Sunday, February 26, 2017

በአገራችን በቀን 10 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ህይወታቸው ያጣሉ – በአዲስ አበባ ብቻ ባለፉት 6 ወራት 244 ሰዎች በመኪና አደጋ ህይወታቸው አልፏል፡፡




በአገራችን በቀን 10 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ህይወታቸው ያጣሉ
– በአዲስ አበባ ብቻ ባለፉት 6 ወራት 244 ሰዎች በመኪና አደጋ ህይወታቸው አልፏል፡፡
– ከ170 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ንብረት ወድሟል
– ከፍተኛ የትራፊክ አደጋ እያደረሱ ያሉት አዳዲስና ዘመናዊ መኪኖች ናቸው
በኢትዮጵያ የትራፊክ አደጋ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱንና በየቀኑ 10 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ህይወታቸውን እንደሚያጡና 31 ያህሉ ለከባድ የአካል ጉዳት እንደሚዳረጉ ተጠቆመ፡፡
ከመንገድ ትራፊክ ደህንነት ቢሮ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው፤ በአገሪቱ በየዕለቱ እየተከሰተ የሚገኘው የትራፊክ አደጋ እጅግ አሳሳቢ የሆነ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ በ2007 ዓ.ም 3847 ሰዎች በአደጋው ህይወታቸውን እንዳጡ ያመለከተው መረጃው፤ በ2008 ዓ.ም ቁጥጥር እየጨመረ መሄዱን ገልጿል፡፡ በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ የተመዘገቡ የተሽከርካሪዎች ቁጥር ከ600 ሺ የማይበልጥ መሆኑን የጠቆመው ይኸው መረጃ፤ እያደረሰ ያለው አደጋ ግን አገሪቱ በአለም አቀፍ ደረጃ በትራፊክ አደጋ ታዋቂነትን እንድታገኝ ያደረጋት ሲሆን 90 በመቶ አደጋ ከሚደርስባቸው አገራት አንዷም ሆናለች ብሏል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ባለፉት ስድስት ወራት፤ ከሐምሌ 2008 እስከ ታህሳስ 2009 ዓ.ም ድረስ 244 የሞት አደጋና 8070 ከባድ የአካል ጉዳት እንዲሁም 585 ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን ይኸው መረጃ አመላክቷል፡፡ 170 ሚሊዮን ብር በላይ ንብረት መውደሙንም ገልጿል፡፡
በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ እየደረሱ ካሉ የትራፊክ አደጋዎች አብዛኛዎቹ የሚከሰቱት ዘመናዊና አዳዲስ በሆኑ መኪኖች መሆኑን የጠቆመው መረጃው ከ5-10 ዓመት ድረስ ያገለገሉ አዳዲስ መኪናዎች አብዛኛውን አደጋ ማድረሳቸውን አመልክቷል፡፡
በአለም አቀፍ ደረጃ ገዳይ ከሚባሉ የተፈጥሮና የሰው ሰራሽ አደጋዎች መካከል የመኪና አደጋ በዘጠነኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን በአለም በየዕለቱ 3400 ሰዎች በዚሁ የመኪና አደጋ ሳቢያ ህይወታቸውን ያጣሉ፡፡ በየዓመቱ 1.24 ሚሊዮን ሰዎች እንደሚሞቱ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

ማጭበርበር የማይሰለቸው ወያኔ የውጪ ሀገር ስደተኞችን ለማቋቋም እየሰራሁ ነው አለ



ማጭበርበር የማይሰለቸው ወያኔ የውጪ ሀገር ስደተኞችን ለማቋቋም እየሰራሁ ነው አለ. የራሱን ዜጎች እያባረረ የሌላ አገር ስደተኞችን የሚያቋቁም ደነዝ አገዛዝ እድሜው አጭር ነው።
– የአውሮፓ ህብረትና ኔዘርላንድ ለስደተኞች ማቋቋሚያ የ720 ሚ. ብር ድጋፍ አድርገዋል
– ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ስደተኞች በየጊዜው እየጨመሩ ነው
ማጭበርበር የማይሰለቸው ወያኔ የውጪ ሀገር ስደተኞችን ለማቋቋም እየሰራሁ ነው አለ   የራሱን ዜጎች እያባረረ የሌላ አገር ስደተኞችን የሚያቋቁም ደነዝ አገዛዝ እድሜው አጭር ነው።  የአውሮፓ ህብረትና የኔዘርላንድ ኤምባሲ፤ በኢትዮጵያ የሚገኙ የውጭ ሀገር ስደተኞችን ለማቋቋምና ስደተኞቹን እያስተናገዱ ያሉ አካባቢዎችን ለመደገፍ የሚውል የ720 ሚሊዮን ብር ፕሮጀክት ይፋ ያደረገ ሲሆን መንግስት በበኩሉ፤ ስደተኞችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ አሰራሮችን እያዘጋጀ መሆኑን አስታውቋል፡፡
በአውሮፓ ህብረትና በኔዘርላንድ ኢምባሲ ይደገፋል የተባለውን የክልላዊ ልማትና እንክብካቤ ፕሮጀክትን በአዲስ አበባ ይፋ ያደረጉት በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት ልኡክ መሪ አምባሳደር ቻንታል ኧብረት፤ ኢትዮጵያ ለምትከተለው “ስደተኞችን እጅን ዘርግቶ የመቀበል” ፖሊሲ አድናቆት እንዳላቸው ገልፀው፤ ህብረቱም ይህን መነሻ አድርጎ ድጋፉን መለገሱን ተናግረዋል፡፡ ማጭበርበር የማይሰለቸው ወያኔ የውጪ ሀገር ስደተኞችን ለማቋቋም እየሰራሁ ነው አለ
720 ሚሊዮን ብሩ ስደተኞቹን ለመንከባከቢያና ስደተኞቹን ተቀብለው እያስተናገዱ ያሉ ማህበረሰቦችን ለመደገፍ እንደሚውል የተገለፀ ሲሆን ለትምህርት፣ ለውሃና ለኃይል አቅርቦት እንዲሁም ለሌሎች የመሰረተ ልማት ዝርጋታዎች ይውላል ተብሏል፡፡  የዚህ ፕሮጀክት ተጠቃሚዎች ስደተኛ ተቀባይ የሆኑት የትግራይ፣ አፋርና የሱማሌ ክልል ሲሆኑ የኤርትራና የሶማሊያ ስደተኞች የዚህ ፕሮግራም ዋነኛ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተገልጿል፡፡
በስነ ስርአቱ ላይ ተገኝተው ስደተኞችን በተመለከተ መንግስት እያከናወናቸው ያሉ መርሃ ግብሮችን ይፋ ያደረጉት የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ጽ/ቤት ም/ዳይሬክተር አቶ ዘይኑ ጀማል፤ በአሁን ወቅት የደቡብ ሱዳን፣ የኤርትራ፣ የሱማሊያ፣ የኬንያና የሌሎች ሀገራትን ጨምሮ 8 መቶ ሺህ ስደተኞች በኢትዮጵያ በተለያዩ ካምፖች እንደሚገኙ ጠቁመው መንግስት ስደተኞችን ማቋቋም የሚያስችል ፕሮግራም መንደፉን አስረድተዋል፡፡ እ.ኤ.አ በመስከረም 2016 ስደተኞችን አስመልክቶ በተደረገው የዓለም መሪዎች ስብሰባ ላይ፤ ኢትዮጵያ ስደተኞችን ለማቋቋም ቃል በገባችው መሰረት፡ የተለያዩ መርሃ ግብሮችን መቅረጿን ያመለከቱት አቶ ዘይኑ፤ ከስደተኞቹ 10 በመቶ ያህሉ (80 ሺህ)  ከካምፕ ውጪ የመኖር መብት ተጠቃሚ እንዲሆኑ፣ የስራ ፍቃድና፣ የነዋሪነት መታወቂያ ደብተር እንዲያገኙ መታቀዱን አስረድተዋል፡፡
አድልኦ ሳይደረግ የሁሉም ሀገር ስደተኞች ከመጀመሪያ ደረጃ አንስቶ እስከ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ድረስ ዘልቀው የትምህርት እድል እንዲያገኙ እንዲሁም በመስኖ ሊለማ የሚችልና 100 ሺህ ስደተኞችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሬት የሰብል ልማት እንዲያለሙበት ማዘጋጀቱን አስታውቀዋል፡፡
በሀገሪቱ ከሚገነቡ የኢንዱስትሪ ፓርኮች መካከል የተወሰኑት ከሚቀጥሯቸው ሰራተኞች 30 በመቶዎቹ ስደተኞች እንዲሆኑ እንደሚደረግም ተገልጿል፡፡ ለመቶ ሺህ ሰዎች ከሚፈጠረው የስራ እድል ውስጥ 30 ሺህ ያህሉን ስደተኞች እንዲጠቀሙበት ለማድረግ ኢትዮጵያ ቃል ገብታለች ተብሏል፡፡ ለዚህ አይነቱ የሥራ ዕድል ከአውሮፓ ህብረት 50 ሚሊዮን ዩሮ እርዳታ  ከአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ 200 ሚሊዮን ዶላር ብድር እንደሚገኝም አምባሳደር ሻንታል በንግግራቸው ጠቁመዋል፡፡
መንግስት ስደተኞች የደህንነት ስጋትም ሆነ የዜጎች ተፎካካሪ ናቸው የሚል እምነት እንደሌለው ገልፀው፤ ስደተኞቹን አደራጅቶ የስራ እድል ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዷል ብለዋል፡፡
በደቡብ ሱዳንና በሶማሊያ ካለው ድርቅ ጋር በተገናኘም በቀጣይ ጊዜያት በርካታ ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የጠቆሙት አቶ ዘይኑ፤ የዝግጁነት እቅድ አውጥተን እየሰራን ነው ብለዋል፡፡ ከደቡብ ሱዳን ብቻ ባለፉት 5 ወራት፣ ከ58 ሺህ በላይ ተጨማሪ ስደተኞችን ተቀብለናል ብለዋል አቶ ዘይኑ፡፡
በጋምቤላ ለእርሻ ኢንቨስትመንት ለባለሀብቶች በተሰጠ መሬት ላይ ስደተኞች እየሰፈሩ ነው የሚለው አቤቱታ ሀሰተኛ መሆኑንም ም/ዳይሬክተሩ ገልፀው፤ ስደተኞቹ ከእንዲህ ያሉ መሬቶች ጋር ግንኙነት የላቸውም ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ ስደተኞችን ተቀብላ በማስተናገድ ከአፍሪካ 2ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠች ሲሆን ከ3 መቶ ሺህ በላይ የደቡብ ሱዳን፣ 250 ሺህ የሶማሊያና 265 ሺህ የኤርትራ ዜጎችን ጨምሮ የኬንያ፣ ሱዳንና የአረብ ሀገራት ስደተኞች ይገኛሉ፡፡  ማጭበርበር የማይሰለቸው ወያኔ የውጪ ሀገር ስደተኞችን ለማቋቋም እየሰራሁ ነው አለ የራሱን ዜጎች እያባረረ የሌላ አገር ስደተኞችን የሚያቋቁም ደነዝ አገዛዝ እድሜው አጭር ነው።

የቀድሞው የጋምቢያ ፕሬዚዳንት የዘረፉት ገንዘብ 1 ቢ. ዶላር ደርሷል

    



በምርጫ ቢሸነፉም ስልጣኔን አልለቅም ብለው ለሳምንታት ካንገራገሩ በኋላ በተደረገባቸው ጫና አገራቸውን ጥለው የተሰደዱት የቀድሞው የጋምቢያ ፕሬዚዳንት ያያ ጃሜህ ከአገሪቱ ካዘና ያለአግባብ የዘረፉት ገንዘብ 1 ቢሊዮን ዶላር ያህል መድረሱን አዲሱ የአገሪቱ መንግስት አስታወቀ፡፡
አዲሱ የአዳማ ባሮው መንግስት ሚኒስትሮች ያወጡትም መረጃ ጠቅሶ ዘ ጋርዲያን እንደዘገበው፣ ተሰናባቹ ያያ ጃሜህ ከተለያዩ የአገሪቱ የመንግስት ተቋማት በየሰበብ አስባቡ ያለ አግባብ ለግል ጥቅማቸው ያዋሉት ገንዘብ በድምሩ 1 ቢሊዮን ዶላር ያህል መድረሱ በምርመራ ተረጋግጧል፡፡
ጃሜህ ከማህበራዊ ዋስትና፣ ከስፖርት እና ከቴሌኮም ድርጅቶች ብቻ 50 ሚሊዮን ዶላር ዘርፈዋል፤ ለግል አውሮፕላናቸው ግዢ ያለ አግባብ ከመንግስት ካዘና 4.5 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ተደርጓል፣ እጅግ በርካታ ገንዘብም ያለ አግባብ ለግል ጥቅማቸው እንዲውል ተደርጓል ብሏል ዘገባው፡፡
ከአገሪቱ የማህበራዊ ዋስትና ካዘና ወጪ የተደረገ 40 ሚሊዮን ዶላር ያህል ገንዘብ የት እንደገባ አለመታወቁን የጠቆመው ዘገባው፣ ገንዘቡ በጃሜህ ኪስ ውስጥ ሳይገባ አይቀርም ተብሎ መጠርጠሩንና ቅንጦት ወዳጁ ጃሜህ በየሰበብ አስባቡ ደጋፊዎቻቸውን ለማስደሰት ባደረጓቸው የእራት ግብዣዎችና የቅንጦት ተግባራት 67 ሺህ ዶላር ያህል ወጪ መደረጉም ተነግሯል፡፡
ይሄም ሆኖ ግን ተመድ ለተጠቀሱት አራት አገራት የሚያስፈልገውን 4.4 ቢሊዮን ዶላር ለማሰባሰብ ያደረገው ጥረት ይህ ነው የሚባል ውጤት አለማግኘቱንና እስካሁን ድረስ ማግኘት የቻለው 90 ሚሊዮን ዶላር ያህል ብቻ መሆኑን የጠቆሙት ዋና ጸሃፊው፣ አለማቀፉ ማህበረስብ በአፋጣኝ የድጋፍ እጁን እንዲዘረጋ ጠይቀዋል፡፡

Friday, February 24, 2017

የጠቅላይ ምኒስትሩ ባዶ ጭሆቶችና ኤርትራ !

   


የጠቅላይ ምኒስትሩ ባዶ ጭሆቶች !
÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷
የኢህኣዴግ መሪዎች በኤርትራና በሻዕብያ ያላቸው ፍቅር ገና ኣልወጣላቸውም። ግብኣተ መሬት እስኪ ገቡ ፍቅራቸው የሚወጣላቸውም ኣይመስሉም።
ሰሞኑ ሃይለማርያም ደሳለኝ ኤርትራን በተመላከተ የተለመደው የሸፍጥ ንግግር ኣድርገዋል።
“የኤርትራ ጉዳይ ትግራይ ክልል ክፉኛ እየጎዳ ስላለ የተለየ ሶስተኛ ኣማራጭ እየፈለግን ነው።” ጠ/ም/ ሃይለማርያም ደሳለኝ የኢትዮ- ኤርትራ ግንኙነት ኣስመልክተው የሰጡት ሓሳብ።
ከዚህ የፊት ባዶ ጭሆት ሁነው የቀሩት ንግግሮች ኣድርገው ነበር።
” የማያዳግም እርምጃ ”
” ተመጣጣኝ እርምጃ ” የሚሉት ፍኮራዎችና ቀረርቶዎች ተናግረው ነበር። እነዚህ ንግግሮች እንደጠበቅናቸው በሻዕብያና ኤርትራ ምንም ተፅእኖና ለውጥ እንዳላመጡ ታዝበናል።
ኣሁን ኤርትራና ሻዕብያ በተመለከተ “ሶስተኛ ኣማራጭ እየፈለግን ነው” ብለው ቀልደዋል። “ሲሰርቀኝ ያየሁት ሲጨምርልኝ ኣላምነውም” እንደሚባለው ከዚህ በፊት ዘራፍ ዘራፍ ብለው ወፍም ማባረር እንዳልቻሉ ኣይተናልና ኣሁንም ምንም ለውጥ እንደማናይ እምን ነው።
ስብሓትና ኢሳያስ
ህወሓትና ሻዕብያ ዕጣፈንታቸው ኣንድ ዓይነት ናቸው። ይሄ ነገር ጠንቅቀው ስለሚያውቁ እርስ በራሳቸው መቼም ኣይጨካከኑም።
ምናልባት ህወሓቶች ባድመን ለሻዕብያ ኣስረክበው እታረቃለው ሊሉን ይችላሉ። ይሄ ውሳኔም ተግባራዊ ከሆነ የኢህኣዴግ መንግስት ግብኣተ መሬት የሚከት ይሆናል።
70 ሺ ኢትዮጵያውያን ውድ ሂወታቸው የከፈሉበት መሬት ለኢህኣዴግ ስልጣን ማራዘምያ ተብሎ ተቆርሶ ለማንም ኣይሰጥም።
የጠቅላይ ምኒስትሩ የተለመደ ጭሆት የሰሙ ኣንዳንድ ወገኖች ባልተለመደ ሁኔታ በደስታ ሲፈነጩ ኣይተናል።
“ሶስተኛው ኣማራጭ” ምን እንደሆነ ሳያውቁ፣ ኣማራጩ ተግባራዊ ይሁን ኣይሁን ሳያረጋግጡ የሚሸልሉና የሚዘሉ ወገኖች ኣጋጥመውናል።
ይሄ የተለመደ ባዶ ጭሆት ተከትለው ያልተለመደ ፈንጠዝያ የሚያሰሙ ወገኖች ስንመለከት “ፈስ ያለበት ዝላይ ኣይችልም” ከማለት ምን ልንላቸው እንችላለን።
ኣቶ ሃይለማርያም ሶስተኛው ኣማራጭ ስላሉት ጉዳይ እኔ በበኩሌ ኣላምኖትም።
ምክንያቱ
ሀ) “የማያዳግም እርምጃ ”
ለ) “ተመጣጣኝ እርምጃ ” የሚሉ ፍኮራዎችዎ ውሃ በልቷቸው ሲቀር ኣያቻለውና ነው።
የኢህኣዴግ ፊተውራሪው ህወሓት በሻዕብያ ፍቅር ቅልጥ ያለና ምንም ቢሆንም በሻዕብያ እንደማይጨክን ኣውቃለው።
ሁለተኛው ፎቶ የባድመ ሰማእታት የመቃብር ቦታ ነው።

አቶ ዓባይ ወልዱ የወልቃይት ዐማሮችን በሰላማዊ ሰልፍ ተቀበሉኝ አለ

   


Image result for abay woldu
አቶ ዓባይ ወልዱ የወልቃይት ዐማሮችን ነገ በሰላማዊ ሰልፍ ተቀበሉኝ አለ፤ 6 መኪና ሙሉ የታጠቀ ኃይል ዛሬ አዲረመጥ ገብቷል
ነገ የካቲት 17 ቀን 2009 ዓም ወደ አዲረመጥ የሚሔደው አቶ ዓባይ ወልዱ በሰላማዊ ሰልፍ ድጋፍ ሕዝቡ እንዲቀበለው ቅስቀሳ እያሠራ ነው። በርካታ ካድሬዎች ተመድበው በእልልታና በሆታ ጌታቸው እንዲቀበሉ ከማስፈራሪያ ጋር ተነግሯቸዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ 6 መኪና ሙሉ የትግሬ ልዩ ኃይል ፖሊሶች ከነሙሉ ትጥቃቸው ዛሬ ገብተዋል። ከወታደራዊ ጥበቃም በተጨማሪ ሰላማዊ ሰልፍም ያደርጋሉ ተብሏል። Muluken Tesfaw

የትረምፕ የውጭ ፖሊሲ – ሰሎሞን አባተ (VOA)


 2  464  466
ሰሎሞን አባተ
ከሩሲያ ጋር አብረው ሊሠሩ የሚችሉባቸውን አካባቢዎች መፈለግ፤ በኢራንና በቻይና ላይ ኾምጠጥ ያለ አቋም በመያዝ ለእሥራኤል መሪ ለቤንጃንሚን ኔታንያሁ ጠንካራ ድጋፍ በመሥጠት በሃገራቸው የውጭ ፖሊሲ ላይ ለውጦችን እንደሚያመጡ ዶናልድ ትራምፕ በምርጫ ዘመቻቸው ወቅት ቃል ሲገቡ ነበር፡፡
እነሆ የዘመቻ ወቅት አብቅቶ የምርጫ ውጤት ለይቶ “ፕሬዚዳንት ትረምፕ” እየተባሉ ሲጠሩ ልክ አንድ ወራቸውን ከትናንት በስተያ ደፈኑ፡፡
አሁን የትረምፕ አስተዳደር የዕይታውን ጥራት እንደገና እየፈተሸ፤ እንደገና እያነጣጠረና የዒላማውንም ምንነት እየለየ ነው፡፡
ቃል መኀላቸውን ከፈፀሙ በኋላ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ባደረጉት ንግግር ከእንግዲህ ወዲያ የሃገራቸው የውጭ ፖሊሲ የሚመራው በአንድ መርህ ብቻ መሆኑን አጠንክረው አውጀዋል፡፡
“ከዛሬ አንስቶ መመሪያችን አሜሪካ ትቅደም ብቻ ነው፤ አሜሪካ ትቅደም፡፡ በንግድ፣ በግብሮች፣ በኢሚግሬሽን፣ በውጭ ጉዳዮች በምንወስደው በያንዳንዱ ውሣኔ!” ብለዋል ትረምፕ፡፡
ፕሬዚዳንቱ በመጀመሪያው የሥራ ወራቸው ለአሥሮች ዓመታት ፀንተው በቆዩ የተለመዱ አሠራሮችና በዓለምአቀፍ ግንኙነቶች ላይ ለውጦችን ማድረግ ጀምረዋል፡፡
ትረምፕ በቅርቡ የእሥራዔልን ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁን ዋይት ሃውስ ውስጥ ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡ ይህ የሁለቱ መሪዎች ስብሰባና ውይይት በቀደሙት ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ዘመን የሻከረውን የዩናይትድ ስቴትስ – እሥራዔል ግንኙነት መሻሻል አዲስ ዘመን ያሳያል ተብሏል፡፡
ትረምፕ ለመንበረ-ርዕሰ-ብሔር ዘአሜሪካ ይወዳደሩ በነበረ ጊዜ የዩናይትድ ስቴትስን ኤምባሲ ከቴል አቪብ ወደ ኢየሩሣሌም እንደሚያዞሩ ቃል ሲገቡ ነበር፡፡ ኔታንያሁ በኃይል በተያዙ የዮርዳኖስ ወንዝ ምዕራባዊ ዳርቻ አካባቢዎች እያካሄደች ያለችውን የሠፈራ ግንባታም የመደገፍ አዝማሚያ ነበር የሚስተዋልባቸው፤ ቢያንስ ሲቃወሙት አልተሰሙም፡፡
አሁን ግን የያኔው ትረምፕ አይደሉም፡፡ አሁን ፕሬዚዳንት ትረምፕ ናቸው፡፡ ፕሬዚዳንት ትረምፕ ያንን በእሥራዔል የአሜሪካን ኤምባሲ አድራሻ የማዞር ሃሣባቸውን ዛሬ ቀዝቀዝ አድርገውታል፡፡ ኔታንያሁ ደግሞ ይህንን የሠፈራ ግንባታ የሚባል ነገራቸውን ገታ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ የእሥራዔልና የፍልስጥዔምን ግጭቶች ለማስቆም ይረዳል ስትል ዩናይትድ ስቴትስ ለረዥም ጊዜ ይዛው ለቆየችው የሁለት መንግሥታት ምሥረታ መፍትኄም ትረምፕ ቀልባቸውን የሰጡ መስለዋል፡፡
“የሁለት መንግሥታት ምሥረታንም፤ የአንድ መንግሥት መፍትኄንም እያስተዋልኩ ነው፤ ሁለቱም ወገኖች የሚወድዱትን እኔም እወድደዋለሁ” ብለዋል ከጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ጋር ሆነው ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት፡፡
ኢራን ኒኩሌር የጦር መሣሪያ እንዳትሠራ ለማድረግ የሚዝቱት ትረምፕ የዛሬ ሁለት ዓመት አካባቢ በአንድ ወገን በቴሕራንና በሌላ ደግሞ በስድስቱ የዓለም ኃያላን መካከል የተፈረመውን ስምምነት አብዝተው ሲነቅፉ ይሰማሉ፡፡ “በዕውኑ መጥፎ ስምምነት” እያሉ ነው የሚጠሩት፡፡
ኢራን በቅርቡ ላካሄደቻቸው የሚሳይል ሙከራዎች ትረምፕ አዳዲስ ማዕቀቦችን ጥለውባታል፡፡ “ኢራን ኒኩሌር የጦር መሣሪያ መቼም ቢሆን ጨርሶ እንዳትሠራ ለማድረግ ሌሎችም እርምጃዎችን እወስዳለሁ፡፡ ምቼም ቢሆን ኒኩሌር የጦር መሣሪያ እንዳትሠራ እያልኩ ነው” ብለዋል፡፡
ሌላው ትረምፕ የሚነሱበት ጉዳይ ሩሲያ ነች፡፡ ምንም እንኳ በሞስኮና በቴሕራን መካከል እጅግ የጠበቀ ግንኙነት እንዳለ ቢታወቅም፤ ምንም እንኳ ባለፈው የዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ ውስጥ እጆቿን ጣልቃ አስገብታለች ተብላ ብትከሰስም፤ ከሩሲያ ጋር እኮ የተሟሟቀ ግንኙነት ቢኖረን አይከፋም ባይ ናቸው፡፡ ይህንን ሃሣባቸውንም በተደጋጋሚ ሲገልፁ ይሰማሉ፡፡
ምክትል ፕሬዚዳንታቸው ማይክ ፔንስ ግን ባለፈው ሣምንት ማብቂያ ላይ ይህ የትረምፕ ሃሣብ ለሚያሰጋቸው የአውሮፓ አጋሮቻቸው የፅናት ማረጋገጫዎችን አጠንክረው ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡
“በፕሬዚዳንት ትረምፕ አመራር ዩናይትድ ስቴትስ ሩሲያን በተጠያቂነት መያዟን የምትቀጥል ቢሆንም ፕሬዚዳንቱ በሚያምኑበት ሁኔታ በጋራ ልንሠራ የምንችልባቸውን አዳዲስ መንገዶችም እንፈልጋለን” ብለዋል ምክትል ፕሬዚዳንት ፔንስ፡፡
ቻይና የገንዘቧን የምንዛሪ አቅም እንዳሻት በማጠማዘዝ ታጭበረብራለች ሲሉ በምረጡኝ ዘመቻቸው ወቅት የሚያብጠለጥሏትን ቻይናን በበጎ እምብዛም ሲያነሱ ተሰምተው አይታወቁም ነበር፡፡ “በጨዋታ ሕግ ተመርተው አያውቁም፤ አሁን መጀመር ያለባቸው ጊዜ እንደሆነ አውቃለሁ” ብለዋል፡፡
ከቻይና በሚገቡ ሸቀጦች ላይ አዳዲስ ታሪፎችን እንደሚጭኑና ዩናይትድ ስቴትስ ከቻይና ጋር ያሏትን የንግድ ፖሊሲዎች እንደሚለውጡ ሲዝቱ ተሰምተዋል፡፡
ይሁን እንጂ ፕሬዚዳንቱ የዋይት ሃውስ ሥራቸውን ከጀመሩ አንስቶ አስተዳደራቸው በእነዚያ ጉዳዮች ላይ ብዙም ሲናገር አይሰማም፡፡ ይልቅ ትኩረቱን ወደ አካባቢያዊ የፖለቲካ ትንቅንቆችና ንትርኮች አዙሯል፡፡
በአንድ በኩል በርግጥ ታይዋንን በሚመለከት ትረምፕ የቆየውን የአሜሪካ የ“አንድ
ቻይና” ፖሊሲ እንደሚደግፉና እንደሚያራምዱ አረጋግጠዋል፡፡ በሌላ በኩል ግን ቻይና በደቡብ ቻይና ባሕር ላይ አለኝ የምትለውን የግዛት ባለቤትነት ጉዳይ ዋሺንግተን ጥያቄ ውስጥ ማስገባቷን ቀጥላለች፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ የባሕር ኃይል የጦር ጄቶች ተሸካሚና አጥቂ ጓድ መደበኛ የውጊያ ልምምዱን እዚያው ደቡብ ቻይና ባሕር ውስጥ ሰሞኑን ጀምሯል፡፡
ይህ ልምምድ እየተካሄደ ያለው ቻይና በአካባቢው ላይ አለኝ በምትለው ሉዓላዊ ይዞታዋ ላይ ጣልቃ እንዳይገባባት እያስጠነቀቀች ባለችበት ሁኔታ ውስጥ ነው፡፡
“በትረምፕ አስተዳደር ውስጥ በቻይና ላይ በተለይ የደቡብ ቻይና ባሕርን በሚመለከት ጠንከር የማለት ፍላጎት እንዳለ ይሰማኛል፡፡ ይሁን እንጂ ግልፅ ፖሊሲ ስለመኖሩ ከመግለጫዎቹ በውል የሚታወቅ ነገር የለም” ብለዋል የስትራተጂያዊና የዓለምአቀፍ ጥናቶች ማዕከል ባልደረባዋ ቦኒ ግሌሰር፡፡
አዲሱ የትረምፕ አስተዳደር መሪው ላይ ከተቀመጠ እነሆ አንድ ወር ተጠቀቀ፡፡ ዶናልድ ትረምፕ የ“አሜሪካ ትቅደም” ፖሊሲያቸውን ምንነት ይበልጥ እያጠሩ በሄዱ መጠን ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ባሏቸው ግንኑነቶች ላይ ይበልጥ የመመቻቸት አዝማሚያ እየያዙ የሚሄዱ ይመስላሉ፡፡

