Saturday, April 30, 2016

የኢትዮጵያዊነት የደረጃ መዳቢ አድርጎ እራሱን ያስቀመጠው አደገኛ የአመለካከት ቡድን እስከአሁን በመወራጨት ላይ እንዳለ ነው። በአንድነት ሽፋን ዳግም ቅኝ ግዛት የለም

 


ሕዝቦችን ያማከለ አንድነት ለትግሉ ስኬት – ልዩነትን በማቻቻል በጋራ መታገል ችላ የማይባል ሃገራዊ አጀንዳ ነው። ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎EthiopianOppositionparties‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ‪#‎Unity‬
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ኢትዮጵያዊነት ችሮታ አሊያም ስጦታ ሲልም በደረጃ የሚሰጥ ዜግነት ሳይሆን የእያንዳንዱ ሕዝብ የማንነት መሰረት የተፈጥሮ ማሕተብ እና የውርስ አደራ የታላቅነት ተምሳሌት ነው ኢትዮጵያዊነት!!! በዚህ ሀገር ፖለቲካ ውስጥ የኢትዮጵያዊነት የደረጃ መዳቢ አድርጎ እራሱን ያስቀመጠው አደገኛ የአመለካከት ቡድን እስከአሁን በመወራጨት ላይ እንዳለ ነው። በአንድነት ሽፋን ዳግም ቅኝ ግዛት የለም::የህዝብን ትግል ለማስጠበቅ የሕዝብን ነጻነት ለማረጋገጥ ሕዝቦችን ያማከለ የጋራ አንድነታችንን ማጠናከር ግድ የሚልበት እና ሃገራዊ/ህዝባዊ ሃላፊነታችንን በመወጣት ወሳኝ ወቅት ላይ መሆናችንን አውቀን የትግል ቃልኪዳናችንን በማጥበቅ ህዝባዊ ድሎችን ማረጋገጥ ሃገራዊ ግዴታችን እንደሆነ ልንገነዘብ ይገባል::ባሳለፍነው የትግል አመታት ውስጥ የተቃዋሚዎች እርስ በእርስ መፈራረጅ መወነጃጀል መናናቅ ለስልጣን ጥመኝነት መሮጥ እንዲሁም ለስም እና ለዝና መትጋት ያለመደማመጥ እና ያለመከባበር ፖለቲካ ተቀራርቦ ያለመነጋገር እና ያለመመካከር ፖለቲካ ሃገራኢ ሆደሰፊነት እና መቻቻልን ያላዘለ ፖለቲካ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የተረፈው ነገር ቢኖር ከጭቆን ወደ ጭቆና ማቅ ውስጥ ከመዘፈቅ ውጪ ምንም የናፈቀውን የነጻነት አየር እንዲተነፍስ አላደረግነውም። የተቃዋሚ ሃይሎች ጥንካሬ እንዲጎለብት በየድርጅቱ ውስጥ ያሉትን እንከኖች በማጥራት በጋራ እና በተመቻቸ የሃሳብ መግባባት ተቻችሉ እና ተግባብቶ የትግል ስትራቴጂን ግብ ለማድረስ ለአንድ ወጥ ህዝባዊ እና ሃገራዊ አጀንዳ ተግቶ መስራት ይጠበቅብናል።
ወያኔ የተቃዋሚዎችን እና የለውጥ ሃይሎችን እርስ በእርስ መፈነካከት በማየት አርጩሜውን ተስፋ በሚጣልባቸው ግለሰቦች እና ፓርቲዎች ላይ እያወናጨፈ ባለበት እንዲሁም የውስጥ አሰራራቸውን በመሰለል በትግሉ ውስጥ ያላቸውን ሚና እንዲኮላሽ በመስራት የውስጥ ድክመቶቻቸውን በመጠቀም እርስ በርስ እንዲፋጁ እና ተቃዋሚዎች እንዲከስሙ ጥንካሪያቸውን እንዳያገኙ ሲሰራ ይህንን እንዴት አድርገን በማሻሻል የወያኔን ሴራ ማክሸፍ አለብን የሚል አመኔታ የሚያስገኝ ሕዝባዊ ስራዎችን በመስራት ጥንካሬን ማግነት እንዲሁም ሕዝባዊ ድጋፎችን ማግኘት ግድ የሚልበት ጊዜ ላይ መሆናቸውን ተቃዋሚዎች ሊያውቁት ይገባል::ተቃዋሚዎች ካለፈው ድክመቶቻችን ተምረን ከዘለፋ እና ከስድብ እንዲሁም ከመፈራረጅ የሴራ ፖለቲካ በመውጣት ጥንካሬዎቻችንን የምናሳይበት ለውጥ የምናመጣበት እንዲሆን በጋራ ጠንክረን መስራት አለብን። አንድነት ሃይል ነው የሚለው ብሂል ለሃገራዊ አጀንዳ መተግበር ትልቅ አስታውጾ አለው::ከኛ በላይ ላሳር ከኛ በላይ አዋቂ የለም የሚል አመለካከት ይዞ ከመክነፍ የህዝብን ጥያቄ መሰረት አድርጎ ተቀራርቦ በመነጋገር እና በመወያየት ሃገራጂ ማኒፌስቶ በማምጣት የጋራ ሃገራዊ አጀንዳ በመቅረጽ ለለውጥ መትጋት ግዴታ ነው::
የኢትዮጵያ ሕዝብ ለውጥ ይፈልጋል። ይህ ሳይታለም የተፈታ እና የሁሉም የነጻነት ፈላጊ ሃይሎች ጥያቄ ነው። በሃገር ውስጥ ያሉትን ፓርቲዎች መዋቅሮቻቸውን በማጠናከር የውስጥ ድክመቶቻቸውን በመቅረፍ እንዲጠነክሩ የማድረግ ግዴታ ከለውጥ ፈላጊ ሃይሎች ይጠበቃል። መመካከር መተራረም ግድ ይላል። በውጪው አለም የሚገኙ የነጻነት እና የለውጥ ሃይሎች እንዲጠናከሩ እና ከጥልፍልፎሽ ፖለቲካ ወተው ጠንካራ ሃይል እንዲሆኑ የዲያስፖራው ሃይል ከበፊቱ በበለጠ መልኩ ሊሰራ ግድ ይለዋል። የወያኔ የጎን ውጋት እና የራስ ምታት የሆነው ዲያስፖራው የጀመረውን የትግል ስልት እና ትጋት በማስፋት ሚዲያዎችን በማጠናከር እና የነጻ አውጪ ፓርቲዎችን በመርዳት በማግባባት ጠንካራ ሰንሰለት ከሃገር ቤት ጋር በመፍጠር ሕዝብን ከጨቋኞች ነጻ ማውጣት አለበት።ዲያስፖራው በየቀኑ ወያኔ የሚፈጥረውን ተራ የቤት ስራ እና የማደናገሪያ ማዘናጊያ አሉባልታ ፊት ሳይሰጠው በለውጡ ጉዳይ ላይ በማተኮር በሃገር ቤት ያለው ሃይል እንዲስማማ የፖለቲካ ጡዘቶች ክፍተት እንዳይኖር ተቀራርቦ እንዲሰራ ትልቁን ሚና መጫወት አለበት::
እውነትን እና ስልጡን ፖለቲካን ቢተናነቀንም እንደምንም ልንውጠው ግድ ይላል::ሁሉም ኢትዮጵያዊ እኩል ነው::እየሄድንበት ያለው መንገድ አስጊም አደገኛም ሲልም ሊወጡት የማይችሉ አዘቅት ነው::በፈረንጅ አገር ወያኔ በግልጽም ይሁን በተዘዋዋሪ የላካቸው ባለስኮላርሺፖች አዛኝ ቂቤ አንጓች የአንድነት ሃይል መስለው ሰርገው በመግባት እየሰሩ ያለው ስራ እጅግ ያሳዝናል::ከመወራጨት ውጪ ከነአጨብጫቢዎቻቸው በኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ እንደማያመጡና የለውጥ እንቅፋት እንደሆኑ ልንነግራቸው ይገባል::የሚዲያ ተቋማት እና የድህረገጽ ውጤቶች ሕዝብን በማስተማር ሕዝብን መብቱን እና ነጻነቱን አውቆ ለሌላው እንዲያስተምር በማድረግ ረገድ አስፈላጊውን ወቅታዊ መረጃ እና መነሳሳትን በማስረጽ ግዴታቸውን ሊወጡ ይገባል። ያለፉ እና የከሰሙ ወሬዎችን እና አሉባልታዎችን ከመርጨት የወያኔ የፈጠራ አደናባሪ እና አዘናጊ አጀንዳዎችን እኝኝ በማለት ከማውራት ብሄር ተኮር ክፋፋይ ሃሳቦችን ከማርከፍከፍ አዛኝ መሳይ መርዝ ሃሳቦችን ከመናገር ተቆጥበን ሕዝቡን ስለመብቱ እና ነጻነቱን በማስተማር ረገድ መትጋት ከተያዘ ለውጥ የማይመጣበት ምንም ምክንያት የለም። ትችትን እና ሂስን ላለመዋጥ እውነትን ላለመቀበል የሚደረጉ ሩጫዎች ታጥቦ ጭቃ እንጂ የትም እንደማያደርሱ እንዲሁም ፓርቲዎችን እና ሰዎችን መፈረጅ እና መወንጀል ሃሳቦችን ማጣጣል ምንም ለውጥ እንደማያመጣ ካለፈው ተምረናል ። ያሳልፍነው የትግል ሂደት ከጭብጨባ እና ስብሰባ ያለፈ ፋይዳ እንዳሌለው ተገንዝበን የወሬ እና ሆይሆይ ትግል ስለማያዋጣ ጥንካሬን እና ለውጥን የምናመጣበትን የትግል ስልት በመመካከር እና በመወያየት ሃሳብን በማቻቻል መረጃ በመለዋወጥ ሃገራዊ የጋራ አጀንዳ ሊኖረን ይገባል እላለሁ።ልዩነትን በማቻቻል በጋራ መታገል ችላ የማይባል ሃገራዊ አጀንዳ ነው። ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬
Minilik Salsawi's photo.

