየቀነሰ መምጣትን ያሳያል፡፡ በአዲስአበባ ለአንድ ካሬ ሜትር መሬት  355 ሽህ ብር የሊዝ መጫረቻ ዋጋ መቅረቡ አመላካች የኢኮኖሚ ውድቀት መሆኑንና የብራችን እሴት  ወደ ወረቀትነት  መቀየርን እንደሚያሳይ  የምጣኔ ኃብት ጠበብት ይገልፃሉ፡፡ በተጨማሪም የሉዓላዊ ቦንድ የቃል ኪዳን ሰነድ አንድ ቢሊዩን ዩኤስ ዶላር ብድር በአጠቃላይ ሦስቱም የኢኮኖሚ ዘርፎች ምሦሶ መወላለቃቸውን ያሳያል፡፡

በ2009 ዓ/ም የመንግስት ባንኮች፣ የመንግሥት የፋይናንስ ድርጅቶች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ስንታየሁ ወልደሚካኤል፣ የሚከታተላቸውን የኢትዩጵያ ንግድ ባንክ፣ የኢትጵያ ልማት ባንክና የኢትዩጵያ መድን ድርጅት የ2009 ዓ/ም የዕቅድና አፈፃፀም
ጠቅላላ ሀብት፤በሶስቱ የመንግሥት የፋይናንስ ተቆማት የ2009 ሂሳብ ዓመት ክንውን መሠረት የ523 ቢሊዩን ብር ጠቅላላ ሀብት መመዝገቡን ሲገለፅ፣ ከታቀደው የ517 ቢሊዩን ብር አኮያ ከ100 በመቶ በላይ ጭማሪ መመዝገቡን ኤጀንሲው አስታውቆል፡፡ በ2008 ዓ/ም ከነበረው የ440.4 ቢሊዩን ብር ጠቅላላ ሀብት አኮያ የ82.6 በመቶ ጭማሪ ተመዝግቦል፡፡ ከጠቅላላው ሀብት ውስጥ በጥሬ ገንዘብ የተመዘገበው 60 ቢሊዩን ብር ገደማ መድረሱም ታውቆል፡፡ ከዚህ ውስጥ በብድር መልክ የተመዘገበው ሃብት 184 ቢሊዩን ብር ሲሆን፣ በኢንቨስትመንት መልክ ከ269 ቢሊዩን ብር በላይ ነው፡፡
አጠቃላይ የዕዳ መጠን፤ በሦስቱ ተቆማት በ2009ዓ/ም ያስመዘገበት አጠቃላይ የዕዳ መጠን 490 ቢሊዩን ብር ሲሆን፣ በ2008ዓ/ም የነበራቸው የእዳ መጠን 415 ቢሊዩን ብር ነበር፡፡ በዚህም መሠረት የፋይናንስ ተቆማቱ ካፒታል መጠባበቂያ ክምችታቸውን ጨምሮ 33 ቢሊዩን ብር መመዝገቡን ኤጀንሲው አስታውቆል፡፡
በብድር ሥርጭት፤በሦስቱ ተቆማት  በብድር ሥርጭት ረገድ ድርጅቶቹ 124 ቢሊዩን ብር ብድር (የብድር ቦንድ ኩፖን ታክሎበት) ማሠራጨታቸው ሲገለፅ፣አብዛኛው ድርሻ የኢትዩጵያ ንግድ ባንክ መሆኑ ተመልክቶል፡፡ባንኩ 94.5 ቢሊዩን ብር ብድር መሰጠቱ፣54 ቢሊዩን ብር ገደማ ብድር መሰብሰቡንና የብድር ክምችቱም በቦንድ የሰጠውን ጨምሮ 420 ቢሊዩን ብር ገደማ መድረሱ ታውቆል፡፡
የተበላሸ የብድር፤ በሦስቱ ተቆማት የተበላሸ የብድር መጠኑ ከጠቅላላው ብድር ውስጥ 2.8 በመቶ መሆኑ ሲገለፅ፣የኢትዩጵያ ብሄራዊ ባንክ ካስቀመጠው የአምስት በመቶ የተበላሹ ብድሮች ጣሪያ አኮያ ዝቅተኛ ሆኖል፡፡ ከዚህም በላይ 14.6 ቢሊዩን ብር ትርፍ ማስመዝገቡን፣ ከ2008ዓ/ም መጠንም የ5.2 በመቶ ብልጫ እንዳለው ታውቆል፡፡
‹‹የኢትዩጵያ መንግሥታዊ ባንኮች የፋይናንስ ዘርፍ ቀውስ››
የኢትዩጵያ ብሔራዊ ባንክ ኃላፊነቱን ያልተወጣ ተቆም ነው፡፡ በሃገሪቱ ለተፈጠረው የፋይናንስ ዘርፍ ቀውስ፣ የገንዘብ አቅርቦት መመጠንና መቆጣጠር አለመቻሉ፣ የገንዘብ ወጪና ብድርን መወሰንና መጠበቅ አለመቻሉ፣ የሃገሪቱን የዓለም ዓቀፍ ተቀማጭና መጠባበቂያ ገንዘብ መቆጣጠርና ማስተዳደር ደካማነቱ፣ ለባንኮች ፍቃድ መስጠት፣መቆጣጠርና ክትትል ማድረግ አቅመቢስነቱ፣ የንግድ ባንኮች ተቀማጭ መያዝ፣እንዲሁም ለንግድ ባንኮች ገንዘብ ማበደር፣ የንግድ ባንኮችን ብድር መቆጣጠርና ክትትል ማድረግ እንዲሁም የወለድ መጠንን መወሰን ጣልቃ ገብነቱ፣ እንደ መንግሥት ወኪል ሆኖ በመስራትና የውጭ ምንዛሪ ምጣኔን መወሰንና መቆጣጠር ተስኖቸዋል፡፡ የባንክ ሙያተኞች በሙስና ተዘፍቀው ከሹማምንቶቹ ጋር ተመሳጥረው የሃገር ሃብት መዝብረዋል፡፡ በሱዳን የግል ካንፓኒ፣የብር ኖቶችንና ሣንቲሞችን በማሳተም የሃገሪቱን የብር ኖቶችን እንደወረቀት በማሳተም የሃገር ሉዓላዊነትንና የህዝቡን ደህንነት ለባዕድ አገር አሳልፈው የሰጡ የብሄራዊ ባንክ ገዥዎችና የህወኃት የጦር አበጋዞች መንግሥት ለፍርድ መቅረባቸው አይቀርም፡፡
ብር ወረቀት፣ ወረቀት ብር፣ የብር ወረቀት፣ የወረቀት ብር (ይቀጥላል)