Thursday, February 23, 2017

በጃናሞራ የዐማራ ገበሬዎች በአገዛዙ ላይ ተቃውሞ እንዳነሱ ተሰማ

   


በጃናሞራ የዐማራ ገበሬዎች በአገዛዙ ላይ ተቃውሞ እንዳነሱ ተሰማ | ኃይለማርያም የወልቃይት የዐማራ ብሔርተኝነት ጥያቄን ካዱ
ከሙሉቀን ተስፋው

– የዐማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛዎች በዳኛ ቢኒያም ዮሐንስ ላይ የተወሰደውን እርምጃ ተቃወሙ፤
– በጃናሞራ የዐማራ ገበሬዎች በአገዛዙ ላይ ተቃውሞ እንዳነሱ ተሰማ፤
– በወገራ የገበሬዎች ቤት የወያኔ ወታደሮች ካምፕ እንደሆነ ተገለጸ
– ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የተነሳ የማንነት ጥያቄ የለም ሲሉ የወልቃይት የዐማራ ብሔርተኝነት ጥያቄን ክደዋል
– በነማስረሻ ሰጤ መዝገብ የተከሰሱ የዐማራ ወጣቶች በሐሰት ውንጀላ ጥፋተኛ ተባሉ፤

ዝርዝር፤
፩ ትናንት የካቲት 14 ቀን 2009 ዓ.ም. በሰሜን ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ የሆኑት አቶ ቢኒያም ዮሐንስ ችሎት ላይ እንዳሉ የወያኔ ደኅንነቶች አፍነው መውሰዳቸውን ተከትሎ የዐማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች ዛሬ ተቃውሟቸውን መግለጻቸው ተሰምቷል፡፡ ዳኞቹ የፍርድ ቤትን አሠራርንና ሕገ መንግሥትን በጠራራ ፀሐይ ሙልጭ አድርጎ የጣሰ የማፍያ ሥራ መሆኑን ለፍትኅ ቢሮ አስታውቀዋል ተብሏል፡፡ ወያኔ ምንም እንኳ በዳኞች ውሳኔ ላይ ጣልቃ በመግባት ይህ የመጀመሪያው ባይሆንም እንዲህ ያለው ዐይን ያወጣ የማፍያ ሥራ ግን በታሪክ ታይቶ አይታወቅም ሲሉ ተችተዋል፡፡ አብዛኛዎቹ ዳኞች መደበኛ ሥራቸውን እንዳላከናወኑ ተገልጧል፡፡
አቶ ቢኒያም ዮሐንስን እንዲታሰር ያደረገው አዲሱ የጎንደር ማረሚያ ቤት ሹም የትግራይ ተወላጁ ጀማል ሰኢድ ሲሆን በዳባት ማረሚያ ቤት በነበረ ጊዜ ለበርካታ ወጣቶች እንግልትና ሞት ተጠያቂ እንደሆነም መረጃዎች እየወጡ ነው፡፡
፪ በሰሜን ጎንደር ዞን የጃናሞራ ዐማራ ገበሬወች ዛሬ የካቲት 15 ቀን 2009 ዓ.ም ተጋድሎ መጀመራቸው ተሰምቷል፡፡ ገበሬዎቹ የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ጉዳይ በአስቸኳይ መፍትሔ ካልተሰጠው እና በዐማራ ወጣቶች ላይ የሚደርሰው ግድያ እና እስራት ካልቆመ ተጋድሏቸውን እንደማያቆሙ ተነግሯል፡፡ በአካባቢው የስልክ አገልግሎት አስቸጋሪ በመሆኑ ዝርዝር ጉዳዮችን ማግኘት አልቻልንም፡፡
፫ በተያያዘ ዜና ደግሞ በወገራ ወረዳ የእንቃሽ አካባቢ ገበሬዎች መኖሪያ ቤቶች ወደ ወታደር ካምፕነት መቀየራቸውን የጎብዝ አለቆች ገልጸውልናል፡፡ ‹‹ቤታችን አቃጥለውት እንደገና ለመሥራት እየሞከርን ነበር፤ ሆኖም ባለፈው ሳምንት መጥተው እንደገና ጦርነት ከፈቱብን፡፡ ተታኩሰን ወደ ጫካ ወጣን፡፡ ካልያዝን ወይም ካልገደልን አንመለስም ብለው ቤታችንን እንደካምፕ እየተጠቀሙ እዚያው እየኖሩ ነው›› ሲሉ አንድ የጎበዝ አለቃ ማምሻውን ገልጾልናል፡፡ እንደ ጎበዝ አለቃዎቹ ገለጻ አሁን ላይ ዝናብ እየዘነበ ሲሆን እርሻም ማረስ የሚጠበቅ ቢሆንም በግፍ ከቤታችን ተፈናቅለን በጫካ ለመኖር ተገደናል ብለዋል፡፡
፬ የወያኔዎቹ አሽከር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ትናንት ባአከር ኹመራ ላይ ከትግሬ ሰፋሪዎች ጋር ባደረገው ንግግር የተነሳ የማንነት ጥያቄ የለም ሲል እንዲናገር የታዘዘውን አስተጋብቷል፡፡ ይህም በመቶ የሚቆጠሩ የዐማራ ወጣቶች ሕይወት የጠፋበትን የወልቃይት ጠገዴ የዐማራ ማንነት ጥያቄን ነው የደመሰሰው፡፡ በሌላ በኩል የብአዴኑ ደመቀ መኮነን በሳምንቱ መጀመሪያ ከጎንደር ከተማ ሕዝብ ጋር ባደረገው ስብሰባ የወልቃይት የማንነት ጥያቄ ዋናው የመወያያ አጀንዳ እንደነበር እንዲሁም እርሱም በአፋጣኝ ሊፈታ እንደሚችል ተናግሮ ወጥቷል፡፡ የፋና ብሮድካስቲንግ የወልቃይት ጠገዴን የማንነት ጥያቄ አፈታት በተመለከተ ዜና ሰርቶ በወያኔዎች ትእዛዝ ወዲያውኑ አንስቶታል፡፡ ስለሆነም ከትግሬ ጠባብ ብሔርተኞች ጋር የሚደረገው የሞት የሽረት ተጋድሎ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የአካባቢው ተወላጆች ተናግረዋል፡፡
፭ በነማስረሻ ሰጤ የክስ መዝገብ በተከሰሱ 6 የዐማራ ወጣቶች ላይ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ 4ኛ ምድብ ችሎት የእስር ውሳኔ መስጠቱ ተገልጧል፡፡ በስድስቱ የዐማራ ወጣቶች ላይ የቀረበው ክስ ከግንቦት 7 ጋር የተያያዘ እንደሆነና ከ6 እስከ 10 ዓመት የሚደርስ ጽኑ እስራት መሆኑን መረጃውን የላኩልን ሰዎች ተናግረዋል፡፡
የዐማራ ተጋድሎ ያሸንፋል/

በኢትዮጵያ ድርቅ ወደ አስከፊ ረሀብ ሊደርስ እንደሚችል ለጋሽ ድርጅቶች እያስጠነቀቁ ነው።

   


በኢትዮጵያ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ባገረሸው ድርቅ 5.7 ሚሊዮን ሕዝብ አስቸኳይ የምግብ ርዳታ ይፈልጋል። ድርቁ ባለፉት ዐስርት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ከታዩት የከፋ መሆኑ አሳሳቢ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ገልፆ ሕዝቡን ከረሃብ ለመታደግ የሚያስችለውን ሥራ ለማከናወን 1 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ያስፈልጋል ብሏል።
በኢትዮጵያ በአምስት ክልሎች ከተከሰተው ድርቅ በተለይ በሁለቱ ክልሎች በኦሮሚያ እና በሶማሊያ የደረሰው ወደ አስከፊ ረሀብ ሊደርስ እንደሚችል ለጋሽ ድርጅቶች እያስጠነቀቁ ነው።
በአሁኑ ሰዓት ድርቁ ከብቶች እየጨረሰ ነው ከተባለበት አካባቢዎች አንዱ የሆነው የቦረና አርብቶ አደሮች ከብቶቻቸው እያለቁ መሆኑን ገልፀው የተረፉትን ገበያ ሲያወጧቸው ከ10 ሺሕ በላይ ይሸጡ የነበሩ ከብቶች ከ400 ብር ያነሰ እንደሚገመቱባቸው ይናገራሉ።

Wednesday, February 22, 2017

ሰላም፡ አንድነት፡ ተስፋ (ሰማያዊ) በግሬስ አባተ

   


thsmown0lm

ሰማያዊን አስመልክቶ ፓርቲው እንደፈረሰ እንዲሁም አዲሶቹ ተመራጮች ላይ በተለይም አዲሱን ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ ላይ አሮጌው ፍረጃ እየወረደ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም በተቃውሞ ጎራው ጉዳይ ላይ ደጋግሜ እንዳልኩት ፈረጃ ስልጡኑን ቁጭ ብሎ የመነጋገር እድልን የሚዘጋ አሮጌ መንገድ ነው፡፡ ይህም የተቃውሞ ጎራውን አንካሳ ሲያረግ የኖረ ነው፡፡ ላንዳንዶች ፓርቲ የግለሰቦች ንብረት ይመስላቸዋል፡፡ ለዚህ ነው ግለሰቦቹ ሲሄዱ የሚፈርስ እነሱ እስካሉ የሚቆም የሚመስላቸው፡፡ ለምሳሌ ኢ/ር ይልቃል የነበረውን ችግር ለመፍታት እድሉ በእጁ ነበር፡፡ ሌላው ሁሉ ቀርቶ በጠቅላላ ጉባኤው ላይ ተሳትፎ መሟገት ይችል ነበር፡፡ በእጁ የነበሩትን መድረኮች ከመጠቀም ይልቅ ዳር ዳር ሲል ቆይቶ በመጨረሻ አማራጭ ያደረገው አሮጌውን መንገድ ነው፡፡ በግለሰቡ ፍቅር የወደቁ ተከታዮቹም ከዛ የተሻለ ነገር ማድረግ አልቻሉም፡፡

በጣም የሚገርመው በማንኛውም ተቋማት ውስጥ በመሪነት ላይ ያሉ ሰዎች ጥሩ ነገር ሲሰራ መመስገናቸው ያለ በተቃራኒው ሲሆን ደግሞ ተጠያቂ የሚሆኑበት ሁኔታ ያለ ቢሆንም በኢትዮጵያ የተቃውሞ ጎራ ውስጥ ግን ለሚሰሩ ስህተቶች ሌሎችን ‹‹ወያኔ›› ማለት እራስን ከስህተት ነፃ የሚያደርግ ነው፡፡ ይህን ሳይመረምሩ አሁንም ላለፉት ሁለት አስርታት በተሄደበት መንገድ ለመሄድ መጣደፍ ሌሎች ሁለት አስርታትን ቁጭ ብሎ ከመቁጠር የዘለለ ነገር አያመጣም፡፡ ለግለሰቦች ከማልቀስ በዘለለ ፓርቲዎች የለውጥ እንቅስቃሴውን መሸከም የሚያስችል አቅም እንዲፈጥሩ ከማገዝ ይልቅ የሥነ-ሥርዓት ኮሚቴው ላይ እንደሆነው የበላይ አመራሮችን የመጠየቅ አቅም መፍጠሩ ከማስመስገን ይልቅ የአሮጌው ፖለቲካ ሰለባ ነው ያደረገው፡፡ በዚህ ሁኔታ እንዴት ተቋማዊ ቅርፅ ያለው የለውጥ ሀይል እንደሚፈጠር ግራ ያጋባል፡፡

ሌላው አንድነት ላይ የሆነውን በማንሳት የሰማያዊም ተመሳሳይ እንደሆነ ለመግለፅ የሚሞከረው ከላይ ለማንሳት እንደሞከርኩት እራስን ከስህተት ነፃ ለማድረግ እንዲሁም ካፈርኩ አይመልሰኝ ነው፡፡ ሌላው ሁሉ ቀርቶ አንድነት ውስጥ ከተፈጠረው ችግር ጀምሮ አባላት ከፅህፈት ቤታቸው በፖሊስ ሃይል እንዲወጡ ተደርጎ ለአቶ ትዕግስቱ አይነት መካሪ አልባ ሰው ፓርቲው እስኪሰጥ አብሮት የነበረው ከፍ ካለው የፓርቲው መዋቅር አንድ ግለሰብ ብቻ ነው፤ አባል የነበሩት በጣት የሚቆጠሩ ነበሩ ሌሎች ከየት እንደመጡ እንኳን አይታወቅም፡፡ በሰማያዊ ውስጥ በብቸኝነት በሚመስል መልኩ አቶ የሺዋስ ላይ ፍረጃ የሚያካሂዱት እንደ አቶ ትዕግስቱ ከምርጫ ቦርድ ሰማያዊን በችሮታ ያገኘ ለማስመሰል ነው፡፡ ለዚህ ነው በጠቅላላ ጉባኤ ስለተሳተፉ ግለሰቦች፣ስለብሔራዊ ምክር ቤት አባላት፣እንዲሁም አሁን ስላሉት ስራ አስፈፃሚ አባላት ትንፍሽ ሲሉ የማይሰማው፡፡ ይህ የአሮጌው ፖለቲካ ሌላው ምሳሌ ነው፡፡

ከላይ እንዳልኩት ይህ አሮጌ ፖለቲካ ውዥንብር በመፍጠሩ ሰማያዊን አንካሳ ሊያደረግ እንደሚሞክር ግልፅ ነው፡፡ አሁን ያለው አመራር ለዚህ ጆሮ ሳይሰጥ ቆፍጠን ብሎ ጥሩ የሚባሉትን በማጎልበት ያለፉትን ህፀፆች በመመርመር ለምሳሌ በውስጠ ዲሞክራሲ እና በተቋማዊነት ላይ ጠንክሮ መስራት ይጠበቅበታል፡፡ ባጠቃላይ የተቃውሞ ፖለቲካውን የአሮጌው ፖለቲካ መፈንጫ ከመሆን ለመታደግ መስራት የሁሉም የለውጥ ሀይል ድርሻ ነው፡

Tuesday, February 21, 2017

ፕ/ር በየነ ምን እያሉ ነው ? ? ? ተስፋው የተንጠለጠለው ኢህአዴግ ላይ ነው


 

ፕ/ር በየነ ምን እያሉ ነው ? ? ?
ካለፉት የተለየና የተሻለ ትኩረት የተሰጠው መሆኑን ም/ ጠ/ሚ/ሩ ኢህአዴግን ወክለው በመክፈቻው ላይ መገኘታቸው ተስፋ እንዲሰንቁ መነሻ እንደሆናቸው ገልጸዋል፡፡
እኔ ፕሮፌሰሩ ተስፋ በመሰነቃቸው ችግር የለብኝም፡፡ ‹ በጎውን ማሰብ ከበጎ ያደርሳል › ከሚል ቀና አስተሳሰብ የመነጨ ነው ቢሉ የተሻለ ነበር፡፡ ግን ተስፋ እንዲሰንቁ ስላበቃቸው ያቀረቡት ምክንያት ፕሮፌሰሩ ምን እያሉን ነው የሚል ጥያቄ አጭሮብኛል፡፡ ጥቂቶችን እንመልከት፡፡
ፕ/ር በየነ ከዚህ በፊት ‹አሁን ከነገሩን የተስፋ መነሻ›› በበለጡ መድረኮች ራሳቸው ተሳትፈዋል፣ በጭንቅ ጊዜ /በክፉ ቀን/ ህወኃት/ኢህአዴግ ስለተቃዋሚዎች ያላቸውን በጎ ነገሮች እና ጭንቁ/ ክፉው ቀን ሲያልፍ የሚሉትንና ያደረጉትን ያውቃሉ ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ከሌሎች ጋር በጠቅላይ ሚ/ር ደረጃ የተደረገውንና የሆነውን ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡ እንመልከታቸው፡፡
1ኛ / በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት ጠ/ሚ/ሩ ስለቃውሞ ጎራው በአደባባይ የሰጡት ቃለ ውዳሴና እንዳበቃ ሲደረግ የነበረው፤
2ኛ/ በ1977 ምርጫ ወቅት በሦስተኛ ወገን አደራዳሪነት /ዲፕሎማቶች–አሜሪካ ቆንሲል እና አውሮፓ ኅብረት/ የወቅቱ ጠ/ሚ/ር አቶ መለስ ዜናዊ ቅንጅትና ኅብረት በጋራ የጠሩት የተቃውሞ እርምጃን ይሰርዙት እንጂ ‹ከሰማይ በታች ባለ በማንኛውም ጉዳይ እንነጋገራለን › ባሉበት ኅብረቱን ወክለው ተደራዳሪው እርሳቸው ነበሩ፤በድርድር በተገኘው ውጤት መሰረት ከሌሊቱ 6፡00 ሰዓት ተቃውሞው መሰረዙን ‹ ያበሰሩን › አንዱ እርሳቸው ነበሩ፡፡ ከተቃውሞው መሰረዝ በኋላ የሆነውን ያውቃሉ፡፡
3ኛ/እርሳቸው የተሳተፉበት በተወካዮች ምክር ቤት አባል ፓርቲዎች መካከል የተደረጉ ድርድሮች፤ የተደረሰባቸው ስምምነቶችና ተግባራዊነታቸው፤
4ኛ/ የቀድሞው ሦስት ፓርቲዎች ጋር ያረቀቁት የሥነምግባር ደንብ (አዋጅ የሆነው) ከአርቃቂዎቹና ቀዳሚ ፈራሚዎቹ መኢአድ ከጋራ ምክር ቤት ለመውጣት የተገደደበት እውነታ፤
5ኛ/ በኢህአዴግ ፈቃድ ስለተቋቋመውና ‹መድረክ› የሥነ ምግባር ደንቡን አልፍምም በማለት ለማያሳተፍበት የ ‹‹ ፓርቲዎች የጋራ የፖለቲካ መድረክ›› የተለየ ውጤት ያለማምጣት ሲናገሩ እንደነበር፤ የማናውቃቸው የጓር ድርድሮች የመኖር ዕድል እንደተጠበቀ ሆኖ- ሁላችንም የምናውቀው የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡
በእነዚህ ሁሉ በውይይቱ የተደረሰባቸው ስምምነቶች፣ የተፈረሙ ውሎች … እና በተግባር የተፈጸመውን እያወቁ፣ አሁን ድርድር እየተደረገ ነው በሚባልበት ጊዜ የብዙ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች በተለይ ደግሞ እርሳቸው ጠንካራ የሰላማዊ ታጋይ ስለመሆናቸው የሚመሰክሩላቸውን ምክትላቸውን አስረው ባሉበት እንደምን የም/ጠ/ሚሩ መገኘትን ከወትሮው የተለየ ተስፋ እንዳሰነቃቸው አልገባኝም ፡፡ የተስፋው መገለጫ ግራ አጋባኝ ፣ የአስተያየቱ ጊዜ ፈጠነብኝ፡፡
በተያያዘ ሌላ ጥያቄ የጫረብኝ ጉዳይ አለ፡፡ ስለድርድሩ ስድስት ፓርቲዎች በጋራ መግለጫ ሲሰጡ እርሳቸው የሚመሩት ‹መድረክ› ስለምን አብሮ እንዳልቆመ አለማስረዳታቸው ነው፡፡ ይህን ሳያስረዱ በተናጠል አቋም ይዞ በሚደረግ ‹ድርድር› እንዴት ተስፋ ይሰነቃል፤ አሁንም ተስፋው የተንጠለጠለው ኢህአዴግ ላይ ነው ማለት አይሆንም ትላላችሁ? ለዚህ ጥያቀዬ መነሻ የሆነኝን የተከበሩ አቶ ቡልቻ ከአራት ዓመት በፊት/ አዲስ ገጽ -ታህሳስ 2005/ የመድረክና አንድነትን ውዝግብ በሚመለከት ‹ ስለመድረክ › የተናገሩትን ልጥቀስ ፡፡ ‹‹ሳናፍር እውነቱን እንነጋገር ካልን ብቻችንን አጥቂዎቻችንን መመከት አልቻልንም፡፡ይህን ስል በፖለቲካ ሙግት፣ በገንዘብና ዓለምአቀፍ ደረጃ የፖለቲካ ድጋፍ ማግነትን አስመልክቶ እንጂ በጦር ኃይል ማለቴ አይደለም፡፡ ….የእርሰስ በርስ ጦርነት በፍልስፍናዬ የተወገዘ ነው፡፡ ›› ዛሬስ መድረክ አከዚያን ጊዜ የተሻለ የፖለቲካ ሙግት የማድረግ አቅም ላይ ነውን ? የሚለውን ሳስብ ብቸኝነቱ የተናጠል ጉዞው ቢያሳስበኝ ነው፡፡ ከዚህ ጋር መነሳት ያለበት ከ‹ቀለብተኞቹና የኢህአዴግ ስሪቶች ውጪ› ያሉት ወይም ነን የሚሉት የተቃውሞ ጎራው በኅብረት ያለመቆም ጉዳይ ነው፣ ቢያንስ ስለድርድሩ የጋራ አቋም ለመውሰድና በአንድ ድምጽ ለመደራደር እንደምን ወይም ለምን ተሳናቸው ?፡፡ ዛሬም እዚያው ናቸው ፣ ተነጣጥለው ውጤት ይጠብቃሉ ማለት ነው? ከጊዜ ጋር መልስ የሚያገኝ ቢሆንም እኔ ግን አይታየኝም፡፡ እየሆነ ያለው ነገር የተቃዋሚ ጎራው አመራሮችን በህዝብ ትዝብት ላይ የሚጥላቸው፣ የህዝብ ተኣማኒነትን አሳጥቶ እነርሱ የሰነቁትን ተስፋ ህዝብ እንዳይጋራና ከጎናቸው እንዳይቆም የሚያደርግ ነው፡፡
የመከራ ቀናችን እንዲያጥር፣ ዘላቂ መፍትሄ እንድንቀዳጅ፣ ማስተዋሉን ፣ በጎውን በልቡናችን ያሳድረው፡፡ በቸር ያገናኘን፡፡ 13/06/09.

Monday, February 20, 2017

ይልቅ ወሬ ልንገርህ: ስለ ቀድሞው የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ‘የኑሮ አቤቱታ’

(ቁምነገር መጽሔት) የመጀመሪያውን የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳን ታውቃቸዋለህ አይደል? እንዴታ አልክ? እነሆ እኝሁ የቀድሞ ፕሬዚዳንት የኑሮ አቤቱታ ስለማሰታቸውን ዕለታዊው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ነግሮናል፤ እንዴት አልክ?ፕሬዚዳንቱ ከጋዜጣው ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ላይ ‹የሀገሪቱ አቅም በሚፈቅደው መሠረት የሚገባኝን ክብር አላገኘሁም› ስለማለታቸው ዘግቧል፡፡ እንዴት አልክ? ለመሆኑ ሀገሪቱን ለስድስት ኣመታት ያህል በመምራት በርካታ አምባሳደሮችንና ዲፕሎማቶችን ሲቀበሉና ሲሸኙ ስለኖሩት ዶ/ር ነጋሶ ከስልጣን ከወረዱ በኋላ እንዴት አይነት ኑሮ እየኖሩ እንደሆነ ታውቃልህ? አታውቅም አይደል?

ይኸውልህ፤ እሳቸው እንዲህ ይላሉ፤
‹ አሁን ካለሁበት ቤት ውጣ ተብዬ ሁለቴ ተፅፏል፡፡ ለቤት ውስጥ እና ለኑሮ የማወጣውን ገንዘብ ተከልክያለሁ፡፡ የምኖረው በ1ሺህ 700 ብር የፓርላማ ደመወዝ ነው፡፡ መኪናም ተቀምቻለሁ፡፡ ይህን የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ቢያውቁት ጥሩ ነው፡፡ የቤት ሠራተኛ ባለቤቴ ናት የቀጠረችው፡፡ ጥበቃም በትንሽ ገንዘብ ቀጥሬ ነው። ለህክምና የባለቤቴ ጓደኞች መደሃኒት ገዝተው ባይልኩልኝ ከባድ ነበር የሚሆንብኝ፡፡ ጠዋት እና ማታ አምስት ኪኒን ነው የምወስደው፡፡ የደም ስሮቼ ይዘጋጋሉ፡፡ ለህክምና እና ምርምራ ከሄድኩኝ ሁለት ዓመት ሞልቶኛል፡፡ የስኳር እና የልብ በሽታ አለብኝ፡፡ ለመመርመር እና ውድ መደሃኒቶች ለመግዛት ገንዘብ የለኝም፡፡ ባለፈው ሳምንት ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ፕሬዚዳንቱ ጋር በታክሲ ነው የሄድኩት፡፡ የአገሪቱ አቅም በሚፈቅደው መጠን ክብር እና ጥቅም ይገባኝ ነበር። ይህ ለእኔ ተከልክሏል፡፡ ጥሩ ባለቤት እና የሰው ፍቅር ስላለኝ ደስ ይለኛል፡፡ ግን ይህ አገር እና መንግስት የሚገባኝን ጥቅምና ክብር አልሰጠኝም፡፡ ለወደፊትም ይህን ታሪክ ይፈርደዋል፡፡›
ለምን እንዲህ ሊሆን ቻለ? አልክ?
ዶከተር ነጋሶ ይቀጥላሉ፡- ‹ወገንተኛ ሆነሃል ተብዬ ነው፡፡ እውነቱን ከተናገርን እኔ የ1997 ዓ.ም ምርጫ በግል ነው የተሳተፍኩት፡፡ በግል ተሳትፌ ፓርላማ ከገባሁ በኋላም በምን ጉዳይ ላይ ወገንተኛ እንደሆንኩ መረጃ የለም፡፡ አዋጅ 255/94 አንቀፅ 7 ጥሷል ነው የተባልኩት፡፡ በአንቀፅ 13 መሰረትም መቀጣት አለበት ተባለ፡፡ ፍርድ ቤት እስከ ሰበር ሰሚ ድረስ ሄጄ ፍርድ በትክክል አልተሰጠኝም፡፡ ግን የመጀመሪያው ፍርድ ቤትም በግል በምርጫ መሳተፉ ችግር የለውም ብሏል፡፡ «ርዕሰ ብሄሩ ለህገ መንግስቱ፣ ለአገሪቱ እና ለህሊናው ታማኝ መሆን አለበት» ይላል ህገ መንግስቱ፡፡ ይህ እያለ ነው ኢ- ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ጥቅማ ጥቅም የተከለከልኩት፡፡ አሁን ካለሁበትም ቤት በማንኛውም ሰዓት በፖሊስ ያስወጡኛል ብዬ ነው በፍርሃት የምኖረው፡፡›
ታዲያ ይሄስ አሰራር ጥልቅ ተሃድሶ አያስፈልገውም ወይ አልክ? አንድ ወዳጄ ምን አለ መሰለህ? ‹ተሃድሶው ወደ ፊት ስለሚመጣው እንጂ ስላለፈው ነገር የሚጨነቅ አይደለም› በል ቻዎ. . 