በጃዋር መሃመድ ሀሳቦች ላይ! – አስራት አብርሃም


የጃዋር ፖለቲካ ተራማጅ አይደለም የምልበት ዋና ምክንያት አሁንም ፖለቲካው ከሶስቱ ብሄሮች (አማራ፣ ኦሮሞና ትግራይ) ጠበኛ ልሂቃን እይታ ያልወጣ መሆኑ ነው። ለእኔ አሁን ባለችው ኢትዮጵያ ተራማጅ አስተሳሰብ የምለው የተለመደውን የብሄር ፖለቲካ ካርድ እንስቶ በተሻለ ሁኔታ መጫወት ሳይሆን በዜግነት መብት ላይ የሚያተኩር፤ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን የሚመች ስርዓት ለማምጣት የሚታገል፤ ፍቅርና ወንድማማችነትን ሃገራዊነትን የሚሰብክ፤ እኩልነትና ዴሞክራሲ ለማምጣት በእምነትና በመርህ የሚገዝ ሰው፤ ወይም ተቋም ነው ወይም አስተሳሰብ ነው።
በዚህ በእኩል በሶሻል ሚዲያው ተፅዕኖ ፈጣሪ ከሆኑ ኢትዮጵያዊያን ውስጥ የዜግነት ብሄርተኝነት የሚያቀነቅን፤ ቅንነትና የአቋም ያለመዋዠቅ ያለው ሰው “ከጎሣ ይልቅ ሰብአዊነትን እናስቀድም” የሚለው ኦባንግ ሜቶ (Obang Metho) እና ድርጅቱ “ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ” (Solidarity Movement for a New Ethiopia) ብቻ ይመስለኛል። አለበዚያ ስለፖለቲካዊ ለውጥ፣ ዴሞክራሲና እኩልነት አስባለሁ እያሉ፣ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ የደቡብ ኢትዮጵያ፣ የሶማሌ፣ የትግራይ፣ የአፋር፣ የጋምቤላ፣ የቤንሻንጉል ወዘተ ህዝብ ያገለለ ፖለቲካዊ ትብብር ውጤታማ ይሆናል ብሎ አያስብም። ይሄ አካሄድ ስርዓቱን በአቋራጭ ለመጣል ይጠቅም እንደሆነ እንጂ ሰላም፣ ፍትህ፣ ሃገራዊ አንድነት፣ ዴሞክራሲና እኩልነት ግን በዚህ መንገድ ፈፅሞ ሊገኝ አይችልም፤ በሀገሪቱ ያሉትን ዜጎች ያገለለ ከመሆኑ አንፃር ሃገራዊ አስተሳሰብም አይደለም። ከዚህ አንፃር የጃዋር ሀሳብ ተራማጅ ያለመሆኑ ብቻ ሳይሆን ጠቃሚም አይደለም።
ሁለተኛው የጃዋር መሀመድ ችግር ዘላቂ (consistency) የሆነ የፖለቲካ አቋም ወይም እምነት ያለመኖር ነው። በፖለቲካ ትግል ውስጥ የማትደራደርባቸውና በቀላሉ የማትለውጣቸው መሰረታዊ የሆኑ ፖለቲካዊ አቋሞች ወይም እምነቶች ወይም ራስህን የምትገልፅበት ማንነቶች ይኖራሉ። አንድ ሰው ወይም ፖለቲካዊ ድርጅት አቋሙ ለወዳጅም ለጠላትም ግልፅ ሆኖ ሲታይ ወይ ሲታወቅ ነው ለመደራደርም ሰጥቶ ለመቀበልም የተመቸ የሚሆነው። ማንነቱና ፖለቲካዊ አቋሙ የሚታወቅ ከሆነ ከእነዚህ መሰረታዊ አቋሞች ውጭ ባሉት ጉዳዮች ላይ ለመደራደር አስቸጋሪ አይሆንም። ስለዚህ በፖለቲካ ትግል ውስጥ መተጣጠፍና መገለባበጥ የሚቻለው መሰረታዊ ባልሆኑ ፖለቲካዊ አቋሞችና የትግል ታክቲኮች ላይ ብቻ ነው። ከዚህ ያለፈ መገለባበጥና መለዋወጥ መርህ አልባነት ከመሆኑ ውጪ ፖለቲካዊ ጥበብ አይመስለኝም። ምክንያቱም የራሱ የሆነ ፅኑ ፖለቲካዊ አቋም ከሌለው አካል ጋር ሌላው ለመደራደርና በሙሉ ልብ አብሮ ለመጓዝና ለመስራት ያስቸግሯል።
ለምሳሌ የአማራና የኦሮሞ ህዝብ በግጭትና በትብብር ለዘመናት አብሮ የኖረ ነው ያለው ከአሁን በፊት ይለው ከነበረው ጋር ፍፁም ተቃራኒ ነው። ከቀኝ ገዥና ተገዥ ትርክት ባንዴ ወደዚህ ጫፍ አትመጣም። አሁን መጨረሻ ላይ ይህን ሀቅ የተገጠለት ማድረግ የፈለገውን ማድረግ ስላልቻለ እንጂ ከልቡ ስለሚያምንበት ነው ለማለትም እቸገራለሁ። ይህ እውነት በኦሮሞውና በአማራው ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ልዩ ልዩ ህዝቦች ሁሉ ተመሳሳይ የግጭትና የትብብር ረጅም ታሪክ እንዳላቸው እርግጥ ነው። በትግራይና በአማራ፣ በኦሮሞውና በደቡቡ እንደዚህ ዓይነት ግንኝነቶች ነበሩ፤ አሁንም አሉ። ስለዚህ ይህን እውነት በተሸራረፈ መንገድ ሳይሆን እንዲህ በተሟላ ሁኔታ መገንዘብ ያስፈልግ ነበር፤ ነገር ግን ጃዋር ለጊዜው የአማራው ልሂቅ የታክቲክ ትብብር ስለሆነ የፈለገው የሁለቱን ህዝቦች ግንኙነት ብቻ ነጥሎ በማውጣት ሊጠቀምበት ፈልጓል ማለት ነው። እንደዚያም ሆነ በእነዚህ ሁለት ልሂቃን መካከል የሚኖርን ትብብር በምን ላይ የተመሰረተ እንደሆነ ያስቀመጠው ነገር የለም። “ፖለቲካ ማለት ማን ምን አገኘ?” የሚል ጥያቄ የያዘ በመሆኑ ሰጥቶ የመቀበል ጉዳይ ነው።
ጃዋር የኦሮሞ ፖለቲካ ወኪል አድርገን እናስበውና ለአማራ ልሂቃን የእንተባበር ጥያቄ ሲያቀርብ ከእርሱ በእኩል ምን ለመስጠት ነው የፈለገው? የሚለውን ስናይ ምንም ሆኖ ነው ያኘሁት። ህወሀትን በጋራ አስወግደን እኛ የኦሮምያን ለም መሬት ባለቤት እንሆናለን፤ እናንተ ደግሞ የመተማ፤ የጠገዴና የወልቃይት ለም መሬት ባለቤት ትሆናላችሁ ዓይነት ነገር እንጂ ኢትዮጵያ በጋራ እንጠቀማለን፣ አብረን በሰላም እንዳአንድ ሃገር እንኖራለን፤ የኢትዮጵያ የግዛት አንድነት ሳይሸራረፍ ይቀጥላል የሚል ምንም ነገር አላየሁበትም። ከእነዚህ ሁለት ክልሎች ውጨ ያለውን ህዝብና መሬት ምን እንደሚሆን የተቀመጠ ነገር የለም። ይሄ በጣም አስፈሪው ገፅታው ነው። ሁሉት ብሄሮች በዚህ ጉዳይ ሊስማሙ የሚችሉት ሁለቱም ከዋናው ሃገር ለመገንጠል በአንድ ላይ ለመዋጋት ሲስማሙ ነው ልክ እንደ ህወሀትና ሻዕቢያ። ለምሳሌ ይሄ በኦነግና በኦጋዴን ነፃ አውጪ ግንባር ማካከል የነበረው ትብብር በዚህ ዓይነቱ ስሜት የተቃኘ ነበር።
በመሰረቱ የአማራ ልሂቃን አሁን በኢህአዴግ የተሰጣቸውን ክልል ብቻ ይዘው ለመኖር የጃዋርን ትብብር የሚያስፈልጋው አይመስለኝም። ሌላው የአማራ ልሂቃን ኦሮሚያ እንድትገነጠል የሚፈልጉ አይመስለኝም፤ ስለዚህ ጃዋር ከእነዚህ ጋር ለመስራት ከፈለገ አቋሙን ነው በትክክል መቀየር ያለበት። አንደኛ በኢትዮጵያ የግዛት አንድነት ማመን አለበት፤ ሁለተኛ ህዝቦቿ የተሳሰረ የጋራ እድል እንዳላቸው፤ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለማምጣት የሁሉም ተሳትፎ እንደሚያስፈልግ መቀበል ይኖርበታል። እንደዚሁም በኢትዮጵያ ጨቋኝ ስርዓቶች እንጂ በቀኝ ግዛት መልክ የገዥና የተገዥ ግንኙነት እንዳልነበረ ከልብ መረዳት ያስፈልጋል።
በሌላ በእኩል ኦፌኮ የኦሮሞ ህዝብ ወኪል እንደሆነ ገልፀዋል፤ እንደዚያ ከሆነ ደግሞ የኦፌኮ ፕሮግራም ማየት ይኖርብናል ማለት ነው። ኦፌኮ በኢትዮጵያ ትክክለኛ ፌደራሊዝምና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲኖር ይፈልጋል፤ አሁን ያለውን የኦሮሚያ ክልል ካርታ ያለመሸራረፍ እንዲከበር ይፈልጋል፤ አዲስ አበባ በኦሮሚያ ግዛት ውስጥ የሚገኝ በመሆኑ ኦሮሚያ ከአዲስ አበባ ልዩ ጥቅም እንድታኝ ይፈልጋል፤ ኦሮምኛ ልክ እንደአማርኛ የፌደራል መንግስት የስራ ቋንቋ እንዲሆን ይፈልጋል። ስለዚህ የአማራ ልሂቃን ቢያንስ በእነዚህ ከመገንጠል በመለስ ያሉትን የኦሮሞ ፖለቲካ ጥያቄዎች ለመቀበል ይችሉ ይሆናል፤ ይህን ሲቀበሉ ግን የሚያገኙት ነገር ሊኖር ይገባል። ይሄ ሲሆን ሌላው ደቡብ ትግራዩ አፋሩ ጋምቤላው ቤንሻንጉሉ ምንድነው የሚያደርገው ዝም ብሎ ያያል። ሀሳቡ ራሱ ገና ከመነሻው የከሸፈ መሆኑ የሚያሳየው እዚህ ላይ ነው።
ኦፌኮ ይህን ፍላጎቱን በተወሰነም ቢሆን በመድረክ ውስጥ ያሉትን ፓርቲዎች ለማሳመን ሙከራ ያደርጋል፤ ለምሳሌ ሁለተኛ ቋንቋ ይኑር በሚለው ጉዳይ ላይ አረና፣ የያኔው አንድነት፤ የበየነ ፓርቲዎች ተቀብለውት ነበር። ከዚህ ውጪ ከአንድ ወገን ብቻ የሚደረግ ትብብር ኢህአዴግ እስከሚወድቅ ድረስ ብቻ የሚቆይ እንጂ ዘላቂ አይሆንም። ሌላው ጃዋር እንደሚያስበው ህዝብ ዝም ብሎ ተባበር ስላልከው ብቻ አይተባበርም፤ አንድላይ ሁን ስላልከው ብቻ ተነድቶ አንድ ላይ አይሆንም፤ ሰው የከብት መንጋ አይደለምና። ይሄ ህዝብን መናቅ ነው፤ ህወሀትም እስከዛሬ ሲያደርገው የኖረውን ነገር ነው።
ሶስተኛው ነገር የትግራይ ልሂቃን ተራማጅ ለመሆን አልቻሉም ያለበት ነገር ነው። አንደኛ እውነትነት ያለው አይደለም፤ ሁለተኛ ደግሞ የእርሱ የተራማጅነት መለኪያ ምን እንደሆነ ግልፅ አይደለም፤ እሱ ሜኒሶታ ሆኖ አቧራ ባስነሳ ቁጥር ለምን ድጋፍ አልሰጡኝም ከሆነ ብዙ የሚያስኬድ አይደለም። እንደ ትግራይ ልሂቅነታቸው የራሳቸው የሆነ ክልላዊና ሃገራዊ አጀንዳዎች ይኖራቸዋል። ከዚህ ፍላጎቻቸው ተቃራኒ የሆኑ እንቅስቃሴዎች ሲደረጉ ድጋፍ ላይሰጡ ይችላሉ። ለምሳሌ እኔ በኢትዮጵያዊ ብሄርተኝነት አምናለሁ፤ ህወሀት ለኢትዮጵያ ጥሩ ስርዓት እንዳልሆነም አውቃለሁ። በዚህ ምክንያትም በተቻለኝ አቅም ሁሉ ስታገለው ኖሬያለሁ፤ ነገር ግን “የትግራይን ህዝብ ከህወሀት ጋራ ደርበን እንመታለን” የሚሉትን አንዳንድ ፅንፍ የረገጡ ኃይሎች አልቀበላቸውም።
አስር ሺህ የማይሞላ ትግርኛ ተናጋሪ በስርዓቱ ተጠቃሚ ስለሆኑ “የትግራይ ህዝብ ሁሉ ተጠቃሚ ነው” የሚለኝም አልቀበልም፤ ምክንያቱም እኔ ትግራይ ውስጥ ኖሬ ነው እውነታውን የማይቀው። ስለዚህ እኔ በትክክል ስለማውቀው ነገር አሜሪካ ወይም አውሮፓ ወይም አዲስ አበባ ሆኖ ተቃራኒው እንዲነግረኝ አልፈልግም። ሌላው የጃዋር መከራከሪያ ደካማ የሚያደርገው ምክንያት ደግሞ “አራት መቶ ሰው ሲጨፈጨፍ አንድም የትግራይ ልሂቅ ወጥቶ “አረ ይኼ ግድያ ትክክል አይደለም” አለማለቱ እንደሆነ አስቀምጠዋል።
እርሱ አልሰማም ይሆናል እንጂ ቢያንስ እራሱ “የኦሮሞ ህዝብ ወኪል ነው” ካለው ኦፌኮ ጋር አብሮ በመድረክ ጥላ ስር ያለው አረና በስራ አስፈፃሚ ደረጃ ተወክሎ አብሮ መግለጫ ሲሰጥ ተመክቻለሁ። እነ አረጋዊ በርሄ፣ ግደይ ዘርዓፅዮንና የመሳሰሉት አንጋፋ የትግራይ ፖለቲከኞች አሉበት የሚባለው ሸንጎ የተባለ በውጭ የሚኖሩ ፓርቲዎች ስብስብም ግድያውን አውግዘዋል። እንግዲህ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ኦፌኮ የኦሮሞ ህዝብ ወኪል ነው ካለ አረናም የትግራይ ህዝብ ወኪል የማይሆንበት ምንም ምክንያት የለም። ስለዚህ የትግራይ ልሂቃን ወገናቸው በሆነው የኦሮሞ ህዝብ ላይ ስለደረሰው ነገር ለጃዋር ስልክ እየደወሉ ወይም በፌስቡኩ ስር ተስልፈው አቋማቸውን ማሳወቅ የነበረባቸው አይመስለኝም። እንዲያውም እኔ አልፎ አልፎ ከትግራይ ልጆች ጋር ስንወያይ የኦሮሞ ፖለቲካ በኢትዮጵያ ባለው የኃይል አሰላለፍ እንደተፈጥሯዊ አጋር የማየት ሁኔታ ነው የማየው። ይሄ ህወሀት የፈጠረው ትፅዕኖ ሊሆን ይችላል። እንደእኔ እምነት ግን አንድ ህዝብ በአንድ ሃገር ውስጥ ከሌላው ነጥሉ አጋር አንዱን ደግሞ ጠላት ወይም ስጋት የማድረግ አካሄድ አላምንበትም።
ስለተራማጅነት ከተነሳ አረና በነበርኩበት ወቅት ኦሮምኛ ሁለተኛ ብሄራዊ ቋንቋ እንዲሆን በመድረክ መለስተኛ ፕሮግራም ላይ ተወያይቶ በሙሉ ድምፅ ነበር ያፀደቀው፤ ለእኔ ከዚህ በላይ ተራማጅነት የለም። ከአቶ ገብሩ አስራት በስተቀር ያለበት ጉዳይ ራሱ በጣም አስቂኝ ነው፤ አቶ ገብሩ አስራት በአረና ውስጥ ካሉት ወይም ከአረና ውጪ ካሉት የህወሀት ተቃዋሚዎች በኦሮሞ ጉዳይ ላይ የተለየ አቋም ያለው አይመስለኝም፤ “ከገብሩ በስተቀር ዓረና ውስጥ ያሉትን ወጣቶች “የአንድነት ኃይል” ተፅዕኖ አለባቸው” እየተባለ በመድረክ ኮሪደር አከባቢ የሚወራውን ነው የደገመው፤ ምንም አዲስ ነገር የለውም። መድረክን እንደ አንድ ኃይል አለመስወዱ ግን መድረክ ከሚያደርገው እንቅስቃሴ ደካማነት አንፃር ተገቢ ሊሆን ይችላል።
ሌላው የሕወሓት አወዳደቅ የትግራይ ሕዝብን ይዞ እንዳይወድቅ መጥንቀቅ አስፈላጊ ነው፤ …. ማንም ይኹን ምን ኢትዮጵያ ውስጥ የአንድ ብሔረሰብ መጎዳት ለኢትዮጵያም ኾነ ለአጠቃላዩ የምሥራቅ አፍሪካ መልካም አይደለም።” ያለው ተገቢ የሆነ ግንዛቤ ነው። ቢያንስ ምንም ምንም በማይደርስበት የውጭ ዓለም ተቀምጠው፤ በርገራቸውን እየገመጡ “የእኛ ትግል የትግራይ ህዝብ ካልደገፈ እኛ ወደ ስልጣን ስንመጣ ወዮውለት” ከሚሉት አንዳንድ የዲያስፖራ ፖለቲከኞች የተሻለ አቋም ነው።
በመሰረቱ ህወሀትንና የትግራይን ህዝብ ለይቶ የማያይ የፖለቲካ አስተሳስብም ሆነ እንቅስቃሴ መጨረሻው ውድቀትና መከራ ለሁላችን ያመጣ እንደሆነ እንጂ ለድል የሚበቃ አስተሳሰብ አይደለም። የትግራይ ህዝብ ከህወሀት የተለየ ምን ሊያደርጉለት እንደሚችሉ ማሳመን ያለባቸው እነርሱ ናቸው፤ ይህን ማድረግ ካልቻሉ የራሳቸው ችግር ነው። ገና ለገና መንግስት ሲሆኑ ሊያጠቁኝ ይችላሉ ብሎ ፈርቶ የትግራይ ህዝብ ማንምም ሊደግፍ አይችልም፤ እንደዚያ ዓይነት ታሪክም የለውም። ስለዚህ ሊማርከው ያልቻለን ፖለቲካ ያለመደገፍ መብቱ ነው፤ ህወሀት መጥፎ ስለሆነ ሌለው ሁሉ ጥሩ ነው ማለት አይደለም። እኔ የሚያሳስበኝ ነፃ ያለመሆኑ ነው እንጂ ነፃ ሆኖ ህወሀትም ቢደግፍ ህዝብ እንደህዝብ ተሳስቷል የምልበት ሞራል አይኖረኝም ነበር። እንዲያውም እንደህዝብ በህወሀት ታግቶ እየኖረ ያለ በመሆኑ ሊታሰብለት ነው የሚገባው።
ተራማጅ የሆነ ፖለቲካዊ አስተሳሰብ ያለው ማንኛውም ሃይል የትግራይ ህዝብ ነፃ ሆኖ የፈለገውን እንዲደግፍ ነው እድል ማመቻቸት ያለበት እንጂ በልዩ ልዩ ተፅዕኖና በፍራቻ ውስጥ ሆኖ እየኖረ ለህወሀት ይደግፋል ማለት እጅግ በጣም ፍርደ ገምድልነት ነው። በድንብ መሰመር ያለበት ጉዳይ እንዲህ ከሚያስቡ ኃይሎችና ግለሰቦች ጋር የትግራይ ልሂቅ ትብብር ሊኖረው አይችልም።
ለሁሉም ነገር አስታራቂው ሀሳብ የሚመስለኝ፤ በዜግነታዊ ብሄርተኝነት (Civic Nationalism) ሁላችንንም እኩል የምንሆንበትን ስርዓት ለማምጣት እንታገል የሚል ነው። ሁሉም ኢትዮጵያዊ ተጠቃሚ የሚያርግ፤ በህግ የበላይነት የሚመራ፤ አድልዎ የሌለበት ስርዓት ታግለን እንትከል የሚል ጥሩ ሀሳብ ነው። ይሄ ሀገር እዚህ እንዲገኝ ሁሉም አስተዋፅኡ አድርጎበታል፤ ችግር እየሆነ ያለው ሁሉም ተጠቃሚ ያለመሆኑ ነው። ይሄ ነው ማስተካከል ያለብን። ሁለተኛ ደግሞ መገንጠል መፍትሄ ያለመሆኑ ነው። ከዚያ አከባቢ ነቅለህ አይደለም የምትሄደው፤ አሳባዊ የሆነ መሬት ላይ የሌለ ድንበር አበጅተህ ነው ጎን ለጎን ተፋጥጠህ የምትኖረው። ስለዚህ እንዲህ ተፋጥጠህ ከምትኖር በሰላም ተግባብቶ መኖር አማራጭ የሌለው መፍትሄ ስለሆነ ነው

የኢትዮጵያ መንግሥት ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬን ከእስር እንዲለቅ ዩናይትድ ስቴትስ ጥሪ አቀረበች

 


የኢትዮጵያ መንግሥት ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬን ከእስር እንዲለቅ ዩናይትድ ስቴትስ ጥሪ አቀረበች
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Journalism‬ ‪#‎FreethePress‬ ‪#‎WoubishetTaye‬
ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ እ.አ.አ. ሰኔ 19, 2011 በመንግስት ባለሥልጣናት ታሰረ። ውብሸት በአማርኛ ቋንቋ የሚሰራጨው የአውራምባው ታይምስ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ነበር።
አንድ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት እንደገለጸው ውብሸት ከመታሰሩ በፊት ገዢው ፓርቲ የሚተች ጽሁፍ አቅርቦ ነበር። ውብሸት አዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው ዩኒቲ ኮሌጅ ነው የጋዜጠኝነት ሞያውን የጀመረው። ከዚያም አሁን በታገደው ሃዳር በተባለ ነፃ ሳምንታዊ ጋዜጣ ሞያውን ቀጠለ። እ.አ.አ. ጥር 19, 2012 በአዲስ አበባ የሚገኝ ፍርድ ቤት በአሸባሪነትና እና ለአሸባሪነት ገንዘብ በመከፈል ወንጀለኛ ተባለ። ከዚያም 14 አመታት እስራት ተፈርዶበት በአሁኑ ወቅት በዝዋይ ማረምያ ቤት ይገኛል። የጤንነቱ ጉዳይም አስጊ ሁኔታ ላይ ይገኛል። የኢትዮጵያ መንግስት ውብሸት ታዬን እንዲለቅ እንጠይቃለን። የሽብር ህጉም በነጻ ሃሳብን ለመግለጽ እንቅፋት እንዳይሆና የጋዜጠኞችን ስራ ለማጣጣል መንግስቱ እንዳይጠቀምበት ጥሪ እናቀርባለን።
Read More : http://amharic.voanews.com/a/woubishet-taye-highlighted-in-state-department-campaign-call-to-free-press-/3308942.html

ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ እ.አ.አ. ሰኔ 19, 2011 በመንግስት ባለሥልጣናት ታሰረ

Friday, April 29, 2016

አቡነ ፋኑዔል (አባ መላኩ) ለናሽቪል ደ/ቀራንዮ መድኃኔ ዓለም ቤተ/ክ ላሰራጩት መልዕክት የተሰጠ መልስ (PDF)


123
አቡነ ፋኑኤል የፓትርያርክ አክልልና አርዌ ብርት ጨብጠው በየክብረ በዓሉ ሲታዩ። 

በትምህርት ሥርዓቱና በመምህራን ላይ የተደቀነ አደጋ – ከቀድሞው መምህራን ማህበር የተሰጠ መግለጫ



Teachers Unionበታሪክ አጋጣሚ በሥልጣን ላይ የተቆናጠጡ ገዢ ሃይሎች ሁሉ ሕዝብ የሚያነሳቸውን የመብት ጥያቄዎች በአግባቡ ሲመልሱ አልታዩም። ከሕዝብ ፍላጎትና ጥያቄ ይልቅ የራሳቸውን የፖለቲካ ፍላጎትና ጥቅም በማስቀደም ሕዝቡን ለርሃብ፣ ለድንቁርና፣ ለስደትና ውርደት፣ አገሪቷን ለውድቀት ዳርገዋል። በተለይ ወያኔ/ኢህአዴግ በመማር ማስተማር ሙያ ላይ የተሰማራውን ሃይል የተለያዩ ስያሜዎችን በመስጠትና በወያኔያዊ ግምገማ በማስመረር ልምድ ያካበቱ መምህራንን ከሥራ ማባረሩና ሙያውን ለቀው እንዲሄዱ ተጽዕኖ ማድረጉ ለትምህርት ውድቀት አመላካች አርምጃ ነው። [ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]

የከሸፈው የብአዴን/ህወሃት/ኢህአዴግ ስብሰባ በዳላስ!



ባሳለፍነው ሳምንት እሁድ April 24, 2016 ወያኔ/ኢህአዴግ ጠፍጥፎ የሰራው የበአዴን ከፍተኛ ባለስልጣናት ከክልሉ ተወላጆች ጋር በልማት ዙርያ እወያያለሁ በሚል የዘወትር ዲስኩራቸው ለማሰማት ወደ ዳላስ/ቴክሳስ መምጣታቸውና ስብሰባ ማድረጋቸው የሚታወስ ነው። ስብሰባው በበአዴን የዳላስ ተወካዮችና በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኢንባሲ የተዘጋጀ ነው ቢባልም ከመግቢያው በር ጀምሮ ተቆጣጣሪ የነበሩት የህወሃት/ኢህአዴግ ሰዎች ነበሩ። የክልሉ ተወላጆች ጨምሮ አያሌ ኢትዮጵያውያን ወደ ስብሰባው ስፍራ ቢያመሩም የመግቢያ ቲኬት የላችሁም በሚል ወደ አዳራሹ እንዳይገቡ ታግደዋል።
webshet taye
የስብሰባው አዳራሽ ባዶ እንዳይሆንባቸው የህወሃት/ኢህአዴግ አባላት የተገኙ ሲሆን በቅጡ ተቆጥረው በአጠቃላይ ከ45 አይበልጡም ነበር። ከ50,000 በላይ ኢትዮጵያውያን በሚገኙበት ዳላስ ከተማ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለስልጣን መጥቶ ትንሽ ቁጥር ያለው ህዝብ ስብሰባው ላይ መሳተፉ የዳላስ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ምን ያክል በወያኔ ተስፋ የቆረጡና የተማረሩ መሆናቸውን ነው።
ስብሰባው ላይ ከተሳተፉትና ካዘጋጁት ውስጥ ተኮላ፣ ፀሃይጽድቅ፣ ኢብራሂም፣ ሙሉጎጃም ገዳሙ፣ አቶ መሰረት፣ ወ/ሮ መሰረት፣ አያሌው አርጋው፣ ወ/ሮ አለምፀሃይና ሌሎችም ይገኙበታል። ሰው በላ የሆነውን አንባገነኑና ፋሽስቱ የወያኔ/ኢህአዴግ ስርዓትን እድሜ ለማራዘም በታማኝነት ተግተው የሚሰሩት እንዚህ ጥቂት አደርባዮች ለይቶ በማወቅ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል። አብዛኛዎቹ በኮሚኒቲያችን፣ በቤተክርስቲያን፣ ኢትዮጵያዊ በሆኑ የሲቪክ ማህበራት ውስጥ እራሳቸው ሸሽገው የወያኔ 52 ገፅ የዲያስፖራ ፖሊሲ ለማስፈፀም የስለላ ስራ ሲሰሩ ቆይተዋል።
እነዚህ ተላላኪ የወያኔ ተኩላዎችን ለይቶ በማወቅ እራሳችን እንጠብቅ፤ ለሌሎችም እናሳውቅ። ለሆዱ ያደረ ባንዳ ዘመድና ጓደኛው ሆዱና ሆዱ ብቻ ነውና!
የነፃነት ቀን እሩቅ አይደለም!
በፅናት እንታገል!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

