Tuesday, October 11, 2016

“አላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ይለቀልቃል” ጃዋር መሃመድ የአፍ ወለምታ ወይስ የመዘባረቅ አባዜ?


ኢትዮጵያዊያን ላለፉት 25 ዓመታት ያልታየ አዲስ የሆነ የመተባባርና የወያኔን አምባገናዊና አፋኝ ሥርዓት ከጫንካቸው ላይ አውርደው ለመፈጥፈጥ የተጠናከረ ትግል በማድረግና በመተባባር ላይ ይገኛሉ። ወያኔ ላለፉት 25 ዓመታት አገሪቷን ሰንጎ ለመግዛት የቻለው ህዝባዊ ተቀባይነትና ከበሬታ ኖሮት አይደለም። ለወያኔ 25 ዓመታት ሥልጣን ማማ ላይ ሰፍሮ ህዝቡን እየጨፈጨፈና አገሪቷን እየዘረፈ ሊኖር ያስቻለው በህዝቦች መካካል ጥላቻን ለመፍጠር በመቻሉና እሱ ከሥልጣን ላይ ተመንግሎ ከወደቀ አንዱ ብሄር ሌላውን ያጠፋል በማለትና በተግባርም የብሔረሰቦችን ግጭት በማነሳሳትና በማራራቅ ላይ ነው። አሁን ግን በተለይም የአማራና የኦሮሞ ህዝብ የቆየ ወንድማማችነቱን እያጠናከረና የጋራ ጥቅሙ ላይ አብሮ መስራት መጀመሩና እንዲሁም የጋራ  ጠላቱ ወያኔ መሆኑን አውቆ ፍቅርና ህብረቱን በማጠናከር ላይ መምጣቱ ወያኔን እያብረከረከ እንደሆነ ይታወቃል። የወያኔ አፈ ቀላጤ ጌታቸው ረዳ ይህንን በብሔረሰቦች መካካል እየተጠናከረ የመጣውን ትብብር እያወገዘና እየኮነነ በቁጭት ሲናገር እዚህ ላይ ይመልከቱ።  
በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ህልውና ላይ አደጋ ያለው ጉዳይ ላይ የሚሰጡ አስተያየቶችም ሆነ የሚተላለፉ መልዕክቶች ጥንቃቄና ብስለት የተሞላባቸው መሆን ይጠበቅባቸዋል። በተለይም የመገናኛ ብዙሃንን የሚቆጣጠሩ ግለሰሶች የሚያሳድሩት ጫና በአሉታዊም ሆነ በአዎንታዊ መልኩ እጅግ ብዙ ነው። በዚህም መሠረት ወጣት ጃዋር መሃመድ በተለያየ ጊዜ ከተናገረ በኋላ እንደሚያስብና እንዲሁም በተደጋጋሚም ከተናገረ በኋላ የተናገረውን እንደሚቀይርና እንደሚያስተባብል ስለተመለከት በዚህ ወሳኝ ወቅት በእጁ የገባውን መነጋገሪያ (ማይክራ ፎን) ለሌሎች ሰከን ብለው ለሚናገሩ በሳሎች ቢሰጥና እሱ ከጀርባ ሆኖ አቅሙና ችሎታው ያለውን ስራዎችን ቢያከናውን መልካም ነው የሚሉ በርካቶች ናቸው። ወጣት ጃዋር “ከአፍ የወጣ አፋፍ” እንደሚባለው አንዴ ከተናገረ በኋላ የተናገረው ነገር አቧራ ሲያስነሳ ያንኑ ነገር መልሶ ለመዋጥ ብዙ ከሚደክምና ጊዜ ከሚያባክን አስቀድሞ ተዘጋጅቶ  አስቦ ቢናገር ይበጀዋል የሚሉም አሉ። ከአሁን በፊት የሜጫዋ  ጉዳይ ብዙ ዋጋ እንዳስከፈለችው የሚረሳው አይመስለንም። ለማንኛውም “የኦሮምያ ሰነድ አዲሱ ቃል ኪዳን?” አማራ፣ ደቡብ፣ ሶማሌ፣ ጋምቤላ … እንዴት?” በሚል ርዕስ የወጣውን መጣጥፍ ለግንዛቤ አንዲረዳ በማለት አውጥተነዋል።  ጽሁፉን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። የኦሮሚያ ሰነድ

No comments:

Post a Comment