የሕወሓት የደህንነት ቢሮ በትግራይ ተወላጆችና በኤርትራውያን ፍጥጫ ውጥረት ውስጥ ሲሆን የ አርበኞች ግንቦት ሰባት ታጋዮች ለግድብ ግንባታ ተወሰዱ። (ቆንጂት ስጦታው)



የሕወሓት የደህንነት ቢሮ በትግራይ ተወላጆችና በኤርትራውያን ፍጥጫ ውጥረት ውስጥ ሲሆን የ አርበኞች ግንቦት ሰባት ታጋዮች ለግድብ ግንባታ ተወሰዱ። (ቆንጂት ስጦታው – መረጃኮም )
ከ አዲስ አበባና አስመራ የተላኩ መረጃዎች በሕወሓት የደህንነት ቢሮ ውስጥ በትግራይ ተወላጆችና በኤርትራውያን መካከል በተነሳው ፍጥጫ የሕወሓት ባለስልጣናት ውጥረት ውስጥ የገቡ ሲሆን የትግራይ ተወላጆችን ኣንስቶ ወደ ክልሎች በተለይ ወደ ትግራይ መድቦ በ አንድ ለመጠርነፍ አና በመሃል ሃገር ያለውን የደህንነትና የስለላ ቡድን በ ኤርትራውያን ለመተካት የተደረገው ሙከራ ከባድ ችግር እንደገጠመው የደህንነት ምንጮች ለመረጃ ዶት ኮም የላኩት መረጃ ይጠቁማል። በኣስመራ በመቀሌና በ አዲስ አበባ በተከታታይ ከ ኤርትራ ለመጡ ሁሉ የኣማርኛና የኦሮሚኛ ቋንቋ ትምህርት ይሰጣል የሚሉት ምንጮች ሕወሓት በትግራይ ተወላጆች ላይ ያለው እምነት እየሟሸሸ ስለሆነ ቁልፍ የደህንነትና የስለላ ስራዎችን በ ኤርትራውያን እየተካ እንደሚገኝ ታውቋል።የኢሳያስ የስጋ ዘመድ የሆነው የማነ ጃማይካ የኣንበሳውን ድርሻ ይዞ ኤርትራውያንን ለደህንነት ቢሮው ይመለምላል ይቀጥራል።
የ አርበኞች ግንቦት ሰባት ታጋዮች ከግድብ ግንባታ ከ አስመራ ሰማኒያ ኣምስት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደሚገኝ ስፍራ መጓጓዝ መቀጠላቸውን በቦታው የሚገኙ ምንጮቻችን ገልጸዋል። ከምጽዋ በቅርብ ርቀት በምትገኘው ሰሜናዊ ቀይ ባህር ግዛት በወያኔ ድጋፍ ለሚገነባው ግድብ በምጽዋ ዶጋሊ ኣሉላ ኣባነጋ ከተወጉበት ኣከባቢ ጊንዳ አቅራቢያ ጋህቴላይ በሚባል የግድብ ግንባታ ስራ ላይ እንደሚገኙ ሲታወቅ በቦታው አይቶ ኢሳያስ ኣፈወርቂ ተገኝተው መጎብኘታቸውን ምንጮቹ ይናገራሉ።
ይህ በወያኔ ርዳታና ድጋፍ በኣርበኞች ግንባር ታጋዮች የጉልበት ሰራተኝነት የሚገነባው ግድብ በከፍተኛ ጥበቃ ስር የሚገኝ ሲሆን ጉዳዩ የማይመለከታቸው ኤርትራውያን በቦታው መግባት ኣይደለም ማለፍ እንደማይችሉ የሻዕቢያ ምንጮቻችን ለእረፍት ከመጡበት አስመራ የላኩት መረጃ ይጠቁማል። ግድቡ ከተጀመረ ሶስት ወር ሆኖታል።የ ኣርበኞች ግንቦት ሰባት ታጋዮች በሙሉ መሳሪያቸውን አስቀምጠው በጉልበት ስራ በሚሳተፉበት በዚሁ የጋህቴላይ ግድብ ስራ ላይ በበላይነት የሚቆጣጠሩት አዲስ አበባና መቀሌ ዩንቨርስቲ ሰልጥነው የመጡ ኢንጂነሮችና ፎርማኖች መሆናቸውን ምንጮቹ ሳይገልጹ ኣላለፉም። ተጨማሪ መረጃዎች ይለቀቃሉ ይጠብቁ ።

ወጣቱ የወልቃይት ጠገዴ የዐማራ የማንነት ኮሚቴ አባል ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ | መርዝ ተሰጥቶት ሊሆን እንደሚችል ጥርጣሬ አለ፤| ሙሉቀን ተስፋው

ወጣቱ የወልቃይት ጠገዴ የዐማራ የማንነት ኮሚቴ አባል ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ | መርዝ ተሰጥቶት ሊሆን እንደሚችል ጥርጣሬ አለ፤| ሙሉቀን ተስፋው
ወጣት አብድልረዚቅ ሞሳ የወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄን አንግበው ከሚንቀሳቀሱ የዐማራ ተወላጆች ግምባር ቀደም ይጠቀሳል። በአዲ ረመጥ፣ በኹመራ፣ በመቀሌና በሌሎችም ቦታዎች ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል በሕግ አግባብ ለመጨረስ ብዙ ለፍቷል።
ወጣት አብድልረዚቅ ሞሳ የወያኔ አገዛዝ ሊይዘው በፈለገ ጊዜ ከቦታ ቦታ በመንቀሳቀስ ከጊዜው እስር ቢያመልጥም የገጠመውን የጤና እክል በሚገባ እንዳይታከም ሆኗል። ሕመሙ ሲጠና ከሁለት ወራት በፊት በድብቅ ባሕር ዳር ታክሞ ወደ አዲረመጥ ተመለሰ። ሆኖም ሕመሙ ተባብሶበት ዛሬ የካቲት 12 ቀን 2009 ዓ.ም ከሰዐት በኋላ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
መረጃውን ያደረሱን ሰዎች እንደሚሉት የሕመሙ መንስኤ ወያኔዎች መርዝ ሰጥተውት ሊሆን እንደሚችል ጥርጣሬያቸውን ገልጸዋል። ወጣት አብድልረዚቅ በ30ዎቹ መጀመሪያ የእድሜ ክልል የሚገኝ ወጣት እንደነበር ለማወቅ ችለናል።
ለወዳጅ ዘመዶቹና ቤተሰቦቹ መጽናናትን እንመኛለን!!

ቤት የለለው ትግራዋይ ሁሉ የቤት ባለቤት ለማድረግ ፓርቲያችን ህወሐትና ዲሞክራሲያዊ መንግስታችን በቁርጠኝነት ወስኗል” – አባይ ወልዱ



የህወሐት አመራር በህዝብ የተጠላው ስርአቱ እድሜ ለመራዘም ታሳቢ በማድረግ ትናንትና የመኖርያ ቤት ከሊዝ ኪራይ ውጭ ፣ በማህበር ፣በግለ ሰው ሊሰጥ ከሆነ በህወሐት መቃብር ነው የሚደረግ ሲል ቆይቶ አሁን የትግራይ ህዝብ ብሎም የመላው ሀገራችን ህዝቦች የመኖርያ ቤት እጦት የወለደው ብሶት ለስልጣኑ ወይ የአፋኝ አገዛዙ እድሜ ለመራዘም በማይችልበት ደረጃ ስለደረሰና ስለሰጋ ተገድዶ እንደ የሽግሩ ቁልፍ መፍትሄ በሀገራችን ያለው የመጠልያ ቤት እጦት መሆኑ ተረድቶ ለጊዜው እንደ ማስታገሻ ወይ የእሳት አደጋ ማጥፍያ ስልት ለመጠቀም እንሆ 70 ሜትር ካሪ መሬት እንሰጣለን በማለት ዋናው አላማው ደግሞ የፖለቲካ ስልጣኑን እድሜ ለማራዘም በማድረግ እንሆ በትግራይ ክልል በ. 12 ትላልቅ ከተሞችና በ104 ታዳጊ ከተሞች 48 ሸ መተማመኛ በህወሐት አመራር ቁጥጥር በሚገኝ ደደቢት በንክ በዝግ በንክ እንዲ ቀመጥ በማድረግ እንዲሁም ለአርሶ አደሮች የመሬት ከሳ 5000 በር በድምር 53 000 ብር እያንዳንዱ ቤት ሰሪ ለመጀመሪያ እንዲ ከፍል ተገደዋል ።
በሌላ በኩል 187 000 ብር በ 12% ወለድ ለደደቢት በድርና ቁጠባ ባንክ ሊከፍሉ ውል እንዲገቡ ተገደዋል ። ይህ ብድር ከመንግስት ባንክ በ3% ይበልጣል ። ስለየባንክ እዳ ልዩነቱ በሚመለከት ካሁን በፊትም ገልጨው ነበር ።
የተከበራችሁ የኢትዮጱያ ህዝቦች አንድ አንድ ወገኖች ቀደም ሲል ዜጎች በሀገራቸው ቤት ሰርተው የሚጠለሉባት መሬት ማግኜት አለባቸው ስትል ነበርክ ፣ አሁን ደግሞ መንግስት መሬት ሲሰጠን ተቃውሞ ታነሳለህ በማለት ብዙ ወቀሳ ሰንዝሯቹሁብኛል ፣ በበኩሌ ግን ይቅርና 70 ሜትር ካሪ መሬት ከዛ ያነሰ ስፋት መሬት ቢሆን አልቃወምም ሁሉም ዜጋ ድንኳን ዘርግቶ የሚኖርባት ብትሆንም መሬት ማግኜት አለበት የሚል እምነት አለኝ ። እኔ እምቃወመው
1. የሚታደለው የቤት መስርያ መሬት ዜጎች ዜጎች በመሆናቸው የማግኜት መብታቸው የተጠበቀ መሆን እያለ የህወሐት መሪዎች እነ አባይ ወልዱና አዲስ አለም ባሌማ ግን በህዝብ እና ተቃዋሚ ፓርቲዎች ባደረጉት ትግል ተጽእኖ ፈጥሮባቸው ሳይወዱ በግድ እሬት እየጣማቸው መሬት ሰጥተውት እያሉ እነዚ እንደቸሩላቸው ከአምላክ በላይ ሆነው ለመታየት ለፖለቲካ ፍጆታ ሊጠቀሙበት መሞከራቸው ነው የሚያናድድ ። መቸ ይብቻ ለፓለቲካ ድጋፍ ማግኛ ዘዴ መጠቀማቸው አልበቃም ቡሎዋቸው የነሱ ዲሞክራሲ ባህሪ እንዳላቸው የውሸት ፕሮፕጋንዳቸው መጠቀምያ ማድረጋቸው ነው ።
2. ያቺ 70 ሜትር ካሪ መሬት ለመኖሪያ ቤት በቂ አይደለችም ። እነዚህ የሀገራችን ሆዳሞች ባለስልጣናትና ቤተሰቦቻቸው ግን ከአዲስ አበባ እስከ ክልሎች ያሉ ምርጥ ከተሞች ከ500 እስከ 1200 ከዛ በላይ መትር ካሬ ስፋት መሬት በመያዝ ሰማይ ጠቀስ ህንጻዎችና ቪሏዎች እንድስቲሪዎች በሞኖፖል ይዘው እያሉ ለቡዙሀኑ ተራ መጠልያ ለመስራት ሰፋ ያለ መሬት መከልከላቸው ምን ያህል ክፎች መሆናቸው ነው ። በተለይ ደግሞ የህወሐት ፣ የባአዴን ፣ የኦሆዴድ ፣ የዲህደን ፣ የአጋር ፓርቲዎች አመራሮችና ሸሪኮቻቸው የሰሩት ቤት የያዙት መሬት እጅጉን ሰፋፊ ቦታዎች ናቸው ። እንዳው ለራሳቸው ከሁለት በላይ ይዞታ መሬትና ቦታ በባለቤትነት ይዘው በአሁኑ ጊዜ ምን ሊታወጅ እንደታሰበ አላውቅም ፣ በአዲስ አበባ በጎንደር ፣ በትግራይ ፡ በባህርዳር ፣ በአዋሳ ፣ በአዳማ ፣ በወሎ በሌሎቹም ወ ዘ ተ በሚሊዮኖች ብር ቤትና ቦታ እሸጡ መሆናቸው ቡዙ ዜጎች ተቃውሞዋቸው እየገለጹ ይገኛሉ ።
3 ቤት ሰሪዎች የቤት መስርያ ገንዘብ ብድር ከሌሎች ባንኮች አወዳድረው እንዳይ በደሩ የህወሐትና ሌሎች ፓርቲዎች ኪስ ከሆኑት የብድርና ቁጠባ ሊበደሩ መገደዳቸው ነው ። መቸ ይህብቻ ገና ስሚንቶ ብረት፣ ጣውላ ፣ የሳኒተሪና የኤለክትሪክ ከጉናና ከአንፓሰል እንዲገዙ ይገደዱ ይሆናሉ ።
4 ህዝብ ለለከቲት 11 ፣ 42ኛ ህወሐት የተመሰረተበት የትጥቅ ትግል የትግራይ ታሪካውነቱ አምኖ በፍላጎቱ እንደማክበር ፈንታየመሬቱ እጣ ከየካቲት ማያያዙነው።
ይህ ሁሉ ሸፍጥ ግን በትግራይ ብቻ እየተፈጸመያለ ነው። 5 ትልቁ ወንጀል ደግሞ ለአርሶ አደሮች የተወሰደባቸው መሬት ለአንድ ሜትር ካሪ ከቤት ሰሪዎች ብር 62 .00 እያለ ለአርሶ አደሮቹ ግን ይሰጣቸው ከነበረው ብር ቀንሰው 23 .00 ብር ሰጥተው 57 %ለገዥዎች ኪስ መሙያ ሆነዋል ። አርሶ አደሩ የወሰደው በር ደግሞ ሲሰላ 43%በመሆኑ የኔ ተቃውሞ ለቤት ሰሪዎች መሬት ማግኜታቸው መቃወም ሳይሆን የጭቁን አርሶ አደር ካሳ መቆረጥ የለበትም ። ለዚሁ ግፍ ቤት ሰሪዎችም ገ ከገንዘቡ ከተቀማ አርሶ አደር ጎን መቆም ነበረባቸው ። አሁንም ጥያቄ ማንሳት አለባቸው ። ከዛ አርሶ አደር ጋር ለወደፊት ም ገረቤት ሆነው ስለሚኖሩ ከወዲሁ ግንኝነታቸውን ማበጀት አለባቸው ።
6 እነዚህ አታላይ ገዥዎች ሳያፍሩ ትናትና መሬት የመንግስት ናት አንተ ህዝብ የመንግስት ጢሰኛ ነህ አርፈህ ተቀመጥ እያሉ ህዝቡን እያሻማቀቁ መሬቱ እየቀሙ በሊዝ 26 አመት ሙሉ በውድ ዋጋ እየቸበቸቡት ነረው አሁን ደግሞ ሲጨንቃቸው አሁን በአስርሺ የሚቆጠር ህዝብ የቤት ባለቤ አድርገናል ለቀረውም ከሚቀጥለው መጋቢት ወር የቤት በለቤት እናደርገዋለን ብለዋል። አሁን ይዘውት ያሉ መፎከር ደግሞ አላማችን ሁሉ ቤት የለለው ትግራዋይ የቤት ባለቤት እናደርገዋን ብለዋል ። ይህ ወደው ሳይሆን በግድ ሊተገቡሩት ናቸው ይህ እርምጃ መውሰዳቸው ደግሞ የሰላማዊ ተቃዋሚ ፓለቲካ ሀይሎች ነው ። ከመሬት መስጠት ተያይዞ ግን ከቤት ሰሪና አርሶ አደሩ ቡዙ ምዝበራ እንደሚፈጽሙ የተረጋገጠ ነው ። ግን ደግሞ ህዝብ ነቅቶ ስላለ ማሳለፍያ መንገዱ ሁሉ ተዘግተዋል ።
ከአስገደ ገብረስላሴ መቀለ ፣
12 / 6 / 2009 / ዓ ም

የወያኔዋ ኢትዮጵያ — የሞቱላት መቃብራቸው የሚፈነቀልባት፤ የገደሏት ግን ሀውልታቸው አገር የሚያጣብብባት ምድር



አቻምየለህ ታምሩ
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ኃይማኖት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ፫ኛ ፓትርያርክ ነበሩ። ብፁዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ አቡነ ተክለ ኃይማኖት በዘመናቸው የነበረው ወታደራዊ መንግስት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያንን አሳልፈው እንዲሰጡ በርካታ ውትወታና ጫና ቢያደረግባቸውም ለምንም አይነት ጫና ሳይንበረከኩ የተሰጣቸውን የቤተ ክርስትያን አደራ ተወጥተው አልፈዋል።
በመጨረሻም በኃይል ቤተ ክርስትያኗን በፖለቲካው ስር ለማድረግ ደርግ እርምጃ ሲጀምር የርሃብ አድማ በማድረግ፤ ገፍቶ ሲመጣም «ሬሳዬን ተራምዳችሁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያንን ትደፍራላችሁ» በማለት ጸንተው በመቆም፤ ከአሥራ ሁለት ዓመታት የፓትርያሪክነት አገልግሎት በኋላ ግንቦት ፳፰ ቀን ፲፱፻፹ ዓ.ም. በተወለዱ በ፸ ዓመት ዕድሜያቸው መላ ዘመናቸውን በጸሎት፣ በጾም፣ በሰጊድ አሳልፈው፤ የሰውነታቸው ክብደት ፳፭ ኪሎ ግራም ደርሶ፤ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩ ጀግና ናቸው።
ብፁዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ አቡነ ተክለ ኃይማኖት የወር ደመወዛቸውን ለህጻናት ማሳደጊያ የሚሰጡ፤ከጸሎት መጽሃፍ፣ ከአንድ የሚቀይሩት ወይባ፣ ከደረት ሰዓትና ከነጠላ ጫማቸው በስተቀር ሌላ ንብረት ያልነበራቸው፤ህይወታቸውን ለአገራቸው የሰጡ፤ሙሉ ጊዜያቸውን በጾምና በጸሎት የሚያሳልፉ መናኝ መነኩሴ ነበሩ። በዘመናት የተነሱ ኃይሎችን ተቋቁመው በመስዕዋት ያቆዩዋትን ቤተክርስቲያን አደራ ተቀብለው፤ለቤተ ክርስቲያናቸው የገቡትን ቃለ መሃላቸውን ጠብቀው ሳያስደፍሯት መስዕዋት ሆነዋል።
Image may contain: 1 person, standing, shoes, sunglasses, shorts and outdoor
ታዲያ ዛሬ የዚህ እውነተኛ አባት መቃብር በግፈኞቹ ተቆፍሮ አጽማቸው ሜዳ ተጥሏል። መስዕዋት የሆኑላት ቤተ ክርስቲያን ለመቃብር ያህል እንኳ ሁለት ክንድ መሬት ነፈገቻቸው።
ቤተ ክርስቲያኗን ያዋረዷት ወያኔዎቹ እነ አባ ገብረ መድህን ወይንም አቡነ ጳውሎስ በየ አደባባዩ ሀውልት ሲቆምላቸው፤ ቤተ ክርስቲያኗን ያስከበሩት አቡነ ተክለ ኃይማኖት ግን ለቤተ ክርስቲያን ፍቅር ሞተው ለመቃብር የሚሆናቸው መሬት እንኳን አላገኙም።
የሚገርመው ለመቃብር የሚሆን መሬት ሳያገኙ መስዕዋት የሆኑት የአቡነ ተክለ ኃይማኖት መቃብር የሚቆፈረው አንድም የመቃብሩን መሬት በሊዝ ለመቸብቸብና ለመድለብ ነው፤
አሊያም የባንዳ ልጆችንና አገርና ቤተ ክርስቲያን የሚያዋርዱትን ባለጊዜዎች ባለመሬት ለማድረግ ነው። ጻድቁ አቡነ ተክለ ኃይማኖት የሞቱላት የቤተ ክርስትያን ልጆች የት ናችሁ? «ቤተ ክርስትያን በማንም ስር አትሆንም» ብለው ስለ ቤተ ክርስትያን ክብር የሞትን ጽዋ ተቀብለው መስዕዋት የሆኑት አባታችሁ መቃብር ሲፈነቀል ዝም ብላችሁ ማየትን ከማን የተማራችሁ ነው? ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ኃይማኖት በልባችሁ ወስጥ የሉም ማለት ነው? የበቁትና የህያዉ የብፁዕ ወ
ቅዱስ አቡነ ተክለ ኃይማኖት ልጆች ነን ብላችሁ ታምኑ የለም? ህያውነት ምንድን ነው? የሞትን እርምጃ ያለፍራት መራመድን የፈራ እንዴት የህያው ልጅ ሊሆን ይችላል? እናንተ የምታወግዟቸው ዮዲት ጉዲትና ግራኝ አህመድ ወያኔ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ኃይማኖት መቃብር ላይ ካደረገው በላይ ምን አደረጉ? አይናችሁ እያየ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ኃይማኖት መቃብር በወያኔ ሲፈርስ ዮዲት ጉዲትና ግራኝ አህመድ ቤተ ክርስቲያንን አወደሙ ብላችሁ የማውገዝ ሞራሉ ይኖራችሁ ይሆን? እዚያ ቅዱስ አባት በለበሱት ስጋ ውስጥ ሁነው የዘሩት የተግባር ፍሬ በእውነተኛው አለም ውስጥ ሆነው ፍሬ አልባ ሆኖ ሲያቱት ምን ይሰማቸው ይሆን?
ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም «መቀበር አልፈልግም፤ ሕይወቴን በሙሉ ተቀብሬ ኖሬአለሁ! ወይም በመቃብር ውስጥ ኖሬአለሁ፤ ድንጋይ እየተደራረበ ተጭኖብኝ አምላክ ድንጋዩን አፈር አድርጎ እያቀለለልኝ ሳልጨፈለቅ ቆይቻለሁ» በማለት «ኑዛዜ» በሚለው ግጥማቸው ከህይወት በኋላ ፍላጎታቸው እንዲህ ሲሉ የገለጹት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ኃይማኖት እጣ ታይቷቸው ይሆን?
Image may contain: 1 person
የሕይወት ጽዋዬ ጥንፍፍ ብሎ ሲያበቃ፤
ሲቀር ባዶውን፣ የቆየ ባዶ
ዕቃ፤
ሲበቃኝ፤ በቃህ ስባል፣
ትንፋሼ ሲቆም በትግል፣
ስሸነፍ ተሟጦ ኃይል፣
ሰው መሆኔ ቀርቶ፣– አስከሬን ስባል፣
እወቁልኝ ይህን ብቻ፣– የገባኝን ያህል
ሞክሬ ነበር ሰው ለመሆን፤
ሰውነት በከፋበት ዘመን፤
መሬት አልነበረኝም በሕይወቴ
መሬት አልፈልግም፤ አሁን በሞቴ
አቃጥሉልኝ ሬሣዬን፤
አመድ እስኪሆን፤
አዋሽ ውስጥ ጨምሩልኝ አመዴን፤
ከአዋሽ ይቀላቀል ከዘመዴ፤
ይቺን አትንፈጉኝ አደራ፣
አመዴ እንኳን እንዲኮራ።

