Tuesday, January 31, 2017

በኔ እምነት በማህበራዊ ሜድያው እጅግ ተሸንፈናል። Wondemagegnehu Addis


ኢትዮጲያ እንድትበታተን እንቅልፍ አጥተው ከሚያድሩ ግለሰቦችና ቡድኖች ምን እንጠብቅ እንደነበር አልገባኝም? አንዳች በጎ ነገር? ምን እንደምንጠብቅ ባለማወቃችን ሽንፈታችን በመደበኛነት እየታየ መጥቷል። እኛ ሳናውቃቸው እነሱ ግን ልባችንን በርብረው ስላወቁት አጠቃላይ አካሄዳችንን ተቆጣጥረውታል።
አንድ ሁለት አረረፍተ ነገር ወርወር ያደርጉና 1ወር ያንጫጩናል። እኛ ለነሱ መልስ ስንሰጥ በመንጋ ተከታዮቻቸው እንወረራለን። አንዳንዶቻችን አፀፋችንን ተመጣጣኝ ያደረግን እየመሰለን እነሱ በሄዱበት መንገድ ምላሽ ስንሰጥ ወጥመዳቸው ውስጥ እንገባላቸዋለን። እነሱም ሲጀመርም ይሄንን ትርፍ አስልተው ነው የሚያደርጉትን የሚያደርጉት። እሰጥ አገባው በርካታ ቁስሎችን በማህበረሰቦቻችን መሀል ፈጥሮ ያልፋል።
ትንሽ አረፍ ስንል ሌላው ደሞ በሆነች ሀረግ ጠቅ ያደርገንና ዞር ይላል። እኛም ወደተለመደው ተግባራችን እንመለሳለን። ለኛ የቤት ስራ ሰጥቶን እሱ ስራውን ይሰራል።
እስኪ እናስተውል ከንዲህ አይነት ድግግሞሽ እስካሁን ያተረፍነው ነገር ምንድነው? ድንገት ብቅ እያሉ እንደፈለጋቸው ሲያንጋጉን፣ ወዲያና ወዲህ ሲያመላልሱን እንዴት መንቃት ተሳነን? ሁሌ መከላከል አይበቃንም ወይ?ከነሱ ምንም አይነት ሀላፊነት የተሞላው ድርጊት መጠበቅ የለብንም። ከሚነሳው አቧራ እነሱ የሚያጋብሱት ፋይዳ እንጂ የሚያጎሉት ምንም የለም። እኛ ግን ብዙ እናጎላለን። ጠላትን ማበሳጨትና ማሳሳት የሚለውን ስሌት በሚገባ እየተገበሩት ነው። አሁን ለኛ የሚጠቅመን ትግሉ ላይ ማተኮር ብቻ ነው። እዚያ ላይ ጊዜያችንን እና አቅማችንን ልናውል ይገባል። ወቅታዊ ከሆኑት እንኩዋን የቅማንት ፣ የቴድሮው አድሀኖም አረ መአት ጉዳዮች ጉዳዮች አሉን።

በኢትዮጲያ አንድነት እናምናለን የምንል ወገኖች መጀመሪያ በመሀከላችን ያለውን ቀዳዳ እንድፈን። ያልሰራናቸው በርካታ የቤት ስራዎች አሉን። እንደ ኢትዮጲያዊ ጠንክረን ስንወጣና በልዩነቶቻችን ተከባብረን መታየት ስንችል ትርጉም ያለው ተፅእኖ ልንፈጥር እንችላለን። በቀላሉ የማንደፈርና የማንገሰስ እንሆናለን። እንከበራለን እንታፈራለንም። ያን ጊዜ የምንለው ይሰማል። አጀንዳ መስጠት የኛ ተራ ይሆናል።
ስለዚህ ትኩረት የምንሰጣቸውን ጉዳዮች እንለይ። አላስፈላጊ በሆነ ጉዳይ ተጠምደን አስፈላጊውን ጉዳይ እያሳደርን ለአፍራሾች ኢላማ አንመቻች።

ጉደኛውን ተራራ (Tullu Gudo) አየነው

ጉደኛውን ተራራ (Tullu Gudo) አየነው!


ዝዋይ ሐይቅ፣ በተለምዶ ዝዋይ በምትባለው ባቱ ከተማ ዳርቻ ላይ፣ በታላቁ ስምጥ ሸለቆ ውስጥ፣ ከአዲስ አበባ በስተደቡብ 100 ማይሎች ርቆ የሚገኝ፣ 440 ስኵዌር ኪሎ ሜትር የሚሰፋ፣ ብዙም የማይወራለት፣ ብዙም ያልለማ፣ ታሪካዊ እና ተፈጥሯዊ ፋይዳው የላቀ፣ ትልቅ ሐይቅ ነው። ሐይቁ 5 ደሴቶች …

የኢሳያስ መንግስት ለቴዎድሮስ አድሃኖም የአለም ጤና ምርጫ የድጋፍ ድምፅ በመስጠት የቁርጥ ቀን ወዳጅነቱን አረጋግጧል፡፡ ( Tesfaye Ru )

   


የኢሳያስ አፈወርቂ ጠላት አማራ እንጂ ወያኔ አለመሆኑን የኢሳያስ መንግስት ለቴዎድሮስ አድሃኖም የአለም ጤና ምርጫ የድጋፍ ድምፅ በመስጠት የቁርጥ ቀን ወዳጅነቱን አረጋግጧል፡፡( Tesfaye Ru )

ኤርትራ ላይ ያከማቸው ቁጥር አልባ የትህዴን ሰራዊት ዝግጅት ከአማራ ጋር ለሚደረግ የወደፊት ጦርነት ነው፡፡ ግንቦት 7ን የሚደግፈው፤ በግንቦት 7 በኩል አማራን ለመውጋት ሳይሆን፥ የአማራ ቁጣ ቀን ተሸሽጓ ማምለጫ ከለላ እንዲሆነው ይመስላል፡፡ ግንቦት 7 ለወያኔና ሻዕቢያ የመጨረሻው ከጥፋት የማምለጫ ካርድ ሊሆን ይችላል፡፡

ስልጣን ከ2ቱ ትግሬዎች ሲያመልጥ፥ የግንቦት 7 ፖለቲካ ን የይቅርታ መንገድ አድርገው ለመጠቀም ይፈልጋሉ፡፡ይህ ማለት ግንቦት 7 የአማራ ህዝብ ጠላት ነው ማለት ሳይሆን፥ በአንድነት ስም ዳግም ከኢትዮጵያ ጋር ለመቀጠል በር ከፋች መርህ ስላለው ነው፡፡ የማይቀረው እውነታ ይህ ነው፦ ወልቃይት አማራ ነኝ ማለት በጀመረበት ሰዓት፤ ይሮቦችም እኛም አማራ ነን ማለት ጀምረው ነበር፡፡ ይህ ምን ማለት ነው፦ ከሰሜናዊ ትግራይ እስከ ምፅዋ ወደብ የሚኖሩ ህዝቦች እኛም ከአማራ ጎን እንሰለፋለን ማለታቸው ነው፡፡

ይህ ማለት፦ አክሱም የአማራ ነው፣ ወልቃይትም የአማራ ነው፣ ምፅዋም የአማራ ነው፣ ሃሰብም የአማራ ነው፡፡ መቀሌና አስመራ ግን ብትፈልጉ ገደል ግቡ ማለት ነው፡፡መጪዋ ኢትዮጵያ የአሰመራና የመቀሌ ትግሬን በወገንነት ሳይሆን በጠላትነት የፈረጀች አዲስ አገር ልትሆን የምትችልበት ሰፊ አማራጭ አለ፡፡

Monday, January 30, 2017

በቅማንትና አማራ ስም ህዝብ ለማፋጀት አዲስ እቅድ ወጣ! ሕዝብ ይወቀው! ከፍተኛ ጥንቃቄ!


   

በቅማንትና አማራ ስም ህዝብ ለማፋጀት አዲስ እቅድ ወጣ!
ሕዝብ ይወቀው! Must Share! ከፍተኛ ጥንቃቄ!
የሰሜን ጎንደርን ህዝብ በቅማንት እና አማራ የማይገቡ ወረዳና ቀበሌዎችን በማካለል የውሸት ሪፈረደምን ተግባራዊ በማድረግ የእርስ በርስ ጦርነት እንዲያደርጉ እና እነሱም ጣልቃ በመግባት የሚፈልጉትን በግላጭ ለመግደልና ለማሰቃየት እኩይ ተግባሩን በቀላሉ ለማሳለጥ የሚያስችሉ ካድሬዎቹን አሰልጥኖ ስራ አስጀምሯል፡፡ ወያኔ የሚያደርገውን ደም አፋሳሽ አዲስና ተጨማሪ ክለላ ህዝቡ ሆን ተብሎ እንደተቀነባበረ ሊያውቅና እንደበፊት ቀደሙ በከፍተኛ ብልሃት እንዲያልፉት የሚፈጠረውን ችግር እንዲያመክን መልእክቱ በአስቸኳይ ለሁሉም እንዲዳረስ ይሁን።
ይህንን መሰሉን መሰሪ የወያኔ መርዛማ እቅድ ለማሳካት ዛሬ የሰሜን ጎንደር ዞን የፀጥታ አመራሮች ሁሉም ደባርቅ ነበሩ። የፀጥታ አመራሮች፣ የፖሊስና የልዩኃይል ኃላፊዎች አስቸኳይ ስብሰባ ማድረጋቸው ታውቋል።
ከሁለት አመት በፊት ጀምሮ ወያኔ የወልቃይት ጥያቄ በተለይ ጎልቶ ሲመጣበት በፍቅርና በአንድነት የሚኖረውን የጎንደርን ሕዝብ እርስ በእርስ ለማፋጀት የቅማንትና የአማራ በሚል ትልቅ አደጋ ማድረሱ ይታወቃል። ይህን መሰሪ ተግባር የጎንደር ህዝብ አንከፋፈልም በማለት ጠንካራ ምላሽ ቢሰጥም ወያኔ በዚህ መርዛማ ተግባሩ ሊቀጥል መወሰኑን በተደጋጋሚ መዘገባችን ይታወሳል። በቅርቡ ዋሽንግተን ዲ.ሲ. የወያኔ ኢምባሲ ለሰበሰቧቸው ካድሬወች ጎንደር ያለውን ከባድ ህዝባዊ ትግል ለማክሸፍ የአማራና የቅማንት አጀንዳን ዳግም እንደሚቀሰቅሱት መረጃው ደርሶን አጋልጠናል።
ሙሉነህ ዮሃንስ

ኢትዮጵያ ሰውነታቸውን ባገኙት አጋጣሚ በመሸጥ የሚተዳደሩ ፖለቲከኞች አያስፈልጓትም! ኄኖክ የሺጥላ

ኢትዮጵያ ሰውነታቸውን ባገኙት አጋጣሚ በመሸጥ የሚተዳደሩ ፖለቲከኞች አያስፈልጓትም! ኄኖክ የሺጥላ


ኢትዮጵያ ሰውነታቸውን ባገኙት አጋጣሚ በመሸጥ የሚተዳደሩ ፖለቲከኞች አያስፈልጓትም!
ኤርሚያስ ለገሰ በዋሽንግተን ዲሲ በተደረገው የመፅሃፉ ምረቃው ላይ እነ ሌንጮ ባቲን አመስግኗል። ምክንያት አድርጎ ያቀረበውም « እንዴት እየሄደልህ ነው እያሉ ስለሚጠይቁኝ ነው» ብሏል ። ስለ 11 መፅሃፍ ያነሳው አስቆኛል!
ሰማይ የነካ ቀጣፊነት እና አድርባይነት ማለት ይሄ ነው! በዚህ ችሎታው ነበር የበረከት ስምዖን ሎሌ የነበረው። ኢትዮጵያ እንዲህ ያሉ ሰውነታቸውን ባገኙት አጋጣሚ በመሸጥ የሚተዳደሩ ፖለቲከኞች አያስፈልጓትም! የሚያወሩት ምንም ይሁን ምን የሚያወሩትን የሚያወሩት አምነውበት አይደለም! የፖለቲካ ፍጆታ መሆን የሚችል ፥ የሎሌነት ዘመን ታሪካቸውን መፅሃፍ አድርገው ቢሸጡልን እዳው ገብስ ነው።
እርግጥ አዲስ ማንነትን የወረሱ መስሎን ቀርበናቸው ነበር! ግን ለአዲስ ማንነት ያልተፈጠሩ እንደሆኑ በሂደት በወዳጅነት ዘመናችን ልረዳ ችያለሁ! ከሚሉት ውስጥ አንዱንም አያምኑበትም ! አምታቾች ናቸው! ሰውነትን የነጠፉ ጥርብ ሎሌዎች! እንዲህ ያሉት ሰዎች They are cancerous and an obstacle for the creation of a free spirited generation !
ኄኖክ የሺጥላ

ተቃዋሚዎች በድርድር ቅድመ ሁኔታዎቻቸውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳና የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ ይጠይቃሉ


   

አዲስ አድማስ
ተቃዋሚዎች ከኢህአዴግ ጋር ቅድሚያ ሰጥተው ሊደራደሩባቸው የሚሿቸውን አጀንዳዎች ለአዲስ አድማስ የገለፁ ሲሆን፤ ሁሉም ፓርቲዎች የጋራ አቋም ላይ ለመድረስ ጥረት እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል፡፡
መኢአድና ሰማያዊ ፓርቲ፤ ከኢህአዴግ ጋር ወደ ሌላ ውይይት ከመግባታቸው በፊት የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ እንደሚጠይቁ ገልጸው፤ ማንኛውንም የህዝብ ጥቅም በድርድሩ አሳልፈው እንደማይሰጡ ተናግረዋል፡፡
ኢዴፓ በበኩሉ፤ ከምንም አስቀድሞ፣ ላለፉት 25 ዓመታት ኢህአዴግ በተቃዋሚዎች ላይ ሲፈፅም የነበረውን የመብት ጥሰት አምኖ እንዲቀበል እደራደራለሁ፤ ብሏል፡፡
የመኢአድ ዋና ፀሐፊ አቶ አዳነ ጥላሁን፤ በተጀመረው ድርድርና ውይይት ከተቃዋሚዎች ባሻገር በሀገር ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ቡድኖችና ግለሰቦችም መሳተፍ አለባቸው፤ የሚል አቋም እንዳለው ጠቁመው፤ “የፖለቲካ እስረኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱና በፖለቲካ ሰበብ የተመሰረተ ክስ እንዲቋረጥ” የሚሉ ጥያቄዎችን ለድርድር እናቀርባለን፤ ብለዋል፡፡
በተጨማሪም፣ አሁን በስራ ላይ ያለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲነሳና የፀረ ሽብር አዋጁ ለፓርቲዎች እንቅስቃሴ እንቅፋት በመሆኑ እንዲፈተሽ ወይም እንዲሰረዝ የሚል አቋም ይዘው ወደ ድርድሩ እንደሚገቡ ዋና ጸሐፊው ጠቁመዋል።
መኢአድ በአገሪቱ ተከስቶ የነበረው ግጭት እንዲበርድና የፖለቲካ ድርድር እንዲካሄድ ተቋማት ጣልቃ ገብተው እንዲሸመግሉ፤ ለሁሉም ዋና ዋና የእምነት ተቋማት ማመልከቻ አስገብቶ እንደነበር ያስታወሱት አቶ አዳነ፤ በጎ ምላሽ የሰጠችው ግን፣ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ብቻ ነበረች፤ ብለዋል፡፡
“ይህን የመሳሰሉ ጥረቶች ስናደርግ የቆየን በመሆኑ፣ ወደ ድርድሩ ልንገባ ችለናል፤” ያሉት አቶ አዳነ፤ “በአንዳንድ የማህበረሰብ ሚዲያዎች፣ መኢአድ የህዝብን ጥቅም አሳልፎ እንደሸጠ መቆጠሩ አግባብ አይደለም፤” ሲል ወቅሰዋል፡፡
ኢዴፓ በበኩሉ፤ ወደ ድርድር ከመገባቱ በፊት፣ ባለፉት 25 ዓመታት በተቃዋሚዎች ላይ ከህገ መንግስቱ ውጪ ለተፈፀመባቸው በደል መንግስት ተጠያቂ መሆኑንና ስህተት መስራቱን አምኖ መቀበል አለበት፤ የሚል አቋም መያዙን፣ የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ወንድወሰን ተሾመ አስታውቀዋል፡፡“ብዙዎቹ ሲጣሱ የነበሩ መብቶች፣ በህገ መንግስቱ ላይ የሰፈሩ ናቸው” የሚሉት አቶ ወንድወሰን፤ “መንግስት ህገ – መንግስቱን፣ በመጣስ ፓርቲዎችን ሲበድል መቆየቱን መቀበል አለበት፤” ብለዋል፡፡ “ህዝብ ሲያነሳቸው የነበሩ ሁሉም ጥያቄዎች መመመለስ አለባቸው” የሚል አቋም ይዞ ወደ ድርድሩ እንደሚገባ የገለፁት ኃላፊው፤ እነዚህንም ለማሳካት በፅናት እንደሚደራደር አመልክተዋል፡፡
የሠማያዊ ፓርቲ ሊቀ መንበር፤ (በሊቀመንበርነታቸው ጉዳይ የምርጫ ቦርድ ውሳኔ ይጠበቃል) አቶ የሸዋስ አሰፋ፣ በአርቲስት ዘለቀ ገሠሠ የሚመራ ቡድንን ጨምሮ ሌሎች ቡድኖች በተደጋጋሚ ለድርድሩ እንዲቀርቡ እያነጋገሯቸው እንደነበርና ጥሪውንም ከኢህአዴግ ሳይሆን ከነዚህ ወገኖች ይጠብቁ እንደነበር አብራርተው፣ አሁን በኢህአዴግ መጠራቱ ያልጠበቁት መሆኑን ይገልፃሉ።
ፓርቲያቸው ከዚህ ድርድር የሚጠብቀው ውጤት ወደ ዲሞክራሲያዊ ስርአት የሚደረግ ሽግግር መሆኑን የጠቆሙት አቶ የሸዋስ፤ “ዋናው አላማችን ሃገርና ህዝብን ማዳን፣ የህዝብን ጥያቄ ማስመለስና ለህዝብ መብቶች መከራከር ነው፤” ብለዋል፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ ‹‹በድርድሩ ተሳታፊ መሆን የነበረባቸው በእስር ላይ የሚገኙ ፖለቲከኞች እንዲፈቱ፣ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታሠሩ ሰዎች በቅድሚያ እንዲለቀቁ›› የሚል አቋም ይዞ ወደ ድርድሩ እንደሚገባ አቶ የሸዋስ አስታውቀዋል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁም እንዲነሳ ጥያቄ እንደሚያቀርብ አቶ የሸዋስ ጠቁመዋል፡፡
ፓርቲዎች፣ “ማን ድርድሩን ይምራ፤ እነማን ይታዘቡት፤ ሚዲያዎች እንዴት ይዘግቡት፤›› በሚሉ ጉዳዮችና በድርድሩ እንዲወያዩባቸው የሚፈልጓቸውን ርዕሠ ጉዳዮች በዝርዝር በማዘጋጀት እስከ ጥር 25 ለፓርላማ ጽ/ቤት እንደሚያስገቡ ይጠበቃል፡፡

ፓትርያርኩ: አወዛጋቢው የአዲስ አበባ አድባራት ከደረጃ ዝቅ የተደረጉ፤ ከሥራና ደመወዝ የታገዱና የተሰናበቱ ሠራተኞች ዝውውር አቤቱታ እንዲጣራ አዘዙ


 

ከደረጃ ዝቅ የተደረጉ፤ ከሥራና ደመወዝ የታገዱና የተሰናበቱ ይገኙበታል
የዋና ሥራ አስኪያጁ አካሔድ የፓትርያርኩን መመሪያ የጣሰ ነው፤ ተብሏል
ከሚገባቸው በላይ የሰው ኃይል ክምችት በመያዝ እየተጨናነቁ በሚገኙት የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት፣ የሚካሔደው የሓላፊዎችና የሠራተኞች ዝውውር እንዲሁም ከሥራ የማገድና የማሰናበት ርምጃ በአስቸኳይ እንዲጣራ፣ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ አዘዙ፡፡
ፓትርያርኩ ትእዛዙን የሰጡት፣ በመ/ር ጎይትኦም ያይኑ ዋና ሥራ አስኪያጅነት የሚመራው የሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት፣ ከሕግና ሥነ ሥርዓት ውጭ የአስተዳደር በደል አድርሶብናል፤ የሚሉ የሃያ አመልካቾችን አቤቱታ፣ በአካልና በጽሑፍ ከተቀበሉ በኋላ በልዩ ጽ/ቤታቸው በኩል በጻፉት ደብዳቤ ነው፡፡
ከአስተዳዳሪነት ጀምሮ ባሉት የጽ/ቤት ሓላፊነቶች የሚሠሩት አቤቱታ አቅራቢዎቹ፦ ደመወዝ፣ አበልና የሥራ ደረጃን በሚቀንስ እንዲሁም፣ የተዛወሩበትን የሥራ መደብ፣ ደመወዝና አበል በማይጠቅስ ውሳኔ ተገቢ ያልሆነ ዝውውር ተፈጽሞብናል፤ ባልተጣራና ባልተወሰነ የሥራ ግድፈት ከሥራና ደመወዝ እንድንታገድና እንድንሰናበት በማድረግ በደል ደርሶብናል፤ በሚል ማመልከታቸውንና ፍትሐዊ ውሳኔ እንዲሰጣቸው መጠየቃቸውን ልዩ ጽ/ቤቱ በደብዳቤው ገልጿል፡፡
ሠራተኞቹ፣ ከአንዱ አጥቢያ ወደ ሌላው እንዲዛወሩ፤ ከሥራና ደመወዝ እንዲሰናበቱ የተደረገበት ማስረጃ ተገቢነት፣ ካቀረቡት አቤቱታና ከቤተ ክርስቲያኒቱ ሕግጋት አንፃር እየተገናዘበ በሀገረ ስብከቱ አስተዳደር ጉባኤ እንዲመረመር ፓትርያርኩ አዘዋል፤ አፈጻጸሙም፣ ሕጋዊውን አሠራር ያልተከተለ ኾኖ ሲገኝ፣ የሀገረ ስብከቱ አስተዳደር በምልዓተ ጉባኤ አስተካክሎና አርሞ አፋጣኝ ውሳኔ በመስጠት፣ ውጤቱ በአስቸኳይ እንዲገለጽላቸው በመመሪያቸው ማሳሰባቸውንም ልዩ ጽ/ቤቱ አስታውቋል፡፡
አቤቱታው፣ ባለፈው ኅዳር ለጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ቀርቦ የታየና ሀገረ ስብከቱ በሕጉ መሠረት አስቸኳይ አስተዳደራዊ ውሳኔ እንዲሰጥ አስቀድሞ የታዘዘበት ከመሆኑም በላይ፤ ለሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም፣ ለሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንና ለፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴርም ደርሶ በሚመለከተው አካል መፍትሔ እንዲያገኝ ሲጠየቅ መቆየቱ ተወስቷል፡፡
አቤት ባዮቹ፣ በተለይ ለሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም በጻፉት ደብዳቤ፣ የሀ/ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ፥ ከሕገ ወጥ ዝውውር በተጨማሪ፣ የሙስና ተግባራትን እንደሚፈጽሙና ያለምንም ጥፋት ከባድ ማስጠንቀቂያ የጻፉባቸውም ይህን በመቃወማቸውና የመብት ጥያቄ በማንሣታቸው እንደኾነ በቅሬታቸው ጠቅሰዋል፡፡
በሌላ በኩል፣ አቤቱታውን የሚያጣራ ስምንት አባላት ያሉት ቡድን ባለፈው ማክሰኞ በዋና ሥራ አስኪያጁ ተቋቁሞ ጉዳዩን የሚመለከት ሰነድ በማስቀረብ ሲያጠና መቆየቱን የጠቀሱ የሀገረ ስብከቱ ምንጮች፤ የማጣራቱ ውጤትም፣ ከትላንት በስቲያ በተካሔደውና ዋና ሥራ አስኪያጁን ጨምሮ 11 የዋና ክፍል ሓላፊዎች በተገኙበት የአስተዳደር ጉባኤ ታይቶ ውሳኔ ማግኘቱን ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡
ምንጮቹ እንደተናገሩት፣ ከኻያዎቹ አቅራቢዎች መካከል፣ ሦስት የአድባራት ጸሐፊዎች፣ በዝውውሩ የተቀነሰባቸው ደመወዝ ካለ ባሉበት እንዲስተካከል፤ ታቦት ታቅፈው ሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት ድረስ ይዘው በመምጣት ከፍተኛ ድፍረትና የቀኖና ጥሰት ፈጽመዋል በሚል ከሥራና ደመወዝ በተሰናበቱ አንድ አለቃና ሦስት ሠራተኞች ላይ የተወሰደው የማሰናበት ውሳኔ ባለበት እንዲጸና፤ የተቀሩት 13 ሠራተኞችም፣ ይቅርታ እየጠየቁ በተገኘው ቦታ እንዲመደቡ መወሰኑን አስታውቀዋል፡፡
በበርካታ የሰነድ ማስረጃዎች የተደገፈውን አቤቱታ ማጣራት የሚገባው፣ 14 አባላት ያሉት የሀገረ ስብከቱ አስተዳደር ጉባኤ እንጂ፣ ዋና ሥራ አስኪያጁ በራሳቸው መርጠው ያቋቋሙት ቡድን አለመኾኑን የሚጠቅሱ ወገኖች በበኩላቸው፤ አካሔዱ፣ የፓትርያርኩን መመሪያ እንደሚፃረር፤ በጥቅማጥቅምና በአቅም ማነስ የተሠሩ የጽ/ቤቱን ስሕተቶች ለመሸፋፈን የተደረገ ሙከራ በመሆኑ እንደሚቃወሙት ገልጸዋል፡፡
በሕገ ቤተ ክርስቲያን በሰፈረው የልዩ ሀገረ ስብከት ድንጋጌ መሠረት፣ በፓትርያርኩ የበላይ ሓላፊነት የሚመራው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት፤ በእገሌ ሥራና በጀት እየተባሉ መዋቅርን፣ ዕውቀትን፣ ልምድንና በጀትን ማዕከል ባላደረጉ የዝውውር፣ ቅጥርና ሽግሽግ አሠራሮች ጋራ ተያይዘው በሚነሡ ውዝግቦች እየታወከ እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡ ራሱን ችሎ ሊቀ ጳጳስ እንዲመደብለትና ሓላፊነትና ተጠያቂነት ያለበት ጠንካራ መዋቅርና አደረጃጀት እንዲዘረጋለት የተላለፉ ውሳኔዎች አፈጻጸምም መጓተቱን ምንጮች ጨምረው ገልጸዋል፡፡

