አቶ አበበ ውቤ ታሰረ፤ ወያኔ የመኢአድ አባላትን ማሳደዱን ቀጥሏል
አቶ አበበ ውቤ ከጥቅምት 9 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ በቦሌ አምቼ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ እንደሚገኝ የቤተሰቡ አባላት ገለጹ፡፡ አቶ አበበ ቀደም ባሉት ቀናት በደኅንነት ሰዎች ማወከብ ይደርስበት እንደነበር በተደጋጋሚ ተናግሯል፡፡ አቶ አበበ ውቤ አሁን ከሕትመት በወጣችው የቀለም ቀንድ ጋዜጣ ሥራ አስኪጅ ሆኖ አገልግሏል፡፡ አቶ አበበ ውቤ ለረዥም ዓመታት በመኢአድ ውስጥ በተለያዩ ኃላፊነቶች ላይ ሠርቷል፡፡
አገዛዙ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት አባላትንና ደጋፊዎችን ማሠርና ማሳደድ እንደቀጠለበት መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ከአንድ ሳምንት በፊት አቶ ኢዮብ ከበደ እና አቶ ጫንያለው ዘየደን ለቀናት ከታሠሩ በኋላ መፈታታቸው ይታወቃል፡፡ የድርጅቱ የሰሜን ምዕራብ ቀጠና ኃላፊና ም/ፕሬዝዳንት የነበረው አቶ ዘመነ ምሕረት ላይ የግድያ ማደኛ መውጣቱን ባለፉት ቀናት የዘገብን ሲሆን የድርጅቱ ሊቀ መንበር አቶ ማሙሸት አማረ በከፍተኛ ሥጋት ውስጥ እንደሚኖርም ለማወቅ ተችሏል፡፡
No comments:
Post a Comment