ኤፍሬም ታምሩ የሰሜን አሜሪካ የሙዚቃ ኮንሰርት በሰሜን አሜሪካ የተለለያዩ ከተሞች ሊካሄድ ነው | ሚኒሶታ ሜይ 21 ይደረጋል



ephrem Tamiru 2015
(ዘ-ሐበሻ) የስመጥሩው አርቲስት ኤፍሬም ታምሩ የሙዚቃ ኮንሰርት በሰሜን አሜሪካ የተለያዩ ከተሞች ሊካሄድ መሆኑ ተሰማ:: ከላስ ቬጋስ ከተማ ይጀመራል የተባለው የኤፍሬም የሙዚቃ ኮንሰርት ሜይ 21 በሚኒሶታ እንደሚካሄድም ታውቋል::
የላስቬጋስ ኮንሰርት ሜይ 10 እንደሚደረግ አዘጋጆቹ ይፋ ያደረጉ ሲሆን በሚኒያፖሊስ ሚኒሶታ የኤፍሬምን የሙዚቃ ኮንሰርት የሚያዘጋጁት ዘ-ሐበሻ; ሶል ዲዛይን እና ፕሮሞሽን እንዲሁም ራስ ላውንጅ ፕሮሞሽን እንዳስታወቁት ሜይ 21 በሴንት ፖል ዳንሰርስ ስቱዲዮ ይካሄዳል:: አብሮትም አቢሲኒያ ባንድ ወደ ሚኒሶታ ይመጣል::
ኤፍሬም በሲያትል; በዋሽንግተን ዲሲ; በአትላንታ እና በተለያዩ ከተሞችም በዚህ የበጋ ወራት ኮንሰርቶቹን ያቀርባል ተብሎ ይጠበቃል::
ኤፍሬም የቀድሞው ሥራዎቹን እንደአዲስ ከሮሃ ባንድ ጋር በመሆን እንደአዲስ ካወጣ በኋላ በተለያዩ ስቴቶች እየዞረ ኮንሰርቱን ሲያቀርብ የመጀመሪያው ይሆናል:: በተለይ ሚኒሶታ ኤፍሬም ለመጨረሻ ጊዜ የመጣው ከ9 ዓመት በፊት በመሆኑ አድናቂዎቹ በጉጉት ይጠብቁታል

Thursday, April 28, 2016

የፍቅር ቁስል – አርአያ ተስፋማሪያም April 28, 2016 – ኢየሩሳሌም አርአያ


grief
አቤል አሜሪካ የመጣው የ5 ልጅ እያለ ነበር። ትምህርቱን ቀጥሎ በወጣት አፍላነት እድሜ ሲደርስ አብራው ትማር ከነበረች ሀበሻ ፍቅር ይጀምራሉ። ልጅት በድንገት ፅንስ ትቋጥርና ትወልዳለች። ቆንጆዎቹ ሀበሻ ጥንዶች በልጅ ታጅበው ፍቅራቸውን ይቀጥላሉ።
አቤል ከ12 አመት በፊት ኢትዮጵያ ያመራል። የአሜሪካና ኢትዮጵያን ባህል ሲመለከት ውስጡ ይነካል። ገዳማትና ቤ/ክርስቲያ ይዞርና የፈጣሪን መንገድ ይይዛል። አቤል ከተመለሰ ከአመት በኋላ ልጅ የወለደችለት ፍቅረኛው ሄለን ወደ አገር ቤት ታመራለች። በሚኒባስ እየሄደች መኪናው ተገልብጦ ህይወቷ ያልፋል። አቤል ሲናገር “ፍቅሬን አፈር አለበስኳት። ወደመቃብር ስትወርድ ፍቅርና መውደዴን ይዛው ሄደች። አብሬ ቀበርኩት። 10 አመት አንድ ሴት ሳልቀርብ የብቸኝነት ኑሮ እገፋለሁ። በየአመቱ አገር ቤት እየሄድኩ መቃብሯን እጎበኛለሁ። እግዚአብሔርን ማወቅ በጀመርኩ ማግስት ፍቅሬን ነጠቀኝ። ግን እምነቴን አልተውኩም! በወጣትነቴ ተጎዳሁ። ልጄን ባየሁ ቁጥር ፍቅሬ ድቅን ትላለች! የፍቅር ቁስሌን ለብቻዬ አስታምማለሁ!”
ሀዘን በሸረሸረው ገፅታ በዝምታ ተመሰጠ። በግምት 29 አመት እድሜ የሚሆነው አቤል የ10 አመት የብቸኝነት ህይወቱ ያሳዝናል! በእንባና ሀዘን የተከበበ ህይወት!

የጸሃይ ብርሃን እንዳናይ፤ ውሃ እንኳን እንድንለምን ተደርገናል። ልጆቻችንና ዘመዶቻችን እኛን ለማየት እንዳይችሉ ተደርገናል።” የኦፌኮ አመራር አባላት April 27, 2016 – ቆንጅት ስጦታው — 3 Comments ↓


“የጸሃይ ብርሃን እንዳናይ፤ ውሃ እንኳን እንድንለምን ተደርገናል። ልጆቻችንና ዘመዶቻችን እኛን ለማየት እንዳይችሉ ተደርገናል።” አቶ ደጀኔ ጣፋ ታሳሪ የኦሮሞ ፌድራሊስት አመራር አባል።
“ከማዕከላዊ ምርመራ ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ስንመጣ መድሃኒት ውሰዱ ተባልን። መድሃኒቱንአንወስድም ሌላ አማራጭ ጠየቅን።” አቶ በቀለ ገርባ፤ ታሳሪ የኦሮሞ ፌድራሊስት አመራር አባል።
“በማረሚያ ቤቱ ‘ጨለማ ቤት’ የሚባል የለም። አንዳንድ ታሳሪዎች የተለየ ጠባይ ሲያሳዩና”ሲደባደቡ“ ግን ከቤተሰብ አባላት ጋር የመገናኘት ዕድል የሚያሳጣ ቅጣት ሊጣልባቸው ይችላል።”የማረሚያ ቤቱ ተወካይ።
Text: በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች ከተቀሰቀሱት የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች ጋር ተያይዞ “የኦሮሞነጻነት ግንባርን የሽብር ተልዕኮ ለማሳካት አመጽ በማነሳሳት ተሳትፋችኃል፤” የሚል ውንጀላቀርቦባቸው በእሥር ላይ የሚገኙት የኦፌኮ አመራር አባላት “ደረሱብን” ያሏቸውን በደሎች ተንተርሶበሕግ ታሳሪዎች አያያዝ ዙሪያ ያተኮረ የሕግ ትንታኔ ነው።
“ካለፈው አርብ አንስቶ ልጠይቃቸውና ስንቅ ለማቀበል እንኳን ተስኖናል፤” ሲሉ የቤተሰብአባሎቻቸው ያቀረቧቸውን ቅሬታዎች በትላንትናው ምሽት መዘገባችን ይታወሳል

የቀድሞ የጋምቤላ ፕ/ት 9 ዓመት ተፈረደባቸው (በእጅ ጽሁፋቸው የጻፉትና ምስጢር የያዘው የክስ መቃወሚያቸው እጃችን ገብቷል)



okello
(ዘ-ሐበሻ) የኖርዌይ ዜግነት እንዳላቸው የሚነገርላቸውና ደቡብ ሱዳን ላይ ታፍነው ተወስደው የታሰሩት የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኦኬሎ አኳይ “አገርን ለመገንጠል” በሚል በቀረበባቸው ክስ የ9 ዓመት እስራት ተፈረደባቸው:: ኦኬሎ ከፍርድ በፊት ለሚዲያ ይድረስልኝ በሚል የላኩትና ለፍርድ ቤቱም በእጅ ጽፉፋቸው አስገብተውት የነበረው የክስ መቃወሚያ ዘሐበሻ እጅ ደርሷል:: ይዘነዋል::
ከኦኬሎ ጋር በተባባሪነት የተቀሰሱት ዴቭድ ኡጁሉ 9 ዓመት; ኡቻን ኦፔይ 7 ዓመት; ኡማን ኝክየው 7ዓመት; .ኡጁሉ ቻም 7ዓመት; ኦታካ ኡዋር 7ዓመት እና ኡባንግ ኡመድ 7 ዓመት ተፈርዶባቸዋል::

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ተባረሩ

3

8b0067e1ba18cd789b122c804be56585_XL
(ዘ-ሐበሻ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ አቶ ዮሐንስ ሳህሌ ከአሰልጣነታቸው መባረራቸው ተሰማ:: በአንድ ወር የ75 ሺህ ብር ተከፋይ የነበሩት እኚሁ አሰልጣኝ ብሄራዊ ቡድኑን ከሚያዝያ 26/2007 ዓ.ም ጀምሮ ሲያሰለጥኑት ቆይተዋል::
የቀደሞው የደደቢት እግር ኳስ ክለብ አሰልጣኝ አቶ ዮሐንስ ሳህሌ ከአሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው የተረከቡትን ብሄራዊ ቡድን ውጤታማ ሊያደርጉ ይችላሉ ተብሎ ተስፋ የተጣለባቸው ቢሆንም በ እርሳቸው ዘመን ብሄራዊ ቡድኑ የሶማሊያ ብሔራዊ ቡድንን ከማሸነፉ ውጭ ምንም አመርቂ ውጤት አላመጡም እየተባሉ በስፖርት ተንታኞች ዘንድ ሲተቹ ቆይተዋል::
75 000 ብር ወርሃዊ ደመወው; ተሽከርካሪ ከሾፌር ጋር እንዲሁም ባለመስመር የሞባይል ስልክና የጤና ኢንሹራንስ ከተለያዩ ጥቅማትቅሞች ጋር እየተከፈላቸው ብሐራዊ ቡድኑን ሲያሰለጥኑ የነበሩት አቶ ዮሐንስ በተጨማሪ ምክትል አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ እና የበረኞች አሰልጣኝ አሊ ረዲም አብረው መሰናበታቸው ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ያመለከታል::

በአዲስ አበባ ባለ5 ፎቅ ህንጻ ተደረመሰ

5

addis ababa
በአዲስ አበባ በተለምዶው ሠሚት የሚባለው የአዲስ አበባ ሰፈር የደረሰው ይኸው የህንፃ መደርመስ ዛሬ ንጋት ላይ ያጋጠመ ሲሆን በወቅቱ በፎቁ ላይ ሰው ስላልነበረ የሰው ህይወት ተርፏል ሲል አድማስ ራድዮ ዘገበ::
አድማስ ራድዮ እንደዘገበው ፎቁ የተጀመረ ፎቅ ነው። ከታች ግን ሁለት ባንኮች ባላለቀው ፎቅ ስር ሆነው አገልግሎት ይሰጡ ነበር። በአገር ቤት በያንዳንዱ ያላለቀ ፎቅ ሥር ባንኮች እንዳሉ ይታወቃል።
እንደራዲዮው ዘገባ የባንኮቹ የጥበቃ ሰራተኞች ህንፃው ከመድርመሱ በፊት ከባድ ድምፅ በመስማታቸው ከአደጋው ሊያመልጡ ችለዋል። በአዲስ አበባ የሚሰሩ ህንጻዎች ጥራት ጉዳይና ባላለቁ ህንጻዎች ውስጥ ሥራ መጀመር ሁልጊዜም ትችት ሲቀርብበት እንደነበር የሚታወስ ነው።

በጋምቤላ ውጥረቱ እየተባባሰ መሆኑ ተገለጸ (የፍኖተ ዴሞክራሲ ራድዮ አጫጭር ዜናዎች)




ሚያዚያ 18 ቀን 2008 ዓ.ም.ዜና (April 26, 2016 NEWS)
# በጋምቤላ ውጥረቱ እየተባባሰ መሆኑ ተገለጸ
# ለጥጥ ልማት በማለት ብድር ወስደውና ደን መንጥረው የነበሩ ግለሰቦች ጠፉ ተባለ
# የትንሣዔ በዓልን አስታኮ ወያኔ የሸማቾች ማህበራት ሱቆች እያቋቋመ ነው
# የጄኔራሉን ገዳዮች ባስቸኳይ እንዲይዙ የብሩንዲው ፕሬዚዳንት ለጦር ኃይሉ መመሪያ ሰጡ
# አልሸባብ በባይደዋ የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ጦር ሰፈርን ወርሮ ጉዳት አደረሰ
# የእርዳታ ሰጭ ድርጅቶች በሱማሊያ የገባውን ድርቅና ረሃብ ለመቋቋም የምግብ እርዳታ ያስፈልጋል አሉ
#ሬክ ማቻር ጁባ ገቡ
ሚያዚያ 18 ቀን 2008 ዓ.ም.
Ø ጋምቤላ 18 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ባለው የደቡብ ሱዳን የጀዊ ስደተኞች ሰፈር የፈነዳው ግጭትና ግድያ ትላንትም ቀጥሎ እንደነበር በቦታው ያሉ ምስክሮች ገልጸዋል ። በቦታው የሰፈሩት ስደተኞች መቶ በመቶ የደቡብ ሱዳን አማጽያን መሪ የሪያክ ማሻር ተከታዮችና የኑዌር ተወላጆች ሲሆኑ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን ሾፌር የነበረው ኢትዮጵያው ሁለት ስደተኛ ህጻናትን በመኪና ገጭቶና ገድሎ በመሰወሩ ኑዌሮቹ በሰፈሩ ያሉትን ኢትዮጵያውያን ለመግደል ተነስተው ብዙዎችን እንደገደሉ ይታወቃል ። ከተገደሉት ውስጥ የስደተኛው ኮሚሽን ኢትዮጵያዊ ሰራተኞችም እንዳሉበት ታውቋል። ጀዊ የአንዋኮች አካባቢ ስትሆን ወያኔ ኑዌሮችን በዚያ ያሰፈረው ለተንኮል ነው ተብሎም ተጋልጧል። ወያኔ ከግድያው በኋላ ዜጎችን ለመከላከል ምንም እርምጃ ባለመውሰዱ ኢትዮጵያውያኑ ተደራጅተው የስደተኛውን ሰፈር ማጥቃታቸው ታውቋል። የሟቹ ቁጥርም ቀላል አልሆነም ። የተባበሩት መንግስታት የስድተኛ ኮሚሽን ሰራተኞቹን ከጀዊ አካባቢ አሽሽቷል። ግጭቱ ገና አልበረደም ሲል ዛሬም የደረስ ዜና ያረጋግጣል ።
Gambela
Ø ወያኔ ለዘረፋና ለስርቆት እንዲያመቸው ከ 100 ሺ ሄክታር በላይ የጋምቤላ መሬትን ለጥጥ እርሻ በማለት ለንግድ ሸሪኮቹ በመስጠትና ለልማትም በማለት 3 ቢሊዮን ብድር በመፍቀድ የጥጥ ምርትን እናሳድጋለን በማለት ፕሮፓጋንዳውን ካሰራጨ ወዲህ የጥጥ ምርቱም ሳይኖር ልማቱም ሳይካሄድ ደን ተጨፍጭፎ ከቆየ በኋላ በብድር የተሰጠው ገንዘብ ለምን ተግባር እንደዋለ እንኳ ለማወቅ አለምቻሉ ተገልጿል። ለጥጥ ልማት በማለት መሬት ወስደው ደን መንጥረው ገንዘብ ተበድረው ጠፉ የተባሉ ሰዎችና ኢንቬስተሮች እነማን እንደሆኑ ባይገለጽም ወያኔ ምርመራና ማጣራት ጀምሬያለሁ ብሏል። ጉዳዩን የተከታተሉ ወገኖች ግን ዘረፋውና የተፈጥሮ ወድመቱ በወያኔ አባላትና በንግድ ሸሪኮቻቸው መፈጸሙን ይናገራሉ።
Ø በአባይ ወንዝ ግድብና አጠቃቀም ዙሪያ ወያኔና ግብጽ የገቡበትን የፖሊቲካና የዲፕሎማሲ ውዝግብ ለማብረድ በወያኔ ፓርላማ አፈጉባዔ የሚመራ አንድ የልኡካን ቡድን ግብጽንና ሱዳንን መጎብኘቱ ይታወሳል። የጉብኝቱ ዓላማ የታሰበለትን ግብ ይምታ አይምታ ባይታወቅም በወቅቱ የነበረውን የዲፕሎማሲ ውጥረት ግን ሳያለዝበው እንዳልቀረ ተገምቷል፡፤ ወያኔ ከሱዳን ጋር መልካም ወዳጀነት ፈጥሮ በድንበር አካባቢ ለም መሬቶችን አሳልፎ ከሰጠና ሱዳንም በአገሩ የሚገኙ የወያኔ ተቃዋሚዎችን እያፈነ ለወያኔ ለመስጠት ጥረት በሚያደርግበትና በሁለቱ አገሮች መካከል የድንበር ጥበቃ ውል ተፈርሞ ባለበት በአሁኑ ሰዓት የሱዳን ሕዝብ ዲፕሎማሲ የተባለ ቡድን የወያኔን ባለስልጣኖችን እንደሚያነጋግር ተገልጿል። ጉብኝቱ ግንቦት 1 ቀን 2008 ዓም የሚጀመር ሲሆን የዲፕሎማሲው ቡድን ከወያኔው ጠቅላይ ሚኒስትር ተብየው ጀምሮ ከሌሎች የወያኔ ባለስልጣኖችን ያናገጋራል ተብሏል፡፤
Ø መጭውን የትንሳዔ በዓል አስታኮ የወያኔ አገዛዝ ሱቆችን በማደራጀት አባ ወራዎችን በቡድን እየመደበ እንደሚያሰማራ ታውቋል። ከአስራ አምስት እስከ ሃያ የሚደርሱ አባወራዎች በአንድና በሁለት ሱቆች ሸቀጦች እንዲሸጡ በማደራጀትና በማስገደድ ነዋሪዎንና የነጋዴው ህብረተሰብን ለማጋጨት እየተሞከረ መሆኑ ተገልጿል። ሱቆቹ በዋናነት ስኳርና ዘይት የሚያቀርቡ ሲሆን ሌሎች ሸቀጦችንም ሊጨምሩ እንደሚችሉ ተነግሯል። የወያኔ አገዛዝ በመላ ኢትዮጵያ ላንሳራፋው የኑሮ ውድነት ተጠያቂ መሆኑ የሚታወቅ ቢሆንም የችግሩ መነሻና ምንጭ የነጋዴው ህብረተሰብ እንደሆነ አድርጎ በማቅረብ ነጋዴዎችን ከሕዝብ ጋር ለማጋጨት የሸማቾች ማህበራትን ማቋቋሙ ይታወቃል። የፋሲካ በዓልን ተንተርሶ እንደ ቅቤ እንቁላል ዶሮ በግና በሬዎች የመሳሰሉ የምግብ አቅርቦቶች ዋጋ ጭማሪ እያሳየ መሆኑ ታውቋል።
Ø ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ለወያኔ ማስረከብ የለመደበት የኬንያ መንግስት የታይዋን ተወላጅ ሆነው በህገወጥነት የወነጀላቸውን የታይዋን ተወላጆች አስሮ ለሀገራቸው ሳይሆን ለቻይና ማስረከቡ ተጋለጠ። ቻይና ታይዋን ግዛቴ ናት ብትልም ቻይናና ታይዋን ሁለት የተለያዩ ሀገሮች ሆነው እንድሉ ይታወቃል። ወያኔ በበኩል ኬንያ እንደ የመን የሚመጡ ተቃዋሚዎችን አግታ እንድታስረክብ ዝርዝር ስሞችን ሰጧል ተብሎም መረጃ አለ ።
Ø ከጥቂት ቀናት በፊት በብሩንዲ አንድ የጄኔራል ማእርግ ያላቸው ከፍተኛ ባለስልጣን ከነባለቤታቸው ባልታወቁ ሰዎች መገደላቸው የሚታወስ ሲሆን ገዳዮችን አፈላልገው እንድይዙ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ለወታደሮቻቸው የአንድ ሳምንት የጊዜ ገደብ ያለበት ጥብቅ መመሪያ የሰጡ መሆናቸው ታውቋል። ፕሬዚዳንቱ ለሟቾቹ ቤተሰቦች ሀዘናቸውን የገለጹ ሲሆን የአገሪቱ የጦር ኃይልም አንድነቱን አጠናክሮ ሁኔታውን በቁጥጥር ስር እንዲያደርግ ተማጽነዋል። የፕሬዚዳንቱ ትእዛዝ በብሩንዲ እየተካሄደ ያለውን ግድያ ያፋፍማል የሚል ስጋት ፈጥሯል። የብሩንዲ የእርስ በርስ ግጭት ከጀመረ ወዲህ የመንግስት ባለስልጣኖች ማንነታቸው ባልታወቀ ሰዎች ሲገደሉ የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ደግሞ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የጅምላ ግድያ እያካሄዱ ከመሆናቸውም በላይ በርካታ ሰዎችን አስረው ሰቆቃዊ ድርጊት እየፈጸሙባቸው መሆኑ ይነገራል።
Ø በሱማሊያ ከዋናዋ ከተማ ከሞጋዲሾ ሰሜን ምዕራብ 250 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ከምትገኘው ከባይደዋ ከተማ አጠገብ በሚገኘው የአፍሪካ ህብረት እና የሱማሊያ መንግስት የጦር ካምፕ ላይ አልሸባብ ጥቃት ሰንስዝሮ ቢያንስ 20 ወታደሮችን የገደለ መሆኑ ከስፍራው የተገኘው ዜና ይገልጻል። ከተወሰነ የተኩስ ልውውጥ በኋላም የአፍሪካ ህብረት የሰላም አሰከባሪ ሃይሎች እና የሱማሊያ ወታደሮች የጦር ሰፍሩን መልሰው መቆጣጠራቸው ተነግሯል። የአልሸባብ አጥቂዎችም ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው የአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ ኃይል ቢገልጽም ከአልሸባብ በኩል የተሰማ ዜና የለም።
Ø መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና የሰብአዊ እርዳታ ሰጭ ድርጅቶች በጋራ ባወጡት መግለጫ በሱማሊያ የገባውን ከፍተኛ ድርቅና ረሃብ ለመቋቋም አስቸኳይ እርዳታ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። ድርጅቶቹ በጋራ መግለጫቸው ላለፉት አራት አመታት በሱማሊያ ዝናም በመጥፋቱ ምክንያት ከ5 ሚሊዮን በላይ የሚሆን ሕዝብ መሰደዱን ገልጸው ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ ከፍተኛ እልቂት ሊኖር እንደሚችል ተናግረዋል። ከስድስት ዓመት በፊት በሱማሊያ በገባው ድርቅ ምክንያት ከ250 ሺ ሰው በላይ የሞተ መሆኑን አስታውሰው ተመሳሳይ የሕዝብ እልቂት እንዳይደርስ ከፍተኛ እርዳታ መሰብሰብ አለበት ብለዋል።
Ø ከጥቂት ቀናት በፊት ከአንድ የቱርክ የንግድ መርከብ ላይ በባህር ላይ አፋኞች ተጠልፈው ተወስደው የነበሩ ስድስት የመርከቡ ሰራተኞች የተለቀቁ መሆናቸውን የንግድ መርከቡ ባለስልጣኖች ገልጸዋል። ሚያዚያ 3 ቀን 2008 ዓም. ማንነታቸው ያለታወቀ የባህር ላይ አፋኞች መርከቧ ላይ በመውጣቱ ካፕቴኑ የሚገኝበትን ስድስት ሰዎች በቁጥጥር ስር ማድረጋቸው የታወቀ ሲሆን ማክሰኞ ሚያዚያ 18 ቀን 2008 ለቀዋቸዋል ተብሏል። የተለቀቁት የመርከቧ ሰራተኞች በጥሩ የጤና ሁኔታ ላይ መሆናቸው ቢነገርም ለመለቀቃቸው ካሳ መከፈሉ እና አለመከፈሉ የተገለጸ ነገር የለም። በዚህ ዓመት ብቻ በናይጄሪያ ወደብ አካባቢ ከ32 በላይ የመርከብ ጠለፋዎች የተካሄዱ መሆናቸው ከተባበሩት መንግስታ ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት አካባቢ የተገኙ ዜናዎች ይጠቁማሉ።
Ø የደቡብ ሱዳን አማጽያን መሪ ሪክ ማቻር ለአንድ ሳምንት ያህል ጉዟቸው ካዘገዩ በኋላ በዛሬው ቀን ጁባ ገብተዋል። የአማጽያኑ ድርጅት ቀደም ብሎ ባወጣው መግለጫ ሚስተር ማቻር ዛሬ ሚያዚያ 18 ቀን ከቀኑ ስምንት ሰዓት ላይ ጁባ የሚገቡ መሆናቸውን ገልጾ የነበረ ሲሆን በታቀደው መሰረት ለምክትል ፕሬዚዳንቱ ቦታ ለመያዝ ቃለ መሃላ ፈጽመዋል ተብሏል። ሚስተር ማቻር ጁባ ይገባሉ ተብሎ ታቅዶ የነበረው ሚያዚያ 10 ቀን የነበረ ሲሆን ከዚያ በኋላ በተደጋጋሚ በታቀዱት ቀናት ወደ ጃባ ባለመለሳቸው በዓለም አቅፉ ህብረተሰብ በሌሎች ላይ ከፍተኛ ስጋት ፈጥሮ እንድነበር አይዘነጋም።

