Wednesday, May 31, 2017

በሁለተኛው የGTP እቅድም አማራን የማያሳፍረው ባቡር – አያለው መንበር



ነፍሱን አይማረውና መለስ ዜናዊ የተባለ ሰይጣን የአማራ ጥላቻውን ከተወጣበት ጉዳይ እስካሁን መልስ ያላገኘው የአባይ ግድብ ወደ ቤኒሻንጉል ጉባ መሄድና አማራን ያገለለው የባበር ግንባታ ይገኝበታል።
የአባይ ግድብን በተመለከተ የብአዴን ሰዎች እንደ ቱቦ የተሰጣቸውን ከማሳለፍ የዘለለ አሳማኝ ምክንያት ሰጥተውን አያውቁም።ባንድ ወቅት አንድ ጓደኛየ “ሬድዋን ማለት የመለስ ሶፍትዌር የተገጠመለት ሲዲን የሚያጫውት ቴፕ” ማለት ነው ያለኝ አይረሳኝም።እንደ እነ ካሳ ተ/ብርሃን፣አዲሱ ለገሰ፣በረከት ስሞን፣ወዘተ የመሰሉ ሰዎች ለረጅም አመታት ጭንቅላታቸው ላይ ያስቀመጡት የመለስ ሶፍት ዌር የአማራውን ህዝብ እንዳያዳምጡ፣ ጥያቄውን እንዲያፍኑ፣ ህዝቡ ተስፋ እንዳይኖረው፣ በጭፍን ብቻ እንዲከተላቸው ሲሰሩ ኑረው ዛሬም ሞት አልወስድልን ብሎ ይኸው ህዝባችን ደባ ይፈፅሙበታል።
ይህንን እንኳን እያወቀ በአባይ ቁጭት ያለበት አማራ ግን ከፍተኛውን ገንዘብ በማዋጣት የአባይ ግድብን እያሰራ ነው።በዚህ ግድብ ላይ ቱባ የተባሉ የብአዴን ባለስልጣናት የሰጡት መልስ ዛሬ ላይ ሁኘ ሳስበው ለአማራ የማይቆረቆሩ መሆናቸውን የማረጋግጥበት አንዱ ነው።”ውሃው የሚተኛበት ሰፊ ቦታና ግድቡን ለመያዝ የሚያስችል ጎርጅ ከዚያ የተሻለ ስላልተገኘ” የሚል መልስ ነበር የሰጡን።ይሁን መሰራቱ አይከፋም ብለን ዝም አልን።
የአማራውን ህዝብ በቀጥታ ይጠቅማል የተባለው የጣና በለስ የተቀናጀ የስርኳ ልማት ፕሮጀክት ግን አርሶ አደሩን አፈናቅሎ አንደኛው ፌዝ እንኳን ማለቅ አቅቶት ቁሟል።
ባቡሩ ደግሞ ከአራቱ የአማራ ግዛቶች ከአዲስ አበባ ውጭ አንዱን እንኳን ተጠቃሚ ሳያደርግ በወሎ አድርጎ ሲያልፍ ወልድያና ደሴን ወይም ኮምቦልቻን ሳይረግጥ ጊዜ የሰጣት መቀሌ ይገባል።
የጋይንት ሰው በኩራዝ ራት እየበላ መብራቱ ግን በጋይንት አልፎ ትግራይ እንደገባው ማለት ነው።የጋይንት ሰው ወደ መቀሌ የሚሄደው መብራት ፖል ስር ቆሞ “ምን እያደረግክ ነው? ሲባል የትግራይን ህዝብ ራት እያበላው” ብሎ ማለቱን ከዛው ከራሱ ከህዝቡ መስማቴን አስታውሳለው።
የአማራ ከተሞችን እነ ወልድያና ደሴን ሳይረግጥ መቀሌ እንዲገባ ያደረገው ሰይጣኑ መለስ ነው።
ይህም አልበቃውም።በሁለተኛው ዙር እንኳን ለትግራይ ተጨማሪ ወደ ሽሬ እንዲገነባ ዲዛይን ያስወጣውም በ2002 ዓ.ም ነበር።እንግዲህ የድንጋይ እርከን ሊያስጭንበት ነው አትሉኝም።የአማራ ጥላቻውን ለመወጣት እንጅ።
ዘረኛ መሪ ባይኖራት ኖሮ በምዕራብ በኩል (በአማራዋ ከተማ መተማ) ከሱዳን ጋርዋና የንግድ ልውውጧን እንድትዘረጋ ቅድሚያ ልተሰጠው ይገባ ነበር።በሀገሪቱ ለ50 ዓመት የወጭ ንግድን የመጀመሪያ ደረጃ ይዞ የነበረውን ቡናን በመቅደም አንደኛ ደረጃ ላይ ያለው ሰሊጥ የሚመረተው ምዕራብ አማራ ነው።የሀገሪቱን 48 በመቶውን የሰሊጥ ውጭ ገበያ አቅርቦት በማቅረብ የመጀመሪያ ደረጃ ላይ ያለው አማራ ግን ባቡር አያስፈልገውም።
ምክንያቱም ትግሬ አይደለምና። በህወሃት ስሌት “አማራ ደርግን አልታገለምና” ተጠቃሚ መሆን የለበትም።ይህ አካባቢ ከሰሊጥ በተጨማሪ በጥጥ ምርት፣በማሽላ፣በእጣንና ሙጫ፣በቀንድ ከብትም የተትረፈረፈ ምርት ባለቤት ነው።
ወደ ጎጃም ስናቀና ደግሞ ጤፍን ጨምሮ የሀገሪቱ ሰፊ የግብርና ምርት የሚመረትበት ነው።ቁሞ ቀሩ ጣና በለስ ፕሮጀክት እዚህ ነው።የአባይ ግድብ መሄጃም ይሄው ነው። (የአባይ ግድብ ከመብራት አልፎ ሌላ የኦኮኖሚ ምንጭ ለማድረፍ እንደታቀደ ልብ ይሏል)።ይህም ግን የባቡር መንገድ የለውም።አሁንም ባብሩ የመጀመሪያውን ዙር መቀሌን ተጠቃሚ አድርጎ በሁለተኛ ዙር የተያዘው የአማራንም ለመሰረዝ እና ለትግራይ ለመስጠት ደፋ ቀና እያሉ ነው።
በአንድ ወቅት “አማራን የማያሳፍረው ኢትዮጵያዊ ባቡር” በማለት ወንድይራድ አስማማው የገለፀበት መንገድ ከህሊናችን አይጠፋም።ዛሬ ብቻ ሳይሆን ባብሩ አማራን ወደፊትም አያሳፍርም።ቁርጣችሁን እወቁት።
የትግራይ ፖለቲካ ሚዛን ማስጠበቂያው የአማራው ቅኝ ገዥ ህወሃት የተባለው የትግሬዎች ቡድንም የአማራን ጥያቄ እያፈነ ህዝቡን በድህነት አረንቋ ያማቅቀዋል፣የፍትህ እጦት ውስጥ ያሰቃየዋል።

Tuesday, May 30, 2017

የህወሓት ዳኛ መሰወር አነጋጋሪ ሆኗል




BBN News | የዳኛዉ መሰወር ህወሃት በሰዉ ከተጠቀመ በሗላ አዉጥቶ እንደሚወረዉር አመላካች ነዉ ተብሏል። ቢቢኤን የዳኛዉን መሰወር አስመልክቶ ቀደም ሲል የዘገበ ቢሆንም ዛሬ በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ መረጃዎች አሉት።
የህወሓትን ፖለቲካ በዳኝነት ስም ሲያስፈጽሙ የነበሩት ግለሰብ መሰወር አነጋጋሪ ሆነ፡፡ ዳኛ ልዑል ገ/ማርያም የተባሉት እኚሁ ሰው ከስራቸው ላይ ከጠፉ ስምንት ወራት የተቆጠሩ ሲሆን፣ እስካሁን ድረስም የት እንዳሉ አይታወቅም ተብሏል፡፡ በፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ስምንተኛ ወንጀል ችሎት የሚያስችሉት እኚሁ ሰው፣ ያሉበት ቦታ ካለመታወቁም በላይ የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰጡ ይገኛሉ፡፡ የገዥው ፓርቲ ፓርላማ ‹‹ዳኛው ዕድሜአቸው 57 ዓመት በመሆኑና በጤና ምክንያት መሥራት ስላልቻሉ፣ የጡረታ መብታቸው ተከብሮ ከግንቦት 1 ቀን 2009 ጀምሮ ይሰናበቱ፡፡›› የሚል ውሳኔ ማሳለፉን መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡
ለከባድ ህክምና ኖርዌይ ናቸው የሚሉት እንዳሉ ሁሉ፣ አይ ደቡብ አፍሪካ ህክምና ላይ ናቸው የሚሉ ወገኖችም አሉ፡፡ የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ለገዥው ፓርቲ ፓርላማ ባቀረበው የውሳኔ ሐሳብ፣ በ2009 ለተከታታይ ስምንት ወራት ‹‹በሕመም ምክንያት›› በሥራ ገበታቸው ላይ መገኘት አለመቻላቸውን ገልጿል፡፡ ሆኖም ግን ጉባዔው፣ ሰውዬው የተሰወሩት በህመም ምክንያት ይሁን አይሁን እርግጠኛ አለመሆኑም ተነግሯል፡፡ ግለሰቡ ያሉበትን ቦታ ባለቤታቸው ጭምር አያውቁም መባሉ ደግሞ ጉዳዩን የበለጠ እንቆቅልሽ አድርጎታል፡፡ ይህን ተከትሎም የገዥው ፓርቲ ፓርላማ ባካሔደው ስብሰባ ዳኛው ላለፉት ስምንት ወራት በስራቸው ላይ ባለመገኘታቸው ከስራ እንዲሰናበቱ መወሰኑን መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡
አንዳንድ መረጃዎች እንደሚገልጹት ከሆነ ደግሞ፣ ዳኛው ምናልባት ከህወሓት ጋር ግጭት ውስጥ ገብተው በምስጢር ሳይገደሉ አልቀረም፡፡ የህወሓትን ትዕዛዝ በመቀበል በበርካታ ንጹኃን ዜጎች ላይ ፖለቲካዊ ፍርድ ሲያሳልፉ የነበሩት እኚሁ ሰው፣ ከዚህ ቀደም ካስቻሏቸው የፍርድ ቤት ጉዳዮች አንዱ፣ የቀድሞ ቅንጅት ፓርቲ ጉዳይ ይጠቀሳል፡፡ የ1997ቱን ምርጫ ተከትሎ በእነ ኢንጂነር ኃይሉ ሻውል መዝገብ በወቅቱ በርካታ ፖለቲከኞችን እስር ቤት መወርወራቸው አይዘነጋም፡፡ ከዚያ በኋላም የድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁንን ጨምሮ በርካታ ፖለቲካ ነክ መዝገቦችን ክህግ ውጪ በማስፈጸም፣ ህወሓትን ሲያገለግሉ ነበር፡፡

ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገንዘብ ተበድረው አልከፈሉም የተባሉ የውጭ ዜጎች በ25 ዓመት እስራት ተቀጡ





ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገንዘብ ተበድረው አልከፈሉም የተባሉ የውጭ ዜጎች በእስራት መቀጣታቸው ተገለጸ፡፡ ተከሳሾቹ ከዚህ ቀደም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 3 ነጥብ 5 ሚሊዬን የአሜሪካ ዶላር መበደራቸው የተገለጸ ሲሆን፣ ገንዘቡን ከተበደሩ በኋላም ወደ ዱባይ ማሸሻቸው ተነግሯል፡፡ ማይክል ማሰን የተባለው ተከሳሽ በትውልድ ደቡብ አፍሪካዊ በዜግነት አሜሪካዊ ሲሆን፣ አይመን አብዱል ሞትሊን የተባለው ሁለተኛው ተከሳሽ ደግሞ በትውልድ ግብጻዊው እንዲሁም በዜግነት አሜሪካዊ መሆኑን የተገኘው መረጃ አመልክቷል፡፡
ተከሳሾቹ ገንዘቡን ከባንኩ የተበደሩት በጋራ ባቋቋሙት አንድ ድርጅት ስም መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ ‹‹በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከ2003 እስከ 2005 ድረስ በኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኘው ስታር ፓይፕ በተባለ ሃገር በቀል ኩባንያ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለተለያዩ ማሽነሪዎች ማስመጫ በሚል ገንዘብ ተበድረዋል፡፡›› ይላል የዓቃቤ ህግ የክስ ዝርዝር፡፡ ክሱ አክሎም ‹‹ተከሳሾቹ የተበደሩትን 3 ነጥብ 5 ሚሊዬን የአሜሪካ ዶላር ወደ ዱባይ በማሸሽና በራሳቸው የሂሳብ አካውንት በማስገባት ሃሰተኛ ሰነድ አዘጋጅተዋል፡፡›› ያለ ሲሆን፤ ቀጥሎም የማይሰሩ ወይም የተበላሹ በርካታ ማሽኖችን ወደ ኢትዮጵያ በማስገባት ማጭበርበር መፈጸማቸው በክሱ ላይ ተጠቁሟል፡፡
ተከሳሾቹ ከባድ የማታለል ወንጀልን ጨምሮ በህገ ወጥ መንገድ የተገኘ ገንዘብን ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብና ሃሰተኛ ሰነድ በመጠቀም ወንጀሎች ክስ እንደተመሰረተባቸው ተነግሯል፡፡ ተከሳሾቹ ወንጀሉን አለመፈጸማቸውን የገለጹ ሲሆን፣ ጉዳዩን ሲከታተል የቆየው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት፣ ሚስተር አይመን አብዱል ሞትሊን የተባሉትን እና በክሱ ላይ 2ኛ ተከሳሽ ሆነው የተቀመጡትን ግለሰብ በ25 አመት ፅኑ እስራትና በ252 ሺህ ብር እንዲቀጡ ውሳኔ ማሳለፉ ተሰምቷል፡፡ አንደኛ ተከሳሽ የሆኑት ግለሰብ ደግሞ የመከላከያ ምስክር እንዲያቀርቡ ለግንቦት 25 ቀን 2009 ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን የተገኘው መረጃ አመልክቷል፡፡

