Wednesday, October 12, 2016

ወያኔ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተገድን አድርጎ አማራውን በሶስት ዙር ትጥቁን ለማስፈታት ወስኗል።


ፋሽስት ወያኔ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተገድን አድርጎ አማራውን በሶስት ዙር ትጥቁን ለማስፈታት ወስኗል። ከውስጥ አርበኞቻችንና የጎበዝ አለቆቻችን ባገኘነው መረጃ መሰረት ፋሽስት ወያኔ በመጀመሪያ ዙር ትጥቅ የሚያስፈታው የአማራን ልዩ ኃይል ነው። የአማራን ልዩ ኃይል ትጥቁን ካስፈታች በኋላ የቀጣዩ ዙር ኢላማ ደግሞ የአማራ ገበሬ ነው። በእቅዱ መሰረት በሶስተኛ ደረጃ ትጥቃቸውን እንዲፈቱ የሚደረጉት የአማራ ሚሊሻዎች ወይንም በተለምዶ «ጉጅሌ» የሚባሉት ናቸው።
በዚህ መሰረት ዛሬ የአማራ ልዩ ሀይል አባላት ከዛሬ ጀምሮ ትጥቅ እንዲፈቱ እየተደረገ ነው። ትጥቅ እንዲፈቱ የተደረጉት ሁሉም የልዩ ኃይል አባላት አይደሉም። በቅድሚያ ትጥቅ እንዲፈቱ የተደረጉት የልዩ ኃይል አባላት የአማራ ተጋድሎ ሲካሄድ «ግደሉ» የሚል ተልኮ ተሰጥቷቸው «ወገናችንን አንገድልም!» በማለት የህዝብ ወገን መሆናቸውን ያስመሰከሩት ህዝብ አክባሪዎች ናቸው። እነዚህ የህዝብ ልጆች መሳሪያቸውን እንዲያስረክቡ ከተደረጉ በኋላ ለግዳጅ በተጠንቀቅ እንዲጠብቁ ተነግሯቸዋል፡፡
ተስፋ የቆረጠ ህዝብ ትጥቁን ስለፈታ፣ ስለተገደለ፣ ወይንም ስለታሰረ ተጋድሎውን ሊያቆም አይችልም። ይህ ያልገባው ወያኔ የማይበስል ነገር ጥዶ በከንቱ ማገዶ ይጨርሳል!

No comments:

Post a Comment