በጋምቤላው ጭፈጨፋ የደ/ሱዳን ሹመኞች እጅ መኖሩን አንድ የአገሪቱ የጦር ጄ/ል አጋለጡ | ኢትዮጵያ ዛሬም ለባእዳኖቹ ምቹ አልጋ ፣ለልጆቿ ግን ቀጋ የመሆኑዋ ጉዳይ እያነጋገረ ነው



“ ባለሰልጣኑ በጋምቤላው ጭፍጨፋ ዙሪያ አካፋን አካፋ ብለው መጥራት ይገባቸዋል” ሌ/ጄኔራል ዲቪድ ያ ኡ ያ ኡ
ኢትዮጵያ ዛሬም ለባእዳኖቹ ምቹ አልጋ ፣ለልጆቿ ግን ቀጋ የመሆኑዋ ጉዳይ እያነጋገረ ነው
ከታምሩ ገዳ
ከሳምንት በፊት በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ በጋምቤላ ክልላዊ መስተዳደር በሚገኙ የኑኢር ማህበረሰብ ላይ ከጎረቤት ደ/ሱዳን አንደመጡ የሚነገረላቸው እጅግ ዘመናዊ የጦር መሳሪያ እና የደ/ሱዳን የመከላከያ ሰራዊቱን የድምብ ልብስ ያጠለቁ መሆናቸው የተነገረላቸው የሞራሌ ጎሳ ተወላጆች በ 10 የኑዊር መንደሮች ላይ በከፈቱት የጅምላ የተኩስ እሩምታ ከ 200 በላይ ሰዎች ህይወትን በመቅጠፍ ከ100 በላይ ጨቅላ ህጻናትን ደግሞ አፍነው በመወሰድ ፣ከ 2ሺህ በላይ የቀንድ ከበቶቻቸውን በመዝረፋቸው ሳቢያ በበርካታ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊናኦች ዘንድ ከፍተኛ የሆነ ብሄራዊ ሃዘን እና ቁጭት መቀሰቀሱ አይዘነጋም።
tan
ታዲያ ከዚሁ ሰሞነኛው የጋምቤላው ጭፍጨፋ ጋር በተያያዘ የተለያዩ አሰተያየቶች እየተሰነዘሩ ሲሆን የተወሰኑ ወገኖች በጭፍጨፋው ላይ የደ/ሱዳን የመከላከያ ጦር እጁ እንደነበረበት የሚናገሩ ሲሆን በተቃራኒው ጎራ “ በጭፍጨፋው ላይ የተሳተፈው የደ/ሱዳን ስራዊት ሳይሆን ለስረቱ ቀረብ ያሉ የ አካባቢው ፖለቲከኞች ናቸው “የሚሉ ወገኖች ከደ/ሱዳን ባለሰልጣናት ዘንድ ብቅ ብቅ ማለታቸው ታውቋል። ይህንን (የሁለተኛውን )ሃሳብ ከሚያቀነቅኑት መካከል የደ/ሱዳን ዲሞክራቲክ ሙቭመንት (SSDM/SSDA) ዋና ሊቀመንበር የነበሩት ሌትናል ጄነራል ዲቪድ ያኡ ያኡ የሰሞኑን የጋምቤላውን ጭፍጨፋን በጸኑ ያወገዙ ሲሆን ጥቃቱን አድራሺዎቹ ሊኪዋንጋሎ ከተባለ አካባቢ ከሚገኙ ኒያርጀኒ፣ዎጎን፣ማንያታካ፣ቶልቶል እና ማንታይድ ከተባሉ መንደሮች በሚገባ የተደራጁ እንደሆኑ እና ይህ ክልል ደግሞ በአሁኑ ወቅት የቦማ ግዛት ሃገር ገዢ (ገቨርነር )የሆኑት ባባ ኒዳን የትውልድ ስፍራ ሲሆን አኚሁ ሃገረ ገዢው ከዚህ ቀደም ከነዋሪው ሕዝብ ጋር ስላላቸው ቁርኘት በተመለከት ሌ/ ጄ/ል ዲቪድ ሲገልጹ” ሃገረ ገዢው ቀደም ሲል ፒቦር የተባለች ከተማን ለመውረር ሕዝቡን የዘመናዊ የጦር መሳሪያ ባለቤት በማድረግ እና ጥይቶችን በገፍ በማቀበል ጥቃት ለመፈጸማቸው በግላጭ የሚታወቅ ሲሆን ይሄው የጦር መሳሪያ እ ወታራዊ ቁስ ሰሞኑን ጋምቤላ ወስጥ በኑኢር ልጆች ላይ ለተፈጸመው አሳቃቂ እና ተግባር ላይ ውሏል” ሲሉ የ ደ/ሱዳን ባለሰልጣኑ (የሞራሌ ተወላጆችን ያሰታጠቁ የአካባቢውን ሹምን) ቁጥር አንድ ተያቂ ናቸው ሲሉ ወንጅለዋቸዋል።
photo
የቦማ ግዛት ሃገረ ገዢው ከዚህ ቀደም በእልቂቱ ላይ የ ደ/ሱዳን ጦር እጆች ሰለመኖራቸው በተመለከት የሰጡትን ትችት በተመለከት ጄ/ል ዲቪድ ሲናገሩ “ እኛ አማጺያኖች ከወቅቱ ከጁባ መንግስት ጋር ስራዊታችን ኣንዲጣመር እና እርቀ ሰላም እንድናደረግ መንገድ በጠረገችልን አገር ( በ ኢትዮጵያ እና በሕዝቧ) ላይ የጦር መሳሪያ በጭራሽ አናነሳም ። ይልቁንም ለዚሁ የሰበ ጡራን ፍጅት እና ሰቆቃ ተጠያዊ የሆኑት የቦማ ግዛት ገዢው ባባ ኒዳን ለተፈጸመው ወንጀል ሃላፊነቱን እንዲወስዱ፣ አካፋንም አካፋ በሎ መጥራት (ወንጀለኞቹን የማጋለጥ እና ለፍርድ የማቅረቡ እርማጃን )መማር አለባቸው፣ ባለሰልጣኑ ተራ እና መሰረተ ቢስ ውንጀላቸውን ትተውም በግፍ ታፍነው የተወሰዱት 108 በላይ ኢትዮጵያዊያን ህጻናት እና የተዘረፉት የቀንድ ከብቶች ለህጋዊ ባለቤቶቻቸው (ለጋምቤላ ማህበረሰብ )ይመለሱ ዘንድ ከአካባቢው የጎበዝ አልቆች ጋር በግላጭ መነጋገር አለባቸው ።” በማለት ጄ/ል ዲቪድ ለሃገር ገዢው፣ ለ ባባ ፣የተማጸኖ መልእክት ለከዋል ። የቀደሞው ስራዊታቸንም “እጁ ከደሙ ንጹህ ነው” ሲል ትከላክለዋል።
ላለፉት ሁለት አመታት በአርሰ በርስ ጦርነት የታመሱት ት ፣ለበርካታ ሰላማዊ ዜጎች መሞት እና መሰደድ ምክንያት የሆኑት የደ/ሱዳን ዋንኛ ፖለቲከኞች ፕ/ቱ ሳልቫ ኪርር እና እስከ ትላንትናው እለት ድረስ ጋምቤላ እና አ/አ ውስጥ ሲዝናኑ ቆይተው በአለማቀፉ ማህበረሰብ ጫና እና ግፊት ወዳፈራረሷት የደ/ሱዳን መዲና የሆነቸው ጁባ ለመሄድ የተገደዱት ዶ/ር ሪክ መክችር የምክትል ቦታውን ዳግም እንዲይዙ የተደረገ ሲሆን ሁለቱ ፖለቲከኞች (ሳልቫ ኪርር እና መክቻር ) በአሁኑ ወቅት ሰለ ወንበራቸው እና ሰለ ራሳቸው መጻኢ ተስፋ ማሰብ እና ማሰላሰል አንጂ በእነርሱ ጦስ ሳቢያ ለተሰደዱ ከ200 ሺህ በላይ ዜጎቻቸውን ላሰጠለለች ከዚያም አልፎ ባለፈው ሳምንት በጋምቤላው የጃዊ የሰደተኞች ጣቢያ በተፈጠርው ድንገተኛ የመኪና ግጭት ሳቢያ የሁለት የደ/ሱዳን ሰደተኞች ህይወት መጥፋቱን ተከትሎ ከ 10 በላይ ሰላማዊ ኢትዮጵያዊያኖች በአካባቢው አጠራር (ደገኞች/የመሃል አገር ትወላጆች ) ላይ የደረሰው የብቀላ እና ሃይል የተቀላቀለበት እርምጃ ሳቢያ የህይውት መጥፋትን በተመለከተ (አንዲያውም በወቅት ዶ/ር ማክችር ድርጊቱ ሲፈጸም በከተማ ውስጥ ነበሩ ይባላል) ፣ ከዚያ በመለጠቅ የሞራሌ ጎሳዎች ባለፈው ሳምንት በእነርሱ ሹማምንቶች የተጥቅ ደጋፍ ታግዘው በ208 ላይ ሰላማዊ የጋምቤላ ነዋሪዎች ላይ ስለ ተፈጸመው ጭፍጨፋ እስከ አሁን ድረስ ጠጠር ያለ የማውገዝ እና ፈጣን እርምጃ የመወሰድ እንቀሰቃሴ ያለማድረጋቸው ጉዳይ “ኢትዮጵያ ድሮም ሆነ ዛሬ ለ ባእዳኖች የሞቀ አልጋ ፣ለልጆቿ ግን የቀጋ እሾህ ነች”የሚለው ብሄል በበዙዎች አይምሮ ውስጥ ሰሞኑን ዳግም እንዲመላለስ አድርጎታል።
ይህ ማለት ደግሞ ዛሬ በአንዳንድ አገሮች እንደምናየው እና ወግኖቻቸን እንደሚያበሻቅጧቸው “ሰደተኞች አገራችንን ለቀው ይወጡልን ዘመቻ አይነት እናካሄድ “ማለት ሳይሆን በኢትዮጵያ መሬት የሚገኙ የትኛውም አገር ሰደተኞች የአገሪቱን እና የህዝቧን ክብር እና ባህል በማይነካ መንገድ እንዲሰተናገዱ ፣ አደብ የሚያሰገዛ እና ለሰደተኞች ሲባል የዜጎቹንም ህይውት በግፍ እና በከንቱ የማይቀጭ ፣ ክብራችውን እና መብታቸውን የማይደፈጥጥ መንግስት፣የህግ አስከባሪ ሃይል ይኑር ። እንዲሁም ህዝባዊ ስር አትም ይዘርጋ ማለት ነ

Wednesday, April 27, 2016

የዘንድሮዋ ግንቦት 20 – እስክንድር ነጋ ፤ የሕሊና እስረኛ (ከቃሊቲ)