በቃኝ የማታውቀው ይሉኝታ ቢሷ ትግራይ

   


በቃኝ የማታውቀው ይሉኝታ ቢሷ ትግራይ
(አያሌው መንበር)
ህወሃቶች አጀንዳ መዘዝ ሲያደርጉ መቸም የሚያክላቸው የለም።ዛሬ ደግሞ በVOA ጋዜጠኛዋ አዳነች ፍሰሃየ በኩል መቀሌን ከሁለቱ የአማራ ከተሞች (ከባህር ዳርና ደብረ ብርሃን)፣ከአዋሳ፣…ወዘተ እያወዳደሩ፣ ሁለት ትግሬዎችን ለምስክርነት በመጥራት <<እኛ እኮ ነን በድህነት ውስጥ ያለን፣የተረሳን ነን>> የሚልን አስቂኝ ዘገባ በመስራት አጀንዳ ሰጥተውናል።ይህ ጉዳይ ባለፈው ሳምንት አባይ ወልዱ የትግራይ ኪራይሰብሳቢዎች “በህዝቡ ስም አትነግዱ” በማለት ከገለፀው ጋር ተቀራራቢ ይሁን ተቃራኒ አንባቢ የሚፈርደው ሆኖ እውነታው ግን የሚከተለው ነው።
በዚህ ጉዳይ ላይ ሰፋ ያለ ነገር ለማሰስሰብ አስቤ በይደር ይዠው የነበረውን እቅድ ይህንን እንዳየው ግን ወቅቱ አሁን ነው መሰለኝ ብየ የመንግስትና የNGO መረጃዎችን ለማገላበጥ ሞከርኩ።ከዚያም አሸማቃቂ ሀገራዊ መረጃዎችን ተመለከትኩ።በእርግጥ በመረጃው መሰረት ከሆነ ለውጦችም ይታያሉ።
እንዲያው የሆነው ሆኖ እ.ኤ.አ በ1995 46 የኢትዮጵያ ህዝብ በመቶው ህዝብ ከዓለማቀፉ የድህነት መስመር በታች እንደሚኖር ይህ አሃዝ በ2004/5 እንደቀነሰ ያሳያል።ሌላ የመንግስት የGTP II አሃዝ የድህነት መጠኑ በ2014 ወደ 23 በመቶ እንደወረደ ያመላክታል።
በመጀመሪያው ጊዜ (ከ95 እስከ 2004) በዚህ ዳታ ላይ የድህነት መጠኑ በትግራይ ሰፋ ብሎ 48.5 በመቶ በአማራ ደግሞ 40 በመቶ ነበር ይላል Poverty and Inequality in Ethiopia 1995 to 2004 በሚል በአ.አ.ዩኒቨርሲቲው ጣሰው ወልደ ሀና፣ በዓለማቀፉ የምግብ ፖሊሲ የጥናት ተቋሙ John Hoddinott እና Stefan Dercon በተባሉ የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን አማካኝነት የተጠናቀረውና መነሻውን መንግስታዊ ዳታ ያደረገው መረጃ።
ይህንን መረጃ ከ1995 እስከ 2011 ስንመለከት የትግራይ የድህነት ቅነሳ አሃዝ ከ48 በመቶ ወደ 30 (የ18 በመቶ ልዩነት አሳይቴ) ሲወርድ የአማራው ግን ከ40 በመቶ ወደ 30 በመቶ (10 በመቶ ብቻ ነው) ቅናሽ ያሳየው።
ይህ እንግዲህ ባለው የሀገር ውስጥ የምጣኔ ሀብታዊ እድገት እንኳን እንደሌላው እኩል መጠቀም ያለመቻሉ አንዱና ዋናው ማሳያ ነው።በ2014 በተደረሰበት የ23 በመቶ የድህነት ቅነሳ (ከድህነት ወለል በታች የሚኖር ህዝብን) ክልላዊ ንፅፅር ለጊዜው ባለገኘውም ከዚህ የተለየ አሃዝ እንደማይኖር ግን ነባራዊ ሁኔታው ይነግረናል።
አንዳንድ ተጨማሪ ሰነዶችን ለማገላበጥ ያህል እስኪ የኢህአዴግን “የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ” ትንሽ እንቃኘው።በዚህ እቅድ ውስጥ የተለያዩ ሀገራዉፕ ዳታዎች ታጭቀዋል።ክልላዊ የአፈፃፀም ንፅፅር አለመሰራቱ ሆን ተብሎ ለትችት እንዳይጋለጥ ቢመስልም ያለው ላይ ተንተርሶ ግን አስተያየት መስጠት ይቻላል።ለአሁኑ የቁጠባና እና ኢንቨስትመምት እንዲሁም ወጭ ንግድን (Export) እንመልከት።
ቁጠባ በየትኛውም ሀገር ተርፎህ ሳይሆን አብቃቅተህ ለተሻለ ነገር ስትል የምታስቀምጠው ሀብት ነው።በዚህ መለኪያ ስናየው ኢትዮጵያውያን አብቃቅተው ብቻ ሳይሆን ተቸጋግረውም ቢሆን ይቆጥባሉ።በተለይም የቁጠባና ብድር ተቋማት እንደ አስገዳጅ ህግ እያደረጉ አርሶ አደሩን እየቀፈደዱ ያስቆጥባሉ።የቀበሌ አመራርም መገምገሚያው እንደነበር እኔ ራሴ አረጋግጫለው።የሆነው ሁኖ ቁጠባ ብዙ ክፋት የለውም።ክፋቱ ግን የቆጠብከው ለራስህና ለአካባቢህ ሳይውል ሲቀር ነው።
በኢትዮጵያ ያለው የቁጠባ መጠን እጅግ ዝቅተኛ ይባልበት ከነበረው ከ10 በመቶ በታች ቁጠባ በጥቅል የሀገር ውስጥ ምርት ያለው ድርሻ አሃዝ ተምዘግዝጎ ወደ 25 በመቶ እየተጠጋ ነው።ከዚህ ውስጥ የአማራ ክልል ትልቅ ድርሻ አለው።
ቁጠባ ብዙ ጊዜ የሚውለው ለሀገር ውስጥ ኢንቨስትመንት ነው።የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ፍሰት ደግሞ አማራን ተጠቃሚ ያላደረገ እንደሆነ አንድ ዳታ ልጨምር።
አንድ የመንግስት መረጃ እንደሚያሳየው ባለፈው ዓመት ወደ 2ሺህ የሚጠጋ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ሲሰጥ ለትግራይ 6 ሚሊዮን ህዝብ 187 ፕሮጀክት፣ ለ30 ሚሊዮን አማራ ህዝብ ግን 159 ፕሮጀክት (ለዚያውም ሊሰራ የማይችል) ነው የተሰጠው።በቀላል ሂሳብ ስሌት ስንመለከት ትግራይ 187 ሲደርሳት አማራ 159 ሳይሆን 935 ፕሮጀክቶች ሊደርሱት ይገባ ነበር።
በገቢ ደረጃም ዶ/ር አክሎግ ቢራራ በገለፁት መሰረት ከ2006 እስከ 2009 ወደ ትግራይ በኢንቨስትመምት ስም 12.6 ቢሊዮን ብር ፈሰስ ሲደረግ ወደ አማራ የሄደው 2.8 ቢሊዮን ብር ብቻ ነው።የአማራው ከትግራዩ በ4 እጥፍ ያንሳል፤ አማራው ከትግራይ ህዝብ ደግሞ በትንሹ በ6 እጥፍ ይበልጣል።
ወደ ምሳሌ ብንገባ እንኳን ባለፉው ዓመት 2008 ዓ.ም እኮ የ5 ቢሊዮን ብር ግዙፍ (በሀገር ደረጃ ምናልባት ግዙፍ ይመስለኛል) ፋብሪካ የተመረቀው፣ በዚህ ወር እኮ ነው የመጀመሪያው #ሞተር ፋብሪካ እዛው መቀሌው የተመረቀው፤በዓመት 18 ቢሊዮን ብር ገቢ ያስገኛል የሚባለው 120 ፋብሪካን በአንድ ላይ ያቅፋል የተባለው በ2.3 ቢሊዮን ብር የአግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪ ፓርክ እየተገነባ ያለው መቀሌ አይደለም እንዴ?፣90 አምራች ኢንዱስትሪዎችንና ባለሀብቶችን ያሳተፈው የትግራዩ የአምራች ኢንዱስትሪ ኤግዚቪሽን እኮ እየተካሄደ ያለውና የእናንተን ተጠቃሚነት ያሳየን ትናንት ግንቦት 19 ነው….የኬሚካል፣የጨርቃጨርቅ፣ የብረታብረት ፋብሪካዎች ትግራይ አይደሉምን? ይህ እኮ ሀቅን መካድ ነው።
የሀገር ውስጥ ኢንቨስትመንትን ስናይ ደግሞ ለአማራ የተመደበው 4.5 ቢሊዮን ብር በሲስተም ለትግራይ መሰጠቱ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው።ስለሆነም አማራ የሚቆጥበው የቁጠባ ገንዘብ ለትግራይ ኢንቨስትመንት እየዋለ ነው ማለት አይደለምን?
ሌላው ጉዳይ የገቢ ጉዳይ ነው።የኢትዮጵያ የገቢ አሰባሰብ ሁኔታን ስንመለከት እ.ኤ.አ በ2009 ከነበረበት 54 ቢሊዮን ገደማ በ2016 ወደ 170 ቢሊዮን ብር አድጓል።ከዚህ ውስጥ የአማራ ግብር ከፋይነት ድርሻ በሀገሪቱን ከፍተኛ ነው።
የክልሉ ገቢ አሰባሰብ በ2012 ዓ.ም (ከሶስት ዓመት በኋላ) የክልሉ ወደ 18 ቢሊዮን ያድጋል ይላል እቅዱ።የሚሰበሰበው ገንዘብ በቀጥታ ወደፌደራል ገቢ ሆኖ ነው የበጀት ድልድል የሚደረገው።
ይህ የታክስ ገቢ አሰባሰብ የሚያደገው እንግዲህ የህዝቡ የገቢ መጠን ሳያድግ፣ ብዙም Value add ባልተደረገበት፣ የክልሉ ህዝብም ግብርና ላይ በተንጠለጠለበት ነው።
ሰብስቦ ለራሱ እንዳይጠቀም እንኳን የሚልከው ወደ ፌደራል መንግስት ነው።ከዚያም አጠቃላይ የሀገሪቱ አቅም ታይቶ ነው የሚከፋፈለው።የሀገሪቱ ከፍተኛ በጀት ለካፒታል ፕሮጅፕክቶች ማስፈፀሚያ ሲበጀትም አማራ ተጠቃሚ አይሆንም።ምክንያቱም ባለፈው እንደጠቀስነው ለአማራ ህዝብ በሀገር አቀፍ ደረጃ ይገነባሉ ተብለው ከተያዙት ፕሮጀክቶች ከሀምሳ በላይ ሳይፈፀሙ ሲቀሩ በትግራይ ግን በየጊዜው ነው የምረቃ ሪቫን የሚቆረጠው።ስለዚህ አማራ ሁለት ጊዜ ይበደላል ማለት ነው።
የወደፊቱን የሀገሩቱን ማክሮ ኢኮኖሚ ስንመለከት ደግሞ የበለጠ ያሳስበናል።አብዛኛው አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ያለው ትግራይና አዲስ አበባ ዙሪያ ነው።የግብርናን ጉዳይም በኢኮኖሚው ውስጥ ያለውን ድርሻ እናውቀዋለን። የግብርና ውጤቶች ወጭ ንግድ ድርሻ 3.6፣ በመቶ የአምራች ኢንዱስትሪው ደግሞ 12.5 በመቶ ነው።
በ2020 በአብዛኛው አማራ የሚያመርተውና የሚተዳደርበት የግብርና ምርቶች ወጭ ንግድ ድርሻ በ6.5 በመቶ እንዲታድግ እቅድ ሲያዝ ትግራይንል አ.አ ዙሪያን ያማከለው አምራች ኢንዱስትሪ ግን ወደ 26 በመቶ እንዲያድግ አቅጣጫ ተቀምጦ እየተሰራበት ነው።ይህንን ስንመለከት ኢንዱስትሪ ወደ አማራ እንዲስፋፋና ፍትሃዊ እንዲሆን የተቀመጠ አቅጣጫ ሳይኖር ወይም 1/3ኛ የሀገሪቱ የግብርና ምርት አምራቹን ተጠቃሚ የሚያደርግ የግብርና ምርት ወጭ ንግድ እድገትን የሚያሳይ እቅድ ሳይነደፍ ለቀጣዩ ዘመንም አማራ ዛሬ ቆም ብሎ እምቢ ካላለ የበለጠ ችግር ውስጥ እየገባ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል።በደላችን በሁሉም ዘርፍ ነውና ትግላችንም ሁሉን ዓቀፍ መሆን አለበት።..
እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ
አዳነች ፍሳሀየ ትግራይ ከእነ “ባህር ዳር፣ደብረ ብርሃን፣አዋሳ፣አዲስ አበባ” ስትነፃፀር ችላ ተብላ በድህነት አረንቋ እየማቀቀች ነው የምትለን ሁለት ትግሬዎችን ለስምክርነት ጠርታ እንግዲህ አይኗን በጨው ቀብታ ነው።ትንሽ ስጋ እንደ መርፌ ትወጋ ነውና ነገሩ።
ሀገሪቱ ለሁለት ዓመታት ውስጥ ውስጥ ሆና በተከታታይ እድገት ውጥ ማለፏ እኮ ወደነጋቲቭ የገባውን የኦሮሚያና አማራ የምጣኔ ሀብት መነቃቃት ትግራይ በእጇ ስላስገባች እንጅ ሌላ ምንም ሎጅክ የለውም።ለአንድ ሀገር እድገት እንቅፋት ከሚባሉት አንዱ የሰላምና መረጋጋት አለመኖር ነው።ኦሮሚያም አማራም ባልተረጋጋ ህይወት ውስጥ ናቸው።
የሀገሪቱ እድገት ግን ቀጥሏል እያሉን ነው።ይህ ለምን ሆነ ሲባል ምንም እንኳን ተጨማሪ ጥናት ቢያስፈልግም መገመት ግን አያዳግትም። የአምራች ኢንዱስትሪው ትግራይ ላይ በመገንባቱ የአለመረጋጋቱ ሰለባ አለመሆኑ ትልቅ ድርሻ ይይዛል።የአገልግሎት ዘርፉ (ባህር ዳርና ጎንደር ብዙ ሆቴሎች ከ90 በመቶ በላይ ሰራተኛ ቀንሰዋል) ሽባ ሁኗል።4ቱም የትግራይ አየር ማረፊያዎች እና ሆቴሎች ግን ስራ ላይ ናቸው።አሁንም የአገልግሎት ዘርፉ አልቆመም።የግብርና ምርት ላይ መሰረት ያደረገው አማራው ደግሞ ገበሬው ወቅቱን ጠብቆ ባያዘምርም ቢያንስ ስራ አላቆመምና ራሱን መመገብ ችሏል።
በጥቅሉ “የሀገሪቱ” (የትግራይና የትግራይ ባለሀብቶች) እድገት ያላቆመው የምጣኔ ሀብት ክምችቱ ወደ ትግራይ መዞሩ መሆኑን ልብ ይሏል።የክልሉን የኢንዱስትሪ ዝርዝር ማውጣት የሚቻል ከሆነ እንጨምራለን።የአዲስ አበባን ካነሳንም የምጣኔ ሀብት ዘረፋው የተያዘው በጥቂት የትግራይ ተውላጅ ፊውዳሎች ነው።
ታድያ በየትኛው መስፈርት ነው ዛሬ መቀሌ በተፈጥሮ ብቻ እያደጉ ካሉት ከአዋሳ ወይም ከባህር ዳር ጋር የምትነፃፀረው?
መቀሌ ማለት እኮ ልክ ምዕራባውያኑ አልሸባብን እየደገፉ እንውጋው እንደሚባለው ሁሉን ቅልጭም አድርጋ ውጣ አላየውም አልሰማሁም እያለች ሰጭውንም ሌላውን በነገር የምትጎሽም አጋሰስ ከሆነች ሰነባብታለች።ይህች ጩኸት የመጣችው የሌላው አካባቢ ጩኸት ስለበረከተ አፍ ለማዘጋት ነው።
ለማንኛውም አዳነች ፍሳሃየ የተባለች ጋዜጠኛ የምትሄድበት መንገድ አሳፋሪነት ዛሬም ቀጥሏል፤ የህወሃት አጀንዳ ሰጭነት ወደ ውጭም ተሸጋግሮ ይኸው በመጨረሻ “ትግራይ በድህነት አረንቋ” በማለት ይሳለቁብናል።
ከድህነትም ከህወሃት ስናይፐር ጋርም ስቃዩን እያየ ያለው አማራውና ኦሮሞው ግን ዛሬም ስለሰብአዊነት ይጮሃል።የመኖር መብቴ ይከበርልኝ እያለ ይጠይቃል።ህወሃት ደግሞ እኔ እኮ አንተን አላውቅህም፤ላንተ አልታገልኩም እያለ መግደሉን ቀጥሏል።