Sunday, February 19, 2017

አዲሳ አድማስ- ኢህአዴግና ተቃዋሚዎች ለድርድሩ መመሪያ ሰነድ ለማዘጋጀት ተስማሙ


 
By editor February 18, 2017 23:35      


‹‹የመጀመሪያ አጀንዳችሁን ለፓርላማው ፅ/ቤት አስገቡ” – ገዥው ፓርቲ
“አደራዳሪያችንን ሳናውቅ አጀንዳ አናቀርብም፣” – ተቃዋሚዎች
“ሁሉም ፓርቲ በእጣ፣ በዙር ያደራድር” – ገዥው ፓርቲ
“ገለልተኛ አካል ያደራድረን” – ተቃዋሚዎች
ሚዲያዎች በመግለጫ ብቻ እንዲስተናገዱ ሃሳብ ቀርቧል
ገዥው ፓርቲና ተቃዋሚዎች በሁለተኛው ቀጠሮአቸው ድርድሩ የሚመራበት የጋራ መመሪያ ሰነድ እንዲዘጋጅ ተስማምተው፤ ያቀረቡት ሀሳብ በንባብ ተሰምቷል፡፡
ፓርቲዎቹ ቀደም ሲል በነበረው ስብሰባቸው ድርድሩ በማን ይመራ፣ ማን ይታዘበው፣ በምን ዓይነት ስነ ምግባርና ስርአት ይመራ እና ሚዲያዎች እንዴት ባለ መንገድ ይዘግቡት በሚሉ 4 ፍሬ ነገሮች ላይ ያላቸውን ሀሳብ እንዲያቀርቡ በተጠየቁት መሰረት፤ በቡድንና በተናጥል ተከፋፍለው፣ ለፓርላማው ፅ/ቤት ያቀረቡት ሀሳብ ባለፈው ረቡዕ በንባብ ከተሰማ በኋላ፣ ሰፊ በመሆኑ ተቀናጅቶ በአንድ ሰነድ እንዲቀርብ ተስማምተዋል፡፡
ኢህአዴግ የድርድሩ አላማ “በክርክርና በድርድሩ የሚነሱ ሀሳቦችን በግብአትነት በመውሰድ የሚሻሻሉ ህጎች ማሻሻል፤ እንዲሁም የአፈፃፀም ጉድለቶችን ማስተካከል” ነው ሲል መድረክ በበኩሉ “የሀገሪቱን የፖለቲካ ምህዳር ችግር ነቅሶ በማውጣት መፍትሄ እንዲሰጥ ማስቻል” የድርድሩ አላማ ይሁን በማለት ሀሳቡን አቅርቧል፡፡ መኢአድን ጨምሮ 6 ፓርቲዎች፤ በድርድሩ ህዝብ የሚጠብቀው ነፃና ፍትሃዊ በሆነ የምርጫ አካሄድ፣ በራሱ ፍላጎት መንግስት ማውረድና ወደ ስልጣን ማምጣት ነው” የሚል ሀሳብ አቅርቦ እንደነበርና በንባብ ሳይሰማለት መቅረቱን የመኢአድ ም/ፕሬዚዳንት አቶ ሙሉጌታ አበበ ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡
በንባብ ከተሰማው የየፓርቲዎቹ ፕሮፖዛል መረዳት እንደተቻለው፣ ገዥው ፓርቲ ድርድሩ በማን ይመራ ለሚለው “ሁሉም ፓርቲ በእጣ ተከፋፍሎ፣ በየተራ እንምራ” የሚል ሀሳብ አቅርቧል።
መኢአድ፣ ኢዴፓና ሰማያዊ የተካተቱበት የ6 ፓርቲዎች ቡድን ደግሞ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ባላቸው 11 ገለልተኛ ሰዎች ድርድሩ እንዲመራ ሀሳብ ያቀረቡ ሲሆን መድረክ በበኩሉ፤ 4 ገለልተኛ ግለሰቦች ድርድሩን ይምሩት የሚል ሀሳብ አቅርቧል። ሌሎች ፓርቲዎችም በተመሳሳይ ድርድሩ በገለልተኛ ወገኖች እንዲመራ ፍላጎት እንዳላቸው አስታውቀዋል፡፡
ድርድሩን ማን ይታዘበው በሚለው ላይ ገዥውን ፓርቲ ጨምሮ አብዛኛው ተቃዋሚ ፓርቲ፤ ገለልተኛ ወገኖች ድርድሩን እንዲታዘቡት ሀሳብ ያቀረቡ ሲሆን ገዥው ፓርቲ ታዋቂ ሰዎች ይታዘቡት ሲል፤ የእነመኢአድ ቡድን፤ ታዛቢዎቹ ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ ሀገር ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሆኑ እንዲሁም ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ እንደ አሜሪካና እንግሊዝ አምባሳደሮች የመሳሰሉ ተፅዕኖ ፈጣሪ የውጭ ዜጎችና የሲቪክ ማህበራት እንዲሆኑ ሀሳብ አቅርቧል፡፡
ፓርቲዎቹ ድርድሩ ይመራበት ያሉትን የስነ ምግባርና ስነ ስርአት ሀሳብም አቅርበዋል፡፡ ገዥው ፓርቲም ሆነ ተቃዋሚዎች፣ የፓርቲዎችን ኃላፊነትነና ልዕለ ስብዕና የሚነኩ ንግግሮችና ተግባራት የተከለከሉ እንዲሆኑ ሀሳብ አቀርዋል፡፡
በድርድሩ አንድ ፓርቲ በ4 ግለሰቦች ይወከል የሚል ሀሳብ ኢህአዴግ ያቀረበ ሲሆን የእነ መኢአድ ቡድን በ3 ግለሰቦች እንዲወከል ሀሳብ ማቅረቡን መረዳት ተችሏል፡፡
ኢህአዴግ የድርድር መድረኩ ስያሜ “የገዥው ፓርቲ እና የተፎካካሪ ፓርቲዎች የጋራ ፎረም” እንዲባል ሀሳብ ሲያቀርብ፤ ተቃዋሚዎች በበኩላቸው፤ መድረኩ ከወዲሁ “ፎረም” ከተባለ በህዝብ ዘንድ ሊኖር የሚችለውን አመኔታ ስለሚያሳጣ ጠቃሚ አይሆንም በሚል ለጊዜው “የገዥው ፓርቲ እና ተፎካካሪ ፓርቲዎች ድርድር” በሚል ይጠራ ማለታቸውን የመኢአድ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሙሉጌታ አበበ አስረድተዋል፡፡
የሚዲያ አዘገጋገብን በተመለከተ ገዥው ፓርቲና ተቃዋሚዎች ተቀራራቢ ሀሳብ ያቀረቡ ሲሆን በዚህም ሚዲያዎች ሁሉንም የድርድር ሂደት በቀጥታ እየተከታተሉ ከሚዘግቡ ይልቅ በመግለጫዎች እንዲስተናገዱ ሃሳብ ቀርቧል፡፡
የድርድሮቹን መግለጫዎችም በቀጥታ ከፓርቲዎች ሳይሆን በገለልተኛ አደራዳሪው አካል በኩል ሚዲያዎች እንዲያገኙ የነመኢአድ ቡድን ሃሳብ አቅርቧል፡፡ ማንኛውም ሚዲያ ሂደቱን አዛብቶ የሚዘግብ ከሆነ፣ በሃገሪቱ ህግ መሰረት እንዲቀጣ፣ ሂደቱን ከመዘገብ እስከ መታገድ የሚደርስ ቅጣት እንዲወሰንበትም ይሄው ቡድን ሃሳብ አቅርቧል፡፡
በረቡዕ ውይይት ኢህአዴግ ፓርቲዎች ሊወያዩ ወይም ሊደራደሩ የሚፈልጉባቸውን አጀንዳዎች ከወዲሁ ለፓርላማው ፅ/ቤት እንዲያስገቡ የጠየቀ ሲሆን የሂደቱ ተሳታፊ የሆኑት የመኢአድ ም/ፕሬዚዳንት አቶ ሙሉጌታ የመደራደሪያ አጀንዳችንንና ሃሳባችንን ፈቅደን ልንሠጥ የምንችለው ለሚመለከተው ገለልተኛ አደራዳሪ ወገን ብቻ ነው›› የሚል አቋም መያዙን አስረድተዋል፡፡
የመጀመሪያውን የድርድርና ውይይት መድረክ ኢህአዴግን ወክለው የመሩት የኢህአዴግ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ እንደነበሩ ያስታወሱት አቶ ሙሉጌታ በወቅቱ ፓርቲያቸውን ጨምሮ አንዳንድ ተቃዋሚ ፓርቲዎች፤ “መድረኩ ወሣኝ ሆኖ ሣለ እንዴት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አይሠበስቡንም? የሚል ሃሳብ ተሰንዝሮ እንደነበር ጠቁመው፤ “ማስተካከያ የተደረገበት በሚመስል መልኩ የረቡዕ መድረክ በም/ጠ/ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተመርቷል፤ ይህንንም በበጎ ተመልክተነዋል” ብለዋል፡፡
በሌላ በኩል በዚሁ የረቡዕ እለት የድርድር መድረክ ላይ የሶስት ፓርቲዎች ጥምረት የሆነው በፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ የሚመራው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ለየት ያለ ሃሳብ ያቀረበ ሲሆን ድርድሩም በኢህአዴግና በመድረክ መካከል እንዲካሄድ ጠይቋል፡፡ ፓርቲዎቹ በመረጧቸው ኮሚቴዎች የሚሰናዳላቸውን ሰነድ ተመልክተው ቀጣዩን ሂደት  ለማስቀጠል በፓርላማው ፅ/ቤት በድጋሚ ለመገናኘት ለየካቲት 17 ቀን 2009 ዓ.ም ተቀጣጥረዋል፡፡

ኑ፣ የካቲት 12 ሰማዕታትን መታሰቢያ ዕለት በፌስቡክ እንክብር።

ኑ፣ የካቲት 12 ሰማዕታትን መታሰቢያ ዕለት በፌስቡክ እንክብር።

 
By ሳተናውFebruary 19, 2017 00:07


 3  83  87
አገር ከወረረው አገሩን ለወራሪው የሸጠው ይብሳል!
የካቲት አስራ ሁለት የሰማዕታት ዕለትን የተለያዩ ታሪኮችን እያስታወስን እናስበው። ሙሉ በሙሉ ኢትዮጲያዊ ነኝ ብለን መናገር የምንችለው ታሪካችንን በሚገባ ስናውቀው ነው። ፓስፖርት ብንቀይር አክስንታችንን ብንለውጥ ኢትዮጲያውነታችንን ግን መደብቅ አንችልም።
ጥሊያን በሄደበት እና በወረራቸው አገሮች የሚቀጥራቸው ቅጠረኛ ሹም ባሻህወችን የሚያለብሳቸው በስተቀኝ በኩል የሚታየው አይነት ነጭ ወይም ካኪ መለዮ ነው።
በስተግራ ያለው ደግሞ በራስ አበበ አረጋይ እና በደጃዝማች ሙሉጌታ ብሊ የተመራው በውሮጳ አቆጣጠር 1936 ማይጨው ላይ እጅግ ዘመናዊ በሆነ የጦር መሳሪያ እና በአየር በታጀበው የፍሽስት ወታደር የተሸነፈው በታሪክ የመጀመሪያው የኢትዮጲያ ጦር ሠራዊት መለዮ (uniform) ነው። ከዚህ በፊት የኢትዮጲያ ሠራዊት መለዮ ወይም Uniform አልነበረውም።
ከዚህ ሽንፈት በኋላም የኢትዮጲያ ጦር መለዮ ለባሽ አልነበረም,። ሁሉም ከየታዛው መንደሩ እና ቀበሌው እጀ ጠባቡን እና ኩታውን ለብሶ ነው በባዶ እግሩ ሚስቱን ልጁን ትቶ በፋሽስት ጦር ላይ የዘመተው። በውሮጳ አቆጣጠር በ1941 ንጉሰ ነገስቱ ከእንግሊዝ አገር ሲመለሱ እንደገና በድጋሚ ዘመን ቀመስ መለዮ የለበሰ፣ የብረት ቆብ የደፋ ቀበቶ የታጠቀ ብረት የነገተ ፣ የጦር ሠራዊት አቋቋሙ።

የወልቃይት ጠገዴ ዐማራ ምሕረት የሚባለው የይስሙላ ማታላያ ነው – ሙሉቀን ተስፋው

የወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ ኮሚቴዎችንና ደጋፊዎችን ሕጋዊ ስለሆናችሁ በነጻነት የመንቀሳቀስ መብት እንዳላቸው በመግለጽ እንዲገቡ ካደረጉ በኋላ ደብዛቸውን እያጠፏቸው ነው። ለምሳሌ አቶ ካሳ ጥሩ የተባሉትን የዳንሻ ተወካይ ዐማራ በምሕረት በወንድማቸው በኩል እንዲገቡና እንዲንቀሳቀሱ በደብዳቤ ከገለጹ በኋላ ተይዘው የት እንዳሉ አይታወቅም።
ሁሉም የወልቃይት ጠገዴ ዐማራ ምሕረት የሚባለው የይስሙላ ማታላያ መሆኑን ይረዳ ዘንድ ደብዳቤውን አብረን አቅርበነዋል።
የዐማራ ተጋድሎ ያሸንፋል

ወያኔ ወደ ደቡብ ሱዳን ሰራዊት እያስጠጋች ነው!



አሶሳ ጊዘን ለደቡብ ሱዳን ቅርብ የሆነች በጣም ሞቃታማ የወረዳ ከተማ ነች። በዚሁ በኩል ብዛት ያለው የወያኔ ሰራዊት ማታ ከ4:00 ሰዓት በኃላ የማቅረብ ስራ በ09/02 009 ዓ.ም ሰርቷል። በርግጥ ወደ ውስጥ ደቡብ ሱዳን ውስጥ ይግቡ ድንበሩ ላይ ይመሽጉ እያጣራን ነው። የስደተኞች ካምፕ እዚያው አካባቢ ይገኛል፡፡ የአካባቢው ሰው በማያይበት እና ባልሠማበት ሁኔታ ነው ይህን እየፈፀሙ ያሉት። ወያኔ ከደቡብ ሱዳን ጋር ያላት ችግር እየተወሳሰበ መሄዱ ሲዘገብ ቆይቷል። ግብፅም እዛ የሚሊታሪ ቤዝ ማቋቋሟ ይታወቃል። እዛ አካባቢ መንጌ ወረዳ ሸርቆሌ እና ጊዘን ወረዳዎች አካባቢ ያሉ የበርታ ማህበረሰብ ተወላጆች በትግራይ የእርሻ ኢንቨስተሮች እና ወርቅ አውጪዎች ስለተበደሉ የሚሸፋቱና የሚወጉት ተፈጥረዋል። የአባይ ግድብ ጀርባም ነው። ግብፅም ከሞከረች እጇ የሚረዝምበት መሿለኪያ ቦታ አለው፡፡
ሙሉነህ ዮሃንስ

Saturday, February 18, 2017

ህወኃት /ኢህአዴግ ሆይ – ‹‹ ጀምበር ሳለች እሩጥ-

   



ህወኃት /ኢህአዴግ ሆይ – ‹‹ ጀምበር ሳለች እሩጥ- (2) ›› //
ዛሬም ባለፈው በጻፍኩት ‹ምክር› መግቢያ  ባልኩት ‹‹ እኔን የሚያሳስበኝ የዛሬው ዘረኛ ገዢ ቡድን መወገድ አይደለም፡፡ ይህ አገዛዝ የሚወገድበት መንገድ ነው፡፡ በተለመደው  ከሆነ – ማለትም ይህን አገዛዝ አጥፍተን ቀብረን በከርሰ መቃብሩ ላይ አዲስ ሥርዓት ለመገንባት ከሆነ ለውጥ አይደለም፡፡ እንዲሁም በከርሰ መቃብሩ ላይ የለማች ፣ የበለጸገች ፣ የሰው ልጆች መብት የተከበሩባት ፣ ሁሉም ከችግር ወጥቶ ተብነሽንሾ የሚኖርባትን  … ኢትዮጵያ በቀላሉና ያለችግርና ፈተና   በማግስቱ ተገንብታ የምናገኝ/ ወይም የምንገነባ  የሚመስለን ከሆነ አሁንም የምንጠብቀውን የምንታገልለትን ዓላማ የተረዳነው በተሳሳተ መንገድ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ ›› በሚለው ልጀምር፡፡
ያለፈው ደርግ አገዛዝ በህዝብ ትግል ተገርስሶ  በባለ ጠብመንጃው ህወኃት/ኢህአዴግ ተቀብሮ ፣ ብሶት ወለደኝ ያለን  ሥልጣን ላይ እንደወጣ የተገቡልንን ቃላት እና ያለንበትን እውነት በማሳየት ከላይ የተቀመጠውን  ሃሳብ ለማስረገጥ አንዳንድ ነገሮችን በአጭር ላንሳ፡- በጥቅል ፕሮፖጋንዳና በህዝብ ሕይወት ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት የተለያዩ ናቸው፡
  1. ምርትና ምርታማነት፣  የሁለት አሃዝ/ ዲጅት ተከታታይ ዕድገት ፡- አዎን ዝናብ ጠብቀን በበሬ እያረስን በየዓመቱ በሚሊዮኖች እየተራቡብን ባለው ሁኔታ የቀድሞው ጠቅላይ ሚ/ር ሥልጣን ላይ እንደወጡ   ‹‹ በቀጣይ አስር ዓመታት ህዝባችንን ሶስት ጊዜ እናበላለን ››፣ ቀጥለውም ‹‹ በምግብ እህል ራሳችንን ችለን በቆሎ ለጎረቤት አገሮች መሸጥ ጀምረናል›› እንዳሉት ለሌላው  መሸጡ ቀርቶ ህዝባችንን ማብላት ቀላል አይደለም፡፡ እንዲህ መዋሸት ይቻላል፤ ግን ለውጥ ካሰብን እነርሱ/አገዛዞች በጠገቡት ህዝብን ‹ጠግበሃልና  አግሳ› ፣ ምርታማነታችን አድጎ በሄክታር ይህን ያህል ደረሰ፣ በዚህ መቶኛ አደገ፣ ተመነደገ ማለት  እንጂ  ረሃብን ማጥፋት አይቻልም፡፡ለዚህም በየዓመቱ የልመና አቁማዳ ይዞን የመዞራችን ሃቅ፣ በሴፍቲኔት የሚኖሩ ዜጎች ብዛት፣ ድርቅ ኮሽ ባለ ቁጥር በሚሊዮኖች ለአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ መዳረጋቸው፣… የሚያረጋግጠው ነው፡፡ በመሆኑም   ነገ ማንም ቢመጣ እነዚህን ዓይነት ችግሮች በበነጋውና  ያለህዝብ ተሳትፎ በራሱ/በመንግስት ብቻ ያስወግዳል ማለት አይደለም ፡፡ የዜጎች መብት ባልተከበረበት፣ የህግ የበላይነት ባልሰፈነበት፣ ዜጎች የአገሪቱን ችግሮች ተረድተውና ነባራዊና ተጨባጩን ሁኔታ ተቀብለው   ለመፍትሄው በጋራ ለመስራት ባልቆረጡበት ፣ …… በአገራቸው ሉዓላዊነትና በራሳቸው ክብር ላይ የሚያነሱት ጥያቄ ባልተመለሰበት … ምርትና ምርታማነትን አፍነው /ሰንገው የያዙ ፖሊሲዎች ባልተስተካከሉበት … በፕሮፖጋንዳ፣  በኃይል አፈና፣፣ …. ዘላቂ መፍትሄ አይመጣም ነው፡፡ ፕሮፖጋንዳ  እንጀራ አይሆንም፡፡
  2. ሰብዐዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች፡- ህወኃት/ኢህአዴግ በአገራችን  ከመቼውም ጊዜ በላይ ተከብረዋልል ይለናል፡፡ ህዝቡ ደግሞ ከዕለት ተዕለት ኑሮው ተነስቶ ‹ማሞ ሌላ መታወቂያው ሌላ› እያለ ከሁለት አስርተ ዓመታት በላይ ቢገፋም አሁን ግን ‹ቀልዱን ተዉት› በማለት ከዳር አስከዳር ማለት በሚያስችል ሁኔታ ‹ እምቢኝ › በማለት ተነስቷል፡፡ ለዚህ ህዝባዊ የበቃኝ ህዝባዊ እንቅስቃሴ መንግስት/ገዢው ፓርቲ ራሱን  ወደ ውስጥ ከመመልከት ይልቅ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተቃውሞውን ለማፈን የሚያደርገው ሁሉ ለጊዜው እንቅስቃሴውን ያረግበው እንደሆን እንጂ ዘላቂ መፍትሄ እንደማያመጣ ለመናገር የፖለቲካ ተንታኝነት ወይም ነቢይነት አይጠይቅም ፡፡ ከያቅጣጫው የሚሰማው የህዝብ ብሶት ፣ በየማጎሪያው በዜጎች ላይ የሚፈጸመው አሰቃቂና ዘግናኝ ኢሰብዐዊ ድርጊት /ቶርቸር / ከእኛ አልፎ በዓለም  አደባባይ የዋለ ተጨባጭ ሃቅ ነው፡፡ ዜጎችን በፖለቲካ አመለካከታቸው እያሰሩና እያሰቃዩ፣ የዲሞክራሲ ተቋማትን እያቀጨጩ ወይም እያጠፉ የሰብዐዊና ዲሞክራሲያዊ  መብት ጠበቃ ነኝ ማለት በህዝብ ላይ ከማሾፍ የዘለለ፣ ወይም ህዝብን ከመናቅ የተለየ ትርጉም  የለውም፡፡ ህዝብን እያሰቃዩና እያፈኑ መብትህ ተጠብቆልሃል ማለት ፣ ያለፉትን አገዛዞች ጭቆና ሃያ አምስት ዓመት እያወሩ ‹‹ እኔ ከሌለሁ ያለፉ አገዛዞች ከመቃብር ተነስተው ይመጡብሃል ፣ አገርህ ትበታተናለች›› የሚለው ማስፈራሪያ  አልሰራም ፡፡ በህዝብ ሥም እየማሉ የሚሰራ ፕሮፖጋንዳና የህዝብ መብት ማክበር ለየቅል ናቸው፡፡ ስለዚህ መፍትሄው የህዝቡን ሰብዐዊና ዲሞክራሲያዊ  መብት ካሳለፍነው ነባራዊ ሁኔታና ካለንበት ተጨባጭ እውነታ የህዝቡን ሰብዐዊና ዲሞክራሲያዊ መብት ካሳለፍነው ነባራዊ ሁኔታና ካለንበት ተጨባጭ እውነታ በሚጣጣም መልኩ( የዕድገት፣ እውቀት … ) ደረጃችን ባገናዘበና በሚጣጣም መልኩ  በተግባር ማረጋገጥ ብቻ ነው ፡፡
  3. የህግ የበላይነትና ፍትሃዊ ሥርዓት፡- የገዢው ፓርቲ አባል ከህግ የበላይ በሆኑበት  /በህግ  በማይጠየቁበት አገር መኖራችን  አደባባይ የሞቀው ምስጢር በሆነበት ፣ የፍትህ ተቋማት ገለልተኝነት አጠያያቂነት ሳይሆን በገዢው ፓርቲ አገልጋይነት በህዝብና በሙያው በተሰማሩ  በተረጋገጠበት፣ ዜጎች በፖለቲካ አመለካከታቸውና ዘራቸው  በፈጠራ ተወንጅለው ክስ ሳይመሰረትባቸው ለዓመታት በሚታሰሩበት፣ በተጠረጠሩበት ወንጀል ፍትህ ሳያገኙ ለዓመታት በወህኒ በሚማቅቁበት፣ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተነገሩ በህዝብና አገር ሃብት ላይ የተፈጸሙ ዘረፋዎች በማያስጠይቁበት፣  ዳኞች የፍርድ ውሳኔ በስልክ በሚቀበሉበት . . . የመኖራችንን እውነት የዕለት ተዕለት ህይወታችን እየነገረን ባለበት ህወኃት/ኢህአዴግ ራሱን የህግ የበላይነት ተምሳሌት ፣የፍትሃዊነት አራማጅ አድርጎ በማቅረብ ህዝቡ  ‹አይሰማም›  ብሎ ከጀመረው ትግል ‹ ጥልቅ ተሃድሶ › በሚል ግርግር ወደኋላ መመለስ አይቻልም፡፡
ህወኃት/ኢህአዴግ የራሱን ህገመንግስት ራሱ እየረገጠና እየጨፈለቀ ‹‹ ለዓለም ምሳሌ የሚሆን ፣ የሚቀናብን ህገ መንግስት ባለቤቶች ነን›› ብሎ ቢናገርና በምሁር ተብዬዎች ቢያስነግር ፤ ህዝብን ከላይ በተገለጹት ሁኔታዎች የማሰቃየው ህገ መንግስቱንና ህገመንግስታዊ ሥርዓቱን ለማስከበር ነው ብሎ በጠመንጃና ወታደር  የዜጎችን ሰብዐዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ማፈን ለጥቂት ጊዜ እፎይታ ቢሰጥ እንጂ ዘላቂ መፍትሄ እንደማያመጣ ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታት ካሳለፍነው ህይወት ህያው ምስክር ነን፡፡
  1. የህዝብ የሥልጣን ምንጭነትና ባለቤትነት፡- ይህ በህገመንግስቱ መቀመጡ አያጠያይቅም ፡፡ ቀስቃሽና ወስዋሽ አያስፈልገውም ፡፡ እያጠያየቀ ያለው ታዛኝ ‹ ስልኩት ወዴት ሲጠሩት አቤት › እንዲል የተዋቀረው በህዝብ ድምጽ  ዘረፋ ከገዢው ፓርቲ ጎን በመቆሙ የህዝቡን አመኔታና የሥልጣኑን ክብር ያጣው ምርጫ ቦርድ ይህን ህገመንግስታዊ የህዝብ መብት ሊያስከብር አልቻለም፣ አይችልም ነው፡፡ የራሱን በህገመንግስት የተቀመጠለትን  መብትና በህግ የተሰጠውን ሥልጣን ማስከበር፣ መጠቀምና መተግበር ያልቻለ ምርጫ ቦርድ የህዝብን የሥልጣን ምንጭነት ሊያረጋግጥ ፣ባለቤትነቱን ሊያስከብር አይችልም ነው፡፡ህዝብ የሥልጣን ምንጭነቱንና ባለቤትነቱን  በዚህ ምርጫ ቦርድ አመራር በሚደረግ ምርጫ አስመልሳለሁ፣ ለውጥ ይመጣል፣ ድምጼ ይከበራል የሚል ተስፋው የተሟጠጠው ዛሬ ሳይሆን  ከምርጫ 97 ወዲህ ነው፡፡ ዛሬማ ከመሟጠጥ አልፎ ተንጣፎ በማለቁ ምርጫ 2007 ማግስት ጀምሮ የሚያሰማውን ‹በቃን› መፈክርና የሚያደርገውን ህዝባዊ እምቢተኝነት ትግል እያየን ነው፡፡
  2. የብሄር ብሄረሰቦች መብት መረጋገጥና ፍትሃዊ ልማት፡- ይህ በህወኃት/ኢህአዴግ ህዳር 29 በሚከበረው በዓል ላይ ብሄር/ብሀሄረሰቦች በሚያሳዩት ጭፈራ፣ የህዝብን ተጠቃሚነት ባላረጋገጠ የሁለት ዲጅት ተከታታይ እድገት ህዝቡ በኢቢሲ እየቀረበ በሚሰጠው ምስክርነት (ፕሮፖጋንዳ ) መረጋገጡ በየዕለቱ ኢቢሲን ስንከፍት ምንመለከተው ነው፡፡በግልጽ  የማይነገረን  በክልሎች መካከል የተፈጠሩ ግጭቶች በወቅቱና በህግና ታሪክ አግባብ መፍትሄ ሳይበጅለት የሚደርሰው  የህይወት፣ አካልና ቁሳዊ ጥፋትና ማኅበራዊ ቀውስ  ነው (በኦሮሚያና በሱማሌ ክልሎች፣በትግራይና  አማራ፣ …) እንዲሁም ብሄር/ብሄረሰቦች የሚያነሱት የማንነትና ህገመንግስታዊ የመብት  ጥያቄን በማፈን የሚወሰደው የአፈና እርምጃ ( ኮንሶ፣ ወልቃይት ጠገዴ፣ ሃመር ) የሚያሳዩት የተገላቢጦሹን ነው፡፡ እነዚሁ ችግሮች ከህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ካጠሉት የቀጣይ ግንኙነት ጥቁር ግርዶሽ አልፈው  በኢህአዴግ  አባል ድርጅቶች መካከልም ያለውን ግንኙነት እያወኩ ስለመሆኑ የ‹‹ጠባብነትና ትምክህተኝነት ፍረጃዎች አመላካች ናቸው፡፡ ይህ በሆነበት በፕሮፖጋንዳ የህዝቦችን መብት የሚያከብር፣ የሚያነሱትን ጥያቄ የሚመልስ፣ ያላቸውን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት የሚያጠናክር ፣… ዘላቂ መፍትሄ አይመጣም ፡፡
ሌሎች በፕሮፖጋንዳውና የህዝብ  ተጨባጭ ህይወት መካከል ያሉትን  ተቃርኖዎች በስፋትና ጥልቀት ማሳየት ይቻላል፡፡ ግን ‹ ነገር ቢበዛ በአህያ አይጫንም › እንዲሉ ነውና እናጠቃለው፡፡
ህወኃት/ኢህአዴግ ዲሽ ለማውረድ በሰው ጣሪያ መንጠልጠል፣ ኢሳትን ኦኤምን አትስሙ የሚል አዋጅ፣ ሰማያዊ፣ ቄይ ፣ ጥቁር አትልበሱ መመሪያ፣ ህዝብ ( ሴቶች፣ ወጣቶች ፣ ህጻናት)  ለመሰብሰብ የ50 ብር ጉቦ ማቅረብ፣….፣ ስለኑሮኣችን ‹የሚያስረዱን› ሆድአደር ምሁራንና ልማታዊ ጋዜጠኞች ፣ ድምጽ አስዘራፊ ምርጫ ቦርድ፣  በአምሳልህ የፈጠርካቸው ‹ተቃዋሚ ፓርቲዎች›  … ሳያስፈልጉህ  ኑሮኣችንና  እኛው ከህይወታችን ፣ በመሰከረልህና ደጋግመን በመረጥንህ  ነበር፡፡ እስከዛሬ የሄድክበትና አሁንም የሙጥኝ ብለህ የያዝከው መንገድ  ሩጫህን ጨርሰሃል ከምንልበት አሳልፎህ  ‹ ሩጫዬን ጨርሻለሁ › ብለህ ለመጻፍ ቁልቁለቱን  በፍጥነት እየነዳህ መሆኑን አስተውል፡፡
ከነዚህ የምናየው በፕሮፖጋንዳ ህዝብን ለተወሰነ ጊዜ ማታለል፣ በማስፈራራት መግዛት ይቻላል፡፡ ግን ሁሌም አይቻልም፣ አሁን ላይ ህዝብ በፕሮፖጋንዳ ጠግቦ ማግሳት፣ በጠመንጃ ፈርቶ መገዛት ፣ የዘር የበላይነትን ተቀብሎ መሸማቀቅ፣…  ‹‹በቃኝ›› ብሎ አደባባይ መውጣቱ ያረጋገጠውም ይህንኑ ነው፡፡ እያልኩ ያለሁት ህወኃት/ኢህአዴግ ቢሄድ ፣ቢቀበር የፖለቲካ ባህላችን ካልተቄየረ፣ በአገራዊ ጉዳዮች ላይ መግባባት ካልፈጠርን ፣ ትግላችን ፓርቲን ከማጥፋት/መቅበር  ወደ አመለካከቱን መታገል፣ አድራጎቱን መቃወም ካልተሸጋገረ፣ በፖለቲካ አመለካከታችንና ትግላችን ከዘረኛነት ወደ ኅብረትና የጋራ ጉዳዮቻችን  ካላደግን …  መንግስት ልንቀይር እንችላለን እንጂ የሥርዓት ለውጥ ስለማምጣታችን ማረጋጫ የለንም፡፡ ከዚህ በመነሳት እያልን ያለነው ከላይ ያነሳናቸው እውነታዎች ሥር ሰደው ባሉበት  ነገ ማንም ቢመጣ  በበነጋውና  ያለህዝብ ተሳትፎ በራሱ/በመንግስት ብቻ ያስወግዳል ማለት አይደለም ፡፡ የዜጎች መብት ባልተከበረበት፣ የህግ በላነት ባልሰፈነበት፣ ዜጎች የአገሪቱን ችግሮች ተረድተውና ነባራዊና ተጨባጩን ሁኔታ ተቀብለው   ለመፍትሄው በጋራ ለመስራት ባልቆረጡበት ፣ …… በአገራቸው ሉዓላዊነትና በራሳቸው ክብር ላይ የሚያነሱት ጥያቄ ባልተመለሰበት … ምርትና ምርታማነትን አፍነው /ሰንገው የያዙ ፖሊሲዎች ባልተስተካከሉበት …፣ በፕሮፖጋንዳ፣ በኃይል አፈና፣ …. ዘላቂ መፍትሄ ሊመጣ ያለመቻሉን  ነው፡፡
በመሆኑም – አዎን ስለቀጣዩ ጊዜና ዘላቂው መፍትሄ እናተኩር ማለቴ  ህወኃት/ኢህአዴግ  በያዘው መንገድ ለመቀጠል የሚያደርገው ሁሉ ‹‹ ላታመልጪኝ  – ምናለ ባታደክሚኝ› እንደተባለው ስለመሆኑ ቅንጣት ጥርጣሬ የለኝም፡፡ ፈላስፎችም  ‹እርግጠኝነትን› የፍልስፍና  እንጂ ‹የፖለቲካ › ጠላት ነው አላሉም ፡፡ ስለቀጣዩ ጊዜና ዘላቂው መፍትሄ  እንጨነቅ ስል በተለመደው በኃይል ላይ የተመሰረተ የቀደመውን የሚቀብር፣ ያለፉትን ተደማማሪ የዕድገት እርምጃዎች ደምስሶ/ክዶ ከዜሮ የሚጀምር፣የወር ባለተራ ገዢ መንግስት  የመተካት  አዙሪት ልንወጣ  አንችልምና  በሥርኣት  ለውጥ የዜጎችን ሰብዐዊና ዲሞክራሲያዊ መብትና ክብር የሚያረጋግጥ ፣ ዘላቂና ቀጣይ ሠላምና ልማት የሚያጎናጽፍ የሁላችን፣  በሁላችን ፣ለሁላችን መፍትሄ ለማምጣት በኅብረት እንነሳ  ማለቴ ነው፡፡
ይህ ማለት ሲጠቃለል ‹‹ ህወኃት/ኢህአዴግ በየቱም መንገድ መሄዱ አይቀሬ መሆኑ ሃቅ ነው፡፡ እኔ እያልኩኝ ያለሁት እና የሚያሳስበኝ  ኢህአዴግ ሲሄድ የሚከተለው/የሚተካውን እንዴት እናምጣው ብለን እንመካከርበት ነው፡፡ ከተቻለ ኢህአዴግንም የዘላቂው መፍትሄ አካል አድርገን/አሳትፈን  ከተለመደው  የመቀባበር አዙሪት  ወጥተን ፣ ካልተቻለም ማለትም ህወኃት/ኢህአዴግ  የቀረበለትን አማራጭ ካልተቀበለና በለመድኩት የአፈና መንገድ እቀጥላለሁ ካለ የኢትዮጵያ ህዝብና የለውጥ ኃይሎች ከአዙሪቱ ውጪ ዘላቂ መፍትሄ እንዴት እናምጣ በሚለው ላይ ስለአገራችንና ህዝባችን ቀጣይ ዕጣ ፋንታ  በኢህአዴግ ላይ እንምከርበትና በሠላም እናስወግደው በሚለው ላይ በአገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ የጋራ ዓላማ ይዘን  በጋራ በትብብር/ኅብረት እንስራ ›› ማለት ነው፡፡
ስለዚህ ህወኃት/ኢህአዴግ በፕሮፖጋንዳ የመቀጠል ጀንበር አዘቅዝቃበታለች፣ ከመጥለቋ በፊት ሊፈጥን ይገባል ፡፡ እንደመግቢያው ባለፈው የዘላቂ መፍትሄ መደምደሚያ ላብቃ፡፡
‹‹….ስለዚህ ህወኃት/ኢህአዴግ ሆይ- በጥልቅ ተሃድሶና ‹ከተቃዋሚዎች ጋር ድርድር አደረግሁ› በሚል  በሚሰራ ፕሮፖጋንዳም ሆነ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በሚፈጸም አፈና ዕድሜ የማራዘም ጀንበር እያዘቀዘቀች  ከመጥለቂያው ተቃርባለችና ‹ ጀንበር ሳለች እሩጥ› ምክራችን ሲሆን ከዚህም ከማንም በላይ ተጠቃሚው አንተ ነህና እወቅበት ማለታችን ለሁላችንም ጠቃሚ ስለሆነና በመሳሪያ ኃይል አምላኪ የመንግስት ለውጥ  ታሪካችንን ስለሚቀይር ነው፡፡››
ለአገራችንና ህዝባችን ደግ ደጉን ያሳስበን፣ መልካሙን ያስተግብረን ዘንድ ቀና ልቡና ብሩህ አዕምሮ፣ ብልህ አመራር … ያድለን ዘንድ ትግላችንን በጸሎት እያገዝን ወደማይቀረው ዘላቂና ቀጣይ መፍትሄ –  የሥርዓት ለውጥ – ጉዞኣችንን በህብረት እናፋጥነው፡፡
10/ 06/09 ግርማ በቀለ ወ/ዮኃንስ ፡፡