ይኸው የወርሃ ሚያዝያ 2008ን የመጀምሪያ ሳምንት አገባደድን:: ግንቦት ተንደርድሮ እየመጣ ነው:: ኢሕአዴግ ሥልጣን የያዘበትን 25ኛ ዓመት ለማክበር ደፋ ቀና ማለት ጀምሯል:: ሩብ ምዕተ ዓመታትን በታላቁ ቤተመንግስት ማሳለፍ ቀላል አይደለም:: የአንድ ትውልድ ዕድሜ ነው:: እንኳን በተማሪዎች አብራክ ውስጥ ለተወለደ ድርጅት ይቅርና፣ በነባሮቹ የኢትዮጵያ ነገሥታት ሚዛንም ረዥም የሥልጣን ዕድሜ ነው:: ሥልጣን ላይ ለረዥም ጊዜ መቆይታቸውን እንደጀብድ ለሚቆጥሩት የኢሕአዴግ ነባር መሪዎች፣ የዘንድሮዋ ግንቦት 20 በተለየ ሁኔታ ጮቤ የሚረገጥባት ናት::
ኢሕአዴግ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ ትሩፋት ነው:: ንቅናቄው ከውልደት እስከ ህልፈቱ ከ1953 – 1966 – 13 ዓመታትን አስቆጥሯል:: ከ1966ቱ አብዮት በኋላ፣ የአባላቱ ብርቱ ሕልም ፍሬ አፍርቶ ወደ ተደራጀ የፖለቲካ ትግል ቢያድግም፣ በአንድ ጥላ ሥር ሊያስገባቸው የሚችል መሪ ድርጅት Vanguard Party የሚሉትን መፍጠር ባለመቻሉ ተማሪዎቹ ወደ ተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች እንደጨው ተበትነዋል:: በትህምርት ቤት የነበራቸው መፈቃቀር፣ መተሳሰብ፣ በቅንነትና ተስፋ የውሃ ሽታ ሆኖ፣ ወደ መወነጃጀሉ ፣ ወደ መከፋፈሉ፣ ወደ መካካዱ፣ ወደ መቀኛነቱ፣ ወደ ክፋቱና ወደ መጠፋፋቱ ዓለም ጭው ብለው ገብተዋል::
ይህ ሂደት ብልጭ ድርግም እያሉ የኖሩ በርካታ የፖለቲካ ቃላትን አፍርቷል::: አብዮት፣ ኢምፔሪሊያዝም፣ ፊውዳሊዝም፣ ተራማጅ፣ አድሃሪ፣ በዝባዥ፣ ጨቋኝ ፣ ፋሺስት፣ አናርኪስት፣ ጠባብ፣ ትምክህት፣ አምባገነን፣ ዴሞክራሲ፣ ገንጣይ፣ አስገንጣይ፣ አክራሪ፣ ለዘብተኛ፣ ጽኑ፣ ወላዋይ፣ ሐቀኛ፣ አስመሳይ፣ ጀግና፣ ባንዳ፣ ታማኝ፣ ከሃዲ፣ ሃገር ወዳድ፣ ቅጥረኛ፣ ታጋይ፣ ነፍጠኛ፣ አብዮታዊ ዲሞክራሲ፣ ሊብራል ዲሞክራሲ፣ ቦናፖርቲስት፣ ተንበርካኪ፣ ብሄር፣ ብሄረሰብ፣ ሕዝቦች፣ ወዘተ::
እነዚህ ቃላት የሚጋሩን የአፍሪቃ ሃገራት ማግኘት በእጅጉ ይከብዳል:: ኢትዮጵያ እንደሃይማኖቶቿ፣ እንደ ምግቦቿ፣ እንደ አላብስቶቿ፣ እንደዜማዎቿ፣ እንደነሥነጽሁፏ፣ እንደ ስዕሎቿ፣ እንደ ታሪኳ፣ እንደ መሬት አቀማመጧ ሁሉ በፖለቲካውም ልዩ ናት::
እንዲህ ዓይነቱን የተለየ ማንነት አሜሪካውያን ኤክሴፕሽናሊዝም (exceptional-ism) ይሉታል:: በብዙ መመዘኛዎች አሜሪካ ኤክሴፕሽናል ናት ብለው ያምናሉ:: በዚህ እሳቤ እስከ ሁለተኛው ዓለም ጦርነት ድረስ ራሳቸውን ከዓለም ፖለቲካ አግልለው ኖረዋል:: በአውሮፓ እንግሊዞች፣ በኤሺያ ጃፓኖች፣ በመካከለኛው ምስራቅ ኢራኖች፣ ይህን ስሜት ይጋሩታል:: በላቲን አሜሪካ “ኤክሴፕሽናል ነኝ” የሚል ሃገር ስለመኖሩ አላውቅም:: ዓለም ላይ ካሉት 200 ሃገራት መካከል በዚህ ምድብ ሊካተቱ የሚሉት ከአስር ቢያንሱ እንጂ አይበልጡም:: ለጥሩም ሆነ ለመጥፎ፣ ስብሰቡ የጥቂቶች ነው::
የኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄም ከሃገሪቱ ታሪክ ባልተለየ መልኩ ልዩ የሚያደርጉት ገጽታዎች አሉት:: “ሙሉ ለሙሉ የተለየ ነበር” ማለት ግን አይቻልም:: ይህን መንታ ባህሪ “በ66ቱ አብዮት ላይ ጥሩ መጽሐፍ ነው” የሚባለው የጆን ማርካኪስ (John Markakis) – አናቶሚ ኦፍ ኤ ትራዴሽናል ፖሊቲ ( Anatomy of a Traditional Polity) ውስጥ ቁልጭ ብሎ ተቀምጧል::
ንቅናቄዎን ልዩ ከማያደርጉት ባህሪያቱ መካከል፣ በዚህ ዘመን በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በብዙ ሃገራትም የተማሪዎች እንቅስቃሴ የነበረ መሆኑ አንዱ ነው:: በሌላ አነጋገር፣ የተማሪዎች ንቅናቄ የዘመኑ ፋሽን ነበር:: ጆን ማርካኪስ እንዲህ ያስቀምጡታል::
“Radical student agitation was a hallmark of the 1960s in all non-communist Countries Ethiopia Students, eager to imitate western models, naturally became engaged”
“በ1960ዎቹ ( እ.ኤ.አ) ኮሚኒስት ባልነበሩት ሃገራት የተጋጋለ የተማሪዎች ንቅናቄ የዘመኑ መለያ ነበር:: ይህ የምዕራባዊያንን ፈለግ ለመከከተል ጉጉት የነበራቸው የኢትዮጵያ ተማሪዎች የራሳቸውን ንቅናቄ አቀጣጥለዋል” (በcontext የተተረጎመ ነው::)
ልዩ ከሚያደርጉት መካከል ደግሞ ሦስት ባህሪያቱን ማንሳት ይቻላል:: በቀዳሚነት ተማሪዎቹ ለሥልጣንና ለሹመት የነበራቸው ከፍተኛ ጉጉት ይገኛል:: ይህ ጥማት በምዕራዊያኑ ተማሪዎች ዘንድ አልነበረም:: ማርካኪስ እንዲህ ያስቀመጡታል:-
“The First Ethiopians who came back with degrees from abroad had become ministers and ambassadors. Students felt entitled to advance as rapidly. Law and Humanities courses were overflowing. Engineering and since were less appealing. Many students disdained and avoided teaching or other forms of social service in the province.”
“ከውጭ ሃገራት ድግሪ ይዘው ወደ ሃገራቸው የተመለሱት የመጀመሪዎቹ ኢትዮጵያውያን ሚኒስተሮችና አምባሳደሮች ሆነዋል:: (እ.ኤ.አ በ1960ዎቹ የነበሩት) ተማሪዎችም “በዚያው ፍጥነት የማደግ መብት አለን” የሚል ስሜት ነበራቸው:: (በተማሪዎቹ ዘንድ) ምህንድስናና ሳይንስ ብዙም ተፈላጊ አልነበሩም:: ወደ ክፍለሃገር ሄዶ ማስተማርም ሆነ ማህበራዊ አገልግሎት መስጠትን ይጠሉና ይሸሹ ነበር::”
በዚያ ዘመን የነበረው ቢሮክራሲ ግን፣ እንኳን ሚኒስትርና አምባሳደር ሊያደርጋቸው ቀርቶ ፣ የተመረቁትን ሁሉ ተቀብሎ ሥራ ለመስጠት እየተንገዳገደ ነበር:: የኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ፣ “ከምረቃ በኋላ ሥራ እናጣለን” ብለው የሰጉ ተማሪዎች ንቁ ተሳትፎ ያደረጉበት ነበር:: ተማሪው ለሃገርና ለሕዝብ ብቻ ብሎ አልተነሳም::: ከኢትዮጵያ ሌላ ለየትኛውም ሃገር ንቅናቄ ይህን ማለት አይቻልም::
ማርካኪስ፣ በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ የነበረውን ነፃነት ለንቅናቄው መወለድና ማበብ እንደ አበይት ምክንያት ያስቀምጡታል:: ይህም የኢትዮጵያን ተማሪዎች ንቅናቄ ልዩ ከሚያደርጉት – በሦስተኛ ዓለም ከነበሩት – ገጽታዎቹ አንዱ ነበር::
ማርካኪስ እንዲህ ብለዋል:-
“With the university, the students succeeded in joining almost complete freedom of expression, and their publications launched quite uninhibited attacks on the regime although they refrain from attacking the person of the emperor”
“ተማሪዎቹ በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ ሃሳብን በነጽሳነት የመግለጽን መብት ከሞላ ጎደል ሙሉ ለሙሉ ለማስከበር ችለዋል:: ሕትመቶቻቸውን የአጼውን ስብዕና ከማጥቃት ቢቆጠቡም መንግስትን ግን ያለምንም ፍርሃት ይተቹ ነበር” ((በcontext የተተረጎመ)
የተማሪዎቹን ቀልብ በዋናነት የሳበው ግን፣ ወቅታዊው የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ አልሆነም:: ወሳኝ የሆኑትን የሃገራቸውን ታሪክ፣ ፖለቲካና የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ አልሆነም:: ወሳኝ የሆኑትን የሃገራቸውን ታሪክ፣ ፖለቲካና ኢኮኖሚ በሁለተኛ ደረጃ አስቀምተው ማርክሲም ላይ አተኩረዋል:: ይህ ሲሆን መንግስት ጣልጋ አልገባባቸውም:: በዚህ ሳቢያ ማርክሲዝም በአደባባይ ከተሰበከባቸው ጥቂት የአፍሪካ ሃገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ ለመሆን በቅታለች:: ይህ እውነታ የተማሪውን ንቅናቄ የአጼው መንግስት የአካዳሚ ነፃነት ውጤት ያደርገዋል:
በሦስተኝነት፣ የኢትዮጵያን ተማሪዎች ንቅናቄ ልዩ ከሚያደርጉት ባህሪያቱ መካከል የአባላቱ ድህነት ጉልህ ስፍራ ይሰጠዋል:: ይህ ክፍተት ንቅናቄው የግድ የውጭ ኃይሎች፣ ጥገኛ አድርጎታል:: የንቅናቄው አድማስ ከዩኒቨርሲቲው ግቢ ውጥቶ ወደ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲዛመት፣ ከተማሪዎች በሚሰብሰብ መዋጮ የተደራረበውን ወጪ የሚሸፈንበት ሁኔታ አልነበረም:: በዚህ ክፍተት፣ በዘመኑ ከነበሩት ሁለት ልዕለ ኃያላን መካከል አንዷ የነበረችው ማርክሲሥቷ ሶቭየት ኅብረት ተማሪዎቹን ስኳር ታልሳቸው እንደነበር ማርካኪስ ጽፈዋል::
“After Haile Selassie expelled several soviet and East European embassy officers in 1968 and 1969 for subversive contacts with students, Moscow refined its techniques. It was less risky to work with Ethiopian students abroad. Hence forth, money, propaganda and advice for student’s agitation in Ethiopia came in large part through Marxist- dominated Ethiopia student organizations in Europe and America. Under the guise of supporting literacy campaigns and welfare projects, these organizations sent far larger sums of money than they would conceivably have collected on their won to their counter parts in Addis Ababa’
“እ.ኤ.አ በ1968 እና በ1964 የሶቭየትና የምሥራቅ አውሮፓ ዲፕሎማቶች ‘ከተማሪዎች ጋር ሕገ-ወጥ ግንኙነት አድርጋችኋል’ ተብለው ከተባረሩ በኋላ፣ ሞስኮ ስልቷን ቀየረች:: ውጭ ካሉት ተማሪዎች ጋር መሥራቱ የተሻለ አማራጭ ሆኖ ተገኘ:: ከዚህ በኋላ ሃገር ውስጥ ለነበረው የተማሪዎች ንቅናቄኤ የሚሰጠው የገንዘብ፣ የፕሮፓጋንዳና የምክር ድጋፍ፣ ማርክሲስቶች በሚመሯቸውና በአውሮፓና በአሜሪካ በነበሩ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማህበራት በኩል እንዲላክ ተደረገ:: እነዚህ ማህበራት ለመሰረተ ትምህርትና ለማህበራዊ ዋስትና ድጋፍ እንሰጣለን’ በሚል ሽፋን ከአባላቶቻቸው ሊያሰባስቡት ከሚችሉት በላይ ገንዘብ ወደ አዲስ አበባ ልከዋል::”
ይህ ሁሉ በጥቂት ተማሪዎች ፈቃድ የተፈጸመ ሲሆን በእኔ ግምት በክሮኮዳይሎች crocodiles ብዙሃኑ ተማሪዎች እስከአሁን ድረስ ምን እንደተደረገ አያውቁም:: ይህ መረጃ ጨለማ፣ በብዙሃኑ ተማሪ በጭፍን ይከተላቸው የነበሩትን የንቅናቄው መሪዎች፣ ማርክሲዝምን የተቀበሉት ለገንዘብ ብለው ነበር ወይ? የሚል ጥያቄ እንዳስነሳ ያስገድደኛል:: የተማሪው ንቅናቄ ከከሰመ በኋላ እንደታየው፣ በመሪዎቹም ሆነ በብዙሃኑ ተማሪ ዘንድ፣ ማርክሲዝም ቅብ ነበር እንጂ ውስጣቸው ሰርጾ የገባ እምነት አልነበረም::
ፈረንጆች “…with the benefit of hindsight…” የሚሉት ነገር አላቸው:: “ግዜው ካለፈ በኋላ በአንክሮ ሲታይ” እንደማለት ነው:: የተማሪው ንቅናቄ በዚህ ዓይነቱ መነጽር ሲቃኝ የውጭ ኃይሎች መሣሪያ መሆኑ ብዙም አያስደንቅም:: የገንዘብ ብቻ ሳይሆን የታሪክም ደሃ ነበርና:: ጥራዝ ነጠቅ ማርክሲዝምን በተላበሰው ንቅናቄ ዘንድ፣ ታሪክ፣ ባህል፣ ማንነትና ኃይማኖት የመሳሰሉ ነገሮች በመደብ የተከፋፈለ ማህበረሰብ ኋላቀር ቅሪቶች ናቸው ተብለው በመፈረጃቸው በንቀት የሚታዩ ነበሩ:: ለኢትዮጵያ የተለየ ታሪክና ማንነት ቦታ አልነበረውም::
በዚህ ሳቢያ፣ ስለ1984ቱ “ፓሪስ ኮሚውን” (የፓሪስ አመጽ) መወያየትና መከራከር ይወዱ የነበሩት የተማሪው ንቅናቄ አባላት – ልክ የዛሬ ዘመን ወጣቶች ስለ እንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ በአንክሮ እንደሚከራከሩት – እንኳን የጥንቱን የኢትዮጵያ ታሪክ ይቅርና፣ በፓሪስ ኮሚውን የቅርብ ርቀት (እ.ኤ.አ በ1860ዎቹ) የእንግሊዝ ጦር በኢትዮጵያ ላይ ስለፈጸመው ወረራና ስላስከተለው እንደምታ ምንም እውቀት ሳይቀራምቱና ሳይመጋገቡ ቀርተዋል::
ተማሪዎች በዚህ መልክ እስከ 1966 ድረስ ከቀጠሉ በኋላ፣ በአብዮቱ ፍንዳታ ማግስት ያቋቋሟቸው የፖለቲካ ድርጅቶች ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ወስደዋቸዋል:: ህብረብሄራዊ ድርጅቶች ያቋቋሙትም ማክርሲዝም ላይ ተቸክለው በመቅረታቸው መንግስታዊ ጭቆናን እስከመጨረሻው ድረስ መቋቋም የሚችሉ አባላትን ማፍራት ሳይችሉ ቀርተዋል:: እነ ኢሕ አፓና መኢሶን በደርግ ጭፍጨፋና አፈና ብቻ አልጠፉም:: በማርክሲዝም ብቻ የታነጹት አባሎቻቸው፣ በድንጋያማ መሬት ላይ እንደወደቀ ዛፍ፣ ጸሃይ ሲበረታባቸው – በመከራ ጊዜ – በቀላሉ ደርቀዋል:: በአንጻሩ፣ የብሄር ድርጅቶች ያቋቋሙት ተማሪዎች – የኤርትራ፣ የትግራይ፣ የኦሮሞ፣ የሲዳማ፣ ወዘተ – ሃገራዊውን ታሪክ ከማርክሲዝም ያልተናነሰ ቦታ በመስጠታቸው፣ ብርቱ መከራን መቋቋም የሚችሉ አባላትን አፍርተው – በተለይ የኤርትራና የትግራዮቹ – ደርግን ለመጣል በቅተዋል:: የሕብረብሄራዊ ድርጅቶች ማርክሲስቶች እንደተመኙት፣ ታሪክን ከኢትዮጵያ ፖለቲካ ነቅሎ ማውጣት አልተቻለም::
ተማሪዎቹ እንቅስቃሴያቸውን ከጀመሩ 55 ዓመታት በኋላም ከ1953 – 2003 የዮሐንስና የምኒልክ የ19ኛው ክፍለ ዘመን ፖለቲካ የፈጠረው ሽኩቻ፣ የኢሕአዴግ ቅኝት ጸረ-ዲሞክራሲያዊ እንዲሆን ምክንያት ከሆኑት ግብአቶች መካከል አንዱ ሆኖ ይገኛል:: የታሪክ ጣጣ የኦሮሞና የተማሪ ብሄረተኞችን ነፍስ እረፍት እንደነሳ ነው:: የታሪክን ህጸጾች የማይቀበሉ ቀላል የማይባል የፖለቲካ ኃይልም አለ:: ይህ ሁሉ ተደማምሮ በኢትዮጵያ አንድነት ላይ የተጋረጠ አደጋ ነው:: መፍትሄው ከአዲሱ ዘመን ዴሞክራቶች ይጠበቃል::
እስክንድር ነጋ፣
የሕሊና እስረኛ፣
ቃሊቲ::