በቦሌ ክፍለከተማ ወራ ጋኑ አካባቢ 2 ሰዎች በፌደራል ፖሊስ ተገደሉ * በርካታ ሰዎች የደረሱበት ጠፋ

በቦሌ ክፍለከተማ ወራ ጋኑ አካባቢ 2 ሰዎች በፌደራል ፖሊስ ተገደሉ * በርካታ ሰዎች የደረሱበት ጠፋ
-----------------------------------------------
(ዘ-ሐበሻ) በአዲስ አበባ ከተማ በቦሌ ክፍለ ከተማ ስር ባለው ወራ ጋኑ በተባለው አካባቢ የመንግስት ሃይሎች የአካባቢውን ነዋሪዎችን መኖሪያ ቤቶች በማፍረስ ለሃብታሞች መሬቱን እየቸበቸቡት ሲሆን ዛሬም ቤቶቹን ለማፍረስ ከሄደው ግብረሃይል ጋር የነበረው ፌደራል ፖሊስ 2 ሰዎችን መግደሉን የአካባቢው ሰዎች አስታወቁ::
ከስፍራው የሚመጡ መረጃዎች እንደጠቆሙት በዚሁ አካባቢ ሰሞኑን መሬቱን ለባለሃብቶች መሸጡን ተከትሎ ከ6 ሺህ የማያንሱ ቤቶች ህገወጥ ናቸው በሚል ፈርሰዋል::
ፌደራል ፖሊስ ባለፈው ሳምንት እንዲሁ በዚሁ አካባቢ ቤቶችን ሲያፈርስ በህዝቡ ተቃውሞ ሲደርስበት ከ10 በላይ ሰዎችን መግደሉን ዘ-ሐበሻ መዘገቧ የማይዘነጋ ሲሆን ዛሬም ድርጊቱን የተቃወሙና የት ሄደን እንኑር ያሉ ወገኖች ከመደብደባቸውም በተጨማሪ 2ቱ ሲገደሉ ከ20 በላይ ሰዎችም ታፍነው መወሰዳቸውና የት እንደደረሱ እንደማይታወቅ የአካባቢው ሰዎች ገልጸዋል::

በሳውዲ ህጋዊ የመኖሪያ ሰነድ የሌላቸው ኢትዮጵያውያን እጣ ፈንታ አልታወቀም

በሳውዲ ህጋዊ የመኖሪያ ሰነድ የሌላቸው ኢትዮጵያውያን እጣ ፈንታ አልታወቀም
ኢሳት (ግንቦት 22: 2009)
በሳውዲ አረቢያ ህጋዊ የመኖሪያ ሰነድ የሌላቸው ከ700 መቶ ሺ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን እጣ ፈንታ አለመታወቁ ተገለጸ።
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሳውዲ አረቢያ ያለፈቃድ ይኖሩ የነበሩ 40ሺ ኢትዮጵያውያን ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ ከሳውዲ አረቢያ ህጋዊ የመውጫ ቪዛ አግኝተዋል ቢልም፣ ሌሎች ከ700 ሺ በላይ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ አደጋ እንደተጋረጠባቸው ለማወቅ ተችሏል።
በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ እነዚህ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ቢመለሱ ምን ሊገጥማቸው እንደሚችል ባላወቁበት ሁኔታ ሳውዲ አረቢያን ለቀው ለመውጣት ፈቃደኛ አለመሆናቸው ተመልክቷል። ሆኖም፣ ህጋዊ ሰነድ የሌላቸው ኢትዮጵያውያን እስከ ሰኔ 21 2009 ቀን አም ከሳውዲ አ...ረቢያ የማይወጡ ከሆነ እስራትን ጨምሮ የተለያዩ አንግልቶች ሊደርስባቸው እንደሚችል የስደተኞች ድርጅትን ዋቢ በማድረግ መዘገባችን ይታወሳል። ሳውዲ አረቢያ ያስመቀመጠችው የጊዜ ግደብ ሊጠናቀቅ ወደ አንድ ወር አካባቢ ቢቀረውም፣ እስካሁን ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱ ዜጎች ቁጥር እጅግ አነስተኛ መሆኑ ተመልቷል።
በኢትዮጵያ የዘር ፖለቲካና ኢኮኖሚያዊ ጫናዎች ዜጎች አገር ለቀው በመሰደድ በአረብ አገራት በጉልበት ስራ ላይ እንዲሰማሩ እንዳደረጋቸው ባለሙያዎች ይናገራሉ።
ከዚህ በፊት በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ ዜጎቹ ላይ እንግልት፣ ግድያ እና አስገድዶ መደፈር ሲደርስባቸው የኢትዮጵያ መንግስት ምንም አይነት ዕርምጃም ሆነ ተቃውሞ ባለማቅረቡ በተደጋጋሚ ቅሬታ ሲቀርብበት ቆይቷል። ባለፈው ሳምንት በሳውዲ አረቢያ የሚኖሩ ኢሳት ያነጋገራቸው ሰዎች እንደገለጹት፣ ከመንግስት ምንም አይነት እርዳታ አግኝተው እንደማያውቁ ተናግረዋል።

Monday, May 29, 2017

የሕወሓት የደህንነት ቢሮ በኦሮሚያ ክልል የሕዝብ ንቅናቄና ግጭት ለመፍጠር እቅድ እየነደፈ ነው ።



የሕወሓት የደህንነት ቢሮ በኦሮሚያ ክልል የሕዝብ ንቅናቄና ግጭት ለመፍጠር እቅድ እየነደፈ ነው ።

Minilik Salsawi ከሕወሓት የደህንነት ሰወች የተገኘው መረጃ እንደ ሚጠቁመው የኦሕዴድ አባላት እንቅስቃሴ ያልጣመውና በኦሮሚያ ክልል ሕዝቡን የበይ ተመልካች ያደረጉት የሕወሓት ዘራፊዎች ጥቅም መነካቱ ፣ ሕወሓት በኦሮሚያ ያለውን የበላይነት እያጣ መሔዱ ፣ የኦህዴድ ሰወች ከጎሰኝነት ይልቅ የኢኮኖሚ ለውጥ ማለታቸው እንዲሁም በኢሕአዴግ ውስጥ የበላይነት ለመያዝ ኦህዴድ ማፍጠጡ ያስደነበራቸው ሕወሓቶች በኦሮሚያ ክልል የሕዝብ ንቅናቄና ግጭት ለመፍጠር እቅድ መንደፍ መጀመራቸው ታውቋል ።

በኦሮሚያና በአማራ ክልል የተሰማሩና በሕወሓት የሚደገፉ በዝባዥ የትግራይ ሰወች ስጋት ያዘለ አቤቱታ ለባለስልጣናት እያሰሙ ሲሆን የኦሕዴድ አመራሮችም በከፍተኛ ደረጃ ወደ ሕዝቡ ቢስፋፉም ሕዝቡን ዝም ለማሰኘት የተሸረበ ሴራ ነው ቢባልም አሁን አሁን ነገሮች ከሕወሓት ሐሳብና እቅድ ውጪ እየሆኑ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ ። የደሕንነት ቢሮው በኢሕአዴግ ውስጥ የተነሳውን ሽኩቻ በቁጥጥር ስር ለማዋልም እየሰራ ይገኛል ። #ምንሊክሳልሳዊ

በዓለማያ ዩንቨርሲቲ ለግንቦት 20 በዓል የተሰቀሉ ባንዲራዎች ተቃጠሉ፤



በዓለማያ ዩንቨርሲቲ ለግንቦት 20 በዓል የተሰቀሉ ባንዲራዎች ተቃጠሉ፤ Muluken Tesfaw

በዓለማያ ዩንቨርሲቲ ከግንቦት 17 ቀን ጀምሮ የግንቦት 20 በዓልን ለማክበር በሚል የአገዛዙና የክልሎች ባንዲራዎች በዩንቨርሲቲው የተለያዩ አካባቢዎች ተሰቅለው ሰንብተው ነበር፡፡ ሆኖም ግንቦት 19 ቀን 2009 ዓ.ም. በሌሊት አብዛኛዎቹ ባንዲራዎች ተለቃቅመው ሌሊቱን ተቃጥለው አድረዋል፡፡