የአግባው ሰጠኝ ሕይወት አደጋ ውስጥ ነው



የአግባው ሰጠኝ ሕይወት አደጋ ውስጥ ነው፤
አግባው ዝዋይ ተወስዶ የደረሰበትን ድብደባ ለፍርድ ቤቱ ቤቱ ገልፆ እስር ቤቱ ለምን ይህን ድርገት እንደፈፀመ እንዲያስረዳ፣ የተፈፀመበት ድብደባ በህክምና ምርመራ እንዲ ረጋገጥለት አቤቱታ አቅርቦ የነበር ሲሆን በትናንትናው እለት መልስ ሰጥተዋል።
መልሱም በአንድ በኩል አግባው ሊያመልጥ እንደነበር የሚገልፅ ሲሆነ በሌላ በኩል ደግሞ የእርስ በእረስ ፀብ እንደነበርና አግባውም በፀቡ ተጎድቶ ሊሆን እንደሚችል በመግለፅ ለማስተባበል የሞከሩበት ነው። አግባው ነሃሴ 1 በዋለው ችሎት ልብሱን አውልቆ እንዲያሳይ ጠይቆ የተከለከለ ሲሆን ማረሚያ ቤቱ ምላሽ ከሰጠ በሁዋላ ትናንት ከማረሚያ ቤቱ ውጭ የሚገኝ የህክምና ተቋም ተመርምሮ እንዲያሳይ ቢጠይቅም ፍርድ ቤቱ ፈቃደኛ አልሆነም።
አግባው ሰጠኝ በቂሊንጦ ቃጠሎ የተጠረጠሩ ሰዎች የታሰሩበት ዞን 5 ታሰሮ የነበር ሲሆን ከዝዋይ መልስ ይቅርታ ጠይቀው ከ ሺህ በላይ እስረኛ ከሚታሰርበት ዞን 2 አዛውረውታል። የማረሚያ ቤቱ አስተዳደሮች ይቅርታ ከጠየቁ በሁዋላ ከአቅማችን በላይ ነው ብለው ለፍርድ ቤቱ መልስ የሰጡ ሲሆን አግባው ካልቻሉ ብቻውን ወይንም እነ መቶ አለቃ ማስረሻ የታሰሩበት ዞን 4 ሊያስሩት ይችሉ እንደነበር፣ ነገር ግን ዞን 2 መቀየሩ እሱን ለማጥቃት ሊሆን እንደሚችል ስጋቱን ገልፆአል። ለህይወቱ ዋስትና እንደሌለው ገልፆአል።
ጎንደር አንድ ሰው ሲሞት እሱን መበቀል እንደሚፈልጉም ገልፆአል። ፍርድ ቤቱ በማተሚያ ቤቱ አሰራር እንደማይገባና ከዚህ በሁዋላ ምንም ሊያደርግ እንደማይችል በመግለፅ ለፍርድ ቤቱ በአግባቡ መልሰ የማይሰጡትን የማረሚያ ቤቱን አመራሮች መክሰስ እንደሚችል መፍትሄ ብሎ አቅርቦለታል።