ለሊዮ ቶሎስቶይ የተጻፈ ደብዳቤ – ዲ/ን ዳንኤል ክብረት



(እውነተኛ የሰሙኑ ገጠመኝ) – ለሊዮ ቶሎስቶይ የተጻፈ ደብዳቤ – ዲ/ን ዳንኤል ክብረት
አንድ ወዳጄ ከሳምንታት በፊት አንድ ቴአትር ይጽፍና በአዲስ አበባ ከተማ ካሉት ቴአትር ቤቶች ወደ አንዱ ይሄዳል፡፡ ድርሰቱን ለግምገማ እንዲያስገባ ይነገረዋል፡፡ አስገባ፡፡ በቀደም ዕለት የግምገማውን ውጤት ለማየት ወደ ቤተ ተውኔቱ ያመራል፡፡ መዝገብ ቤቶቹም “የግምገማው ውጤት ደርሷል፡፡ መታወቂያዎትን አሳይተው ፈርመው መውሰድ ይችላሉ” ይሉታል፡፡ ከደረት ኪሱ መዥለጥ አድርጎ መታወቂያውን ሰጣቸው። የመዝገብ ቤቱ ባልደረባ መታወቂያውንና ደብዳቤውን አስተያየና “እርስዎ መውሰድ አይችሉም፤ መውሰድ የሚችለው ደራሲው ነው” ይሉታል፡፡ እርሱም ደረቱን ነፍቶ “የድርሰቱ ባለቤት እኔ ነኝና ልውሰድ” ይላል፡፡ መዝገብ ቤቶቹም “እዚህ ላይ የተጻፈው ግን የእርስዎ ስም ሳይሆን የደራሲው ስም ነው” ይሉታል፡፡ ግራ ገባው፡፡ እዚህ ቴአትር ቤት ይህንኑ ድርሰት ይዞ የመጣ ሌላ ደራሲ ይኖር ይሆን? ብሎ አሰበ። የትርጉም ሥራዎች አንዱ ችግር ይህ ነው፡፡ የተለያዩ ሰዎች አንድን ሥራ ያውም በተመሳሳይ ጊዜ ተርጉመው ሊያቀርቡት ይችላሉ፡፡
“የተጻፈውን ደብዳቤ ማየት እችላለሁ” ይላል ወዳጄ፤ የተጻፈለትን ሰው ስም ለማየት ጓጉቶ፡፡
“መውሰድ አይችሉም እንጂ ማየትስ ይችላሉ” አለው፤ የመዝገብ ቤቱ ባልደረባ፡፡
ወዳጄ ወደ ማኅደሩ አንገቱን ልኮ ሲመለከተው ግን ክው ብሎ ነበር የቀረው፡፡
የወዳጄ የቴአትር ደርሰት የዝነኛው ሩሲያዊ ደራሲ የሊዮ ቶሎይስቶይ ድርሰት ነው፡፡ ወዳጄ ወደ አማርኛ ተርጉሞ ነው ያቀረበው፡፡ በድርሰቱ ጽሑፍ ላይ “ደራሲ ሊዮ ቶሎይስቶይ፣ ተርጓሚ እገሌ” ይላል፡፡ አስደናቂው የቴአትር ቤቱ ደብዳቤ  “ለአቶ ሊዮ ቶሎይስቶይ” ተብሎ ነው የተጻፈው። ለዚህ ነበር መዝገብ ቤቱ መስጠት የቸገረው። ወዳጄ መጀመሪያ ነደደው፣ ቀጥሎ ገረመው፣ በመጨረሻም ዞረበት፡፡ ለማረጋገጥም ፊርማና ማኅተሙን አየው፡፡
“ሊዮ ቶሎይስቶይኮ የለም” አለ ወዳጄ፤ የሚናገረው ነገር ግራ ገብቶት፡፡
“ታድያ አቶ ሊዮ ሲመጡ ይውሰዱ፣ ወይም እርስዎ ሕጋዊ ውክልና ይዘው ይምጡና ይውሰዱላቸው” አለ የመዝገብ ቤቱ ባልደረባ ነገሩን ያቀለለ መስሎት፡፡
“ከማን ነው ውክልና የማመጣው” አለ ወዳጄ፤ የማሽላ ሳቅ ስቆ፡፡
የመዝገብ ቤቱ ባልደረባ መነጽሩን አፍንጫው ላይ አስደግፎ መዝገቡን እያየ፤ “ከአቶ ሊዮ ቶሎይስቶይ ነዋ፡፡ ዛሬ’ኮ ውክልና ቀላል ሆኗል፡፡ በ30 ደቂቃ ይጨርሱታል፡፡ ወጭ ሀገር ከሆኑም መላክ ይችላሉ” አለው፡፡
“ሊዮ ቶሎይስቶይን ታውቀዋለህ?” አለው፡፡
“እዚህ ቴአትር ቤት ድርሰት ይዞ የሚመጣው ብዙ ነው፡፡ ስንቱን ዐውቀዋለሁ ብለው ነው። በተለይ ጀማሪ ደራሲዎችን አናውቃቸውም፡፡ ጀማሪ ጸሐፊ ይሆን?” አለና በግማሽ መነጽሩ እያየ መለሰለት፡፡ እንዴት አድርጎ ሊያስረዳው ይችላል። ሊቃውንት ተብለው የተቀመጡት ኮሚቴዎች ያላወቁትን፣ ይህንን የመዝገብ ቤት ሹም ዕወቅ ማለት ግፍ ነው፡፡ ‹ድኃው ምን አረገ ሊቆቹን ነው መርገም› አለ ገሞራው፡፡
“ሊዮ ቶሎይስቶይኮ ሞቷል፡፡ እንዴት ነው ለሞተ ሰው ደብዳቤ የምትጽፉት?”
“ውይ፣ ውይ፣ ውይ” ብሎ የመዝገብ ቤቱ ሹም አዘነ፡፡ ባያውቀውም በባህሉ መሠረት ለሞተ ሰው ማዘን ያለ ነው፡፡
“መቼ ነው የሞቱት? አይ ሰው መሆን ቴአትራቸው ሳይታይላቸው፤ ትንሽ ቢሆን ገንዘብ ሳያገኙ፤ አይ ሰው፤ ሰውና እንጨት ተሰባሪ ነው” አለ የመዝገብ ቤቱ ባልደረባ አንገቱን እየነቀነቀ፡፡
“የሞተውማ በ1903 ዓም የዛሬ 106 ዓመት በኅዳር ወር ነው” አለው ወዳጄ፡፡ የመዝገብ ቤቱ ባልደረባ ግራ ገባው፡፡ እስከዛሬ የተገመገመ ድራማ ሲያስረክብ እንጂ ድራማ ሠርቶ አያውቅም፤ አሁን ግን ራሱ ድራማ እየሠራ መሰለው፡፡
“አሁን የሚሉኝ ነገር እዚህ አንዳንዶች ጽፈው ከሚያመጡት የተሻለ ድራማ ይወጣዋል” አለና መዝገብ ቤቱ ሳቀ፡፡
“እንዴት የሚገመግሙት ሰዎች ሊዮ ቶሎይስቶይን አያውቁትም? ለመሆኑ ምን ተምረው ነው ገምጋሚ የሆኑት፡፡ የድርሰት አብነቶችን ሳያውቁ ምኑን ነው የሚገመግሙት? በ1821 ዓም ራሽያ ተወልዶ፣ በ1903 ዓ.ም የሞተውን ታላቁን የድርሰት ሰው ቶሎይስቶይን የማያውቅ የድርሰት ገምጋሚ፣ ቴአትሮቻችንን ቢጥል ምን ይገርማል። ቴአትር የማያውቁ ሰዎች ቴአትር ከገመገሙ ቴአትር ሞቷል በለኛ፡፡”
የመዝገብ ቤት ባልደረባው አንገቱን እየነቀነቀ “ጌታው እኛ የታዘዝነው፣ አቶ ሊዮ ቶሎይስቶይ ለሚባሉ ሰው አስፈርማችሁ ስጡ ተብለን ነው፡፡ እርስዎ ደግሞ ሞተዋል እያሉ ነው፡፡ ይሄ እንግዲህ ከዐቅማችን በላይ ነው፡፡ አለቆቻችንን ያነጋግሩ” አለው፡፡
ወዳጄም እያዘነም፣ እየተበሳጨም፣ እየተገረመም መጣና ተረከልን፡፡
አንድ መምህሬ “ጥበብ በነጋድያን እጅ ስትወድቅ ሸቀጥ፣ በሹመኞች እጅ ስትወድቅ ቀልድ፣ በሆዳሞች እጅ ስትወድቅ ዳቦ፣ በምንደኞች እጅ ስትወድቅ የሥራ ልብስ፣ በዐዋቂዎች እጅ ስትወድቅ ዘውድ ትሆናለች” ይሉ ነበር፡፡ ጥበብን የማያፈቅራት ሰው እንኳን ሊገመግማት ሊያደንቃት አይችልም፡፡ ታዋቂው ባለቅኔ መጋቤ ምሥጢር ወልደ ሩፋኤል ቅኔ ተቀኝቶ ሲወርድ፣ እንኳን ቅኔ ሊያውቅ ቋንቋው ያልቀናለት ሹም ያገኘውና ‹ይበል ነው› ይለዋል። መጋቤ ምሥጢርም “አንተ ከሰማኸውማ ምኑን ቅኔ ተቀኘሁት” አለ አሉ። ጥበብ መጀመሪያ ፍላጎት፣ ከዚያም ዕውቀት፣ ቀጥሎም ተመስጦ፣ በመጨረሻም አንክሮ ትሻለች። ጥበብን የተማረ ሁሉ አይደርስባትም፡፡ ‹አይቴ ብሔራ ለጥበብ – የጥበብ ሀገሯ ወዴት ነው› እያለ የሚፈልጋት እንጂ፡፡ ጥበብን የተሾመባት ሁሉ አያውቃትም፡፡ ‹ወበአይቴ ተረክበ አሠረ ፍኖታ – የጎዳናዋ ፍለጋ በወዴት ተገኘ› ብሎ የሚመረምራት እንጂ፡፡ ጥበብን ባለ ገንዘብ አይገዛትም፤ ‹መኑ ዐደወ ባሕረ ወተሣየጣ በወርቅ ቀይሕ – ባሕሩን ተሻግሮ በቀይ ወርቅ የገዛት ማነው?› እያለ በአንክሮ የሚከተላት እንጂ፡፡ ጥበብን ምንደኛ ቅጥረኛ አይደርስባትም፣ ‹ወመኑ ዐርገ መልዕልተ ደመናት ወአውረዳ – ከደመናት በላይ ወጥቶ ያወረዳት ማነው?› እያለ የሚመሰጥ እንጂ፡፡
የንጉሡ የዐፄ ኃይለ ሥላሴ አማች ደጃዝማች ካሣ፣ የመጀመሪያው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ሆነው ይሾማሉ፡፡ ዕውቀት በሹመት ይገኝ ይመስል፣ ደጃዝማቹ በዩኒቨርሲቲ በር እንኳን ሳያልፉ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ሆነው መሾማቸው ሕዝቡን አስደነቀው፡፡ በዚህ ጊዜ፡-
ላም እሳት ወለደች
ወንፊት ውኃ ቀዳ
ሺ ግመል አለፈ በመርፌ ቀዳዳ
በሰንበሌጥ ቁጣ ወደቀ አሉ ዋርካ
ተከካ አልተከካ
ተቦካ አልተቦካ
ተሳካ አልተሳካ
የምንቸገረኝ ቤት ሁል ጊዜ ፋሲካ
በትእዛዝ ሊቅ መሆን ይህም አለ ለካ፡፡
ተብሎ ተገጠመ ይባላል፡፡
አንዱ ጓደኛችንም ተርጓሚውን እንዲህ አለው፤ “ለምን ‹ለቶልስቶይ፣ ባለበት› ብለህ ደብዳቤ አትጽፍለትም፡፡
ይድረስ ለሊዮ ቶሎይስቶይ፡፡ ይኼው ከስምንተኛው ሺ መድረሳችን ታወቀ፡፡ ለዕውቀት ያልደረሱ፣ ለመብል ያላነሡ፣ በትእዛዝ ሊቅ፣ በድጋፍ ምሩቅ የሆኑ፣ አበል የሚሰበስባቸው፣ ጥበብ የማይገዳቸው የሀገሬ ሹማምንት መፈጠርህንም፣ መሞትህንም ሳያውቁ፤ በሞትክ በመቶ ስድስት ዓመትህ ከመዝገብ ቤት መጥተህ ደብዳቤ እንድትወስድ ጽፈውልሃል፡፡ ክቻልክ የገነትን ጠባቂ መልአክ አስፈቅደህ ናና፣ ደብዳቤህን ፈርመህ ውሰድ፡፡ ምናልባት የቀበሌ መታወቂያ ይቸግርህ ከሆነ፣ ምርጫ ሲደርስ ከመጣህ ማውጣቱ ይቀልሃል፡፡ የቤት ምዝገባ ሰሞን ግን እንዳትመጣ፡፡ አሳዛኙ ነገር ከ70 ዓመት በፊት ጽፈኸው ዓለምን ጉድ ያሰኘህበት ድርሰትህ፣ በቴአትር ቤታችን ገምጋሚ ኮሚቴ፣ ከልማታዊነትና ከሕዝባዊ ከብሔር ብሔረሰቦች መብት አንጻር ማረሚያ ስለተሰጠው፣ እርሱን አስተካክለህ እንደገና ለማሳተም መሬት ላይ መቆየት የግድ ሊሆንብህ ነው፡፡ ያውም ድርሰትህ የኋላ ዘመን መሆኑ ከታወቀ፣ የነፍጠኛና የጉልተኛ ድርሰት ነው ከመባል ከተረፈልህ ነው፡፡ ስትመጣ ስሙን እንጂ ድርሰቱን ብዙም ለማናውቀው የሀገርህ ሰው ለፑሽኪን ያሠራንለትን አደባባይ ትጎበኛለህ፡፡”

ድርድር ወይስ ውይይት? – ያሬድ ከፍያለው



ድርድር ወይስ ውይይት? – ያሬድ ከፍያለው
የአገራችን የፖለቲካ ምህዳር ለተቃዋሚዎች (እኔ “አማራጭ የፖለቲካ ሀይሎች” ማለቱን እመርጣለሁ) ፈታኝ እየሆነ መምጣቱን ብዙዎች ይስማማሉ። አማራጭ ኃይሎቹ  በተለያዩ መድረኮች ምህዳሩ እንዲሰፋ ገዥውን ፓርቲ ሲማጸኑ ቆይተዋል፤ በምህዳሩ መጥበብ ሳቢያ ሊከተሉ  የሚችሉ ችግሮችን በመጥቀስም ጭምር።  እንደ ብዙዎቹ እምነት፣ ገዥው ፓርቲ ለረጅም ጊዜያት  ለመድበለ ፓርቲ ስርዓት ቁርጠኝነት  ባለማሳየቱ፣ በየደረጃው የሚገኙ ደጋፊዎቹ አማራጭ ኃይሎችን ሲያዋክቡ ቆይተዋል።  በቅርቡ ግን ገዥው ፓርቲ ከአማራጭ  ኃይሎች ጋር ለመነጋገር የሚያስችል መድረክ ለማዘጋጀት መወሰኑ በብዙዎች ዘንድ ተስፋን ፈንጥቋል። አማራጭ የፖለቲካ ኃይሎቹ ለመገናኛ ብዙኃን (አዲስ አድማስ ጥር 13 ቀን 2009 እትምን ጨምሮ)  በሰጡት መግለጫ፤ በገዥው ፓርቲ በኩል ቅንነቱ ካለ መድረኩ የፖለቲካ ምህዳሩን  የሚያሻሽሉ ስምምነቶች ይደረሱበታል የሚል ተስፋ አላቸው። አንዳንዶቹ መድረኩ የድርድር መንፈስ እንዲኖረው ሲፈልጉ፣ ሌሎች  ደግሞ  በቅድሚያ ከገዥው ፓርቲ ጋር  በቅድመ ሁኔታዎች ላይ መግባባት እንደሚፈልጉ ገልጸዋል።
የመድረኩ ይዘት የውይይት ይሁን የድርድር ገና የተለየ አይመስለኝም። ሆኖም የሁለቱ (ውይይት እና ድርድር) መሰረታዊ ይዘታቸው የሚታወቅ በመሆኑ ለውጤታማነታቸው አስፈላጊ የሆኑ ቅድመ ሁኔታዎችን መናገር የሚከብድ አይሆንም።  በእኔ እምነት ውይይት ሰጥቶ መቀበልን  የማይጠይቅ በመሆኑ የመሳካት እድሉ ሰፊ ነው። ድርድር ግን  በባህሪው ሰጥቶ መቀበልን ይፈልጋል። ለድርድር ገዥውም ሆነ አማራጭ ኃይሎች የሚቀበሉትና የሚሰጡት  መሰረታዊ ነገር ያስፈልጋቸዋል።
የመድረኩ ይዘት የድርድር ከሆነ ኢህአዴግ አይሸራረፉም ብሎ  ደጋፊና ታማኝ አባሎቹን እስከማጣት የደረሰባቸው የፖለቲካ ባህል፣ አሰራር፣ አላማዎቹንና ግቦቹን ለድርድር ማቅረብን ሊጠይቀውም ይችላል። ከተሳካ  ለተቃዋሚ ኃይሎች ትልቅ ድል ይሆናል። ነገር ግን መነሳት ያለበት ጥያቄ አለ፤ የድርድር እድል ሊኖር ይችላልን? የሚል። በእኔ እምነት የድርድር መሰረታዊ ቅድመ ሁኔታዎች ስለሌሉ የድርድር እድሉ ዜሮ ነው።  መግባባት ካለ የሚሆነው ኢህአዴግ ቅንነቱ አይሎ አሊያም በአርቆ አሳቢነት ምህዳሩን ለማስተካከል ምክር ይጠይቃል፤ አማራጭ ኃይሎቹ የምህዳሩን ውስንነቶች ይዘረዝራሉ፤ ምክክሮችም ይደረጋሉ። በዚህም መሰረት ገዥው ፓርቲ ነባራዊ ሁኔታዎችን ከግምት አስገብቶ በፓርቲ ደረጃ የተስማማባቸውን እርምጃዎች ይወስዳል።
በዚህ መነሻነት አማራጭ ሃይሎቹ ሊያቀርቡዋቸው የሚገቡ የሚሻሻሉ  የአሰራር፣ የህግና የተቋማዊ አደረጃጀት ጉዳዮችን ለማየት እንሞክራለን።
የመጀመሪያ መሆን ያለበት ገዥው ፓርቲ፤ “ኢህአዴግ ለኢትዮጵያ ህዳሴ ብቸኛ ሀዋርያ ነው” በሚለው እምነትና አሰራር ምትክ፣ “አማራጭ ሃይሎች ለሃገሪቷ እድገት ጉልበት ናቸው” ወደሚል እምነት መሸጋገሩ ላይ እራሱም ሆነ አማራጭ ሀይሎቹ እርግጠኛ መሆን ይኖርባቸዋል። ለውጡን እውን ለማድረግም የሚወሰዱ ዝርዝር እርምጃዎች ሊቀመጡ ይገባል። ለውጡን  ለመለካት እንዲቻልም  ሊመዘኑ የሚችሉ መለኪያዎች መድረኩ ማስቀመጥ ይኖርበታል፡፡ የውጤቱ መዛኝ አካልና የምዘናው ወቅትም ከወዲሁ ስምምነት ሊደረስበት ያስፈልጋል። ይህም ከዚህ በፊት ሲታዩ የቆዩ «ምህዳሩን አስፍቻለሁ» የሚለው የገዥው ፓርቲ  መግለጫና  «ስቃይ ላይ ነን» የሚለው የአማራጭ ሃይሎች አቤቱታ፣ በመረጃ ላይ ብቻ  እንዲመረኮዝ ያግዛል። ምናልባት ከተከሰተ ማለት ነው።
ሌላው የፖለቲካ፣ የማህበራዊ፣ የኢኮኖሚና የእምነት ማህበራት ከተጽዕኖ ውጭ እንዲመሰረቱና እንዲተዳደሩ፣ ከወከባና ጫና ነጻ እንዲሆኑም  ማድረግ ሊሆን ይገባል። የተማሪዎች፣ የመምህራን፣ የሰራተኞች፣ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣ የንግድ፣ የሰብአዊ መብት፣ የእምነት፡ የባህል ማህበራትና ሌሎችም ከተጽዕኖ ነጻ ሆነው እንዲቋቋሙና እንዲተዳደሩ ማድረግ ላይ መነጋገር ይጠበቅባቸዋል። በተመሳሳይ ለውጡን  መገምገም እንዲቻል  ሊመዘኑ የሚችሉ መለኪያዎች በሚለኩበት ጊዜ ጭምር  ሊቀመጡ ይገባል። መዛኙ አካልም ከወዲሁ ስምምነት ሊደረስበት ይገባል።
የፖለቲካ አመለካከት ከሃገር ወገናዊነት በታች ስፍራ እንዲኖረው የሚያደርግ የፖለቲካ  ባህል እንዲዳብር መስራት ሌላው ይሆናል። ለምሳሌ በመንግስት ተቋማት የሚኖር ቅጥር፣ እድገት፣ ሹመት፣ የትምህርትና ስልጠና እና ሌሎች ጥቅማጥቅሞች ብቃትና ዜግነትን ብቻ ያማከለ እንዲሆን ማድረግ አንዱ ነው።  የገጠርና የከተማ ነዋሪዎች የማናቸውም የፖለቲካ ድርጅት አባል መሆን እንዲችሉ፣ ካልፈለጉም በሃገራቸው ፍሬዎችና እድሎች የመጠቀም እኩል መብት ያላቸው  መሆኑ ላይ ገዥው ፓርቲ በእምነትም ሆነ በአሰራር ቁርጠኝነት እንዲያሳይ የሚያደርጉ እርምጃዎች ላይ ጠንካራ ውይይት ሊደረግ ይገባል።  የሚጠበቁ ውጤቶችም ሊለኩ በሚችል መልኩ ሊቀመጡ  ያስፈልጋል። በተመሳሳይ ለውጡ ሊመዘንባቸው የሚያስችሉ የህግና የአሰራር መለኪያዎች በጊዜ ሰሌዳ መቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡
ምርጫ ቦርድ በመድብለ ፓርቲ ስርዓት ላይ ካለው ወሳኝነት አንጻር የቦርዱ አባላት አሰያየም፣ የጽ/ቤቱ  አደረጃጀት፣ የሃላፊዎችና ሰራተኞች ቅጥር  ሌላው  የውይይት ርዕስ ሊሆን የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡ ተመሳሳይ ለውጡን  ለመገምገም እንዲቻል  ሊመዘኑ የሚችሉ መለኪያዎች ሊበጁ ያስፈልጋል። መዛኙ አካልና የምዘናው ወቅትም እንዲሁ።
በፍትህ ስርዓቱ ነጻነት ላይ በሚታዩ ጉድለቶች ዙሪያ በተመሳሳይ ውይይት ያስፈልጋል። ከነገስታቱ ዘመን ጀምሮ በሃገራችን የተለመደው ገዥ ፓርቲ፣ በመንግስት ተቋማት ውስጥ ያለው ገደብ የለሽ ጣልቃ ገብነት በሃገሪቱ ውስጥ ለሚታዩ ብዙ ችግሮች መንስኤ በመሆኑ መለያ ሊበጅለት ያስፈልጋል። የመንግስት ተቋማትም  የተጣለባቸውን ሃላፊነት ከመወጣት ውጭ ገዢ ፓርቲውንና የፓርቲ አመራሮችን ዘላለማዊነት ለማጽናት  መትጋታቸውን እንዲያቆሙ መደረግ አለበት። በመከላከያና በጸጥታ አካላት ዙሪያም ውይይቱ ልዩ ትኩረት ሊሰጥ ይገባዋል።   እዚህ ላይ የሌሎች ሃገራት ተመክሮ ቀርቦ  ሊመከርበት ያስፈልጋል። ይህ ሲሆን የፍትህና የጸጥታ ኃይሎች፣ ስልጣን ላይ ላለው ገዥ ፓርቲ አገልጋይ ከመሆን ይልቅ ወደ መንግስትና ህዝብ አገልጋይነት  ይሸጋገራሉ።

ትራምፕ፤ ምርጫው መጭበርበሩን እንዲጣራ አደርጋለሁ አሉ



አዲሱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ ባለፈው የአገሪቱ ምርጫ፣ ከመራጮች ምዝገባ ጋር በተያያዘ የማጭበርበር ድርጊት መፈጸሙ እንዲጣራ የሚያደርግ ትዕዛዝ እንደሚሰጡ አስታውቀዋል፡፡
ትራምፕ ባለፈው ማክሰኞ በትዊተር ገጻቸው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ በሁለት ግዛቶች በመራጭነት የተመዘገቡ አሉ፣ ህጋዊ ያልሆኑ መራጮች ተመዝግበዋል፣ በህይወት የሌሉ ሰዎች ድምጽ ለመስጠት ተመዝግበዋል የሚሉትን ጨምሮ ከመራጮች ጋር በተያያዘ ተፈጽመዋል የተባሉ መጭበርበሮችን እንዲጣራ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል። በምርመራው የተገኘውን ውጤት መሰረት በማድረግም፣ የአገሪቱን የምርጫ ድምጽ አሰጣጥ ስርዓት የምናስተካክል ይሆናል ብለዋል ትራምፕ፡፡
ትራምፕ ተፈጽሟል የተባለውን መጭበርበር አጣራለሁ ይበሉ እንጂ፣ የመንግስት ባለስልጣናትና የምርጫ ሃላፊዎች በምርጫው ሂደት መጭበርበር መፈጸሙን የሚያመለክቱ ምንም አይነት ተጨባጭ ማስረጃዎች አለመቅረባቸውን ሲናገሩ መቆየታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ፕሬዚዳንቱ ይህን መግለጫ ያወጡት ባለፈው ማክሰኞ በተደረገው የዋይት ሃውስ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ቃል አቀባዩ ሻን ስፓይሰር፤” በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ህገወጥ ስደተኞች በምርጫው ድምጻቸውን ሰጥተዋል” ብለው መናገራቸውን ተከትሎ እንደሆነ ዘገባው ገልጧል፡፡
ቢቢሲ በበኩሉ፤ ትራምፕ የምርጫው ሰሞን ጀምሮ መጭበርበር መፈጸሙን በትዊተር ገጻቸው ላይ ባስተላለፏቸው መልዕክቶች ሲገልጹና “በምርጫው አምስት ሚሊዮን ያህል ህገ-ወጥ መራጮች ለሄላሪ ድምጻቸውን ሰጥተዋል” የሚል ክስ ሲያቀርቡ እንደነበር አስታውሶ፣ ይህን ክሳቸውን የሚደግፍ ምንም አይነት ማረጋገጫ አለማቅረባቸውን ዘግቧል፡፡

የባቡሩም የስኳሩም… ያስደነግጣል! ( ኤልያስ )

 