በዚህ ምክንያት በዩንቨርሲቲው አመራሮች፣ የጥበቃ ሠራተኞችና በአገዛዙ የደኅንነት ሰዎች መካከል ከፍተኛ ውጥረት ተፈጥሯል ተብሏል፡፡ የግንቦት 20 በዓል በዚሁ ምክንያት ዩንቨርሲቲው ሠራተኞችና ተማሪዎች ከማክበር መገላገላቸውን ገልጸዋል፡፡ የዩንቨርሲቲው ተረኛ ጥበቃዎች ከዚሁ ጋር በተያያዘ ታስረዋል፡፡

Sunday, May 28, 2017

አሁንስ ሊመጣ ላለው ዝግጁ ነን?።


    




ለለውጥ እንደቆመ ወይ ምኞተኛ በመሆን ሳይሆን እራሱን ካገዛዙ በኩል አድርጎም ይህን ቢያደርጉ ያ፤ ይህ ቢሆን ደግሞ ያ እያሉ መጣዊውን ያገራችንን ሁኔታና የገዥዎቻችንን መጣዊ እጣ ፋንታ በሁሉም አቅጣጫ ለማየት ቢሞከርም የዚህ ስርአት እድሜ አጭር መሆኑ ግልፅ ብሎ የሚታይ እየሆነ ነው። በፊትም ህዝብ ተቆጥቶ አደባባዬች ላይ መውጫው ጊዜ ላይ መደረሱን ቀድመው ያዩም ሲወተውቱም የነበሩ ነበሩ።
እንደሚገሉ፤ እንደሚያስሩን፤ ከኛም አልፎ ቤተሰባችን ላይ ሊደርስ የሚችለውን መቼ አጣናው። መገዛትንና ተቆራፍዶ መኖርን ምርጫ አድርገን ልንወስደው  አንችልም። ምንም አይነት መሰዋትነት ቢያስከፍለን ልንታገለው ወስነናል።  በሚሉ የወጣቶች ድምፅ ሞገድ ሲሞላ ማየት ለቻለ ሊመጣ ያለውን ህዝባዊ ቁጣ አይቀሬነት አመላካች ነበር።  ጥረቱ  የምር ተደርጎ አልተወሰደም እንጂ ቄሮዎች አውራ የሆኑ ድርጅቶችን ቀርበው “እኛ ልናፈነዳው ዝግጁታችንን ጨርሰናል። ተባብረን ብናደርገው የተሻለ ነው በሚል  ህዝባዊ እንቢታው ከመነሳቱ ከአመታት በፊት  ሞክረዋል”።
አሁንም ጨፍጫፊ አንባገነኖችና፤ ዘራፊዎች ስልጣን ላይ አሉ። ዘጠና ሚሊዬን በጭራሽ ደስተኛ ያልሆነና ተበዳይ ህዝብ ደግሞ በሌላ ጎን አፍጦ አለ። የሰባዊ መብት፤ የፍትህ፤ የጤና፤ የምግብ፤ የመጠጥ ውሀ፤ የትራንሰፖርት፤ የስራ አጥነት፤ የኑሮ ውድነት፤….. የቀውሱ ብዘት ተዘርዝሮ አያልቅም። መሀል ዋና ከተማው አዲስ አበባ ውስጥ ታይፎይድና ታይፈስ አንዴ ያልታመመ ሰው ፈልጎ ማግኘት አይቻልም። ምን አለባት በለስልጣናቱን ጨምሮ። ተስቦዎች ከመራቆትና ከረሀብ ገር ቀጥተኛ ቁርኝት አላቸው። የቆሼው እልቂት አይነት አንድ ጠዋት ስንነሳ በሺዎች ባልታወቀ ተላላፊ በሽታ  አለቁ የሚል ዜና ቢሰማ  በአገራችን ሁኔታ  የማይጠበቅ አይደለም።  ዜጋውን ካገሩ ማሳደዱን በርትተውበታል።   የአፍሪካ አገሮች አስር ቤቶች በወገኖቻችን ተጣበዋል። በአረብ አገራት በሴት እቶቻችን ላይ እየደረሰ ያለው መከራውም ጎዞውም ቀጥሏል። በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ ከባድ ችጋር እንደ አምናውና  እንደካቻምናው ዘንድሮንም ተሻግሮ ለከርሞው የማያልፈን መሆኑን ሊደብቁት የሚቻላቸው አልሆነም። ዜጋው ይህንን ሁሉ ያውቃል። መንግሰት ዶላር እንደቸገረው፤ የአገዛዙን መዳከምና መከፋፈልም እየሰማ ነው። በህዋዋት ውስጥ ያለው መከፋፈል ብቻ ሳይሆን አጋር ከሚሏቸው ድርጅቶች ጋር ያለው ግንኙነት ወደተሻለ አይደለም ወደነበረበት መመለሱ እራሱ በሰማያዊ ታምር ካልሆነ ከዚህ በሗላ የሚቻል አይደለም።
ውጪዎቹም ለኛ በመጨነቅም ብቻ ባይሆን በጣም ብዙ ህዝብ ስለሆንን የኢትዬጵያ ሁኔታ በጊዜ መላ ካልተባለበት ቀውሱም ሆነ ጦሱ ትልቅ፤ መመለሻውም አስቸጋሪ እንደሆነ ያውቃሉ። በዚህ ምክንያት እየበረታ የመጣባቸውን ውጫዊ ጫናም  እየሰማ ነው። ይህ እየጨመረም ሂያጅ ነው። በተጨማሪም አገዛዙን አጣብቂኝ ውስጥ የሚከቱ አካባባያዊና አለምአቀፋያዊ  የሁኔታዎችን መቀያየርንም ይሰማል።
አገዛዙ ላፉም ቢሆን ዲሞክርያሲያዊ፤ ሰብአዊ፤ ባለ ነፃ ሜዲያ የመሆኑን ነገር ከተወው  ቆይቷል። ለገበሬው፤ ለብሔር ብሔረሰቦች፤ ክልል፤ ኢህአዲግ እራሱ ህዘብ እያየው ታሪክ  እየሆነ ነው። “ወደመጣችሁበት” ትንቢት ሆነ መሰል ህዋዋቶች ብቻቸውን ቆመዋል። ይሄም  ሂደት እየጨመረ ሄያጅ ነው። ስለተናጋና ተጓታች ስለሆነ ለይስሙላም ቢሆን የነበሩ ነገር ግን የማይኖሩና የማይደረጉ ተመሳሳይነት ያላቸው ነገሮች እየጨመሩ  መሄዳችው አይቀርም። ይህን ሁሉ ደማምሮ ሲያይየ የሚደርስበት ድምዳሜ ያገዛዙን ፍፃሜና ለነፃነቱ የተፈጠረውን ምልካም አጋጣሚም ነው።
ወታደር ከካንብ ወጥቶ ከህዝብ ጋር መኖር ጀምሯል። በህገመንግሰት ሳይሆን ባስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እየተሞከረ ነው። በየቤቱ የገባውን የሟቾቹን የታሳሪዎችን ብዛት፤ ለተናጋሪው የከበደውን ግፍና ነውር፤ ህዘብን ህዝብ ላይ ማስነሳትና የጅ አዙር ፍጅት ሁሉ ተስፋ መቁረጥና ለመግዛት አቅም ማጣት ያመጣው መሆኑን ህዘብ አያጣውም። እንደህዝብ ለመንግሰት ተሀድሶ የሚባል ነገር የለም፡፤ እርጅና ነው። ሞት ነው። እንግዲህ ጥልቅን ሳይጨምር ቢያየውም ማለት ነው። ከተቃዋሚዎች ጋር የተባለውን ህዝብ ጉዳይ የሰጠው አልሆነም። የጠረቤዛውን መፍትሄ ከመጥላት አይደለም። ወይ ሊሆን የሚችልበት የሰናፍጭ ቅንጣት ታህል እድል ኖሮ አልታየው ብሎም አይደለም። ህዝብም ሆነ ህዋዋቶችም እራሳቸው ተቀናቃኞችም ቢሆን በዚህም ሆነ አስገዳጅ  በሆነው መንገድ መጨረሻው ለባለስልጣናቱ ተመሳሳይ መሆኑን አሳምረው ስለሚያውቁ ነው። ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ ጫወታ ብቻ ነው።
“አገዛዙን ያስጠላነው እኛ ነን። ማስታረቅም እንችላለን”። ያው አመል የሆነ አጉል ህዝብ ላይ መታበይ ነው። ይህን የሚሉት በታምር ሆነ እንበልና “አገዛዙ ስልጣኑን በሰላም ሊሰጣቸው  ቢሆን እንኳ” ይህን እንደመፍትሄ ህዝብ እንዲገዛው የማድረግ ተቀባይነቱ የላቸውም። ይህንን እነሱም አያጡትም። በተረፈ ተቃዋሚዎች ካገዛዙ ጋር ለጠረቤዛ ዙሪያ መፍትሄ መቀመጣቸው ለነሱ አጉል ልፋትና የባከነ ጊዜ ከመሆኑ ውጪ ህዝብን ከትግሉ ከማዘናጋት አኳያ የሚቀርበው ምክንያት ብዙም አያሳምንም። በመሳተፋቸው የሚያስገኙትም። ቢያገኙም የሚጠቅማቸው። ይህም ሆኖ ደግሞ የሚያጡት  ታላቅ የሆነ ነገር ያለበት ጉዳይ አይደለም። ሰላማዊው መፍትሄ እዚህ ደረጃ ለመደረሱ የዝሆኑን ድርሻ አሁንም ገዥዎቻችን ናቸው የሚወስዱት። ዋናው አሳሳቢ የሆነው ይህንን የሚያህል አገራዊ ቁምነገር በይበልጥ አገር ውስጥ ለለውጥ የቆሙ ክፍሎች እንደ ሁለተኛ አማራጭ እንኳ አገዛዙን ባላካተተ ሊዘጋጁበት አይደለም መታሰቡ እራሱ ትክክል አይደለም የሚል ክርክር ላይ መሆናቸው ነው።  ይህ አላስፈላጊ የስልጣን ፍክክርን ማስከተሉ ስለማይቀር መንገራገጭ ውስጥ ሊከተን  የሚችልበት እድል  አለው። የመከራው ዘመን መቋጨት ሲቻልም እያረዘመው ነው።
በዋናነት ህዘብ ካገዛዙ ጋር ተፈታትኗል።  ህዝብ  ሀያል መሆኑ ሁሌም ቢሆን  የታወቀ ነው። ሕዝባዊ ሀይሉ  ይገለፅ ዘንድ ምክንያት አለው ወይ?። ጉልበተኛነት ይሰማዋል ወይ? ምሬቱ ምን ደረጃ ደረሷል። ስለሚወስደው እርምጃ እውቀቱ አለው ወይ?  አጋጣሚዎች ተመቻችተዋል ወይ? በመሳሰሉት የሚወሰን ነው የሚሆነው። ጠቅላላ ያገራችን ነባራዊ ሁኔታ የህዘብ ሃያልነት እንደገና ለመገለጥ የተደላደለ ሁኔታ መኖሩን  ነው የሚያሳየው። ሀይሉን በምን መንገድ ፍልሚያው ላይ እንደሚያውለው በቂ እውቀትና ተሞክሮ ያዳበረገበት ሁናቴም ነው ያለው። በሚሊዮኖች ድርሻ በሚያደርጉበት ከተማን ጭር ማድረግ፤ሲያሻው አደባባዬችን መሙላት አልያም መገበያየትን ማቆምና መንገዶችን መዝጋት እንደሚችል ያውቃል። ይህ እያደገና እየሰፋ አገራዊ መልክ እየያዘ መሄዱ አይቀርም። እርቆ ሄዶ ዜጋው በመሳርያ እራሱን ወደመከላከል የዞረበት ሁኔታም ነው ያለው። ተፅኖ ፈጣሪና ወሳኝነት ያላቸው ጠንካራ የተቃውሞ ድምች ከማይጠበቁ  አካባቢዎች መምጣትታቸውና  እየበዛ መሄዱ ሌላው መጣዊው ሁኔታ ላይ አስረጅ ተደርጎ ሊወሰድ የሚችል ነው።
ጠቅለል ባለ ሁኔታ የአገራችን ሁኔታ ይህን ከመሰለና ጉዞው ወዴት እንደሆነ በከፊል እንኳ ለተስማማ በቀጣይ ሊመጣ ያለውን ለማየት አይቸገርም። መልስ የሚያሻው ታላቅ አገራዊ ቁምነገር አሁንስ ለለውጥ ዝግጁዎች ነን ወይ?። የሚለው ነው። በእርግጥ ለለውጥ ቆመናል ላልን  ክፍሎች ብዙ መልስ የሚሹ ተያያዝ ጥያቄዎች ተድርድረው እየጠበቁ ነው። የተባበረ አቅምን ስለመፍጠር፤ ሽግግር፤ ጉዟችንን፤ ታምቀው ታምቀው የቆዩ የተለያዩ የመሀበረሰብ ክፍሎች የነሷቸው ጥያቄዎች ሊካድና የተለመደ ሰበብ ሊሰራለት በማይቻል አደባባይ ላይ ፈንድቷል። ጥያቄዎቹ አገዛዙ እንዲመልሳቸው ታስበው አይደለም መራር መሰዋንት እየተከፈለባቸው ያለው። ግልፅ መሆን ያለበት አበባየሆሽ መጨፈርያ እንጂ  አገራዊ መፍትሄ አይሆንም። ይሄ ያው የተለመደ ጎታታነት ነው። እነዚህ ሁሉ በሚመለከታቸው በጋራ ተሰርተው ቢያንስ ሁሉ ማለፊያ ነው ሊሉው የሚችለው መፍትሄን ይሻል። እነዚህን የቤት ስራዎቻች እየሰራን ነው ወይ?። እየተሰራበት ነው ከተባለ ስራው  ከነበርንበት ምን ያህል ፈቅ ብሏል?። ሌላው ቢቀር ዜጋው ለመብቱ እያደረገ ባለው ተጋድሎ አጋዥ መሆን ባይቻል  አሁን እንኳ አፍራሽና አዳካሚ ከሆነ ሚና ውስጥ መገባት የለበትማ።
ለውጥን አምርሮ ፈልጎ -ለውጥን ምርር ባለ ሁናቴ ፈርቶ ደግሞ አይሆንም። አንዱን መምረጥ የግድ ነው። ዛሬ በገፍ  እየተቀሉም ዜጎች አደባባይ ወጥተው መብታቸውን መጠየቃቸው እንጂ ዛሬ የተፈጠረ አገራዊ ችግር አንድም የለም። አዲስ የሆነ የህዘብ ጥያቄም የለም። መብታቸው ሊሆን ይችላል የሚሰኝ አንድም ጥያቄም የለበትም። እንደውም ከመብትም በላይ ነው። ይህን የሚሉት ስለህልውና ሲያወሩ የዜጋውን ህልውና ከአገር ህልውና እንዴት ለይተውት እንደሆነ  በጭራሽ አይገባም። እነንትናን ሊያስደነግጥ ይችላልና መሬታቸውን እየተቀሙ ለማኝ ሲደረጉ ዝም ይበሉ?። ያላባራ ፍጅት ሲፈፀምባቸው ወይ አንድ ህዘብ ቋንቋው የእስርቤት ቋንቋ እስኪሆን ሲጋዝ ሳይታገሉ ይለቁ ነው ወይ?።
መፍትሄ ፍለጋው ላይ ድንኳን አልበቃ ብሎ የሀዘን ቀን ከሶስት ወደ አንድ ቀን እስኪቀየር ኤድስ ህዘብን ሲያረግፈው አንድና አንድ መፍትሄ “አንድ ወንድ ካንድ ሴት መታቀብ” መሆኑን ሲወተውቱ የነበሩ ነበሩ። የዚህ አይነት መፍትሄ ያምራል። በአድማጭ በቀላሉ ተቀባይነትም አለው።  ሊተገበር የሚችል እንደውም በእርግጥ መፍትሄ ነው ውይ ቢባል በጭራሽ።  ኢትዮጵያ ትቅደም- ኢትዬጵያን ያስቀደመ ነው፤ አስቀድማላው….. ጎራና ግርግዳ መስራት መፍትሄ አይሆንም። ሲጀመር በጭራሽ አዲስ አይደለም። ወደሗላም ቢኬድ የነበሩን አገዛዞች በሙሉ  ይሄው ነው ምክንያታቸው። ሁሉም የለየላቸው ጨካኞችና ጨፍጫፊ አንባገነኖች ግን ነበሩ። የአለም መጨረሻ ሗላ ቀርና ደሀ የሆነው እንደ አንድ አገር ህዘብ ምንም አንሶን ወይ ተረግመን አይደለም። መፍትሄው የማይሰራ ወይ እኩይ ለሆነ አላማ ሲገፋ ስለነበር ነው። ታዲያ ዛሬ እንኳ መፍትሄ ፍለጋው ላይ  ሰው ቅድሚያ የማይደረገው ለምንድን ነው?።

