ለስር ነቀል ለውጥ በሃገር ውስጥም በውጪም ተጠናክሮ ትግሉ ቀጥሏል።
– በኣማራ ክልል እና በኦሮሚያ ክልል ሕዝቡን የማስተባበር ሂደቶች በተሳካ መልኩ የቀጠለ ሲሆን በደቡብ ክልል እና በኣዲስ ኣበባ ጥሩ የሆኑ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ ታውቋል፤ ሕዝቡ በራሱ ኣነሳሽነት ከኣብራኩ በወጡ ሃይሎች ለውጥ መፈለጉን በመተባበር እየገለጸ መቀጠሉን መረጃዎች ያሳያሉ።ኢትዮጵያ ስር ነቀል ለውጥ ያስፈልጋታል ሕዝቦች በእኩልነት በሃገራቸው ጠቃሚና ተጠቃሚ የሚሆኑበት መስመር መዘርጋት ያስፈልጋል የሚሉ ብዙሃን ሕዝቦች ኣደባባይ በመውጣት በኣራቱም የሃገሪቱ ማእዘናት ከመንግስት ጋር ከመጋፈጥ ኣልፈው በቤት ውስጥ ተቃውሞ በማሰማት ላይ ይገኛሉ።
ይህ ማለት ሕዝብ ለውጥ ይፈልጋል ሕዝብ ከስደት ይልቅ በሃገሩ ሰርቶና ተከብሮ መኖር ይፈልጋል የመንግስትን ኣመራር የያዘው ኣገዛዝ ኢትዮጵያውያንን የመኖር ሕለናቸውን ስለገፈፈ በየሰው ሃገር ለብሄራዊ ውርደት ተዳርገዋል። በዘር ላይ የተመረኮዘ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ክፍፍል ኣንድን ዘር የበላይ እንዲሆን በማድረግ ሌሎችን የበይ ተመልካች ኣድርጎ ሃገርን ለድህነት ሕዝብን ለደሃ ደሃ ሰንሰለት ኣቀባብሎ ሰጥቷል።
በእናት ሃገራችን ኢትዮጵያ ላይ ተንሰራፍቶ የሚገኘው የሕወሓት አምባገነን ቡድናዊ አገዛዝ በሕዝብ ላይ የሚፈጽመው የፖለቲካና የኢኮኖሚ በደል ገደቡት አልፎ ዜጎች በገዛ አገራቸው መኖር እንዳይችለ ሆነዋል፥ በሃገራችን ተከስትው ይሚገኙ የፖለቲካ ጫናዎች የኑሮ ውድነት የድርቅ የእስር የግድያ እና የተለያዩ ችግሮች አገዛዙ በሚፈጽመው በደል ላይ ተደራርበው ወገኖቻችንን እጅግ ለከፋ አደጋ አሳልፎ ሰጧቸዋል፤ይህ ከፍተኛ የሆነ ብሄራዊ ውርደት እየታየ ያለው አገዛዙ ለዜጎች ያለውን ንቀት እብሪት እና መንግስታዊ ሃሰተኝነት ከሽብርተኝነቱ ጋር ተቀላቅለው ሕዝቡን አንገፍግፈውታል፥፥የአገዛዙ ግፎች ተዘርዝረው የማያልቁ ሲሆን ለዚህ ደሞ መፍትሄው አገዛዙን አስወግዶ ስር ነቀል ለውጥ ማምጣት ብቻ ነው።
No comments:
Post a Comment