የባቡሩም የስኳሩም… ያስደነግጣል! ( ኤልያስ )
“ፊዚቢሊቲ ስተዲ” እንኳን ለፕሮጀክት … ለትዳርም ያስፈልጋል
ባለፈው ረቡዕ ለንባብ የበቃው የአማርኛው “ሪፖርተር” ጋዜጣ በፊት ገፁ ላይ ያወጣው ዜና በእጅጉ ያስደነግጣል፡፡ (እንኳን ተበዳሪን … አበዳሪንም ጭምር!) ርዕሱ እንዲህ ይላል፡- “የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን በበጀት ዕጥረትና የዕዳ ጫና ፈተና ውስጥ መሆኑን ይፋ አደረገ” ጋዜጣው ላይ የወጣው የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ጌታቸው በትሩ ፎቶግራፍም የዜናውን ድባብ  የሚገልፅ ነው (ድንግጥ ብለዋል!) እውነት ለመናገር ፎቶግራፈሩን አድንቄዋለሁ!፡፡
በነገራችን ላይ … ገና ወደ ውስጥ ሳንገባ፣ ከርዕሱ በላይ የተደረደሩት ቁጥሮች (ዕዳዎች ማለቴ ነው!) የኛ ብቻ ሳይሆን፣ “የሶማሊያንም የሚጨምር ይመስላል፡፡ (ግን እሷ ደግሞ ባቡር የላትም!)
“የዕዳ ክምችቱ 102.5 ቢ. ብር ደርሷል”
“የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ኪሳራ 1.8 ቢ. ብር ነው፡፡”
“የቦንድ ሽያጭ ብድር 17.6 ቢ. ብር ደርሷል።”
የሚገርማችሁ ደግሞ መረጃውን ራሱ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ነው ይፋ ያደረገው። (ወዶ ይሁን ተገዶ አልታወቀም!) የጋዜጣው ዘገባው ይቀጥላል፡- “የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የፋይናንስ እጥረትና የብድር ግዴታ ክፍያዎች የ2009 ዓ.ም ፈተናዎች እንደሆነበት፣ በይፋ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የመንግስት ልማት ድርጅት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሳወቀ” ይላል፡፡ (የምን ዱብ ዕዳ ነው?!)
“ለበጀት ዓመት የገንዘብ ፍላጎት ታሳቢ የተደረጉት 25.9 ቢሊዮን ብር ወይም 43 በመቶ ከውጭ አገር የፋይናንስ ምንጭ በብድር፣ ቀሪውን 34.3 ቢሊዮን ብር ወይም 57 በመቶ ከአገር ውስጥ ምንጮች ለመሰብሰብ ነበር” የሚለው ዘገባው፤ ከውጭ ብድር ይገኛል የተባለው እስካሁን አለመገኘቱን ጠቁሞ፣ ከአገር ውስጥ ይገኛል ተብሎ የታቀደው 10.5 ቢሊዮን ብር ብቻ ከየት ሊገኝ እንደሚችል መታወቁን ገልጿል – ብሏል፡፡ (የአገር ውስጡም ቢሆን እርግጠኛ አይመስልም!)
ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በቅርቡ ስለ ስኳር ፕሮጀክታችን መጓተት አውስተው ሲያበቁ፤ በሌላ በኩል ደግሞ የባቡር ፕሮጀክቶቹ (የአዲስ አበባውም ይሁን የጅቡቲው) በአመርቂ ስኬቱ (በፍጥነት መጠናቀቁንም ይጨምራል!) ተጠቃሽ መሆኑን፣ በዓለም ላይ በዚያ ፍጥነት የሀዲድ መስመር ዘርግቶ ያጠናቀቀ እንደሌለ በመግለፅ … ደረታችንን እንድንነፋ የልብ ልብ ሰጥተውን ነበር፡፡
ለተጓተተው የስኳር ፕሮጀክትም ማካካሻ ሆኖን ነበር፡፡ (‹‹ባቡሬ መፅናኛዬ›› ዓይነት!) ግን እንዳለመታደል ብዙም ሳንቆይ… ባቡሩ የዕዳ ክምር እንዳለበት በይፋ ተነገረን (አናሳዝንም!) እናላችሁ …  “በአጠቃላይ የኮርፖሬሽኑ የዕዳ ክምችት በ2008 ዓ.ም መጨረሻ ከነበረበት 95.97 ቢሊዮን ብር፣ ወደ 105.52 ቢሊዮን ብር አድጓል” ይላል – የሪፖርተር ዘገባ። (ዱብዕዳ ነው!) በኋላ ላይ ግን ከዕዳውም በላይ ያስገረመኝ የኮርፖሬሽኑ ሥራ አስኪያጅ የገለጡት የማይታመን እውነታ ነው፡፡ እንዲህ ይላሉ፡- “የባቡር ፕሮጀክቶቹ ሲጀመሩ ዕዳ ውስጥ እንደሚገቡ ይታወቅ ነበር፡፡ እንደዚህ ያለ ፕሮጀክት ውስጥ ደፍረን የገባነው መውጫ እንፈልጋለን በሚል መርህ ነው” (ዓይን እያየ ዕዳ ውስጥ!) እኔ የምለው ግን በየፕሮጀክቱ በድፍረት መግባት ፋሽን ሆነ እንዴ?!
የሚቀጥለው አንድ ዓመት ለኮርፖሬሽኑ ፈተና እንደሚሆንበት የተናገሩት ዶ/ር ጌታቸው፤ በ2018 ግን መፍትሄ አለኝ ባይ ናቸው፡፡ (የተጠና ነው ያልተጠና?!) “የ2018 መውጫ መንገድህ ምንድን ነው ካላችሁ፣ የባቡር መስመሩን ከቱሪዝምና ከመሳሰሉት እሴት የሚጨምሩ ቢዝነስ ስራዎች ጋር እናቀናጀዋለን” በማለት ለም/ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ አብራርተዋል – ሥራ አስኪያጁ፡፡ (ይሄ የበለጠ አስፈራኝ!) እዚህኛውም ውስጥ ያለ ጥናት ቢገቡበትስ?!
የኮርፖሬሽኑ ኃላፊ እንደ መፍትሄ ካቀረቧቸው ሀሳቦች ውስጥ ለእኔ የተዋጠልኝ የመጨረሻው ብቻ ነው፡፡ (“ጨለምተኛ” የሚለውን ፍረጃ አልወደውም!) እናም … ዋና ሥራ አስፈፃሚው ምን አሉ መሰላችሁ? “የከፋ ነገር ቢመጣ ደግሞ የኮርፖሬሽኑን የተወሰነ ድርሻ ለውጭ ኢንቨስተሮች በመሸጥ የዕዳ ጫናውን መቀነስ ይቻላል” ዕዳ የተከመረበትን የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የ6 ወር ሪፖርት ያደመጠው የፓርላማው ቋሚ ኮሚቴ … ምን ቢል ጥሩ ነው? ትችትና ተግሳፅ ግን እንዳትጠብቁ፡፡  (“በርቱ አንበሶቼ!” ነው ያላቸው፡፡)
እንደውም የኮርፖሬሽኑን የፕሮጀክት አፈፃፀም አድንቋል፤ ቋሚ ኮሚቴው፡፡ ያልተጠናቀቁ ቀሪ ስራዎች እንዲያልቁም አሳስቧል ተብሏል፡፡ በተረፈ ግን … “ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር በመሆን የገንዘብ ችግሩ መፈታት አለበት” ብሏል፡፡  ግን ሌላው ቢቀር… የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ፤ “የባቡር ፕሮጀክቶቹ ሲጀመሩ ዕዳ ውስጥ እንደሚገቡ ይታወቅ ነበር፤ እንደዚህ ያለ ፕሮጀክት ውስጥ ደፍረን የገባነው መውጫ እንፈልጋለን … በሚል መርህ ነው” ሲሉ የተናገሩት ብቻውን … ፓርላማውን ሙሉ ቀን አያከራክረውም? በነገራችን ላይ የአስሩ የስኳር ፋብሪካዎች … ለአስር ዓመት መዘግየትና የ70 ቢ. ብር ኪሳራም … መንስኤው ሌላ ሳይሆን ‹‹በድፍረት ዘሎ መግባት›› መሆኑን … ጠ/ሚኒስትሩ በቅርቡ ለፓርላማ ሲያስረዱ የሰማሁ መሰለኝ፡፡ በአንድ ጊዜ 10 የስኳር ፋብሪካ ፕሮጀክቶች መጀመራቸው … ፋብሪካዎቹ እንዲቋቋሙ የተመረጡባቸው ቦታዎች አስቸጋሪነት … የአቅምና የባለሙያ ውስንነት … ፕሮጀክቱን እንዳጓተቱ አስረድተዋል። (ሁሉም ግን ራሱ መንግስት የፈጠራቸው ችግሮች ናቸው!!) በእነዚሁ ሁሉ ችግሮች ላይ ደግሞ “የአዋጭነት ጥናት” (feasibility study) ሳይሰራ በድፍረት በቀጥታ ወደ ፕሮጀክቶቹ ተገባ፡፡ (Adios! አለ ፈረንጅ!) ከዚያስ ውጤቱ ምን ሆነ? 10 ዓመት ሙሉ ጠብ የማይል የስኳር ፕሮጀክት!! (ላም አለኝ በሰማይ…!) እና .. እዚህ ገባ የማንለው የ70 ቢ. ብር ኪሳራ!! (ይሄም የብድር ዕዳ ሆኖ ብቅ ማለቱ አይቀርም!) እኔ አሁን እንደገባኝና ጠ/ሚኒስትሩም በፓርላማ ሊያስረዱ እንደጣሩት … በስኳር ፕሮጀክቶቹ ላይ የጠፋው ገንዘብና የባከነው ጊዜ፣ አገራዊ አቅምን ለመገንባት እንደዋለ ብንቆጥረው ነው የሚሻለው!”  (‹‹ውሾን ያነሳ ውሾ ነው!”)
ዋናው ቁም ነገር ግን የቢዝነስ ፕሮጀክት ውስጥ… ትዳር ውስጥም Feasibility Study ሳይሰራ ዘው ተብሎ አይገባም፡፡ (ፍቺ ይከተላላ!) ሽማግሌዎች እንኳን “ተጠናንታችኋል?” ይላሉ-ወጣቶች ትዳር ለመያዝ ሲቸኩሉ! (“ፊዚቢሊቲ ስተዲ ማለታቸው ነው!”)

‹‹…ነገሩ አልሆን ብሎ፣ ሁኔታው ሲጠጥር ጠጣሩ እንዲላላ፣ የላላውን ወጥር…›› የሚሉ በሳሎች ያስፈልጋሉ፡፡


   

Addis Admass ርዕሰ አንቀፅ
ልማድ የልጅነት አባዜ አለው፤ አድጎ ተመንድጎም ራሳችን ላይ ፎቅ ሊሰራብን ይችላል። መላቀቅ ያለብን ብዙ ልማድ አለ! ይሄ ከባህላችን፣ ከማህበራዊ ኑሯችን፣ ከፖለቲካችንና ጋር በቅርብ የተሳሰረ ነው፡፡ ስነ ልቦናዊ ግንኙነቱም ከዚሁ የሚመነጭ ነው፡፡ ይሄን ወደ አገር ጉዳይ መንዝሮ ማየት ጉዳዩን በሚገባ መሰረት ያበጅለታል፡፡ እየተዘወተሩና እየተለመዱ የሚመጡ የአገራችን ጉዳዮች ውለው አድረው፣ ጎልበተው መታየታቸው አይቀሬ ነው፡፡ ትናንሽ ዕቅዶች ወደ ትላልቅ ፈቅዶች የሚያድጉት ትናንሾቹ በአግባቡ ሲፈፀሙ ነው፡፡ ለዚያ የጊዜ ስሌት፣ የዝርዝር አያያዝና የቁጥጥርና ግምገማ ሥርዓት በአግባቡ ማዘጋጀት ተገቢ ነው፡፡ ይህን ፈፃሚውና አስፈፃሚው አካል፣ የራሱ አቅልና ብስለት ያለው ሊሆን ይገባል፡፡
እዚህ ላይ ነው እንግዲህ የራስ አመለካከት ከአገር አመለካከት ጋር ይራራቅና ጣጣ የሚያመጣው፡፡ እያንዳንዱን ሰው ቀርፆ፣ ሰው ለማድረግ አዳጋች ነው፡፡ ይህን የሚሠሩ ተቋማት እጅግ ጥቂት ናቸው፡፡ ለዚህ ብሩህ አስተዋፅኦ የሚያደርጉ የሲቪል ማህበራት ቁጥርም፣ አቅምም በጣም ውስን ነው፡፡ ይህ የሆነው ፋይዳቸውን ከልቡ ያመነበት ወገን ባለመኖሩ ነው፡፡ ጊዜም ባይኖር ጊዜ ወስዶ፣ ለጥያቄው መልስ መስጠት ያስፈልጋል፡፡ አማካዩ መንገድ ይሄው ነው፡፡ ከገዢው ፓርቲና ከተቃዋሚው ድርድር ባሻገር የህዝብን አስተሳሰብ የሚያሰባስብ፣ ወደ ተግባር እንዲያመራም የሚያግዝ ኃይል ያስፈልጋል፡፡
‹‹ከእናንተ ሌላ እኛም አለንኮ›› የሚል የህብረተሰብን ክፍል ማን ይታደገው ማለት አለብን፡፡ በጥቁርና በነጭ መካከል ያለውን ግራጫ መስመር፣ ስፋቱን ስለማንገነዘብ ጠቀሜታውም የዚያኑ ያህል ይሳሳብናል፡፡ ‹‹መካር የሌለው ንጉሥ፣ ለአንድ ዓመት አይነግሥ›› የሚለው አባባል፣ አበው ያለ ነገር አላሉትም፡፡ ለአመራሩ፣ ለገዢው ክፍል፣አማካሪ ያስፈልገዋል፡፡ በእርግጥ አማካሪ ሲባል በዕውቀት የረቀቀ፤ በልምድ የበለፀገና  ጊዜ ያስተማረው ሊሆን ይገባል! መንግሥት ሲቸኩል የሚያለዝበውም፣ ሲጠጥር የሚያልመው፤ ግትር ሲል የሚያላላው፣ አይዞህ ባይም፣ ገሳጭም፣ ነው የሚያሻው፡፡ የጥንት የጠዋቱ ገጣሚ ገሞራው፤ እንዳለው፡- ‹‹…ነገሩ አልሆን ብሎ፣ ሁኔታው ሲጠጥር ጠጣሩ እንዲላላ፣ የላላውን ወጥር…›› የሚሉ በሳሎች ያስፈልጋሉ፡፡ በመደራደር ብዙ መንገድ መሄድ ይቻላል፡፡
ነገር ግን አንድ ዕውነት መረሳት የለበትም፡፡ ማናቸውም ወገን ብቻውን በቂ አይደለም፡፡ ገና ሶስተኛም ወገን ተጨምሮ አይበቃም ብሎ ማሰብ ብልህነት ነው። ጉዳዩን መሠረታዊ የሚያደርገው የሀገራችን ችግር ስፋት ነው፡፡ የፍትሕ መጓደል፣ የዲሞክራሲ አለመብሰል፣ የሀብት አለመደላደል፣ የተቋማት ሥርዓት አለመሻሻል፣ መልካም አስተዳደር አለመታደል፣ ያልተመለሱት ጥያቄዎች መልስ አጥተው መንሳፈፍ፣ ወዘተ ምኑ ቅጡ! ለዚህ ነው አገር ሙሉ ድርጅት ቢፈጠር እንኳ የአገር ቋት አይሞላም የምንለው!
እነዚህ ሁሉ በቅጡ ቢሰባሰቡና ኢኮኖሚውን ካቀረቀረበት ቢያቀኑት ድንገት ፎቀቅ እንል እንደሁ እንጂ ነገረ-ሥራችን እንኳ ከድጡ ወደ ማጡ እየሆነብን መቸገራችን የዕለት የሠርክ ሀቅ ነው፡፡ ስለዚህ ተራው ዜጋ ‹‹የምበላው ሳጣ፣ ልጄ ጥርስ አወጣ›› ቢል አይፈረድበትም! ኑሮው ከሥረ-መሠረቱ እናሻሽልለት! በዓል በመጣ ቁጥር የሚሰቀቀው አያሌ ነው! የእኛን መጥገብ ብቻ አንይ!! ይህንን ተደራዳሪዎቹ ወገኖች፣ እነሆ ወቅቱ መጥቷልና በምን መቀነቻ አጥብቀን እንያዘው ብለው ማሰብ ይገባቸዋል፡፡ ፀፀታችንን ሳይሆን ነገርአችንን እናስብ! የመሪዎችን ጉባኤ ስናስብም የአገራችንን መረጋጋት እንፈይድ!!

የዶናልድ ትራምፕ ትርጉም፣ በኢትዮጵያና በኬንያ! ዮሃንስ ሰ.



• ድሮ… አሜሪካን እየተሳደብንም ቢሆን፣ እርዳታ አይቀርብንም ነበር
• (“የአሜሪካ ወዳጅነት መሆን ሌላ! የአሜሪካ እርዳታ መቀበል ሌላ!”)
• ዘንድሮ… የእርዳታ ገንዘብ የዶናልድ ትራምፕ ኢላማ ውስጥ ገብቷል።
• “ነገር ለሚፈልጉን፣ እርዳታ አንሰጥም”… እያሉ ነው – ሰውዬው።
“ሌሎች አገሮች ላይ፣ ጫና አናደርግም። እንዲህ አድርጉ… እንዲያ ሁኑ አንልም” የሚለው የዶናልድ ትራምፕ ንግግር፣ ለብዙ የአፍሪካ መንግስታት፣ በጣም አስደሳች ሊሆን ይችላል። ይህም ብቻ አይደለም። ሃሙስ እለት ለጉብኝት አሜሪካ የገቡት፣ የእንግሊዟ ጠቅላይ ሚኒስትር ቴረሳ ሜይ፣ ተመሳሳይ ሃሳብ ሰንዝረዋል። “ሌሎች አገሮችን በኛ አምሳል ለመቅረፅ ጣልቃ መግባት… ከእንግዲህ አይደገምም” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሯ። “ኪሳራ እንጂ ትርፍ የለውም። ጊዜው አልፎበታል” የሚል መልእክት ነው ያስተላለፉት።
የአፍሪካ መንግስታት፣ “ጣልቃ ገብነትም ሆነ ጫና፣ ከእንግዲህ አይኖርም” የሚል ንግግር ሲሰሙ፣ አብዛኞቹ እንደሚደሰቱ ባያጠራጥርም፤ ሌላ ጣጣ አለባቸው። የእርዳታ ገንዘብም፣ እንደ ድሮው እንደዘበት አንመድብም ብለዋል ትራምፕ። ይሄ፣ ለብዙ የአፍሪካ መንግስታት፣ በጣም አሳሳቢ ይሆንባቸዋል – ለኢትዮጵያም ጭምር።
ለበርካታ ተከታታይ ዓመታት፣ ከአሜሪካ መንግስት፣ ከፍተኛ የኢኮኖሚ እርዳታ በማግኘት ከሚጠቀሱ ቀዳሚ 10 አገራት መካከል፣ ኢትዮጵያ አንዷ ናት። አምና ደግሞ፣ አፍጋኒስታንን በመከተል፣ በ2ኛ ደረጃ የምትጠቀስ፣ ዋና እርዳታ ተቀባይ ሆናለች። 770 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ ደርሷታል (ከ17 ቢሊዮን ብር ገደማ)።
ለነገሩ ለኬንያና ለደቡብ ሱዳን፣ ለናይጄሪያና ለላይቤሪያ፣… ከአፍሪካ ውጭ ደግሞ ለዮርዳኖስና ለፓኪስታን የተለገሰው እርዳታም ቀላል አይደለም (እያንዳንዳቸው ከ4 እስከ 5 መቶ ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ እርዳታ ከአሜሪካ ተቀብለዋል።)
አስገራሚው ነገር ይሄ አይደለም። ምክንያቱም፣ የአሜሪካ እርዳታ፣ ከአመት አመት የማይቋረጥ ከመሆኑ የተነሳ፣ እንደ መደበኛ የገቢ ምንጭ የሚታይ ሆኗል። በቃ፣ ከአሜሪካ መንግስት እርዳታ መቀበል፣ በየአመቱ የተለመደ አይቀሬ ጉዳይ ነው። ለምሳሌ ኢትዮጵያ፣ ባለፉት ሰባት ተከታታይ ዓመታት፣ ሳንቲም አልጎደለባትም። ከአሜሪካ የሚመደብላት የእርዳታ ገንዘብ፣ ከ650 ሚሊዮን ዶላር በታች ሆኖባት አያውቅም። በሰባት ዓመታት ውስጥ 5 ቢሊዮን ዶላር እርዳታ አፍሳለች – ከአሜሪካ። እነ ዮርዳኖስና ፓኪስታን፣ ኬንያና ናይጄሪያም… እርዳታው ተቋርጦባቸው አያውቅም።
አዎ… እርዳታ እንደ መደበኛ የገቢ ምንጭ መታየቱ፣… “የሆነ የሚገርም ነገር” እንዳለው አልክድም። ግን፣ የተለመደ ጉዳይ ስለሆነ፣… እንደ ጉድ አይወራም።
አስገራሚው ነገር ሌላ ነው። ዋናዎቹ እርዳታ ተቀባይ አገራት፣ በአደባባይ… በዓለም መድረክ… የአሜሪካ “ወዳጆች” አለመምሰላቸው ነው አስገራሚው ነገር። በደፈናው፣ “የአሜሪካ አድናቂዎች አይደሉም” ብዬ ጥቅል የስሜት ድምዳሜ እየተናገርኩ እንዳልሆነ ልብ በሉልኝ። በቁጥር የተሰራ መረጃ አይቼ ነው የማቀርብላችሁ – በስሜት የተመራ ሳይሆን በስሌት የተቀመረ ድምዳሜ ላይ ለመድረስ።
ባለፈው ሐምሌ ወር፣ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት፣ በ72 ገፅ ሰንዶ ያቀረበው ሪፖርት፣ ምን ላይ ያተኮረ መሰላችሁ? በተባበሩት መንግስታት ጉባኤዎች ላይ፣ ከየአገሩ የመጡ የመንግስት ተወካዮች፣ ምን ምን ውሳኔዎችን እንደደገፉና እንደተቃወሙ ነው፣ ሪፖርቱ የሚዘረዝረው።
ሪፖርቱ እንደገለፀው፣ የዩኤን ጠቅላላ ጉባኤ፣ በአንድ አመት ውስጥ፣  79 ውሳኔዎችን አስተናግዷል። እያንዳንዱ ውሳኔ የሚተላለፈውም፣… የሁሉም አገራት ተወካዮች በሚሰጡት የድጋፍና የተቃውሞ ድምፅ ነው። እንግዲህ፣… ወዳጅና ጠላት የሚለየው እዚህ ላይ ነው።
ወዳጅ እና “ወዳጅ መሳይ”
ያው… እንደ ውሳኔው አይነት፣ የአሜሪካ መንግስት፣ አቋሙን ይገልፃል። በተቃውሞ ውሳኔውን ውድቅ ለማድረግ፣ ወይም ደግሞ ውሳኔውን ለማፅደቅ የድጋፍ ድምፅ ይሰጣል። ዋናዎቹ የአሜሪካ ወዳጆች፣ ብዙውን ጊዜ፣ የአሜሪካ አይነት ተመሳሳይ አቋም በመያዝ፣ ድምፃቸውን ይሰጣሉ። ድሮስ? ወዳጅነታቸው የተመሰረተው፣ ተቀራራቢ አስተሳሰብና አቋም በመያዛቸው አይደል? እናም በዩኤን መድረክ ላይ፣… ለምሳሌ… የካናዳ መንግስት አቋም ብዙውን ጊዜ ከአሜሪካ መንግስት ጋር ተመሳሳይ ነው። በቁጥር እንግለፀው።
የካናዳ መንግስት፣ በ65 ውሳኔዎች ላይ፣ ከአሜሪካ አቋሞች ጎን ቆሟል። በ5 ውሳኔዎች ላይ ግን፣ ተቃራኒ አቋም ይዟል። በአጭሩ፣ የካናዳ መንግስት፣ 90% ከአሜሪካ ጎን የሚቆም አስተማማኝ ወዳጅ ነው ማለት ይቻላል። የሚያለያይ ነገር የላቸውም ማለት አይደለም። አለ። ግን፣ ከሚያቃርን ይልቅ የሚያቀራርባቸው ነገር ይበልጣል። ወዳጅነታቸው የሚለካውም በዚሁ የሃሳብና የአቋም ቅርርባቸው ነው።
አውስትራሊያ፣ እንግሊዝና ፈረንሳይም፣ ብዙውን ጊዜ ከአሜሪካ ጎን ነው የሚቆሙት (በ80% ውሳኔዎች ላይ)። በሌላ አነጋገር፣ ከሚያለያያቸው ነገር ይልቅ፣ የሚያስማማቸው ነገር ይበዛል – አራት እጥፍ ያህል ነው። እነ ሃንጋሪና ፖላንድ ደግሞ፣ ከ70% በላይ ከአሜሪካ ጎን ይቆማሉ። ከካናዳና ከእንግሊዝ ጀምሮ፣ እነዚህን የመሳሰሉ አገራት  ናቸው ዋናዎቹ የአሜሪካ ወዳጆች። ግን ብዙ አይደሉም።
አምና፣ በዩኤን መድረክ፣ ከ50% በላይ በሆኑ ጉዳዮች ላይ፣ የአሜሪካ ጎን የቆሙ አገራት፣ 54 ብቻ ናቸው።
ከእነዚህ ቀጥላ የተጠቀሰችው አገር፣ ሩዋንዳ ናት። ሩዋንዳ፣ በ21 ጉዳዮች ላይ ከአሜሪካ ጎን ቆማለች። በ23 ጉዳዮች ላይ ደግሞ፣ ከአሜሪካ ጋር የሚቃረን ሃሳብ በመያዝ ድምፅ ሰጥታለች። ለአሜሪካ፣ የሩዋንዳ ወዳጅነት፣ “ግማሽ ግማሽ ነው” ልንለው እንችላለን።
ሌሎቹ 137 አገራትስ? ባላንጣ?
አብዛኞቹ የአለማችን አገራት፣ ብዙውን ጊዜ የአሜሪካ መንግስትን አቋም በመቃወም፣ ተቃራኒ ድምፅ የሚሰጡ አገራት ናቸው። ታዲያ፣ በሁሉም ነገር ላይ፣ የአሜሪካ ተቃራኒ ይሆናሉ ማለት አይደለም። ለምሳሌ የራሺያን አቋም መጥቀስ ይቻላል።
በ27 ጉዳዮች ላይ፣ የራሺያ አቋም፣ ከአሜሪካ አቋም ጋር አንድ አይነት ነበር። በ38 ጉዳዮች ላይ ግን፣ የራሺያ አቋም፣ ከአሜሪካ አቋም ጋር ይቃረናል። ከሚያስማማቸው ነገር ይልቅ፣ የሚያለያያቸው ነገር በዛ ማለት ነው። ነገር ግን፣ “ራሺያ የአሜሪካ ጠላት ናት” ብሎ ለመፈረጅ ይከብዳል። ለምን በሉ?
የአሜሪካ አቋምን በመቃወም፣ ሌሎች ብዙ አገራት፣ ከራሺያ የባሱ ናቸው። እንዴት ብትሉ፣ ከራሺያ በባሰ ሁኔታ፣ አሜሪካን የሚቃወሙ አገራት፣ 125 ናቸው።
ለምሳሌ፣ እዚያው አሜሪካ አጠገብ ያለችውን ሜክሲኮ መጥቀስ ይቻላል። በ29 ጉዳዮች ላይ ከአሜሪካ ጋር በመስማማት ድምፅ ብትሰጥም፣ በ45 ጉዳዮች ላይ፣ ከአሜሪካ ጋር የሚቃረን አቋም ይዛለች። እንዲያም ሆኖ፣ ሜክሲኮ፣ በየአመቱ ከአሜሪካ፣ ከ100 ሚሊዮን ዶላር በላይ እርዳታ ታገኛለች። መች ይሄ ብቻ!
ኢትዮጵያና ኬንያ
በዓመት ከ500 ሚሊዮን ዶላር በላይ እርዳታ ከአሜሪካ የሚመደብለት የኬንያ መንግስትን ተመልከቱ። የኬንያ መንግስት በ23 ጉዳዮች ላይ፣ የአሜሪካ አቋምን የደገፈ ቢሆንም፣ በ48 ጉዳዮች ላይ የአሜሪካ አቋምን ሲቃወም ታይቷል። ከሚያስማማ ነገር ይልቅ፣ የሚያቃርን ነገራቸው ይበልጣል – ከእጥፍ በላይ።
እንግዲህ ይታያችሁ። ከአሜሪካ፣ እጅግ ከፍተኛ የኢኮኖሚ እርዳታ በማግኘት በኩል፣ አምናና ካቻምና በአራተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠች አገር ናት – ኬንያ። በሰባት አመታት ውስጥ እንደ ኢትዮጵያ፣ 5 ቢሊዮን ዶላር የኢኮኖሚ እርዳታ ከአሜሪካ አግኝታለች።
እንዲያም ሆኖ፣ በአለማቀፉ የፖለቲካና የዲፕሎማሲ መድረክ፣ አሜሪካን ለመደገፍ ሳይሆን፣ አሜሪካን ለመቃወም የምትሰጠው ድምፅ ይበልጣል – ለዚያውም እጥፍ ያህል።
የኢትዮጵያ አሰላለፍስ እንዴት ነው?
ያው እንደኬንያ ነው። በ22 ጉዳዮች ላይ፣ የኢትዮጵያ አቋም፣ ከአሜሪካ ጋር የሚስማማ ነበር። በ48 ጉዳዮች ላይ ግን፣ ከአሜሪካ ጋር የሚቃረን አቋም!
ሌሎቹ የዘወትር እርዳታ ተቀባዮች፣… እነኡጋንዳ፣ ባንግላዲሽ፣ ኢራቅ፣ ናይጄሪያ፣ የመሳሰሉ አገራት ባህርይም፣ ከኬንያና ከኢትዮጵያ ጋር ይመሳሰላል። ይሄ አያስገርምም? በየዓመቱ ከአሜሪካ ብዙ መቶ ሚሊዮን ዶላር እርዳታ የሚቀበሉ ቢሆኑም፤ በየአመቱ የሚይዙት አቋም ግን፣ የአሜሪካ ዋና ባላንጣ ያስመስላቸዋል።
ምናለፋችሁ!… የነ ኢትዮጵያና የነኬንያ አቋም፣ በአብዛኛው ከለየላቸው የአሜሪካ ባላንጣዎች ጋር… ማለትም ከቬኔዝዌላና ከኩባ፣ ከዚምባብዌና ከቻይና ጋር በጣም ይቀራረባል። ለምሳሌ፣ ኩባ፣ በ18 ጉዳዮች ላይ ከአሜሪካ ጋር የሚስማማ አቋም ይዛ ነው፣ በ52 ጉዳዮች ላይ ከአሜሪካ ጋር የሚቃረን አቋም ያስተጋባችው። ያው፣ ቁጥሮቹን ስናያቸው… ከኢትዮጵያና ከኬንያ ቁጥሮች ጋር ተቀራራቢ ናቸው። ይሄ ተገቢ አይደለም።
በአንድ ጎን እርዳታ እየተቀበሉ፣ በሌላ በኩሉ ደግሞ የጎን ውጋት መሆን… በቃ አያምርም። እነ ኢትዮጵያና እነ ኬንያ፣ በጭራሽ… በጭራሽ፣ እንደ ኩባና እንደ ቬኔዝዌላ፣ በዩኤን መድረክ፣ የአሜሪካ ባላንጣ መሆን አልነበረባቸውም። አዎ፣ እንዲያ “መሆን አልነበረባቸውም”።
ካሁን በኋላ ግን፣ እንደ ድሮው፣ መሆን የሚችሉ አይመስልም።
ዶናልድ ትራምፕ፣ የድሮውን የእርዳታ አመዳደብ ለመቀየር እንዳቀዱ ኒውዮርክ ታይምስ ዘግቧል። እንዴት? “የአሜሪካ አቋምን አዘውትረው የሚቃወሙ መንግስታት በርካታ ናቸው፤ በየአመቱ የምንሰጣቸውን እርዳታ መቀነስ አለብን” የሚል ነው የትራምፕ ሃሳብ።

በማህበራዊ ድረገጾች ትኩረትን የሳበ መነጋገሪያ ጉዳይ የጥንዶቹ ሰርግ


 .
ፍቅር እንጂ ቤሳቢስቲን የሌላቸው ኬንያውያን ጥንዶች…
ከተስፋ በቀር ይህ ነው የሚሉት ጥሪት ያልቋጠሩ ፍቅረኛሞች ዊልሰን እና አን ሙቱራ!…
ፍራፍሬ በማዞር አስር አምስት እየለቀመ ኑሮውን የሚገፋው የ27 አመቱ ዊልሰን እና የ24 አመቷ አን፣ ከተዋወቁና የፍቅርን አክርማ መቅጨት ከጀመሩ ቆይተዋል፡፡
ከሶስት አመታት በላይ በፍቅረኝነት የዘለቁት ጥንዶቹ፣ ትዳር መስርተው በአንድ ጎጆ ለመኖር ካሰቡ ሶስት አመታት አልፏቸዋል፡፡
ችግሩ ግን፣ የመጋባት ፍላጎት እንጂ የመጋቢያ ገንዘብ አልነበራቸውም፡፡ እንደሌሎቹ ኬንያውያን ሰርግ ደግሰው ለመጋባት ይቅርና፣ ለመፈራረሚያ የሚሆነውን የመዘጋጃቤት ክፍያ የሚሸፍንላቸው 300 ዶላር አልነበራቸውም፡፡
ከዛሬ ነገ ይሞላልናል በሚል ተስፋ ብዙ ጠበቁ…
እንዳሰቡት ግን አልሞላላቸውም!…
ጥንዶቹ ያቺን 300 ዶላር ሊያገኙ ባለመቻላቸው፣ ጋብቻቸውን ለሁለት ጊዜ አራዝመዋል…
ተስፋ እያደረጉ መዋደዳቸውን ቀጠሉ…
.
በስተመጨረሻ ግን…
ከወራት በፊት፣ ዊልሰን እና አን ተስማሙ…
ቀለል ባለ ሰርግ ለመጋባት ወሰኑ!….
ለጥንዶቹ ቀለል ያለ ሰርግ ማለት፣ 1 ዶላር ብቻ የሚወጣበት ሰርግ ማለት ነው!…
ባለፈው እሁድ ማለዳ…
ሙሽሮቹ ዊልሰን እና አን ሙቱራ ያቀዱትን እውን ሊያደርጉ ተነሱ…
.
ሱፉን ግጥም ያላደረገ፣ በክራባት ያልታነቀ፣ ካረጀች ስስ ቲሸርት በቀር ያልደረበ ሙሽራ ዊልሰን… ያልተኳለች፣ ቬሎ ያልለበሰች፣ አበባ ያልታቀፈች፣ አለምሽ ዛሬ ነው እያለ የሚያጅባት ዘመድ ወዳጅ የሌላት ሙሽራውን ይዞ ከቤቱ ወጣ…
ሙሽራውና ሙሽሪት፣ ያለ ሊሙዚን፣ ያለ አጃቢ፣ ያለ አበባ በታኝ፣ ያለ ሻማ አብሪ በፍቅር ብቻ ደምቀው ወደ ቤተ ክርስቲያን አመሩ…
በሃይማኖታዊ ስርዓት ቃል ተገባብተው ተጋቡ…
በአንድ ዶላር የገዟቸውን የብረት ቀለበቶች አንደኛቸው በሌላኛቸው ጣት ላይ አጠለቁ!…
ሰርጋቸውን አጠናቀቁ!…
.

