በኣስቸኳይ ጊዜ ኣዋጅ ሰበብ ሕዝቡ ገንዘቡንና ሞባይሉን እየተዘረፈ ነው ሲል ኣንድ ፌዴራል ፖሊስ ገለጸ።ከዚህ በታች ያለው መረጃ በውስጥ መስመር የመጣ ነው። በጣም ከሚታመን የፌዴራል ፖሊስ የተገኘ ስለሆነ መረጃውን ለማካፈል ወድጃለሁ። እነሆ፦
“ወዳጄ እንዴት ከርመሃል? እኛ እንደምታውቀው ሸገርን እያመስናት እንገኛለን። ከቻልክ ይህችን መልእክት ለህብረተሰቡ እንዲደርስ አድርግልኝ። በአዱገነት በድሬዳዋ በአዳማ በባህርዳር በጎንደር በሻሸመኔ በአሰላ በአምቦ በጅማና በሌሎች ከተሞች ድንገተኛ ፍተሻዎች እንዲደረጉ መመሪያ ወርዷል። ሸገር ከእሁድ ጀምሮ ፍተሻ እየተደረገ ነው። በእነዚህ ፍተሻዎች ላይ የተሰማሩት የእኛና የደህንነት ሰዎች አስፈላጊ የተባለ ማናቸውንም እርምጃ መውሰድ እንችላለን።

እነዚህ ፍተሻዎች የሚደረጉት ጨለማን ተገን ተደርገው ነው። ለፍተሻ በተመረጡባቸው አካባቢዎች አስቀድሞ መብራት እንዲጠፋ ይደረጋል። ከላይ የወረደው መመሪያ ህገወጥ መሳሪያ እንድንፈትሽ ቢሆንም በፍተሻ ወቅት የተገኘ ገንዘብ በተለይ ዶላር ዩሮ ምናምን ሁሉ ላይ እርምጃ እየወሰደ ነው። ከእሁድ ማታ ጀምሮ በተደረገው ፍተሻ ብቻ ከተለያዩ ሰዎች በጣም ብዙ ገንዘብ የተወሰደ ቢሆንም እስካሁን ማንም ገቢ ያደረገ ሰው ግን የለም። አባሉ እርስ በርሱ ተከፋፍሏል። በተለይ ዶላር ቤት ውስጥ ይዘው የተገኙ ሰዎች ገንዘባቸውን መወረስ ብቻ ሳይሆን ለእስራትም እየተዳረጉ ናቸው። ወጣቶች ደግሞ ስልኮቻቸው ላይ በዋትሳፕና ቫይበር በኢሞ መልእክቶችን ተጻጽፈው ከተገኘ ትኩረት እንድናደርግ ተነግሮናል። መልእክቶቹ ምንም አይነት ቢሆኑ ችግር የለም። የፍቅርና የሰላምታ መልእክቶች ኮድ ሊሆኑ ይችላሉ ተብለናል። የውጭ ሀገር የስልክ ቁጥሮች በስልክ አድራሻ የመዘገቡ ካሉ ከጸረ ሰላም ሀይሎች ጋር ግንኙነት ያላቸው ሊሆኑ ስለሚችሉ ጥብቅ እርምጃ እንድንወስድ ተነግሮናል።
ስለዚህ ሰዎች የወዳጅ ዘመዶቻቸው እንኳን ቢሆን በውጭ ሀገር የሚኖር ሰው ስልክ ቁጥር በስልክ አድራሻ እንዳይዙ ለሰው ቢነገር ጥሩ ነው። ወደሌላ ቦታ ግዳጅ ሳልሄድ አልቀርም። መሄዴ ቁርጥ ከሆነ ምልክት አደርግልሃለሁ ሰላም ሁን”
No comments:
Post a Comment