Monday, August 14, 2017

የሜቴክ ሌብነት በትራንስፖርት ሴክተር



የሜቴክ ሌብነት በትራንስፖርት ሴክተር (ክፍል አንድ) በበዛብህ ሲሳይ , ሀይድራባድ ህንድ (2009)
ለዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆነኝ ሰሞኑ በቀድሞ የስርዓቱ ልሳን በነበረው በአቶ ኤርሚያስ ለገሰ ያስነበበን ሜቴክ ከንግድ መርከብ ስለገዛቸው ሁለት መርከቦች እና ሊያቋቁመው ስላሰበው የውሃ ትራንስፖርት ንግድ ስራ እንዲሁም በአገሪቷ ላይ ያደረሰውን ኪሳራ ካየሁ በኃላ ነው፡፡ እውነት ነው ተቋሙ ሲቋቋም ጀምሮ ለገዢው ጉጅሌ ኢኮኖሚያዊ ትርፍ እንዲያመጣ ተብሎ ብቻ ሳይሆን የትግራይ ተወላጆችን በሰሜን በኤርትራዋኖች ለይ እንዲሁም በደቡብ ደግሞ በሰፊው የኢትዮጰያ ህዝብ ላይ የፖለቲካዊ ልእልና እንዲኖራቸው በማሰብ ጭምር ነው፡፡
ስለዚህ አቶ ኤርምያስ እንደ አስቀመጠው የሜቴክ መሪዎቹ ሲጋራን በቄንጥ ሚያጨሱ ብቻ ሳይሆኑ ለዚህ እኩይ አላማቸው የሚሳተፉላቸውን ሆድ-አደር ምሁራንን ወይም ባለሰርተፊኬቶችን እንዴት ማስተዳደርና መጠቀም እንዳለባቸው ስለሚያውቁ ሌብነቱ እጅግ የረቀቀ እንዲሆንና ጉዳቱም የብዙ ቀጣይ ትውልዶች መስዋትነት የሚጠይቅ እንዲሆን አስችሏል፡፡ ለዚህ እኩይ አላማቸውም አንዳንዳዴም የፈረንጅ ጫማ ላሾችንም (Bootlikers) ይጠቀማሉ ለምሳሌ እንደነ ዴቪድ ዴጎር ያሉ የአለም ባንክ ሰራተኛ ሳይሆኑ ከመንግስት ሌቦች ጋር በድለላ በመሳተፍ ሌብነቱን የሚያጧጥፉትን ያቀርቧቸዋል፡፡
ይህ ግለሰብ በተለይ ለአርከበ፣ ለመኩሪያ፣ እንዲሁም ለወርቅነህ እጅግ ቅርብ እንደሆነ እና ተቀማጭነቱን ደቡብ አፍሪካ አድርጎ የሌብነት ድለላውን በቢሊየን ዶላር የሚያጧጥፋ ነው፡፡ በነገራችን የአለም ባንክ ሆኑ ሌሎች አበዳሪ ተቋማት እንደነዚህ አይነት የት እንደሚሰሩ ማይታወቅ ግለሰቦችን የሚጠቀሙት በሚፈጸመው ወንጀል ላለመጠየቅ ነው፡፡ ሌሎች ከአገር ዉስጥ ደግሞ የሲ.አይ ኤ ትክሎች ከሆኑት አንድሪያስ እሸቴ፣ አብዱ እንዲሁም በስመ ኢኮኖሚስት የሚነግደው ዘመዴነህ ንጋቱ የድለላውን ስራ ከሚያቀላጥፉት ዋናዎቹ ናቸው፡፡ በዚህና በሚቀጥለው ፅሁፌ ሜቴክ በትራንፖርት ሴክተሩ የሚፈፅመውን ሌብነትና እነማን በ ‘ምሁር-ነን’ ሰበብ ተልዕኮውን እንዲያሳካ እንደሚረዱት እናያለን፡፡ መልካም ንባብ! ገዥው ህውሃት ለሃያ ስድስተ አመታት ሲያራምደው እንደነበረው የሌብነት ፖሊሲ ሜቴክም መቆጣጠር የሚፈልገው የኢኮኖሚ አውታር በዋነኝነት ከአገር ውስጥ ወይም ከዉጭ ሃገር ልዩ የፋይናንስ ድጋፍ ያላቸውን የኢኮኖሚ ሴክተሮች ሲሆን ትራንስፖርት ደግሞ አንዱና ዋነኛ ነው፡፡
የአለም ባንክ፣የአፍሪካ ልማት ባንክ እና የቻይና ኤግዚም ባንክ አብዛኛውን ብድራቸውን የሚሰጡት ለዚሁ ለትራንስፖርት መሰረተ-ልማት ግንባታ ነው፡፡ ለዚህም ነው ሜቴክ ገና ጥርሱን ሳይነቅል ዘሎ ዝርፊያውን የጀመረው የቀድሞ ኢትዮ- ጂቡቲ ባቡር ሃዲድ በመንቀልና በመመዝበር የሆነው፡፡ ለዚህም አዛኝ መስሎ የተበተነውን የቀድሞ የባቡር ሰራተኞችን ደሞዝ እከፍላለሁ በሚል ተልካሻ ሰበብ ድርጅቱን በስውር በመውረስ ጅቡቲን ያህል አገር መስዋዕትነት የከፈልንበትን ታሪካዊውን የባቡር ሃዲድ ወረሰው፡፡ ሃዲዱም በ1907 የተመረተ ንፁህ የባቡር ሃዲድ ብረት ነበር፡፡ ይህንን ውንብድና ለማገዝ አዲሱ የባቡር ፕላን ሆን ተብሎ የድሮውን ወደ 12 ቦታ እንዲቆርጠው በማድረግ የቀድሞው መስመር መልሶ ለአገልግሎት እንዳይውል ለአንዴና ለመጨረሻ ወንበዴው ሜቴክ ወሰነበት፡፡
የሚያሳዝነው ይህ የቀድሞ የኢትዮ-ጂቡቲ ባቡር እንደ ፈረንጆች አቆጣጠር በ2006 ከአውሮጳ ህብረት በተገኘ የ50 ሚሊዮን ዩሮ ብድር የመልሶ ማልማት ስራ ጀምሮ የነበረ ሲሆን ሜቴክ ሲያቋርጠው ብዙም ስራ ተሰርቶ ነበር (ግርጌ ፎቶውን ይመልከቱ)፡፡ በመስኩ የተሰማሩ ባለሞያዎች እንሚሉት የቀድሞ የባቡር መስመር በትክክል ቢሰራ ኢትዮጵያ የምታስገባውንም ሆነ የምታስወጣውን ጭነት በአስተማማኝ ከማስተናገዱ አልፎ ሃገሪቱ በሚቀጥሉት ሃያ አመታት ልታመጣው የምትችለውን (የሚባለውን የ7%)የኢኮኖሚ እድገትም መሸከም የሚችል ነበር፡፡ ይሄ ለጄ/ር ክንፈ እና ዶ/ር አርከበ የሚገባ ስሌት አይመስለኝም፡፡ አራቱን የሂሳብ ስሌቶች እንኳን በቅጡ ማስላት እንደሚከብዳቸው ከነሱ ጋር የሰራ ሁሉ ያውቃል፡፡ ለዚህም ነው የአዲስ አበባ ባቡርም በሰዓት ሃያ ሺህ ህዝብ ያመላልሳል ብለው ቡፋያቸወን ነፍተው አመት እንኳን ሳይሆነው ከ41 ባቡሮች 19ኙ በመለዋወጫ እጦት እንደማይሰሩ ሪፖርተር ያስነበበን፡፡ ወደ ኢትዮ- ጂቡቲ ባቡር ስንመለስ ሌላ ቢቀር እንኳን ታሪካዊነቱ ታይቶ ልክ በሰለጠኑት አገራት እንደሚገኙት የድሮ የባቡር መስመሮች ለቱሪዚም አገልግሎት መዋል ይችል ነበር፡፡
በተለይ አዲስ ከተዘረጋው መስመር በበለጠ በብዙ ከተሞች ላይ ማረፊያ ተሪሚናሉች ስላሉት ከተሞችን በበለጠ በንግድ በማስተሳሰር ከፍተኛ አስተዎጽኦ ማምጣት ይችል ነበር፡፡ይሄም አዲሱ ባቡር ወደ 32 በሚሆኑ ቦታ/ከተሞች ላይ ብቻ ሲያርፍ የቀድሞ ባቡር ግን ከ100 በላይ ቦታዎች/ከተሞች ላይ በማረፍ የባቡር መስመሩን ተከትለው በተቆረቆሩት ከተሞች ያሉ ነዋሪዎችን በበለጠ የኢኮኖሚና የማህበረሰብ ትስስራቸውን ያጠናክር ነበር፡፡ ሆኖም እነዚህ ለታሪክ ምንም ደንታ የሌላቸው የትግራይ ጉጅሌዎችን ያቀፈው ሜቴክ ታሪካዊዉን የበቡር ሃዲድ ብረት ሃላፊነት በጎደለው መንገድ ስልቅጥ አድርጎ በላው፡፡ በሚቀጥለው ፅሁፌ ደግሞ ሜቴክን ከጀርባ አዝለው ስለሚንቀሳቀሱ ሆድ-አደር ምሁሮችና የረቀቀ የሌብነት ሴራቸውን የአዲስ አበባ የመንገዶችና ትራንስፖርት ቢሮን እንዲሁም የኢንፎርሜሽንና ኮሚኒኬሽን ኤጀንሲን ዋቢ በባድረግ ለማሳያየት እሞክራለሁ፡፡ ሰላም ሁኑ!

Tuesday, August 8, 2017

ከሳሞራ ቀጥሎ ያለው ዋና የሜቴክ ፈላጭ ቆራጭ ሌላኛው ታሳሪ ሊሆን ይችላል!