Image may contain: 4 people, people smiling, text
ይህን ተከትሎ

ጥንዶቹ የአለም መገናኛ ብዙሃን መነጋገሪያ ሆኑ!…
በአነስተኛ ወጪ የተከናወነው የዓለማችን ሰርግ ተባለ – የዊልሰን እና የአን ጋብቻ!…
ቢቢሲ ቅድም እንደዘገበው…
የጥንዶቹ ሰርግ በማህበራዊ ድረገጾች ትኩረትን የሳበ መነጋገሪያ ጉዳይ ሆኗል…
“ፍቅር ይበቃል!… ፍቅረኛሞች ትዳር ለመመስረት ፍቅር እንጂ፣ ገንዘብ እስኪኖራቸው መጠበቅ የለባቸውም!… ሳያመነቱ በፍቅር ይጋቡ… ኦና ቤታቸውን ፈጣሪ አምላክ ይሞላዋል!…” ብላለች አን ለቢቢሲ፡፡
የሁለቱ ጋብቻ በመገናኛ ብዙሃን ይፋ መደረጉን ተከትሎ…

በርካታ ግለሰቦችና ኩባንያዎች ለእነዚህ ድንቅ ጥንዶች የአድናቆት እና የስጦታ መዓት ማዥጎድጎድ ጀምረዋል
ቦንፋየር አድቬንቸርስ የተባለ ታወቂ የኬንያ አስጎብኝ ድርጅት፣ ጭር ባለ ማለዳ የተጋቡት ሙሽሮቹ፣ በአንድ ታዋቂ የናይሮቢ ባለ አራት ኮከብ ሆቴል ውስጥ ለአምስት ቀናት ለሚያደርጉት የጫጉላ ሽርሽር ሙሉ ወጫቸውን እንደሚሸፍንላቸው ቃል ገብቶላቸዋል
ሌላ የኬንያ ድርጅትም ሌላ ሰርግ ሊደግስላቸው ተፍ ተፍ እያለ ነው፡፡
ይሄው ድርጅት የሙሽሮቹ ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች የሚታደሙበት ሌላ ድል ያለ ድግስ ደግሶ በደመቀ ሰርግ ዳግም ሊሞሽራቸው ቃል ገብቷል፡፡ ሌላ ኩባንያ ደግሞ፣ የሁለተኛውን ሰርግ የፎቶግራፍና የቪዲዮ ስራ ለእኔ ተውልኝ… ቤሳቢስቲን ሳላስከፍል አሽቀብንኜ እሰራላችኋለሁ ብሏቸዋል፡፡
በአሜሪካ የምትኖር አንዲት ኬኒያዊም ለስራ መጀመሪያ የሚሆናቸውን መነሻ ካፒታል ልትሰጣቸው ቃል ገብታለች…
የኬክ፣ የበግ፣ የልብስና የጌጣጌጥ ስጦታውማ አይነሳ!…
.
ፍቅር ይበቃል!…

የህወሓት መሪዎች ደብቁኝ እያሉ ነው !



የህወሓት መሪዎች ደብቁኝ እያሉ ነው ! konjit sitotaw of mereja com
!!!!!!!!!!!!!!!!!!
የህወሓት መሪዎች ከልዩ ታማኝ ካድሬዎችና ጀሮ ጠቢ የትግራይ ተወላጆች ጋር በኣውሮፓ ተደብቀው ልዩ ስብሰባ ለማካሄድ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ።
ህወሓቶች ኣውሮፓ ከሚኖሩ ተጋሩ ተደብቀው ከሰላዮቻቸውና ታማኝ ካድሬዎቻቸው ብቻ ለመሰብሰብ ለየካቲት 10 /2009 ዓ/ም በእንግሊዝና ጀርመን ቀጠሮ ይዘዋል።
እነዚህ በትግራይ ህዝብ መጠላታቸው ያወቁት መሪዎች ከታማኝ ካድሬዎቻቸው ብቻ ለመወያየት በኢምባሲዎቻቸውና የግል ፌስቡክ ኣካውንት ታማኞች ናቸው ብለው ላመኗቸው ተጋሩ ብቻ መልእክት እየተለዋወጡ ይገኛሉ።
የትግራይ ክልል ገዢዎች እዩኝ እዩኝ እንዳላሉ ሁሉ ደብቁኝ ማለት ጀምረዋል።
ህወሓት ከተጋሩ ድብብቆሽና ሽሽት የት ያድርሰው ይሆን?

ደቡብ ሱዳን ወያኔን ለማስወገድ የትጥቅ ትግል የመረጡ ኋይሎችን መርዳት ከጀመረች የኤርትራ አቋም ይለይለታል። (ቆንጂት ስጦታው)

   


ደቡብ ሱዳን ወያኔን ለማስወገድ የትጥቅ ትግል የመረጡ ኋይሎችን መርዳት ከጀመረች የኤርትራ አቋም ይለይለታል። (ቆንጂት ስጦታው)…………..ይህን ሰሞን መልካም ዜናዎች እየተሰሙ ነው። የደቡብ ሱዳን መሪ ሳልቫ ኬር ድንገተኛ የግብጽ ጉብኝት በወታደራዊ ስምምነት ላይ ጠበቅ ብሎ መታየቱ ግብጽ በደቡብ ሱዳን የኣባይን ወንዝ የሚቀራመቱ ሃገሮችን ተቃዋሚ ሃይላት ወታደራዊ ስልጠና ለመስጠት ማቀዷ ከዩጋንዳው ሙሴቪኒ ጋርም በደረሰች ስምምነት የወያኔ መንግስት ላይ ማሴሯ ኢንዲያን ኦሽን ሌተርና ሌሎች የምስራቅ አፍሪካ ሚዲያዎች ሲነግሩን ከርመዋል።በኤርትራ ውስጥ የሚገኙ እና በተለያዩ ዙሮች እንደተመረቁ የሚነገርላቸው የነጻነት ሃይሎችን ወደ ደቡብ ሱዳን ለማዘዋወር የሚደረገው ስራ ከባድ ፈተና ከሻእቢያ ይገጥመዋል።……..ይህ መልካም ዜና ተከትሎ የሕዝቡ ውይይት በሰፊው እየተሰም ነው። ውይይቱ ያተኮረው ደቡብ ሱዳን ወያኔን ለመጣል የትጥቅ ትግል የመረጡ ሃይሎችን መደርደሪያ መሬት ከፈቀደች ወታደራዊ ስልጣና እንዲያገኙ ካደረገች በኤርትራ ያሉና በተለያየ ጊዜ የተመረቁ የነጻነት ሃይሎች በኣስመራ መልካም ፈቃድ ወደ ደቡብ ሱዳን እንዲሄዱ ይፈቀድላቸው ይሆን የሚሉ ጥያቀዎች እየተነሱ ነው።የኤርትራ መንግስት የነጻነት ታጋዮችን ለመርዳት ከሚሰበሰበው ገንዘብ መካከለኛ የውጪ ምንዛሬ ያገኛል ከወያኔ ጋር የመረጃ ልውውጥ ስላለው ፈቃደኛ አይሆንም እንዲሁም በነጻነት ታጋዮቹ ላይ የጉልበት ብዝበዛ ስለሚያደርግ የተገኘውን እድል ለማክሸፍ ከወያኔ ጋር ተረባርቦ ይሰራል የሚሉ አስተያየቶች እየተሰሙ ነው። ………  በኤርትራ ውስጥ የሚገኙ እና በተለያዩ ዙሮች እንደተመረቁ የሚነገርላቸው የነጻነት ሃይሎችን ወደ ደቡብ ሱዳን ለማዘዋወር የሚደረገው ስራ ከባድ ፈተና ከሻእቢያ ይገጥመዋል።ሻእቢያ የነጻነት ሃይሉ መነገጃ እንዳደረጋቸውና በፍጹም ወደ ጦር ሜዳ እንደማይልካቸው ከላካቸውም መረጃውን ለወያኔ አድርሶ አስከብቦ እንደሚያስመታቸው ከዚህ ቀደም በኤርትራ ቆይተው ጉዳዩን የታዘቡ ሃይሎች ይናገራሉ። በቀጣይነት የሚሆነው እየጠበቅን ለነጻነት ሃይሉ መልካም ምኞታችንን እንገልጻለን።

በጎንደር/በጌምድር ኦሮሞዎች ይገዙ ነበር – #ግርማ_ካሳ

   


አንዳንድ የኦሮሞ ብሄረተኞች አንደኛ ኦሮሞው ከሌላው ኢትዮጵያዊ የተለየ ማንነት እንዳለውና ኦሮሞነት እና ኢትዮጵያዊነት የተለያዩ እንደሆኑ ፣ ሁለተኛ በኢትዮጵያ ይገዛና “ጨቋኝ” የነበረው “አማራ” የሚሉት ማህበረሰብ ብቻ መሆኑን ሊነግሩን ይሞክራሉ።
ታሪክ ግን የሚለው ሌላ ነገር ነው። አጼ ቴዎድሮስ ከመንገሳቸው በፊት እንደ አባ ሰሩ ግዋንጉል፣ ራስ አሊ አንደኛ፣ ራስ አሊጋዝ፣ ራስ ጉግሳ መርሳ፣ ራስ ይማም፣ ራስ ማሪዬ፣ ራስ ዶሪ እና ራስ አሊ ሁለተኛ ያሉ የየጁ ኦሮሞ መኳንንት ሰሜን ኢትዮጵያን ይገዙ ነበር። ከሰለሞን ነገድ ናቸው የሚባሉ ንገስታትን እንደው እንደ ምልክት አስቀምጠው ነበር እነዚህ ኦሮሞዎች አገሪቷን ሲያሽከረክሩ የነበሩት።
አንድ ወቅት እንደዉም በጎንደር ቤተ መንግስት አፋን ኦሮሞ የሥራ ቋንቋ እንደነበረም ይነገራል።
ጀግናዋ እቴጌ ጣይቱ “ኦሮሞ ናቸው” ብዬ መጻፌን ተከትሎ “ከበጌምድር ናቸው” የሚል አስተያየት ቀርቦልኛል። ትክክል ነው። እቴጌ ከበጌምደር ነበሩ። ግን ግንዳቸው ወደ የጁም ይሄዳል። የእቴጌ ጣይቱ አባት ራስ ብጡል ሃይለማሪያም፣ የየጁ ኦሮሞ መኳንንትና የንጉሱ እንደራሴ ሆነው ሲገዙ የነበሩት የራስ ጉግሳ መርሳ የልጅ ልጅ ናቸው።
የትግሬው ራስ መንገሻ ሚስት ከፋይ ወሌ ፣ የንግስት ዘዉዲቱ ባለቤት ራስ ጉግሳ ወሌ፣ የሰሜን (የተወሰነ ጊዜም የትግራይ እና የባህር ምድሪ/ኤርትራ ) ገዢ የነበሩትና የእቴጌ ጣይቱ አጎት ራስ ዉቤ ሃይለማሪያም፣ የየጁ ራስ ጉግሳ መርሳ ልጅ ልጆች ናቸው። የአጼ ቴዎድሮስ ባለቤት እቴጌ ተዋበች አሊ፣ የራስ አሊ ሁለተኛ ልጅ ነበሩ። የበጌምድር ራስ የነበሩት ራስ አሊ አንደኛ፣ የራስ ሚካኤል ስሁልን ሞት ተከትሎ የኢትዮጵያ ንጉስ እንደራሴ ሆነው ይገዙ በነበረበት ወቅትም፣ ዋና ከተማቸውን ወደ መግደላ ከማዞራቸው በፊት የአጼ ቴዎድርስ መቀመጫ የነበረችዋን ታሪካዊቷን የደብረ ታቦር ከተማ የመሰረቱት፣ እኝኑ የየጁ ኦሮሞ ገዢ እንደነበሩም ይነገራል።
እንግዲህ አስቡት አሁን ሕወሃት/ኢሕአዴግ በዘር ሸንሽኖ የአማራው ክልል ብሎ በመሰረተው ግዛት እምብርት ምን ያህል በትልቁ የኦሮሞዎች አሻራ እንዳለ። አስቡት ምን ያህል የኦሮሞው ማህበረሰብ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ጋር የተሳሰረና የተዋለደ እንደሆነ።
ዘረኝነትን ለመስበክ፣ አንድን ህዝብ ከሌላው ህዝብ ጋር ሆን ብለው ለማጣላት ጥቂቶች የሚሸርቡት እንጅ፣ ኦሮሞዎች ሌላው ይገዛቸው እንደነበረው ሁሉ እነርሱም የገዙ፣ ሌላው እንደበደላቸው እነርሱም የበደሉ፣ ከሌላው ጋር የተደባለቁ መሆናቸውን ነው ታሪክ የሚያስተምረን። የጸዳ፣ የጠራ የኦሮሞ ማንነት የለም።
እቴጌ ጣይቱ ኦሮሞ ነበረች ስንል፣ ኦሮሞ ብቻ ነበረች ማለታችን አይደለም። ከኦሮሞም፣ ምናልባትም ከትግሬው፣ ከአገው የተደባለቀች ናት። አንድ ወዳጄ እንደተናገረው “ኦሮሞ”፣ “ትግሬ”፣ “አማራ”…..ትል ያልነበረች ማንነቷ ኢትዮጵያዊነት ብቻ የነበረ ታላቅ የኢትዮጱያ ብቻ ሳይሆን የጥቅር ህዝብ እናት ነበረች።
ይሄን ግሩም ሙዚቃ ተጋበዙ።

ወያኔ የቅማንትን ጉዳይ ‹‹በሪፈረንደም›› መፍትሔ እሰጣለለሁ በማለት ካድሬዎቹን አሰልጠኗል፤ • የወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ የሚታሠሩ ሰዎች ቁጥር ጨምሯል

   


ወያኔ የቅማንትን ጉዳይ ‹‹በሪፈረንደም›› መፍትሔ እሰጣለለሁ በማለት ካድሬዎቹን አሰልጠኗል፤
• የወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ የሚታሠሩ ሰዎች ቁጥር ጨምሯል –
በሰሜን ጎንደር ዞን በጎንደር ዙሪያ፣ በላይ አርማጭሆና አካባቢው ባሉ ወረዳዎች ከቅማንት የማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ ሪፈረንደም አካሒዳለሁ የሚለው የወያኔ አገዛዝ ለዚህ ይረዱኛል ያላቸውን ካቢኔዎቹን አሰልጥኖ በዚህ ሳምንት ጨርሷል፡፡ ከዚህ ቀደም ለቅማንት ልዩ ወረዳ ከተካለሉት ቀበሌዎች ውጭ በሆኑ አካባቢዎች ሪፈረንደም እንደሚደረግ የተገለጸ ሲሆን የእርስ በእርስ ግጭት ለመፍጠር የሚደረግ እንቅስቃሴም አለ ተብሏል፡፡ የወልቃይት ጠገዴን የዐማራ ማንነጥ ጥያቄ የትኩረት አቅጣጫ ለማስቀየስ አሁን ሆን ተብሎ የሚጀመረው ሪፈረንደም ወደ ግጭት ሕዝቡ አስቀድሞ ይህን በመገንዘብ አንድነቱን ማሳየት እንዳለበትም መረጃውን ካቀበሉን አካለት አስተያየት ተሰጥቷል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ በአዲሱ ዓመት መጀመሪያ መፍትሔ ይሰጠዋል የተባለው የወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ ተወላጆችን ትግራይ ክልል ጥያቄ አቅርቡ እያሉ እየላኩ በማሳሰር ጥያቄውን ለማጓተት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ነው፡፡ የወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ በጠገዴ ወረዳ አካባቢ ያለው የድንበር እና አጠቃላይ የወልቃይት ጠገዴ የዐማራ ማንነት ጥያቄ በሚል በሁለት ተከፍሎ ይፈታል በሚል በነሐሴ ወር 2008 ዓ.ም. በነበረው የኢሕአዴግ ጉባኤ ተቀምጦ ነበር፡፡ በጊዜው የድንበር ጉዳዩ በ15 ቀን እንደሚያልቅ ነበር ለሕዝብ ቃል የተገባው፡፡ በ15 ቀን ያልቃል የተባለው ጉዳይ ግን ከሰባት ወራት በኋላም ዜጎች እየተገደሉና እየታሰሩበት ነው፡፡ የሚከተሉት የወልቃይት ተወላጆች በእስር ከሚገኙት በጣም ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

አቡነ መቃሪዎስ “በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባዔ ላይ የመንግሥት ተወካይ መገኘት ለኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ታላቅ ውድቀት ነው”


 

አሁን ባለንበት ዘመን ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንና በአጠቃላይም ለአገራችን ሰላም፣ አንድነት፣ ፍትህና እኩልነት የግንባር ሥጋ በመሆን ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ ላይ የሚገኙት ብጹዕ አቡነ መቃሪዎስ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኘው ሲኖዶስ በሚያደርገው ጉባኤ የመንግሥት ተወካይ እንዲገኝ ማድረጉ የቤተክርስቲያን ልዕልናን የሻረና የሃገሪቱን ክብር የሻረ ድርጊት መሆኑን አስታውቀዋል። አቡነ መቃሪዎስ እንዳሉት እነ ስብሃት ነጋ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንና አማራን አከርካሪውን መተናል በማለት የተነሱበትን መርዘኛ ድርጊታቸው አያካሃዱ መሆናቸውን ገልጸዋል። 
ከዚህም በማያያዝ አቡነ መቃሪዎስ ሲያብራሩ “…..ቅዱስ ሲኖዶስ  ምልዓት ጉባዔ ላይ የመንግሥት ተወካይ ጨርሶ መግባት የለበትም። የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ሥርዓት ቤተ ክርስቲያን የሚካሄድበት፣ሚስጢረ ቤተክርስቲያን የሚነገርበት፣ ስለ ቤተክርስቲያን ልዕልና ውይይት የሚካሄድበት ነው። በዚህ መንፈስ ቅዱስ በሚመራው ጉባኤ ላይ በምንም ዓይነት ከግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መንግስት እንዲሁም በበፊቱም መንግሥት እንዲህ ዓይነት ነገር ተደርጎ አያውቅም። በመላው ዓለም በሚገኙ ሌሎች አብያተ ክርስቲያናትም አይተን አናውቅም ….” ብለዋል። ብጹዕ አባታችን በዚህ ጉዳይና በአጠቃላይም ወያኔ በሾማቸው የካድሬነት ሥራ በሚሰሩ ፓትርያርክ፣ ጳጳሳት፣ ካህናትና ሌሎችም እንዴት የቤተክርስቲያን ሥርዓት እንደተጣሰና ቤተክርስቲያኒቷም በታሪክ ታይቶባት የማያውቅ ውርደትና መከራ ውስጥ መግባቷንና መፍትሃውንም ጭምር አስመልክተው በኢሳት የሰጡትን ውይይት ይከታታሉ።

Saturday, January 28, 2017

የአዲስ አበባ

የአዲስ አበባ- ናዝሬት ፈጣን መንገድ ጥናት የግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ መንግስት እቅድ እንደነበረ የዛሬይቱ ኢትዩጵያ ጋዜጣ ቅዳሜ 10 ቀን 1960 ዓ.ም ገጽ 1 እና 3 እንዲህ ያስታዉሰናል፡፡
በሚቀጥሉት 5 ዓመታ ዉስጥ የአዉራ ጎዳና ባለስልጣን የትራፊክ ችግር ለማቅለል ከሚሰራቸዉ የመገናኛ ስራዎች አንዱ የአዲስ አበባ- ናዝሬት ድረስ የሚዘረጋዉ መንታ መንገድ አንዱ ነዉ፡፡ ከአዲስ አበባ- ናዝሬት ድረስ መንገድ በመንታ ለመስራት መታቀዱ ከዚህ በፊትም የተገለጠ ነገር ነዉ፡፡ አሁን እቅዱን በስራ ላይ ለማዋል አስፈላጊ በመሆኑ አሁን የንድፍ ስራዉ በ1960 ዓ.ም ያልቃል፡፡ የቅያሱ ስራ በ1961 ዓ.ም ቀጥሎ የደንበኛ ስራዉን በ1962 ዓ.ም እንዲጀመር ያደርጋል፡፡ አሁን ባለዉ መንገድ ይቀደድ ያልን እንደሆን ብዙ ቤቶች ማፍረስና ግምቱም መስጠት ወጪ የሚያ...በዛ በመሆኑ ሌላ መንታ አዲስ መንገድ መስራት የሚሻል መሆኑን ተረድተናል፡፡
መንግስት አቅሙ ከፈቀደለት መንታ መንገድ በአንድ ጌዜ ይሰራል፤ ግን ለመስራት ካልቻለ አንዱን ሰርቶ ሌላዉን ደግሞ ቦታ ትቶለት ገንዘብ ባለ ጊዜ ሊሰራዉ ይችላል፡፡ አዲስ መንገድ ተሰርቶ በሚያልቅበት ጊዜ መንገዱን ገንዘብ ማስከፈል የሚቻልበት መንገድ አለ፡፡ ይኸዉም አንድ ሰዉ ትራፊክ በማይበዛበትና አደጋ ይደርስብኛል ብሎ ሳይሰጋ ገንዘቡን ከፍሎ እንዲሄድ ይደረጋል፡፡

ክብርና ምስጋና ለእዉነተኛዉ አፍሪካዊ ባለራዕዩ መሪ አባባ ጃንሆይ ቀ.ኃ.ስ
ታሪክ እንዳይነገር ማድረግ ቢቻልም፤ ታሪክ ግን አይሞትም!

ኢሳት ፕሮፌሰር ኃይሌ ላሬቦን ይቅርታ ሊጠይቅ ይገባል! -አቻምየለህ ታምሩ


      


ኢሳት ነፃ ሜዲያ ነኝ የሚል ከሆነ ስራው ሀሳብ አለኝ የሚልን ሁሉ ሀሳቡን እንዲያንሸራሽር መፍቀድና መድረክ ማመቻቸት እንጂ ያለ ስራው እየገባ የማባበልና ባለስፈላጊ ሁኔታ በመግለጫ ስም ማስተባበያ አይሉት ይቅርታ ማቅረብ አይደለም።
ፕሮፌሰር ኃይሌ ላሬቦ
ፕሮፌሰር ኃይሌ ላሬቦ እንደ ታሪክ ሊቅነታቸው በታሪክ «የተመዘገቡ ናቸው» ያሏቸውን ማስረጃዎች እያወሱ ለተጠየቁት ጥያቄ መልስ ሰጥተዋል። የኢሳት ሚና የፕሮፌሰሩን መልስ ለመድረክ ማብቃት ብቻ ነው። የፕሮፌሰሩን ንግግር በሚመለከት መግለጫ ማውጣት የኢሳት ስራ አይደለም። ፕሮፌሰሩ በንግግራቸውና በሰጡት መልስ የሚቀየምና የማይስማማ ሊኖር ይችላል። እንደዚህ አይነት ሁኔታ ሲፈጠር «የሚዲያው» ኢሳት መፍትሔ መሆን ያለበት ፕሮፌሰር ኃይሌ ላሬቦ ካቀረቡት የተለየ ሞጋች ኃሳብ ላለው የታሪክ ሊቅ መድረክ ማመቻቸትና ከተቻለም ከፕሮፌሰር ኃይሌ ላሬቦ ጋር ማከራከር እንጂ በፕሮፌሰር ኃይሌ አቀራረብ ላይ ተመስርቶ በመግለጫ ስም ማስተባበያ አይሉት የይቅርታ አዋጅ ማንበብ አይደለም።
የኢሳት የዛሬው ያልተገባ መግለጫ የአካዳሚክ ነጻነቱን ተጠቅሞ በሚያስተምር የታሪክ ምሁር ላይ የተወሰደ አጸፋዊ የአፈና እርምጃ ነው። ይህ ያልተገባ መግለጫ ፕሮፌሰሩንም መናቅ ነው።
የታሪክ ምሑር በታሪክ የተመዘገቡለትን ቃላትን እየጠቀሰ እንዳያስተምር በሚዴያ በታገዘ ዘመቻ አበሳውን የሚያይ ከሆነ ምንም ነገር ማስተማርና መናገር አይችልም ማለት ነው። የታሪክ ምሑሩ ተመዝግበው ባገኟቸው ስሞች ዛሬ መጠራት አንፈልግም ያለን አካል ያለ ፍላጎቱ መጥራት ትክክል አይደለም። ዛሬ በዚያ ስም ቢጠራ ያቃቅራል። ተቃቅሮ ደግሞ አብሮ መኖር አይቻልም። የታሪክ ምሁር ግን ስራው የተመዘገቡለትን ቃላት ሁሉ ማስተማር ነው።
ፕሮፌሰር ኃይሌ ላሬቦ እንደ ታሪክ አዋቂነታቸው የተመዘገቡላቸውን ቃላት በመናገራቸው ኢሳት «አይነኬዎቼ» ተቀየሙ ብሎ የሚያስብላቸው ከሆነና ይቅርታ መጠየቅ ካሰኘው ራሱን ተጠያቂ ማድረግ ይችላል እንጂ በሰው ሀሳብና አቀራረብ አስተያየትም ሆነ መግለጫ ማቅረብ የእርጎ ዝንብ መሆን ነው።
ስለዚህ ኢሳት በፕሮፌሰር ኃይሌ ላሬቦ የአከዳሚክ ነጻነት ላይ ስላደረሰው ጉዳት፤ በፕሮፌሰሩ ክብር ላይ ስለፈጸመው በደል፤ በሞያ መታመናቸውን [integrity] ስለመጋፋቱ፣ ስላካሄደባቸው የመብት ገፈፋና ሀሳባቸውን ባለማክበር በሞያዊ ልቀታቸው ላይ ስላሳየው ንቀት ፕሮፌሰር ኃይሌ ላሬቦን በሌላ መግለጫ ይቅርታ ሊጠይቅ ይገባል።

Friday, January 27, 2017

ይድረስ ለአቶ ገዱ አንዳርጋቸው: ለሆድ ብሎ ገሎ ሊያልፍ ለሚያደባ ጠላት ከመንበርክክ አብሮ ከሚኖረው ህሊና ጥያቄ መንፃትና አኩሪ ህዝብን ይዞ ስምን ተክሎ ማለፍ



ለሆድ ብሎ ገሎ ሊያልፍ ለሚያደባ ጠላት ከመንበርክክ አብሮ ከሚኖረው ህሊና ጥያቄ መንፃትና አኩሪ ህዝብን ይዞ ስምን ተክሎ ማለፍ
ይድረስ ለውድ ወንድማችን አቶ ገዱ አንዳርጋቸው (አንዱ ባለአደራ የአማራ ልጅ)
ወያኔና ግበረ በላዎቹ መገነዣ ልጣቸው ተርሶ መቀበሪያ ጉድጓዳቸው ተምሶ የግብዓተ መሬቱን ስዓት እየጠበቁ እንዳሉ ከእኛ በጓሮ በር ከምንሰልለውና ከምንሰማው ይልቅ አንት በቀጥታ ድንገት አንዳትሰማው ቢፈለግ እንኳ በመላው ጎንደር ምናልባትም አማራ ህዝብ ያለህን ተቀባይነትና የወያኔ መወደቅ አይቀሬ መሆኑን በሚያወቁ አብረውህ በበሉ ሚስጠሩ እንደሚደርስህ እርግጠኞች ነን። አቶ ገዱ አስኪ ቆም ብለህ አስብ? ከአንተ ጀምሮ ዞን ወረዳ መስተዳድሮችህ ስማቸውን አስተካክለው በማይፀፉ የትግሬ አፋኝ ወታደር አዛዞች እዝ ስር ሆነው በቁም አስረኝነት የ10 ሳንቲም ግምት ያለው ትዕዛዝ የማትስጡ አስተዳደራችሁ ፈርሶ ግዑዛን ሰለመሆናችሁና አጣብቂኝ ውስጥ ሰለመሆናችሁ ነጋሪ አትፈልጉም ብለን እንገምታለን።
የብአዴን ምክትል ሊቀመንበርና የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

