Wednesday, October 12, 2016

የኣስቸኳይ ኣዋጅ ኮማንድ ፖስቱ በእግረ መንገዱ የሚጠራርጋቸው የኢህኣዴግ ኣመራሮችና ጀሌዎቻቸውም ይኖራሉ።


የኣዋጁ ሰለባዎች !
፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣
የኣስቸኳይ ኣዋጁ ሰለባዎች በዋናነት በኢትዮጵያ ተከስቶ ያለው ተቃውሞና ማንኛውም የተቃውሞ ሃይል መሆኑ እሙን ነው። ይሁን እንጂ በእግረ መንገዱ የሚጠራርጋቸው የኢህኣዴግ ኣመራሮችና ጀሌዎቻቸውም ይኖራሉ።
የኣስቸኳይ ኣዋጅ ኮማንድ ፖስቱ ሰለባ ካደረጋቸው ኣመራሮች መሃል ኣባይ ወልዱና ገዱ ኣንዳርጋቸው ይገኝባቸዋል። ሁለቱ ባለ ስልጣናት በሚመሩት ክልል ሁነኛ ደጋፊ ማእከላይ ኮሚቴና የክልል ምክር ቤትች መመፍጠር ችለው ነበር።
፩) የብኣዴኑ ማእከላይ ኮሚቴና የኣማራ ክልል ምክር ቤት በጥልቅ ተሃድሶ ተብየው ግምገማ ገዱና ጓደኞቹ በስልጣኑ ይቆይ ብለው ወስነነበር
፪) የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴና የትግራይ ክልል ምክር ቤትም እንደ ብኣዴን ኣቻው የኣስቸኳይ ኣዋጁ ሰለባዎችና የኮማንድ ፖስቱ ተጠቂዎች ናቸው።
የማእከላይ ኮሚቴ፣ የክልል ምክርቤቶች፣ የታማኝ ካድሬዎች ኔትወርክ ድጋፍ ኣለመረጋጋት እንዳይፈጥርና ሲፈጠርም በማያዳግም ደረጃ ለመምታት እንዳያመች የተሰላ ኣዋጅ ነው።
ኣባይ ወልዱ መቐለ በተካሄደው ግምገማ ከ45 ማእከላይ ኮሚቴ የ35 በስልጣኑ ይቆይ የሚል ድጋፍ፣ 10 ደግሞ ከስልጣኑ ይውረድ የሚል ድምፅ ተሰጥቶበት ነበር።
ገዱ ኣንዳርጋቸውም በተመሳሳይ በስልጣኑ እንዲቆይ የማእከላዊ ኮሚቴ ድጋፍ ተችሮበት ነበር።
ይሁን እንጂ ሁለቱ የክልል መሪዎች በኣስቸኳይ ግዜ ኣዋጅ ኮማንድ ፖስት እንዲነሱ መደረጋቸው እየተነገረ ነው።
በመላ ሃገሪቱ እየተካሄደ ያለው የህዝባዊ ተቃውሞ (ግብፅና ሻዕብያ ሽፋን የተደረገበት) ለመምታት መነሻ ኣድርጎ የወጣው ኣዋጅ “ለሃጥእ የመጣ ለፃድቅ ይተርፋል” እንደሚባለው ሁለቱ መሪዎችና ጀሌዎቻቸው ለመምታትም የመጣ ይመስላል።
እነዚህ መሪዎች ለማውረድ ይፈለግ የነበረው የምርክርቤት ኣሰራር በማፍረስ ውሳኔው ተግባራዊ ሊደረግ ተፈልገዋል።
የኣባይ ወልዱ ደጋፊዎች ኣዋጁ ተንተርሶ የተወሰደው እርምጃ “መፈንቅለ መንግስት ተደረገብን” የሚል ተቃውሞ ውስጥ ውስጡን እያስወሩ ይገኛሉ።
ባጭሩ የኣስቸኳይ ግዜ ኣዋጁ ሰለባዎች የተቃውሞ ሃይል ብቻ ሳይሆኑ የኢህኣዴግ ባለ ቱባ ኔትወርክ ባለስልጣናትም መሆናቸው ክስተቱ ያሳያል።
ጉልቻ ቢለዋወጥ ወጥ ኣያጣፍጥም !
ለውጥ እንፈልጋለን ! ነፃነት እንሻለን ! ፍትህ ናፍቆናል!
ነፃነታችን በእጃችን !
No automatic alt text available.

No comments:

Post a Comment