...
እንደ አንድ የመሀበረሰብ አካል መቶ የማይሞላ ጋዜጠኛ ወይ አስተማሪ ጥያቄ የመጠየቅ መብት አለው። የአንድ አገር ዜጎች እንደ ጋንባላ ወይ እንደ አፋር ግን ጥያቄ መጠየቅ፤ የተለየ ፍላጎት ሊኖራቸው አይችልም። የኦሮሞ ህዝብ የመብት ጥያቄ አንስቷል። ስለዚህ አርማጌዲዬን ሊሆን ነው።  ከዚህ አይነቱ እሳቦት መውጣት አለብን።  አገር የጭቃ ቤት አይደለም። ዜጎች መብታቸውን ስለጠየቁ የሚፈርስ። ህዘብን ማሸማቀቁና ማሰጠኑም ለከት አጥቷል። ልጓም ሊበጅለት ይገባል። ጥቂት፤ ኦነጎች፤ ዘረኞች፤ ጎጠኞች፤ ጠባቦች፤ ግንጣዬች… አሁን ደግሞ በአሜሪካ ተቀምጠው ይህ ሁሉ  እራስን መሸንገያና ሌላውን ህዝብ ማወናበጃ  ብቻ ነው። ህዘብ ለመብቱ የታገለው ፍፁም ጨዋነት ባለበት በሆነበት ነው ይህ ሁሉ ውርጂብኝ። አገዛዙ ፍጅት ከሚፈፅምበት አመክንዬ ጋር በሚያሳዝን ሁናቴ ብዙው ውርጂብኝ ተመሳሳይነት አለው።
በአሉ ግርማ ይህን አይነቱ ሁኔታ በፈጠረበት ስሜት ይመስለኛል
“ እስቲ ላንጎራጉር – ከአድማስ ባሻገር፤ ያለ ሰው ቢወዱት ምን ያደርጋል አገር”። ያለው።  በምንመ ምክንያት ይፃፈው ሰሞኑን የሚሰማኝን ስሜተ በትክክል ገልፆልኛል። ልጨምር ብል የምጨምረው  “ፍቅሩና መተባበሩ ቀርቶ- መጨካከኑ ቢቀር ምን አለ”። የሚለውን ብቻ ነው
ሊሰራበረት የሚገባው ፖለቲካው ግን ብቻ አይደለም። ትግሉም ነው። ብዙ ድክመቶች ብዙ ያልተሟሉ እንከኖች  አሉት። የመታገያ እቅዱ በወረቀት ላይ መቀመጥ አለበት። የለውጥ ሀይልን ስለማደራጀት፤ የገንዘብ አቅምን ስለመገንባት፤ መረጃ አሰባሰብ፤ አያያዝና አጠቃቀማችን። መሳርያ በጁ ያለወን ጨምሮ ከዚህ የበሰበሰ ስርአት ጋር የተነካኩ ዙጎቻችንን በለውጡ ሊኖራቸው ስለሚገባ ድርሻ ። አገር ውስጥ ያለው ነባራዊ ሁኔታ የተመቸ አይደለም እነዚህን ስራዎች ወደወጪ አውጥቶ  መስራት ስለሚቻልበት ሁኔታ። በዋናነት የስርአቱን ፍፃሜ ለማድረግ ኢኮኖሚውን ወይስ መሳርያ በጁ ያለውን?። የምርጫ ካርድ ቀዳዶ መጣል ወይስ የተገኘችውን ቀዳዳ ሁሉ ትግሉን ሊያግዝ በሚችል መንገድ መጠቀም?፤ የረጅም ጊዜ የሚቀጥል ህዝባዊ እንቢተኛነት ወይስ በጣም ፈጣን የሆነ በሳምንት ውስጥ ማጠናቀቅ በሚያስችል ደረጃ ማቀድና መዘጋጀት? …… ብዙ ብዙ።
ብሔራዊ ጭቆና ይብቃ!።

የሲያትል ስብሰባ፣ ፕሮፌሰር መስፍን ወለደማሪያም እና ግንቦት 7 (ቬሮኒካ መላኩ)

May 28, 2017 17:48      




ማኔ ቴቄል ፋሬስ (በሚዛን ተመዘንህ፥ ቀልለህም ተገኘህ !) ትን. ዳንኤል ፭፡፳፭
የዛሬው ፅሁፌ የሚያጠነጥነው ሰሞኑን አሜሪካ ሲያትል ተደርጎ የነበረውን የተለያዩ “ድርጅቶችና “ግለሰቦች የተሳተፉበትን ስብሰባ ተከትሎ በሁለት ጉዳዮች ላይ ይሆናል ።
አንድ በፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማሪያም ዙሪያ ሲሆን ሁለተኛው ደሞ አርበኞች ግንቦት 7 በተባለው ድርጅት ላይ ይሆናል።
ከላይ እንደጠቀስኩት የዚህ ፅሁፍ ቆስቋሽ በሲያትል በውስጠ ታዋቂነት በግንቦት7 ዋና አስተባባሪነት የተጣመሩ ድርጅቶች ያዘጋጁት ስብሰባ ነው።
ለሳምንታት ይሄ ስብሰባ ከመደረጉ በፊት በማህበራዊ ድረገፅ የተለጠፈው ማስታወቂያ ላይ የተሳታፊ ተጋባዥ እንግዶችን ስብጥር ስመለከት ቀድሞውንም ጥርጣሬ ነበረኝ። ይሄው እንደጠረጠርኩት አማራ ባልተጋበዘበትና ባልተሳተፈበት ስብሰባ ሲብጠለጠል ዋለ።
“ጨቋኟ አማራ ጠላታችን ነው!” ብሎ ደደቢት የገባው አረጋዊ በርሄ፣ “አማራ የሚባል ህዝብ የለም” ያለው ፕሮፌሰር መስፍን፣ የአርባጉጉና የበደኖ አርበኞች የተሳተፉበትና አማራ ያልተወከለበት ስብሰባ ከመሆኑ አንፃር የጉባኤውን ውጤት ቀድሞ መተንበይ የሚያስቸግር አልነበረም።
ፕሮፌሰር መስፍን ረጅም የህይወት ዘመናቸውን አወዛጋቢ ሆነው እንደኖሩ ብዙዎች ይስማማሉ። ቀኑ እየገፋ እየተዋገደ እና እየመሸ ሲመጣ “ኑዛዜ” ያደርጋሉ ብለን ስንጠብቅ አሁንም አወዛጋቢነታቸው ቀጥሏል።
እዚህ ላይ አንባቢ እንድገነዘብልኝ የምፈልገው ለአንድ ክፍለ ዘመን ትንሽ የቀረው አመታት የኖሩትን አረጋዊ “ለመዘርጠጥ” አስቤ የፃፍኩት እንዳይመስልብኝ ነው። ፕሮፌሰሩ አማኝ እንደሆኑ አውቃለሁኝ። ዶሮ ሳይጮህ ሶስት ጊዜ “የለም” ብለው የካዱትን ህዝብ ተፀፅተው ጥፋታቸውን በንስሃ ያጥባሉ ብዬ ስጠብቅ ጭራሽ ሌላ አጀንዳ ይዘው ብቅ አሉ።
በሌላ በኩል ኑዛዜ ማለቴ ምሁሩን ለመክሰስ ሳይሆን በአንድ ወቅት “ጠመንጃው ያለው በእጃችሁ ሆኖ ጊዜውም ሁኔታውም እየፈቀደላችሁ የኛን የብእር ብትር እንደት ትጠብቃላችሁ? መርማሪ ኮሚሽን ምናምን እያላችሁ ስታመነቱ በስፔን አቢዮት እንደደረሰው ጎርፉ እኛንም እናንተንም ጠራርጎ እንዳይወስድ አፈራለሁ።”
የሚል ወኔ ቀስቃሽ ንግግር ለደርግ አድርገዋል የሚል ክስ ከብዙ ሰዎች ስለተነሳባቸው እንደው ይሄን ጉዳይ በደንብ ቢያብራሩት ለማለት ነው።
ይሄ ነገር መንግስቱ ሃይለማሪያምም ተናገረው። ጠቅላይ ሚንስቲር የነበረው ፍቅረስላሴም ወግደረስም ደገመው፣ ምክትል ፕሬዚደንት የነበረው ፍስሃ ደስታም ሰለሰው። ፕሮፌሰሩም የትርጉም ልዩነት እንዳለው ነገሩን እንጅ የተባለውን ማለታቸውን አልካዱም።
“አውቄ በስህተት ሳላውቅ በድንቁርና የሰራሁት ሃጢያት ካለ ይደምሰስልኝ?” ማለት ባህላችን ነው። ቢያንስ እርምጃ ከተወሰደባቸው 90 በመቶ የሚሆኑት አማራ ናቸው በማለት ነው።
አሁን ይዘው የመጡት አጀንዳ ደሞ ” ማንነትን መስረቅ መመንተፍ” ነው። አርበኛው በላይ ዘለቀ “ኦሮሞ” ነው የሚል ነው።( https://www.youtube.com/watch?v=_uK66IcXfHs ) ይሄ ነገር ቆየት ያለ ነው። መጀመሪያ ተስፋዬ ገ/አብ ያለው መሰለኝ። ኦነጎቹ ዘፈን ዘፍነውበት ኢሳት ላይ ሰምቸዋለሁኝ። አሁን ፕሮፌሰሩ የተስፋዬ ገ/አብ ቃለአቀባይ ሆነው ቁጭ አሉ። ይሄ የበላይ ዘለቀ ማንነት ጉዳይ የግለሰብ ብቻ ሳይሆን ውስጡም ፖለቲካዊ ተንኮል አለበት። ለጊዜው ያን መግለፅ አልፈልግም።

Friday, May 26, 2017

ታጋዮችን በማሠር የሕዝብን ጥያቄ ማቆም አይቻልም!