አንዱ ኢትዮጵያዊ ጅግና ባንድ ወቅት ሁሉም ያመኑዋቸው የማይጠረጥሩዋቸው ሁሉ ከዱዋቸው ከክሃዲዎቹ በእጃቸው የገቡትን ከሳር ጎጆ በማስገባት ሲቃጠሉ ለማየት ከተቀመጡበት ከፍ ካለ ቦታ ሆነው ከሃዲዎቹን ወደ ሳር ጎጆ እንዲያስገባ የመደቡትን ኃላፊ (አሁን አንት በቆምክበት ቦታ የቆመውን ማለት ነው) ሞላ? ብለው ይጠይቁታል እረ አንድ ይቀረዋል በሎ ይመልስላቸዋል ከአንተስ ምን እጠብቃለሁ በል አንተም ግባ ብለው አብሮ ተቃጠለ ይባላል። የአንተም ዕጣ ፈንታ ይህ እንደሆነ ጠንቅቀህ ታውቃለህ “አይጋ ፎረምን ያዩአል”…. ልዩነቱ ይህ ትልቅ ሰው በሀገር ፍቅር ነደው አሁንም ከሰው ያልተሳካላቸውን ድንገት በእሳቱ ተፈትኖ ከአመዱ ሰው ባገኝ አያሉ እያለቀሱ ማድረጋቸው። የአንተዎቹ አለቆች ደግም ለግል ሆዳቸው እንዝረፍ እንደፈለግን እንሁን ሀገር ወገን ገደል ይግባ የሚሉ የሀገርም የወገን ለአገልጋዮቻቸው ለእናንተም ፍቅር የሌላቸው ሆዳሞች መሆናቸው ነው።
አቶ ገዱ ይህ ከእኛ ወገኖችህ የመጀመሪያም የመጨረሻም ምክራችን ነው። እባክህ 37 ሚሊዮን ህዝብ ይዘህ ለ6 ሚሊንም ቢሆን ግጥሚያው አትፍራ? ብትሞት የምትሞተው አንድ ሞት ነው ሞትህ ግን ለልጆችህ አስከ ትውልዳችው ስምህን ከምደር በላይ ዘላዓለማዊ ክብርና ሞገስ ትተህላቸው ከማለፍ ውጭ የምታጣው ነገር የለም። ምክንያቱም እንደ ወያኔ ውሳኔ በእኛ ደጀንነት እንጅ የመኖር ፈቃድህ የእርድ ቀንህን አየጠበቅ እንደሆነ እርገጠኛ ነህ። ይህንም በፍፁም መሰሪነታቸው አንት ልትጠቀምባቸው ትችላለህ ተብለው የሚሰጉ የልዩ ኃይል የማረሚያ ቤቱንና ሌሎች ጀግኖችህን አያሰሩ ቀነዘሉ ተቆርጦ እንደሚደርቅ ዛፍ አጅ አግርህን ክተክተው እየጣሉሀ እንደሁ እንዴት አትረዳም?
በትንሽ መንደሮች በቁጠር አርበኞች ከመላው ኢትዮጵያ የመጣውን ጦር እንዴት እያስተናገድን አየመለስነው እንደሆነ ከምታየው ሰርቶ ማሳያ ብትረዳና እኛ የምንልህን በመቀበል አቋም ይዘህ አምቢ ለአማራ… እምቢ ለኢትዮጰያ… አሻፈረኝ ህዝቤን አትንኩ ተከተለኝ ወገን በማለት ለመሪነት ብትዘጋጅ የምትሳሳላቸውን ቤተሰቦችህን ጨምሮ በአንት ላይ አይደልም ሞት ዝንብ እንደማናሳርፍ መላ ኢትዮጵንም በስዓታት በመድረስ ነፃ እንደምናወጣት ቅንጣት ባትጠራጠርና ስም ብናስር። አትፍራ…. መቸም ሟች ነህ ልዩነቱ በክብር ከመኖር ተስፋ ጋር የክብር ሞት ለመሞት ወይም የተወሰነልህን የማይቀር የወያኔን የውርደት ሞት ለመሞት መዘጋጀት ናቸው።
አንት ባታደርገውም ወያኔ በሚያገኛት ትንሽ ቀን ምናልባት ወራት ወደ እኛ ጎንደሬ አርበኞች የማይነካ አሳት አንድም ትግሬ ሳይጨምሩ አየላኩ እንደማገዶ እንጨት የሚያልቁት ኢትዮጵያዊ ልጆቻችን ሞት አንጅ ወያኔንማ አያክርምን አናከርመውም…።
አሳዛኙ ግን ለእኛ አንት በአድሜህ በትምህርት በባህልም ከእነሱ የተሻለክ ነህ ብለን ስለምንገምት እነዚህ እንጀራ ጠግበው ያልበሉ ሊተኩሱት ቀርቶ ሊሽከሙት የማይችሉትን ጠመንጃ አሸክሞ በርሃብ ለጥይት የሚማግዳቸው ተተኪ ንፁሃን ኢትዮጵያዊ ተባበሪ መሆንህና ወንጀሉን ዝም ብለህ ማየትህ አጅግ እጅግ ያሳዝናል አንተስ ሽክሙን እንዴት ቻልከው?
ስለዚህ ምከረው ምከረው አምቢ ካላ መካራ ይምከረው በሚባለው የአባቶች አባባል ባለብን የደም የስጋ የማንነት ትስስር እራስህን እንደትፈትሽ የከበረ ምክራችን እንለግሳለን መንገዱንም እንዲያሳይህ እንፀልይልሃለን።
ድል ለኢትዮጵያዊያን
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላዓለም ትኑር
መላው ጎንደር አማራ ኢትዮጵያዊያን ንቅናቄ
እባካችሁ ይህ መልዕክት የሚደርሳችሁ ሁሉ በተቻለ መጠን መልዕክቱ ለአቶ ገዱ አንዲደርስ አድርጉልን አናመስግናለን።

የጅቡቲ አፋሮች ትግል እንዴት ከሸፈ? ክፍል 3 – ከይገርማል


ጉዞ ወደጅቡቲ በረሀ  

ወደጅቡቲ ይዞኝ ከሚሄደው ሰው ጋር ለመገናኘት ባቲ ከተማ ፍኖተ ሰላም ከሚባል ሆቴል በሀምሌ 1984 ዓ.ም የወሩ የመጀመሪያ ቀናት አካባቢ ቀጠሮ ተይዞልኛል። ከሆቴሉ ስደርስ ቀጠሮ የያዘችልኝ ልጅ ከአንድ መካከለኛ ቁመት ካለው ቀጠን ካለ ጠይም የአፋር ወጣት ጋር እያወራች ነበር። “ኦ! እንኳን ደህና መጣህ፡ ስንጠብቅህ ነበር” አለችኝ እንዳየችኝ። የሩጫ ያህል ተጣድፌ ከእቅፌ አስገባኋት። በጭንቅ ጊዜ የደረሰችልኝ እህቴን ምን ማለት እንዳለብኝ ማወቅ ተስኖኛል። ለረጅም ጊዜ ተለይቶ ሲናፍቅ እንደኖረ ፍቅረኛ ተጠምጥሜ ይዠ አልለቃት ብል “ኧረ በቃ!” አለችኝ እየሳቀችና ከእቅፌ ለማምለጥ እየሞከረች። “ላደረግሽልኝ ሁሉ አመሰግናለሁ!” አልኋት ሀፍረት ቢጤ ሽው እያለብኝ። “ደግሞ እንዲህ የሚያስብል ምን ውለታ ውየልህ ነው? አጋነንኸው እኰ! ለማንኛውም ይዞህ የሚሄደው እሱ ነው፤ ተዋወቁ!” አለችኝ ወደ ወጣቱ እየጠቆመች። የትውውቁ ሥነስርዓት እንዳለቀ ቡናና ሻይ አዝዘን ፉት እያልን በእርሷ አስተርጓሚነት ብዙ አወራን። በመጨረሻ ጉዟችን በሚቀጥለው ቀን እንዲሆን ተስማምተን የምንገናኝበትን ሰዓት ቆርጠን ስናበቃ መልካሙን ሁሉ ተመኝታልኝ ከአፋሩ ወጣት ጋር ሄደች።

ወጣቱ በቀጠሯችን መሰረት በበነጋታው እኩለቀን አካባቢ አልጋ ከያዝሁበት ሆቴል መጣ። ተዘጋጅቸ ጨርሸ የርሱን መምጣት እየጠበቅሁ ስለነበር እንደደረሰ ሻንጣየን አንጠልጥየ መኪና ፍለጋ ወጣን። ብዙም ሳንቸገር ወደአሰብ  የሚሄድ አንድ የጭነት መኪና አግኝተን እስከማንዳ ድረስ ለሁለታችን 30 ብር ከፍየ ጉዟችንን ጀመርን።
ሚሌን እልፍ እንዳልን አንድ ወንድና አንድ ሴት አፋር አስቆሙን። “እኒህ ሰዎች 5 ሣንቲም ያወጡበት ይመስል በንብረታችን ያዝዛሉ” አለ ሾፌሩ እየተነጫነጨ። ምን ለማለት እንደፈለገ ስላልገባኝ ዝምታን መረጥሁ። ለነገሩ አብሮኝ ያለውም ወጣት አፋር ስለሆነ በአማርኛ ስናወራ በርሱ ላይ ሊፈጠር የሚችለውን ስሜትም ስለማላውቅ ነው። ጥቂት ከተጓዝን በኋላ ከሴቲቱ ጋር ያለው አፋር በተሰባበረ አማረኛ መኪናውን እንዲያቆም ሾፌሩን ጠየቀው። ዝናብ ዘንቦ ስለነበር በመንገዱ ዳርቻወች ጎርፍ ይታያል። አፋሩ ከዚያ ጎርፍ በሆነ ዕቃ ጨልፎ ግጥም አድርጎ ጠጣ። ለሴትዮዋም ሰጣትና እርሷም እንደሱ ጭልጥ አድርጋ ጠጣች። “አሃ! ባቲን ካለፉ ውሀ ወለድ በሽታ የለም ማለት ነው!” አልሁ ለራሴ።
ማንዳ የደረስነው አመሻሽ ላይ ነው። ርሀብ እየተሰማኝ አይደለም። ቢሆንም አብሮኝ ላለው ልጅ ስል ምግብ ቤት መሄድ ይኖርብናል። እራት እንድንበላ በምልክት ስነግረው ገባው። ከዚህ የበለጠ መግባቢያ፣ ከዚህ የበለጠ ቋንቋ ምን አለ! እንድከተለው በምልክት ነግሮኝ ወደአንዲት ደሳሳ ጎጆ መራኝ። በዚች ደሳሳ ምግብ ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ “ሉህሉህ”ን ተዋወቅሁ። ሉህሉህ ማለት በመጥበሻ የምትጋገር ዝርግ ሳህን የምታህል እንጀራ ናት። አንድ ሉህሉህ በድፍን ምስር ወጥ ዋጋው ሁለት ብር ነበር።
ከምሽቱ አራት ሰዓት አካባቢ ሲሆን ወደጅቡቲ የሚሄዱ የአፋር ነጋዴወች ግመሎቻቸውን ሸክፈው ለጉዞ ተነሱ። አብሮኝ ያለው የአፋር ወጣት የእንከተላቸው ምልክት ስላሳየኝ አብረናቸው ለመሄድ ተጣደፍን። ግመሎች ሥነስርአት ያላቸው ናቸው። አንድ ሰው ብቻ ከፊት ያለውን ግመል የታችኛውን ከንፈሩን በገመድ አስሮ ይመራል። ከኋላ የሚከተለው ግመል ከንፈር ከፊተኛው ግመል ጅራት ጋር ይታሰራል። ለጉዞ የተሰናዱ ግመሎች በሙሉ በዚህ መልክ ይያያዛሉ። ከፊት የሚስበው ሰው የሚሄድበትን ተከትሎ ሁሉም ግመል እንደ ጉንዳን ሰራዊት በሰልፍ ይጓዛል። ወደግራ እሄዳለሁ፣ ወደቀኝ አዘነብላለሁ ብሎ የሚያስቸግር የለም። ብዙም ርቀን ሳንሄድ ልቤ ስልብ አለብኝ። ወበቁም ከአቅሜ በላይ ነበር። ከነጋዴወች ጋር እኩል መራመድ አቅቶኝ ከኋላ ቀረን። ከንፈሬም ጉሮሮየም ደረቁ። ችግሬን የተረዳው ጓደኛየ እየመራ ውሀ ወደምናገኝበት ቦታ ይዞኝ ሄደ። በዚያ መንገድ ብዙ ጊዜ የተመላለሰ ስለሆነ ምን የት እንዳለ ያውቃል። የተቋጠረ ውሀ ካለበት ጐድጓዳ ቦታ ላይ ስንደርስ ወደውሀው እያመለከተኝ እንድጠጣ ጋበዘኝ። ጨልፈን የምንጠጣበት እቃ እንኳ አልያዝንም። እኒያ አፋሮች ጎርፍ ጠጡ ብየ ስገረም የነበርሁት ሰውየ ሰውነቴን ዘረጋግቸ በሆዴ ከመሬት ተስማማሁና ያንን ተቋጥሮ የከረመ ውሀ እዘርፈው ጀመር። ሆዴ እየተነፋ ሄደ እንጅ እርካታን አላገኝ አልሁ። በቃህ አለኝ ጓደኛየ በምልክት። ሆዴ እየቆየ እየተነረተ ጉሮሮየ ደረሰ። ወደላይ የለ ወደታች የለ! ከዚህ በኋላ አልሄድም አልሁና ከመንገድ ወጣ ብየ ብትንትን ብየ ተኛሁ። ጠዋት ስነቃ አፋሩ ጓደኛየ ከጎኔ ተቀምጧል። ስለውለታው የማመሰግንበት የተረፈ አቅም አልነበረኝም። ለማመን ይከብዳል፤ ገና በጠዋቱ ሙቀቱ አንጀት ስልብ ያደርጋል። እንደምንም ተጎትቸ ተነስቸ እያዘገምን ቡያ ከምትባል የጅቡቲ መንደር ደረስን። ከኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ተለየሁ ማለት ነው። አሁን ያለሁት ውጪ ሀገር ነው።

አገሬን ሊያፈርሱ ተመካከሩባት



ጠላታችን ነግሶ በደም የሚኖረው ሰው-በላው ስርዓት
የወያኔ መንግስት ህጻናት ገዳዩ በትረ-አጋዚ ህውሃት፣
ምን ነክቷቸው ይሆን የጥበት ቁንጮዎች እነ አባ ሜንጫ
ምሁር ነን የሚሉ  የጥላቻ ጠበብት የሰይጣን መፈንጫ፣
አውሬው ተቀምጦ የሁላችን ጠላት
እምዬን ጠመዱ ተመካከሩባት
አገሬን ሊያጠፉ ዘግተው አሴሩባት
የናት ጡት ነካሾች  ኢትዮጲያን ሊያፈርሷት፣
ዥጉርጉሯ ነብር ቁስል ቢበዛባት
ጅቦች ተጠራሩ ቁርሳቸው ሊያደርጓት፣
ቀን አይቶ እንዲነሳ ተላላፊ ተውሳክ ጥገኛ በሽታ
እምዬ ስትደክም የገባች መስሏቸው ከሚሞቱት ተርታ
ልጆች እንደሌሏት ቀድመው የሚሰዉ ሊሆኗት መከታ
ዘረኞች ፎከሩ፣ ተስማሙ፣ እማማን ሊያጠፉ በመለስ በሽታ፣
ያለቀውን ወጣት መሰላል አድርገው
ኢትዮጲያዊነትን አጥላልተው ተዋግተው
ተረት ተረት ታሪክ፣ ጥላቻ አሰራጭተው
እቅዳቸው ሆኗል፣ ንጉሣን ሊሆኑ በየመንደራቸው፣
ደም እንደጎርፍ ፈሶ፣ በሃረር በባሌ በሸዋ በአርሲ በጎንደር በጎጃም
የወላጆች እንባ ወደ አምላክ ሲፈስ ፍትህን ፍለጋ ከእውነተኛው ዓለም
ለአገር የተሰዉት ቃላቸው ይህ ነበር፣ ለሞት ያበቃቸው፣ የወጣቶቹ ህልም
ፍትህ እንዲሰፍን በኢትዮጲያ ምድር፣ ዘረኝነት ጠፍቶ ሰብዓዊነት ይቅደም፣
የወጣቶቹ ራዕይ ወዳው ተካደና እንዳልሆነ ሆኖ ጭራሽ ተቀያይሮ
ጥላቻ ተዘራ በህሊና ቢሶች ሰልጥነው በወጡ ከወያኔ ጉያ ከገንጣዮች ጓሮ፣
የመለስ በሽታ በነሱ ላይ ሰፍሮ ቤቱን ሰርቶባቸው
በጭንቅላታቸው የጥላቻውን ድር ስላደራባቸው
እምነትን ከእምነት፣ ዘርንም ከዘሩ ማጣላት ስራቸው
ተምረናል ቢሉም፣ ከዘረኝነት ዉጭ ማሰብ ተሳናቸው
በሚነግሩንና በሚያከናዉኑት እኩይ ተግባራቸው
በሩቅ ይኑሩ እንጂ፣ ከወያኔ ጋራ ፍጹም አንድ ናቸው።
ወለለተ አገሬ

Zimbabwe deports 34 migrants from Ethiopia




zwnews.com – 34 undocumented Ethiopian migrants were taken into custody after they were caught being moved around by smugglers.
They will all be deported soon by the Zimbabwe Immigration Department.
Among the illegal immigrants were four boys aged between 11 and 12, the individuals who are all men were arrested while hiding at a Marondera farm.
They pleaded guilty on Tuesday before magistrate Shane Kubonera, who then convicted and discharged the group into the hands of immigration officials.
On December 16 last year, the suspects were transported from Mutoko to Marondera en route to Beitbridge by Cletto Nyandoro and Gift Bere.
They were allegedly later dropped at Plot 3, Bemba Farm in Marondera, by Nyandoro, who had gone to Marondera Town to buy food for them.
 Acting on a tip-off, Zimbabwe Police stormed the farm and arrested the suspects after discovering that they had no travel papers.

አርበኞች ግንቦት 7 የት አለ? ለሚለው ጥያቄ የድርጅቱ አመራር ምላሽ ሰጡ | አማራ ነን ብለው የተነሱትን “ለመደራጀት ጥሩ ሰዓት የመረጡ አልመሰለኝም” አሉ


አርበኞች ግንቦት 7 የት አለ? ለሚለው ጥያቄ የድርጅቱ አመራር ምላሽ ሰጡ | አማራ ነን ብለው የተነሱትን “ለመደራጀት ጥሩ ሰዓት የመረጡ አልመሰለኝም” አሉ


(ዘ-ሐበሻ) ከአውስትራሊያ የሚሠራጨው ኤስ ቢኤስ ራድዮ ላይ እንግዳ ሆነው የቀረቡት የአርበኞች ግንቦት 7 የፍትሕ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የውጭ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አበበ ቦጋለ በአሁኑ ወቅት ድርጅታቸው በምን ዓይነት የትግል እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል? በሚል ላቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጡ:: ጋዜጠኛው በአማራ ስም ስለተደራጁ ወገኖች ዙሪያም ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን አቶ አበበ “በአማራ ስም የተደራጁት ወገኖች ለመደራጀት የመረጡበት ሰዓት ጥሩ አይመስለኝም; እዚህ ዲያስፖራ ላይ እንጅ ሃገር ቤት መሠረት እንደሌላቸው ከሚደርሱን መረጃዎች ለማረጋገጥ ችለናል” ብለዋል::

በታሪክ ወራሪዎች ነበሩ ፥ ተወራሪውችም ነበር ፥ የሰው ባሮች ነበሩ ፥ የሰው ጌቶችም ነን የሚሉ ነበሩ ። ኄኖክ የሺጥላ


ኢሳት የ ሃይሌ ላሬቦን ቃለ መጠይቅ "ያልተገባ ነገር የተላለፈበት"በማለት የእከክልኝ ፥ ልከክልህ መግለጫ አውጥቷል። ያልተገባነቱ ከምን አንፃር ነው ? ከታሪክ አንፃር ከሆን እርሳቸው ( ሃይሌ ላሬቦ ) ያሉት ወይም ( የተናገሩት እና የጠቀሱት ) ነገር ልክ እንዳልሆነ የሚያብራራ የታሪክ ምሁር ጋብዞ እውቀት እና እውነት ላይ በተመሰረተ ውይይት ችግሩን መፍታት።
"ጋላ" መባል እልነበረበት ከሆነ፥ ሃይሌ ላሬቦ አይደሉም ጋላ የሚለውን ስም ያወጡት ወይም ያመጡት። በታሪክ « ጋላ» ይባል ነበር አሉ! ይህም ልክ አለመሆኑን የሚያስረዳ ምሁር መጋበዝ፥ ማወያየት ፥ የተሸነፈው ( ወይም በውይይቱ ) ነጥብ የጣለው አካል እጅ ይስጥ!
በታሪክ ወራሪዎች ነበሩ ፥ ተወራሪውችም ነበር ፥ የሰው ባሮች ነበሩ ፥ የሰው ጌቶችም ነን የሚሉ ነበሩ ። ሰዎች እንደ ...መጋዣ በገመድ ታስረው ወፍጮ ያዞሩ ነበር፥ ወይን ይጨምቁ ነበር፥ ረራራ ይምሱ ነበር ፥ መንገድ ይሰሩ ነበር፥ ቋጥኝ ይፈልጡ ነበር ! ባርነተታቸው የምድራዊ ታሪካቸው እና የህይወት ውጣ ውረዳቸው አንዱ አካል ነው ። በቀኝ የተገዙ ሃገሮች ለቀኝ ገዢዎቻቸው አሽከሮች ነበሩ። አሽከርነታቸው ሰዋዊ ክብራቸውን ሙሉ በሙሉ አሳልፎ እስተመስጠት ይደርሳል። በጌቶቻቸው ተደፍረው ያረገዙ ባሮች ከገደል ላይ የሚወረወሩበት ዘመን ነበር ! እኒህ ባሮች አሽከርነቱን በፍቃድ ባያደርጉትም ስንኳ ፥ በታሪክ አሽከር ሁነው ያለፉ ናቸው። ህንዶች ባንድ ወቅት ተገደውም ቢሆን የእንግሊዝ አሽከሮች ነበሩ ፥ እንግሊዝ ደቡብ አፍሪካን ስትወር በባርነት የተያዙ ህንዶች ባምቡ መንጣሪዎች ነበሩ ! ዛሬ የነዛ ህንዶች የልጅ ልጅ ልጆች በደቡብ አፍሪካ ትልቅ ባለ ሃብቶች ናቸው ! ደቡብ አፍሪካን ሃገሬ ፥ ደርባንን የኛ ወደብ ይላሉ ! ደደብ ስለሆኑ ይሆን እንዲህ የሚያስቡት ? ፊሊፒኖዎች በስፓንያርድ ኮሎኒ ስር በወደቁ ጊዜ ፥ የስፔን አሽከሮች ነበሩ ፥ እንግሊዝ እና ፈረንሳይ የመቶ አመት ጦርነት ሲያደርጉ እንደ ዧን ዷ አርክ አይነት ታጋይን ፈረንሳይ ያፈራችው ከባርነት ለመውጣት የቆረጡ ልጆች ስላላት ነበር ፥ እነ ስኮትላንድ ፥ አየር ላንድ እና ወዘተም እንዲሁ የባርነት ግፍ እዳ ቀማሾች ነበሩ ። ቡሮች በወረሯት ደቡብ አፍሪካ ፥ አይናቸውን የጣሉ እንግሊዞች ከቡሮች ጋር ጦርነት ገጥመው ከብዙ ትግል በኋላ ታሸነፏቸው በኋላ ፥ ቡሮቹን ( አፍሪካንስ ( ወይም ደቾች ናቸው )) ባሪያ አድርገዋቸዋል ! ወደ እኛ ሀገር ስንመጣ ጣልያን ኤርትራን በወረረ ጊዜ ፥ በምፅዋ እና አስመራ የሚኖሩ ኤርትራዊያኖች በተወሰነ ደረጃ የጣልያን አሽከሮች ነበሩ ፥ በትግራይም እንዲሁ የትግሬ የጣልያን አሽከር ነበር። አሽከርነቱ ታሪክ ነው ፥ አሽከር ሆኖ መቆየት ግን የግለሰቡ ፍቃድ ነው !
ስለዚህ ውይይቱ መሆን ያለበት ፥ ለምን እንዲህ ትሉናላችሁ ሳይሆን ፥ የተባለው ነገር የነበረ ነው ወይ ? ማስረጃ አለው ወይ ? ምስክር መዛግብቶች መጥቀስ ይቻላል ወይ ፥ ከዚያ ባሻገር እንዲህ ያለው ታሪክ ለነገ ያለው ጠቀሜታው ምንድን ነው የሚሉት ይመስሉኛል አብይ ቁም ነገሮች።
ሃይሌ ላሬቦ ለምሳሌ « ግራኝ መሃመድን » እንደ አንድ ለስልጣን እንደሚዋጋ ኢትዮጵያዊ እንደሚያዩት ተናግረዋል ፥ ምክንያታቸውንም አስቀምጠዋል ። ይህንን ትንታኔያቸውን ልንገረምበት ሳይሆን ፥ ልንመረምረው ፥ አፍራሽ ከሆነ ማስረጆቻችን አቅርበን ልንፋለው ይገባል እንጂ ፥ እንዲሁ በደፈናው « የማሪያም ጠላት » ብሎ መፈረጅ አግባብ አይመስለኝም ! ኢሳትም በውስጡ የታሪክ እውቀት ያላቸው ምሁራኖች ቢኖሩት « ላሩም ለሽንቱም » መግለጫ ከማውጣት እና በማያቀጥነው ሁሉ ከመቅጠን ፥ ሰፊ ውይይቶች አድርጎ ፥ የተሻለ የታሪክ መግባባት እና መረዳት ላይ ታዳሚው እንዲደርስ ባደረገ ነበር ! ይህንን ከማድረግ ይልቅ፥ እንደለመደው በ ሶሻል ሚዲያ ላይ በሚወነጨፉ ተወርዋሪ ማስጠንቀቂያዎች ቅዘን በቅዘን በመሆን ፥ ለለንደኑ ቃለ መጠይቅ ከ ዋሽንግተን ዲስ ማስታባበያ ሲወጣ እያየነው ነው ! ይህ መታረም አለበት ባይ ነኝ! በተጨማሪ የግንቦት ሰባት ከነ ሌንጮ ጋር ያለው ውህደት እንዲህ ባሉ ነገሮች ይፈርስም ስለሚመስላቸው ፥ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን የጌቶቻቸውም ቁጣም ይኖርበት ይሆናል ! የጎባጣ አሽከር ሆነና ነገሩ ግንቦት ሰባት ላቅለሰለሸው ኢሳት የሚያስመልሰው ከሆነ ችግር ነው!
በመጨረሻ
ፓፕሎ ፒካሶ ናዚ ሂትለር የስፓኒሽ ከተማን ሲያወድም የሚያሳይ አንድ ኩቢዝም ስዕል ሰርቶ ነበር። የስዕሉ ስም ጉሬንሺያ ይባላል። ታዲያ የቢካሶን ጋለሪ ሂትለር የመጎብኘት እድል አጋጥሞት ነበርና ፒካሶን እንዲህ ሲል ይጠይቀዋል
አንተ ነህ ይህንን የሰራኸው ?
ፒካሶም ፈጠን ይልና « አይ እንተ ነህ !» በማለት ለሂትለር ይመልስለታል !
እና ምን ለማለት ነው ፥ ሃይሌ ላሬቦ ተናገሩት እንጂ ታሪኩን አልሰሩትም !!!
ኄኖክ የሺጥላ

Thursday, January 26, 2017

የኖርዌይ አምባሳደር ከሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ጋር ውይይት አካሄዱ !



