Wednesday, October 12, 2016

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የማን ናት?


የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የማን ናት? [ ክፍል ፪] 
ከአራት ቀን በፊት ማለትም እ.ኤ.አ. ጥቅምት 8 ቀን 2016 አ.ም. «የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የማን ናት?» በሚል ርዕስ ሙሰኛው «ፓትሪያርክ» «አቡነ» ማቲያስ ታሪካዊቷን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በትግራይ ተወላጆች ብቻ እንዴት እንደሞሏት የሚያሳይና በመረጃ የዋጀ የመጀመሪያ ክፍል ጥንቅር አቅርቤ ነበር። እነሆ ክፍል ሁለት ይቀጥላል።
በአዲስ አበባ ውስጥ ያሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አብያተ ክርስትያናትና አድባራት በሶስት ደረጃዎች ይከፈላሉ። አንደኛ ደረጃ የሚባሉት አብያተ ክርስትያናት እጅግ ብዙ ገቢ የሚያስገኙና ገቢ ሊያስገኙ የሚችሉ ሱቆች፣ ትምህርት ቤት፣ የመቃብር ቦታ ወዘተ ያለባቸው አብያተ ክርስትያናት ናቸው። እነዚህም አብያተ ክርስትያናትና አድባራት ብዛታቸው ሀያ ነው። አራዳ ጊዮርጊስ፣ ቦሌ መድኃኔዓለም፣ ኡራኤል፣ ልደታ ለማርያም፣ ቅድስት ሥላሴ፣ አማኑኤል፣ አዲሱ ሚካኤል፣ እንጦጦ ኪዳነ ምህረት፣ ቅድስት ማርያም፣ ወዘተ አንደኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ አብያተ ክርስትያናት ናቸው። በወያኔ ቤተ ክህነት ቋንቋ አንድ ሰው «ተሾመ» የሚባለው በነዚህ አድባራት ውስጥ ሲሾም ነው።
እነዚህ አንደኛ ደረጃ በመባል የወያኔ ቤተ ክህነት የመደባቸው አድባራት ውስጥ ጸሐፊና አስተዳዳሪው ሆነው በአባ ማቲያስ የሚሾሙት ከዘጠ አምስት በመቶ በላይ የትግራይ ሰዎች ናቸው። እነዚህ አንደኛ ደረጃ በመባል በሚታወቁት አብያተ ክርስትያናት በአባ ማቲያስ የሚሾሙት የትግራይ ሰዎች ሁሉም የድርጅት አባላት ናቸው። ይህ ማለት እነዚህ ሰዎች ሲሾሙ የመንግስት ይሁንታ አለበት ማለት ነው። እነዚህ በትግሬነታቸው ተደራጅተው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን የወረሷት የትግራይ ሰዎች የቤተ ክርስቲያን ዘረፋ እጅግ የሚዘገንን ነው። እነዚህ ሰዎች ቤተ ክርስቲያኗን የሚዘርፏት በሚሊዮን በሚቆጠር ገንዘብ ነው። ዘራፊዎቹ የትግራይ ሹመኞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን መብደር በወያኔ ፈቃድ የተቀመጡ ስለሆኑ ስለዝርፊያቸው አይከሰሱም። ቢከሰሱም ቅጣቱ በትንሹ ይዘርፉበት ከነበረው የበለጠ ወደሚዘረፍበት ቦታ መዘዋወር ነው።
የወያኔ የቤ ተክርስቲያን አስተዳደር ሁለተኛ ደረጃ አድባራት ብሎ የሰየማቸው መለስተኛ ገቢ የሚገኝባቸውን ቤተ ክርስቲያንን ሲሆን እነዚህም ቦታ አስተዳዳሪና ጸሓፊ የሚመደቡት ከዘጠና በመቶ በላይ ከትግራይ ሰዎች ነው። ቅዱስ ማርቆስ፣ ቁስቄም፣ ገነተ ኢየሱስ፣ ቂርቆስ፣ ወዘተ በዚህ ደረጃ ከሚካተቱት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አብያተ ክርስትያናትና አድባራት መካከል ናቸው።
