Monday, October 31, 2016

የሕወሓት ኮማንድ ፖስት የፖለቲካ ድርጅት ኣባላትን ማፈን ጀመረ። ዘረፋው ተጠናክሮ ቀጥሏል።

የሕወሓት ኮማንድ ፖስት የፖለቲካ ድርጅት ኣባላትን ማፈን ጀመረ። ዘረፋው ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በኢትዮጵያ ውስጥ ኣስቸኳይ ጊዜ ኣዋጅ ኣውጥቶ በኣፈናና በዘረፋ ላይ የተሰማራው የሕወሓት ኮማንድ ፖስት የሚባለው መስሪያ ቤት የፖለቲካ ድርጅት ኣባላቶችን በማፈ እና ሕዝብን በማስፈራራት በፍተሻ ስም ዘረፋ ላይ መሆኑን ሕዝቡ በምሬት ገለጸ።
በዚህም መሰረት ከሰማያዊ ፓርቲ የታፈኑት ወደ ኮማንድ ፖስቱ የተላለፉ ሾን ከኣዋጁ በፊት መታፈናቸው ቢገለጽም ሰሚ ኣካል ባለመገኘቱ በእስር እየተንገላቱ እንደሆነ ታውቋል። ከትላንትና ጀምሮ በተጀመረው ኣፈና የቀድሞው አንድነት ፓርቲ የፖለቲካ ጉዳይ ሃላፊ የነበረው አቶ ሰሎሞን ስዩም ትናንት ምሽት በደህንነቶች ከመኖሪያ ታፍኖ መወሰዱን ለማወቅ ተችሏል።እንዲሁም የቀድሞ አንድነት ፓርቲ ኦዲት እና ኢንስፔክሽን ሃላፊ እንዲሁም የብሄራዊ ምክር ቤት አባል የነበረው ወጣት ዳግማዊ ተሰማ በዛሬው እለት በድህንነት ሃይሎች ተይዞ ፮ኛ ፖሊስ ጣቢያ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።
ኣፈናውን ኣጠናክሮ የቀጠለው ኮማንድ ፖስቱ ሌሎች የፖለቲካ ድርጅት ኣባላትን በክትትል ቀለበት ውስጥ ኣስገብቶ ለመያዝ መዘጋጀቱ ታውቋል። ከተመሰረተ ገና ኣንድ ሳምንት ሳይሞላ ከኣስራ ኣምስት ሺህ ዜጎች በላይ እስር ቤት እንደከተተ የሚነገርለት ኮማንድ ፖስቱ ስራው ማፈን\ማሰር ብቻ ሳይሆን ዘረፋም እንደሆነ የገለጹት ምንጮች በሕዝቡ ላይ የገንዘብና የሞባይል የጌጣጌጥና የኤለክትሮኒክስ እቃዎችን በመዝረፍ ላይ እንደሚገኙ ሲታወቅ እነዚሁ የኮማንድ ፖስት ኣባላት በተሰጣቸው ስድ ስልጣን ነገ ሴቶችን ከመድፈር እንደማይመለሱ በመናገር ሕዝቡ ሮሮውን በማሰማት ላይ ይገኛል። #ምንሊክሳልሳዊ

No comments:

Post a Comment