Tuesday, April 26, 2016

ሥርዓተ ዕለተ ስቅለት ዘደብረ ሊባኖስ – ዳንኤል ክብረት


ከ500 ዓመታት በፊት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ዕለተ ስቅለትን እንዴት ታከብር እንደነበር በመጠኑ ሊያሳዩን ከሚችሉ መዛግብት አንዱ ‹ዜና ደብረ ሊባኖስ› የተሰኘው መዝገብ ነው፡፡ ዜና ደብረ ሊባኖስ በ1586 ዓም የተጻፈ መጽሐፍ ነው፡፡ መጽሐፉ አምስት ነገሮችን ይዟል፡፡ የደብረ ሊባኖስን ታሪክ ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት እስከ ዐፄ ሰርጸ ድንግል ዘመን፤ የደብረ ሊባኖስ ገዳም ጥንታዊ ሥርዓተ ማኅበር፤ የደብረ ሊባኖስ ገዳም ጥንታዊ ሥርዓተ ጸሎት፤ በመጽሐፈ መነኮሳት መልክ የተጻፈ የልዩ ልዩ መነኮሳት አስደናቂ መንፈሳዊ ሕይወት እና በዐፄ ሰርጸ ድንግል ዘመን የተፈጸሙ አንዳንድ ሀገራዊ ኩነቶች፡፡
እስካሁን በተደረገው ጥናት ዜና ደብረ ሊባኖስ ሦስት ቅጅዎች አሉት፡፡ የመጀመሪያው በፓሪስ ብሔራዊ ቤተ መጻሕፍት፣ በአንቶንዮ ዲአባዲ ስብስብ ውስጥ በቁጥር 108 ተመዝግቦ የሚገኘው፤ ሁለተኛው ከደብረ ጽጌ ማርያም የተገኘውና በማይክሮ ፊልም ተነሥቶ በEMML 7346 ተመዝግቦ የሚገኘው፤ ሦስተኛው ደግሞ በደቡብ ጎንደር ማኅደረ ማርያም ደብር የሚገኘው ቅጅ ነው፡፡ ከሦስቱም ቁልጭ ብሎ የሚነበበው የማኅደረ ማርያሙ ቅጅ ነው፡፡ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ከምናገኛቸው ጉዳዮች አንዱ በቤተ ክርስቲያን በዓላት ስለሚደረጉ ጸሎቶችና የጸሎቱ ሥነ ሥርዓት አንዱ ነው፡፡ አንዳንድ ሥርዓቶች በዘመን ብዛት ተረስተዋል፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ ተጎርደዋል፡፡ የጥንቱን ከዛሬው ማስተያየትና የጎደለውን ለመሙላት፣ የተረሳውን ለማስታወስ፣ የተሳተውንም ለማቅናት መሞከር ብልህነት ነው፡፡ እስኪ ለምሳሌ ሥርዓተ ዕለተ ስቅለቱን እንየው፡፡
ደግሞም የዕለተ ስቅለት ሥርዓት (ወግ) ይህ ነው፡፡ (ጠዋት) በ3 ሰዓት ቤተ ክርስቲያንን በወርቀ ዘቦ ግምጃ ካስጌጡ፣ ሥዕላትንም በየመስቀያቸው ካስቀመጡ በኋላ የመጻሕፍት ንባብ በየተራቸው ይሁን፡፡ የስቅለቱንም ሥዕል በመካከል ያኑሩት፡፡ ሦስት ማዕጠንቶችንም በፊቱ ይስቀሉ፡፡ ሁለት ዲያቆናትም አንዱ በቀኙ ሌላውም በግራው የሐር መነሳንስ ይዘው፣ የሐር ልብስም ለብሰው፣ ራሳቸውም ተሸፍኖ ይቁሙ፡፡ እስኪመሽና የስቅለቱ ሥዕል እስኪነሣ ድረስም እንዲሁ ይሁኑ፡፡
ወዳነሣነው ነገር እንመለስ፡፡
የመዓልቱን ቅኔ አድርሰውም በጌታችን ምሳሌ ይገረፉ ዘንድ ወደ ምሥራቅ ይሂዱ፡፡ ይህንንም ፈጽመው ወደ መዓልቱ ቅኔ ይመለሱ፡፡ ያመስግኑ፣ የመዝሙረ(ዳዊትንም) ቃል ሃምሳውን በሦስት ሰዓት፣ ሃምሳውን በስድስት ሰዓት፣ ሃምሳውን በ9 ሰዓት ይድገሙ፤ በምሽትም ጊዜ የስቅለቱ ሥዕል ከተገነዘ በኋላ 150ውን ይድገሙ፡፡ መዝሙረ ዳዊትም በሰሙነ ሕማማት ጊዜ ይድረስ፡፡ አንደኛው በመንፈቀ ሌሊት፣ አንደኛው በነግህ፣ አንደኛው በ3 ሰዓት፣ በ6 ሰዓትና በ9 ሰዓት ሃምሳ ሃምሳ በሰሙነ ሕማማቱ ሁሉ አምስቱ ቀን እስኪፈጸም ድረስ ይድረስ፡፡ በአንድ ቀንም ሦስት ጊዜ (ሙሉው መዝሙረ ዳዊት) ይድረስ፡፡ ሰኞ ዕለትና ማክሰኞ ዕለትም እንዲሁ እስከ ዓርብ ድረስ ይደረግ፡፡ በዕለተ ዓርብ ግን አራት ጊዜ(ሙሉው መዝሙረ ዳዊት) ይድረስ፡፡ በ3 ሰዓት፣ በ3 ቃል ‹ግፍዖሙ እግዚኦ ወጽብዖሙ እግዚኦ› በዜማ ይበል፡፡ ሕዝቡም በግራና በቀኝ ሆነው እስኪፈጸም ድረስ እየሰገዱ ይቀበሉት፡፡ የስቅለቱንም ሥዕል ይግለጡት፡፡ መገለጡም ሰባት ጊዜ ይሁን፡፡ አንደኛው ‹ግፍዖሙ› ሲባል፣ አንደኛው ወንጌል ሲነበብ፣ አንደኛው ‹በመስቀልከ ንሰግድ› ሲባል፣ አንደኛው በቀትር ወንጌል ሲነበብ፣ አንድ ጊዜም ‹አምንስቲቲ› ሲባል ነው፡፡ በመጨረሻ ሦስት ጊዜ ‹አምንስቲቲ› ይበሉ፡፡
ከዚያም ተነሥተው መልክዐ ወልድን ‹ሰላም ለጸአተ ነፍስከ› እስከሚለው ድረስ ይቀኙ፡፡ ከግብረ ሕማማትም በኋላ መጻሕፍትን ማንበብ ይቀጥሉ፡፡ ዮሐንስ አፈወርቅና መጽሐፈ ምሥጢር፡፡ ነገረ ማርያምም ከሁለቱ መጻሕፍት ይቅደም፡፡ ዳግመኛም መጽሐፈ ዶርሆ፣ ርቱዐ ሃይማኖት፣ ተስፋ ክርስቲያንና መልእክተ አቃርዮስ ዘሀገረ ሮሐ ይነበቡ፡፡ በ9 ሰዓት በንባበ ወንጌል ሰዓት ሥዕለ ስቅለቱን አንድ ጊዜ ይግለጡት፣ አንድ ጊዜ ደግሞ በምሽት ሁለት ዲያቆናት ሥዕለ ስቅለቱን ይሸከሙት፤ ቄሰ ገበዙም ‹ንሰግድ ለከ ክርስቶስ ምስለ አቡከ ሔር ሰማያዊ› ይበል፡፡ የሚከተሉትም በንዑስ የእዝል ዜማ ‹ኪርኤ ኤላይሶን› እያሉ በአራት መዓዝን መቶ መቶ ጊዜ ስግደትን ከማብዛት ጋር ይቀበሉት፡፡ ቁጥሩም ሲመላ ሥዕለ ስቅለቱን ጎንበስ ያድርጉት፡፡ ያልብሱት፣ በስቅለት ሥዕል ላይም መጋረጃ ይጋርዱ፤ በራሳቸውም ተሸክመውት ‹ኪርኤ ኤላይሶን› እያሉ ወደ ቤተ መቅደስ ይግቡ፡፡ እያንዳንዳቸውም በቀኝ ገብተው በግራ ይውጡ፡፡ መንበረ ታቦቱንም ሦስት ጊዜ ይዙሩት፡፡ ከዚያም በመንበሩ እግር ሥር በከርሰ ሐመሩ ሥዕለ ስቅለቱን ያስቀምጡት፡፡ ደም ባለበት በችንካሮቹ ሁሉ የከርቤ ዱቄት ይጨምሩበት ዘንድ ይግለጡት፡፡ ሲጨርሱም በልብስ ይሸፍኑት፤ መጋረጃውንም ይጋርዱት፡፡
ከዚህ በኋላም ቄሱ ስላረፉት ወገኖች ይለምን፡፡ እርሱም ‹ብቋዕ እግዚኦ› ነው፡፡ ወደ መዓልት ቅኔም ይውጡና መዝሙረ ዳዊትን ፈጽመው ያንብቡ፡፡ መጽሐፈ ሕማማትንም ያስከትሉ፡፡ ሲፈጸምም ካህኑ ‹ተሰቅለ ወሐመ› ይበል፡፡ ቀጥሎም ‹ንሴብሖ› ይበል፡፡ አስከትሎም ‹እግዚኦ ኢትጸመመኒ› የሚለውን ያንብብ፡፡ ሕዝቡም ‹ለይሁዳ ለወልዱ ላዕለ ውሉደ ውሉዱ› ይበሉ፡፡ ከዚያ ደግሞ ‹ብጹዕ ብእሲ›ን እስከ ፍጻሜው ያንብብ፡፡ መብራቶችንም ሁሉ አጥፍተው ወደየቤታቸው ይሂዱ፡፡ በዚያ ሌሊትም መጽሐፈ አፈወርቅንና መጽሐፈ ምሥጢርን ያንብቡ፡፡ ደግሞም ዳዊትን ከወንጌልና ከጸዋትው ጋር እንደ ሰሙነ ሕማማት አድርገው ያንብቡ፡፡
በነጋም ጊዜ(ቅዳሜ) መኃልየ መኀልይን ያንብቡ፡፡ ቀጥለውም ‹ቅዱስ፣ ዘተወልደ፣ ወዘተጠምቀ፣ ወዘተንሠአ› ይበሉ፡፡ መዝሙረ ያሬድንም ያስከትሉ፡፡ ‹ገብረ ሰላመ› ከተባለ በኋላ አስቀድመው ከቤተ ክርስቲያን ይውጡና ዲያቆኑ ‹ስግዱ ለእግዚአብሔር› ይበል፡፡ ከሁሉም የሚበልጠው የሊቃነ ጳጳሳትን ቡራኬ ያንብብ፡፡ ይህቺም ሥርዓት ዳግመኛ በርእሰ ዐውደ ዓመት እንዲሁ ትፈጸም፡፡ በፋሲካ ዋዜማ ዕለት ከሁሉ የሚበልጠው(ሊቅ) ራእየ ዮሐንስን በቀትር ጊዜ ያንብብ፡፡ የቅዳሴ ዮሐንስ አፈወርቅ ሰዓት ሲደርስም ‹አሌዕለከ› በሚለው ፋንታ ‹ይትነሣእ እግዚአብሔር› የሚለውን ይበል፡፡ ‹ሐዳፌ ነፍስ› የሚለውን ግን አይበል፡፡ ወደ ቤታቸውም አይሂዱ፣ ነገር ግን ወንጌላትንና መዝሙራትን፣ ጸሎታትንም ሁሉ እያነበቡ በቤተ ክርስቲያን ይደሩ እንጂ፡፡ አንደኛውም ወንጌለ ዮሐንስን በመንበሩ ላይ ያንብብ፤ ከዚያም ቄሱ ሥዕለ ስቅለቱን ከማንሣቱ በፊት ይጠን፡፡ ካህናቱም አፈወርቅንና መጽሐፈ ምሥጢርን ያንብቡ፡፡ ከዚያም ሙሉውን መዝሙረ ዳዊት ከወንጌልና ከጸዋትው ጋር ልክ እንደ ዕለታተ ሰሙነ ሕማማት አድርገው ያድርሱ፡፡
ያን ጊዜም ዲያቆኑ ከወንጌል በፊት ከመዝሙረ ዳዊት ‹ወተንሥአ እግዚአብሔር› የሚለውን ይስበክ፡፡ ሦስት ወንጌላትንም ያንብቡ፡፡ አንደኛው ወንጌልም ለቁርባን ሰዓት ይቆይ፡፡ በዕለቱም መምህሩ ይቀድስ፡፡ እርሱም ካልቻለ በዕለተ ዓርብ ወንጌሉን ያደረሰው ይቀድስ፡፡ በትንሣኤ ምሽትም ካህናቱ በረከት ለመቀበል ተሰብስበው ‹ተስኢነነ› እንዲሉ ሥርዓት አለ፡፡ ይህም ከሌለ ደግሞ ‹እግዚአብሔር ነግሠ› አለ፡፡ ከፋሲካ ዋዜማ እስከ ግብር ፍጻሜ ድረስ ቡራኬ አለ፡፡ ይኼውም ‹ግብር ዘወሀብከኒ ዘውእቱ ጸጋ ዘአብ› የሚለው ነው፡፡ ከጾሙ እስከ ወርኃ ፋሲካ የሚሆነውን ‹ሥርዓተ ከኒሳ› ተፈጸመ፡፡ ነገር ማብዛቱን ትተን በአጭሩ አቀረብነው፡፡

በትግራይ የእምባስነይቲ ህዝብ ቅሬታውን በሰልፍ ገለፀ – VOA



በትግራይ ክልል የእምባስነይቲ ህዝብ ቀድሞ የነበረውን ወረዳ እንዲመለስለት ከ20 ዓመታት በላይ ጠይቆ አወንታዊ መልስ ባለማግኘቱ ምክንያት የተሰማውን ቅሬታ ትላንት በሰላማዊ ሰልፍ ገልጿል። መንግስት የቆየውን ወረዳችን የማይመልስልን ከሆነ ከወረዳ እስከ ተወካዮች ምክር ቤት የወከልናቸውን ሰዎች ከዛሬ ጀምሮ ውክልናችን ማንሳታችን እንገልፃለን ብሏል ህዝቡ።

እንግሊዙ‬ ዕለታዊ ጋዜጣ 18 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን በድርቅ መጠቃታቸውን ገለጸ – የፍኖተ ዴሞክራሲ ራድዮ አጫጭር ዜናዎች April 26, 2016 |



ሚያዚያ 17 ቀን 2008 ዓ.ም.ዜና (April 25, 2016 NEWS)

‪#‎የእንግሊዙ‬ ዕለታዊ ጋዜጣ 18 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን በድርቅ መጠቃታቸውን ገለጸ
‪#‎በጋምቤላ‬ ተቃውሟቸውን ለማሰማት በወጡት ዜጎች ላይ የወያኔ ወታደሮች ግድያና የአካል ጉዳት አደረሱ
‪#‎የግብጹ‬ ሲሲ ሰላማዊ ሰልፍ አደራጆችን አስጠነቀቁ
‪#‎በብሩንዲ‬ የተናጠል ግድያው እየቀጠለ መሆኑ ተነገረ
‪#‎የዳርፉር‬ ግዛት በአምስት አሰተዳድር ክልሎች እንድትከፋፈል ሕዝቡ አጽድቋል በማለት የሱዳን መንግስት መግለጫ ሰጠ

ሚያዚያ 17 ቀን 2008 ዓ.ም.

Ø የእንግሊዙ ዕለታዊ ጋዘጣ ዘ ቴሌግራፍ የእርዳታ ድርቶችንና በመስክ ላይ ያሉ ሰራተኞችን ጠቅሶ እንደዘገበው በኢትዮጵያ ያለው ድርቅና ረሃብ ከ18 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያንን እያጠቃ መሆኑን ግልጽ አድርጓል። እስከ አሁን ድረስ በወያኔና በዕርዳታ ድርጅቶች በኩል የረሃብና የድርቁ ተረጅ ወገኖች ቁጥር እስከ 12 ሚሊዮን ይገመት እንደነበር ይታወቃል። በአዲሱ አሀዝ መሠረት ከኢትዮጵያ ሕዝብ 20 ከመቶ የሚሆነው በአሁኑ ጊዜ የእርዳታ ፈላጊ አድርጎታል። የወያኔ ባለስልጣኖች የተረጅውን ሕዝብ ቁጥር መጨመር ደፍረው ባያናግሩትም የዓለም አቀፉ ኅብረተሰብ ለረሃብና ለድርቁ የሚሰጠው ዕርዳታ ከተረጅው ቁጥር ጋር አይመጣጠንም በማለት አድበስብሰው ለማለፍ ሙከራ እያደረጉ መሆኑ እየተነገረ ነው።
File Photo
File Photo

Ø በጋምቤላ ከደቡብ ሱዳን የመጡ ታጣቂዎች በመቶ የሚቆጠሩ ገድለው በመቶ በሚቆጠሩ ህጻናት አፍነው ከወሰዱና በሺ የሚቆጠሩ ከብቶችን ከነዱ ወዲህ በጋምቤላ ያለው ዘግናኝ እልቂት የዓለም ሕዝብ ዓይንና ጆሮ እየሳበ ነው። በጃዊ ስደተኛ ጣቢያ አቅራቢያ አንድ ኢትዮጵያዊ አሽከርካሪ የደቡብ ሱዳን ስደተኛ ላይ የመኪና አደጋ በማድረሰ ህይወቱ እንዲያልፍ አድርጓል በሚል ምክንያት በካምፕ ውስጥ የነበሩት ስደተኛች አብዛኞቹ የኦሮሞ እና የአማራ ተወላጅ የሆኑ ኢትዮጵያውያንን በአሰቃቂ ሁኔታ መግደላቸው የሚታወስ ሲሆን ድርጊቱን ለመቃወም አደባባይ በወጡ ዜጎች ላይ የወያኔ ፖሊሶችና ወታደሮች በወሰዱት እርምጃ ግድያና የመቁሰል አደጋ ማድረሳችው ታውቋል። ለተቃውሞ ከወጡት መካከል 5 መገደላቸውና ከ 15 በላይ መቁሰላቸው ተገልጿል። በጋምቤላ ውጥረቱ እየከረረ ሲሆን ቁጣውም እየባሰ መምጣቱ ይነገራል ወያኔ በስደተኞቹ ስም የሚሰጠው ገንዘብ እንዳይጓደልበት ጥቃቱን ችላ ከማለቱም በላይ እያባባሰው ይገኛል።
Ø በግብጽ በተለያዩ ቡድኖች የተድራጀና የተቀናጀ ከፍተኛ የሆነ የተቃውሞ ስልፍ መታቀዱን ተከትሎ የአገሪቷ ፕሬዚዳንት ሲሲ ሰልፉን ለማስቆም በቴሌቪዥን ከባድ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል። የግብጽ ሕዝብ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአገሪቱ የኢኮኖሚ ሁኔታ መዳከምና እንዲሁም የጸጥታ ኃይሎች በሰላማዊ ሕዝብ ላይ በሚወስዱት አፈና ምክንያት መማረሩን በመግለጸ ተቃውሞ እያሰማ ሲሆን ከጥቂት ሳምንታት በፊት ሁለት በግብጽ ቁጥጥር ስር ያሉ ደሴቶችን የሲሲ መንግስት ለሳኡዲ አረቢያ መስጠቱ ደግሞ ምሬቱ ይበልጥ እንዲባባስ አድርጎታል። የተለያዩ ቡድኖች የተቃውሞ ስልፍ ለማድረግ መወጣናቸው በመታወቁና ሰልፉም ሊያስከትለው የሚችለው ከፍተኛ ችግር ስጋት ስለፈጠረ ፕሬዚዳንት ሲሲ በይፋ ማስጠንቀቁያ መስጠት ተገደዋል። በንግግራቸው ላይ “የግብጽን መጥፋት የሚፈልጉ ኃይሎች እንደገና ጸጥታዋን ለማድፍረስ እየተዘጋጁ ነው ካሉ በኋላ የኛ ተግባር የህዝቡን ደህንነትና ጸጥታ መጠበቅ ስለሆነ አስፈላጊውን ርምጃ እንወስዳለን” ብለዋል። የጸጥታ ኃይሎች በተለያዩ ቦታዎች የተሰማሩ ሲሆን ሰላማዊ ስልፎችን ያደራጃሉ፤ ግለሰቦችን ይቀሰቅሳሉ ብለው የሚገምቷቸውን ግልሰሰቦችን ጋዜጠኞችንና የህግ ባለሙያዎችን ከየቤታቸው በመልቀም ያሰሯቸው መሆኑ ታውቋል። በወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ሲሲ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ ከ 1000 ሰዎች በላይ የተገደሉ ሲሆን ወደ 40 ሺ የሚገመቱ ሰዎች መታሰራቸውም ይነገራል።

Ø በብሩንዲ የተናጠል ግድያው እየቀጠለ መሆኑ ተገለጸ። ሰኞ ሚያዚያ 16 ቀን 2008 ዓ..ም የብሩንዲ ምክትል ፕሬዚዳንት የጸጥታ አማካሪ የሆኑት ጄኔራል ካሩዛ እና ባለቤታቸው በመኪና ልጃቸውን ትምህርት ቤት ካደረሱ በኋላ ባልታወቁ ሰዎች የተገደሉ መሆኑ ተነግሯል። ለድርጊቱ ኃላፊነቱን የወሰደ ወገን የለም። ባለፈው ነሐሴ ወር የፕሬዚዳንቱ የግል የጸጥታ ጉዳይ ኃላፊ የሆኑት ጄኔራል ማንነታቸው ባልታወቀ ሰዎች መገደላቸው አይዘነጋም። እሁድ ሚያዚያ 15 ቀንም የብሩንዲ የሰብአዊ ጉዳይ ሚኒስትር ከቤተክርስቲያን ሲወጡ ቦምብ ተወርውሮባቸው ሳይጎዱ በህይወት ሊያመልጡ ችለዋል። በብሩዲ በተለይ በከፍተኛ ባለስልጣኖችና የጦር መኮንኖች ላይ የሚካሄደው የተናጠል ግድያ የብሩንዲን ፕሬዚዳንት አስተዳደር እያናጋው ነው ተብሏል። የብሩንዲ የውስጥ ችግር ከጀመረ ጀምሮ ከ400 በላይ የሆኑ ሰዎች መገደላቸው ይታወቃል።

በተያያዘ ዜና ሄግ የሚገኘው የዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት በብሩንዲ እየተካሄዱ ባሉ ወንጀሎች ላይ ክስ ለመስረት አቃቤ ህጉ የመጀመሪያ ደረጃ ጥናትና ምርመራ እያካሄደ መሆኑ ታውቋል። የመጀመሪያ ደረጃው ጥናት እንደተጠናቀቀ ሙሉ የሆነው የምርመራና ማስረጃ የማሰባብ ስራ የሚጀመር መሆኑና ጥፋተኛ ናቸው ተብለው የሚከሰሱ ሰዎችም ለፍርድ እንደሚቀርቡ ተነግሯል።

Ø በዳርፉር ለሶስት ተከታታይ ቀኖች በተካሄደ የውሳኔ ሕዝብ ምርጫ አብዛኛው ሕዝብ ዳርፉር በአምስት ክልሎች መከፋፈሏን መደገፉን የሱዳን መንግስት ገልጿል። በመንግስቱ መግለጫ መሰረት በተካሄደው ምርጫ ድምጽ ለመስጠት ከተመዘገበው መካከል በምርጫው የተሳተፈው 97 በመቶ የሚሆነው እንደሆነ ሲነገር ድምጽ ከሰጠው መካከል ደግሞ 98 በመቶ የሚሆነው መራጭ ዳርፉር ለአምስት ክልሎች መከፋፈሏን መርጧል ተብሏል። በርክታ ተፈናቃዮች ድምጽ መስጠት በማይችሉበት ሁኔታና ኃይልና ማስፈራሪያ በሰፈነበት ሁኔታ የሚካሄድ የውሳኔ ሕዝብ ምርጫ እውነተኛ የሕዝብ ፍላጎት አያንጸባርቅም በማለት አማጽያኑ ኃይሎች ምርጫው እንዳይካሄድ አድማ ያደረጉ ሲሆን የምዕራብ አገሮችም የጸጥታው ሁኔታ ለነጻና ርቱዓዊ ምርጫ ምቹ ባለመሆኑ ምርጫው መካሄድ የለበትም ማለታቸው ይታወሳል። የሱዳን መንግስት ባለስልጣኖች ምርጫው የአረብ አገሮችና ሌሎች ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች ባሉበት የተካሄደ በመሆኑ የሕዝቡን እውነተኛ ስሜትና ፍላጎት ያንጸባርቃል እያሉ ናቸው።

መንድሜ፣ እስክንድር (አይበገሬው) ነጋ፡ ብቻህን አይደለህም እናም እንወድሀለን!


ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም    
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
ወንድማችንን እስክንድር ነጋን እናስታውስ፣
Eskinder Nega 1                                             /ዘ-ህወሀት (የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ) ታላቁ እስክንድር ነጋ ከሕዝብ ትውስታ እና ህሊና ተፍቆ እና ጠፍቶ ከማየት በላይ የሚወደው ነገር የለም፡፡ ዘ-ህወሀት ዓለም እስክንድር ነጋን እንዲረሳው ይፈልጋል፡፡ የእርሱ ትዝታ እየደበዘዘ ሙሉ በሙሉ እንዲጠፋ ይፈልጋሉ፡፡ እርሱ መታወስ ያለበት ከሆነ ደግሞ የዓለም ሕዝብ እርሱን በአሸባሪነት ማስታወስ እንደሚኖርበት ይፈልጋሉ፡፡
የእስክንድር ጉዳይ እ.ኤ.አ በ1964 በደቡብ አፍሪካ የጥቂት ነጮች ዘረኛ የበላይ አገዛዝ አፓርታይድ ኔልሰን ማንዴላን አሸባሪ በማለት በሀሰት በመወንጀል የእድሜ ልክ እስራት በመበየን ወደ ሮቢን ደሴት የማጎሪያ እስር ቤት ወስደው ዘብጥያ ካወረዷቸው ጋር አንድ ዓይነት ነው፡፡ ማንዴላ ከ27 ዓመታት የአፓርታይድ የእስራት ጊዜ በኋላ ከማጎሪያው እስር ቤት በመውጣት ደቡብ አፍሪካን ከመጥፎ አደጋ አድነዋታል፡፡
አናሳው የደቡብ አፍሪካ የጥቂት ነጮች የበላይነት አገዛዝ አፓርታይድ ማንዴላን ከሕዝብ ትውስታ ሰውሮ በማቆየት ጥረቱ ላይ ስኬታማ ሳይሆን ቀርቷል፡፡ ዘ-ህወሀትም በተመሳሳይ መልኩ እስክንድር ነጋን ከሕዝብ ትውስታ ለማጥፋት ከቶውንም አይችልም፡፡ እስክንድር ነጋ ከማጎሪያው እስር ቤት ይወጣል፣ ወዲያውኑም የእርሱን ቦታ አሳሪዎቹ ተክተው ይወስዳሉ፡፡
የእስክንድር ነጋ ምስል፣ ጽሑፎች እና ሌሎች የትችት ስራዎቹ እና በረከቶቹ ሁሉ በማህበራዊ ሜዲያዎች እና በበርካታ ድረ ገጾች ታላቅ ክብር ባላቸው ዓለም አቀፍ የፕሬስ እና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ጭምር ይወጣል፡፡ ከሳምንት በፊት አንድ ዓለም አቀፍ ድርጅት የእስክንድር እስራት በሕገወጥ መልኩ እና በዘ-ህወሀት አጭበርባሪነት መሆኑን ገልጾ  በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቀቅ ጥሪ አቅርቧል፡፡
የእስክንድር ነጋ ምስል በማህበራዊ ድረ ገጼ አናት ላይ ይገኛል፡፡ በእኔ ማህበራዊ ድረ ገጽ (https://www.facebook.com/al.mariam) እኔን የማይመስል ምስል እንዳለ ሰው ሳይጠይቀኝ የዋለበት ጊዜ የለም፡፡ አትጨነቁ እያልኩ እንደህ በማለት እነግራቸዋለሁ፡፡ “ያ የወንድሜ የእስክንድር ነጋ ምስል ነው!”
አንባቢዎቼ ጥቂት ውለታዎችን እንድታደርጉልኝ በትህትና እጠይቃለሁ፡፡
ይህንን ትችት ከማንበባችሁ በፊት የእስክንድርን የእጅ ጽሑፍ እና የዘ-ህወሀት የማጎሪያ እስር እየተባለ ከሚጠራው እስር ቤት ቤት የተጻፈውን ደብዳቤ እንድታነቡት እጠይቃለሁ፡፡ (ይህንን ደብዳቤ ለማንበብ በእንግሊዘኛ  እዚህ ጋ ይጫኑ፡፡)
(**የእስክንድርን የእጅ ጽሑፍ ደብዳቤ በማያቋርጥ መልኩ በዘ-ህወሀት የማጎሪያ እስር ቤት ዘበኞች እና ሰላዮች ክትትል ስር ሆኖ ይህንን የመሰለውን ጠንካራ ሀሳቡን ለመግለጽ ባደረገው ልዩ የሆነ ጥረት ምክንያት የኮምፒውተር የፊደላት መክተቢያ ቆልፎችን ሳንጠቀም ለክብሩ ስንል እንዳለ አቅርበነዋል፡፡)
ከዚህም በተጨማሪ በዋሺንግተን ፖስት ጋዜጠኛ በካርል በርነስተይን (እ.ኤ.አ ነሐሴ1974 የዋተርጌትን ቅሌት ያጋለጠው እና ፕሬዚዳንት ሪቻርድ ኒክሰንን ከስልጣናቸው በገዛ ፈቃዳቸው እንዲለቁ ያደረጋቸው እና በዓለም ላይ ታላቅ እውቅና ያለው ጋዜጠኛ) እና ሌቭ ሽሬበር (እ.ኤ.አ የ2016 የኦስካር ምርጥ ስዕሎች አሸናፊ የሆነው እና የተከበረ ዳይሬክተር፣ ያዘጋጁትን ተንቀሳቃሽ ፊልም አንባቢዎቼ እንዲመለከቱት እጠይቃለሁ፡፡
(የቪዲዮ ምስሉን ለመመልከት እዚህ ጋ ይጫኑ ፡፡ ካርል በርንስተይን እና ሌቭ ሽሬበር አሸባሪን ለመከላከል ብለው እንደዚህ ያለ በፍቅር የተሞላ መሳጭ ንግግር ያደርጋሉን?) 
ከሁሉም በላይ ደግሞ በእስክንድር ነጋ ላይ በባለቤቱ በሰርካለም ፋሲል (እርሷም የተከበረ የጋዜጠኝነት ሽልማት አሸናፊ ኢትዮጵያዊት ጋዜጠኛ እና ለመብቷ በአንድ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ ለፕሬስ ነጻነት መከላከል ከባለቤቷ ጋር ታስራ የነበረችው) አማካይነት (በእንግሊዝኛ ንኡስ ርዕሶች) የተዘጋጀውን እና ልብ የሚሰብረውን የ3 ደቂቃ የቪዲዮ ፊልም አንባቢዎቼ እንዲመለከቱት እጠይቃለሁ፡፡ (የቪዲዮኑን ፊልም  እዚህ ጋ በመጫን  መመልከት ይችላሉ፡፡)
ሰርካለም ልጇን ናፍቆትን በዘ-ህወሀት የማጎሪያ እስር ቤት እ.ኤ.አ በ2007 ተገላግላለች፡፡
Amnesty 4እስክንድርን ወንድሜ ብዬ ስጠራ እና ሰርካለምን እህቴ ብዬ ስጠራ ኩራት ይሰማኛል፡፡ በእነርሱ መስዋዕትነት፣ በእነርሱ ድፍረት፣ ጽናት እና አይበገሬ ታማኝነት እና በእነርሱ ግላዊ አርአያነት እራሴን ዝቅ አድርጌ እመለከታለሁ፡፡
እስክንድር ነጋ እና ሰርካለም ለኢትዮጵያ ምርጦች እና ባለብሩህ አእምሮ ጋዜጠኞች፣ ለሰላማዊ አማጺዎች፣ በዘ-ህወሀት ግልጽ እና ድብቅ የማጎሪያ እስር ቤቶች ውስጥ በመማቀቅ ላይ ለሚገኙት የፖለቲካ እና የሲቪክ ማህበረሰብ መሪዎች እና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች አርአያ እና ቀንዲል ናቸው፡፡ እስክንድር ነጋን በማስብበት ጊዜ በቀለ ገርባን፣ አህመዲን ጀቤልን፣ ውብሸት ታዬን፣ ተመስገን ደሳለኝን፣ አንዷለም አራጌን፣ አንዳርጋቸው ጽጌን፣ እማዋይሽ ዓለሙን፣ ዴልዴሳ ዋቆ ጃርሶን፣ አኬሎ አቆይ ኡቹላን፣ የዞን ዘጠኝ ጦማርያንን እና በሺዎች የሚቆጠሩትን የሌሎችን የፖለቲካ እስረኞችንም በተጨማሪ አስባለሁ፡፡
እስክንድር ነጋን በምናስብበት ጊዜ ሁሉንም በሙሉ እናስታውሳለን!
የእስክንድር ነጋ የፍርድ ቤት ሂደት እና ስቃይ፣
እስክንድር ነጋ ልዩ የሆነ ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ እና በኢትዮጵያ ጽኑ የፕሬስ ነጻነት ተሟጋች  ነው፡፡ እ.ኤ.አ ከ1993 ጀምሮ የዘ-ህወሀት ፍርሀት የለሽ ተቺ ነው፡፡ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ውስጥ እስክንድር እና ባለቤቱ ሰርካለም በዘ-ህወሀት የተዘጉ ጋዜጦችን ማለትም ኢትዮጲስ፣ አስኳል፣ ሳተናው እና ምኒልክን ጨምሮ የተለያዩ ጋዜጦችን እያቋቋሙ መስራት ጀምረው ነበር፡፡
እ.ኤ.አ በ2011 በዘ-ህወሀት በቁጥጥር ስር ውሎ ወደማጎሪያው እስር ቤት እስከገባበት ጊዜ  ድረስ እስክንድር እረፍትየለሽ በኢትዮጵያ ዲያስፖራ ዘንድ ሰፊ አንባቢ ያለው ጦማሪ ነበር፡፡ ዘ-ህወሀትን በተለይም አሁን በህይወት የሌለውን መሪውን አምባገነኑን መለስ ዜናዊን ስልጣንን ከሕግ አግባብ ውጭ መጠቀምን፣ ሙስና እና የመልካም አስተዳደር እጦት ጉዳዮች ላይ ግንባሩን ሳያጥፍ ፊት ለፊት ይታገል ነበር፡፡ ዘ-ህወሀት እስክንድር ነጋን ለመቁጠር በሚያዳግት ለበርካታ ጊዚያት በሸፍጥ ውንጀላ ክስ እየመሰረተ በማጎሪያው እስር ቤት ሲያስረው ቆይቷል፡፡
ዘ-ህወሀት እስክንድርን እ.ኤ.አ በ2011 አሸባሪነት የሚል የሸፍጥ ክስ በመመስረት ወደ ማጎሪያው እስር ቤት ዘብጥያ ወረወረው፡፡ የእርሱ ወንጀል ሆኖ የተቆጠረው፣
1ኛ) በፕሬስ ነጻነት ላይ ጭቆና እያራመደ ያለውን ዘ-ህወሀትን መተቸቱ፣
2ኛ) ዜጠኞች በጅምላ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ እየተደረጉ ወደ ዘብጥያ መጣልን በመቃወሙ፣
3ኛ) የዓረብ የጸደይ አብዮት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖረውን እንደምታ ለኢትዮጵያ ህዝብ ማወያየቱ ነበር፡፡
ዘ-ህወሀት እስክንድር የአሸባሪ ቡድን አባል ነው፣ ለውጭ ኃይሎች ሰላይ ነው፣ እናም በኢትዮጵያ ላይ የሚደረገውን የአሸባሪዎች ጥቃት ለማሳለጥ የተዘጋጀ አሸባሪ ነው በማለት በእስክንድር ላይ ስም የማጥፋት እና የማጠልሸት ያልተሳካ የፕሮፓጋንዳ ሙከራ ዘመቻውን ለማሳየት ሞከረ፡፡
አሁን በህይወት የሌለው አምባገነኑ መለስ ዜናዊ በግል በእስክንድር ላይ ከፍተኛ የሆነ ጥላቻ እንደነበረው ታማዕኒነት ያላቸው መረጃዎች አሉኝ፡፡ መለስ እስክንድር እንደሚያደርገው በተስፋ የተሞላ ንግግር ዓይነት ማድረጉን አይደግፍም፡፡
እስክንድር ለአምባገነኑ ለመለስ ቅንጣት የምታህል ፍርሀት አያሳይም፡፡ እስክንድር ስለመለስ የፈለገውን ያህል የሚመጣ ነገር ቢኖርም ባይኖርም በእራስ መተማመን ስሜት ይናገራል፡፡
አምባገነኑ መለስ እስክንድርን ይጠላዋል ምክንያቱም ይፈራዋል፡፡ አምባገነኑ መለስ የእስክንድርን ብዕር ይፈራዋል ምክንያቱም የእስክንድር ብዕር በመለስ ላይ ያለውን ያልተቀባባውን ደረቅ እውነታ መዞ ያወጣልና፡፡
አምባገነኑ መለስ ዜናዊ በርካታ ነገሮችን መከላከል ይችላል፡፡ ሆኖም ግን እውነትን መከላከል ፈጥሞ አይችልም፡፡
እ.ኤ.አ በመስከረም 2010 እስክንድር እና ሰርካለም የኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ለሆኑት ለሊ ቦሊንገር ደብዳቤ በመጻፍ ስለአምባገነኑ መለስ ያለውን እውነታ ተናግረዋል፡፡ በዚያ ደብዳቤ እስክንድር እና ሰርካለም አምባገነኑ መለስ ዜናዊ በእነርሱ ላይ በግል እና በፕሬስ ነጻነት ላይ የሰራቸውን ወንጀሎች በሙሉ ዘርዝረው አቅርበዋል፡፡ ለአምባገነኑ መለስ ዜናዊ ጥሪ እንዳይደረግለት እንዲህ የሚል ተመጽዕኖ አቅርበዋል፣ “በሀገሩ የመናገር ነጻነትን በትጋት የሚደፈጥጥ መሪ የእራሱን ሀሳብ በክብር ለመግለጽ በነሐሴ ወር በኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ የሚደረገውን ጉባኤ በጉጉት በመጠባበቅ ላይ ይገኛል፡፡“
እ.ኤ.አ መጋቢት 2011 “ግልጽ ደብዳቤ ለጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ” በሚል ርዕስ እስክንድር ለአምባገነኑ መለስ እውነታውን እስከ ጥርሱ ድረስ ነግሮታል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ አምባገነኑ መለስ ምናልባትም ስሙን መለስ ከሀዲው በሚል በመቀየር ባታላይነቱ እና በከሀዲነቱ ለበርካታዎቹ ለዘ-ህወሀት ለታገሉ እና ለሞቱ ጓደኞቹ እንዲህ የሚል የነብይነት ከሀዲ ዕጣ ፈንታውን በትክክል ይገልጻል፡
“ማናቸውም መሪዎች [ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ሥላሴ፣ ወታደራዊው ጠንካራው መንግስቱ ኃይለማርያም እናም ሌሎችም የአሜሪካ ፕሬዚዳንቶች] ኢትዮጵያዊ ወይም ደግሞ አሜሪካዊም ቢሆኑ መለስ ዜናዊ እንዳደረገው ሁሉ በንዴት የሚጦፉ እና ስሜታዊነት የሚያጠቃቸው እና የጓደኝነት ምግባራቸውን ሊመለስ በማይችል መልኩ ሊያቋርጡ ይችላሉ፡፡ በመለስ ዜናዊ እና በስዬ አብረሃእንዲሁም በሌሎች መካከል የጠፋው ጓደኝነት በጣም አስቸጋሪ በሆነው ጊዜ ለሶስት አስርት ዓመታት ዘልቋል፡፡ አዲስ ጓደኞች በጠፉት በሌሎች የሚሸፈነውን ክፍተት ሊሞሉ አይችሉም፡፡ ሆኖም ግን አውሪያዊ ስሜታዊነት እና ከብቸኝነት ሊመጣ የሚችለው ባህሪ ግን ትንሹ የመለስ መገለጫ ነው፡፡“
በዚያ አንቀጽ ላይ የሰፈረው እውነታ የመለስን ውስጣዊ ባህሪ እንዴት እንደሚነጣጥለው ማሰብ እችላለሁ፡፡ አምባገነኑ መለስ በቅርብ ጓደኞቹ እና በወታደራዊ ጓደኞቹ ላይ ያደረገውን ነገር የሚያውቅ እና ጸጸትም የሚሰማው ነው ይባላል፡፡ (መለስ ለተፈጸመ ስቃይ እና መከራ ምንም ዓይነት ጸጸት እና ርህራሄ አለው ብዬ አላምንም፡፡) ሆኖም ግን ጸጸት እና ርህራሄ የሚኖረው ቢሆን እንኳን እንዲህ የሚለውን የሸክስፒርን ጥልቅ የግጥም ስሜት የሚያስብ ከሆነ በጣም የሚገርመኝ ይሆናል፡ “…እራሴን አከበርኩ እናም ለዕጣ ፈንታዬ ቃል ገባሁ፣/በተስፋ አንዱ ዋና ከበርቴ ለመሆን፣/ እንደ እርሱ ለመሆን፣ እርሱ እንዳሉት ጓደኞች ለመሆን…“ አምባገነኑ መለስ ጠላት እንጅ ጓደኞች አልነበሩትም፡፡
በዚያው ደብዳቤ ላይ እስክንድር ለአምባገነኑ መለስ ወደፊት ማለቱን ትቶ ስልጣኑን እንዲለቅ እንዲህ በማለት ነግሮታል፡
“አቶ መለስ ዜናዊ፡ አንተ ከስልጣንህ እንድትወርድ እና ቢሮህን እንድትለቅ ሕዝቡ ይፈልጋል፣ ሕዝቡ አንተን አይፈልግም፡፡ በአሁኑ ጊዜ ይህንን ደብዳቤ እየጻፍኩ ባለበት ጊዜ ህዝቡ በሰሜን አፍሪካ እየተፈጸመ ያለውን ክስተት በቅርበት በመመልከት ላይ ነው፡፡ ሕዝቡ በአፍሪካ ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ በሚኖሩት እንደምታዎች ላይ በመከራከር ላይ ይገኛል፡፡ እናም በተራዎቹ ሊቢያውን ጀግንነት ላይ በመደመም ላይ ይገኛሉ፡፡ ጊዜው ከመምሸቱ በፊት ሕዝቡን አዳምጥ፡፡“
እ.ኤ.አ ሐምሌ 2011 የጭቆና አገዛዝ ወደ ታሪክ ቆሻሻ ቅርጫት ውስጥ ይጣላል፣ እናም ዴሞክራሲ በዘ-ህወሀት አመድ ላይ በኢትዮጵያ ውስጥ ያብባል በማለት እስክንድር ለመለስ እንዲህ ሲል በአጽንኦ ነግሮታል፡
“ዴሞክራሲ የሰው ልጆች ሁሉ የጋራ ዕጣፈንታ ነው፡፡ ኤስኪሞ ወይም ደግሞ ዙሉ፣ ክርሰቲያን ወይም ሙስሊም፣ ነጭ ወይም ጥቁር፣ የሰለጠነ ወይም በማደግ ላይ ያለ ብትሆንም እንኳ ልታስወግደው አትችልም፡፡ በእርግጠኝነት ይኸ ጉዳይ ዓለም አቀፋዊ ክስተት ነው፡፡ እናም ከረዥም ጉዞ በኋላ የኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ ትግል እውን ለመሆን በማዕዘኑ አካባቢ በመዞር ላይ ይገኛል፡፡ ሁላችንም በዚያ አካባቢ ነን፡፡ ነጻ እንሆናለን!“
