Monday, October 31, 2016

የወያኔ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የእሳት ቃጠሎን አጣርቻለሁ አለ


የወያኔ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የእሳት ቃጠሎን አጣርቻለሁ አለ  በመጪው ሳምንት ሪፖርቱን ለፓርላማ ያቀርባል
ነሐሴ 24 ቀን 2008 ዓ.ም በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ላይ የደረሰውን የእሳት አደጋ ተከትሎ የ22 ታራሚዎች ህይወት ማለፉ የሚታወስ ሲሆንየወያኔ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ቃጠሎውን በተመለከተ ያደረገውን የምርመራ ሪፖርት በመጪው ሳምንት ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ያቀርባል ተብሏል፡፡
አደጋው የደረሰ ሰሞን በስፍራው ተገኝተው ሁኔታውን የተመለከቱት የኮሚሽኑ ከፍተኛ አመራሮች፤ የእሳቱን መንስኤና የደረሰውን ጉዳት በተመለከተ ኮሚሽኑ በአጭር ጊዜ ውስጥ አጣርቶ የምርመራ ውጤቱን ይፋ እንደሚያደርግ መግለፃቸው ይታወሳል፡፡  የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ብርሃኑ አባዲ፤ ምርመራውና ማጣራቱ ተጠናቆ ሪፖርቱ መዘጋጀቱን ጠቁመው፤ በመጪው ሳምንት ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት እንደሚቀርብ ገልፀዋል፡፡
በማረሚያ ቤቱ ላይ የደረሰውን የእሳት አደጋ ተከትሎ በወቅቱ 2 ታራሚዎች በጥይት፣ ቀሪዎቹ በቃጠሎው ህይወታቸው ማለፉ መገለፁ የሚታወስ ነው፡፡ ባለፈው ዓመት ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ሌላ በጎንደርና ደብረ ታቦር ወህኒ ቤቶችም በደረሰው የቃጠሎ አደጋ የታራሚዎች ህይወት ማለፉ አይዘነጋም፡፡

No comments:

Post a Comment