Norwegian Embassy in Addis baba
የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ እንዲሁም የፓርቲው የውጪ ጉዳይ ኃላፊ መምህር አበበ አካሉ፤ የኖርዊይ አምባሳደር ባደረጉላቸው ጥሪ መሰረት ከአምባሳደር አንድሪያስ እና ከሥራ ባልደረቦቻቸው ጋር በኖርዌይ ኢምባሲ ውይይት አካሄዱ ።
አምባሳደሩ እንደገለጽት ከሆነ፣ የኖርዌይ መንግሥት የኢትዮጵያን እና የአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ

የአሉባልታ አስማት የሆነው የወሬው ሰርከስ ደርቷል – ቆንጅት ስጦታው



– ሐሜቶቻችንና አሉባልታዎቻችን እኮ በሙያተኛ ቢጠኑ ከነዳጅ የበለጠ ስንት የመፍትሔ ሐሳብ ይፈልቅ ነበር፧የማይሰማ የለም ፖለቲካ እንደ ማስቲካ ጣእሙ ሲያልቅ አኝኮ አኝኮ መትፋት በማስባል በመባባል የአሉባልታ አስማት የሆነው የወሬው ሰርከስ ደርቷል አሉ። መቀጣጠል፣ መንጠላጠል ከዚያ ደግሞ መነጣጠሉና መነጣጠቁ የባሰብን ለዚያ ሳይሆን አይቀርም። እሰይ አበጀን፦ ወሬና አሉባልታ ባይኖሩልን ኖሮ፣ ኑሮ እንደሚሰነዝርብን የከባድ ሚዛን ቡጢ ዘመን እንሻገር ነበር፧ እንኳን የ‘ትራንስፎርሜሽን’ ተራ ቁጥር ልንቀያይር፧ የምሬን እኮ ነው።
እናላችሁ ሰሞኑን በማለት፣ በመባልና በማስባል ሰንጠረዥ ጨዋታ ብዙ ስሰማ ነፍሱን ይማረውና ‘አልን ተባልን አስባልን’ ያለው ድንቅ ጸሐፊ ፅ አለኝ። መቼም ነፍስ ይማር የምንለው ሰው ቁጥር፣ ከዋጋ ግሽበቱ ጋር የእናት ልጅ ሆኗል መሰል። ደግሞ ‘ዲ፡ኤን፡ኤ’ እናስመርምር ብላችሁ በቋፍ ያለውን ሥጋ ለባሽ ‘ዴሊት’ እንዳታስደርጉት አደራ። “ጥናቱ ቀርቶብኝ ወሬ በጋቱኝ” አለች አሉ። እንጃ ማን እንደሆነች።
የአሉባልታውያንን ማንነት ከምንመረምር የሚያምርብንና የምንችለውን ‘አሉን’ ብንመረምር ይኼን ጊዜ ስንት ደህና ነገር ይገኝ ነበር። አንዴ የባሻዬ ልጅ፣ “ነዳጅ ካላወጣን በስተቀር ችግራችን አይፈታም ብለው የሚያስቡ ሰዎች ይገርሙኛል፤” አለኝ። ‘የማይገርምና የማይራገም ሰው አለ፧’ እያልኩ በውስጤ፣ “አንተ ምን ትላለህ፧” ስለው፣ “ሐሜቶቻችንና አሉባልታዎቻችን እኮ በሙያተኛ ቢጠኑ ከነዳጅ የበለጠ ስንት የመፍትሔ ሐሳብ ይፈልቅ ነበር፧” ነበር ያለኝ።
ምንጭ እየደረቀ እሱ ከአሉባልታዎቻችን መፍትሔ እንዲፈልቁ ያስባል። አይ አብዝቶ መማር ግን አንዳንዴ። እኔማ ምን እለዋለሁ ያው እንኳን እሱ የመረጃና የደኅንነት ቢሮ ሳይቀር ሰርጎ በማይገባበት በልቤ አዳራሽ “የደላው ሙቅ ያኝካል” ብዬ ተረትኩበታ፦ “ባልተርት ተረትነቴን በምን አስታውሰው ነበር፧” ነው ያለችው፧ ኧረ እኔ የት አውቄያ፧ ሁሉን አዋቂ ነኝ እንዴ፧ ስምንተኛው ሺሕስ ስምንትን ሲያይ ባሰበት መሰል !!!

ታላቅ አውሮፓ አቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ = ፌብሯሪ 16/2017 – ብራስልስ ቤልጄም የአውሮፓ ኮሚሽን ፊት ለፊት


ታላቅ አውሮፓ አቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ = ፌብሯሪ 16/2017 – ብራስልስ ቤልጄም የአውሮፓ ኮሚሽን ፊት ለፊት

ታላቅ አውሮፓ አቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ = ፌብሯሪ 16/2017 ከ13.00ጀምሮ
ቦታ = በሹማን ብራስልስ ቤልጄም የአውሮፓ ኮሚሽን ፊት ለፊት
ዝርዝር መረጃ ከስልክ ቁጥሮች ጋር በማስታወቂያው ምስል ያገኛሉ።
በኢትዮጵያ ውስጥ እየተደረገ የሚገኘውን ግድያ ኣፈናና እስር የጭቆናና የኣምባገነን አገዛዝ በመቃወም የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ ድምጻችንን በጋራ ለማሰማት እንሰባሰብ በሰቆቃ ውስጥ የሚገኙ ወገኖቻችንን ተሰባስበን ነፃ እናውጣ።

ብትፋቀሩ ይሻላል ጎሳ እየለያችሁ ከምትጣሉ – እቴጌ ጣይ

ብትፋቀሩ ይሻላል ጎሳ እየለያችሁ ከምትጣሉ – እቴጌ ጣይ


#ግርማ_ካሳ
16179771_1356218334400112_7320202301805627935_o (1)
አቻሜለህ ታምሩ የሚከተለውን ለጥፎ አነበብኩ። ምስጋንዬን ለዚህ ወጣት አክቲቪስት። ከዚህ በፊት አንብቤ የማላውቀው መነበብ ያለበት የእትጌ ጣይቱ እጹብ ድንቅ ግሩም ደብዳቤ ። እቴጌ ጣይቱ ከአንድ መቶ አመት በፊት የነበሩ ሴት ናቸው። ኦሮሞ ነበሩ። እንግዲህ አስቡት ያኔ የነበሩ አባቶቻችን እና እናቶቻችን ምን ያህል የበሰሉና ፣ የሰለጠኑ እንደነበሩ።
“እናንተ ብትስማሙ እርስ በርሳችሁ ብትፋቀሩ አንድነትችሁን ብታፀኑ ይሻላል እንጂ ትግሬ የብቻ ነው፣ ሸዋ የብቻ ነው፣ ቤገምድር ጎጃም የብቻ ነው እያላችሁ ጎሣ እየለያችሁ ብትጣሉ ምን ትረባላችሁ” ሲሉ ነበር እቴጌይቱ የጻፊት።
የአሁኖቹ ዘረኛ መሪዎች የ እቴጌ ጣይቱ አንድ አሥረኛ እንኳን ብስለት ቢኖራቸው ኖሮ አገር አሁን ያለችበት ደረጃ አትደርስም ነበር።
የእቴጌ ደብዳቤ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ይነበባል፤
__________________
የራስጌ ማኅተም፡ ዝማኅተም ዘእቴጌ ጣይቱ ብርሃን ዘኢትዮጵያ የተላከ ከእቴጌ ጣይቱ ብርሃን ዘኢትዮጵያ፤ ይድረስ ከማህበረ ዴር ሥልጣን ወደብረ ገነት ዘኢየሩሳሌም፣ እንዴት ሰንብታችኋል፡ እኔ እግዚአብሔር ይመስገን ደህና ነኝ።
እናንተ ብትስማሙ እርስ በርሳችሁ ብትፋቀሩ አንድነትችሁን ብታፀኑ ይሻላል እንጂ ትግሬ የብቻ ነው፣ ሸዋ የብቻ ነው፣ ቤገምድር ጎጃም የብቻ ነው እያላችሁ ጎሣ እየለያችሁ ብትጣሉ ምን ትረባላችሁ።
እኛስ በኢየሩሳሌም ነገር ይህንን ያህል መድከማችን ያነን ያህል ብር ባንክ አግብተን የዚያን ወለድና ከቤቱ የሚወጣውን ክራይ መስጠታችን እንዳትቸገሩ የሰው ፊት እንዳታዩ ያነን እየበላችሁ ለኛም የጌታችን ደም ከፈሰሰበት ላይ ዳዊት እንድትደግሙልን እንድታዝኑልን እናንተም ፩ነታችሁ እንዲጸና ብለን ነው እንጂ ገንዘቡ ተርፎ ባገራችን በኢትዮጵያ ለምንሰጠው ሰው አጥተን አይደለም።
አሁንም ስለ እግዚአብሔር ብላችሁ እናንተም እርስ በርሳችሁ ተፋቀሩ፡ ለኛም ዳዊት ድገሙልን እዘኑልኝ። ሳትቸገሩ እንዴት የድፍን አውሮፓ መሳቂያ ትሆናላችሁ። አሁንም ይኸው እማሆይ ወለተ ተክሌ መቃብሬ ከዚያው ይሁን ብላ መጥታለችና አደራችሁን ምኑም በምኑም ነገር እንዳታስቀይሟት። እንግዲህ እሷ እንዲህ አደረጉኝ ብላ የላከችብኝ እንደሆነ እናንተንም እጣላችኋለሁ እኔንም እንዳታስቀይሙኝ።
ሰኔ ፳፱ [29] ቀን ፲፱፻ [1900] ዓመት አዲስ አበባ ከተማ ተጻፈ።

የህወሃት ድራማ ተዋናኞች ሆይ! እጃችሁን ከወልቃይት ላይ አንሱ !


የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ህዝብ በፋሽስቱና በተስፋፊው የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጭ ቡድን የተፈጸመበትን የዘር ማፅዳትና በትግሪያዊነት የመተካት እኩይ ወንጀል ለመመከትና ለመቀልበስ እንዲሁም በመጥፋት ላይ የሚገኘውን ዘሩን ከፈፅሞ ጥፋት ለማዳን ከ1972 ዓ.ም ጀምሮ ሲያደርግ የኖረውን ህዝባዊ ተጋድሎ በወልቃይት ህዝብ አማራ ብሔርተኝነት የማንነት ጥያቄ አቅራቢ ኮሚቴ አማካኝነት የካቲት 24, 2008 ዓ.ም ጎንደር ከተማ “ላንድ ማርክ” አዳራሽ ውስጥ በተጠራ ታሪካዊና ታላቅ ህዝባዊ ስብሰባ ለጎንደር ህዝብ የሃገር ሽማግሌዎችና ተወካዮች ትግሉን በይፋ ማስረከቡ ይታወቃል።ይልቁንም ይህን ታሪካዊ የትግል ቅብብሎሽ ከሃምሌ 5, 2008 ዓ.ም ጀምሮ እዛው ጎንደር ከተማ ላይ በተከፈለው ታላቅ ህዝባዊ መስዋዕትነት የጎንደር ህዝብ ስለወልቃይት የገባውን ቃልኪዳን በደሙ አፅንቶና አትሞት ያለፈ ሲሆን። ይህ ጎንደር ላይ በንፁሃን ወገኖቻችን ደም የታሰረው ታሪካዊ ውል፤ በቆራጥ የአማራ ህዝብ ልጆች ውድ የህይዎት መስዋዕትነት የፀና፣ መላውን ኢትዮጵያዊ በደም ካሳ ያስተሳሰረና፣ ወጣቱን ትውልድ ከወልቃይት ህዝብ ትግል ጋር በማይጠፋ ቃልኪዳን ያቆራኘ የህዝባችን ለዘመናት ያደረገው ትግል ታላቁ ድልና ስኬት ሆኖ አግኝተነዋል።
የወልቃይት ህዝብ የአማራ ብሔርተኝነት የማንነት ጥያቄ ማለት የጎንደር ህዝብ “ድንበራችን ተከዜ ነው!” እያለ ደሙን እንደ ጅረት ያፈሰሰለት፣ የጎጃም ወጣት “ወልቃይት ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ!” እያለ ምድሪቱን በደሙ ያጨቀየለት ፣ የኦሮሞ ኤጆሌ “ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ ይፈታ!” በማለት ከነህይወቱ በቢሾፍቱ ገደል በግፍ የተወረወረለት፣ ኢትዮጵያዊና የኢትዮጵያ ወዳጆች ሁሉ በአንድነት “የንጹሃን ወገኖቻችን ደም በግፍ ማፍሰስ ይቁም!” “ወልቃይት አማራ ነው!” እያሉ በዓለም ታላላቅ አደባባዮች ቀን ከሌሊት፣ ክረምት ከበጋ የተሰለፉለትና የጮሁለት፣ በአጠቃላይ ህዝባችን በአንድነትና በህብረት ሆኖ ከአፅናፍ እስከ አፅናፍ የታገለለትና መስዋዕትነት የከፈለለት የኢትዮጵያውያን ሁሉ ተቀዳሚ አጀንዳ፣ የኢትዮጵያውያን ሁሉ ግንባር ቀደም ጥያቄ ነው!
ይህን ህዝባዊ ጥያቄ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ህዝብ በአደባባይ በጠየቀው መሰረት መመልስ የነገውን ህዝባዊ ቁጣና ቅጣት አሻግሮ መመልከትና ከታሪክ መማር የሚችል የማንኛውም አካል ተቀዳሚ ተግባር መሆን እንዳለበት ልሳነ ግፉዓን ድርጅት በፅኑ ያምናል። ነገር ግን ከጅምሩ የኢትዮጵያና የህዝቧ ጠላት ሆኖ የተነሳው የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጭ ቡድን ይህን ሃገርንና ትውልድን ከዳር እስከ ዳር በአንድነት ያሰለፈና ያስቆጣ ህዝባዊ ጥያቄ በሰላማዊና አግባብነት ባለው ህጋዊ መንገድ መፍትሄ ከመስጠት ይልቅ በተቃራኒውና በተለመደው ፋሽስታዊ የሃይልና የጭካኔ መንገድ የህዝብ መሪዎችንና ተወካዮችን በጀምላ በማሰር፣ በተለያዩ የማሰቃያ ዘዴዎች በማሰቃየትና፣ በማሳደድ ለማንበርከክ መሞከርና በአላማቸው እስከ መጨረሻው የፀኑትንና በመራር ስቃይ ውስጥ ሆነው እንኳ ያልተንበረከኩትን ትንታግ የህዝብ ልጆች በግፍ በመግደልና  አስከሬናቸውን በገበያ መካከል በመጎተት ህዝብን ለማሸበር መጣርና እስከ የማይቀረው ውድቀት ድረስ አጥፍቶ በመጥፋት ለመግዛት መሞከርን ነው።
ከላይ በአጭሩ እንደተገለፀው የወልቃይት አማራ ብሔርተኝነት የማንነት ጥያቄ አቅራቢ ኮሚቴ ከህዝብ የተቀበለውን ታላቅ ተልዕኮና የትውልድ አደራ ለጎንደር፣ ለአማራና፣ ብሎም ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እጅግ በተሳካ፣ ታሪካዊ ደረጃውንና፣ ሂድቱን በጠበቀ ሁኔታ ህዝባዊ ትግሉን አስረክቧልና ምንም አይነት ኢፍትሃዊ የጭካኔና የአፈና መንገድ በህዝባችን ላይ ቢተገበር ትግሉን ሊያጎለብተው እንጂ ሊቀለብሰውም ሆነ ሊያዳፍነው እንደማይችል የኢትዮጵያ ህዝብ የትግል ታሪክ ህያው ምስክር ነው።
ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ ህዝብ በተደጋጋሚ የሚያስተላልፈውን የቁጣ መልዕክት ዛሬም ድረስ በሃይል እጨፈልቃለሁ የሚለው ፋሽስቱና አጥፍቶ ጠፊው የህወሃት እኩይ ቡድን እንደለመደው ሁሉ ዛሬም ህዝብን ወደ ባሰ ቁጣና ተቃውሞ የሚያስገባ ሌላ ተልካሻ ሴራ ውስጥ ተወሽቆ ሲንቦጫረቅ እንደሚውል በተጨባጭ መረጃ ለማረጋገጥ ችለናል። ይኸውም ፦
1ኛ. ሃሰተኛ የወልቃይት አማራ ብሔርተኝነት የማንነት ጥያቄ አቅራቢ ኮሚቴ ማቋቋም
ህወሃት እንደ ለመደው በአንድ በኩል እውነተኛ የህዝብ ወኪሎችንና መሪዎችን በግፍ በማሰር እያሰቃየና በሽብር ወንጀል በመክሰስ በህግ ሽፋን ሞትና እድሜ ልክ እስራት ለማስፈረድ የተበላበትን የ“አኬልዳማ ክፍል …” ድራማ ላይ እየተወነ፤  በሌላ በኩል ለጊዚያዊ ጥቅም ባደሩና በተለያዩ ህወሃታዊ የማንበርከኪያ ወጥመዶች ተጠልፈው ለህወሃት ርካሽ የጥፋት አላማ በተንበረከኩ ደካሞችና ሆድ አደሮች ተጠቅሞ ሃሰተኛ የኮሚቴ አባላትና መሪዎች እየጠፈጠፈ መክረሙንና ህዝብን እንደ ህፃን ልጅ አይናችሁን ጨፍኑና ላሞኛችሁ እያለ ሲጃጃል እነሆ 25 ዓመታት እንደዋዛ አለፉ።
ትላንት በሌሎች እንዳየነው ሁሉ ዛሬ ደግሞ ተረኛ ሁኖ የተገኘው “የወልቃይት አማራ ብሔርተኝነት የማንነት ጥያቄ” አቅራቢ ኮሚቴ ነው። ምንም እንኳ የወልቃይት ህዝብ እንደ አንድ ልብ መካሪ፤ እንደ አንድ አንደበት ተናጋሪ በመሆን ከ 50 ሺ በላይ የህዝብ ፊርማ በማሰባሰብ “ትግሬ ሁን የተባልኩትና ወደ ትግራይ ክልል የተካለልኩት ያለአግባብ በሃይል ነው” “የአማራዊ ብሔርተኝነት ማንነቴ ይከበርልኝ!” “ድንበሬ ተከዜ ነው!” በማለት ጥያቄውንና ውክልናውን ለመረጣቸው ወኪሎቹ ከነ ሙሉ ፊርማው በመስጠት በሰላማዊ መንገድ መፍትሄ እንዲሰጠው ቢጠይቅም ምላሹ ግድያና እስራት ስለሆነ ዛሬም እምነቱንና ቃሉን ጠብቆ በፅናት ከወኪሎቹ ጋር በመቆም መራራውንና አስከፊውን ትግል እያደረገ ይገኛል።
ይህ ህዝባዊ ፅናትና ቁርጠኝነት ያርበተበተው ፋሽስቱ ህወሃት ዛሬም እንደ ትላንቱ ታማኝ ተላላኪዎቹንና አንዳንድ ለሆዳቸው ያደሩ ተንበርካኪዎችን በሃገር ውስጥና በውጭ ሃገር በማፈላለግ ለማሰባሰብና ሃሰተኛ የወልቃይት አማራ ብሔርተኝነት የማንነት ኮሚቴ ለማቋቋም እየዳከረ እንደሚገኝ በተጨባጭ ደርሰንበታል።
ለዚህም ርካሽ ተግባር ተባባሪ ሆነው የተገኙት የሃሰተኛው የወልቃይት አማራ ብሔርተኝነት የማንነት ኮሚቴ አባላት ሁለት አበይት ተልዕኮ የተዘጋጀላቸው ሲሆን እርሱም ፦
  1. በወልቃይት የአማራ ብሔርተኝነት የማንነት ጥያቄ መነሻነት በሃገሪቱ ለተከሰተው አለመረጋጋትና ለደረሰው ሃገራዊ ኪሳራና ለጠፋው የሰው ህይወት ሁሉ በወልቃይት ህዝብ ስም መንግስትን ይቅርታ መጠየቅና፣

  1. በወልቃይት ህዝብ ስም “የወልቃይት የአማራ ብሔርተኝነት የማንነት ጥያቄን” እንደ አዲስ ለትግራይ ክልል መንግስት አስተዳደር ማቅረብና የትግራይ ክልል በሚሰጠው “የራስ ገዝ” አስተዳደር ተስማምቶ ዳግም ወልቃይትን በህጋዊነት ሽፋን ከነዋሪው 90% ለሚሆነው የትግሬ ሰፋሪ ወልቃይትን በሃስተኛው ኮሚቴ ፊርማ ማስረከብን መዳረሻው ያደረገ እኩይ እቅድ ነው።
2ኛ. በእስር ላይ በሚገኘው የወልቃይት የአማራ ብሔርተኝነት የማንነት ጥያቄ አቅራቢ ኮሚቴ አባላት ላይ የሃሰት ምስክር አቅርቦ ማስመስከርና ማስፈረድ።
የወልቃይት የአማራ ብሔርተኝነት የማንነት ጥያቄ አቅራቢ ኮሚቴ ሰላማዊና ህጋዊ አባላትንና የህዝብ መሪዎችን በግፍ አስሮ ማሰቃየትና በሃሰተኛው የካንጋሮ ፍርድ ቤት ውስጥ በሚሰራ የተለመደ ተራ ድራማ በሞትና በእድሜ ልክ እስራት ለመቅጣት መሞከር ማለት የኢትዮጵያን ህዝብ “ጥፋተኛ ነኝ በጥልቅ እታደሳለሁና ጊዜ ስጡኝ” ያስለመነ፣ 100% ተመርጫለሁ ባለ በአመቱ 100% ካቢኔውን በአዲስ ለመተካትና፣ ሃገራችን በታሪኳ አይታው በማታውቀው ሁኔታ ከ6 ወር በላይ ለሆነና መቋጫው በማይታወቅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅና በወታደራዊ አገዛዝ ስር እንድትወድቅ ያስገደደን ህዝባዊ ጥያቄና ቁጣ ላይ በመንግስት ደረጃ መሳለቅና በቀጣይ ከሚመጣው ህዝባዊ ቁጣ መውጫ ቀዳዳ እንዳይኖር አድርጎ በእራስ ላይና ቆሜለታለሁ በሚሉት ህዝብ ላይ አርማጌዶን እንደማወጅ ይቆጠራል።
በአንፃሩ ደግሞ በ200 ሺ ብር የገንዘብ ክፍያና በተለያዩ ጥቅማጥቅሞች ተደልለው በወልቃይት የአማራ ብሔርተኝነት የማንነት ጥያቄ ኮሚቴ አባላት ላይ ለመመስከር በህወሃት የተዘጋጁት
1ኛ. አቶ መኮንን ጋረድ
2ኛ. አቶ ሰጠኝ ለማ ገሪማ
3ኛ. አቶ ተገን መርሻ
4ኛ. አቶ ፀጋይ ሙሉ
መሆናቸውን በተጨባጭ መረጃ አረጋግጠናል። ሌሎች በድርድር ላይ ያሉትንም እንደ ሚወስዱት አቋም ተከታትለን በቅርቡ ይፋ እናደርጋለን።
ይልቁንስ ቀልዱን ለጊዜው እዚህ ላይ አቁሙትና በህግ ሽፋን በግፍ ታፍነውና በየማሰቃያ ቤቱ እየተሰቃዩ የሚገኙ የህዝብ ልጆችን ማለትም፦
ሀ) አዲስ አበባ ላይ የታፈኑ                                    ለ) ጎንደር ላይ የታፈኑ
1ኛ. አቶ ነጋ ባንቲሁን                                       1ኛ. አቶ አታላይ ዛፌ
2ኛ. አቶ አዲሱ ሰረበ                                       2ኛ. አቶ አለነ ሻማ
3ኛ. አቶ ጌታቸው አደመ
4ኛ. አቶ መብራቱ ጌታሁን
5ኛ. ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ
6ኛ. ወጣት ንግስት ይርጋ
7ኛ. አቶ ክንድሺ ሃጎስ …..ወዘተ………
ሐ) በወልቃይትና አካባቢው ታፍነው ሁመራ በእስር ላይ የሚገኙ
1ኛ. አቶ አሊጋዝ አየለ            7ኛ. አቶ ሰጠኝ ድረስ
2ኛ. አቶ ሞላ ሃይሉ      8ኛ. አቶ ባየው ካሰኝ
3ኛ. አቶ ሰለሞን ግዛቴ            9ኛ. አቶ ሰጠኝ አረሩ
4ኛ. አቶ አሻግረው ገዛሃኝ      10ኛ. አቶ መሐመድ ያሲን
5ኛ. አቶ ግዛቸው ድረስ            11ኛ. አቶ መኮነን ደስታ
6ኛ. አቶ ጎይቶም አማረ            12ኛ. አቶ ሊላይ ብርሃኔ….ወዘተ……
እንዲሁም በዚህ ዝርዝር ውስጥ ልናካትታቸው ያልቻልናቸውን የወልቃይት ተወላጆች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱና ወደ ቤተሰቦቻቸውና ህዝባቸው እንዲቀላቀሉ እናሳስባለን።
በመጨረሻም ልሳነ ግፉዓን ድርጅት በአንክሮ ማሳሰብና ማስገንዘብ የሚፈልገው ነገር ቢኖር የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጭ ድርጅት በወልቃይት ህዝብ ላይ የፈፀመው ግፍና ያደረሰው መከራ የንጹሃንን መገፋት በሚያየውና በእውነተኛው ዳኛና ፈራጅ በሆነው በሃያሉ በእግዚአብሄር ፊት ፅዋው ሞልቶ ነበርና ህዝባችን ለዘመናት ዘሩን ከጥፋት ለማዳን ያደረገው ፍትሃዊ ትግል በሃምሌ 5, 2008 ዓ.ም ጎንደር ከተማ ላይ በተደረገው ታላቅ መስዋዕትነት ምክንያት በተቀጣጠለው የአማራ አናብስት ቁጣና ተጋድሎ የሚገባውን ታሪካዊ ክብሩንና ቦታውን ሊይዝ ችሏል። ስለሆነም ከዚያች ታሪካዊ እለት ጀምሮ የወልቃይት ህዝብ ጥያቄ ከወልቃይት ህዝብ እጅ ሊወጣ ችሏል። የወልቃይት ጥያቄ ከኮሚቴዎችና ከፍትህ ተቋማት እጅ ላይመልስ አፍትልኳል። ይልቁንም የወልቃይት ህዝብ ጥያቄ የአደባባይ ጥያቄና የቀጣዩ ትውልድ የትግል አጀንዳ ወደ መሆን ተሸጋግሯል። እዚህ ላይ ከአዲስ አበባ የማስፋፋት ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ የኦሮሞ ወጣቶች ያነሱትን የአደባባይ ጥያቄና ተቃውሞ እንዲሁም ህወሃት መራሹ መንግስት ለጥያቄው በአደባባይ የሰጠውን ምላሽ ልብ ይሏል።
ስለዚህ ለህዝባችን ጥያቄ መፍትሄው አንድና አንድ ብቻ ነው ብሎ ልሳነ ግፉዓን ድርጅት ብፅኑ ያምናል። ይኋውም የተለመደውን ተራ ቀልድና ድራማ በአስቸኳይ አቁሞ ህዝብ ከኮሚቴ ጥያቄ ወደ አደባባይ ትግል ያሸጋገረውን የአደባባይ ጥያቄ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአደባባይ ፍትህ መመለስ ብቻ ነው።
ጀግናውና ብርቱው ህዝባችን ሆይ! ለዘመናት ልጆችህን ከሊቅ እስከ ደቂቅ ገብረህ የተጓዝክበት ትግል ዛሬ የጠላትህን የጣረሞት ጩሃት ለመስማት አብቅቶሃልና ደስ ሊልህ ይገባል። ነገር ግን ይህ ወደ ማይቀርለት ታሪካዊ ሞቱ በውርደት እየተሸኘ ያለው ፍሽስት ቡድን አጫፋሪና ፍርፋሪ ለቃሚ የነበሩት ጥቂት ግለሰቦች ሞቱ የተረጋገጠውን ህወሃት ለማዳን የመጨረሻ እድላቸውን ለመሞከር በሚል እላይ ታች መንቀዥቀዣቸውን ተያይዘውታል። ህወሃት ግን ከቶ ላይመለስ ሞቷልና የባንዳዎችን ልፈፋና ድለላ ሰምተህ ከድሉ ማዕድ ፊትህን እንዳትመልስ አደራ እንላለን! ይልቁንም አንድነትህን አጠናክረህና ሃያሉ ክንድህን አስተባብረህ የጠላትህ ግብአተ ፍፃሜ ላይ ተረባረብ!
ለህዝባችን ሃይል ፅናት የሆነውን ሃያሉን እግዚአብሄርን እናመሰግናለን!
ድል የህዝብ ነው!
ልሳነ ግፉዓን ድርጅት
ጥር 17, 2009 ዓ.ም

