Friday, October 7, 2016

የዐማራ መሰናዶ ትምህርት ቤቶች በተማሪ ድርቀት ተመተዋል


የዐማራ መሰናዶ ትምህርት ቤቶች በተማሪ ድርቀት ተመተዋል
በ2008 ዓ.ም. የ10ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና በመሰረቁ ምክንያት የተማሪዎች ውጤት ጋሽቧል፡፡ ይህ የውጤት ግሽበት ግን ለዐማራ ልጆች አይደለም፡፡ ትምህርት ሚንስትር ፈተናው እንደተሰረቀ እያወቀ የ12ኛን ክፍል ፈተና ብቻ ሲሰርዝ የ10ኛ ክፍልን ግን ባለበት አስኬደው፡፡
ይህ የተሰረቀ ፈተና ለዐማራ ልጆች አልደረሰም፡፡ በዚህም ምክንያት አጥንተው የተፈተኑት የዐማራ ተማሪዎች ውጤታቸው ከሌሎች ክልሎች ጋር ሲነጻጸር እጅግ የወረደ ሆነ፡፡ በዚህ ዓመት በጠቅላላው 10ኛ ክፍል ከተፈተኑ ተማሪዎች ከአገር አቀፉ ጋር ሲወዳደር 24 በመቶ በዐማራ ዝቅ ያለ ነው፡፡ ከጠቅላላ ተፈታኞች 32 በመቶ ብቻ እንዲያልፉ ተደርጓል፡፡ 
ከዚህ በፊት የነበሩ የዐማራ የተማሪዎችን ውጤት ስንመለከት ለምሳሌ በ2007 ዓ›ም. በአጠቃላይ 1664 ተማሪዎች በሁሉም የትምህርት ዓይነቶች “A” ያመጡ ሲሆን ይህ ቁጥር በ2008 ዓ.ም. ወደ 618 ዝቅ በሏል፡፡ እስካሁን ድረስ ወደ መሰናዶ የሚገቡ የዐማራ ተማሪዎች ከ74 በመቶ ወርዶ የማያውቅ ቢሆንም በዚህ ዓመት ወደ 32 በመቶ ዝቅ ብሏል፡፡ ከሌሎች ክልሎች አንጻር ሲታይም የዐማራ ተማሪዎች ውጤት ከአርብቶ አደሮችና ከፊል አርሶ አደር አካባቢዎች ሁሉ የወረደ እና ከ9ኙ ክልሎች 8ኛ ደረጃን ይዟል፡፡
የዐማራውን ሕዝብ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ለመበደል የሚሻው የወያኔ መንግሥት ደግሞ እስካሁን የመሰናዶ መግቢያ ውጤትን ክልሎች የሚወስኑት ቢሆንም በዚህ ዓመት የዐማራ ተማሪዎች ዝቅተኛ ውጤት በማምጣታቸው ምክንያት በትምህርት ሚንስቴር እንዲወስን ሆኗል፡፡ በ2007 ዓ.ም. ወደ መሰናዶ የሚገቡ ተማሪዎች መግቢያ ውጤት 2.4 የነበረ ቢሆንም በዚህ ዓመት ወደ 2.75 ከፍ ተደርጎ ተሰቅሏል፡፡
ለዚህ ሁሉ ምክንያቱ ምን እንደሆነ በዐማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የሚሠሩ ሰዎችን ስናነጋግር የፈተና አስቀድሞ መሰረቅ እና የተሰረቀው ፈተናም በአጠቃላይ በሁሉም አካባቢዎች እኩል አለመዳረሱ ነው ብለዋል፡፡ ለዚህም እንደማሳያ አድርገው ያቀረቧቸው ነጥቦች አሉ፡፡ ለምሳሌ በዚህ ዓመት ከሁሉም የዐማራ አካባቢዎች በ12ኛ ክፍል የመጨረሻውን ደረጃ ዝቅተኛ ውጤት ያዝመዘገቡት የባሕር ዳር፣ ጎንደርና ደሴ ልዩ ዞኖች ሲሆኑ በ10ኛ ክፍል ደግሞ ከፍተኛውን ውጤት ያዝመዘገቡት እነዚሁ ልዩ ዞኖች ናቸው፡፡ ይኽም የኢንተርኔት አገልግሎት ባለባቸው አካባቢዎች የ10ኛ ክፍል ፈተና በእነዚህ ቦታዎች መዳረሱን የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡ በተጨማሪም በአዲስ አበባ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች መምህራን ፈተናውን አስቀድመው ያርሙ እንደነበር በግልጽ ተናግረዋል፡፡
የትምህርት ሚንስትር ሆን ብሎ የዐማራ ወጣቶችን ከትምህርት ገበታቸው ውጭ ለማድረግ የመሰናዶ መግቢያ ውጤትን አገር አቀፍ በሆነ መልኩ ወስኗል፡፡ ይህም የዐማራ ተማሪዎችን በእጅጉ ይጎዳል የሚል አስተያየትም ተሰንዝሯል፡፡

No comments:

Post a Comment