ጄኔራል ክንፈ ሊታሰሩ ይችላሉ የሚል ጭምጭምታ አይሏል!
– ከረፈደ የተጀመረው የኢህአዴግ የፀረ-ሙስና ዘመቻ የሜቴኩን ጄኔራል ክንፈ ዳኜን ሊነካ ይችላል የሚል ጭምጭምታ ከሜቴክ ሠራተኞች ከራሳቸው መስተጋባት ከጀመረ ሳምንታት ተቆጥረዋል፡፡ ከወር በፊት ታይቶ በማይታወቅ ድፍረት በተወካዮች ምክር ቤት አባላት ክፉኛ የተተቹት ጄኔራል ክንፈ ‹‹‹በግሌ የማምነው ለዚህ አገር ልማት እየወደቅንና እየተሰዋን እንደምንሠራ ነው፡፡ መጠየቅ ካለብኝ እኔ ልጠየቅ፡፡›› ካሉባት ዕለት ጀምሮ ሰውየው በደኅንነቶች ሊደፈሩ ይችላሉ የሚለው ጭምጭምታ ሲራገብ ቆይቶ ነበር፡፡
ከሰሞኑ የጸረ ሙስና ዘመቻ ጋር ተያይዞ ይኸው ጭምጭምታ እያደገ መጥቷል፡፡
በተለይም የርሳቸው ጽሕፈት ቤት የሚገኝበትና ከሜክሲኮ ወደ ሳርቤት የሚወስደው ዋና መንገድ ላይ በስተቀኝ የሚገኘው የመከላከያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ግቢ ሠራተኞች በክበባቸው ሻይ ቡና እያሉ የሚያወሩት ይህንኑ ጉዳይ ሆኗል፡፡ ትልቁ አለቃቸው ከዛሬ ነገ ችግር ውስጥ ሊገቡ እንደሚችሉ መጠርጠር የጀመሩት በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የደኅንነት ሰዎች በመሥሪያ ቤቶቻቸው በስፋት ማንዣበባቸውን ተከትሎ ነው፡፡
ቶቶት አካባቢና ኤምፔሪያል አሞራው ሕንጻ ዉስጥ የተጠለሉ የሜቴክ ሠራተኞችም ቢሆን ትልቁ አለቃቸው የማይደፈሩ እንደሆኑ ቢያውቁም ሊታሰሩ ይችላሉ የሚለው ሀሜት በስፋት መወራቱ አሳስቧቸዋል፡፡ ዘመቻውን በሚመራው ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ጽኅፈት ቤትና አቶ ጌታቸው አሰፋ በሚመራው የመረጃና ደኅንነት ቢሮ መካከል የጄኔራል ክንፈ ጉዳይ አለመግባባት መፍጠር የጀመረው ዛሬ አይደለም ይላሉ፣ ነገሩን እናውቃለን የሚሉ ወገኖች፡፡
ጄኔራሉ ከፍ ያለ የአገር ፍቅር ያለው፣ ቀንተሌት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል የሚሠራ፣ በ‹‹ይቻላል›› ጥልቅ መንፈስ የተሞላ መሆኑ በስፋት በከፍተኛ አመራሩ ዘንድ ስለሚታወቅለት ብዙዎች ይሳሱለታል፡፡ በአንጻሩ ጥብቅ የመንግሥት የፋይናንስ አሠራርን ቸል ብሎ በዘፈቀደና በየዋህነት አንዳንዴም በማንአለብኝነት ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ለማስፈጸም በወታደራዊ አስተሳሰብ የሚታትትር መሆኑ ‹‹የዋህና ደፋር ጄኔራል ነው›› ያደርገዋል ይላል አንድ የቀድሞ የሜቴክ ባልደረባ፡፡ ይህ ባህሪው ደግሞ አገሪቷን በቢሊዮን የሚቆጠር ዋጋ እንድትከፍል አድርጓታል ሲል ሐሳቡን ይቋጫል፡፡
ዞሮ ዞሮ የርሱ በሕግ ፊት መቆምና አለመቆም ስለሕወሓትና ስለ ጠቅላላው የኢህአዴግ አሰላለፍ የሚነግረን ብዙ ነገር ይኖራል፡፡
የልማት ባንኩ ሰው የት ጠፉ?
– የልማት ባንኩ የቀድሞ አለቃ አቶ ኢሳያስ ባህረ ሌላው በሐሜት ደረጃ የሚጠበቁ ታሳሪ ናቸው፡፡
በሰፋፊ እርሻዎች ብድር በቢሊዮን የሚቆጠር ብር መባከኑን ተከትሎ ጠዋት ከጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ተሰብስበው ከሰዓት ከኃላፊነታቸው የተሰናበቱት አቶ ኢሳያስ በአሁኑ ወቅት የት እንዳሉ አውቃለሁ የሚል የለም፡፡ ሆኖም ከኃላፊነታቸው ከመሰናበታቸው ቀደም ብሎ ረፋዱን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በመሩት ስብሰባ አቶ ኢሳያስ በፋይናንስ አማካሪዎችና የፓርቲው ሰዎች ክፉኛ ተብጠልጥለው እንደነበር ይነገራል፡፡ በስብሰባው አቶ ፍጹም አረጋ፣ አቶ አበራ ሙላት፣ አቶ በቃሉ ዘለቀና ሌሎች ኃያል ባለሥልጣናት ተገኝተው ነበር፡፡ ከኦህዴድና ከብአዴን የተወከሉ የፓርቲው ሰዎች ብድር በብሔር እየተሰጠ እስኪመስለን ድረስ ነው በልማት ባንክ እየተሰደብን ያለነው ብለው አስተያየት መስጠታቸው ድንጋጤን ፈጥሮ ነበር፡፡ የልማት ባንክ ለአንድ ብሔር ሰዎች የማድላትን ጉዳይ በድፍረት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፊት ከተናገሩት ውስጥ ከሰሞኑ ወደ አርብቶ አደር ጉዳዮች ሚኒስትርነት ዙውውር ያካሄዱት አቶ ከበደ ጫኔ ናቸው፡፡ ከፍ ያለ ውጥረት ሰፍኖበት ነበር የተባለው ይህ ስብሰባ መርገብ የቻለው አቶ ኢሳያስ ራሳቸው በሰጡት የማጠቃለያ ሀሳብ ነበር፤ ‹‹እዚህ የምትተቹኝ ሁላችሁም እየደወላችሁ እከሌን አስተናግደው እያላችሁ ባለሐብት ስትልኩብኝ የነበራችሁ ናችሁ፣ እኔን ለመተቸት ሞራል አላችሁ ብዬ አላምንም፡፡››
አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ስልጠና እየሰጡ ነው
-ለሌላ ዙር ሹመት ታጭተዋል ተብሎ ግምት የተሰጣቸው የአይርላንዱ አምባሳደራችን አቶ ሬድዋን ሁሴን ‹‹ለመካከለኛ ዲፕሎማቶች ስልጠና ለመስጠት ነው የመጣሁት፣ ስለ ሹመት የማውቀው ነገር የለም›› ሲሉ ራቅ ላለ አንድ የቤተሰብ አባል መናገራቸውን የዚህ ዜና ዘጋቢ ተረድታለች፡፡ ምናልባት ከመስከረሙ የኢህአዴግ ጉባኤ በኋላ ጎልቶ ከሚወጣው ቡድን ጋር እዚሁ ቆይተው ቁልፍ ሥልጣን ሊይዙ እንደሚችሉ ግን አሁንም ይጠረጠራል፡፡ በፓርቲው ውስጥ ብዙ ሊጠቅሙ እየቻሉ ነው ያለጊዜያቸው ገለል የተደረጉት ይላሉ ውስጥ አዋቂዎች፡፡
የካሳ መጨረሻ ዋሺንግተን መሆኑ እርግጥ ሆኗል
-የዉጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ምንጮች የሰቆጣው ሰው አቶ ካሳ ተክለብርሃን ወደ ዋሺንግተን ቢሮ መላካቸውን አረጋግጠናል ብለዋል፡፡ ለስላሳ አንደበትና ከኢህአዴግ ሹሞች በተለየ አብዝቶ የማዳመጥ ተሰጥኦ ያላቸው አቶ ካሳ ከወረዳ የጽሕፈት ቤት ኃላፊነት እስከ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤነት፣ ከሲቪል ሰርቪስ ዲግሪ እስከ እስከ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የቦርድ ሰብሳቢነት የደረሱት ታጋሽና ቻይ በመሆናቸው ነው ይባላል፡፡ ከአቶ በረከት ስምኦን ጋር በቅራኔ ዉስጥ የቆዩት አቶ ካሳ በስልጣን መሰላል ብዙ መራመድ ያስቡ ስለነበር በአምባሳደርነቱ መሾማቸው ብዙም ደስተኛ እንዳላደረጋቸው ይነገራል፡፡ በተያያዘ ወሬ ወደ ካናዳ ተጉዘው በአቅም ማነስ የሚወረፉትን ወይዘሮ ብርቱካንን ይተካሉ የተባሉት የአቶ እውነቱ ብላታ መጨረሻ ቶሮንቶ ሳይሆን ብራስልስ ነው ብለዋል እነዚሁ ምንጮች፡፡