በአፋር የሚገኘው የኤርታዓሌ እሳተ ጎመራ ገንፍሎ እየፈሰሰ ነው

(ዘ-ሐበሻ) በመንግስት ቁጥጥር ሥር የሚገኙት የመገናኛ ብዙሃን ዛሬ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ጠቅሰው እንደዘገቡት በዓፋር ክልል የሚገኘው ኤርታዓሌ እሳተጎመራ ከፍተኛ እንቅስቃሴ አድርጎ ሞልቶ እየፈሰሰ ነው::
ፕሮፌሰር ገዛኸኝ ይርጉ ለመንግስት መገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ “የዓለምና የአገር ውስጥ ቱሪስቶች መስህብ የሆነው አስደናቂው ኤርታዓሌ እሳተጎመራ ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ ፍሳሹ ገንፍሎ መልቶና ከዋናው መያዣው ጉድጓድ ወጥቶ በብዛት እየፈሰሰ ነው:: የኤርተዓሌ የቀለጠው ዓለት ፍሳሽ አልፎ ተርፎ የተወሰነ ኪሎ ሜትሮችን ርቆ ሄዶ ሌላ ጕድጓድ ሞልቶ በተጨማሪ ወደ ደቡብ እየፈሰሰ መሆኑን ነው” ብለዋል::
ፕሮፌሰሩ ጨምረውም “አዲስ ክስተት የተፈጥረው ወደ ኤርታዓሌ መሄጃ በስተቀኝ በኩል አንድ ሌላ ስንጥቅ ተከፍቶ እንደዚሁ ተመሳሳይ ፍሳሽ ወይም ላቫ እየወጣና እየፈሰሰመሆኑን የአካባቢው ሰዎች ነግረውናል:: አከባቢው ሩቅ ነው በዙም ነዋሪም ስለሌለው በአሁን ሰዓት የሚያመጣው ችግር የለም፤ እየቀጠለ ከሄደ ግን አደጋ ሊያመጣ ይችላል” ካሉ በኋላ ሆኖም ግን እንዲያውም ወደ ደቡብ አቅጣጫ ወደ አፍዴራ ከተማ ፍሳሹ እየሄደ በመሆኑ ሁኔታው በዚሁ ከቀጠለና ካልቆመ አስቸጋሪ ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚችል ማመልከታቸውን መንግስታዊ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል::

የወያኔ ብሄራዊ መረጃ ተደማጭነት አላቸው የሚባሉ ግለስቦች እንዲታፈኑ በሚስጥር ማሳሰቡ ተሰማ

የልዑል ዓለሜ ዘገባ
በብሄር ብሄረሰብ አስተዳደር ክልል ውስጥ የተዋቅሩ የብሄራዊ መረጃ ቅርንጫፍ አስተዳደር ባለስልጣን አካሎች እነርስም ተጠሪነታቸው ለክልል የደህንነት ብሄራዊ መርጃ ክንፍ የሆኑ የየወረዳው የፀጥታ ዘርፍ ሀላፊዋች በአካባቢያቸው የሚኖሩ የተቃራኒ ፓርቲ አባላቶችንና አመራሮችን የእለት ተእለት እንቅስቃሴ በማጥናት እንዲያቀርቡ ከብሄራዊ መረጃ የህዝብ ግንኙንት እና መምሪያ አምራር ባልስልጣናት ቀጭን ትእዛዝ ወርዶላቸዋል::

ብሄርዊ መረጃው ያወረደው ትእዝዝ በተለየ መልኩ ሕዝብን በማሳመን ተደማጭንት አላቸው የሚባሉ ግለስቦች እንዲታፈኑ የሚያዝ ከመሆኑ ባሻገር በሀገር አቀፍ ደረጃ በሽብርተኝነት ከተፈረጁ ፖርቲዎች ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ግንኙነት አላቸው ተብለው የሚጠረጠሩ 2000 ሺ ይሚጠጉ ግልስቦችን ስም ዝርዝር አዳብሎ ከጥብቅ አጽንኦት ጋር ያስተላለፈ ሲሆን ድንገትኝና አደገኛ ሐገርዊ ጥቃት በእነዚግለስቦች እንደተቀናበረ. አውስቷል::

የህወሀቱ ብሄራዊ የመረጃ ደህንነት ከተራ የአካባቢና የወረዳ ፀጥታ ዘርፍ ሀላፊዎች ጋር በብርቱ ያወራረደው ትእዛዝ አርበኞች ግንቦት 7 ለ 460 አባልት ህቡሕ አደራጆች ከፍተኛ የጥቅም በጀት ያፈሰሰ ነው ከማለቱ ባሻገር 900 የታጠቁና የተበተኑ ግዳጅ ተወጪዎች መሰማራታቸውን ፍንጭ ሰጥቷል::

የህወሑት በአዴን አማራር ትጃሮች ከሚለው የቀጠለ — ከአስገደ ገብረስላሴ

ትላንትና ስለትጃሩ የህወሐት አማራር በትግራይ ህዝብ ስም እየነገደ የሚፈጽመው ምዝበራ ከቡዙዏቹ በጥቂቱ ለመግለጽ ሞክሬ አለሁ ፣ ዛሬ ደግሞ የህወሐት ስሪት ስለሆኑ የበአዴን ትጃሮችና ሌሎች በመጠኑም ቢሆን እማውቀው እገልጻለሁ ስለ እምትከታተሉኝ አመሰግናለሁ ።
ቢሊየኖሩ የህወሐት አማራር በትግሉ ጊዜ በተለያዬ መንገድ ያጣራቀመው ብር ፣ዶላር ፣ፓወንድ፣ደችማርክ፣ የሱኡዲ ሩያል ፣ እጅግ ቡዙ ቁሳቁስ ሽጦ ወዘተ ካጣራቀመው ሀብት የኤፈርት ኩባንያዏች ካቋቋመ በኃላ ሁሉም የህወሐት ስሪት ፓርቲዏች በተለይ የበአዴን አማራር በኤፈርት ሀብት የቅናት ምልክት በማንጸባረቃቸው ፣ የህወሐት ትጃሩ አመራር ለአጋር ፓርቲዏች እንደ መስታገሻ ታሳቢ በማድረግ ፣
1 ለበአዴን 60 የተላያዩ መኪኖች ፣ከሞቶ ሚሊዮን በላይ ብርን በመደጎም የአሁኑ የበአዴኑ ትጃር ጥረትን ፣ የአማራ ብድርና ቁጠባ ባንክ እንዲቋቋም አደረገ ።
2 ለኦዴድ አማራር ከ100 ሚሊዮን በላይ ብር እና 35 የጭነት ካሜኖች በመደጎም ድንሾ የሚባል ኩባንያ በማቋቋም የተለያዩ ኩባንያዏች ተቋቁመው ነበር ግን በኦሆዴድ አማራር በሙሱና ተመዘበሩ ። በአሁኑ ጊዜ ምን ደረጃ እንዳሉ መረጃ የለኝም ።
3 የዴሄደን አማራርም በወቅቱ ይቋቋም ስለነበረ እነመለስ ብልጦች ነበሩ እና ደህዴን ጥያቄ ማስነሳቱ አይቀርም ከሚል ታሳቢ በማድረግ ፣ አስቀድመው 70 ሚሊዮን ብርና ከ15 በላይ የጭነት መኪና ተሰጥቶዋቸው ወንዶ የሚባል ኩባንያ እንዲያቋቁም በህወሐት መመሪያ ተሰጥቶዋቸው ተቋቋመ ። ይህ ኩባንያ ቡዙ ሳይራመድ ከስሞ እንደቀረ ነው መረጃውን ያለኝ ።
እንግዲህ የኦሆዴድና የዴሄደን አማራር ኩባኒያዏች እንተዏውና ከህወሐት ትጃሮቹ በ2ኛ ደረጃ የሚሰለፍ የበአዴን ትጃሩ ጥረት እንመልከት ።
የበአዴን አማራር ጥረት ስንትና እነማን የሚባሉ ኩባንያዏች ናቸው ?

Tuesday, January 24, 2017

የህብር ሬዲዮ ጥር 14 ቀን 2009 ፕሮግራም

<…ተቃዋሚዎች ጋር እንደራደራለን የሚሉት እነሱ ቀለብ ከሚሰፍሩላቸው የስም ተቃዋሚዎች ጋር አንዳንዶችም በስልክ እየተጠሩ ገና ለገና እንታሰራለን በሚል የሚደረግ ሕወሃት/ኢህአዴግ ለራሱ ፕፖፖጋንዳ የሚያደርገው እንጂ ዶ/ር መረራ፣በቀለ ገርባን ጨምሮ በርካታ የተቃዋሚ መሪዎችና አባላት፣ጋዜጠኞች ታስረው ተቃዋሚ አጥፍተው ያው ለምዕራባውያን ፍጆታ ካልሆነ እንዲህ ያለው ማታለያ አይሰራም…>
– አክቲቪስት ነጌሳ ኦዶ ዱቤ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ዓለም አቀፍ የድጋፍ ቡድን ሊቀመንበር ሰሞኑን ገዢው ፓርቲ በኢትዮጵያ ከተቃዋሚዎች ጋር እያደረኩ ነው ስለሚለው ውይይትና ድርድር በተመለከተ ከህብር ተጠይቀው ከሰጡት ማብራሪያ የተወሰደ( ክፍል አንድን ያድምጡት)
<…የሕወሃት ባህሪ ከበረሃ ጀምሮ የሚከተለው ተመሳሳይ ስልት ነው። ሲጨንቀው እንደራደር ይላል በእውነተኛ ድርድር አያምንም። በረሃ ለድርድር የጠሯቸውን በተኙበት ገሏል። ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታት ሚከተሉት ያንኑ ነው። አሁን እነሱ ድርድር የሚሉትን ማጭበርበሪያ ማንም አይቀበለውም ይልቁን ራሳቸውን ነው የሚሸውዱት … ይሄ ሁሉ ተቃዋሚ ታስሮ ና ተደራደር ስትባል ከረቫት አስረህ መሄድ ክህደት ነው …>
– አክቲቪስት መስፍን አማን በኔዘርላንድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ሊቀመንበርና ከቀድሞ የቅንጅት መሪዎች አንዱ ገዢው ፓርቲ እያደረኩ ነው ስለሚለው ድርድር ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ክፍል አንድን ያዳምጡት)
የአሜሪካው አዲሱ ፕ/ት ዶናልድ ትራም ስልጣን መጨበጥን ተከትሎ በአለም ላይ የተስተዋሉት የድጋፍ፥የተቃው እና የስጋት አስተያየቶች ሲቃኙ (ልዩ ጥንቅር)
<…የአማራ ጉባዔ ዓላማ አማራው በአማራነቱ ራሱን ችሎ የሚደራጅበትን ትልቅ መሰረት ለመጣል ነው። የአማራ ኮሚኒቲን ለማጠናከር ነው። በጉባዔው ላይ የተለያዩ የአማራ ድርጅቶችና ምሁራን ተገኝተው የተለያዩ ገለጻዎችን አድርገዋል። በስብሰባው ሰፊ ግንዛቤ የሚያስገኝ ስራ ሰርተናል ።አገር ቤት ላለው ትግል ጉባዔው ምን ፋይዳ ያደርጋል ለተባለው ግን …> አቶ ውብሸት መኮንን በሜሪላንድ ሲልቨር ስፕሪንግ የተደረገው የአማራ ጉባዔ አስተባባሪዎች አንዱ ስለ ጉባዔው ጠይቀናቸው ከተናገሩት(ቀሪውን ያድምጡት)
ከኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ አመራር ከዶ/ር ኤርሚያስ አለሙ እና ከኢትዮጵአ ብሄራዊ የሽግግር ም/ቤት ሊቀመንበር አቶ ስለሺ ጥላሁን ጋር ያደረግነው ቃለ መጠይቅ ( ሁለተኛ ክፍል )
ሌሎችም
ዜናዎቻችን
ሕወሓት/ኢህአዴግ ተቃዋሚ አጥፍቶ የሚያደርገውን የይስሙላ ድርድር ሕዝቡ እንዳማይቀበለው ተገለጸ

ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የተራበው ህዝብ ቁጥር እየጨመረ ነው – ዘነበ ዘ ቂርቆስ

የወያኔ ስርዓት ኢትዮጵያን ከተቆጣጠረ ጀምሮ ከ5 ያላነሱ ከባድ ርሃቦች ተከስተዋል ሆኖም ግን በባባሪያ አሳዳሪዎቻቸው ምዕራባውያን ከለላ ምክንያት እስከ ዛሬ ገበናቸው እየተሸፈነ ቆይቷል ሆኖም ግን ከጊዜ ወደ እየባሰበት እንጂ እየተሻሻለ መምጣት ያቃተው የረሃብ ጉዳይ ለተከታታይ ሁለተኛ ዓመት ዘንድሮ በድጋሚ በምስራቅ በምዕራብ እና አንዳንድ የሰሜኑ ክፍሎች የርሃብተኛው ቁጥር እየጨመረ ይገኛል በተለይ በምስራቁ የኢትዮጵያ ክፍል ኦጋዴን አካባቢ ከፍተኛ ከፍተኛ የሆነ የረሃብ አደጋ አንዣቧል ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የረሃቡን አደጋ ከወዲሁ ለመከላከል በአገሪቷ ያለው የአስቸኳይጊዜ አዋጁ እንቅፋት እየሆነ እንዳለና ተረጂዎች በጊዜው እርዳታ ለማግኘት ባለመቻላቸው ምክንያት ለከፍተኛ የጤና መቃወስና ለሞት አደጋ ተጋልጠው ይገኛሉ ። አንዳንዶቹም አቅም ያላቸው አካባቢያቸውንና ቄያቸውን ለቀው ለመውጣት ቢሞክሩም አሁን በአገሪቷ ያለው ወታደራዊ አገዛዝ አካባቢውን ለቆ መሄድ ማንኛውንም እርምጃ ሊያስወስድ በመቻሉ ይህንን በመፍራት ባሉበት እንዲቀሩ ሆነዋል ።
በተለይ በዚህ በኦጋዴን አካባቢ ያለው አስተዳደር በደል ከሁሉ የከፋ እንደሆነና በቅርቡ እንደምናስታውሰው የሱማሌው ክልል ፕሬዚዳንት አብዲ ሞሃመድ ኦማር የክልሉን በጀት ከ25 ሚሊዮን ብር በላይ ለትግራይ ህዝብ መልሶ ማቋቋሚያ በሚል ያለ ህዝብ ፈቃድ አውጥተው ለባሪያ አሳዳሪዎቻቸው መስጠቱ አይዘነጋም ።
ዋይ ዋይ ሲሉ የረሃብን ጉንፋን ሲስሉ
ዘነበ ዘ ቂርቆስ


 

“ድሃ ተበደለ፤ ፍርድ ተጓደለ” ኢህአዴግ የማይቀርፈው ሙስና — አክሎግ ቢራራ (ዶር)


አክሎግ ቢራራ (ዶር)
“ድርጅታዊ ምዝበራ” ብየ የሰየምኩትን መጽሃፍ ስጽፍ ከሁሉም በላይ ያሳሰቡኝና ያስጨነቁኝ አስኳል ጉዳዮች ሶስት ናቸው፤
ዶ/ር አክሎግ ቢራራ
ዶ/ር አክሎግ ቢራራ
አንድ፤ አብዛኛው በድህነት፤ በረሃብ፤ በበሽታ፤ በሰብአዊ መብቶት ረገጣ፤ በአስተዳደር ብልሽት የሚሰቃየው ከ90 በመቶ በላይ የሚገመተው የኢትዮጵያ ሕዝብ አሰቃቂ ደረጃ ላይ መድረሱ ነው።
አክሎግ ቢራራ (ዶር)
ሁለት፤ አስደናቂ እድገት ታሳያለች በምትባለው የምግ ጥገኛዋ ኢትዮጵያ፤ መብቱ ተገፎ፤ የስራ እድል አጥቶ፤ በአገሩ በኢትዮጵያ እየኖረ ፈጥሮና ስርቶ ራሱን የማሻሻል እድሉ ዝግ የሆነበት ከ70 በመቶ በላይ የሚገመተው የደርግና “የኢህአዴግ አዲስ ትውልድ” በገዢው ፓርቲ መገለልና መብቶቹ ሁሉ መታፈን ነው። የዚህ ተተኪ ትውልድ እጣው ለመብቱ ሲከራከር ግድያ፤ አፈናና እንዲሰወር መደረግ ነው። ባለፈው ዓመት ስንት ወጣት እንደሞተ ባይታወቅም ከሁለት ሽህ በላይ እንደሚገመት የውስጥ ተመልካቾች ይናገራሉ። ከ110,000  ያላነሰ ኦሮሞና አማራ ወጣት እንደታሰረ ይገመታል። ገዢው ፓርቲ መሰረታዊ ችግሮችን ለመፍታት ፈቃደኛ ስላልሆነና ብቃትም ስለሌለው መፍትሄው ማፈን፤ ማሰር፤ መግደል፤ እንዲሰወርና እንዲሰደድ ማስገደድ ሆኗል። በዚህ አይነት ሂደት እስር ቤቶችን ካላስፋፋ በስተቀር ያሉት እስር ቤቶች አይበቁም።
ሶስት፤ አንድ ስርዓት በሙስና የተበከለ ከሆነ ሰላምና እርጋታ አይኖርም። በዜጎች መካከል ያለው የገቢና የኑሮ ልዩነት እየተባባሰ ይሄዳል። ይህ አሰቃቂ ሁኔታ ቀስ በቀስ ለአገር መፈራረስ ዋና መንስኤ ይሆናል። ኪራይ ሰብሳቢነትና ሙስና መዋቅራዊ ሲሆን የሚያስከትለውን አደጋ በመረጃ ተደግፋ ያቀረበችው ደራሲ ሳራህ ቸየዝ “Thieves of State: why corruption threatens global security,” በሚለው መጽሃፏ አፍጋኒስታን፤ ግብጽ፤ ሶሪያ፤ ኢራቅ፤ ናይጀሪያና ሌሎች ተመሳሳይ አገሮች እንዴት በመፈራረስ ላይ እንዳሉ ታሳያለች። ዋናው ነጥቧ የፓርቲና የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ለሕዝብ ያለባቸውን አደራና ሃላፊነት ትተውና ረስተው፤ ራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ስላከበሩ አገሮቻቸው የጦርነት አውድማ ሆነዋል የሚል ነው። የሞባረክ መንግሥት የወደቀበት ዋና ምክንያት ሕዝቡን አፍኖ፤ ስልጣኑን ተጠቅሞ፤ ራሱን፤ ቤተሰቦቹን፤ ወዳጆቹንና ደጋፊዎቹን፤ ጀኔራሎቹን ጨምሮ ስላከበረ ነው የሚል ድምዳሜ አቅርባለች። በሙስና የተበከለ አምባገነን መንግሥት የመሳሪያ የበላይነትም ቢኖረው በሕዝብ አመጽ እንደሚወድቅ አሳይታለች። የሙስና አደጋው ለአገር መፈራረስ ግብአት እንደሚሆን መረጃዎችን አቅርባለች።

አማራውን ፍለጋ (መስቀሉ አየለ)

የአማራው ህብረተሰብ በታሪክ አጋጣሚ እንደ ሎተሪ እጣ ከወጣላቸውና ከበታችነት ስሜት (የኢንፌሪየሪቲ ኮምፕሌክስ) ፣ ኤክዞኖፎቢያ፣ ወዘተ መገለጫ የሆነው የዘረኝነት ወይንም ስሙን ሲያጣፍጡት ብሄርተኝነት የሚሉትን የስነልቦና ቀውስ አምልጦ የወጣ፣ አማራዊነትን በኢትይጵያዊነት ተክቶ ማሳደግ (ማኒፌስት ማድረግ) የቻለ ህዝብ ነው። ይሕ መታደል ነው። ከማንነት ወደ ሰውነት ማደግ ነው። ከመንደርተኝነት ወጥቶ ዩኒቨርሳል የሆነ መገለጫን ገንዘብ ማድረግ ነው። ይህንን ነገር ከታደሉት በአለም ውስጥ ካሉት በጣት የሚቆጠሩት ህዝቦች
፩) የሰርብ ህዝብ፤
፪) የራሽያ ህዝብ፤
ይኽ ህዝብ ከናፖሊዮን እስከ ናዚ… ከናዚ እስከ የዘመኑ የአሜሪካ ኒዮ ኮንሰርቫቲቨ በየዘመኑ የተነሱትን አምባገነኖን ልክ ያስገባን በምን አይነት ከሰማይ ባለ መከራ ተፈትኖ ያልተሰበረ ህዝብ ነው። ፫ የእንግሊዝ ህዝብ፤ የመጫረሻው ኢምፓየር ሆኖ መውጣቱ ሳይንስና ቴክኖሎጅ ከተፈጠረበት ዘመን ጋር መግጠሙ አመች ሁኔታ ፈጥሮለት አሁን አለማችን የምትመራበትን Time & Space መለኪያዎች ወጥነት ባለው መልኩ ቅርጽ መስጠታቸው; የአለም አገሮችን ካርታ መወሰናቸው; ፣ቋንቋቸውን አለም አቀፍ ማድረጋቸው፤ እንዲሁም አለማቀፋዊ ተቁዋማትን በመልካቸው ቀርጾው በማለፋቸው የራሳቸውን አሻራ በመጣል የተሳካላቸው በመሆኑ ይኽ ነገር ዛሬ ድረስ ለማንም በሚታይ መልኩ የፈተረላቸው ሳይኮሎጅካል አድቫንቴጅ የማይካድ ነው።

ከጥልቅ ተሃድሶው ማግስት ዘመቻ ዘ-ፀዓት (ገለታው ዘለቀ)