ታጋዮችን በማሠር የሕዝብን ጥያቄ ማቆም አይቻልም!
ሰማያዊ ፓርቲ ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ ለለውጥ ቁርጠኛ አቋም ያላቸውን ወጣት ፖለቲከኞች ያፈራ የፖለቲካ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ፓርቲው የሚደርስበትን ጫናና ፈተና ተቋቁሞ የኢትዮጵያ ሕዝብ እውነተኛ የሥልጣን ባለቤት እንዲሆን በፅኑ እየታገለም ይገኛል፡፡
ሆኖም ገዥው ፓርቲ በእያንዳንዱ የፓርቲው እንቅስቃሴ ውስጥ ጣልቃ በመግባት አመራርና አባላቱን እያፈሠ ወደ እስር ቤት መወርወሩ የተለመደ ተግባሩ ሆኗል፡፡ ሕዝብ መብቱን እንዲያውቅና እንዲጠይቅ ፓርቲያችን የሚያደርጋቸውን የአዳራሽና የአደባባይ ስብሰባዎች ህገ-መንግሥቱን በመጣስ በህገ-ወጥ መንገድ ከማፈኑም በተጨማሪ የፈጠራ ክስ እየፈበረከ በሰላማዊ መንገድ በድፍረትና በቆራጥነት የሚታገሉ አባላቶቻችንን ማሰርና ማንገላታቱን ዛሬም አባብሶ ቀጥሎበታል፡፡
በአቶ ጌታቸው ሽፈራውና በአቶ ዮናታን ተስፋዬ ላይ የተላለፈው የቅጣት ውሳኔ የኢህአዴግ አገዛዝ የፍትህ ሥርዓቱን ለፖለቲካ መጠቀሚያነት እያዋለው መሆኑን በግልፅ ከማረጋገጡ በላይ ሥርዓቱ ምንም ዓይነት የመሻሻል ምልክት ማምጣት እንደማይችል ማሳያ ነው፡፡
በእነ በድሉ መንግሥቱ፣ በእነ ማሩ ዳኘው፣ በእነ ብስራት አቢ፣ በእነ እየሩሳሌም ተስፋው፣ በእነ ቴዎድሮስ አስፋው፣ በእነ ሉሉ መሠለ፣ በእነ አግባው ሰጠኝ እና በሌሎችም የክስ መዝገቦች በፓርቲያችን አመራርና አባላት እንዲሁም ጋዜጠኞችና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ላይ የሚደርሰው እንግልት ዜጐቹ ባላቸው የፖለቲካ አመለካከት ልዩነትና ሀሳባቸውን በነፃነት የመግለፅ ህገ-መንግሥታዊ መብታቸውን በመጠቀማቸው፤ ለሀገራቸውና ለወገናቸው ከመቆርቆራቸው የተነሳ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡
ይህ የግፍ እስር በሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራርና አባላት ላይም እንደሚፈፀም እናውቃለን፡፡ በሰማያዊ ፓርቲ ውስጥ ከመሥራችነት ጀምሮ እስከ አመራርነት የደረሱ አባላትን ማሳደድ የቀጠለ ሲሆን፤ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በፊት 94 አመራርና አባላት ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በኋላ ደግሞ በአዲስ አበባ 23፣ በባህር ዳር 20፣ በኦሮሚያ 17፣ በደቡብ 26 አባላቶቻችን በእስርና በእንግልት ላይ መሆናቸውን በተለያዩ ጊዜያት መግለፃችን የሚታወስ ነው፡፡
በመሆኑም መንግሥት የሕዝብን ጥያቄ በአግባቡ ከመመለስ ይልቅ በአምባገነንነት በሕዝብና በፓርቲያችን አባላት ላይ የሚፈፅመውን የግፍ ተግባር እንዲያቆም በአፅንኦት እንጠይቃለን፡፡ “ታጋይና ምስማር ሲመቱት ይጠብቃል” እንዲሉ ታጋዮችን በማሠር የሕዝብን ጥያቄ ማቆም እንደማይቻል እያሳወቅን፤ ሰማያዊ ፓርቲም ሕዝብ የስልጣን ባለቤት እስኪሆን ድረስ ትግሉን አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
“ኢትዮጵያ በነፃነትና በክብር ለዘላለም ፀንታ ትኖራለች!”
ግንቦት 18 ቀን 2009 ዓ.ም.
አዲስ አበባ

Wednesday, May 24, 2017

የነገረ ኢትዬጵያ ዋና አዘጋጅ ጌታቸው ሽፈራው የጥፋተኝነት ዉሳኔ ተላለፈበት


By ሳተናውMay 24, 2017 07:38



( የሰማያዊ ፓርቲ ብሄራዊ ሸንጎ የህዝብ ግንኙነት ንዑስ ኮሚቴ)
ጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው
በከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ዛሬ ግንቦት 16 ቀን 2009 ዓ.ም በዋለው ችሎት የጥፋተኝነት ውሳኔ በጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራሁ ላይ አስተላለፈ::በችሎቱ ላይ እንደተነበበው ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው የሰማያዊ ፓርቲ ልሳን የሆነውን ነገረ ኢትዬጵያ ጋዜጣ እንደሽፋን በመጠቀም በተለያዩ የአገሪቱ ክፍል የሚገኙ ከሰማያዊ አባላት መረጃ በማሰባሰብ በውጭ ሀገር ለሚገኘው ኢሳት ለተሰኘ የቴሌቭዥን ጣብያና ለግንቦት 7 አመራሮች መረጃ ታስተላልፋለህ የሚል ነው::
የቅጣት ውሳኔ ለመስጠት አርብ ግንቦት 18 2009 ዓ.ም ተቀጥሯል:: ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው የቅጣት ማቅለያ በችሎቱ እንዲያቀርብ ቢጠየቅም ማቅረብ እንደማይፈልግ ታውቋል::

Tuesday, May 23, 2017

አለም የሚመራው በለየላቸው ማጅራት መቾች ነው – መስቀሉ አየለ

May 23, 2017 22:10      




ጆርጅ ቡሽና ቶኒ ብሌየር ኢራቅ ውስጥ አንድ ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ሰው ገድለዋል።አካለ ጎደሎ ሆኖ የቀረውና የተፈናቀለውን ሰው ሲጨመርበት ደግሞ ስሌቱን ሆድ አይችለውም። ይኽ አሃዝ የጸጥታው ምክር ቤት እራሱ በሾማቸው አጣሪ ኮሚሽን የተረጋገጠ ቢሆንም በመጨረሻ ሰአት የምርመራው ውጤት ግን ለሚቀጥሉት ስልሳ አመታት ለህዝብ እንዳይገለጥ ወስነው በደንበኛ የብረት ካዝና ቆለፉበት። ያን ግዜ ተጠያቂዎቹ በህይወት ስለማይኖሩ እንዲሁ ወሬ ዘርተው ጋዜጣ ይሰሩበታል ነው ማለት ነው።
ሳውዲ አረቢያ የሚባለው አገር የአንድ ሰው ንብረት ነው። አገሩም የተጠራው የዛሬ መቶ አመት ገደማ በነበረው የዘላኖቹ አለቃ ስም ነው፤ አልሳውድ ይባል ነበር፤ የንጉሳዊ ቤተሰብ እየተባለ ዛሬ ድረስ የዘር ግንድ የሚመዘዘው ከዚህ ሰው ነው። የርሱ የልጅ ልጆች ደግሞ አይሲስ የሚባል አደገኛ ቫይረስ ፈጥረው ይኸው አለሙን መከራ ያበሉታል።ነገሩ እንዲህ ነው። በዚሁ በሳውዲ አረቢያ ውስጥ በአስገድዶ መድፈር፣ በድራግ ሽያጭ፣ በግድያ፣ በኦርጋን ትራፊኪንግና በሌሎች ከባባድ ወንጀሎች ተከሰው የሞት ፍርዳቸውን ይጠብቁ የተነበሩትን ወንጀለኞች በሚስጥር ከእስር ቤት አውጥተው አይሲስን ሲፈጥሩ እና መካከለኛውን ምስራቅ በእሳት ሲያነዱት የምዕራባውያን ቡራኬ ስላለበት ነው።
ዛሬ ሳውዲ አረቢያ የሚባል የፍየል ጠባቆዎች ስብስብ የመንን ከደቡብ አሜአሪካና ከምስራቅ አውሮፓ የጦር አውሮፕላን የሚያበሩ መርሰነሪ ገዝቶ ያስደበድባል፤ዛሬ የመን የሰው ደም ለጠማው የዘመኑ ኢሊምናቴና መሶናይት የተሰጠች የመስዋእት ጠቦት ሆና እለት እለት እንደመና የእሳት ድኝ ከሰማይ ይወርድላታል። በውስጥ በተደረገ ስምምነት ማንኛውም አይነት የምእራቡ የዜና ትቋም ስለየመን አዳርና ውሎ ትንፍሽ እንዳይል ተደርጎዋል።
የጸጥታው ምክር ቤትም ሆነ የተባበሩት መንግስታትም ቢሆኑ ስለጉዳዩ አጀንዳ ይዘው ለመወያየት እንኩዋን ፈቃደኛ አይደሉም።
ዩክሬንን ጨምሮ የምስራቅ አውሮፓ አገሮች ሁሉ ከአሜሪካኖቹ በላይ አሜሪካዊ መሆን በሚፈልጉ ባንዳ መሪዎች እንዲሞሉ ተደርጎዋል።አንደበተ ቁጥቧን ፕሬዝደንት ዲልማ ሮውሴፍን ያህል ቅን መሪ አንስተው ነፍሱን ለአሜሪካ የሸጠውን ማይክል ተመርን ያነገሱት ብራዚላውያን ዛሬ አይናቸው ሲገለጥ ውረድ ማለት ጀምረዋል።እርሱ ስልጣን ላይ በወጣ ማግስት ድፍን ብራዝሊን ለአሜሪካ በቆዳ ምላሽ መቸብቸብ ሲጀምር ብራዚላውያን ግን ዘግይተውም ቢሆን አይናቸውን በመግለጣቸው አገሪቱ ሌላ ዙር ትርምስ ውስጥ መገባቷ ነው መዘዙ።
እንዲህ ካናቱ የገማ አለማቀፍ ተቋም እረጋ ብለው ሲያዩት ነገሩ ሁሉ ይበልጥ ውስጡን ለቄስ ነው። በነፍስ የሚስያቡ ሰዎች ገብተው የሚወጡበት አይደለም።ዛሬ እነ ቢልጌት ደግሞ የአለምን የህዝብ ቁጥር ለመቀነስ ብዙ ገንዘብ የፈሰሰበት ትላልቅ ፕሮጀክት ይዘው በር ላይ እየጠበቁ ነው። ለዚህ ፖሊሲ ተፈጻሚነት ደግሞ ቴድሮስ አድሃኖም የመሳሰሉ የፍናፍንት ስነልቦና ያለው ደርቲ ሰው ያስፈልጋል። ሁለት አመት ሙሉ አሰልጣኝ ቀጥረው ሲያዘጋጁት መክረማቸው ለዚሁ ነበር።
ነጮችን የቢግባንግ ባሌቤት ያደረጋቸው የለም፤ ይኽች ምድር የሁሉም ናት ባለቤት የላትም። ሰው ሆነን የተፈጠርን እኛ ይሕችን ፕላኔት ከሁሉም ተጋርተን ለመኖር የማንም በጎ ፈቃድ አያስፈልገንም። ቆዳውን ቀይሮና ስሙን አሳምሮ ነገር ግን የሂትለሩን የዘር ፍጅት ሚንስቴር ጆሴፍ ጊዮብልስን ተክቶ የመጣው ቢል ጌትና ኩባንያው በዛሬው እለት ሁለት እግሩን በአለማቀፉ የጤና ድርጅት ላይ ተክሏል። ከዚህ ሴራ ጀርባ ያለውን እውነት ደግሞ ያየነው እኛ ኢትዮጵያውያን ብቻ በመሆናችን ብቻችንን ጮኸናል። በተጻራሪው ፤ጆሮ ዳባ ልበስ ማለቱን የመረጠው አለም ግን ከጩኸታችን ጀርባ ያነበረውን ቁጭት አንድ ቀን በዓይኑ ያየዋል።
ባለፈው ሰሞን የራሽያው ፕሬዝዳንት ፑቲን በአደባባይ ወጥቶ እንዳጋለጠው በኮንጎ ውስጥ ተበትኖ ድፍን ምእራብ አፍሪካ ከአንድ አመት ለበለጠ ግዜ ሲበላው ከከረመው የኢቮላ ሰደድ እሳት ጀርባ እጁ ያለበት ዋነኛው ሰው ቢልጌት መሆኑን እንዲሁም የአለም የጤና ድርጅት አፋጣኝ እርምጃ እንዳይወሰድና የሰዎችን ህይወት መታደግ እንዳይቻል ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ ለበርካታ ወራት ድምጹን ያጠፋው በዚህ በጡት አባቶቹ በነቢልጌት ተጽእኖ እንደ ነበረ እንቅጩን አውጥቶ ለአለም ህዝብ አሳይቷል።
በዚሁ አጋጣሚ ግን ግልጽ መሆን ያለበት አንዱ ቁልፍ ጉዳይ በግዜው ድፍን አለም የበረራ መስመሩን በሙሉ ፤ የንግድ እንዲሁም የቱሪዝም አገልግሎትን አቋርጦ፣በሩን በምዕራብ አፍሪካ ላይ ሲዘጋ፤እነ ሞሮኮ የአፍሪካ ዋንጫን እስከ መሰሰረዝ ሲደርሱ የወያኔው ሚንስቴር ግን ቁጭ ብሎ ሲያሰላ የነበረው ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚገኘውን ትርፍ ሲሆን ይባስ ብሎ በመቶ የሚቆጠሩ ፤ዕእርዳታ ሰጭ ታስክ ፎርስዕ ወደ ላይቤሪያ ካዘመተበት ባዶ እብሪት ጀርባ ያለውን እውነት መጎርጎሩ አይከፋም።

