Saturday, October 8, 2016

የትግራይ ተወላጆች ቢሾፍቱን ለቀው እየወጡ ይገኛሉ


Bishoftu, Ethiopia
በደብረዘይት (ቢሾፍቱ) ይኖሩ የነበሩ የትግራይ ተወላጆች ዛሬ   ሙሉ በሙሉ ከተማዋን ለቀው መውጣታቸውን በስልክ ካነጋገርናቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ማረጋገጥ ችለናል።
የትግራይ ተወላጆቹ ከተማዋን ለቅቀው የወጡት በቢሾፍቱ የኢሬቻ በዓል የሰዎች ሕይወት መጥፋቱን ተከትሎ የአካባቢው ሕዝብ ከጫፍ እስከጫፍ ነቅሎ በወውጣት እያካሀደ ባለው ሕዝባዊ አመጽ ሊመጣ ካለው አደጋ ለማምለጥ ነው ተብሏል። ህወሃት በዜጎች ላይ እየፈጸመ ያለውን ግድያ በከተማዋ ያሉ ሁሉ ሲቃወም የትግራይ ተወላጆች ግን ዝም ማለታቸው ሕዝቡን በእጅጉ እንዳስቆጣው ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።
የትግራይ ተወላጆቹ ሃብት ንብረታቸውን እየጣሉ ከተማዋን ለቅቀው ወዴት እንደሄዱ የታወቀ ነገር የለም።
ላለፉት አራት ቀናት በደብረዘይት እንደ አብዛኞቹ ከተሞች የንግድ እና የስራ እንቅስቃሴ ቆሟል። ሱቆች ተዘግተዋል፣ ሕዝብም ከቤቱ አይወጣም። አልፎ አልፎ የከባድ መሳርያ ድምጽ የሚሰማ ሲሆን መንግስታዊ ተቋማት እና ከህወሃት/ኦህዴድ ጋር ንክኪ ያላቸው ተቋማት ወድመዋል።
በናዝሬት መግቢያ የምትገኘው ዱላላ ማርያም ወረዳ የህወሃት/ኦህዴድ ንብረቶች እና ጽ/ቤቶች ወድመዋል። ሊበን ጭቆላ ወረዳ አመራሩ ተነስቶ ወረዳው በሕዝብ እየተመራ ይገኛል። ወንጂ የስኳር ፋብሪካው ብቻ ሳይሆን አገዳውም ሙሉ በሙሉ መቃጠሉን ከስፍራው ያነጋገርናቸው እማኞች አረጋግጠዋል።
ከዱከም አንስቶ እስከ አገረማርያም የሚወስደው የጦር ቀጠና በመምሰሉ ምንም አይነት ተሽከርካሪ ላለፉት 6 ቀናት እንዳላዩ እማኞች በስልክ ተናግረዋል። ከደቡብ መስመር አንጻራዊ ሰላም የሚታየው በአዋሳ ከተማ ብቻ ነው።
በዲላ እና ወንዶገነት የህወሃት ባልሰልጣናት መኖርያ ቤቶች አጋይቶባቸዋል። ባለስልጣናቱ እና ከድሬዎቹ በሙሉ ከተማዎቹን እየለቀቁ ወደ አዋሳ ከተማ ገብተዋል።
በዲላ መስጊዶች እና አብያተ-ክርስትያናት በዛሬው እለት ባልታወቀ ሃይል ወድመዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች የህወሃት ካድሬዎች ሆን በለው የሃይማኖት ጸብ ለመቀስቀስ እንዳቃጠሉት ነው የሚናገሩት።
ደምቢዶሎ እና ምእራብ አርሲ የጦር ቀጠና ሆነው መሰንበታቸውን እና በጦርነቱ በርካታ ሰዎች ማለቃቸን የአሜሪካ ድምጽ ራድዮ እማኞችን ጠቅሶ ዘግቧል።

No comments:

Post a Comment