ለወትሮው ከገዢው ፓርቲ አካባቢ የተለመደው የተሃድሶ ትርጉም ለየት ያለ ነበር።  “ኢህአዴግ” ስብሰባዎችን ያደርግና ሲጨርስ “የተሃድሶ ሰኣት!” ይባልና በዚያን ጊዜ የማእድ አገልግሎትና የተለያዩ መጠጦች የኪነት ትርኢት የሚቀርብበት ሰኣት ተሃድሶ ይባላል። ለአንድ የገዠው ፓርቲ አባል ተሃድሶ ሲባል ቶሎ ወደ ህሊናው የሚመጣው ነገር ድግስ ይመስላል።  ከስብሰባ በኋላ ዘና ማለት።  ይሁን እንጂ በቅርቡ ጠቅላይ ሚንስትሩ በጥልቀት በመታደስ ላይ ነን ሲሉ የገለፁ ሲሆን ይህ ተሃድሶ በአእምሮ መታደስን-መለወጥን የሚያሳይ እንደሆነ ተገልፃልናል። ይሁን ይሏል። መቼስ የተሃድሶ ትርጉም ከድግስ አልፎ እውነተኛ ትርጉሙን ከያዘና በአእምሮ መታደስን ከጨመረ አንዳንድ ለውጥ የናፈቀው ቢጓጓ አይፈረድም ይሆናል። በመሆኑም  ተሃድሶ ከተለመደው ትርጉም አልፎ በአእምሮ መለወጥን መታደስን ሪፎርሜሽንን ካመጣ ግሩም ነበር። እንግዲህ ጠቅላይ ሚንስትሩ በጥልቅ ተሃድሶ ላይ ሰነበትን ካሉ ለውጥ ያለ ልክ የናፈቀው ሰው በጥልቀት በመታደስ ላይ ከከረመ ፓርቲ የሚጠብቀው ጥልቀት ያለው ጉዳይ አለ። አንድ ድርጅት በጥልቀት ልታደስ ካለ ጥልቅ ችግሮች ገጥመውታል ማለት ነው። የችግሩን ጥልቀት ተገንዝቧል ማለት ነው።  ይህ ፓርቲ የገጠመውን ጥልቅ ችግር ተረድቶ ለመውጣት ቆርጧል ማለት ነው። እናም ለውጥ ናፋቂው ህዝብ የሚጠብቀው  ጉዳይ መውጣት (exodus) ነው። ገዢው ፓርቲ እንደ ፓርቲም እንደ ግለሰብም በምን በምን ጉዳዮች ላይ መውጣት exodus ሊያውጅ ይገባል? በሚለው ላይ ትንሽ እንወያይ።
  1. የፓለቲካ ኮሚትመንት ለማምጣት መውጣት
በጥልቅ መታደስ ማለት በጥልቀት ራስን ከውጭ ወደ ውስጥ ከውስጥ ወደ ውጭ አይቶ  በደካማው ጎን ላይ ለመፀፀት ብቻ አይደለም። ጥልቅ ተሃድሶ መውጣት ማለት ነው። ዘ ፀዓት ማለት ነው። ህዝብ ካልወደዳቸው የፓለቲካ አስተሳሰቦች፣ ከያዙን የብሄር ፓለቲካዊ አርበኝነት ስሜትና አደረጃጀት፣ ከፍርሃት፣ ብዙ አመት ተጉዘንባቸው ከህዝብ ካጋጩን አስተሳሰቦች በጀግንነት መውጣት ማለት ነው ጥልቅ ተሃድሶ ማለት። በጥልቅ ተሃድሶ ውስጥ ከረምኩ ያለ ፓርቲ ከግምገማው ማግስት ካጠፋቸው ጥፋቶች ሙሉ በሙሉ መመለስ ይጠይቃል። ከመፀፀት ያለፈ እርምጃ ይሻል።
ከብዙ ዓመታት በፊት አንድ ጲላጦስ የሚባል ዳኛ ነበር። ይህ ዳኛ ተሰሚነት የነበረው አንቱ የተባለ ዳኛ ነበር። ታዲያ አንድ ቀን አንድ  ለሙያው ያለውን አርበኝነት የሚፈትን ሰዓት መጣበት። አንድ ንፁህ ሰው በሃሰት ተከሶ ወደዚህ ዳኛ መጣ። በዚህ ንፁህ ሰው ላይ ህዝብን የሚያወናብድ ስራ ተሰርቶ አገር ተሸብሯል። ጲላጦስ ግን ሁሉን ያውቅ ነበርና በዚህ ሰው ላይ ለመፍረድ አንጀቱ አልቻለም። ይሁን እንጂ የቆረጠና የወጣ ዳኛ አልነበረም። ከዚያም ከዚህም ሳይጠየቅ ይህን ፈተና ለመወጣት የጣረ ብልጣብልጥ ዳኛ ነበር። እናም ለካህናቱና ለተከታዮቻቸው እኔ ከዚህ ሰው ምንም ጥፋት አላየሁም ነገር ግን እናንተ ካላችሁ የፈለጋችሁትን አድርጉ አላቸው። ይህ ብቻ ሳይሆን ለበኣል አንድ ወንጀለኛ ይለቀቅ ዘንድ አሳብ አቀረበና በርባን የተባለውን ወንበዴ  ለቀቀ። በርግጥ ኢየሱስን የሰቀለው የእስራኤል ህዝብ ወይም አይሁዳውያን ሁሉ አይደሉም። የተወሰኑ ካህናት ያወናበዷቸው ሰዎች ነበሩ። ጲላጦስ ይህን ያውቃል። ነገር ግን ሙያውን ህሊናውን ሰብሮ ከስራው መቆየትን መረጠ። ነገር ግን ከዚያ ሰው እዳ ነፃ ነኝ ብሎ እጁን መታጠቡ ከተጠያቂነት ነፃ አያወጣውም። ይህ ዳኛ አልወጣም። እጁን ታጠበ እንጂ ከህሊና ክስ ነፃ አይሆንም። ህሊናው አይታጠብለትም። እጁን ቢታጠብም ከፍርሃት የተነሳ ወንጀለኛ ለቆ ንፁህን ሰው አሳልፎ ሰጥቷልና በአእምሮ አይታደስም። ይህ ዳኛ መውጣት ነበረበት። መውጣት እንደ ብርቱካን ሚዴቅሳ ነው። መውጣት ደረጃው ከፍ ያለ ነው። በጥልቅ ተሃድሶ ውስጥ ከገቡ ካድሬዎች መሃል ድርጅቱ ከህዝብ ጋር መራመድ ያልቻለ መሆኑን የተረዱ ነገር ግን በፍርሃት ውስጥ ሆነው ያሉ አባላት ሁሉ ምን አልባት በዚህ ጥልቅ ተሃድሶ ውስጥ እጃቸውን መታጠብ አይበቃም። እምቢኝ ያሉ የወጡ ካድሬዎች ሲኖሩ ነው ለውጥ የሚመጣው። እነ ዶክተር መረራን፣ እነ እስክንድርን የመሳሰሉ ንፁህ ሰዎች ጉዳይ በጥልቀት ለመታደስ ለወሰነ ፓርቲ በርግጥ ለመታደስ ከልብ ፈቃደኛ ይሁን አይሁን ማሳያ ነው። ካድሬዎች በነዚህና በሌሎች ንፁሃን እስራት ላይ እጅ ከመታጠብ አልፈው ሊወጡ ይገባል።   በመሆኑም ከጥልቅ ተሃድሶ ባሻገር የሚጠበቀው ነገር ከፍ ያለ እርምጃና ውሳኔ ነው። እንደ ጲላጦስ ያሉ ካድሬዎች የራሳቸውን ሥራ ከማቆየት ያለፈ ጥቅም አያመጡም። ህዝብ የሚሻው የፓለቲካ ኮሚትመንት ነው። በመሆኑም ከዚህ ጥልቅ ተሃድሶ ህዝብ የሚጠብቀው እጅ መታጠብን ሳይሆን  እንደ ብርቱካን ሚዴቅሳ የውሳኔ ሰው እንድትሆኑ ነው። ያን ጊዜ ነው የጥልቅ ተሃድሶ ትርጉም የሚኖረው። ጲላጦስን አለመሆን ነው። በነገራችን ላይ ዳኛ ጲላጦስ በመጨረሻ ራሱን እንዳጠፋ ተመራማሪዎች ፅፈዋል።
  1. ለብሄራዊ መግባባት ሁኔታዎችን ለማመቻቸት መውጣት
ሌላው ጉዳይ ገዢው ፓርቲ እንደ ፓርቲ ከጥልቅ ተሃድሶ ማግስት የሚጠበቅበት ነገር የብሄራዊ መግባባት ጥሪ ነው። ሃገራችን ከመቼውም ጊዜ በላይ በከፍተኛ ማህበራዊ ቀውስ ውስጥ ናት። ማህበራዊ ካፒታላችን እጅግ ወርዷል። ይህ ደግሞ አደገኛ ነገር ነው። የኢኮኖሚው እድገት ብዙ የመረጃ ችግር እንዳለበት ተገልጿል። ሙስና ሃገሪቱን ሊያፈርስብን ነው። የሰው ልጅ ይራባል። እጅግ ብዙ ህፃናት ጎዳና ወጥተውብናል። ህዝቡ በኑሮ ውድነት እያነባ ነው። ወጣቱ ተሰደደ። ብዙ ወጣት ምድረ በዳ ቀረብን። ሴቶች በአንዳንድ አረብ አገራት ተሰቃዩ። ፓለቲካችን ውጥረት ውስጥ ነው። ሁኔታዎች በዚህ ሊቀጥሉ አይችሉም። በዚህ ወቅት አንድ ገዢ ፓርቲ ጥልቅ ተሃድሶ አደረኩ ካለ የምንጠብቀው ነገር ሃቅኛ ዲያሎግ ለማድረግ  ቆርጦ መውጣትን ነበር።  ከአንዳንድ ፓርቲዎች ጋር መራርጦ ንግግር አደረኩ ለማለት ያህል ሳይሆን መንግስት ከማይወዳቸው ጋርም ለመነጋገር መውጣትን ይጠይቃል ጥልቅ ተሃድሶ። ለሃገራችን መፃኢ እድል ትልቅ ተስፋ ያለው ከምክክር የሚመጣ መፍትሄ ነው። ብዙ ተቃዋሚን አግልሎ ጥቂት ፓርቲዎችን ሰብስቦ ብሄራዊ ምክክር እያደረግን ነው ማለት አይቻልም። ሁሉን አቀፍ ባልሆነ መድረክ ላይ የሚጋበዙ ፓርቲዎችም በሃቀኝነት እኛ ብቻ ሳንሆን ስለሃገራችን የምናስበው ሌሎች ሃይሎችም ስላሉ እነሱም መጋበዝ አለባቸው አለበለዚያ ለማስመሰል የሚደረግ ውይይት ተገቢ አይሆንም ማለት አለባቸው። ለውጥ ፈላጊ ነን ለህዝብ ነው የቆምነው የሚሉ ፓርቲዎች ሁሉ ይህን ጉዳይ ማንሳት አለባቸው። የገዢው ፓርቲ አባላትም መንግስት ሁሉን አቀፍ ውይይት ያደርግ ዘንድ ፓርቲውን ወጥረው መያዝ አለባቸው። እውነት በጥልቀት ከታደሱ።
  1. ይቅርታ ለመጠየቅ መውጣት
በአእምሮ መታደስ ለማምጣት እልህ ወይም ደግሞ ትንሽ ለውጥ ፈልጎ እንደ ጲላጦስ እጅ መታጠብ ጥሩ አይደለም። መሪዎች እንደ ድርጅት ድርጅታቸው በሰራው ስህተት በብዙዎች ህይወት ላይ ተፅእኖ ፈጥሯልና መንግስት ይቅርታ ለመጠየቅ መውጣት አለበት። ይቅርታ እድሜን ይጨምራል። ኮሙኒኬሽንን ያስተካክላል ያድሳል። ከኢትዮጵያ ፓለቲካ ሰፈር የጠፋው ይሄ ነው። ይህ ሁሉ ችግር እየተፈጠረ መንግስት ሃላፊነት የማይወስድ ከሆነ ከህዝብ ጋር ይቆራረጣል። ባለሁበት የዓለም ክፍል መንግስት ወይም መሪዎች ላጠፉት ጥፋት ይቅርታ ሲጠይቁ ማየት የተለመደ ነው። ይህ ዓይነት ልብ ከኢትዮጵያ የፓለቲካ መሪዎች ሰፈር መገኘት አለበት። ይቅርታ መጠየቅ ብቻ ሳይሆን የእርምት ርምጃ መውሰድን የሚጠይቅ ነው ይቅርታ። የኢትዮጵያ ህዝብ ልቦናው ቅን ነው። ይቅርታ ሲባል ርህራሄንና ክብርን በአፀፋው የሚዘረጋ ህዝብ ነው። በመሆኑም በጥልቅ ተሃድሶ ውስጥ ከረምኩ የሚለው ገዢ ፓርቲ የሚጠበቅበት አንዱ ነገር ይቅርታ መጠየቅ ነው። አንዳንዴ የሚገርም ነገር ይሰማል። መንግስት ጥሩ ስራ ሥሠራ ጥሩ ሰራህ አልባልም መጥፎውን ብቻ ነው የሚያዩት ይላል። እንግዲህ ፓለቲካዊ መሪ መሆንን የመረጠ ሰው ይህንን መረዳት አለት። ጤና ኬላ በሰራ ቁጥር አጨብጭቡልኝ ማለት አይገባም። ህዝብ ያውቃል። ምስጋናው ተገቢ ከሆነ ይሰጣል። ብዙ ጊዜ ዜጎች ህንፃ ተሰራልን ብለው መንግስትን ለማመስገን ሰልፍ አይወጡም።  ነገር ግን የመንግስትን ድክመቶች እያወጡ መናገር የበለጠ ህብረተሰቡ ለህይወቱ ይጠቅመዋል። መንግስት ድክመቶቹን  ቶሎ እንዲያስተካክል ከመሻት ፈጣን ለውጥን ከመፈለግ ነው። በመሆኑም የፓለቲካ ፓርቲ ይቅርታ ቢጠይቅ ክብር ይጨምራል።
  1. የባህርይ ለውጥ ለማምጣት መውጣት
አልፎ አልፎ ስለ ገዢው ፓርቲ አመራሮች አስባለሁ። የውነት ለመናገር ባለ ሥልጣን ለምን ያጠፋል አልልም። እንደማንኛውም ዜጋ ማለቴ ነው። የሚገርመኝ ግን የማይማር መሪ ነው። በገዢው ፓርቲ አካባቢ ግምገማ የሚባለው አውጫጭኝ አይነት ነገር የተለመደ ነው። የግል ህይወት ሳይቀር በከፍተኛ ሁኔታ እየተዘረዘረ እርስ በርስ ይገማገማሉ። ግምገማችን ሳሙናችን ሲሉም እሰማለሁ። የሚገርመኝ ታዲያ የአንዳንድ መሪዎችን ሁኔታ አይና አሁን ይሄ መሪ ሰላሳ ኣመት ተገምግሟል? አሁን ይሄ ሰው አርባ ኣመት ተገምግሟል?  እላለሁ።  በዚያ ድርጅት ውስጥ አርባ ዓመት ቆይተው እንዴት ወደ ኋላ ይሄዳሉ እንደምን እውቀትና እንደምን ትህትና አልጨመሩም ያሰኛል። ምን አልባት ይህ ግምገማ ለድርጅቱ ጠቅሞ ይሆናል ። ፈሪ የሆኑ አባላትን ለማፍራት ጠያቂ ካድሬዎችን ለመምታት ጠቅሞ ድርጅቱን ደግፎ ይሆናል እንጀ ገዢው ፓርቲ ከዚህ የግምገማ ባህል ጥሩ ያገር መሪ ሲያፈራልን አናይም። እንዴውም ይህ ግምገማ አንዳንዱን ጥሩ አድርጎ አደንዝዞታል አንዳንዱን ደግሞ የጦፈ ጮሌ አድርጎብናል። የግምገማ መስመሮችን እያጠና ነገር ግን ረቂቅ ሙሰኛ ራእይ የለሽ ብዙ ሰው አፍርተናልና። ገዢው ፓርቲ ይህን ማጥናት ይገባው ነበር። በጥልቅ መታደስ የተባለው ይህን ዘዴ ተጠቅሞ ከሆነ ያ ተሃድሶ የሚባል ነገር ገዢው ፓርቲ መጀመሪያ ከሰጠው የተሃድሶ ትርጉም የዘለለ አይሆንም። ከድግስ ያለፈ ትርጉም አይኖረውም ። ገዢው ፓርቲ ያለበት አንድ ትልቅ ችግር በግምገማ ወቅት ብዙ ጊዜ የሚያየው ተዋንያኑን ነው። የህዝብ ጥያቄ ደግሞ የሲስተም የፓሲሲ ጥያቄ ነው። ከገዢው ፓርቲ ግምገማ የምናተርፈው ፓርቲው አይዲዮሎጂውንና ፓሊዎችን በጥልቀት ገምግሞ ሲወጣ ነው እንጂ የካቢኔ ሹም ሽር አይጠቅምም። የባህሪ ለውጥ ሲባል አንዳንድ መዘንጋት የሌለባቸው ጉዳዮች አሉ። ከፍ ሲል እንዳልነው “የኢህአዴግ” ግምገማ ከባህርይ ለውጥ አንፃር ምን ላይ ከረምክ? ሲባል በሙስና ዙሪያ የአእምሮ መታደስ ለማምጣት ህዝባዊ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ሥሰራ ነበር ቢለን ቀልድ ነው የሚሆነው። እኛ የባህርይ ለውጥ የምንለው አብሮ ለመስራት፣ ለመቻቻል ፓለቲካ፣ ለእርቅ፣ ለአቅም ግንባታ፣ ለአመራር ብቃት፣ ለአርበኝነት ስሜት መዳበር እንጂ ለሙስና የምን የህዝባዊ ግንዛቤ ስራ ነው ደሞ። ስርቆት ወንጀል እንደሆነ ግንዛቤው አለ።  ይህ ነገር የሚጠፋው በጠንካራ ህጎች፣ በዘዴ እንዲሁም በተሻለ ሲስተም ነው።  ሙሰኛ በሆነ ሲስተም ውስጥ ያሉ አባላትን እንዳትሰርቁ በማለት  አይቆምም። ሙስናን ለመምታት ሲስተሙ መለወጥ፣ የፓለቲካውና ሙሰኛ የሆነው የኢኮኖሚ ሥርዓት መለወጥ አለበት። ችግሩ  መንግስት ሙስናን ከላይ ልምታ ቢል ሥርዓቱ ድርምስ ይላል። የስርዓቱ ተራዳ ሙስና ስለሆነ። በመሆኑም ጥልቅ ተሃድሶ በመንግስት አካባቢ ትርጉሙ ከባድ ነው። የስርዓት ለውጥ ነው ጥልቅ ተሃድሶ ማለት።

ሩስያ ከ2015 በኋላ ለተወለዱ ሁሉ ሲጋራ መሸጥ ልትከለክል ነው


 

አለማችን በሲጋራ ሳቢያ በአመት 1 ትሪሊዮን ዶላር ታጣለች
– በ2030 በየአመቱ የሚሞቱ አጫሾች ቁጥር 8 ሚሊዮን ይደርሳል
የሩስያ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እ.ኤ.አ ከ2015 በኋላ ለተወለዱ ሁሉም የአገሪቱ ዜጎች ሲጋራ እንዳይሸጥ የሚከለክል እጅግ ጥብቅ
ህግ በማውጣት ተግባራዊ ለማድረግ ማቀዱን የእንግሊዙ ዘ ታይምስ ዘገበ፡፡ ቀጣዩን የሩስያ ትውልድን ከሲጋራ ነጻ እንደሚያደርግ ቢታሰብም የአፈጻጸሙ ጉዳይ አጠያያቂ ነው የተባለው የሚኒስቴሩ ዕቅድ፣ እንደታሰበው ተግባራዊ የሚደረግ ከሆነ፣ ሩስያ ከአለማችን አገራት እጅግ ጥብቅ የጸረ-ትምባሆ ህግ ያወጣች የመጀመሪያ አገር ትሆናለች ያለው ዘገባው፤ አገሪቱ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በትምባሆ ዙሪያ ጉልህ እርምጃዎችን መውሰድ መጀመሯን ጠቁሟል፡፡ ዕቅዱ ጤናማ ዜጋ ለመፍጠር ቢያስችልም፣ በሌላ በኩል ግን ከጥራት በታች የሆነ የትምባሆ ምርት በጥቁር ገበያ ህገወጥ መንገድ እየተሸጠ የዜጎችን ጤና የከፋ አደጋ ላይ እንዲጥል ምክንያት ሊሆን ይችላል የሚል ስጋት መፍጠሩን እንዲሁም ለሁሉም ዜጎች ሲጋራ አትሽጡ የሚለው ህግ በተጠቃሚዎችና በትምባሆ አምራች ኩባንያዎች ዘንድ ቁጣን ሊቀሰቅስ እንደሚችል መነገሩንም ዘገባው
አመልክቷል፡፡ የሩስያ መንግስት ባለፉት አመታት የሲጋራ አጫሾችን ቁጥር ለመቀነስ በሚል በወሰዳቸው የተለያዩ እርምጃዎች ከፍተኛ ውጤት
ማስመዝገቡን ያስታወሰው ዘገባው፣ ባለፈው የፈረንጆች አመት 2016 ብቻ የአገሪቱ አጫሾች ቁጥር በ10 በመቶ መቀነሱንም አክሎ ገልጧል፡፡
በተያያዘ ዜናም፣ የአለማችን ኢኮኖሚ በሲጋራ ሳቢያ በየአመቱ 1 ትሪሊዮን ዶላር ገደማ ኪሳራ እንደሚገጥመውና በሲጋራ ማጨስ
ሳቢያ በየአመቱ ለህልፈተ ህይወት የሚዳረጉ ሰዎች ቁጥር በመጪዎቹ 13 አመታት፣ 8 ሚሊዮን ያህል ይደርሳል ተብሎ እንደሚገመት
የአለም የጤና ድርጅት ሰሞኑን ባወጣው መረጃ ማስታወቁን ዘገባው አስረድቷል፡፡ ድርጅቱ ባለፈው ማክሰኞ ያወጣውን የጥናት ውጤት
ጠቅሶ ሮይተርስ እንደዘገበው፣ እስካሁን ባለው መረጃ በአለማቀፍ ደረጃ በሲጋራ ሳቢያ 6 ሚሊዮን ያህል ሰዎች በየአመቱ የሚሞቱ
ሲሆን፣ ይህ ቁጥር እስከ 2030 ድረስ 8 ሚሊዮን ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በሲጋራ ለህልፈተ ህይወት ከሚዳረጉት
ሰዎች መካከል ከ80 በመቶ በላይ የሚሆኑት በመካከለኛና በዝቅተኛ ገቢ አገራት የሚገኙ እንደሆኑም ዘገባው ጠቁሟል፡፡

ተሐድሶን የምናይበት መነጽር ላይ እንስማማ!! – በያሬድ አውግቸው

   


የተለያዩ ፍላጎቶችና አመለካከቶችን ለማስተናገድ  የሚፈቅዱ ህጎችና አሰራሮችን መቅረጽ  ሳይቻል በመቅረቱ በንጉሱም ሆነ በደርግ አገዛዝ ብዙ ተቃውሞዎች ተቀስቅሰው እንደነበር ይታወሳል። ተቃውሞዎቹን ተከትሎ የተነሱ ግጭቶችም መጠነ ሰፊ የህይወት መስዋእትነት አስከፍለውናል፡፡ የመስዋዕትነቶቹ ዋነኛ ምክንያት የህዝቦች ድምጽ የሚደመጥበት  የፖለቲካ ስርዓትን በሚፈልጉ ወገኖችና ስልጣንን በብቸኝነት ለመቆጣጠር ልዩ መብት አለን በሚሉት መካከል ስምምነት ላይ መድረስ ባለመቻሉ ነበር፡፡
ከእነዚያ ግጭቶችና ቀውሶች በኋላም ግን፣ ከማዋከብ ነጻ የሆነ የመድብለ ፓርቲ ስርዓትንና  ሰላማዊ  የስልጣን ሽግግርን ብቸኛ ምርጫችን ለማድረግ ከስምምነት ላይ አለመድረሳችን ግራ አጋቢም አስገራሚም ነው። በተመሳሳይ መልኩ፤ ከማናቸውም  ሃገራት በተሻለ ለመደማመጥ የሚያስችሉን እንደ የገዳ ስርዓት አይነት ነባር ሃገራዊ  የዲሞክራሲያዊ ባህሎች ባለቤት ብንሆንም ቅሉ አልተጠቀምንበትም፡፡
በቅርቡ ገዥው ፓርቲ ምክንያታቸው፣ “የውስጤ ችግሮች ናቸው” ያላቸው ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፎች፣ በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች  መከሰታቸው ይታወቃል። ገዥው ፓርቲ የችግሮቹ ዋና መነሻ፣ ስልጣንን ለግል ጥቅም ማዋል፣ የመልካም አስተዳደር እጦትና  ሙስና መሆናቸውን ገልጾ፣ ህዝቡ በኢህአዴግ  መሰረታዊ ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎችና እምነቶች ላይ ምንም አይነት ጥያቄዎች የሉትም የሚለውን ለረጅም ጊዜ የቆየ እምነቱን አሁንም ደግሞታል። እንደ ተቃዋሚ ሃይሎች (በዚህ ጽሁፍ አማራጭ የፖለቲካ ሀይሎች እየተባሉ የሚገለጹት) እምነት ግን የሃገሪቱ የፍትህና የምርጫ ስርዓቶች ነጻ ያለመሆን፣ በሁለቱ ክልሎች ለተከሰቱ ህዝባዊ ተቃውሞዎች  በዋነኛ ምክንያትነት ይቀርባሉ። በእኔ ምልከታ ገዥው ፓርቲና አማራጭ ሃይሎች  ለችግሩ መነሻነት ያቀረቧቸው ምክንያቶች፤ “እሳትን የማጥፋት” እና “የስትራቴጂክ” የመፍትሄ አማራጮችን ያህል ልዩነት ያላቸው ሆነው ነው ያገኘኋቸው፡፡
እንደ አማራጭ ፓርቲዎች እምነት፤ ከመሰረታዊ ችግሮቹ ውስጥ ሙስናና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ብቻ ነጥሎ ማውጣት፣ ከችግሮቹ ይልቅ የበሽታው ምልክቶችን ለማከም እንደ መሞከር ይሆናል። ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ የተለያዩ ህጎችና አደረጃጀቶች መሻሻል አስፈላጊነቱ ባይካድም፣ በብዙ ምክንያቶች  ሙስናና ብልሹ አሰራሮች ፍትህን ለመድፈቃቸው ዋነኛው ምክንያት፣ በገዥው ፓርቲ በኩል የተጠያቂነትና የቁርጠኝነት አለመኖር፤ የፍትህና የጸጥታ ሃይሎች ፍትህን ሳይሆን አስፈጻሚውን አካል ወክለው መስራታቸው፤ በአጠቃላይ ህገመንግስቱና እሱን ተከትለው የወጡ ማስፈጸሚያ ህጎች ላይ ክፍተቶች መኖርና ወደ ስራ መግባት አለመቻላቸው ይጠቀሳሉ። በቀጣይነት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተከትሎ ወይም ጎን ለጎን  በመንግስትና በአማራጭ የፖለቲካ ሀይሎች በኩል መወሰድ የሚገባቸው  እርምጃዎችን  አስመልክቶ  የተወሰኑ አስተያየቶችን  አቀርባለሁ።
ከላይ እንደገለጽነው ስልጣንን ያለ አግባብ መጠቀምና ሙስና፣ የጥያቄዎቹ መነሻ ናቸው የሚል  ድምዳሜ  በመንግስት በኩል መቅረቡ ይታወቃል። ከበፊቱ የተሻለ የትምህርት ዝግጅት ያላቸው ግለሰቦች  በፌደራልና በክልል ካቢኔዎች የተካተቱ ሲሆን በሙስና የተዘፈቁ የመንግስት ሃላፊዎች  ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን የሚገልጹ ዜናዎች ሰምተናል፡፡ በመሰረታዊነት በገዥው ፓርቲ የተገለጹትም  ሆነ በሌሎች ወገኖች የሚነሱ ችግሮችን በዘላቂነት  ለመፍታት ከግለሰባዊነት  የጸዳ /Objective/ ተጠያቂነትን ማጠናከር፤ የመድበለ ፓርቲ ስርዓቱን ለመደገፍ የቆረጡ ፖሊሲዎችና ህጎች መኖር (ለምሳሌ ለአማራጭ የፖለቲካ ሃይሎች የሚደረጉ  ድጋፎችን ማሻሻል ዙሪያ)፤ ከተጽዕኖ የጸዱ የፍትህና የጸጥታ ተቋማት መኖር፤ እንዲሁም ፖሊሲዎቹንና ህጎቹን ለመደገፍ የሚደረጉ የአደረጃጀት ለውጦች አስፈላጊነት  እሙን ነው። የሌሎች በዲሞክራሲያዊ ስርዓት ልምድ ያላቸው ሃገሮች ተሞክሮም ይህንኑ ያሳያል።
ከዚህ ቀደም የነበሩ በአማራጭ ሃይሎችና በገዥው ፓርቲ በኩል የሚታዩ የቃላትና የጽሁፍ ምልልሶች፣ ገዥው ፓርቲ አማራጭ ሀይሎቹን  ለማንኳሰስ፤ አማራጮቹም የሚደርስባቸውን ተጽዕኖ ለማሳየት  ከመሞከር የዘለለ አልነበረም። በመሰረታዊነት  ችግሮቹን ለመቅረፍ ከተፈለገ መወሰድ ያለበት መፍትሄ፣ ሁሉም አካላትን ያካተተ፣ ችግሩን ለአንዴና ለመጨረሻ  ግዜ  መፍታት የሚያስችሉ ከላይ የተገለጹ ህጎችና አደረጃጀቶች ማዘጋጀት ይሆናል።
የህግ ማእቀፎቹና እነሱን ለማስፈጸም የሚገነቡ አደረጃጀቶች፣ ከገዥው ፓርቲ ተጽዕኖ ነጻ የሚያደርጋቸው ስርዓትም ሊዘጋጅላቸው ይገባል። ለምሳሌነት ሃላፊነት የሚሰማቸው ጠንካራ አማራጭ የፖለቲካ ፓርቲዎችን በጠንካራ የህግ ከለላና ጥበቃ መውለድ የሚያስችል የተለጠጠ ህግ አንዱ ነው። ከዚህ በፊትም አንዳንድ ወሳኝ የህዝብ ወኪሎችን ከጥቃት ለመከላከል ሲባል ልዩ ከለላ  የሚሰጡ ህጎችን ስንጠቀም ቆይተናል። ለምሳሌነት ከሃላፊነታቸው እስኪነሱ ድረስ የፓርላማ አባላት ያለመከሰስ መብት እንዲኖራቸው የሚደነግገው ህግ ይታወሳል።  በተመሳሳይ  አማራጭ ሀይሎችን  ከጥቃት ለመጠበቅ ሲባልም፣ ለአማራጭ ሀይሎች የሚደረጉ የገንዘብ ድጋፎች  በህግ ጥበቃ በሚደረግላቸው፣ ሆደ ሰፊ ተቋማት እንዲተዳደሩ ማድረግ ይገባል (ለምሳሌ የፖለቲካ ፓርቲዎች ካውንስል ሊቋቋምና ሊያስተዳድራቸው ይችላል)። ፓርቲዎቹ ስራ ላይ እስካሉ ድረስ በምንም መስፈርት የማይነጠቁት፣ ኪራይ የማይከፈልባቸው ወይም አነስተኛ ኪራይ የሚጠየቅባቸው፣  ለስራና ለስብሰባ  ምቹ የመንግስት ቤቶችን ለአማራጭ ሀይሎች ማቅረብም ሌላው አማራጭ ሊሆን ይችላል። ገዥው ፓርቲ የያዘውን የመንግስት ስልጣን ተጠቅሞ፣ በሃገር ሃብት ድርጅቱን ያጠናከረበት ተሞክሮ እዚህ ላይ ማስታወስ ግድ ይላል።  ለፓርቲዎች የስብሰባና ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነጻነት የሚያጎናጽፉ ህጎችም፣  የገዥው ፓርቲ  አባላት በህግ ማስከበር ሰበብ ጫናዎች እንዳያደርሱ ከለላ በሚሰጥ መልኩ መዘጋጀት  ይገባቸዋል።
የምርጫ ህጉ፤ የምርጫ ቦርድ አደረጃጀት፤ የቦርዱ አባላት ምርጫ እንዲሁም  የምርጫ ቦርድን ጽ/ቤት ሃላፊዎችና ሰራተኞች አመላመል የተመለከቱ ህግና ደንቦች፣ አማራጭ ፓርቲዎችን ባሳተፈ መልኩ መዘጋጀት ይኖርባቸዋል፡፡ የፖሊስና የሃገር መከላከያ ሰራዊት አደረጃጀቶችን በተመለከተ በሃገሪቱ የፖለቲካ መድረክ ጠንካራ አማራጭ ሃይሎች ነጥረው እስኪወጡና ገዥውን ፓርቲ በማናቸውም መልኩ መፎካከር እስኪችሉ ድረስ ለተወሰኑ ዓመታት የሰራዊቶቹ የበላይ አመራሮች ሹመትና ሽረት  ቢያንስ አንድ ወንበር በፓርላማ ያላቸው አማራጭ ሃይሎችን ስምምነት የግድ እንዲያገኝ ገዥው ፓርቲ በህግ ማዕቀፍ ቁርጠኝነቱን ማሳየት ይኖርበታል።  ሌሎች የጸጥታና የሰብአዊ መብት  ተቋማትም በተመሳሳይ ስምምነት ሊኖርባቸው ይገባል።  በሌላ በኩል የሲቪክ ማህበራት፣ ህዝቦች በተደራጀ መንገድ የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊና የፖለቲካ ጉዳዮቻቸውን የሚያንሸራሽሩባቸው ተቋማት በመሆናቸው ገዥው ፓርቲ  ለጥንካሬያቸው  በህግ ማዕቀፍ መስራት አለበት። የገንዘብ ምንጫቸውን በተመለከተ ያለበትን ከልክ ያለፈ ፍርሃትም ማስወገድ ይኖርበታል።
ሌላው የፖለቲካ ፓርቲዎች ጊዜያዊ ተቀባይነት ለማግኘት በሚያስችል መልኩ ፕሮግራማቸውን ከማዘጋጀት ይልቅ  ተአማኒነትንና  ዘላቂ ልማትን በሚያረጋግጥ መልኩ ማዘጋጀት  ይጠበቅባቸዋል። ለዚህም የጥናትና ምርምር ክፍል በፓርቲያቸው መዋቅር ስር ማቋቋምና በቅጡ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ወሳኝ ሚና ይኖረዋል። ለምሳሌነት በገዥው ፓርቲ በኩል በጥንት ዘመን ስነ-ልቦናና ግንዛቤ የተተገበሩ ግጭቶችን ዛሬ እንደተደረጉ አጉልቶ  ማቅረብ ይስተዋላል። በተመሳሳይ  በገዥው ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ እንደ አቅጣጫ ተቀምጠው በመንግስታዊ ተቋሞቻችን ውስጥ እቅድ እንዲዘጋጅላቸው መመሪያ የሚሰጥባቸው ከጥናት ያልተናነሱ አንዳንድ ወሳኝ ስራዎችን አይተናል፤ ሰምተናልም።
ተጨባጭ መነሻ ስለሌላቸው ስራዎቹ   በአፈጻጸም ወቅት ተደጋጋሚ ስር ነቀል  ክለሳ ወይም ለውጥ ሲደረግባቸው ይታያል። በአንዳንድ ተቋማት በፍጥነት የሚለዋወጡ ባለስልጣናት ለስራው ባይተዋር መሆናቸውን ተከትሎ የሚመጡ የአመራር ክፍተቶችም  ለችግሩ የበኩላቸውን ሚና ሲጫወቱ ቆይተዋል። ሌላው ትልቅ ድርሻ መያዝ የሚገባው እርምጃ  የፖለቲካ ባህላችንን መገምመገምና ማስተካከያ ማድረግ ነው፡፡ የፖለቲካ ባህላችንን በጥልቀት ስንገመግም፣ እኛ እና እነሱ በሚለው፣ ጽንፍ በረገጠ ማእቀፍ ወይም መነጽር  ስር ካልሆነ  በቀር ፖለቲካን ማራመድ የማንችል ይመስላል።  “እኔን   ያልደገፈ ሁሉ የሃገር ጠላት ነው” ዓይነት ጽንፍ የረገጠ ንቀት፣ ለትብብርና ለውይይት ቦታ የማይሰጥ በመሆኑ፣  ለፖለቲካው ስርዓት እድገት ማነቆ መሆኑ አያጠያይቅም። ከዚህ አስተሳሰብ ለመውጣት ገዥው ፓርቲም ሆነ ሌሎች አካላት ቁርጠኝነት ማሳየት ይጠበቅባቸዋል።  ምክንያቱም ዘላቂ ሰላምና የዜጎች ነጻነት እውን የሚሆኑት ሁሉም የሃገሪቱ ዜጎች የሚፈልጉትን ተወካይ፣ ወደ  ውሳኔ ሰጭ ወንበሮች ማውጣት ሲችሉ ብቻ ነው። የምድራችን  የዲሞክራሲ ስርዓቶች ታሪክም ያለአንዳች ልዩነት ይህንኑ ያጸኸያሉ፡፡