ህዝባዊ ተቃውሞው ወደ በደቡብ ክልል ተዘምቷል። በዲላ ከተማ ከፍተኛ ተቃውሞ እየተካሄደ ነው። ቤቶች ተቃጥለዋል። ወደ ወንዶ ገነት አካባቢ ከፍተኛ ውጥረት አለ። ፍተሻው ተጠናክሯል።
በዲላ በመካሄድ ላይ ባለው ተቃውሞ ገዢው ፓርቲ ሆን ብሎ ወደ ብሄር ግጭት እንዲለወጥ እየሰራ መሆኑን መረጃዎች ደርሰውናል። አንድን መሬት ለሁለት የተለያዩ ብሄረሰብ ተወላጆች በመስጠት ሆን ተብሎ የብሄር ግጭት እንዲፈጠር ለማድረግ ሞክሯል በማለት ነዋሪዎች ወቀሳ አቅርበዋል። በተቃውሞው የመንግስት መስሪያ ቤቶችና የባለስልጣናት ቤቶች ተቃጥለዋል። በከተማው ከፍተኛ ተኩስ ይሰማል። ነዋሪዎች፣ ተቃውሞው በአገዛዙ ላይ ብቻ እንዲያነጣጥር፣ ወጣቶችም ገዢው ፓርቲ በሰራው ወጥመድ ውስጥ እንዳይገቡ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እያሳሰቡ ነው።
No comments:
Post a Comment