Monday, October 31, 2016

ወያኔን ለማስወገድ፡ አማራን ማደራጀት – የአማራ ህዝብ መድህን ንቅናቄ (አህመን) መግለጫ


የተበታተነውን ትግል ለማሰባሰብ የአማራ ህዝብ መድህን ንቅናቄ \አህመን\ የሚባል ደርጅት አገር ቤት ተቋቋመ::የአማራ ህዝብ መድህን ንቅናቄ (አህመን)የጎበዝ አለቆች ያሉበት፣ የተለያዩ በአማራ ስም የሚንቀሳቀሱት ለማሰባሰብ ፣ የአማራ ተጋድሎን በተቀናጀ መልኩ ለማስኬድ የተቋቋመ ድርጅት ነው። በኢትዮጵያ አንድነትና ሉዓላዊነት ላይ የማይደራደር ደርጅት እንደሆነ ነው መግለጫው የሚጠቁመው።
ወያኔን ለማስወገድ፡ አማራን ማደራጀት – የአማራ ህዝብ መድህን ንቅናቄ (አህመን) መግለጫ
ባለፉት ሥርዓቶች እንደብቸኛ ተጠቃሚ እየተደረገ የፈጠራና የውንጀላ ታሪክ ተሰጥቶን በጭቆና ስር የሚማቅቀው ወግናችን የአማራ ህዝብ መደራጀት የግድ የሆነበት ደረጃ ላይ የተደረሰው በአማራ ልሂቃን ጉትጎታ ሳይሆን ህዝቡ በራሱ ከግፉ መብዛት፡ ከጭቆናው አሰቃቂነት የተነሣ በራሱ በአማራ ህዝብ የተፈጠረ ነው።
አብዛኞቹ የአማራ ልሂቃን ዛሬም ድረስ ወገናቸው “በመደራጀት ለራሴ ቀድሜ በመቆም ነው፡ ለኢትዮጵያ ልበጅ የምችል” ቢላቸውም ቅሉ አሁንም በአንድነት ስር ካሉ ሃይሎች ጋር በመሆን ዛው የህልም ሩጫ ውስጥ መዳከር ላይ ናቸው። ያውም ምንም አይነት የወሳኝነት ሚና በሌላቸው ድርጅቶች ውስጥ በመታቀፍ ጊዜያቸውንና ሃብታቸውን ይሰዋሉ።
ይህ አካሄድ የአማራን ህዝብ ሊጠቅም አይደለም፡ እንደውም ለጥቃት ያጋለጠ ከመሆኑ በላይ እነዚህ ሃይሎች የአማራን ህዝብ ትግልና ተጋድሎ በስሙ መጥራት፡ የሚደርስበትን በደል በይፋ መናገር ሁሉ የሚያሳፍራቸው መሆናቸው ደግሞ ጉዳዮ የበለጠ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ያሳያል።
በርካታ ወጣት የአዲሱ ትውልድ ልሂቃን ግን በሀቀኛ መረጃዎች የተደገፉ ጥፋቶችን በማሳየት ይህንን የአማራን የተጋድሎ ንቅናቄ ፈር ለማስያዝና ወደላቀ ድል ለማድረስ በየአቅጣጫው በመደራጀትና በማንቃት ላይ ናቸው። ከዚህ ደረጃ ትግሉን ያደረሰው ህዝባዊ ንቅናቄው እንጂ የቱም ድርጅት አለመሆኑን ሁላችንም የምናውቀው ሃቅ ሆኖ ሳለ ነገር ግን አንዳንድ የስም አንድነት ድርጅቶች የአማራን ተጋድሎ በስሙ ለመጥራት የሚያፍሩ ሆነው፡ በተጨማሪም በተረት ዓለም እንደሚኖር ምንዱብ ትግሉንና ድሉን በመድረኮቻቸው ሁሉ የራሳቸው በማድረግ ገቢ ማግኛ አድርገውታል፡ ይህም ድርብ ግፍ ነው። የሚደርስበትን ሰቆቃ በፀጥታ ከማለፍ ባሻገር የሚያደርገውን ተጋድሎ ባልዋሉበት ውለው መንጠቅ፡ ድርብ ግፍ ነው።
አሁን የሌሎችን በኛ የሚደረግ በደል የምናወራበትና የምናለቃቅስበት ጊዜ አይደለም። ዛሬ አማራ በጓዳው ያስለቅሱት የነበሩትን ሰቆቃዎች ሁሉ ባደባባይ ለመጋፈጥ ቆርጦና ጨክኖ የወጣበት ሰዓት ላይ ነን። የኛ ድርሻ መሰባሰብ፡ ዘመናዊ ስልትና ዕጣ ፈንታን መቀየስ፡ እንደአንድ ቤተሰብ መምከርና አንድ ልብ፡ አንድ ሃሳብ መሆን፡ ድሉን ከወንድምልቻችንና እህቶቻችን እኩል ለማጣጣም እንድንበቃ መቀናጀት፡ መደራጀት፡ በንድነት ትልቅና ማንም የማይቋቋመው ህጋዊ የአማራው ተወካይ ሆነን መገኘት ነው።
አማራ የሌለበት ትግል ሁሉ ፍሬ ክርስኪ መሆኑን ሌሎች ከኛ በላይ ይረዱታልና፡ የኛ መደራጀት የኢትዮጵያ ወሳኝ ዕጣ መሆኑን ተገንዝበን እስከጀነርነው ድረስ በጽናትና በሆደ ሰፊነት፡ በአማራ ባህል በሽምግልናና ዕርቅ ዳኝነት እየተስማማን፡ በጎበዝ አለቆች የሚመራውን በጠንካራ ባህላችን የተፈጠረውን ትግል፡ በዘመናዊ የፖለቲካ የትግል ስልት ደግፈን ፈጣን ዓለም አቀፍ ድጋፍ ለማግኘት ና ጠላቶቻችን የሚያዋርድ አንድነትና አደረጃጀት ለመፍጠር እንነሳ።
የአማራ ህዝብ መድህን ንቅናቄ (አህመን)

No comments:

Post a Comment