Friday, February 17, 2017

በሱዳን ካርቱም የኢትዮጵያ ኤምባሲ በፖሊስ እንደተክበበ ነው ፤ ስድሳ የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን ታስረዋል። (ቆንጂት ስጦታው)

    


VIDEO : በሱዳን ካርቱም የኢትዮጵያ ኤምባሲ በፖሊስ እንደተክበበ ነው ፤ ስድሳ የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን ታስረዋል። (ቆንጂት ስጦታው)
ቆንጂት ስጦታው፡መረጃ ኮም ፦ከካርቱም የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዲፕሎማቶች ምንጮች የሚወጡ ዘገባዎች እንደሚጠቁሙት ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ በኢትዮጵያ ኤምባሲና ተቃውሞ ሊያሰሙ ኤምባሲው ደጅ ላይ በተሰበሰቡ ኢትዮጵያውያን መካከል በተነሳ ችግር ምክንያት ስድሳ የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን መታሰራቸው ተጠቁሟል።
ሰሞኑን የሱዳን መንግስት በሕጋዊነት በሃገሩ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ ከ አቅም በላይ ክፍያ በመጠየቅ ይመኖሪያ ፍቃድ እንዲያወጡ ያወጣውን ሕግ በመቃወም ኤምባሲው እንዲደራደርላቸው ጠይቀው ስምምነት ላይ የተደረሰ ቢሆንም ኤምባሲው ከዜጎች ጉዳይ በፊት ለሕወሓት አርባ ሁለተኛ አመት ቅድሚያ በመስጠት የዜጎችን የውይይት ስብስባ በመሰረዙ ምክንያት ኢትዮጵያውያኑ ለተቃውሞ ኤምባሲው በመሔዳቸው ኤምባሲው የሱዳን ፖሊሶችን በመጥራት ኢትዮጵያውያኑን በማስከበብ ማሳፍሱ ታውቋል።
የታፈሱ ኢትዮጵያውያን ኣማራት ሻራዋህድ ተብሎ በሚጠራው ፖሊስ ጣቢያ ከታሰሩ በኋላ ማምሻውን በሁለት አይሱዙ ተጭነው ሰጃና ወደሚገኝ ጣቢያ መወሰዳቸውን ለኤምባሲው ቅርብ የሆኑ ምንጮች ተናግረዋል።ኤምባሲው በከፍተኛ ጥበቃ ስራ የሚገኝ ሲሆን የሕወሓት በዓልን እጅግ በቀዘቀዘ ስሜት በዝግ መከበሩን ዲፕሎማቶቹ ይናገራሉ።

ህወሓት ኤርትራን ለማስቆረስ ለምን ጎመዠ? – ጋዜጠኛ ፍቃዱ በርታ




የዛሬ ሁለት ዓመት የካቲት 2007 ዓ/ም፣ አራት ኪሎ ከሚገኑት ካፉዎች በአንዱ  በቀጠሮ ከተገናኘን ከአንድ ወጃጄ ጋር ማኪያቶ ይዘን ወግ ጀምረናል፡፡የመገናኘታችን መንስሄ  የህወሐት 40ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ሰበብ ሆኖን፤ የድርጅቱን ታሪክ በሰፊው የሚዳስስ  ተከታታይ ጽሑፍ  በምሰራበት ፍቱን መጽሔት ላይ ለመሰራት በወጣነው ዕቅድ መሰረት፣ ከመሸጫ መደብሮች ያጠናቸውን ስለህወሓት የሚያወሱ መጽሐፍትን  ከወዳጆቻችንን እየተዋስን በማሰባሰብ ላይ ስለነበር ከዚህ ወዳጄ ጋር የተገናኘነው ያገኘልኝን መጽሐፍ ሊሰጠኝ ነበር ፡፡
በተጋጋለው የሃሳብ ልውውጣችን ጣልቃ፤የህወሓት 40ኛ ዓመት አስመልክቶ መቀሌ ላይ ሰለተካሔደው የአከባበር ስነስርአት ጉዳይ አንስተን ወግ ጀመርን፤‹‹ በመቀሌው ዝግጅት ላይ የሱዳኑ ፣የሶማሊያው፣የጅቡቲው፣የውጋንዳው፣የሩዋንዳው፤ ከምስራቅ አፍሪካ መሪዎች ማን የቀረ አለ? ሁሉም ተገኝተዋል፡፡ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር፣የአውሮፓ ህብረት፣የቻይና እና የደቡብ ኮሪያ ተወካዮች ሁሉ ነበሩ፡፡ ሁኔታቸውን  ካስተዋልከው፣ እያከበሩ ያሉት የድርጅት ሳይሆን የሉዋላዊ አገር በዓል ነው የሚመስለው፡፡ሕዝቡንም በዙያ መልክ እያለማመዱት ነው፤›› አለኝ ወዳጄ በስጨት እያለ፡፡
‹‹ ይህ ሁሉ  ሽርጉድ ትግራይን የመገንጠል ዕቅዳቸውን ተግባራዊ ለማድረግ መንገድ መጀመራቸውን ለማሳየት  ይመስልሃል?›› አስከትዬ ጠየቅኩት፤
‹‹ አዝማሚያቸው እንደዚያ ነው፤››
‹‹ በስንት ዓመት ሊያሳኩት የሚችሉ ይመስልሃል?››
‹‹ በዚህ አካሔዳቸው ከቀጠሉ በ15 ዓመታት ጊዜ ውስጥ የሚያሳኩት ይመስለኛል፤››
ያደቆነ ሰይጣን ሳያቄስ አይቀርም እንደሚባለው፤ የህወሓት የ40 ዓመታት  ትግራይን ከአገርዋ የመለየት ውጥን መሆኑ ነው፤ለመሆኑ ህወሓት እና እኛ እንዴት ለዚህ ተደራረስን?
በኤርትራ ተወላጁ ኢትዮጵያዊ ሀገር ወዳድ ምሑር በፕ/ር ተስፋፅዮን መድኀንዬ የተጻፈው ÇEritrea: Dynamics of a national questionÈ፤ የተሰኘ ባለ 346 ገጾች መጽሐፍ በ1979 ዓ.ም. ለንባብ በቃ፤ የመጽሐፉ ጠቅላላ መልዕክት ሽፋኑ ላይ ቁልጭ ብሎ ይታያል፡፡አፈሙዙን  ቁልቁል ከዘቀዘቀው ክላሺንኮቭ  ጋር የተገጠመው ሳንጃ  ከፊል አካል  መሬቱን ሰርስሮ ገብቶ ከጎኑ ከበቀለ  አበባው ከፈካ ችግኝ ጋር ከገመድ ተያይዞ ይታያል፡፡መጽሐፉ ኢትዮጵያ  ከኤርትራ አማጺያን ጋር መካከል 27 ዓመታት ላስቆጠረው  የእርስ በእርስ ጦርነት ምክኒያት  የአገር ሀብት፣ ለቀጠፈው የሰው ልጅ  ሕይወት፣እንዲሁም  የአገር ህልውና አደጋ ላይ መውደቁ  ለሚሳስባቸው ዜጎች እንደ ፕ/ር ተስፋፅዮን አይነቱን ለአአገር ተቆርቋሪ ዜጋ  ማግኘት እንደ ትልቅ  ፀጋ የሚቆጠር አጋጣሚ ነበር፡፡
ፕ/ር ተስፋፅዮን  በመጽሐፋቸው ከእርስ በርስ ጦርነቱ የደቀነቀውን አደጋ በጥልቀት ከመዳሰሳቸው በተጨማሪ የችግሩ ዘላቂ መፍትሔ በሁለቱ ወገኖች መካከል የሚደረግ አውዳሚ ጦርነት ሳይሆን  የኢትዮጵያ መንግስት እና ሻዕቢያ በጠረጴዛ ዙሪያ በሚያደርጉት ድርድር መሆኑን ያመላክታል፡፡እንደ ተስፋፅዮን እምነት ሻዕቢያ እያካሄደው የነበረው ጦርነት ኢምፔሪያሊስቶች ኢትዮጵያን ላማዳከም የጠነሰሱት ሴራ ውጤት መሆኑን ያስረግጣል፡፡ ከችግሩ መውጫ መንገድም ፣ ንጉሡ ኃይለ ስላሴ ያፈረሱትን እ.ኤ.አ. የ1953ቱ የኤርትራ ሕገ መንግሥት እና በ1952ቱ ኤርትራ በተመድ የጸደቀላትን የፌዴሬሽን መብት ወደቦታው በመመለስ  መሆኑን  ለከመንግስቱ ኃይለ ማሪያም መንግሥት ምክር ለግሰዋል፤ Ç… Ethiopian leaders should seriously consider ‘ Federation’ as the practical solution of Eritrean problem at the moment. They should reconsider their views on the nature and real purpose of Ethio-Eritrean ‘Federation’ effected in 1952È(p.292).
ለኤርትራ አማጽያን ወደ በረሃ  መትመም ሰበብ  ከተመድ ጋር የተገባው  የኤርትራ በፌዴሬሽን ከኢትዮጵያ ጋር የመቀላቀልቃ የስምምነት ውል ተጥሶ፤ የኃይል ውህደት በመፈጸሙ ምክኒያት የመጣ  መዘዝ ነበር፡፡ ምሑሩ ለቀድሞ ለኢትዮጵያ መንግስት  ያቀረቡት ፌዴሬሽኑ ተመልሶ ኤርትራም በኢትዮጵያ ትላ ስር ትኑር፣የኢትዮጵያ እንድነትም ከተደቀነበት አደጋ ይዳን፤የአገሩ አንድነትና ሰላም  ተጠብቆ መኖር ግድ ለሚለው ማንኛውም  ዜጋ ልብን በሲቃ የሚሞላ የምስራች ነበር፡፡
በወቅቱ ለፕ/ሩ አሳብ በኢትዮጵያ መንግሥትም ሆነ በሻእቢያ በኩል የተሰጠ ይፋዊ ምላሽ ይኑር አይኑር የታወቀ ነገር ባይኖርም፤ፈጣን እና አስደንጋጭ ምላሽ ይዞ ብቅ ያለ ሌላ አካል ነበር፡፡
በንዴትና ቁጣ የተንጨረጨረው ጽሑፍ ተቃርኖ የሚጀምረው ገና ከሽፋኑ የተስፋ ፅዮንን መጽሐፍ ሽፋን ቁልቁል በመገልጥ  ነው፡፡ ርእሱምን  ብረት ህዝቢ ኤርትራ ቁልቁል አፉ አይድፋአን (የኤርትራ ሕዝብ ጠመንጃ አይዘቀዘቅም) የሚል ሲሆን፤የጽሑፉም ባለቤት የትግራዩ ነጻ አውጪ መሪ አቶ መለስ ዜናዊ ነበሩ፡፡
አቶ መለስ በጽሑፋቸው ፣ የተስፋ ፅዮንን ኤርትራዊነት ጥርጣሬ ውስጥ ከማስገባት እና በመዘርጠጥ ሳይገቱ ፤ አንድ ሰው እውነተኛ ኤርትራዊ መሆን ከፈለገ ማሟላት አለበት  የሚሉትን ዝርዝር ህገ ደንብ እንደሚከተለው ይተነትናሉ፤ 1.የኤርትራ ጉዳይ የቅኝ ግዛት ጥያቄ ነው ብሎ  የሚያምን ፣ 2.የኤርትራ ጥያቄ ብቸኛ መፍትሔ ፌዴሬሽን ወይም ኮንፌዴሬሽን  ሳይሆን መገነጠከል ብቻ መሆኑን ፤3.የኤርትራ የመገንጠል ጥያቄ በመርህ ሳይሆን በገቢር ደረጃ እንዲከበር ተቀብሎ ከኢትዮጵያ ጋር አብሮ መኖር በሚለው አሳብ ፈጥሞ የማይስማማ ፣4.ሙሉ ለሙሉ ካልሆነ በቀር የኤርትራ መሬት ወይም ጥቅም አሳልፎ በመስጠት ወይም ለኢትዮጵያ በመተው የሚደረግ (የሚመጣ ነጻነት)… የማያወግዝ …ወዘተ  (ከአገር በስተጃርባ ከገጽ 129-130) ከኤርትራ ከተወለዱ እናት እና አባት መገኘቱ ብቻውን ኤርትራዊት  ለመሆን ብቁ እንደማያደርጉት በድርሳነ መለስ ጽሑፋቸው ይደነግጋሉ፡፡እንደ ተስፋፅዮንም  እምነት የሻዕቢያ ጦርነት ኢምፔሪያሊስቶች ኢትዮጵያን ለማዳከም የጠነሰሱት ሴራ ከሆነ የኢትዮጵያ መዳከም እንደ ኢምፔሪያሊስቶቹ ጮቤ የሚያስረግጠው ሕወሐት የሚባል ድርጅት  እንዳለ አለመግለጻቸው ሳይጸጽታቸው የሚቀር አይመስለኝም፡፡
የህወሓት ለኤርትራ መገንጠል የነበረው እንደ እሳት የሚንቀለቀል ፍቅር ከመጠን ያለፈ እንደነበር ‹‹ በጸጸት››  የሚያስታውሱት ስለመሆኑ አንጋፋው ታጋይ አቶ ገብሩ አስራት እንዲህ ያቀምጡታል፤‹‹የኢትዮጵያን እንዲሁም የብሔሬን ጥቅም አስጠብቃለሁ ብሎ የቆመው ህወሓት ፣በኤርትራ ጉዳይ ጣልቃ ገብቶ ፡ የሚጠቅማችሁ ነጻነት ነው ብሎ መከራከሩ ተገቢ እልነበረም፡፡ከራሳቸው ከኤርትራውያን አንድነት ይጠቅመናል የሚል ሐሳብ ሲሰነዘር፡እኛ ጭራሽ ስለአንድነት መወራት የለበትም ብለን፣ ያዙን ልቀቁን ማለታችን ፣ መለስ ብዬ ሳስበው ይጸጽተኛል›› (ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ፣ከ98-101)፡፡ በእርግጥ የአቶ ገብሩ ጸጽት ከልብ ከሆነ ድርጅታቸው  ኤርትራን ለማስገንጠል  የፈለገበት ትክክለኛ ምክንያት  ምን እንደነበር ሊያጋሩን በተገባ ነበር፡፡
ሕወሓት  የኤርትራን ለማስገንጠል  ላሳደረው  መሰሪ ፍላጎት፤ የተስፋ ፅዮን መጽሐፍ በማብጠልጠል ብቻ አላበቃም፤ለምሳሌ በ 1979 ዓ/ም ድርጅቱ አቋሙን ባንጸባረቀበት ‹‹የኤርትራ ሕዝብ ትግል ከየት ወዴት?;›› የተባለው መጽሐፍ የኤርትራ ጥያቄ የቅኝ ግዛት  በመሆኑ የኤርትራ ህዝብ ለነጻነት የሚያደርገው ትግል ትከክለኛ እና ፍትሐዊ መሆኑን በማስቀመጥ ፤እግረ መንገዱን ሻዕቢያ ከኤርትራ ነጻነት ውጭ ሌሎች አማራጮችን እንዳይፈልግ አጣብቂኝ ውስጥ ለመክተት ተጠቅሞበታል፡፡ በሌላ በኩል  የ1981ዱ የመፈንቅለ መንግሥቱ ሙከራ ወቅት፤ ሻእቢያ  ከኩዴታው አድራጊ ጀነራሎች ጋር ለድርድር በተቀመጠበት ሲቀመጥ፤ ኤርትራን ከማስገንጠል ውጪ ባሉት ሁኔታዎች እንደ ማንኝውም ኢትዮጵያዊ ድርጅት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ለመሳተፍ  ስምምነት ላይ ደርሶ ለተግባሪነቱም  የገባውን የተኩስ አቁን ውል ተግባራዊ በማድረግ ለስምምነቱ የገባውን ግዴታ ተወጥቶ ነበር፡፡ ህወሓት በበኩሉ የጀራሎቹን የሰላም ስምምነት ጥሪ ውድቅ ከማድረጉም በተጨማሪ የሻዕቢያ  መስማማት የኤርትራን ሕዝብ የነጻነት ትግል ለሽያጭ ከማቅረብ ጋር አነጻጽሮ የውግዘት መግለጫ እስከ ማውጣት ደርሶ ነበር፡፡ (አባቴ ያቺን ሰዓት፤መጽሐፍ) ፡፡
የኤርትራ መገንጠል  ህወሓትን  ለምን  አስጎመጀው?
በመንግሥት ዩኒቨርስቲ ውስጥ የታሪክ መምህር የሆኑት አቶ መስፍን ዳኛቸው (ስማቸው የተቀየረ)  ህወሓት ኤርትራን በተመለከተ ያራምድ የነበረው አቋም ሲያብራሩ፤‹‹ ህወሓት ለኤርትራ የተለየ ስስ ልብ ኖሮት አያውቅም፤ወይም የሻእቢያ ተላላመኪም ተንበርካኪም ሆኖ አይደለም፤ ይልቅስ ሚናውን የምጣዱ እያለ የእንቅቡ ተንጣጣ ሲያስመስል የነበረው ሆን ብሎ ለዘዴው ነው፡፡ወያኔ የኤርትራ መገንጠል ያስጎመዠው የነበረው፤ ከተደበቀችበት ጉድጓድ ውስጥ ብቅ ስትልለት ቀጨም ለማድረግ  በከፍተኛ ጥንቃቄና ትኩረት አድፎጦ አይጥዋን እንደሚጠባበቅ የተራበ ድመት ነበር፤››
እንደ ታሪክ ተመራማሪው እምነት ፣ህወሓት  የኤርትራ  ሕዝብ ከሻእቢያ ከነጻነት ውጪ ምንም እንዳይቀበል በፕሮፖጋንዳ በማደንዘዝ፤ ሻእቢያን እጁን ጠምዝዞ ወዶም ይሁን በተጽእኖ ፣አውቆም ይሁን ሳያውቅ ህወሓት ባዘጋጀለት ወጥመድ ሰተት ብሎ ገብቶለታል፡፡አቶ መስፍን ለዚህ ሁሉ ምክኒያት ነው የሚሉትን ሲያስቀምጡ፤ ‹‹ ኤርትራና ኢሳያስ ያሉባት ኢትዮጵያ ለወያኔ ምቾት ይነሳዋል፤ ሻእቢያ እና ኢሳያስ አፎርቂ ያቀፈች ኢትዮጵያ ለወያኔ  ያፍነዋል፤ይጠበዋል፤ ጭንቅ ጥብብ ያስኘዋል፤›› ለምን ብትሉ፤‹‹ ኢሳያስና ኤርትራ  ካሉ  ኢትዮጵያ ለወያኔ የምታለብ ላም መሆን እንደማትችል ህወሓት አውቆታል፡፡ኤርትራን የተቀበለች ኢትዮጵያ የህወሓት መፈኝጫ ልትሆን እንደማትችል እነመለስ ዜናዊ አልጠፋቸውም፡፡ለዚህ ነው ለህወሓት እና ለመለስ የስልጣን ጥም ሲባል ኤርትራ ከኢትዮጵያ ተገንጥላ  መሔድ የነበረባት፤››
የሕግና የፖለቲካ ምሑሩ አቶ ደረጄ አበበ (የሳቸውም ስም ተቀይሮዋል) በአቶ መስፍን ትንታኔ መስማማታቸውን ገልጸው፣እንደ እሳቸው እምነት የወያኔ አሻጥር ከዚያም በላይ አልፎ ይሄዳል፤‹‹ የሕወሓት አድርባይነትና ደባ በዚህ የሚበቃ አይደለም፡፡ እንደ ወያኔ ላለ መሰሪ ቡድን የስልጣን ጥም ችጋር ጋር ሲነጻጸር የኢትዮጵያ ሕዝብ ሉዋላዊነትና የግዛት አንድነት አደጋ ላይ መውደቅ ኢምንት ጉዳይ ነው፡፡እንደ ህወሓት ፍላጎት ኤርትራ ትሂድ እንጂ ካዚያ በኋላ የኢትዮጵያን ግዛት ተቆጣጥሮ ሥልጣንም ሃብትም ማካበት ቀላል ነው፡፡  ያም አልበቃ ብሎዋቸው፣ በሕገ መንግስቱ ውስጥ አንቀጽ 39ኝን ያስገቡት ለጌጥ ሳይሆን፤ የኢትዮጵያን ሕዝብ በሰቀቀን እያባነኑ ለመግዛት፤ ሕዝቡ ከእንቅልፉ ነቅቶ ችግር የሚፈጥር ከሆነ  ፣ወይም ግራ ተጋብቶ ሲዘናጋ ወይም በቃን ብለው ሲያስቡ  ትግራይን ይዞ መሔድ ይቻላል ብለው ተማምነው ነው፡፡አሳዛኙ ነገር እነሱ የትግራይ ሪፐንሊክን መገንባት የሚያልሙት ቀሪውን አገር በማፍረስ መሆኑ ነው፤ ››
ከእንግዲህ የኤርትራ ሕዝብ ኢትዮጵያ ጋር መዋሃድ  ቢፈልግ እንኳን ህወሓት እያለ በቀላሉ ያሳካል ብለው አቶ ደረጄ  አያምኑም፤ይልቅስ፣ ‹‹ ሕወሓት በሥልጣን ማማ ላይ ላስቀመጣቸው እና የሕወሓትን ሥርወ-መንግሥት በኢትዮጵያ ሕዝብ ኪሳራ እውን እንዲሆን ላደረገላቸው፣ ሽምጥ እየጋለቡት ለዚህ ላደረሳቸው የሥልጣን ፈረሳቸው ሻእቢያ ‹‹ዕድሜህን ያርዝመው›› ማለታቸው አይቀርም፤››
ከአራት ኪሎው ወዳጄና ከሁለቱ ምሑራን ጋር  ተገናኝተን ይህን ውይይት ካደረግን ሁለት ዓመት ሞላን፡፡ ከዚያ በኃላ ብዙ ነገሮች ተቀያይረዋል፤ ህወሓትም ኢትዮጵያም  የዛሬ ሁለት አመት  እንደነበሩት አይደሉም፤ሶስቱ ሰዎች፤የአራት ኪሎው ወዳጄና ሁለቱ ምሑራን ዛሬ በህወሓትና በአገራችን ላይ የሚኖራቸውይ  እሳቤ  ከያኔው የተለወጠ ሊሆን እንደሚችል ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ምክኒያቱም፣ ዛሬ ቢያንስ ቢያንስ  የህወሓት ጎረቤቶቹ ፣የቴዎድሮስ ልጆች ጎንደሬዎቹ ከህወሓት በስተደቡብ ሆነው እሳት ጨብጠው ቆመዋል…፡፡

“የድንበሩ ጉዳይ የመጨረሻ ደወል!” የመጨረሻው ደውል እባላለሁ



 የመጨረሻው ደውል እባላለሁ  ።

“የድንበሩ ጉዳይ የመጨረሻ ደወል!” የመጨረሻው ደውል እባላለሁ



 የመጨረሻው ደውል እባላለሁ  ። የወያኔ መንግስት ከሱዳን መሪዎች ጋር ለሱዳን ተላልፎ ስለሚሰጠው የድንበር ዙሪያ መሬት ጉዳይ ስምምነት ለመፈራረም በሚቀጥሉት ቀናቶች በመቀሌ ከተማ ቀጠሮ መያዙን ሱዳን ትሪቡን ጋዜጣ ዘግቧል ። ስምምነቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ገበሬዎችን የሚያፈናቅል ከመሆኑም በላይ የአገራችን ሉዓላዊነት የሚዳፈር በመሆኑ ይሄንን ከህዝብ የተደበቀ ታሪካዊ ክህደት በጽኑ እቃወማለሁ።
“የድንበሩ ጉዳይ የመጨረሻ ደወል!”

