Monday, October 24, 2016

ሌሊቱን የ13 የአጋዚ ወታደሮች አስከሬን ወደ አዲስ ዘመን ተወስዷል


ሌሊቱን የ13 የአጋዚ ወታደሮች አስከሬን ወደ አዲስ ዘመን ተወስዷል፤
በሊቦ ከምከም፣ በእብናትና በምስራቅ በለሳ ወረዳዎች የዐማራ ገበሬን ትጥቅ ለማስፈታት የተንቀሳቀሰው የአጋዚ ጦር በለስ አልቀናውም፤ ይልቁንም ብዙ አባላቶቹን ሕይወት አስገብሯል፡፡

ሰሞኑን በርካታ የአጋዚ ጦር አባላት መገደላቸውን የተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ሲዘግቡ የሰነበቱ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ዛሬ ሌሊቱን (ጥቅምት 13 ለ14 ሌሊት) በዐማራ ገበሬዎች የተገደሉ የተጨማሪ 13 የሠራዊቱ አባላት አስከሬን ሲጓጓዝ አድሯል፡፡ ከወያኔ ሠራዊት ጋር የነበረውን ተጋድሎ የተሳተፉ የጎበዝ አለቆች እንደሚሉት 13ቱ ተጨማሪ የወያኔ ጦር አባላት የተገደሉት በሊቦ ከምከም ወረዳ ሊቦና ማርታዲዮስ በሚባሉ ገደላማ ቀበሌዎች ነው፡፡ እንደ ጎበዝ አለቃዎቹ ከሆነ የመቶ አለቃ ማዕረግ የነበረው የኦፕሬሽኑ መሪ በከባድ ቆስሎ በአዲስ ዘመን ሆስፒታል እርዳታ ቢደረግለትም በሕይወት መቆየት አለመቻሉን ገልጸውልናል፡፡

No comments:

Post a Comment