ህዝቡን በስናይፐር የገደለ ብቸኛው የአለማችን ገዳይ የትግራዩ ፋሽስት መንግስት እና ነሀሴ ፩ ሲታሰብ (ዋ-ባህር ዳር)


       



ሰለሞን ይመኑ

በአማራ የማንነት ጥያቄ ዙሪይ ወያኔን ፍርሃትና ድንጋጤ ውስጥ በመክተት በተከፈተበት የማንነትና የህልውና ጥያቄ ለህዝባቸው በመጠየቃቸው በአደባባይ በጥይት አሩር መስዋእት የሆኑ ጀግኖቻችን የምናስብበት ቀን ነው። በዚህ ቀንም የእኛ ጀግኖች ገለው የሞቱ በመሆናቸው የልባችን ኩራት፤የርስታችን ወራሽ፤በርስታችን ተራራ ከፍ አድርገን የምንተክላቸው፤በክብር ከፍ ከፍ የምናደርጋቸው፤ ህያው የሆነ የማይነጥፍ የህልውና እና ከህልም የመባነን የመለከት ድምፅ የለፈፉ፤የጨለማውን ዘመን የብርሃን ወጋገን ፈንጣቂ፤በወያኔ ላይ የደም እዳቸውን ያልከፈልንላቸው፤ ምድራችን ባድማ እንዳትሆን የወያኔ የምድር አራዊትም ብዝበዛቸው እንዲበቃው የማንቂያ ዲወል ደዋዮች፤ የህልውናን ድንቅ ጽላት በልባችን አትመውት ያለፉ፤ የአማራው ህዝብ ለአመታት የተሸከመውን የወያኔ የጭቆና ቀንበር ፈንቅለው በመውጣት የተስፋ ብርሃን የሆኑ፤ ለአመታት የነገሰውን የእኔ ምን አገባኝ የለዘብተኛ አቋም የሰበሩ፤ የማይጠፍ የማንነታችን ነበልባል እሳት በልባችን ውስጥ የለኮሱ፤ የጠላቶቻችን መንጋጋ በመምታት የወያኔ ቅጥረኛ ክፉ ሰሪዎችን ጥርስ ያረገፉ፤ የህዝባቸውን መከራና ሸክም እንዲሁም ጫና ከልባቸው በሚነደው የእኔነት ስሜት ጠላትን በቁጣቸው የቀሰፉ፤ ለማንነታቸው ሲሉ ሰይፍን የሳሉ ቀስትን የገተሩ ለሞት የማይሰስቱ ፤ጀግኖች የሚዘከሩበት የአማራ ተጋድሎ ሰማእታት ቀን ነሐሴ ፩። ሃውልት የሆነው ስራቸውን በብረት በትር ጠብቀን የምንይዝበት የእኛ ሙሴዋቻችን ቀን ነሐሴ ፩፡፡ አሁንም በሞት ጣር እና በስቃይ ድምጽ ሁነው በወያኔ ወታደራዊ ማሰቃያዎች ያሉ ጀግኖቻችን የበለጠ የምናስብበትና መፍትሔ የምንፈልግበትና የምንመካከርበት ቀን እንዲሁም የወገኖቻችን የሰባዊ አያያዝ ሁኔታ የምናውቀውን ሁሉ መረጃ በመያዝ ወደ መፍትሔ የምንጓዝበት ድል አብሳሪ ቀን ነሐሴ ፩።

በዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት(ICC)የእስር ትእዛዝ የተቆረጠላቸው የአፍሪካ አምባገነኖች
** የሱዳኑ የፍትህና እኩልነት ንቅናቄ የጦር መሪ የሆነው ባህር አቡ ጋርዳ ከሌሎች ሃይሎች ጋ በመሆን በሱዳኑ የዳርፉር ጦርነት ወቅት በአፍሪካ ሰላም አስከባሪ ሃይሎች ሳይቀር ጉዳት በማድረሱ
** የኬንያው ሙሃመድ አሊ በወቅቱ የኬንያ ፖሊስ ኮሚሽነር የነበረ እና ከኬንያው ፐሬዚዳንት ምዋዊ ኪባኪ አማካሪ ከነበረው ከ ፍራንሲስ ሙታራ ጋር በመመሳጠር የፐሬዝዳንቱ ተቀናቃኝ የሆነው Orange Democratic Movement ጥቃት ሲፈጽም ኮሚሽነሩ ፖሊስ ጣልቃ ገብቶ ጥቃቱን ባለማክሸፉ ብዙ ንጹሃን በመሞታቸው እና ብዙ ግድያዎች ፤ አስገድዶ መድፈር እና ፆታዊ ትንኮሳ በመፈፀሙ
**የሱዳኑ ኦማር አልበሽር በዳርፉሩ ግጭት ወቅት ስልጣኑን ተጠቅሞ ወታደሩን፤ፖሊስን ፤የደህንነት ሃይሉን፤ እና ጃንጃ ሚኒሻዎችን በመያዝ ፉር፤ማሳሊትና ዛጋዋ ጎሳ ህዝቦችን አማጽያን ናቸው በማለት እንዲገደሉና እንዲደፈሩ ወሲባዊ ጥቃት እንዲደርስባቸውና ጅምላ ጭፍጨፋ እንዲደረግና ጎሳዎችንም የማጥፋት ስራ ሰርቷል፡፡
** የኮቲዲቫሩ ቻርለስ ብሌ ጎዴ በሰባዊነት ላይ የሚፈፀም ወንጀል ክስ የቀረበበት ሲሆን በወቅቱ የኮንግረስ ፓም አፍሪካ የተባለ የወጣቶችን ድርጅት የፐሬዝዳንት ሎረንት ባግቦ ደጋፊ የነበረ ድርጅት መሪ በነበረበት ወቅት አቢጃን አካባቢ በፐሬዝዳንቱ የምርጫ ተፎካካሪ በነበሩት በአላሳኔ ኦታራ(2010 ላይ)ንጹሃን ደጋፊዎች ላይ ከሎረንት ባግቦ ጋር ሁነው ባወጡት እቅድ መሰረት ብዙ ንጹሃን ተገለዋል፤ተደፍረዋል፤ተቀልተዋል እንዲሁም ኢ-ሰባዊ የሆነ አያያዝ በመያዛቸው ከሎረንት ባግቦ ጋር እና ከልጁ ሲሞን ባግቦ ጋር ለፍርድ ቀርበዋል፡፡
** የሊቢያው ጋዳፊ፤ልጁ ሳፊ አል እስላም ጋዳፊ ሊቢያ ላይ በተከናወነው ረጅም ግጭት
** የኬንያው ሁሩ ኬንያታ በፐሬዝዳንት ምዋእ ኪባኪ የምርጭ ወቅት እሱን በመደገፍ በተቃዋሚ ተፎካካሪ ደጋፊዎች ላይ ባደረሱት የብዙ ንጹሃ ግድያ
**ከዚህም ሌላ የኮንጎው ጀርሜን ካታንጋ፤የሊቢያው ቶሃሚ ካሊድ፤የኡጋንዳው ጆሴፍ ኮኔ፤ እንዲሁም በጣም ብዙ ተዘርዝረው የማያልቁ የአፍሪካ አምባገነኖች በህዝባቸው ላይ መሳሪያ ያነሱት እና ህዝባቸውን የጨፈጨፉት ባንድም ይሁን በሌላ መንገድ አንዴ ወጥተው በማይወርዱበት የአፍሪካ የእድሜ ልክ የስልጣን መንበር ላይ ሊያወርዳቸው የሚታገል ካፉ እስከ ገደፉ የጦር መሳሪያ የታጠቀ አማጺሃይል በመኖሩ ነው፡፡ ይህ ማለት አምባገነኖቹ ልክ ናቸው ማለቴ ሳይሆን እንቁ እና ብርቅ የሆነውን የአፍሪካ ስልጣን ለማስለቀቅ የሚችል ተፎካካሪ የትጥቅ አቅም ያለው አማጺ በመኖሩ ነው፡፡
ታዲያ ነብሰ በላውን የፍሽስቱን የወያኔ መንግስት በንጹሃን የባህርዳር ወጣቶች ላይ የተጠቀመው ስናይፐር የጦር መሳሪያ ከምንም በላይ ለፍትህና ዲሞክራሲ ሲሉ ባዶጃቸውን በወጡ ንፁሃን ዜጎች ላይ ሲሆን ይህም ግድያ በፓርላማ በሎሌው ሃይለማሪያም ግልፅ ትእዛዝ የተላለፈ የሞት አዋጅ ነው፡፡ ይህ እንግዲህ ወያኔ የፈጸመው ግድያ፤ድብደባ፤ከልክ ያለፈ በቀልና ሰባዊ መብት ረገጣ ባዶ እጁን ከወጣና መብቱን ከጠየቀ ህዝብ ጋ የተደረገ የዘር ማጥፋት ወንጀል ከላይ ከጠቀስኳቸው የአፍሪካ ጭራቆች በላይ በአማራው ላይ የወያኔ ፍሽስት መንግስት ብዙ ስቃይ ፈጽሟል፡፡ ይህም ምናልባት ለሰልፍ የወጣን ህዝብ በስናይፐር የገደለ የአለማችን ስር የሰደደ መንግስት ያደርገዋል፡፡
ዋ-ባሕር ዳር
*******
ልጆችሽን እንዳትረሽ ከጉያሽ የጠፉትም በአማራ ጠሉ ቅልብ የትግራዩ አጋዚና በአንዳንድ የአማራ ጠል የትግራይ ተወላጅ ባንዳዎች ሲቸገሩ ቤት ለእንግዳ ብለሽ የሰጠሻቸውን መጠለያ ለታማኙ ደም ለሚጠጣው መንግስታቸው በሩን ከፍተው የልጆችሽን የሞት ድግስ ደገሱበት እንዲሁም ለሆዱ ባደረ ጥቂት የስልጣን ጥመኛ የራስሽ እስትንፋስ ጭምር ለልጆችሽ ሞት ተባበሩ፡፡
ዛሬም ቢሆን ከጉያሽ ተደብቀው ጠረንሽን ሲማጉ የነበሩ ባንዳዎች ቀሪ ልጆችሽን ሊያስበሉ ተልኳቸውን ይዘው ተንኮልና ሼር ወደሚከወንበት የደም መሬት ተመልሰዋል ነገም በየዋህነት ትቀበያለሽ፡፡
ዋ- ባሕርዳር
«እናጽዳው ስላችሁ ግዴለም ስትሉ
አንበጣ አወደመው አገሩን በሙሉ
ዳመናው ሲዳምን ይወረዛል ገደል
ይዘገያል እንጅ መች ይረሳል በደል»
ይህ ስንኝ ከፌስቡክ ገጽ ወዳጀ የተዋስኩት ነው፡፡ ግን ገላጭ ስለሆነ ነው፡፡ ከሁሉም በላይ መስዋእት የሆኑትን ወንድሞቻችን ስናስብ የበለጠ እንድንተጋና የደማቸውን ዋጋ የምንከፍል እንሁን፡፡
ነሐሴ 1/2008 በባህርዳር የነፃነትና የፍትህ የፍና ወጊ ድምጽ ከፍ ብሎ ሲሰማ ብዙ ጀግና ወንድምና እህቶቻችን በወያኔ ነብሰ በላው ገዳይ መንግስት ያጣንበት ቀን በመሆኑ እችን ቀን ለኛ ለወገኖቻቸው ሲሉ በከፈሉት መስዋእትነት ፈጣሪ ነብሳቸውን በመልካም ስፍራ እንዲጎበኝልን የሁላችንም ፀሎት በመሆኑ ነብስ ይማርልን።
#ሰለሞን ይመኑ

Monday, August 7, 2017

ትግራይ ውስጥ ባሉ የንግድ ድርጅቶች የሚሰቀሉ ታፔላዎች በትግርኛ ቋንቋ ብቻ እንዲጻፉ አዋጅ ተደነገገ

ኢሳት ዜና
ትግራይ ውስጥ ባሉ የንግድ ድርጅቶች የሚሰቀሉ ታፔላዎች በትግርኛ ቋንቋ ብቻ እንዲጻፉ አዋጅ ተደነገገ።
የትግራይ ክልላዊ መንግስት፤ ማንኛውም የንግድ ማስታወቂያ ታፔላና የግድግዳ ላይ ማስታወቂያ መልዕክቶች በትግርኛ ቋንቋ እንዲፃፉ የሚያዝ አስገዳጅ አዋጅ ሰሞኑን አፀድቆ በስራ ላይ መዋል መጀመሩን አስታወቀ። እንደ አድማስ ዘገባ የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አዋጁን እንዲያስፈፅም ኃላፊነት እንደተሰጠው የቢሮው ኃላፊ ተናግረዋል። ኃላፊው አቶ ዳዊት ኃይሉ አዋጁ ማንኛውም የንግድ ድርጅትም ሆነ አገልግሎት ሰጪ ተቋም፤ የውጪ ተሰቃይ ማስታወቂያውን ወደ ትግርኛ እንዲለውጥ የሚያስገድድ መሆኑን ጠቁመው፤ አዋጁን ተግባራዊ ያላደረገ ድርጅቱ እንደሚታሸግበት አስታውቀዋል። ቀደም ሲል እንዲህ ያለ አስገዳጅ ህግ ባለመኖሩ፣ በክልሉ ከተሞች የሚሰቀሉ የግድግዳ ...ላይ ማስታወቂያዎችና ታፔላዎች የተዘበራረቀ ቋንቋ ይጠቀሙ እንደነበር አቶ ዳዊ አውስተዋል። ኃላፊው አክለውም ይህን የሚያስቀር አዋጅ መፅደቁ ለክልሉ ቋንቋዎች እድገት አስተዋፅኦ ያበረክታል ብለዋል። አዋጁ ገና በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ባይወጣም የመቀሌ ከተማ አብዛኞቹ የንግድ ቤቶችና ተቋማት አዋጁ መውጣቱን ተከትሎ ታፔላቸውን ወደ ትግርኛ ቋንቋ በመቀየር ተጠምደው ሰንብተዋል። በታፔላዎቹ ላይ ጎላ ተደርጎ ከሚቀመጠው ከትግርኛ ቀጥሎ ሌላ ማንኛውንም ቋንቋ መጠቀም እንደሚቻል አቶ ዳዊት አክለው ገልፀዋል፡፡ አማርኛ የፌዴራል ቋንቋ ፣ትግራይ የፌዴራል ስርዓቱ አንድ ክልል ብትሆንም አዲሱ አዋጅ ታፔላዎች ከትግርኛ ጎን ለጎን በአማርኛም ቢሆን እንዲጻፉ አይፈቅድም።