በሶስተኛ ደረጃነት የተቀመጡት ደግሞ የአዲስ አበባ አድባራት ከተማው ራቅ ያሉና ራሳቸውን ለመቻል የሚቸገሩ አዳዲስና ነባር አብያተ ክርስትያናት ናቸው። በእነዚህ አድባራት ውስጥ አስተዳዳሪ ሆነው የሚሾሙት በአብዛኛው የሌሎች ብሔር አባላት ናቸው። ሆኖም ግን የነዚህ አድራባራትም ቢሆን የጸሀፊው ስራ በትግራይ ሰዎች የተያዘ ነው።
ዛሬ የማቀርበው የዝርፊያ ዶሴ በማህበረ ለስብሐት ልደታ ማሪያም ቤተ ክርስቲያን አባ ማቲያስ የሾሟቸው ሁሉም የትግራይ ሰዎች የሆኑ ዘራፊዎች ቤተ ክርስቲያኗን የገፈፏትን በርካታ ሚሊዮን ብር የሚያሳይና በአባ ማቲያስ ቁጥጥር ስር ያለው ቤተ ክርስቲያን ካሳተመው ዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ ላይ የተገኘ የውስጥ ማስረጃ ነው።
ከታች ስማቸው የተጠቀሰው ስድስቱ [ አንዱ ተባባሪ ነው የዘረፈው መጠን አልተጠቀሰም] የአባ ማቲያስ ሌቦች ከአንድ ቤተ ክርስቲያ ብቻ በአንድ ወቅት በርካታ ሚሊዮን ብሮችን ዘርፈዋል። ከዚህ ተነስተን «በአቡነ» ማቲያስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከአንድ ቤተ ክርስቲያን ይህንን ያህል ሚሊዮን ብር የሚሆን የቤተክርስቲያን ሀብት ከዘረፋ በአጠቃላይ ቤተክርስቲያኗን እንዴት ግጠው ጨርሰው በአጽሟ እንዳቆሟት መገመት አይከብድም።
የሆነው ሆኖ በትግሬነታቸው ተቧድነው ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንንራቁቷን ያስቀሯት የአባ ማቲያስ ሹሞች የሆኑት የትግራይ ሌቦች ከአንድ ቤተ ክርስቲያን ዘረፉት ተብሎ ክስ የቀረበባቸው ሰዎች ስምና ዝርዝር እነሆ፤
1. ወ/ሮ አብረኸት ተክሉ የደብሩ ገንዘብ ያዥ 897,365.03 ብር ያጎደሉ እና 2 ዓመት ብቻ የተፈረደባቸው
2. ዲ/ተስፋዬ በቀለ 4.6 ሚሊዮን የሙዳዩ መምፅዋት ብር ያጎደሉና 1 ዓመት ከ8 ወር ብቻ የተፈረደባቸው
3. መ/ሠርዓተ ኃ/ጊዮርጊስ ዕዝራ የቀድሞ ፀሀፊ 393, 7747.70 ብር ያጎደሉና 5000 ብር ብቻ የተቀጡ
4. አቶ ዩሐንስ በርሄ የቀድሞ ተቆጣጣሪ 1.2 ሚሊየን ብር ይዘዉ የተሰወሩና 5000 ብር እንዲቀጡ የተላለፈባቸው
5. ሊቀ ስዩም ኃ/ማርያም አብርሃ በተ.ቁ 3 ላይ ከነበሩት ፀሀፊ በፊት የነበሩ 2.9 ሚሊየን ብር ያጎደሉና 5000 ብር ብቻ እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ የወሰነላቸዉ ሹሙኞች ናቸው ።
ይህንን ከአንድ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ተዘረፈ ተብሎ ክስ የተመሰረተበት የቤተ ክርስቲያን ሀብት ዘራፊዎችን ማንነትና የዝርፊያውን መጠን የሚያሳየው ዶሴ እነሆ!
. . . ይቀጥላል!
Image may contain: one or more people and text

No comments:

Post a Comment