የኢትዮ-ሱዳን ድንበር አከላለል ጉዳይ በመቀሌ እየተመከረበት ነው




BBN News በኢትዮጵያ እና በሱዳን ድንበር መካከል ያለውን አከላለል እና ችግሮች በተመለከተ በመቀሌ ውይይት እየተደረገ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡ በዛሬው ዕለት በተጀመረው በዚሁ ውይይት ላይ የሁለቱ ሀገራት ባለስልጣናት የታደሙ ሲሆን፣ የሱዳን እና የኢትዮጵያ ክልሎች ባለስልጣናትም የውይይቱ ተሳታፊ መሆናቸው ታውቋል፡፡ በዚህም መሰረት ከሱዳን በኩል የገዳሪፍ፣ የጥቁር አባይ፣ የሴናር እና የከሰላ ግዛቶች ኃላፊዎች ሲታደሙ፣ በኢትዮጵያ በኩል ደግሞ የትግራይ፣ የአማራ እና የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ኃላፊዎች ተወክለዋል፡፡
ይኸው ስብሰባ በኢትዮጵያ እና በሱዳን ድንበር አካባቢ ያለውን ተደጋጋሚ ግጭት ለማስቀረት የታለመ ነው ቢባልም፣ ምንጮች እንደሚሉት ከሆነ ግን፣ የሱዳን ባለስልጣናት ወደ ኢትዮጵያ ተወስዶብናል የሚሉትን መሬት ለማስመለስ ጥያቄ ማቅረባቸው ታውቋል፡፡ ሁለቱ ሀገራት ድንበሮቻቸውን ለማካለል ከሁለት ዓመታት በፊት ስምምነት ላይ ደርሰው የነበረ ሲሆን፣ ሆኖም ስምነቱ የኢትዮጵያን ጥቅም ያስደፈረ እንደነበር በወቅቱ ሲገለጽ ቆይቷል፡፡ በርካታ ኢትዮጵያውያንም ይህን ስምምነት በጽኑ ሲቃወሙት እንደነበር አይዘነጋም፡፡
መሬታችን በኢትዮጵያ አርሶ አደሮች ተወስዶብናል የሚሉ የሱዳን የጸጥታ ሃይሎች በተደጋጋሚ የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው በመግባት የአማራ ክልል አርሶ አደሮችን ሰብል አውድመው በመውጣት ተደጋጋሚ ጥቃት መፈጸማቸው ይታወቃል፡፡ እነዚሁ ሰርጎ ገቦች በአካባቢው የሰፈሩ የኢትዮጵያ አርሶ አደሮችን በማፈናቀል ጥቃት ሲያደርሱ መቆየታቸውን የተለያዩ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

Thursday, February 16, 2017

ከብዙ ማጉላላት በኋላ ምርጫ ቦርድ ለመኢአድ እና ሰማያዊ አመራሮች እውቅና ሰጠ – የሚሊዮኖች ድምጽ

    


16780430_617476631771460_1370417707_n 16780023_617476731771450_1559704480_n
መኢአድ እና ሰማያዊ በአገር ቤት ሰላማዊ በሆነ መንገድ የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ናቸው። የመኢአድ ሊቀመንበር ዶር በዛብህ ደምሴ ናቸው። ዶር በዛብህ አንጋፋ የመኢአድ አመራር ሆነው ለብዙ አመታት አገልግለዋል። በቅንጅት ጊዜ የቅንጅት ብሄራዊ ምክር ቤት አባልም ነበሩ።
የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ከአንጋፍ ወጣት ፖለቲከኞች መካከል አንዱ የሆነውና ከነሃብታሙ አያሌው ጋር ለሁለት አመት ታስሮ የነበረው የሺዋስ አሰፋ ነው።
እነዚህ ሁለት ድርጅቶች በምርጫ 2007 ተካፍለው ነበር። ያኔ የድርጅቱ መሪ አቶ አበባው መሐሪና ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ነበሩ። ድርጅቶቹ ጠቅላላ ጉብዬ አድርገው አዲስ አመራር መርጠዋል። አቶ አበባው የጉባየዉን ዉሳኔ ተቀብለው ከሃላፊነታቸው በጸጋ ነው የቀቀኡ ሲሆን፣ ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ግን ምርጫ ቦርድ ድረስ ሄዶ በመክሰስ፣ ጉብዬዉን ለ15 ቀናት እንዲራዘም በማድረግ፣ የጠቅላላ ጉብዬዉን ዉሳኔ ለመቀበል ፋደኛ አልሆኑም። አሁንም ከተወሰኑ አባላት ጋር በመሆኑ አዲሱን የሰማያዊ አመራር በ”ወያኔነት” ለመክሰስ እየሞከሩ ነው። ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት አንድ ቀን ወህኒ አድረው የማያውቁ ሲሆን፣ ለሁለት አመታ የታሰረዉን የሺዋስ አሰፋ፣ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምክንያት ለወራት የታሰሩ የድርጅቱ የዉጭ ጉዳይ ሃላፊ አቶ አበባ አካሉ፣ የሴቶች ጉዳይ ሃላፊ ብሌን መስፍን፣ የድርጅቱ የምክር ቤት ሰብሳቢ ይድነቃቸው ከበደ የመሳስሉ በርካታ ለትግሉ ዋጋ የከፈሉ ታጋዮች ያሉበትን የሰማያዊ አመርር፣ እርሳቸውን አባላት ከሃላፊነት ስላስነሷቸው ብቻ “ወያኔዎች ናቸው” ብሎ ማስወራታቸው ብዙዎችን አስገርሟል።
እነዚህ ሁለት ድርጅቶች፣ ባደረጉት ጠቅላላ ጉባዬ፣ ምርጫ ቦርድ፣ በሕጉ መሰረት ተወካዮችን ልኮ፣ ኮረም መሙላቱን አረጋግጧል። ጉብዬውም የተደረገው በድርጅቶቹ ደንቡ መሰረት፣ አሰራሩ በመከተል መሆኑን አጣርቶ፣ በምርጫ ቦርድ በሕጉ መሰረት፣ ለአዲሱ አመራር እውቅና መስጠት ነበረበት። ሆኖም ግን ምርጫ ቦርድ ያንን ለማድረግ ፍቃደኛ ሳይሆን ለብዙ ወራት ቆይቷል። ድርጅቶቹ የተለያዩ ደብዳቤ ቢጽፉም፣ ምላሽ ለመስጠት ፋደኛ ሳይሆን፣ የተለያዩ ምክንያቶች እየሰጠ፣ ሲያጉላላቸው ቆይቷል።
ሆኖም ከብዙ የደብዳቤዎች መላላክ በኋላ ምርጫ ቦርድ ለመኢአድ እና ለሰማያዊ አዲስ አመራሮች እውቅና ሰጥቷል።
መኢአድ የፖለቲክ ፕሮግራም አሻሻያዎች አድርጎ የነበረ ሲሆን፣ ከአንድነት ፓርቲ ጋር ዉህደት ለመፈጸም በነበረበት ወቅት በጋራ ያጸደቁትን ፖሮግራም፣ ፕሮግራሙ አድርጎ ማጸደቁም ይታወሳል።
በተያያዘ ዜና መኢአድ እና ሰማያዊ አብረው ለመስራት እንደወሰኑ የደረሰን መረጃ ይጠቁማል። በመኢአድ እና በሰማያዊ አመራሮች መካከል ጠንካራ የሆነ መተሳሰር እንዳለ የተረዳን ሲሆን፣ ድርጅቶቹን በይፋ ግንባር ሊፈጠሩ እንደሚችሉ ለማወቅ ችለናል።የቀድሞ የአንድነት ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ለዚህ ለሰማያዊ እና መኢአድ ስብስብ ድጋፍ እንደሚሰጡና ይሄንን ስብስብስ በመቀላቀል ጠንካራ፣ አገር አቀፍ፣ አማራጭ የሚሆን ኢትዮጵያዊ ሃይል ለመመስረት የሚቻልበት ሁኔታም ይፈጠራል ተብሎ ይጠበቃል።
ከብዙ መጉላላት በኋላ ምርጫ ለሰማያዊ የተጻፋ የምርጫ ቦርድ ደብዳቤ

ሀወሐት በ42 አመት በትግልና በስልጣን አገዛዙ ዘመን ለትግራይ ህዝብ ብለው ለመላ የኢትዮጱያ ህዝቦች ካለፉት ገዥዏች የተለዬ ምን ለውጥ አመጣልን ???






የየካቲት 11  42ኛ  የህወሐት በአል ሲከበርና ፈይዳው ፣
——————————————————
ለካቲት 11 / 6  /67 /ዓ ም  ወደ ደደቢት በረሐ ስንዘምት የነበረን  አላማ  የደርግን ስርአት አስወገደን   የተሻሻለች ሁሉም አይነት  ሰብአዊና ዲሞክራሲ መብቶች የሚከበሩባት ፣

ሀወሐት በ42 አመት በትግልና በስልጣን አገዛዙ ዘመን ለትግራይ ህዝብ ብለው ለመላ የኢትዮጱያ ህዝቦች ካለፉት ገዥዏች የተለዬ ምን ለውጥ አመጣልን ???




የየካቲት 11  42ኛ  የህወሐት በአል ሲከበርና ፈይዳው ፣
——————————————————
ለካቲት 11 / 6  /67 /ዓ ም  ወደ ደደቢት በረሐ ስንዘምት የነበረን  አላማ  የደርግን ስርአት አስወገደን   የተሻሻለች ሁሉም አይነት  ሰብአዊና ዲሞክራሲ መብቶች የሚከበሩባት ፣  የህግ የበላይነት የሚረጋገጥባት፣ የተለያዬ ፖለቲካ  አስተሳሰብ  ያላቸው ፖለቲካ ሀይሎች በሰላምና በነጻነት  የሚንቀሳቀሱባት፣ የበለጸገች ኢትዮጱያ  ለመመስረት  እንዲሁም ፣ የላሸቀው  በስብሶ የነበረ ስርአት በማስወገድ  ፍትሐዊ  የሆነ  ከሙሱናና  የተበላሸ  ስርአት የጸዳ ስርአት ለማምጣት ነበር ።
በተጨማሪ  በሀገራችን  ዜጎች በእኩልነት እንዲኖሩ ፣ የተመጣጠነ  የኢኮኖሚ ክፍፍል እንዲኖር ፣ የዘር  የእምነት  የቢሄር ልዩነትና መናናቅ እንዲወገድ ፣ ድኽነት ስደት እንዲጠፍ እንዲወገድ ፣ ለማድረግ ነበር ።
የሁሉም  ኢትየጱያዊ  ማህበራዊና እኮኖሚያዊ  ችግሮች  እንዲቀረፉ  ማድረግ ፣ በተለይ ደግሞ የገጠር ኃላቀር  ንሮና   መሬቱ በመሳፍንቶች  እጅ ስለነበር አርሶአደሩና  የከተማ ነዋሪ የመሬት ባለቤትነት እንዲነረው ታሳቢ በማድረግ ነበር  ወደ ደፈጣ ውግያ  የዘመተው ።
በሀገራችን  የቢሄር ቢሄረሰብ  መብቶች እንደከበሩ  በማኸላቸው የነበረ ግጭት ቂም  በቀል   በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ  የነበረው  የባላባታዊ  የመሳፍንቶች  ዘውዳዊ  ሰርአትና   ለዘውዳዊ  ስርአት  ገልብጦ በሀይሉ ስልጣን  የያዘ  ወታደራዊ ስርአት  በማስወገድ  በመቃብራቸው  በህዝብ  የተመረጠ ህዝባዊ መንግስት  እንዲመሰረት  ለመታገል ነበር  ።
ሌላ ከአድልዏ የጸዳ የትምህርቲ ፣ የጤና  ፓለሲ እንዲኖር ፍትሀዊ በሆነ የትምህርት የመታከም  መብት  እንዲኖር   ፣ የዘውዳዊና የደርግ ባለስልጣናትና የቤተሰቦቻቸው  ቅምጥል ቀርቶ የዜጎችን  እኩል ተገልጋይነት እንዲኖር ነበር ።
በሀገራችን  በመንግስትና  በፓርቲ በለስልጣናት በባለቤትነት የሚያዝ ወይ የሚታወቅ   የንግድና  የእንድስትሪ ተቋማት እንዳይ ነሩ ፡ በሀገራችን የግለሰው  እና የሀብት ባለቤትነት
           ክፍል አንድ የነበሩ አላማዎች ፣
          ————————————
የየካቲት 11  42ኛ  የህወሐት በአል ሲከበርና ፈይዳው ፣
——————————————————
፠፠     ሀወሐት በ42 አመት በትግልና በስልጣን  አገዛዙ  ዘመን   ለትግራይ ህዝብ ብለው ለመላ የኢትዮጱያ  ህዝቦች
ካለፉት ገዥዏች  የተለዬ ምን ለውጥ አመጣልን ???
፠፠  ለካቲት 11 / 6  /67 /ዓ ም  ወደ ደደቢት በረሐ ስንዘምት የነበረን  አላማ  የደርግን ስርአት አስወገደን   የተሻሻለች ሁሉም አይነት  ሰብአዊና ዲሞክራሲ መብቶች የሚከበሩባት ፣  የህግ የበላይነት የሚረጋገጥባት፣ የተለያዬ ፖለቲካ  አስተሳሰብ  ያላቸው ፖለቲካ ሀይሎች በሰላምና በነጻነት  የሚንቀሳቀሱባት፣ የበለጸገች ኢትዮጱያ  ለመመስረት  እንዲሁም ፣ የላሸቀው  በስብሶ የነበረ ስርአት በማስወገድ  ፍትሐዊ  የሆነ  ከሙሱናና  የተበላሸ  ስርአት የጸዳ ስርአት ለማምጣት ነበር ።
፠፠  በተጨማሪ  በሀገራችን  ዜጎች በእኩልነት እንዲኖሩ ፣ የተመጣጠነ  የኢኮኖሚ ክፍፍል እንዲኖር ፣ የዘር  የእምነት  የቢሄር ልዩነትና መናናቅ እንዲወገድ ፣ ድኽነት ስደት እንዲጠፍ እንዲወገድ ፣ ለማድረግ ነበር ።
፠፠    የሁሉም  ኢትየጱያዊ  ማህበራዊና እኮኖሚያዊ  ችግሮች  እንዲቀረፉ  ማድረግ ፣ በተለይ ደግሞ የገጠር ኃላቀር  ንሮና   መሬቱ በመሳፍንቶች  እጅ ስለነበር አርሶአደሩና  የከተማ ነዋሪ የመሬት ባለቤትነት እንዲነረው ታሳቢ በማድረግ ነበር  ወደ ደፈጣ ውግያ  የዘመተው ።
፠፠    በሀገራችን  የቢሄር ቢሄረሰብ  መብቶች እንደከበሩ  በማኸላቸው የነበረ ግጭት ቂም  በቀል   በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ  የነበረው  የባላባታዊ  የመሳፍንቶች  ዘውዳዊ  ሰርአትና   ለዘውዳዊ  ስርአት  ገልብጦ በሀይሉ ስልጣን  የያዘ  ወታደራዊ ስርአት  በማስወገድ  በመቃብራቸው  በህዝብ  የተመረጠ ህዝባዊ መንግስት  እንዲመሰረት  ለመታገል ነበር  ።
፠፠  ሌላ ከአድልዏ የጸዳ የትምህርቲ ፣ የጤና  ፓለሲ እንዲኖር ፍትሀዊ በሆነ የትምህርት የመታከም  መብት  እንዲኖር   ፣ የዘውዳዊና የደርግ ባለስልጣናትና የቤተሰቦቻቸው  ቅምጥል ቀርቶ የዜጎችን  እኩል ተገልጋይነት እንዲኖር ነበር ።
፠፠  በሀገራችን  በመንግስትና  በፓርቲ በለስልጣናት በባለቤትነት የሚያዝ ወይ የሚታወቅ   የንግድና  የእንድስትሪ ተቋማት እንዳይ ነሩ ፡ በሀገራችን የግለሰው  የዲሞክራሲ  መብቶች  እና  የሀብት  የግል ባለቤትነት ገዥና የበላይነት  እንዲ ነረው ነበር  የታገልነው እና  በሞቶ ሽዏች  የሚቆጠሩ ወጣቶች ሂወት የከፈሉበት  ። በዛው ልክ አካላቸው የጎሉበት  ትግል  አሁን በመሬት የምናየው ያለን  ጉድ አልነበረም ።
፠፠  የዘውዳዊ ስርአት የሲ አይ  ኤ የስለላ መረብና የመንግስቱ ሃይለማርያም   የከጅቢ ስለላ ወጥመድ  ህዝባችን  እንዲላቀቅ አላማ ነበረን ።
፠፠  የህወሐት የ42  የልደት በአል   የተመሰረተበት   በአል ሲከበርስ  በምን ደረጃ እንገኛለን  ????  እንግዲህ  የ42 አመት ጉዞው ስመለከተው  ኢትዮጱያ ሀገራችን በተለይ ደግሞ  ያቺ  በአድልዏ  ለምታና  በልጽጋ   የምትባለው 5ሚሊዮን  የተጨቆነ ህዝቢ ያላት የትግራይ ክልል   በሚከተሉት ነጥቦች ይገለጻል ።
———————————————————
፠፠   የዜጎች ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ  መብቶች  የህግ የበላይነት  ለሽታውም የማይታይበት  የአፈና ሞደል የሆነች  አገርና ህዝቦቻ እየተመለከትን  ነው።
፠፠    የዜጎች በነጻ የመደራጀት መብት የተከለከለች  የተወዳዳሪ ፖለቲካ   ፓርቲዏች በነጻ እንዳይንቀሳቀሱ  የተዘጉባት ፣ እንዳውም የፓርት መሪዏች ፡አባሎቻቸው ፣ ደጋፊዏቻቸው  በሀገሪቱ እሱር ቤቶች  የታጎሩባት   ፡ በአጠቃላይ  የቡዛንነትን  ነጻ ተሳትፎ የከሰመባት አገር እየተመለከትን  ነው ።
፠፠      በተለይ በአሁኑ ጊዜ  ዲሞክራሲያውያን የሆኑ የፓርቲ መሪዏች ፣ ጋዜጦኞች ፣ የፓርት ደጋፊዏች  በማሰር በመሰቃየት በአለም  የታወቀች  አገር የሆነች አገር እያየን ነው ።
፠፠ የህትመት ውጤቶች  ነጻ ፕሬስ ፡ የማህበራዊ  ሚድያ  ፣ የመናገር  የመጻፍ ፣ በፈለከው ሚዲያ ለመናገር የተከለከለበት ። የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ፣ የመሰብሰብ ፣  በመንግስት ሚዲያም አንባ ገነኑ ስርአት ከሚፈልገው  ውጭ ለመናገር የማትችልበት  ሁኔታ ያለንበት  4
የህወሐት 42ኛ የልደት በአል  ሲከበር እያየን ነው ።
፠፠   የደርግን  ፋሽሽታዊ  ወታደራዊ አስተዳደርና  አዋጅ ከ 42    አመት በኃላ  ያገረሸባት አገር  ፣ ዜጎች በጅምላ እየተገደሉ እየታሰሩባት ፣ ካገር ውጭ እየተሰደዱ ጭራሹም የዲሞክራሲ ሽታ የማናይባት አገር እያየን ነው።
፠፠  የሀገራችን መሬት ገንዘብ ኩባንያዏች  እንሽራንሾች ፣ባንኮች ፣ እንድስትሪዏች ፣ በመላው ሀገሪቱ ያሉ ህንጻዏች ፡ የትራንስፖርትና  ኮንስትራክሽን ኩባንያዏች፣  የኮንስትራክሽን  ማሽነሪዎች በገዥ ፖርቲ ባለስልጣናት፣ ዘመድ አዝማድ በሞኖፖ ተወረው የተያዙባት የካቲት 11  42ኛ የሀወሐት የልደት በአል ።
፠፠ ለአምስት  ጊዜ የተደረገው  የሀገር  ፓርላማ    ምርጫ የተወዳዳሪ ተቃዋሚ ፓለቲካ ፓርቲዏች የድምጽ ካርድ ሙሉ በሙሉ የተሰረቀበት  ።  በተለይ ደግሞ  በ4ኛ እና  5ኛ  የምርጫ   ዘመን  ህወሐት ኢህአደግ  96.6% እና 100%  አሸንፈናል ያሉበት አስነዋሪ ተግባር የሰሩበት  ፣ ኃላም  ተቃዋሚ ፓርቲዏች እንዳያንሰራሩ  አፍነው በማያዝ  እንቅስቃሲያቸው  በአንድ  ለአምስት የነበረ  የስለላ ወጥመድ አሁን ደግሞ የስለላ ወጥመዱ  ወደ አንድ ለአንድ  የስለላ መዋቅር  በማፈን የሆነ እንቅስቃሴ   እንዳይደረግ
በማፈን  የምትከበር ያለች ለካቲት 11  ናት ። በተጨማሪ ከምርጫ በኃላ ቢሆንም ቡዙ የፓርቲ  መሪዏችና አባሎቻቸው እጩ ተወዳዳሪዎች የታሰሩበት አሁንም እየታሰሩ  ወይ በክስ የቁም እስሮኞች ሆነው  የሚኖሩባት 42ኛ የካቲት 11  ናት ።
፠፠ በዝች አገር ቡዙ ቡቁ  ሙሁራኖች  የተገለሉበት  ብቁ ያልሆኑ ለስሙ ደገተር ፕሮፌሰር  የሚል ስም ተለጥፎባቸው  አገሪቱ ለብልሽት  የተዳረጉባት  በአል እያከበርን ነው ።
፠፠ በሀገራችን ማንም ፓርት  ህወሐት  ኢህአደግ ጭምር በቀጥታ  ይሁን  በተዘዋሪ  በንግድና በእንድስትሪ መስራት አይችልም በሚል ህገመንግስትታዊ ድንጋጌ  በመጣስ እንደ የህወሐት እና  የበአዴን አማራር ቢሊየነር የሆነባት የካቲት በአል እንድናከብር እንገደዳለን ።
፠፠  ህወሐት   በአሁኑ ጊዜ  ታደስኩ እያለ  የውሸት ተሀድሶ  በመታጠቅ እያታለለ  ይገኛል ።  የዘንድሮ የውሼት ተሀድሶ  ግን ህዝቡ ስለነቃባቸው  የህዝብ የአስተሳሰብ አቅጣጫ ለመቀልበስ ነው እንጅ  ህወሐት በአሁኑ ጊዜ  ሊታደስ አይችልም  ።
፠፠  የዘንድሮ የህወሐት 42 አመት የልደት በአል ስናከበር  የሀገራችን ልኡላውነት እንደተደፈረ እና  እንደ ተወረድን የሚከበር ያለው በአል ነው ።
፠፠   በዚሁ 42ኛ የለካቲት  በአል ስናከብር  የተጀመሩ  ፕሮጆክቶች  በሙሱና ምክንያት ያልተጨረሱ  የተጨረሱም ጥራት  የገደላቸው  ከመሆኑም በላይ  አገልግሎት  ሳይሰጡ እየፈረሱ መሆናቸው  በተለይ ደግሞ በትግራይ ክልል  የስፓልት መንገዶች  የውሀ ግድቦች ፣ የውሀ ጉድጓድ   አገልግሎት  ሳይሰጡ ፈርሰዋል ። ወይ ደርቀዋል  ፣ ለምሳሌ  በትግራይ  ክልል ከተቆፎሩት  የውሀ ጉድጓድ  ከ90%  በላይ ደርቀዋል ። ምክንያቱም ከጅምሩ ሲቆፈር ጥናት ያልነበረው ስለሆነ  ነው ።   የኮንደምኔም ህንጻዏች ተሰርተው ሳይጨረሱ የፈረስበት ሁኔታ አለ ። በአድዋ 14 ህንጻዏች  ቁመናቸው ካለቀ በኃላ የፈረሱ  አሉ  መኖርያ   ሊሆኑ አይቹሉም ። በመቀለ ፣በአዲግራት በሌሎች ከተሞችም ጭምር ። ተሰርተው ሰው የሰፈራቸውም ባጭር ጊዜ ወዳቂዎች  ናቸው ።
፠፠ የትግራይ  ህዝብ  በ25 አመት  የህወሐት  አገዛዝ ከሰፍትኔት እና ከሌሎች እርዳታ ሰጭዎች  ጥገኝነት አልዳነም  የሰፍትኔት  አሰጣጥም  ቀዳምነት  ለታማኝ  የህወሐት አባላት ነው የሚሰጥ ፣ አባል ያልሆኑ   ታማኝ ያልሆነ  የሰፍትኔት ፣  ለአደጋ ተብሎ የሚሰጥ ሰንዴና የቅባት  ምግቦች አድላዊ አከፋፈል ነው የሚደረግ  ። ሌላ ከዚህ  ጋር ተያይዞ መታየት  ያለባቸው በአሁኑ ጊዜ እድሚያቸው ከ15   እስከ 45 ከዛ በላይ ያሉ ዜጎች  በሙሉ ለማለት ይቻላል   ወደ ስደት ተበታትነዋል  ።  እንግዲህ  42 አመት የህወሐት በአል ከለይ የተዘረዘሩት ችግሮች  ነው  ይዞልን  የመጣ።
፠፠   ህወሀት ባለፉት  42 አመታት የሀገራችን  ሉአላውነት እንዲጠበቅ ወይ እንዲከበር አላደረገም  ። እንዳውም በህዝብ፡በሰላም የሚታገሉ  ፓርቲዏች  ስለየሀገር ሉአላውነት ይከበር  ብለው ጥያቄ ሲያነሱ በጠላትነት  ይፈረጃሉ ። ህወሐት ህዝባችን ከነ እንስሳ ዘቤታቸው ታፍሰው  በኤርትራ በረሀ የባርያ አገዛዝ እየተፈጸመ  ፡ በሱዳን ፡ በሱዑዲ ህዝባችን ግፍ ሲደርሰው  የሚጣበቅለት አካል አልታየም ። በመሆኑ የዘንድሮ 42ኛ የህወሐት የልደት በአል ሲከበር ሉአሏዊነት ሀገርና ህዝባችን በተዋረደበት  ጊዜ የሚከበር  ያለ በአል  ነው ።
፠፠ ህዝባችን የ31 ኩባንያ ቢሌኖሩ  ትእምት  በሀዝብ ስም በመነገድ  የህወሐት መሪዏች ከነልጆቻቸውና ከነ ዘመድ አዝማዳቸው  ተንደላቅቀው የሚኖሩባትትግራይ ፣ በተመሳሳይ በሞቶ ሽዎች የትግራይ  አካልጉዳቶኞች ስም በነ አስመላሽ ወልደስላሴ  የመንግስት ተጠሪ ምኔስቴር ፡ በአጽብሀ አረጋዊ  የእንባስነይት  ህዝብ  አንተ አትወክለንን  ብሎ የገለለው ፣  ሁለቱ የፓረላማ አባላት  የሚመሩት ቢሌኖሩ የአካል ጉዳተኞች ማህበር  ተንደላቅቀው የሚኖሩባ ትግራ  በአንጻሩ   ህቦቻ ለሰደት ለስራ  አጥነት የተዳጉባት  ያቀፈች  ትግራይ  እያየንባት  ለካቲት 11።
፠፠ 26 አመት ሙሉ  ንጹህ  የሚጠጣ ውሀ የተነፈገባት  ትግራይ፡ የመቀሌ ከተማእንካን ጭራሹ የው ሽታ የለላት የዝነድሮዋ  42 ኛ የካቲት  ሆና አለች ።
፠፠ በዘንድሮዋ ለካቲት  42 ኛ በአል  አይኑ ያፈጠጠ ሙሱና የበላይነት  የያዘበት ፣ የውሸት ተሀድሳቸው   ሙስና እና ኪራይ ሰብሳቢነት  እናስወግዳለን ቢሉንም ሁሉም ሆዳሞች በመሆናቸው  ተሻሽተው ተሻሽመው  ለ100 ሚሊዮን የሸወዱባት ለካቲት 11
፠፠  የህወሐት መሪዏች  የትእምት ኩባንያዎች የህዝብ  ናቸው ብለው ለመሸወድና ለምዝበራቸው  ሸፋን ይሆንላቸው  ዘንድ  ትምሀርት ቤት ሰራን ፣ አሁን ደግሞ ለካቲት  11  ሽፋን በማድረግ  የተሰው ቤተሰብ ሽልማት ለመስጠት ሽርጉድ እያሉ ይገኛሉ ።  የትግራይ ህዝብ ግን ምጽዋት አይደለም የሚፈልገው ፣ እያለ ያለው  ከ31 በላይ  ኩባንያዏች በየአመቱ በአስር ቢሊዮን የሚቆጠር ብር  እየዛቃችሁ ያላችሁ አስረክቡን በራሳችን ቦርድ ዳሪክቶሮች  እንምራቸው  አለን  እያለ ነው ። የዘንድሮዋ የ42ኛ የካቲት በአል ግን  የሚዋጥላችሁ አልልሆነም ።
፠፠    42ኛ ለካቲት 11  በሀገራችን ያሉ የመንግስት ሰራተኞች ስቢክ ማህበራት አንድ ለአንድ የሰለላ ወጥመድ ሰንሰለት በመዘርጋት  ዜጎች እርስ በእርሳቸው  እንዲጠራጠሩ እና እንዲጣረሱ በማድረግ አንድነታችን እንዲላላ አድርገዋል ይህደግሞ የዘንድሮ ለካቲት ለጆችያመጣችሁን ጣጣ  ነወ።
፠፠     በዝህቺ ለካቲት 11  የትግራይ ህዝብ ከሌላ ኢትየጱያዊ ወንድሙ በክፉ አይን እንዲተያይ ፣ እዲጠራጠር ተደርገዋል  ። የማይናቅ ቁጥር ያለው ኢትዮጱያዊም  ለከፋፍለህ አገዛዛቸው  እንዲመች  ለሚሰሩት ተንኮል  ሌጋሲ በመከተል  በድሀ ወንድሙ ኢትዮጱያዊ ትግራዋይ ጥላቻ እያሳዮ ይገኛል ። ይህ ድርጊት ደግሞ  ለከፋፋዮች  አላማ ያሳካል ።
፠፠   የለካቲት 11  42ኛ የህወሐት በአል በውሼት ተሀድሶ ታጅቦ  በሀይለማርያም  ደሳለኝና አጋፋሪዎቹ  በትግራይ ህዝብ የውሼት ልማት በተቀናበረ የውሼት ቃላት ለዎሶ ሊያሰማን ተዘጋጅቶ ይገኛል ።
፠፠ በዚሁ በአል በመላው ትግራይ ያለው የተቃጠለ ቆሽጥ ተጽፎ በተሰጣቸው  እንደ ገደል ማሚቶ ይጭሁብን ይሆናል ።  የትግራይ ህዝብ ግን  ለሚደረገው  የውሼት ዲስኩር  ከመጤፍም አይመለከተውም ።
፠፠   በነገይቱ ለካቲት 11 ከጠ/ም /ሀይለማርያም ደሳለኝ ለ20 አመት  ያህል ዜጎች የዜግነት  የማይሸራረፍ  መብት እያለ  መጠለያ ቤት ሰርተው እንዳይኖሩ  ተነፍጋቸው  መሬታ እና አንጥራ ሀብታ ለኢህአደግ ባለስልጣናትና ዘር ዘራቸው  ተችራ ቆይታ  እነዚህ ሰወች ከሁለት በላይ ህንጻዏች ሰርተው በውጭ ምንዛሪ እያካረዩ  ፣ ለራሳቸው ግን በመንግስት ምርጥ ቤት እኖሩ ተንደላቅቀው  እየኖሩ  በአንጻሩ የትግራይ ህዝብ በውድ ኪራይ እየኖረ  ስለመረረው ፣
፠፠  ዘንድሮ ግን ህዝብ መሮት ለአመጽ  ሊነሳ ጥያቄ በማብዛቱ ሰግተው 70 ሜትር ከሪ  መሬት ቤት መስርያ  ለማስታገሻ መሬት ሰጥተውት  ስላሉ በመቀሌ ያካፋፈሉት የ11  000  መኖሪያ ነገ መሰረተ ዲንጋይ  ያስቀምጣሉ ። በተጨማሪ ያው ጤቱ ሀዘን ነው ልቅሶ ገና ያልታወቀ  የእንድስትሪ ዞን ይገበኙ ይሆናሉ ። በተጨማሪ  በተቀመጠለት የግዜ ገደብ ያላለቀ የአባይ ጸሀዬ የዛሬማ ሽኮር ፋብሪካ ይጎበኛሉ  በተረፈ የትጃሩ የህወሀት መሪዎች  ኩባንያዏች  ይገበኛሉ  ይባላል ::
ከአስገደ ገብረስላሴ ፣
8/6 /2009 ዓ ም ፣
ይቀጥላል !!

