Friday, October 7, 2016

ወታደሮች በካምፕ ውስጥ ያላቸው እንቅስቃሴ እንዲገደብና ፈቃድ እንዳይሰጣቸው ተደረገ። ቦምብ መታጠቅና ስብሰባ ላልተወሰነ ጊዜ ቆሟል።


ወታደሮች በካምፕ ውስጥ ያላቸው እንቅስቃሴ እንዲገደብና ፈቃድ እንዳይሰጣቸው ተደረገ። ቦምብ መታጠቅና ስብሰባ ላልተወሰነ ጊዜ ቆሟል።
 
Minilik Salsawi – mereja.com
በርካታ ወታደሮች በቡድን መጥፋት አንዲሁም በካምፕ ውስጥ የተደረጉ የተኩስ ልውውጦችን ተከትሎ በምስራቅ እዝ የሚገኘው የሕወሓት መኮንኖች ቡድ በሰጠው መመሪያ መሰረት ወታደሮች በካምፕ ውስጥ ያላቸው እንቅስቃሴ እንዲገደብና ፈቃድ እንዳይሰጣቸው ተደረገ። ቦምብ መታጠቅና ስብሰባ ላልተወሰነ ጊዜ ቆሟል። ሲሉ የእዙ ወታደራዊ ደህንነት ኣባል የሆኑ ኣንድ ሰው የላከት መረጃ ይጠቁማል። ወታደራዊ ደህንነቱ እንዳሉት የሶማሊያና የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ወታደሮች ተለይተው ጠንካራ የሆነ የጥላቻና የክፍት ምክሮች እንደሚሰጣቸው በዙሪያቸው ያሉትን ሌሎች ወታደሮች እንዳያምኑና እንዲሰልሉ እየተደረገ መሆኑ ታውቋል።
 
በየወታደራዊ ካምፖች በመላው ሃገሪቱ ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ከፍተኛ የሆነ የስለላ ስራ እንደሚሰራ የሚናገሩት ምንጮች ኣብዛኛው ወታደሮች ዝምታን ቢመርጡም ለስርዓቱ ያላቸውን ተቃውሞ ድንገት ያፈነዱታል ተብሎ ተፈርቷል።ለወታደሮች የሚሰጣቸው ጥይት ኣነስተኛ ሲሆን ቦምብን የመሳሰሉ የፍንዳታ መሳሪያዎች እንዳይታጠቁ ተከልክለዋል። ቦምብ መታጠቅና እንደላውንቸር ያሉ መሳሪያዎችን እንደ ዙ23 እና ታንክ መሰሎችን እንዲይዙ እንደቆጣጠሩ የሚደረጉት የትግራይ ተወላጆች ናቸው ሲሉ ምንጮቹ ለምንሊክ ሳልሳዊ ተናግረዋል።
 
ወታደሮቹ ፈቃድ እንዳያገኙና ስብሰባ እንዳይደረግ ያገዱት ወታደራዊ ኣዛዦች ምክንያታቸው ዛሬም ኣልሸባብ ገፍቶ ሃገራችንን እንዳይወራትና የሻእቢያ መጫወቻ እንዳንሆን የደርግ ወታደሮችን ታሪክ ኣስታውሱ በሚል ፕሮፓጋንዳ በማጀም ወታደሩ በተጤንቀቅ እንዲቆምና ስብሰባና ፈቃዳ በኣልስሀባብ በኩል ያለውን ችግር ሶማሊያ የዘመተው ጦራችን ካረጋጋው በኋላ ይደርሳል በማለት ፕሮፓጋንዳቸውን እየረጩ ይገኛሉ፥ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዜና ሕወሓት የተመረዙ ምግቦችንና መጠጦች በተለያዩ መስመሮች ለመጠቀም ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ወታደራዊ ደህንነቶች ጨምረው ኣስረድተዋል። #ምንሊክሳልሳዊ

No comments:

Post a Comment