እ.ኤ.አ ነሐሴ 2011 ነገሮች ሁሉ አሁን ባሉበት ሁኔታ የሚቀጥሉ ከሆነ መለስ የጋዳፊን ዓይነት አስፈሪ ዕጣ ፈንታ እንደሚገጥመው እንዲህ በማለት አስጠንቅቆት ነበር፡
“የአፍሪካን ግዙፍ አምባገነናዊ አገዛዝ የሚመራው የኢትዮጵያው መለስ ዜናዊ በርካታዎቹ እንደሚጠረጥሩት በመጀመሪያ ጋዳፊ እንዳደረገው ስሌት በመስራት ጽኑ ማስታወሻ ይይዛል…እናም የዓረቡ ዓለም ታላቋ አምባገነን ግብጽ በሙባረክ የአገዛዝ ዘመን እንደሆነችው የጸደይ አብዮት ወርቃማ ሽልማት እንደሆነችው ሁሉ የሰብ ሰሀራ ታላቋ አምባገነን ኢትዮጵያም በተመሳሳይ መልኩ የአፍሪካ የጸደይ አብዮት ሽልማት ትሆናለች፡፡ ካለግብጽ የዓረቡ ዓለም የጸደይ አብዮት ሊኖር አይችልም ነበር፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ከኢትዮጵያ ውጭ የአፍሪካ የጸደይ አብዮት ሊኖር አይችልም፡፡“
እስክንድር እ.ኤ.አ መስከረም 2/2011 አምባገነኑ መለስ ዜናዊ ለሰላማዊ የለውጥ ሽግግር እንቅፋት እንዳይሆን እንዲህ በማለት መክሮት ነበር፡
“ለበርካታ ዘመናት ሰላማዊ ሽግግር ባለመኖሩ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ውድቀት፣ ምናልባትም አደገኛ የሆነ የኃይል እርምጃ የማይቀር ጉዳይ ነው፡፡ ማለት የተፈለገው የነበረው ሁኔታ በነበረበት መልኩ ሊቀጥል ከማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ በኢትዮጵያ ሰላማዊ እና ሕጋዊ የለውጥ እርምጃ ለማድረግ ጥሪ የሚደረግበት ጊዜ ደርሷል፡፡ ታሪክ ላልተወሰነ ጊዜ ሊተላለፍ የሚችልበት ሁኔታ ሊኖር አይችልም፡፡“
እ.ኤ.አ መስከረም 14/2011 እስክንድር በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡
እ.ኤ.አ ሐምሌ 13/2012 እስክንድር በዘ-ህወሀት የይስሙላ የዝንጀሮው ፍርድ ቤት የ18 ዓመታት እስራት ተበየነበት፡፡
ዘ-ህወሀት በእስክንድር ላይ የአሸባሪነት ወንጀል ማስረጃ ይሆነኛል ብሎ ያቀረበው በጥራት ያልተቀዳ በአንድ በከተማ አዳራሽ ለተሰበሰበሰ ሕዝብ የዓረቡ የጸደይ አብዮት በኢትዮጵያ ላይ ስለሚኖረው እንደምታ በሚል ርዕስ እስክንድር ያቀረበውን ንግግር ነበር፡፡
እ.ኤ.አ ነሐሴ 20/2012 አምባገነኑ መለስ መሞቱ ይፋ ሆነ፡፡
የኢትዮጵያ ሳቴላይት ቴሌቪዥን እ.ኤ.አ ሐምሌ 20/2012 (እ.ኢ.አ ደግሞ ሐምሌ 13 ቀን 2004) አምባገነኑ መለስ መሞቱን ይፋ አደረገ፡፡
ቅዱሳን ጽሑፎች አምላክ “ሚስጥራዊ በሆነ መንገድ” ስራውን ይሰራል ይላሉ፡፡
አምባገነኑ መለስ ዜናዊ እስክንድርን የሚጠላው በሚያሳየው ድፍረት፣ ፍርሀትየለሽነት እና ባለው ጽናት ምክንያት ብቻ ኤደለም፡፡ ሆኖም ግን መለስ በእስክንድር ምሁራዊ ክህሎት ላይ ቅናት ያድርበት እንደነበር ጭምር ያሉኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
ባለፉት አስር ዓመታት በተደጋጋሚ ስናገረው እንደቆየሁት መለስ የእራሱን ልዩ ክህሎት ተጠቅሞ እና የነገሮችን ውልመሰረት አጢኖ ዓለም አቀፍ ዲፕሎማቶችን ማሳመን የሚችል ጎበዝ አፈ ምላጭ የውሸት ምሁር ነው፡፡ መለስ ፍሬከርስኪ ስለሆኑ እና ምንም ዓይነት እርባና ስለሌላቸው ነገሮች ብዙ የማውራት ተሰጥኦ የነበረው አጭበርበሪ ከመሆን የዘለለ ሰው አልነበረም፡፡ የቀድሞው በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የነበሩትን ዶናልድ ያማማቶን እንዲህ በማለት በዊኪሊክስ በተለቀቀው መልዕክት የተታለሉ መሆናቸው ግልጽ ሆኗል፣ “በበርካታ አጋጣሚዎች መለስ ዝርዝር የሆኑ ምላሾችን በመስጠት ስለአንድ ጉዳይ አሳሳቢ ሁኔታ ያለባቸውን ቡድኖች በአንድ መስመር ላይ የማሰለፍ ችሎታ እንዳለው ተመልክተናል፡፡“ ቡድኖችን በአንድ መስመር ማሰለፍ እና በቀላሉ የሚሞኙ የምዕራብ ሀገሮች ዲፕሎማቶችን ማቅረብ የመለስ ዋናው ድብቅ ሚስጥር ነው፡፡ መለስን በሚገባ ለሚያውቁ የለየለት አታላይ መሆኑን በውል ይገነዘባሉ፡፡ እስክንድርም ይህንን ነገር አሳምሮ ያውቃል፡፡ መለስ እንደሚበሳጭ የውኃ ተርብ ዓይነት እንደሆነ አምናለሁ፡፡ ይቆጣል፣ ወዲያው ወዲያው በፍጥነት ይተነፍሳል እናም በላይ ያሉት የአካል ክፍሎቹ ሁሉ ይንቀጠቀጣሉ፡፡ ሆኖም ግን ከተቃዋሚዎቹ ጋር ፊት ለፊት ተገናኝቶ በመከራከር እና በመወያየት ተግባራት ላይ አይሰማራም፡፡
ለመሆኑ እስክንድር ነጋ ማን ነው?
እስክንድር ነጋን ለመግለጽ ቀላል እና እጅግ በጣም አስቸጋሪ ነገር ነው፡፡ እስክንድር የኢትዮጵያ ታዋቂ ጋዜጠኛ እና የፖለቲካ እስረኛ ነው፡፡
እ.ኤ.አ ሰኔ 2013 አምነስቲ ኢንተርናሽናል የተባለው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት እስክንድር ነጋ “የህሊና እስረኛ” ነው የሚል መግለጫ አውጥቷል፡፡ የጋዜጠኞች ተከላካይ ኮሚቴ በተመሳሳይ መልኩ እስክንድር የህሊና እስረኛ ለመሆኑ እውቅና ሰጥቷል፡፡ ሌሎች ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች እና የፕሬስ ድርጅቶች ተመሳሳይ የሆኑ መግለጫዎችን አውጥተዋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ እስክንድር በጽናት፣ በምክንያታዊነት እና የፕሬስ ነጻነትን በመከላክል ረገድ በርካታ የሆኑ ዓለም አቀፍ የፕሬስ ሽልማቶችን አሸናፊ ነው፡፡
እስክንድር ከላይ የተጠቀሱትን ነገሮች ሁሉ እና ሌላም ተጨማሪ ነገር ነው፡፡
እስክንድር ነጋ ለእኔ ልዩ ጀግናዬ የሆነው በርካታ ጽሑፎች መጻፍ በመጀመሩ፣ የፕሬስ ነጻነትን ለማስከበር ፍርሀት የለሽ በመሆኑ፣ ወይም ደግሞ ለእርሱ የሚገባውን ዓለም አቀፍ ክብር እና ዝናን በመጎናጸፉ ምክንያት አይደለም፡፡
እስክንድር ለእኔ ልዩ ጀግናዬ ነው ምክንይቱም የመጀመሪያውን ደረጃ የያዘ የነጻነት ታጋይ ነው፡፡ ለመታገል ግን ጠብመንጃ፣ ቢላዋዎችን ወይም ሽብርን አይዝም፡፡
የእርሱ ምርጡ መሳሪያዎቹ ቁራጭ እርሳስ ወይም ደግሞ ብዕር ናቸው፡፡ የእርሱ ብዕር  እውነትን ዘክዝኮ በመትፋት ዘ-ህወሀትን ሽባ የሚያደርግ እና ግራ የሚያጋባ ክስተትን መፍጠር ነው፡፡ የእርሱ ሀሳቦች ተፈጥሯዊ ኃይል አላቸው፡፡
እስክንድር ውሸትን፣ ሙስናን፣ ከሕግ አግባብ ውጭ ስልጣንን መጠቀምን እና ሕገወጥነትን በእውነት ጎራዴ በመጠቀም የሚመትር ጀግና ነው፡፡
ብዕርን ብቻ በመታጠቅ እስክንድር ጨለምተኝነትን በተስፋ፣ ፍርሀትን በድፍረት፣ ቁጣን በምክንያታዊነት፣ እብሪትን በትህትና፣ ድንቁርናን በእውቀት፣ አለመቻቻልን በትዕግስት፣ ጭቆናን በጽናት፣ ጥርጣሬን በእምነት እና ጥላቻን በፍቅር ይዋጋል፡፡
ሆኖም ግን እስክንድር በብዕር ከመዋጋትም በላይ ነው፡፡
ከዚህም በተጨማሪ እስክንድር የደፋርነት ንጉስ ነው፡፡ እስክንድር በቀልተኛ የሆኑትን የዘ-ህወሀት አውሬ ዓይኖች ከተመለከተ በኋላ እንዲህ አለ፡
“ለስምንተኛ ጊዜ በቁጥጥር ስር ልታውሉኝ እና ልታስሩኝ ትችላላችሁ፡፡ ልትደበድቡኝ፣ ልታሰቃዩኝ እና ከሌላው እስረኛ ለብቻ ነጥላችሁ ልታስሩኝ ትችላላችሁ፡፡ መከራ ልታደርሱብኝ እና የሸፍጥ ክስ በመመስረት በተንዛዛ ቀጠሮ እያመላለሳችሁ ፍዳ ልታሳዩኝ ትችላላችሁ፡፡ በሚከረፋው የማጎሪያ እስር ቤታችሁ በረሀብ እንድቀጣ እና የሕክምና አገልግሎት እንዳጣ ልታደርጉ ትችላላችሁ፡፡ ስሜን ልታጠፉ እና ባሕሪዬን ጠላሸት ለመቀባት ትችላላችሁ፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ባለቤቴን ልታዋርዷት እና የእናንተ ወሮበሎች በእኔ ላይ የሚያደርሱትን በደል እየተመለከተ ልጄ እንባ አውጥቶ ሲያለቅስ እናንተ ልትስቁ ትችላላችሁ፡፡ እኔን እና ቤተሰቤን ልታስፈራሩ፣ ልታሸማቅቁ እና ለእኛ ህይወት በመሬት ላይ ገሀነም እንድትሆን ልታደርጉ ትችላላችሁ፡፡ ሆኖም ግን ለእናንተ የጭቆና አገዛዝ፣ ለእናንተ የበከተ ሙስና፣ ለእናንተ የጭካኔ ፌሽታ፣ ለእናንተ አረመኒያዊ ድርጊት እና እንስሳዊ ኋላቀርነት ባህሪ በፍጹም በፍጹም በፍጹም አላጎበድድም፡፡ እስክንድር ነጋ እንደመሆኔ መጠን የእራሴ ዕጣ ፈንታ አዛዥ እና የህይወቴ መርከብ ነጂ/ካፒቴን ሌላ ማንም ሳይሆን እኔው እራሴ ነኝ!“
ከእስክንድር ነጋ እና ከእርሱ ባለቤት ከሰርካለም ፋሲል የበለጠ የማከብራቸው፣ የማደንቃቸው እና የማወድሳቸው በጣም ጥቂት ሰዎች አሉ፡፡ እነርሱን ለማክበር የምስጋና ደብዳቤ ጽፊያለሁ፡፡ እስክንድር፣ ሰርካለም እና ልጃቸው ናፍቆት (ቀኑ ሳይደርስ በእስር ቤት የተወለደ እና በአረመኔው በቀልተኛ በአምባገነኑ መለስ ዜናዊ ትዕዛዝ የህይወት ማዳኛ ኢንኩቤተር የተከለከለው) ናቸው፡፡
እኔ ማድረግ የምችለው ቢሆን ኖሮ እነዚህን የተከበሩ እንቁዎች የሌላ የማንም ሀገር ወይም ደግሞ ተቋም የእኔ ናቸው ብሎ እንዳይጠይቅ ለማድረግ የኢትዮጵያ ሕዝብ ብሄራዊ እሴቶች ናቸው በማለት አውጅ ነበር፡፡ በዚያ ጉዳይ ላይ ሌላ ምርጫ አይሰጣቸውም!
እስክንድርን የኢትዮጵያ የፕሬስ ነጻነት ተሟጋች አድርጌ ለመናገር አልፈልግም፡፡ ከእኔ ይልቅ ስለዚህ ሁኔታ የበለጠ ግልጽ በሆነ መልኩ ሊናገሩ የሚችሉ በርካታዎቹ አሉ፡፡
እስክንድር በዓለም ሁሉ ካሉ የፕሬስ ነጻነት ጀግናዎች ሁሉ ጀግና ነው፡፡
በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ የሆኑ ሰላማዊ አመጸኛ ጋዜጠኞች ሁሉ ስለእርሱ ተናግረዋል፣ በአስቸኳይ ከእስር ቤት እንዲለቀቅም ጠይቀዋል፡፡ ከበርካታዎቹ ጥቂቶቹ የሚከተሉትን ያካትታል፣ ኬኔት ቤስት ከላይቤሪያ፣ ሊዲያ ካቾ ከሜክሲኮ፣ ጁአን ፓብሎ ካርዲናስ ከችሌ፣ ሜይ ችዲያክ ከሊባኖስ፣ ሰር ሀሮልድ ኢቫንስ ከዩናይትድ ኪንግደም፣ አክባር ጋንጂ ከኢራን፣ አሚራ ሀስ ከእስራኤል፣ ዳውድ ክታብ ከዮርዳኖስ፣ ግዌን ሊስተር ከናሚቢያ፣ ሬይሞንድ ሎው ከደቡብ አፍሪካ፣ ቬራን ማቲክ ከሰርቢያ፣ አዳም ሚችንክ ከፖላንድ፣ ፍሬድ ሜምቤ ከዛምቢያ፣ ኒዛር ኔዩፍ ከሶርያ፣ ፓፕ ሳይኔ ከጋምቢያ፣ ፋራጅ ሳርኮሂ ከኢራን፣ ኔዲም ሴነር ከቱርክ፣ አሩን ሻውሬ ከሕንድ፣ ሪካርዶ ኡሴዳ ከፔሩ፣ ጆሴ ሩቤን ዛሞራ ከጓቲማላ ናቸው፡፡ ሌሎች የሰብአዊ መብቶች እና የፕሬስ ድርጅት መሪዎች ደግሞ የሚከተሉትን ያጠቃልላል፡ ማርክ ሀምሪክ የናሽናል ፕሬስ ክለብ ፕሬዚዳንት ከዋሺንግተን ዲ.ሲ፣ አርየህ ኔይር የኦፕን ሶሳይቲ ፋውንዴሽንስ ፕሬዚዳንት፣ ኬኔዝ ሮት የሂዩማን ራይተስ ዎች ዋና ዳይሬክተር፣ ጆኤል ሲሞን የጋዜጠኞች ተከላካይ ኮሚቴ ዋና ዳይሬክተር፣ ዊሊያም ኢስተርሊ በኒዮርክ ዩኒቨርሲሰቲ የኢኮኖሚክስ ፕሮፌሰር ናቸው፡፡
እስክንድር ነጋ፡ አይዞህ ብቻህን አይደለህም!
እስክንድር ነጋ ያልተረሳ መሆኑን እንዲያውቅ እፈልጋለሁ፡፡ ሰርካለም እና ናፍቆት እስክንድር በፍጹም የማይረሳ መሆኑን እንዲያውቁት እፈልጋለሁ፡፡ ለክብራችን እና ለነጻነታችን ሲል ከዘ-ህወሀት ግንባር ለግንባር ገጥሞ እየተፋለመልን ያለውን እንቁ ጀግና እንደምን ልንረሳው እንችላለን?
በአሁኑ ጊዜ የዓለም ሕዝብ በኢትዮጵያ በማጎሪያው እስር ቤት ውስጥ እየማቀቁ ያሉትን እስክንድር ነጋን እና ሁሉንም የፖለቲካ እስረኞች እንዲያስታውስ እፈልጋለሁ፡፡
እስከንድር ነጋን እናስታውሳለን፣ ሁልጊዜ፡፡ እስክንድር ነጋን እናደንቃለን፣ እናከብራለን፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ አስደናቂ እና አፍቃሪ ባል እና አባት በመሆኑ እስክንድር ነጋን እንወደዋለን፡፡
ከሁሉም በላይ እስክንድር ነጋ የኩሩዋ ኢትዮጵያ ልጅ በመሆኑ እናከብረዋለን፣ እናስታውሰዋለን፡፡
የሚካኤል ጃክሰንን የግጥም ስንኞች ትንሽ ለወጥ በማድረግ እኛ የእስክንድር ነጋ ወንድሞች እና አህቶች ስለእርሱ ምን እንደሚሰማን ያለንን ስሜት እንዲህ በማለት ለመግለጽ እንወዳለን፡
ብቸኛ አይደለህም አለን ከጎንህ፣
ሌት ከቀን በማሰብ የምንሳሳልህ፣
ስለውሎ አዳርህ ጤናና ምግብህ፣
ስለጥልቅ ሀሳብህ የሕዝብ ፍቅርህ፡፡
አንተ ለኛ ብለህ፣
ባፋኞች ተወግረህ፣
ስቃይ ተሸክመህ፣
ከደስታ ርቀህ፣
ባጥር ተከልለህ፣
በሸፍጥ ተይዘህ፡፡
ብትኖር በስቃይ፣
ሁሉን ነገር ሳታይ፣
ቢደረመስ ሰማይ፣
ወይ ንቅንቅ ካላማህ ነጻነትን ሳታይ፡፡
በአካል ሩቅ ሆነን ካንተ ጋር ባንሆንም፣
የስቃይ ተጋሪህ ጓደኞች ባንሆንም፣
እኔ ልተካልህ የማንል ብንሆንም፣
በመንፈስ አንድ ነን ልዩነት የለንም፣
ብቸኛ ነኝ ብለህ ፍጹም እንዳትቆዝም፣
በጀግናው ጽናትህ ከቶ አንረሳህም፡፡
ፍቅርህ ቤቱን ሰርቶ በልባችን ውስጥ፣
ሌት ቀን እንድንተጋ ለወሳኙ ለውጥ፣
ለሕዝቦች አርነት ለእድገት መሳለጥ፡፡
አንደበተ ርትኡ የጠላት መጋኛ፣
የሕገወጥነት ታጋይ አመጸኛ፣
የዘር ናፋቂነት የአድልኦ ቀበኛ፣
ሙስናን ተዋጊ ተፋላሚ ዳኛ፣
የፍትህ መሀንዲስ የጠራ እውነተኛ
ፍትህ ሳያሰፍን ከቶ የማይተኛ፣
ብቸኛ አይደለህም ከጎንህ ነን እኛ::
አረመኔ ስርዓት በሸፍጥ ተነስቶ፣
በዘር በኃይማኖት ልዩነት መስርቶ፣
ጥላቻና በቀል በሀገር አስፋፍቶ፣
ነጻነትን ገፎ ፍቅርን አጥፍቶ፣
የሀገሪቱን ሕዝብ ረግጦ አደህይቶ፣
ጉልብትና ኃይሉን ሸፍጡን ተመክቶ፣
ለመጥፎው ድርጊቱ ህይወቱን ሰውቶ፣
በኢትዮጵያ ላይ አይቀር እንዲህ ተንሰራፍቶ፡፡
እኔ እስክንድር ነጋ ነኝ! 
አይበገሬው እስክንድር ነጋ! 
እስክንድር ነጋ እና በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ሁሉም የፖለቲካ አስረኞች በአስቸኳይ ይፈቱ!!!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!  
ሚያዝያ 18 ቀን 2008 ዓ.ም