ታዋቂው የህግ ባለሙያ ጠበቃ ተማም አባቡልጉ ከጅረት መጽሔት ጋር ያደረጉት ቃለምልልስ



ይህ ፁሑፍ በጥር 27ቀን 2009ዓ.ም በጅረት መጽሔት የወጣ ሲኾን ምንም ለውጥ ሳይደረግለት ለማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች እንዲህ ተሰናድቷል፡፡
  • ኮማንድ ፖስቱ መጀመሪያ ህገወጥ ድርጅት ነው፡፡
  • አሁን የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ህዝቡ የሀገሪቱ ባለቤት ይሆናል፡፡
  • የኢትዮጵያ ህዝብ ፍላጎትና የህወሃት አላማ አብረው አይሄዱም
የዛሬ የመጽሔት እንግዳችን ታዋቂው የህግ ባለሙያ ጠበቃ ተማም አባቡልጉ በአቃቢ ህግነት በ1987ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በመጀመሪያ ድግሪ በህግ ተመርቀዋል፡፡ ከተመረቁበት ጀምሮ እስከ 1992ዓ.ም ድረስ በአቃቢ  ሕግ፣ በነገረ ፈጅነት፣ በህግ አማካሪነት ሠርተዋል፡፡ ከ1992ዓ.ም ጀምሮ ከ15 -16 ዓመት ያክል በዚሁ ሙያ ቆይተዋል፡፡ ከአንድ ዓመት በፊት “ህግ በመጣስ” በሚል በጥብቅና ሙያቸው እንዳይሰሩ ታግደዋል፡፡
ከእንግዳችን ጋር በዛሬው ውይይታችን በፍርድ ቤት ስለተወሰነባቸው ቀዳማይ እና ደኃራዊ እግድ፤ አሁን ስላሉበት ነባራዊ ሁኔታ፤ ስለአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲሁም አነጋጋሪ ስለሆነው ስለዶናልድ ትራንፕ መመረጥ እንዲሁም ስለተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች ከጋዜጠኛ ሀብታሙ ምናለ ጋር ሰፋ ያለ ቆይታ አድርገዋል፡፡
ጥያቄ፡-  የጥብቅና መብትህን  በፍርድ ቤት  በፊት ለአንድ ዓመት ከሰባት ወር ታግደሃል፡፡ አንባቢዎቻችንም እንዲያውቁት ምክንያቱን ብትገልጽልኝ
ጠበቃ ተማም፡- ዋናው ኬዙ ሁለት ክስ ነው፡፡ አንደኛው ክስ ባልና ሚስት መሃል ሽምግልና ተቀምጠህ ስታበቃ ‹‹ጠበቃ ሆነሃል የሚል ነው አንድ ዓመት ከሰባት ወር የተቀጣሁት ያለምንም ማስረጃ ነው፡፡ ሽምግልናው ላይ እንዳልነበርኩ አስመስክሪያለሁ ውክልናዬ ሽምግልና ላይ እስከ መገኘት ጭምር ነው የሚለው ጉዳዩን በሽምግልና መጨረስ ይላል፡፡ ከሳሼንና የከሳሼን አባትና አጎት ቃል ብቻ ሰምተው ነው የፈረዱብኝ፡፡ ሽምግልናው ላይ ብገኝ እንኳን ወንጀል አይደለም፤ የሚያስጠይቅ አይደለም፤ ውክልናዬ በሽምግልና እስከ መጨረስ፤ በሽምግልና ላይ መገኘት ይላል፡፡ ብገኝ እንኳን ጥፋት አልነበረም፡፡  የተቀጣሁት እኮ ዝቅተኛ ሆኖ አይደልም ‹‹ተማም አባቡልጉ ላለፉት 16 ዓመታት አንድም ክስ አልተከሰሰም›› ይላል፡፡  የእነ አቡበከርን፣ የእነ አብርሃ ደስታን ክስ ስይዝ ነው ክስ መምጣት የጀመረው ቀጥሎ  ሌላ ክስ መጣ በውስጡ አራት፣  አምስት ክስ አለበት::
ጥያቄ፡- የማን ጠበቃ ሆነህ ነው? ክስ የተከሰስከው ምንስ አድርገሃል ተብለህ?
ጠበቃ ተማም፡- የእነሀብታሙ አያሌው የ4ቱ ፖለቲከኞች ጠበቃ ሁኜ በሄድኩበት ጊዜ ሁሉንም ነገር አሟልቼ ሰውዬው አብርሃ ደስታን ሊጠራልኝ ሄዶ ነው ‹‹ሻይ እንጠጣ›› ብለሃል ተብዬ ነው ክሱ ላይ ምስክር ሆኖ የቀረበው ሰውዬው ብቻ ነው ሌላ የቀረበ የለም፡፡ ሰውዬው ቀረበ ‹‹ብሎሃል?›› ‹‹አዎ ብሎኛል!›› ‹‹ምንድን ነው ከአንተ የሚፈልገው ተማም?››፤ ‹‹ከእኛ ምንም ፈልጎ አያውቅም፤ ሁሉን ነገር አሟልቶ ነው የሚመጣው፤ ውሉ አለው ልጠራለት ሄጃለሁ አለ፡፡›› ጉቦ አልተደረገም፤ ካልተደረገ ደግሞ ወንጀልም አይደለም፡፡ በሎሚ መጽሔት ላይ የሰጠኹት ቃል ደግሞ በኢትዮጵያ የፀረ- ሽብር ህግና የአሜሪካ የሽብር አዋጅ ላይ ያለውን ልዩነት ነው የገለጽኩት የእኛው ተስፋፍቶ የወጣ ነው፡፡ የእኛ Bill of Attender ነው፡፡ ኢትዮጵያውያንን ከሀገራቸው ነጥሎ የሚያስቀር መሆኑን ነው የህግ ትንታኔ የሰጠሁት፤ የፀረ ሽብር አዋጁ ህጋዊ አይደለም ህገ-መንግስቱን ይቃረናል፡፡ ብያለሁ እላለሁ አሁንም መቃወሚያዬን አቅርቤያለሁ ለምን መሰለህ መቃወሚያዬን አቅርቤያለሁ በእነ አቡበከር ላይ በእነ ሀብታሙ አያሌው ላይም አቅርቤዋለሁ በሌሎቹ ላይም አቀርበዋለሁ ለምን በየትኛውም ሀገር 48 አንቀጽ ያለው የሽብር አዋጅ የለም፡፡ ሀገር ማስተዳደደሪያ አይደልም እኮ ለልዩ ሁኔታ የሚወጣ ነው የፀረ ሽብር አዋጅ እኛ ጋር ግን እየተዳደርንበት ነው ሌላው ‹‹የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ህዝቡ እንዳይሰማ አድርገኻል›› ነው፡፡ ህዝቡ እንዳይሰማ ባደርግስ  ኢቲቪ የእኛ ሀብት ነው የእኛ ሀብት ለሁሉም ግልጋሎት መዋል ሲገባው ኢህአዴግ ለብቻ ይዞ ይጠቀምበታል፡፡ በሀገራችን ወንጀል ነው ይሄ እራሱ ለሁሉም ነው የተቋቋመው ለግልህ ይዘህ ማድረግ የለብህም፡፡
ጥያቄ፡- ድጋሚ መቀጣትህን ታውቅ ነበር? 
ጠበቃ ተማም፡- ቀድሜ ያወኩት ነገር የለም:: ታህሳስ 24 ቀን 2009 ዓ.ም ነበር እገዳዬ ስላለቀ ፍቃዴን አድሱልኝ ስል ሰዎቹ የሚያደርጉትን ግራ ተጋብተው ‹‹አቶ ተማም ተጨምሮብሃል›› አሉኝ  እንግዲህ ፋይሌን መንግሥት አለ ብዬ ነው እነሱ ጋር ያስቀመጥኩት፤ ቤቴ ወስጄ አላስቀምጠውም፤ ማን ነው የጨመረብኝ መቼስ ተነገረኝ ስል ‹‹አይ ተጨምሮብሃል 6 ወር መንግሥት በከሰሰህ ክስ›› ተባልኩኝ  6 ወሬን ጨምሬ መጣሁ፡፡ ህገ- ወጥነቱ አንደኛ አልተለጠፈም፤ ሁለተኛ አልተነገረኝም፤ ሶስተኛ በህጉ መሰረት ከ6 ወር በኃላ አይወሰንም የሚል አለ፡፡  በእዚህ ጉዳይ ከእዚህኛው በፊት ነው መሃል ላይ እልባት ማግኘት የነበረበት ቀርቷል፤ ብለን ነው የነበረው እውነቱን ለመናገር ይግባኝ አላልኩበትም፣ አልልበትም፤ ለእኔ መነገር ግን ግዴታ አለበት፡፡ ‹‹ፍቃድ አድሱልኝ›› ስል ‹‹‹ተጨምሮብሃል›› የተባልኩት ከአመት በኃላ ይሄኛው ከተወሰነ በኃላ ነው የተወሰነውን እኔ አላውቅም፡፡
ጥያቄ፡- ይግባኝ ለመጠየቅ ጥረት አድርገሃል? 
ጠበቃ ተማም፡- ቢነገረኝ ነው ይግባኝ የምጠይቀው በእዛኛው ይግባኝ አልጠየኩም ለምን እጠይቃለሁ፤ በየጊዜው የምንፅፈው ውሸት አይደለም ‹‹ፍርድ ቤት ነጻና ገለልተኛ አይደለም›› ህሊና ያለው ሰው የህግ ባለሙያ አይደለም፡፡ ያለማስረጃ ክስ የማይሆነውን ጉዳይ ክስ ነው ብሎ ተቀብሎ ሊፈርድ የመጨረሻ ውሳኔ ነው የተወሰነብኝ ‹‹የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንን ህዝቡ እንዳያይ አድርጓል›› እንዴት ነው የዲስፒሊን ችግር የሚሆነው ወንጀል ከሆነ ወንጀል ይሆናል፡፡ በነገራችን ላይ ‹‹ከፖሊስ ጋር አይተባበርም›› ይላል፡፡ ከፖሊስ ጋር የመተባበር ግዴታ የለብኝም፤ ፖሊስ ደንበኞቼን እንዳይደበድባቸው ነው መከላከል ያለብኝ ይሄ ከፖሊስ ጋር አለመተባበር አይደለም ሌላው ከፖሊሱ ጋር ሻይ እንጠጣ ማለት ምንድን ነው ነውሩ ኢትዮጵያዊነት ነው::
ጥያቄ፡- በቀጣይነት ምን ልታደርግ አስበሃል? ብዙ አመት ነው የተቀጣኸው
ጠበቃ ተማም፡- ብዙ አመት ነው የተቀጣሁት እነ ኤልያስ እነ አናንያ ምን አጥፍተው ነው ምንም እኮ አላጠፉም! በመጀመሪያ እንደ እዚህ አይነት ነገሮችን ስለማውቅ እኔ እንደውም ለኢትዮጵያ ነው የምፀልየው ኢትዮጵያ ውስጥ የሚሰሩ ግፎች የመጨረሻችን የእንባ ሀገር እያደረጋት ነው ይሄን ሀገር ወደሌላ አደጋ ውስጥ አትውሰድብን ብለን ነው የምንፀልየው ሰው በግፍ የሚገደልበት ሀገር ነው ከ500 በላይ ወገኖቼ ተገለውብኛል፡፡ በአማራና በኦሮሚያ እነዚህ ሁሉ እኮ ወንድሞቻችን ናቸው በእሬቻ ሰዎች ተገለዋል ያን ያደረጉ ሰዎች አልተጠየቁም ፍትህ አላገኙም፡፡ እነዚህ ሁሉ ተፈፅመዋል እነዚህ ሁሉ ቤተሰብ አላቸው እኔ ቤተሰብ አለኝ የእኔ ቤተሰብ ይራባል እነዛ ግን ልጆቻቸውን ያጡ አሉ ስለዚህ የሁላችንም ፍትህ አንድ ላይ ይበየናል ብዬ ነው የምጠብቀው
ጥያቄ፡- ስለዚህ ወደ ቀጣይ ነገር አትሄድም? 
ጠበቃ ተማም፡- ወደየት ትሄዳለህ ሀገሩ እኮ የእኛ አይደለም! ሀገሩ የአንተ፣ መንግሥቱ የአንተ ሲሆን፣ ሥርዓቱ የአንተ ሲሆን ደረጃውን ጠብቀህ ትሄዳለህ፡፡ አሁን ያለው ውሸትና የማስመሰል ሥራ ነው፡፡ ሆን ብለህ ኢትዮጵያውያንን ለሀገር የሚያስቡ ሰዎችን ከጨዋታ ውጪ የማድረግ፤ አቅም የማሳጣት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ፍላጎትና የህወሃት አላማ አብረው አይሄዱም አሁን የህወሃት(ኢህአዴግ) ፍላጎት የኢትዮጵያንን ህዝብ ፍላጎት በመጋፋት ጭምር ነው ሊቀጥል የሚፈልገው ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በመሆን የቆሙ ሰዎች በሙሉ የእዚህ ሥርዓት ጠላት ተደርገው ነው የሚወሰዱት በማሰር፣ በመግደል ፣ ገንዘብ፣ በማሳጣት፣ በማሳደድ ሀብታሙ አያሌው ላይ የሆነው ተመልከት የተናገረው ለህዝብ ነው፡፡ በመጀመሪያ ኢህአዴግ ነበር፤ አካሄዱ ትክክል እንዳልሆነ አወቀ፤ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጎን እሰለፋለሁ ብሎ አቅጣጫውን  ቀየረ፤ ጠላት ተደርጎ ተያዘ፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ነጻ ሲወጣ አብረን ነፃ እንወጣለን፡፡ በሀገራችን ነው የምንኖረው በሀገራችን መሥራት መብት ማንም ይሰጠናል ማንም ይነፍገናል ብለን አናስብም፡፡ ሀገር ከልጆችህ፣ ከቤተሰብ በላይ ነው ይሄም ትልቅ ነገር ነው በእርግጥ ካልሰራህ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ችግር ያጋጥመሃል ግን በእዚህ አይነት ውስጥ አልፈናል፡፡ አንደኛ ጊዜው አልፏል ሁለተኛ ይሄ ሆን ተብሎ የተደረገ ስለሆነ በህግ መሄድ እራስን ማታለል ነው የሚመስለኝ
ጥያቄ፡- የአንተ የግል ጉዳይ  እዚህ ጋር እንቋጨውና ኮማንድ ፖስት ብለው አውጀዋል በሰለጠነው አለም አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ነው ይሄን እንዴት እናጣጥመው?
ጠበቃ ተማም፡- ኮማንድ ፖስቱ ማለት አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማለት አይደለም!፤ ኮማንድ ፖስቱ ማለት የእዝ አካል ማለት ነው፡፡ ኮማንድ ፖስት ተብሎ አይቋቋም፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመሬት መንቀጥቀጥ፣ የጎርፍ አደጋ፣ ሀገር ስትወረር ይታወጃል፡፡ ህዝብ መብት ሲጠይቅ ግን አይታወጅም፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ አማራና ኦሮሞ መብቴን ተነጠኩ ብለው ነው የጠየቀው፤ በእዛ ጊዜ የሚደረገው ምንድን ነው መልስ መስጠት ነው፡፡ ካልቻለ ደግሞ ሥልጣን መልቀቅ ነው እንጂ ኮማንድ ፖስቱ ማወጅ አይደለም፡፡
ጥያቄ፡- ኮማንድ ፖስቱ ሲታወጅና፤ ከታወጀ ጀምሮ እስካሁን ባለው ሁኔታ ምን ተገነዘብክ?
ጠበቃ ተማም፡- እጆቻቸውን ነው የፈቱት በነገራችን ላይ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምንም ማለት አየደለም የሽብር አዋጁ የገነዘውን የህዝቡን መብት ኮማንድ ፖስቱ የሬሳ ሳጥን ውስጥ ከቶ ነው ሚስማር የመታበት ትንሽ የቀረችዋን መብት ነው የዘጓት በየትኛው የወንጀል  መርህ  መስማትን ወንጀል የሚያደርገው ህግ የለም የሰዎች አስተሳሰብ ነው እውነቱን ለመነጋገር ህግ ነው ብለህ ማመን በህግ መቀለድ ነው፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ህግ ነው አልለውም፡፡ ህግም ከህገ- መንግሥቱም አንጻር መሄድ አለበት፤ ሰዋዊም መሆን አለበት፤ ምክንያታዊ መሆን አለበት፤ ተገቢ አስተሳሰብ (logical) ሎጂካል መሆን አለበት፡፡ መስማት ለምንድን ነው ወንጀል ሊሆን የሚችለው መናገር ወንጀል ሊሆን ይችላል፤ ስም ማጥፋት ስላለበት ነው ኮማንድ ፖስቱ ስሰማ ምንም አልመሰለኝም ‹‹የኢትዮጵያ ህዝብ ከፍርሃት ቆፈን ወጥቷል›› ወደ ፍርሃት ቆፈን ለመመለስ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ስነልቦናን በፍርሃት ለመመለስ የተጠቀሙት ቃል ነው ሌላ ምንም የለውም፡፡
ጥያቄ፡- ኮማንድ ፖስቱ ግን እንደ ህግ ባለሙያ ስታየው አስፈላጊ ነው?   
ጠበቃ ተማም፡- ኮማንድ ፖስቱ መጀመሪያ ህገወጥ ድርጅት ነው፡፡ በእርግጠኝነት ኢ-ህገ መንግሥትታዊ ነው፡፡ በህገ መንግሥት አንቀጽ 93 ላይ ኮማንድ ፖስቱ ይታወጃል አይልም!፡፡  በሰላም፣ በጦርነት ጊዜ፣ ሀገሪቷን የማስተዳደር ሥልጣን የሚንስትሮች ምክር ቤት ነው ይላል፡፡ ህገ መንግሥቱ 93 ላይ ኮማንድ ፖስቱ ይቋቋማል አይልም፡፡ ይሄ ኮማንድ ፖስቱ ኦሮሚያ ውስጥ የኦሮሚያን መንግሥት አፍርሶ ሀገሪቷን ያስተዳድር ነበር እኮ ስለዚህ በህግ አልተቋቋመም፡፡ መጀመሪያ በህግ ሳይቋቋም ስልጣን ማስተላለፍ መፈንቅለ መንግሥት ነው፡፡ የተደረገው በህገ-መንግሥት የተቋቋመ መንግሥት ላይ በእነ ብአዴን፣ ደኢህዴን፣ ኦህዴድ ላይ መፈንቅለ መንግሥት አደርጎ የህወሃት የወታደራዊና የደህንነት ክንፉ ስልጣን የያዘበት ነው፡፡ በህገ መንግሥቱ የሌለ ህገ-ወጥ አካል ነው ህጋዊ ለመሆን እኮ ENABLing Law ይባላል፡፡  በህግ መቋቋሚያ አዋጅ መኖር አለበት:: የመቋቋሚያ አዋጅ ያቋቋመው ይሄ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ነው፡፡ ስለዚህ ህገ- ወጥ ነው፡፡  የኢትዮጵያ ህገ መንግሥት አንቀጽ 9 ንዑስ 3 የሚለው ‹‹በሌላ መልኩ ስልጣን መያዝ አይቻልም››ይላል፡፡ ሀገሪቷን የሚመሩት የሚሾሙት እነሱ ናቸው ጠቅላይ ሚንስቴር ኃይለማርያም ደሳለኝ ያስጠይቃቸዋል፡፡ ለምን በህገ-መንግሥት የሌለ ቡድን ሽፋን ነው የሰጡት የኢህአዴግን ህገወጥነት የሚያሳይ ነው፡፡ ይሄን ያደረጉ ሰዎች ህገ- መንግሥን በመናድ ነው መከሰስ ያለባቸው ህገ መንግሥቱ ውስጥ የሌለ ቡድን ማቋቋም በኢትዮጵያ ህገ መንግሥት አይቻልም፡፡ አንድም ቦታ ፈልግ ኮማንድ ፖስት የሚባል የለም፡፡ በሰላም ጊዜ፣ በጦርነት፣በአደጋ ጊዜ በአስቸኳይ ጊዜ ሀገሪቱን የማስተዳደር ሥልጣን የሚንስትሮች ምክር ቤት ነው፡፡ ሚንስትሮች ምክር ቤት ተሰባስቦ እኔ ተገልብጫለሁ ከአሁን በኃላ ሌላ ቡድን ተቋቋሟል ሀገሪቱን ያሰተዳድራል ማለቱ ህገ-ወጥ ነው፡፡ ሀገሪቷ ውስጥ ሁለት መንግሥት የመኖር ሁኔታ ነው ያሳየን አንዱ ማስክ እየፈለገ ነው ዶክተሮችን፣ ፕሮፌሰሮችን መንግሥት አመጣ፡፡ ካባ ለማልበስ ነው የተሞከረው አንዱ  ከአንዱ ጋር አልተቀናጀም አሁን እነዚህ የተሾሙት ለኮማንድ ፖስቱ ነው ማለት ነው፡፡ እንደ ደርግ ወታደራዊ አገዛዝ ነው ‹‹እከሌን እከሌን አስገብተናል እንደሚባለው›› አሁንም ‹‹እከሌን እከሌን አስገብተናል›› ለምሳሌ አቶ ወርቅነህ ገበየው ‹‹የኮማንድ ፖስቱ ውጭ ጉዳይ ኃላፊ ተብሎ ነበር መሾም የነበረበት ካልሆነ ሌላ መንግሥት ነው የኾነው ሁለት መንግሥት ነው ያለው ነው የሚባለው በነገራችን ላይ ለምንም ነገር ደንታ ያላቸው አይመስለኝም፡፡ ለህገ መንግስቱም ደንታ የላቸውም፡፡
ጥያቄ፡- ኮማንድ ፖስት ሲታወጅ  የኦህዴድ፣ ብአዴን  መጠንከር  ወይም  የመብት ጥያቄን  ህወሃት ላይ ማስነሳታቸው ተከትሎ እነዚህን ለማብረድ ታስቦ ይሆናል?