አርበኞች ግንቦት 7 ትምህርትና ስልጠና መምሪያ በርካታ ቁጥር ያላቸውን ምልምል አርበኛ ታጋዮች አሰልጥኖ አስመረቅሁ አለ



የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ

********************************
የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ትምህርትና ስልጠና መምሪያ በርካታ ቁጥር ያላቸውን ምልምል አርበኛ ታጋዮች በወታደራዊ፣ በፖለቲካ፣ በእጅበእጅ (ቴኳንዶ)፣ በመረጃና ደህንነት እንዲሁም በጉሬላ ውጊያ ለበርካታ ወራት ሲያሰለጥናቸው ቆይቶ እሁድ ግንቦት 13 ቀን 2009 ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ ማስመረቁ ታውቋል፡፡
በምርቃት ስነ-ስርዓቱ ላይም የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ከፍተኛ አመራሮች ና ከተለያዩ ግንባሮች የመጡ አርበኛ ታጋዮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል ፡፡
የትምህርትና ስልጠና መምሪያ ምክትል ሃላፊ የሆኑት አርበኛ ታጋይ ካሳሁን ይነሱም አሁን ወቅቱ ህዝቡ በአንድነት ሆ ብሎ የተነሳበትና ከምንም ጊዜ በላይ ህዝብ አርበኞች ግንቦት 7ትን የሚጠብቅበት ጊዜ ላይ ነው የምንገኘው ፡፡ በዚህ ጊዜ ለዚህ ትግል የቻላችሁትን ሁሉ አስተዋፅዎ ለማድረግ በቁርጠኝነት በመነሳታችሁና ለህዝብ አለኝታ ለመሆን የሚጠበቅባችሁን ስልጠና በአግባቡ በመወጣታችሁና ይህን አድካሚ ስልጠና ጨርሳችሁ ለዛሬ ለምርቃት ቀናችሁ በመድረሳችሁ እንኳን ደስ አላችሁ በማለት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል

Monday, May 22, 2017

የዶ/ር ቴዎድሮስ ለዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ሆነው ከተመረጡም ለሕወሓት የባሰ አደጋ ይዞበት ይመጣል

  





የጉዳያችን ማስታወሻ
ዶ/ር ማርጋሬት ቻን ተሰናባቹ የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር
ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ለዓለም ጤና ድርጅት ከፍተኛ የስራ ኃላፊነት ከቀሩት ሶስት ግለሰቦች ውስጥ አንዱ እጩ መሆናቸው እና የመጨረሻ ድምፅ የመስጠቱ ስነ-ስርዓት ማክሰኞ ግንቦት 15፣2009 ዓም ድምፅ እንደሚሰጥ ለማወቅ ተችሏል። ዛሬ ሰኞ ማለዳ በስዊዘርላንድ ዋና ከተማ ጄኔቭ በተሰናባቿ የድርጅቱ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ማርጋሬት ቻን (Dr Margaret Chan) ለቀጣይ ሰባት ቀናት በሚቆየው የድርጅቱ 70ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እንደተናገሩት ተሰብሳቢዎቹ ኢ-ፍትሃዊ እኩልነት በተቻለ መጠን እንዲቀንስ አበክረው እንዲሰሩ አሳስበዋል። “ፍትሃዊ እኩልነት ላይ ትኩረት መደረግ አለበት ስል ደግሞ” አሉ ወይዘሮዋ ዶክተር ቀጠሉና ” የዓለም ጤና ድርጅት የስነ ምግባር መመርያ መርህ ´የዓለም ጤና ድርጅት ለፍትሃዊ ተጠቃሚነት ፀንቶ ይቆማል´ የሚለውን አንቀፅ በማስታወስ ነው ” አሉ። ከእዚህ ጋርም አያይዘው ድርጅቱ ለምርምር ትኩረት እይዲያደርግ እና ከመንግስታዊ ካልሆኑ አካላት ጋር የሚደረገው ግንኙነት መጠናከር እንዳለበት ይህም የሲቪሉን ማኅበረሰብ ለማዳመጥ እንደሚረዳ እና የሲቪሉ ማኅበረሰብ መንግስትን እና እንደ ሲጋራ፣የምግብ እና አልኮል ፋብሪካዎች ሕብረተሰቡን የሚጎዳ ተግባራት ሲሰሩ አደብ የሚያስይዛቸው መሆኑን ጠቁመዋል።ከእዚሁ ጋር ተያይዞም የድርጅቱ ተሰናባች ዳይሬክተር ንግግር እንደጀመሩ ከአዳራሹ የጋዜጠኞች መቀመጫ ሰገነት ላይ ዶ/ር ቴዎድሮስን የሚቃወም ድምፅ ከአክቲቪስት ዘላለም ተሰማ ተሰምቷል።ዘላለም ከ190 በላይ የሀገር ተወካዮች ፊት ባሰማው ድምፅ ” ቴዎድሮስ ለፕሬዝዳንትነት አይሆንም! አፍሪካ ደግማ ታስብበት!” የሚል ድምፅ በእንግሊዝኛ አሰምቷል።የአክትቪስቱ ተቃውሞ በደቂቃዎች ውስጥ በዓለም ዙርያ በማኅበራዊ ሚድያ ተሰራጭቷል።
በድርጅቱ የዛሬ ውሎ ማብቂያ ላይ ማክሰኞ እለት የድርጅቱ ፕሬዝዳንትን ለመወሰን ምርጫ እንደሚደረግ እና ምርጫው ላይ አንድ ሀገር አንድ ሰው ብቻ እንዲወክል በድርጅቱ ህንፃ ሌላኛው ክፍል ላይ ነገ እንዲገናኙ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።
በሰሞኑ የዶ/ር ቴዎድሮስ ለዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተርነት መወዳደር በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ዓቢይ የፖለቲካ መከራከሪያ ሆኖ ቀርቧል።መመረጥ አለባቸው ብለው የሚከራከሩት መሰረት የሚያደርጉት የሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ስለነበሩ በድርጅት ፍቅር የተጠመዱ፣ ሁለተኛዎቹ ከድርጅት ፍቅር በላይ የትግራይ ብሄርተኝነት አይሎባቸው ” የእኛ አካባቢ ነው” ከሚል ብቻ የሚደግፉ እና ሶስተኛዎቹ ሌላ ቦታውን ከሚይዘው ኢትዮጵያዊ ሰው ቢሆንበት ይሻላል የሚሉ ናቸው።
በተቃዋሚዎች በኩል ደግሞ ደጋግሞ የሚነገረው ዶ/ር ቴዎድሮስን የምንቃወመው ትግራይ ስለሆነ እና ስላልሆነ አይደለም የምትለው አረፍተ ነገር ቀዳሚ ስትሆን፣ ከእዚህ በተለየ ግን ዶ/ር ቴዎድሮስ የአንድ አካባቢ ፍላጎት እና ነፃነት አስከብራለሁ የሚለው ሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ሆነው አብረው በወሰኗቸው ውሳኔዎች የበርካታ ግድያዎች፣እስሮች እና ሰቆቃዎች ተባባሪ ናቸው።በሌላ በኩል በዐማራ ክልል በተሰጠ የወሊድ መቆጣጠርያ እንክብል እና ክትባት ሳቢያ ከሁለት ሚልዮን በላይ ዜጎች እንዳይወለዱ አስደርገዋል።በሌላ በኩል በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፉ ግሎባል ፈንድ ውስጥ የገንዘብ ቅሌት ውስጥ እጃቸው አለበት የሚሉ እና በኢትዮጵያ ተከስቶ የነበረው የኮሌራ በሽታ እንዲደበቅ አድርገዋል የሚሉ ይገኙባቸዋል።በተለይ የኮሌራ በሽታ መደበቅ ጉዳይ ላይ የኒው ዮርክ ታይምስ እና ዋሽንግተን ፖስት ጋዜጦችም ባለፈው ሳምንት በሰፊው የፃፉበት ጉዳይ ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ሌላው ሊተኮርበት የሚገባው ጉዳይ ዶ/ር ቴዎድሮስ ዓለም ዓቀፋዊ አስተሳሰብ የሚያላብሳቸው ምን ጉዳይ አለ? ብለን ብንጠይቅ ያለፈ ታሪካቸው በአንድ ክልል ነፃነት ቆምያለሁ የሚለው ስሙንም እስካሁኗ ሰዓት ድረስ የትግራይ ነፃ አውጪ ብሎ የሚጠራው ድርጅት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል እንደነበሩ እና በእዚሁ መስመር ብቻ የውጭ ጉዳይነቱንም ሆነ የጤና ሚኒስትርነቱን ቦታ ይዘው እንደነበር የሚታወቅ ነው።ስለሆነም አንድ ሰው ብሔራዊ ሳይሆን በአንድ ክልል ነፃነት በቆመ ድርጅት አስተሳሰብ ታንፆ እንዴት ዓለም ዓቀፋዊ አስተሳሰብ ሊዳብር ይችላል? ዓለም አቀፋዊ አስተሳሰብ ሁሉን እኩል አድርጎ የማየት ክህሎት እንጂ የትግራይ ነፃ አውጪ ነኝ በሚል ድርጅት ግንብ ውስጥ መታጠር አይረዳም።ስለሆነም ዶ/ር ቴዎድሮስ ዓለም አቀፋዊ አስተሳሰብ ለማዳበር ከአንድ በዘር ላይ ከተመሰረተ ድርጅት አስተሳሰብ እራሳቸውን ማላቀቅ አስፈላጊ ነው።
በመጨረሻም ዶ/ር ቴዎድሮስ ለዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተርነት ቢመረጡ ለሕወሐት ይዞ የሚመጣው እራሱን የቻለ አደጋ አለው።ብዙዎች የስርዓቱ ደጋፊዎች ሕወሓት አንዱ ባለሥልጣኑ ለከፍተኛ የዓለም ድርጅት መሪነት መመረጣቸው የስነ – ልቦና እርካታ እንደሚያገኙ የሚያስቡ አሉ።ሆኖም ግን ውጤቱ የተቃራኒው ነው የሚሆነው።የዶ/ር ቴዎድሮስ መመረጥ ሕወሓት ማን ነው? ምን ያህል ሕዝብ በድርጅቱ ውሳኔ ተገድሏል? ድርጅቱ ለአንድ ጎሳ የቆመ መሆኑን እራሱ ከስሙ ጀምሮ እንደሚተርክ፣ እና የመሳሰሉት ሁሉ ለዓለም የበለጠ ግልጥ ይሆናል። ይሄውም ዶር ቴዎድሮስ ከተመረጡም በኃላ የኢትዮጵያውያን ተቃውሞ እንደማይቆም ግልጥ ነው።
አንድ የዓለም አቀፍ ድርጅት ፕሬዝዳንት በተንቀሳቀሰ ቁጥር ተቃውሞ የሚገጥመው ከሆነ ዓለም አቀፍ ሚድያዎችን ትኩረት በእጅጉ ይስባል።ተቃውሞ ማድረግ ደግሞ አንድ ግለሰም ምንም ያህል ዲፕሎማሲያዊ ከለላ ቢኖረውም የማንም ሰው መብት ነው። ይህ ማለት ኮንጎ ውስጥ ያለ ገጠር መንደር ውስጥ ያለች እናት ሕወሓት ማን ነው ? ትላለች ማለት ነው።ብራዚል ውስጥ ያሉ ወጣቶች ተቃውሞው እና ዶ/ር ቴዎድሮስ የመጡበትን ድርጅት ሕወሓት በአፍሪካ አደገኛ የሰብዓዊ መብት የጣሰ ድርጅት መሆኑ የበለጠ የታወቀ ይሆናል።የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር በእየሄዱበት ተቃውሞ የሚገጥማቸው ብቸኛ ሰው ይሆናሉ ማለት ነው።በመሆኑም ሕወሓት በዶ/ር ቴዎድሮስ መመረጥ የበለጠ ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ የተጋለጠ ይሆናል።ይህ ሁኔታም ዶ/ር ቴዎድሮስ ከተመረጡ የስራ ጊዜያቸውን ሳይጨርሱ ስራቸውን ለመልቀቅ ሊያስገድዳቸው ይችላል።አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር ያሰበው እና ሰው ያሰበው መለያየቱ እና እግዚአብሔር የበለጠ ሊሰራ ሲፈልግ እንዴት እንደሚሄድ የሚታይበት አንዱ አጋጣሚ ነው። ሕወሓት በዓለም ዙርያ የሰራቸው እኩይ ተግባራት ሁሉ እንዲጋለጥ የእግዚአብሔር መንገድ ይህ ሊሆን ይችላል።ለእዚህ አንድ አባባል አለ።አንድ ብርጭቆ ከሁለተኛ ፎቅ ላይ ቢወድቅ አይጎዳ ይሆናል ከአስረኛ ፎቅ ላይ ከወደቀ ግን ስብርባሪውም አይገኝም።ሕወሓት በዓለም ላይ የበለጠ እንዲጋለጥ ዶ/ር ቴዎድሮስ አስረኛ ፎቅ ላይ መውጣት አለባቸው ይሆናል።ከአስረኛ ፎቅ ላይ የወጣ የሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የነበረ ሰው የሕወሓትን በዘር ላይ የተመሰረተ አደረጃጀት፣የኢትዮጵያን ምጣኔ ሀብት መቀራመት እና በሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮያውያን መገደል እና ሰቆቃ ለዓለም የበለጠ በዶ/ር ቴዎድሮስ ላይ በሚደረጉ ቀጣይ ተቃውሞዎች እንዲጋለጥ የተወሰነው ከላይ እንደሆነ ማን ያውቃል? ” ማን ያውቃል የመስከረም ወር እና የመስቀል ወፍ ቀጠሮ እንዳላቸው” ነው ያሉት ደራሲ እና ገጣሚ መንግስቱ ለማ።
ጉዳያችን GUDAYACHN

