Saturday, October 1, 2016

ኢትዮጽያ ውስጥ የማይጠፋ ነገር የለም ። ተሰደው ወደ ኢትዮጵያ የመጡ 80 ሺህ የኤርትራ ስደተኞች ጠፉብኝ ሲል UNHCR ተናገረ


///ኢትዮጽያ ውስጥ የማይጠፋ ነገር የለም///
ተሰደው ወደ ኢትዮጵያ የመጡ 80 ሺህ የኤርትራ ስደተኞች ጠፉብኝ ሲል UNHCR ተናገረ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን የኢትዮጵያው ቢሮ እንዳለው እስከ ነሀሴ መጨረሻ 161 ሺህ 615 ኤርትራውያን በስደት ወደ ኢትዮጵያ የገቡ እና የተመዘገቡ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 81 ሺህ ገደማ የሚሆኑ በስድስቱም መጠለያ ካምፓች ውስጥ የሉም ተብሏል፡፡

አቶ ክሱት ገ/እግዚአብሔር የUNHCR ቃል አቀባይ ሲሆኑ ለሸገር እንደተናገሩት በርግጥ ኤርትራውያኑ ከሌሎች ስደተኞች በተለየ ሁኔታ በከተሞች መኖር እንዲችሉ በኢትዮጵያ መንግሥት መብት የተሰጣቸው ቢሆንም እነዚህ ግን በህጋዊ መንገድ ያልወጡ ናቸው ብለዋል፡፡

UNHCR ስደተኞቹ የት እንዳሉ ፍለጋ እያደረገ መሆኑንም ሰምተናል፡፡በህጉ መሠረት ስደተኞች በስደት ከገቡ በኋላ እስከ አራት ወራት ቢኖሩም ባይኖሩም እንደ ስደተኛ ይመዘገባሉ ካዛ በኋላ የሚደረግላቸው ድጋፍ ይቋረጣል ይላሉ ቃል አቀባዩ፡፡በክረምቱ ወቅት ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ የሚደረገው ስደት ቁጥሩ በአንፃራዊነት ይቀንሳል ምክንያቱ ደግሞ ወንዝ ስለሚሞላ መሻገር ስለሚያዳግት መሆኑንም አቶ ክሱት ነግረውናል፡፡

በበጋው ወቅት በአማካይ በወር እስከ 3 ሺህ የኤርትራ ስደተኛ ወደ ኢትዮጵያ ይገቡ የነበረ ሲሆን በክረምቱ ወቅት ቁጥሩ 2 ሺህ እና ከዛ በታች ይገመታል ሲሉ አቶ ክሱት ነግረውናል፡፡ኢትዮጵያ ከአለም አቀፍ የረድኤት ተቋማት ጋር በትብብር 6 የስደተኛ ካምፖችን ያዘጋጀች ሲሆን አራቱ በትግራይ፣ ሁለቱ በአፋር ክልሎች ይገኛሉ፡፡

No comments:

Post a Comment