Monday, October 24, 2016

ሶማሊያ ዉስጥ ያለዉ የኢትዮጵያ ጦር እያፈገፈግ ነዉ


ሶማሊያ ዉስጥ ያለዉ የኢትዮጵያ ጦር እያፈገፈግ ነዉ
ቢቢኤን ጥቅምት13/2009
ኢትዮጵያ ዉስጥ ባለዉ ዉጥረት ወይም ከአሜሪካ መንግስት ጋር ባለዉ አለመግባባት ሳቢያ ይሁን ባይታወቅም ሶማሊያ ዉስጥ የከተመዉ የኢትዮጵያ ሰራዊት ቁጥሩን እያመናመነና እያፈገፈገ መሆኑን የተለያዩ ምንጮች እየዘገቡ ነዉ። አልሸባብን ለማጥቃትና ለማመናመን በምእራቡ አለም በጀት ሶማሊያ የገባዉ የኢትዮጵያ ጦር ተደጋጋሚ ጥቃት በአልሸባብ እንደሚደርስበትም ይታወቃል።
የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት ማፈግፈጉን ተከትሎ አልሸባብ ሐልጋን የተባለችዉን የሶማሊያ ከተማ ተቆጣጥሬያለሁ ሲል አሳዉቋል። የአካባቢዉ ሰዎች ለመገናኛ ብዙሗን እንደገለጹት የኢትዮጵያ ወታደሮች በሐልጋን የሚገኘዉን የጦር ሰፈር አዉድመዋል፣ምሽጋቸዉንም ደርምሰዋል። የተቆጣጠሩትን ቦታ በመተዉና ሰባ ኪሎ ሜትር በማፈግፈግ ታንክና በልድወይኒ ወደ ሚባለዉ ግዛት እቅንተዋል።አሶሸት ፕሬስ የአካባቢዉን ነዋሪዎች ዋቢ አድርጎ እንደዘገበዉ ታንክና ከባድ የጦር መሳሪያን የያዙ የኢትዮጵያ ወታደሮች ተከታትለዉ ወደ ሌላ ቦታ ሲጓዙ ታይተዋል።
በአፍሪካ ህብረት ጥምር ጦር አሚሶም ስም ሶማሊያ ገብቶ የሰፈረዉ የኢትዮጵያ የጦር ሰራዊት አያሌ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን እንደሚፈጽም የመገናኛ ብዙሗንና የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ይዘግባሉ። አልሸባብ አጽፋዊ ምላሽ እንደሚሰጥ ቢታወቅም በዚህ የጦርነት ኢንዱስትሪ ተጠቃሚ የሚሆኑት የህወሃት ባለስልጣናት የሚደርሰዉን ጥቃት በመደበቅ በድሃ ልጆች ደም ይነግዳሉ የሚል ክስ ይቀርብባቸዋል።
አገር ዉስጥ በተነሳበት ህዝባዊ እምቢተኝነት ከፍተኛ ዉጥረት ዉስጥ ያለዉ ህወሃት መራሹ መንግስት ቀደም ሲል ጦሩን ከሶማሊያ በባሌ በኩል እየሳበ ለሌላ አገራዊ ጥፋት እየተዘጋጀ ነዉ የሚል መረጃ መኖሩ ይታወቃል።የኢትዮጵያ ጦር በሐልጋን ሶማሊያ የጦር ሰፈርን አፍርሶ ፣ ምሽግን ደርምሶ መኮብለሉ ከነ አሜሪካ ጋር ላለዉ ዲፕሎማሲያዊ ኪሳራ መገለጫ ነዉ የሚል አስተያየት እየተሰጠበት ነዉ። አሜሪካ ቀደም ሲል አርባ ምንጭ ዉስጥ የነበረውን የሰዉ አልባ አዉሮፕላን መቆጣጠሪያ ጣቢያዋን አፍርሳና ጥላ መዉጣቷ ይታወቃል። ቢቢኤን

No comments:

Post a Comment