ተቃውሞው ኣዲስ ኣበባ ፉሪና ኣለም ገና ገብቷል።
ፉሪ የጀመረው ተቃውሞ ወደ አለምገናም ቀጥሏል። ፉሪ ሱቆች፣ ካፌዎች፣ ባንኮች እና ባጠቃላይ መንገድ ዳር ያሉ ንግድ ቤቶች በጠቅላላ ዝግ ናቸው። ፉሪ መንገዱ ዳር እስከ ጆሞ ድረስ በታጠቁ የፌደራል እና የኦሮሚያን ዩኒፎርም የለበሱ ፓሊሶች በመንገዱ ፈሰዋል። ወጣቶች በየቅያሱ በየቅያሱ ተሰባስበው ይታያሉ። ባጃጅ እና ታክሲዎች የትራንስፓርት አገልግሎት እየሰጡ አይደለም። ጆሞ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቻቸውን በጊዜ ለቀው ቤተሰብ እየወሰዳቸው ነው። የትራንስፓርት እጥረቱ መሃል አዲስ አበባም ደርሷል። ሜክሲኮ ጋርም ከፍተኛ የታክሲ እጥረት አለ።
No comments:
Post a Comment