Sunday, August 6, 2017

በባህርዳር ሁለት የቦምብ ፍንዳታ ደረሰ | ከተማዋ በአጋዚ ወታደሮች ተወራለች



Filed unde     


File Photo
(ዘ-ሐበሻ) በአምባገነኑ ሕወሓት መራሹ መንግስት ባለፈው ዓመት ነሐሴ 1,2008 ዓ.ም የተገደሉትን ከ50 በላይ ንጹሃን ዜጎች ለማሰብ በባህርዳር ነገ ሰኞ የቤት ያለመውጣት አድማ የተጠራ ሲሆን በከተማዋ ዛሬ ሁለት ቦምብ መፈንዳቱን የዘ-ሐበሻ ምንጮች ገለጹ::
እንደዘ-ሐበሻ ምንጮች ገለጻ የቦምብ ፍንዳታው የተፈጸመው በባህርዳር በተለምዶው 11 ቀበሌ ብ አዴን ጽህፈት አቅራቢያ እና ፔዳ መስመር በሚባል አካባቢ ነው::
ለሁለቱ ቦምብ ፍንዳታዎች ኃላፊነቱን የወሰደ አካል ባይኖርም በባህርዳር በአሁኑ ወቅት ጥብቅ ፍተሻ እየተደረገ መሆኑንና ከተማዋም በወታደሮች መከበቧ ታውቋል::
ባህርዳር ነገ ሰኞ ሕዝቡ አድማውን በተሳካ ሁኔታ ያከናውናል ተብሎ ይጠበቃል::

Friday, August 4, 2017

Ethiopia: Bahir Dar to commemorate youth massacred by regime security


ESAT News (August 4, 2017)
The city of Bahir Dar is to commemorate the massacre of over 50 anti-government protesters in August 2016 by snipers of the regime security.
Organizers of the commemoration told ESAT that they have called for a stay at home strike for Monday August 7, 2017, the one year anniversary of the mass killings. Over 50 youth were shot and killed by security forces on that fateful day.
The organizers also called on the people of the city of Gondar to join the commemoration to show respect for the youth who lost their lives in the brutal actions of the Agazi forces, special forces of the TPLF.
The protests in the Amhara region was mainly sparked by the demand by the people of Wolkait in Gondar for the restoration of their identity as well as land annexed to Tigray by the Tigrayan dominated regime.
At least 200 people were killed in the protest in Gondar and Bahir Dar last year as the Amhara region joined the anti-government protest in the Oromo region where security forces killed at least 1500 people.

Thursday, August 3, 2017

በአዲስ አባባ የመጠጥ ዉሃ እና የኤሌክትሪክ ኅይል እጥረት ተከስቷል


Filed under: News Feature,የዕለቱ ዜናዎች |


 



file photo
ይድነቃቸው ከበደ

በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች ከፍተኛ የሆነ የንፁህ መጠጥ ዉሃ እጥረት ተከስቷል። በከተማዋ ከሚያጋጥመዉ የመጠጥ ዉሃ መቆራረጥና መጥፋት ባሻገር የንጽህና ጉድለትም ሌላዉ አሳሳቢ ችግር ነው ።በከተማው ውስጥ የተፈጠረው የዉሃ እጥረት ችግር ተከትሎ ፤ ከመኖሪያ ቤት እረጅም እርቀት በመጓዝ ለበርካታ ስዓታት በመሰለፍ ለአንድ ጀሪካን ዉኃ እስከ 20 ብር ግዢ እየተፈጸሙ ሲሆን፣ የአዲስ አበባ ነዋሪ የዝናብ ዉሃ በጀረኪና እና በባልዲ በማጠራቀም የእለት ፍጆታን እንደ-አማራጭ እየተጠቀመ ነው። የዉሃ መጥፋትና መቆራረጥ በአዲስ አበባ የተለመደ ችግር ሲሆን፣ የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት የሚመለከተው አካል በአፋጣኝ ምላሽ መስጠት አልቻለም።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር እና የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ጣቢያዎች በአብዛኛውን ግንባታቸው ተጠናቆል እየተባለ በሰፊው ቢወራም፤ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጡ ቀርቶ በመደበኛነት እስከ ሁለት እና ሦስት ቀን ድረስ በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች መብራት እየጠፋ ነው።
ሆኖም ግን በአገር ውስጥ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ እና መጥፋት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ለጎረቤት አገር ከፍተኛ መጠን ያለው የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ እየተከናወነ ነው።በአዲስ አበባ ከተማ ያለው የመብራት ኃይል አቅርቦት ችግር በነዋሪዎች ላይ እያስከተለ ያለው ጉዳት መጠኑ እየጨመረ ሲሆን፣ በአገልግሎት መስጫ ተቋማት ፣በንግድ ቤቶች ፣ አነስተኛ ምርት አምራቾች ላይ የኤሌክትሪክ ኃይል እና የንፁህ ውሃ መጠጥ መጥፋት እና መቆራረጥ ከፍተኛ የሆነ ችግር እየፈጠረ ነው።

ሰበር መረጃ….. የብሄራዊ መረጃ እና የመከላከያ ወታደራዊ ደህንነቶች ከፍተኛ አሰሳ እያደረገ እንደሚገኝ ታምናኝ ምንጮች አሳወቁ – ልኡል አለሜ