ጠበቃ ተማም፡- ለእዚህ ነው እሱን መፈንቅለ መንግሥት ያደረገ ነው የምለው ‹‹ኮማንድ ፖስቱ የህወሃት ወታደራዊ ክንፍ ነው፡፡›› በእነሱ እጅ እሳት ለመያዝ የተቋቋመው ኢህአዴግ የሚለውን ካባ የለበሰው ጥምረት ውስጥ ጥያቄ ሲያቀርቡበት እንደ ለእኔ ያዙልኝ ብሎ ነበር የሰጣቸው እነ ኦሮሞን ያዙልኝ ብሎ ነበር የሰጣቸው ኃላ ህዝቡም አልቀበልም አለ እነዚህ ሰዎች የመብት ጥያቄ ማንሳት ጀመሩ እነዚህን አስወግዶ የሰጣቸውን ሀገር መልሶ የወሰደበት ነው ወታደራዊ ክንፉ ስለዚህ እንደዛ ልትል ትችላለህ እነዚህ የኦህዴድ የመብት ጥያቄ እንደ ድሮ አናገለግልም ባይነት የህዝብ ወገንተኝነት ማሳየት የፈጠረው ነው ሊባል ይችላል፡፡
ጥያቄ፡- ስለዚህ እነዚህ አጋሮቹ ወደ ህዝብ እየተቀላቀሉ ያሉበት ሁኔታ ነው ያለው ማለት እንችላለን? 
ጠበቃ ተማም፡- እንዴ አዎ! በእዚህ እኮ ነው ህዝቡ 2 ለ 0 እየመራ ነው ያለው የምንለው ህዝቡ አሁን የመብት የጥያቄውን መልሰው ደብድበውት ህዝቡ ‹‹የመብት ጥያቄውን አላደረኩም! በቃ ስህተት ነው!›› ካለ ወደ መጀመሪያው ተመልሰው የሚቀጥሉ ከሆነ ህዝቡ ተሸነፈ ማለት ነው፡፡ ህወሃት በድብቅ ያደርግ የነበረውን ፊት ለፊት አውጥቶ በወታደራዊ ማድረጉ ለህዝቡ ድል ነው ብዬ  ነው የማምነው
 ጥያቄ፡- በተቃራኒው ተቃዋሚ ፓርቲዎች ደግሞ በመፈረካከስ ላይ ይገኛሉ፤ ምንስ ይጠበቃል?   
ጠበቃ ተማም፡- በመጀመሪያ ደረጃ አንድ በመሆን ከኢህአዴግ ፊት ሊቆሙ ይገባል፡፡ ኢህአዴግን ‹‹አስቸኳይ ጊዜ አዋጅህን ሻር›› ማለት አለባቸው፡፡ ሳያማክራቸው ነው ያወጣው በሌላ ሀገር ተቃዋሚዎች ተነግሯቸው ነው የሚወጣው ፓርቲዎች በአንድነት ከህዝባቸው ጋር መቆም አለባቸው፡፡ ጥያቄዎቻቸውን በጋራ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ኢህአዴግን ማጀቢያ መሆን የለባቸውም በህግ ስለመኖራቸው በኢህአዴግ ፍላጎት አለመሆኑን ማሳየት አለባቸው፡፡
ጥያቄ፡- ፓርቲዎች ምን ማድረግ አለባቸው? 
ጠበቃ ተማም፡- በአንድ ላይ መሆን፤ ካልሆነም መፍረስ መድብለ ፓርቲ የለም ብለው የኢህአዴግን ጭንብል ማውለቅ አለባቸው፡፡ ተስማምተው መድብለ ፓርቲ እንዳቋቋሙት ሁሉ ተስማምተው ማፍረስ፤ ነጻና ገለልተኛ ፍርድ ቤት፣ምርጫ ቦርድ በሌለበት ፍትሓዊ ምርጫ የለም! ስለዚህ የኢህአዴግ ማስፈፀሚያ ላለመሆን መወሰን አለባቸው፡፡ ኢህአዴግን ለመለወጥ ማስገደድ ያስፈልጋል፡፡ ኢትዮጵያ አሁን የነጻነት መንገድ ላይ አይደለችም እንደውም በእዚህ አካሄድ ከ1000 ዓመት በኃላ እንኳን ወደ ዴሞክራሲ አንደርስም ምክንያቱም ከዴሞክራሲ ቀኝ ኃላ ዞረን በሌላአቅጣጫ እየሄድን ስላለን በእዚህ ቀጥ ብለን ብንሄድ ወደ ባሰ አምባገነንነት ነው የምንሄደው ወደ ባሰ አምባገነንነት በሂደት የምንደርስበት ነገር የለም ስለዚህ አጠቃላይ ለውጥ ነው የሚያስፈልገው
ጥያቄ፡- አዋጁ ለህዝቡም፣ ለመንግሥትም የሚሰጠው ጥቅም ምንድን ነው?   
ጠበቃ ተማም፡- ለህዝቡ እኮ አይደለም የወጣው፡፡ ህዝቡ የሚያገኘው ጉዳት ብቻ ነው ህዝቡ መብቱንም አያገኝም፡፡ ከፍርሃቱ እየነቃ ነበር ወደ ፍርሃቱ ይመለሳል! ኢህአዴግ ህዝቡን አስፈራርቶ እንደ መጀመሪያው ይቀጥላል መልሱ ካልተመለሰለት የሚኖረው እንዴት ነው እንደ ፍልስጤምና እስራኤል በመሳሪያ ኃይል አንዱ አንዱን እያስገበረ መኖር የኢትዮጵያ ህዝብ ፍልስጤማዊ ሆኖ ኢህአዴግ እስራኤላዊ ሆኖ ተገዳጁ ሆኖ ነው TPLf (Eprdf) የህዝብ ተቀባይነት እንደሌለው አረጋግጧል፡፡ በመሳሪያ ኃይል ተጠቅሞ ህዝቡን አስከብሮ መኖር የፈለገበት ሁኔታ መኖሩ ነው የሚታየው
 ጥያቄ፡- ኮማንድ ፖስቱ ከእዚህ በኃላ ምን አይነት ሄደቶች ይኖራሉ? 
ጠበቃ ተማም፡- ጨዋታው ያለው በህወሃትና በኢትዮጵያ ህዝብ መካከል ነው፡፡ በኢትዮጵያ ህዝብ በአንድ በኩል እና የህወሃት ኢህአዴግ በአንድ በኩል ነው ትግሉ እየተደረገ ያለው አሁን ስታይ ኢህአዴግ የህዝብ ሚና ወገን የሆኑትን እነ ዶ/ር መራራን እና ወጣቶችን እያሰረ ነው መጨረሻ ላይ ማን ያሸንፋል ነው ህወሃት ያሸንፋል የኢትዮጵያ ህዝብ ያሸንፋል ነው አሁን ጨዋታውን የኢትዮጵያ ህዝብ እየመራ ነው፡፡ ከእዚህ በኃላ ደግሞ እንዳየነው ህዝቡ ተሸንፎ አያውቅም ያለምንም ጥርጥር ይሄ ጨዋታ በኢትዮጵያ ህዝብ አሸናፊነት እንደሚጠናቀቅ ባለሙሉ ተስፋ ነኝ!
ጥያቄ፡- አሁን ኮማንድ ፖስቱ ምናልባት ይቀጥላልም አይቀጥልም የሚል ነገር አለ
ጠበቃ ተማም፡- ይቀጥላሉ! እንጂ ለምንድን ነው የማይቀጥሉት ህዝቡን ፀጥ ረጭ አድርገው ነው ማኖር የሚፈልጉት፤ የእንግሊዝ የጸረ ሽብር አዋጅ ሲወጣ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅነት ነው፡፡  የእኛ እስካሁን አለ 48 አንቀጽ አለው ይሄንንም ሰፋ ሰፋ አደርጎታል፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ 32 አንቀጽ አሉት ስለዚህ በ2012 የውሸት ምርጫ ድረስ ያስኬዱታል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ህዝቡን ፀጥ ማሰኘቱ ሰላም አስገኝቶለታል ብለው ስለሚያስቡ ነው፡፡
ጥያቄ፡- ታሰረው የሚወጡ ልጆች ሲወጡ ምን አይነት መንፈስ የሚኖራቸው ይመስልሃል
ጠበቃ ተማም፡- የንዴት፣ የቁጭት፣ በሀገርህ የመጠቃት፣ አቅምና ጠባቂ የማጣት፣ የመበደል ስሜት ነው የሚሰማቸው እንኳን እነሱ እኔም የቁጭት ስሜት ነው የሚሰማኝ ምክንያቱም አንድ ህዝብ የእራስህ መንግሥት በማጣት የተደራጀ ኃይል የጥቃት ሰለባ ስትሆን ቁጭት ነው የሚሰማህ ከእዚህ ውጪ ሊሆን አይችልም፡፡
ጥያቄ፡- የኮማንድ ፖስቱ ሥጋት የለብህም? 
ጠበቃ ተማም፡- ‹‹ስጋት የለብኝም!›› ኮማንድ ፖስቱ እራሱ የሥጋት ውጤት ነው ህወሃት ሰግቶ ያደረገው የመጨረሻ መወራጫው ነው፡፡ ከህዝብ ጋር ባለው ትግል ህዝብን በቁጥጥር ስር ለማዋል ነው፡፡ እንደውም ልፋታችንን ቀንሰውታል፡፡ እነዚህ ሁሉ ሲደረጉ ነው የነበሩት በኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከ1967ዓ.ም ጀምሮ አልተነሳም ኢህአዴግ ሲመጣ እሱኑኑ እኮ ነው የቀጠለው ሰው ያለአግባብ ይታሰራል፤ ከኮማንድ ፖስቱ በፊትም አይደለም እንዴ 500 ሰዎች ኦሮሚያ የተገደሉት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወቅት እንኳን በህገ-መንግሥቱ አንቀጽ 25 ላይ የእኩልነት መብት መንካት እና የጭካኔ አያያዝ ተከልክሏል፡፡ በእርግጠኝነት በኢትዮጵያ ውስጥ ከእዛ በፊት ጭካኔያዊ አያያዝ ነበር፡፡ በኃላም ቀጥሏል ስለዚህ እውነቱን ለመናገር መታሰር አይደለም መገደል አይደለም እኔ ከታሰርኩ ፣አንተ ታሰርክ ከበደ ታሰረ ምን ለውጥ አለው ይሄ እኮ የሚያሳይህ መጀመሪያ የኢትዮጵያ ህዝብ ቦክቶ ይኖር ነበር፡፡ እምቢ አለው መልሰህ ትፈራኛለህ አለው ግብግብ ላይ ነው ያሉት በቃ ህዝቡን አሳምኖ መግዛት አልቻሉም፡፡ ህዝቡን መብቱን ሊሰጡት አልቻሉም፡፡ ስለዚህ ፈርተህ ትኖራለህ ነው ያው ወታደሮቹን ሰው ላይ ማዝመት ነው በ1997ዓ.ም ዘምቷል፡፡  ስለዚህ እኔ ይሄ ሀገር የማን ነው? የሚል ጥያቄን ያወጣው እኛ ላይ የሚዘምተው ወታደር የማን ነው? ወታደር ድንበር ነው የሚጠብቀው እኛ ላይ የሚዘምት ወታደር የህዝብ ኃይል ይበልጣል የወታደር ኃይል እሱን የምናየው ነው የሚሆነው አንዱ አስተማሪያችን ታሪክ ነውና ከታሪክ እንደምናውቀው ህዝብ ተሸንፎ አያውቅም የኢትዮጵያ ህዝብ ደግሞ መርሳት የሌለብን ነገር በ1966ዓ.ም አብዮት አካባቢ ብዙዎች እንሚሉት አይደለም የኢትዮጵያ ህዝብ ፈሪ ህዝብ አይደለም ጀግና ህዝብ ነው፡፡
ጥያቄ፡- የኢትዮጵያስ ቀጣይ መጻኢ ምን ይመስላል? 
ጠበቃ ተማም፡- ብሩህ ነገር ነው የሚታየኝ ለምንድን ነው የሚሆነው የኢትጵያ ህዝብ አሁን ፊት ለፊት ወጥቷል፡፡ ህዝቡ ማንነቱን፣ አንድነቱን፣ በጋራ ካልሆነ መብቱን እንደማያገኝ አውቋል፡፡ የጫላ መብት የገብረ እግዚአብሔር መብት ሳይከበር እንደማይከበር አውቋል፡፡ የመብትና የልዩ መብት ልዩነትን አውቋል፡፡ አምባገነኖች የእኔ ነህ ብለው የሚሰጡህ መብትና አንተ በዜግነትህ የምታገኘው መብት ልዩነቱን አውቋል፡፡ ስለዚህ ሚናውን ስለለየ የኢትዮጵያ ህዝብ ሀገሪቱ የውሸት ሳይሆን የእውነት የእሱ መሆኑን አውቋል፡፡ ሉዓላዊ የሥልጣን አካል ድሮ ከነገሥታቱ ሲወድቅ ህዝቡ መውሰድ ነበረበት ደርግ ወሰደበት፤ ከደርግ ኢህአዴግ ወሰደባቸው ስለዚህ ህዝቡ የሥልጣን ባለቤት አልሆነም የሀገሪቱ እድል በእራሱ መወሰን እንዳለበት ህዝቡ ገብቶታል፡፡ አሁን የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ህዝቡ የሀገሪቱ ባለቤት ይሆናል፡፡ እና እኔ የሚታየኝ ብሩህ ተስፋ ነው ኢትዮጵያ የህግ የበላይነት የተከበረባት፤ የዜጎቿ መብት የተረጋገጠባት፤ ዴሞክራሲ የሰፈነባት፤ በኢኮኖሚ የበለፀገች፤ ህዝቦቿ ተከባብረው የሚኖሩባት ሀገር በቅርብ ቀን አንተ ትብስ፤ አንቺ ትብስ የሚባልባት ሀገር ለመሆን 11ኛው ሰዓት ላይ ነው ያለችው
ጥያቄ፡- ይሄን ማን ሊመራው ይችላል? 
ጠበቃ ተማም፡- የኢትዮጵያ ህዝብ ራሱ
ጥያቄ፡- ካለመሪ? 
ጠበቃ ተማም፡- የኢትዮጵያ ህዝብ ራሱ መሪ ያበጃል! እኔ የማምንበት አንድ ነገር አለ ኢትዮጵያ ጥሎ የማይጥላት የእራሷ አምላክ አላት እንደሚለው ዜመኛው በእርግጠኝነት የምናገረው የኢትዮጵያ ህዝብ በመውደቅ ላይ አይደለም እየመራ ነው ያለው አምባገነኖችን አስፈራርቶ ጭምብላቸውን ገላልጦ ፊት ለፊት እንዲወጡ ነው እያደረገ ያለው የኢትዮጵያ ህዝብ በድል እየመራ ነው፡፡
ጥያቄ፡- ጠ/ሚንስቴር ኃ/ ማርያም ደሳለኝ ኮማንድ ፖስት በመቋቋሙ ድል እንዳስመዘገቡ በአድናቆትም ነጮቹ እንደጨበጧቸው ነግረውናል
ጠበቃ ተማም፡- ብርታት በወታደራዊ አስተዳደር መምራት ከሆነ ወረራ ነው፡፡ የእነሱ ጳጳስ ማኪያቬሊ እራሱ ወታደርህን ደብቅ ነው የሚለው በህግ መግዛት አቅቶህ በወታደር መግዛት የትም ሀገር ጥንካሬ ሆኖ አያውቅም ፈረንጆቹ ህዝባችሁን ደፈጠጣችሁ በቁጥጥር ስር አደረጋችሁ ብለው ነው ጨበጡን ብለው ያወሩት በኢትዮጵያ አምባገነን መንግሥታት ታሪክ ውስጥ አምባገኖችም ነበሩ፡፡ እንደእዚህ አይነት አሳፋሪ ንግግር አዳምጬ አላውቅም መባልም የለበትም፡፡ አንድ ሰው ከግብፅ የመጣ ታሰሯል? በእዚህ ጉዳይ ማንም የታሰረ የለም ማነው የታሰረው? እነ ዳንኤል ሺበሺ፣ መራራ ጉዲና፣ ኦሮሞዎች ናቸው ተሰብስበው የታሰሩት፤ መንደር ሥራ ፈተው የሚውሉ ልጆች ናቸው የታሰሩት፡፡ መንግሥት ሥራ መስጠት ሲገባው ሥራም ሳይሰጥ ቆይቶ ነው ሰብስቦ እያሰረ ያለው፤ መብት የጠየቁትን አሸነፍን ፈረንጆች ጨበጡን ብለህ ታወራለህ? ያሳፍራል፡፡
ጥያቄ፡- እጃችንን ጨበጡ ያሉት ሀገራቸው ላይ በዴሞክራሲ ከፍ ብለው የሚታዩ ሀገራት ናቸው
ጠበቃ ተማም፡- ዴሞክራት ሀገራትማ እነሱን እንደ አሻንጉሊት አድርገው የሚጠቀሙባቸው ናቸው፡፡ ተመልክተህ እንደሆነ ስለውጭ ሰው ነው የሚያወራው እነ አሜሪካን ከሶማሌ ጋር ከተዋጋህላቸው ‹‹ምርጥ ነህ!›› ይሉሃል፡፡ ገንዘብ ይሰጡሃል ይደግፉሃል፡፡ እነሱም ይሄን ያውቃሉ አሁን እነትራንፕ መጥተዋል ትራንፕ የነቃ ሰው ነው፡፡ ሽብርተኞችን የሚፈጥሩት አምባገነኖች መሆኑን ተረድቷል፡፡ ከአሁን በኃላ ለሽብርተኞች ብሎ የሚሰጣቸው ገንዘብ አይኖርም፡፡ ሽብርተኞችን እየፈጠሩ ቢዝነስ እንደሚሰሩ አውቋል፡፡ ነጋዴም ስለሆነ ገንዘብ ላይሰጥ ይችላል፡፡
ጥያቄ፡- የትራንፕ  መመረጥ ኢህአዴግን ያስደስተዋል? ያስከፋዋል?
ጠበቃ ተማም፡- የትራንፕ መመረጥ እኔን አስደስቶኛል፡፡ አሜሪካኖች ካስደሰታቸው መምረጣቸው ትክክል ነው፡፡ ትራንፕ የንግድ ሰው ስለሆነ የመጣበትም መንገድ ጠንካራ ስለሆነ ሰውዬውም ትልቅ ነገሮችን የሚረዱ ናቸው ብዬ ስለማስብ ኢህአዴግን ያስከፋዋል ብዬ ነው የማስበው፡፡ በቀላሉ የሚያታልሉት አይደለም፡፡ትራንፕ ብር አይሰጣቸውም የዲፕሎማሲያዊ ድጋፍ አይሰጣቸውም እጃቸውን አይጨብጥም፡፡ በእርግጥ እናንተ ምን አይነት ‹‹ጎበዝ ናችሁ! ህዝባችሁን ስለመታቸሁ!›› አይላቸውም ብር እሰጣችኃለሁ አይላቸውም፡፡ ስለዚህ ኢህአዴግን አያስደስተውም፡፡ እኛን ግን አስደስቶናል በእዚህ አጋጣሚ ትራንፕም አምባገነኖች የአሜሪካን መሪዎችን ሞኝ አድርገው እንደሚወስዱ ማወቅ ያለበት ይመስለኛል፡፡ ለአፍሪካና ለአረብ አምባገነኖች ዲፕሎማሲያዊ ድጋፍ እንደማይሰጥና የአሜሪካንን ህዝብ ገንዘብ ለአሜሪካኖች እንደሚያውል እጁንም ከእኛ ላይ እንደሚያነሳ በነገራችን ላይ እንደ እነ አብርሃም ሊንከን የባሪያዎችን ነፃነት በማምጣት ነው፡፡ የተደነቀው አሁን ደግሞ ባርነት ያለው አፍሪካ ውስጥ ነው፡፡ ትራንፕ የአፍሪካንን ህዝብ ከባርነት በማውጣት ክህዝቡ ጋር በመቆም ካልሆነ ደግሞ አምባገነኖችን ባለመርዳት እንደ እነ አብርሃም ሊንከን አሜሪካንን እንዳቋቋሙት ጆርጅ ዋሽንግተን ታሪክ ሊሰራ ይችላል ብዬ ነው የማስበው
ጥያቄ፡- ብታገኘው ምን ትለዋለህ?
ጠበቃ ተማም፡- ባገኘው ‹‹ታሪክ ሥራ እለዋለሁ!›› በፊትህ ያለው ታሪክ በአሜሪካ ውስጥ አይደለም ያለው አሜሪካን ትልቅ የሚያደርግ አንተንም እንደ ሌሎቹ ትልልቅ ሰዎች ትልቅ የሚያደርግ የአፍሪካንን አምባገነን ባለመርዳት የአፍሪካ ህዝብን ከመደገፍ የአፍሪካን ህዝብ ከእራሱ ገዢዎች ባርነት በመውጣት ስለሆነ ‹‹ታሪክ ሥራ እለዋለሁ!›› በእርግጠኝነት ደግሞ ትራንፕም ነገሮችን የሚረዳ ስለሚሆን ያን እንደሚያደርግ እርግጠኛ ነኝ!
ጥያቄ፡- ስለኢትዮጵያስ ምን ትለዋለህ?
ጠበቃ ተማም፡- እኛ አሁን ያለንበት ሁኔታ የአሜሪካን ጥቁሮች ከ1865 በፊት የነበረውን በነበረው ጊዜ እንደነበረው አይነት እንደሆነ እነግረዋለሁ፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ በሀገሩ መሪዎች ቅኝ እየተገዛ መሆኑን እነግረዋለሁ የኢትዮጵያ ህዝብ ደግሞ ተባብሮ በውጭ ኃይል ቅኝ ያልተገዙ ሆነው አሁን ግን በዘመናዊ ቅኝ አገዛዝ  የተደራጁ ኃይሎች እየገዙት መሆኑን፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ቅኝ ገዢዎችን አዋርዶ እንደመለሰ ሁሉ እነዚህንም አዋርዶ እንደሚመልስ በእዚህ ውስጥ የአሜሪካኖች ሚና ከህዝቡ ጋር መቆም ካልሆነ ከህዝቡ ጋር የዘላለም ቂም ማትረፍ እንደሆነ አነግረዋለሁ ስለዚህ መስመርህን አስተካክል እለዋለሁ ማለት ነው፡፡
ጥያቄ፡- ማስተላለፍ የምትፈልገው መልእክት? 
ጠበቃ ተማም፡- ‹‹ዞሮ ዞሮ ግፍ መልስ አለው፤ ውጤት አለው፡፡ ነገሮች በተወጠሩ መጠን ነው ወጣሪውን የሚገፉት ስለዚህ ነገሩን እያከረሩ ያሉ አካላት ከእዚህ አቋማቸው ቢታቀቡና የኢትዮጵያን ህዝብ እንደሀገር፣ እንደህዝብ ይቅርና እንደሰው እንዲመለከቱት፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ተዋርዶ አይቀርም! ከእዚህ ውርደት ይወጣል፤ የእዛን ጊዜ ደግሞ ሒሳብ መተሳሰብ ይኖራል፤ ያ እንዳይሆን እንዳይፈጠር አቅም አለን የሚሉ አካላት ህዝቡ ላይ የሚያደርጉትን በደል ለእራሳችሁ ብላችሁ ገታ አደርጉ፤ መሸነፋችሁ አይቀርም ትሸነፋላችሁ፤ ስትሸነፉም ደግሞ ያደረጋችሁትን በህግ ትጠየቃላችሁ፤ የህግ ባለሙያዎች መቼም ጠበቃ መሆናችን አይቀርም ስለዚህ ወንጀሎቻችሁን አታብዙ ነው የምለው
ጥያቄ፡- ስለሰጠኸን ቃለ መጠይቅ ከልብ አመሰግናለሁ
ጠበቃ ተማም፡-  እኔም አመሰግናለሁ