  
By ሳተናውAugust 3, 2017 06:33



ሐምሌ 05/2009
Members of the Ethiopian army patrol
ክልል ስድስት እየተባለ በሚጠራዉ በቤንሻንጉል ጉምዝ በርታ አካባቢ ምስጥራዊ በሆነ ቅንጅት በመከላከያ ወታደራዊ ዘርፍ እና በብሄራዊ መረጃ የልዩ ስልጠና ክፍል ላለፉት 6 ወራት የአርበኞች ግንቦት 7 ወታደሮሮች ነን በሚል መልኩ ሲሰለጥኑ የነበሩ 9 ወጣቶችን ጭነዉ ወደ አሶሳ ሲጓዙ የነበሩ ሁለት ኮድ አ.አ ላንድ ክሩዘር ተሽከርካሪዎች የደረሱበት መጥፋታቸዉን ተንተርሶ የብሄራዊ መረጃ እና የመከላከያ ወታደራዊ ደህንነቶች በክልሉ ከፍተኛ አሰሳ እያደረገ እንደሚገኝ ታምናኝ ምንጮች አሳወቁ።
በተደጋጋሚ የአርበኞች ግንቦት 7ን ወታደሮች ማረኩኝ እንዲሁም እጅ ሰጡ  እያለ ፕሮፓጋንዳዉን የሚነዛዉ የህወሃት ቡድን እነዚህን 9 ሰልጣኞች ላለፉት 6 ወራት ኮነሬል ተስፋዬ በተባለ በኦሮምያ ክልል የአዲስ አበባን መስፋፋት ማስተር ፕላኑን በመቃወም በአምቦ ለተቃዉሞ ሰልፍ የወጡ ወጣቶችን በጭካኔ እንዲታደኑና ከፍተኛ ኢሰባዊ ግፍ እንዲፈጸምባቸዉ ትእዛዝ በመስጠት በሚታወቅ መኮንን ይሰለጥኑ የነበረ ሲሆን
በስልጠናዉ ላይ የመመሪያና የተዋረድ ንድፎችን በማዉጣት ኮነሬል ገብረ ዮሓንስ ግንባር ቀደም  የኦፕሬሽን ሐላፊ በመሆን በከፍተኛ ሚስጥር ይከዉኑት እንደነበር መረጃዎች ጠቁመዋል
ወጣቶቹ ለከፍተኛ የሽብር ተግባር የተቀናበሩና ከአዲስ አበባ እንዲሁም ከሰሜን ሸዋ የተመለመሉ ከፍተኛ የገንዘብ ወጪም የተደረገባቸዉ ነበሩ።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !

Wednesday, August 2, 2017

ፕ/ር መረራን እንዲህ በካቴና አስረው ፍርድ ቤት ማቅረባቸውን ስናይ የሰዎቹን በቀለኝነትና ሰውን በማንገላታት የሚያገኙትን እርካታ የሚያሳይ ነው


 ሳተናውAugust 1, 2017 15:01
  

ዶ/ር መረራ ለዛሬ ሃምሌ 25/2009 ተቀጥረው የነበረው በክሱ ላይ በማስረጃ ዝርዝር የተጠቀሱ የአቃቤ ህግ ምስክሮችን ዝርዝር ለተከሳሽ (ዶ/ር መረራ) ማሳወቅን ወይም አለማሳወቅን በተመለከተ የፌደሬሽን ምክር ቤትን ምላሽ (ትርጓሜ) ለመስማት ነበር።
ሆኖም የ19ኛ ችሎት ዳኞች ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ምላሽ እንዳላገኙ በመግለፅ፤ ፌደሬሽን ምክር ቤት ለህገመንግስት አጣሪ ኮሚቴ ትርጓሜውን እንዲሰራ የላከው ደብዳቤ ግልባጭ እንደደረሳቸው ተናግረዋል።
የዶ/ር መረራ ጉዲና ጠበቃዎች የሚከተለውን ሃሳብ አንስተው ተከራክረዋል። ደንበኛችን ከታሰሩ 9ወር ሆኗቸዋል፤ የተፋጠነ ፍትህ የማግኘት መብታቸው እየተከበረ አይደለም፤ ፌደሬሽን ምክር ቤት የተላከው የትርጉም ጉዳይ ፍ/ቤቱ በራሱ የሚወስነው ነገር ስለሆነ ችሎቱ ራሱ ቢወስን፤ ተመሳሳይ ወንጀሎችን የሚያየው 4ኛ ችሎት ተመሳሳይ ጉዳዮችን ችሎቱ በራሱ ነው የሚወስነው፤ ደንበኛችን ከቆዩበት ጊዜ አንፃር፣ ከእድሜያቸው፣ ካበረከቱት አስተዋፅኦ እና ከጤናቸው አኳያ ክሳቸው በክረምትም እንዲታይ እና አጭር ቀጠሮ እንዲሰጥ ጠይቀዋል።
በሌላ በኩል የዶ/ር መረራ ጠበቃ ዶ/ር ያእቆብ ሃ/ማርያም፤ “የታደሰ የጥብቅና ፈቃድ እና ውክልና እያለኝ ወህኒ ቤቱ ደንበኛዬ ዶ/ር መረራን እንዳላገኝ ከልክሎኛል። ስለሆነም ፍርድ ቤቱ በህገመንግስቱ አንቀፅ 21 መሰረት ደንበኛዬን እንዳገኝ ለወህኒ ቤቱ ትእዛዝ እንዲሰጥልኝ አመለክታለሁ።” ሲሉ አቤቱታቸውን አቅርበዋል።
ዳኞችም የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተዋል። የምስክሮች ጥበቃ አዋጅ እና በፀረሽብር ህጉ አንቀፅ 32 ላይ የተደነገገው ህገመንግስታዊ ትርጉሙ አሻሚ መሆኑን የገለፁት ዳኞች፤ ተከሳሽ የአቃቤ ህግ ምስክሮች የመቅረብ ያለመቅረብን በተመለከተ ያቀረቡትን መቃወሚያቸውን ውድቅ ሚያደርጉ ካልሆነ በስተቀር የፌዴሬሽን ምክርቤትን ትርጓሜ መጠበቅ ግድ መሆኑን ገልፀዋል። 4ኛ ችሎት ተመሰሳሳይ ጉዳዬችን በራሱ ይሰራዋል የተባለውን ጉዳይ በተመለከተ፤ ለሌሎች ችሎቶች ገዢ የሚሆነው ሰበር ሰሚ ችሎት የሚሰጠው ውሳኔ ብቻ መሆኑን ጠቅሰዋል— ዳኞቹ። ክሱ በክረምት እንዲታይ ለቀረበላቸው ጥያቄ፤ የፍርድ ቤቱ የእረፍት ጊዜ በመቃረቡ እና የዛሬ አመት ክስ የተመሰረተበት መዝገብ ጉዳይ እስከ ነሃሴ 12, 2009 ስለሚያዩ፤ የእነ ዶ/ር መረራን መዝገብ በክረምት ማየት እንደማይችሉ ተናግረዋል።
በዚህም መሰረት የፌዴሬሽን ምክርቤትን ምላሽ ለመጠባበቅ ለጥቅምት 6/2010 ቀጠሮ ሰጥተዋል። የጠበቃ ዶ/ር ያእቆብን አቤቱታ በተመለከተም ለቃሊቲ ማረሚያ ቤት ደንበኛቸውን እንዲያገናኟቸው ትእዛዝ እንዲወጣ ተብሏል።