የትራምፕ ወደ ሳኡዲ አረቢያ መሔድ ኢትዮጵያ ካለችበት መልከዓምድራዊ የፖለቲካ ሁናቴ ጋር የሚገናኝ በመሆኑ አትኩሮት በመስጠት ጉዳዩን ልንከታተለው ይገባል | የሳዲቅ አህመድ ትንታኔ

ባንዳው ማነው? መጋረጃው ሲገለጥ !……… [ቬሮኒካ መላኩ]

[ቬሮኒካ መላኩ]
…………………………
ባለፈው የፈረንጆቹ አዲስ አመት አካባቢ አንድወዳጄ ከወደ እንግሊዝ ” እስኪ እነዚህን ዶኪመንቶች የሚጠቅሙ ከሆነ ” በማለት ላከልኝ ። ሁለት መፅሃፎች እና የእንግሊዝ ፓርላማ በ 1868 አካባቢ ኢትዮጵያን ለመውረርና አፄ ቴዎድሮስን ለመውጋት ውይይት ያደረገባቸው ቃለ ጉባኤ ኮፒ ኖሯል የላከልኝ ። ያን ቃለ ጉባኤ ሳነበው አንዱ የእንግሊዝ ፓርላማ House of Lords አባል የትግራይ ገዥ የነበረውን በዝብዝ ካሳ (በኋላ አፄ ዮሃንስ) በባንዳነት እንደሚረዳቸው ማረጋገጫ እንዳገኘ የተፃፈውን አነበብኩኝ።
ሌላው መፅሃፍም ውስጥ የበዝብዝ ካሳ ሰራዊት ከዝሆንና ከበቅሎ የተረፈ የእንግሊዝን ጓዝ በትከሻው ተሸክሞ ወደ መቅደላ ሲገሰግስ ያሳያል ። እንደዚሁ በሌላም ቀን የአምባሳደር ዘውዴ ረታን መፅሃፍ ሳነብ የአፄ ዮሃንስ የልጅ ልጅ ደጃዝማች ሃይለስላሴ ጉግሳ መቀሌ ከተማ ላይ የኢትዮጵያን ባንድራ አውርዶ የጣሊያንን ባንድራ ሲሰቅል የሚያሳየውን ፎቶ ተመልክቼ ቅፍፍ ብሎኝ ውሎ ነበር።

ሰሞኑን በስፋት በዚህ ማህበራዊ ድረገፅ “ባንዳና ” “ኢትዮጵያዊ ” የሚሉት ስያሜዎች በስፋት ጥቅም ላይ እየዋሉ ነው። አስገራሚው ነገር ታዲያ “ባንዳ ” የሚለውን መጠሪያ ለሌላው እየተጠቀሙ ያሉት የባንዳወቹ የልጅ ልጆች ሲሆኑ “ኢትዮጵያዊ ” የሚለውንም ሲጠቀሙበት የታዩት ለወትሮው ኢትዮጵያ የሚል ስም ሲሰሙ የሚያንገሸግሻቸው እና ትግሬ ሪፐብሊክን ለመመስረት ትግል ከጀመሩት ኢትዮጵያ ጠል ከሆኑ ሰዎች መሆኑ ነው ።

ታድያ ይሄ ጉዳይ ሲደጋገምብኝ አንድ የአገሬ አርሶ አደር የተናገረውን ተረትን አስታወሰኝ፡፡ «አያ ለመሆኑ ብሳና ይነቅዛል ? ;» ቢለው
«… ምን ነካህ ለእንጨቱ ሁሉ ያስተማረው ማን ሆነና» አለ ይባላል።
እረ ጎበዝ እንከባበር እንጅ? “ለመሆኑ ባንዳነት ለአለም ህዝብ ማን ያስተማረውና? ” እንደው እንደዚህ ያለውን ድፍረትና ቅጥፈት ከወደየት አገኛችሁት?

ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ ባለፉባቸው ዘመናት ማለት የሚፈልጉትን በቅኔ፣ በግጥምና በግዕዝ ችሎታቸው እየታገዙ ጠንካራና አመራማሪ መልዕክቶችን ያስተላልፉ ነበር አሉ ።
በጣሊያን ዘመን አገርን ከወረራ ለማዳን አርበኛው በዱር በገደሉ ሲዋጋ ህዝቡም ህይወቱን ሲሰዋ ጥቂት ሰዎች ግን ለጣሊያን በባንዳነት አድረው ክህደታቸውን በግልጽ ያሳዩ ነበር። የነዚህን አድር ባዮች መጥፎ ምግባር የሚያውቁት ነጋድራስም በቅኔ ሸንቆጥ ያደርጓቸው ነበር አሉ ።
ታድያ አንድ ቀን ንጉሡ በተገኙበት የዒላማ ተኩስ ላይ ከወደ ትግራይ የመጣ በፊት በባንዳነት የሚታወቅና ቤተ መንግስት አካባቢ የሚያረጠርጥ ሰው በመጀመሪያው ጥይት አልሞ ይመታል። ይህ ሰው በጠላት ወረራ ወቅት ባንዳ እንደነበረ የሚያውቁት ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ «ወይ ጉድ ባንዴ ቡን አረጋት»ሲሉ በቀልድ ባንዳነቱን ነገሩት አሉ ።
አንዱ የባንዳ ዋና ፀባይ ከመጣው ጋር ልጥፍ የማለት አስመሳይ ባህሪያቸው ነው ።

መቼም በቅርብ አመታት በተከታታይ በኢትዮጵያ ጦርነቶች በተሳተፉ ፈረንጅ የአይን እማኞች ታትመውና ተተርጉመው የወጡት መፃህፍት ስለ ባንዳነትና አገር ክህደት የዘረገፉት ታሪክ ጉድ የሚያስብል ነው። ለካ ባንዳም የሚበቅልበት የተወሰነ ቦታና መሬት አለው የሚያስብል ነው ።

በኮሌኔል አሌህንድሮ ዴልባዬ ተፅፎ በተስፋዬ መኮንን የተተረጎመው ” ቀይ አንበሳ ” እና የሃበሻ ጀብዱ በሚል ርእስ በተጫነ ጆብሬ መኰንን የተፃፈውን ታሪክ የጣሊያን ወረራን ለመመከት የኢትዮጵያ ጀግኖች ያደረጉትን ታላቅ መስዋዕትነት የሚተርኩና የትግራይ ባንዳዎች በአርበኞችና በአገር ላይ የፈፀሙትን ለመግለፅ እንኳን የሚያሸማቅቅ ጉድ ዘርግፈውታል ። ለአርበኞች በእንጀራና በውሃ የውሻ መርዝ እየጨመሩ እስከመስጠት የሚደርስ ባንዳዊ ተግባር ሲፈፅሙ ያስነብቡናል ።

የመጽሐፎቹ ጸሐፊ የቼክ ተወላጁ አዶልፍ ፓትሪክ እና አሌህንድሮ ደል ባዬ ጃንሆይ ከውጪ ሀገር ለጦር አማካሪነት ካስመጧቸው ጥቂት የውጪ ሰዎች መካከል ናቸው። ፓትሪክ በታማኝነት ልክ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ አርበኛ በቆራጥነት በተለያዩ ግንባሮች የጣሊያንን ጦር የተፋለሙና በቅርብ የራስ ካሳ አማካሪ በመሆን በተለያዩ የጦር አውድማ የተደረጉን ጦርነቶች በውጊያ በስለላና በምክር የራስ ካሳን ጦር እስከመጨረሻው ሲያግዙ የቆዩ በመሆናቸው ይህ መጽሐፋቸው ።
ጀግና ባለበት ጥቂት እንክርዳድ ባንዳ አይጠፋምና በትግራይ የነበሩ ሽፍቶች ከወገናቸው መሳሪያ ለመንጠቅ ሲሉ በወገናቸው ጦር ላይ በተለያየ ጊዜ ያደረሱት ጉዳት ቀላል እንዳልነበር ያስነብቡናል።

የአገራችን ሰው “ቆማጣን ቆማጣ ካላሉት ገብቶ ይፈተፍታል።>> አ ንደሚባለው ጭምብሉ ተገፎ እስኪታይ ድረስ ደግሞ ትርምስና መደነጋገር ውስጥ ሳይገቡ በረጋ መንፈስ ነገሮችን ለማጣራትና መርምሮ ከእውነቱ ለመድረስ ጊዜ መስጠት ያስፈልጋል በማለት ዝም ብንላቸው የሹምባሽ ልጆች ባልዋሉበት ኩበት ለቀማ ሲሄዱ መመልከት ትእግስት የሚያስጨርስ ጉዳይ ነው ።

ይች ለአለም ጤና ድርጅት የምትደረግ ውድድር ያመጣችው ጣጣ መሆኑ ነው። በዚህም የተነሳ የአርበኛ ልጅ ባንዳ ፣ የባንዳ ልጅ ደሞ አርበኛ ሲባል እየሰማን እያነበብንም ነው።
የወያኔዎች እና የልጆቻቸው ውሸት እና ተንኮል የሚገር መሆኑንም እየተመለከትን ነው ። የዘመኑ አራዶች «ስጥ፤ ቀደዳ፤ ረገጣ፤ ሌላም ሌላም» የሚሉት አይነት መሆኑ ነው ። ውሽት እንዲህ በተለያየ ስያሜ ሲጠራ የእሱ አጋፋሪ የሆኑት ደግሞ «ቀዳጅ፤ ሰጪ፤ ረጋጭ» መሆናቸው ነው ።
የቴዎድሮስ አድሃኖም አይነቱ ውሸታም ደግሞ ባልዞረ ባልነበረበት ጉዳይ እንደነበረና እንደተካፈለ አድርጎ «ሲረቅ ተመልክቻለሁ፤ ሲፈረምም አይቻለሁ» ብሎ ውሸቱን በመሀላ የሚያፀድቅ፤ ልፈለጥ፤ ልቆረጥ ብሎ የሚልና የሚምል፤ ምላጭ የሆነ ውሸታም ከአፈርኩ አይመልሰኝ የሚል ዓይነት ሰው ነው። የህፃን ብሪቱን ጉዳይ ማስታወሱ ብቻ በቂ ነው ። ሰሞኑን ዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣም ዉሸቱን በአለም አደባባይ ይፋ አውጥቶታል ።

ባለፈው ፅሁፌ ቴድሮስ አድሃኖምን የቬኑሱ ነጋዴ ሻይሎክን ነው ብዬ ነበር። ቴድሮስ ሻይሎክ ብቻ ሳይሆን ኢያጎም ጭምር ነው።
በሸክስፒር « ኦቴሎ» ቲያትር ውስጥ የተሳለው ገፀ- ባሕርይ ኢያጎ በውሸቱ የየዋሁን «ኦቴሎ» ን ልብ አታልሏል፡፡
የኢያጎ የሀሰት (የውሸት) ዘር ኦቴሎ ልቦና ላይ ተዘርቶ በሕሊናው በቅሎ ካደገ በኋላ ምንም በማታውቀው በዴዝዲሞና የሕይወት አውድማ ላይ ተወቅቷል፡፡ የውሸት ውጤት ጥፋት ሆኗል ። የሕይወት ዋጋ አስከፍሏል። የዋሾዎች ግብ ይሄው ነው። ኢያጎ በሰይጣናዊ ሀሳቡ ያተረፈው ነገር የለም። ሊኖርም አይችልም። ቴድሮስም ኢያጎና ሻይሎክን አጣምሮ የያዘ ከይሲ ነው። በአማራ ሴቶች ላይ የፈፀመውን ግፍ ማስታወሱ በቂ ነው ።

ሳላስበው ወደ ሌላ አጀንደ ገባሁኝ መሰለኝ ። ይሄ አህያ ቀንድ ፣ አሳማ ክንፍ አወጣ አይነት አስቂኝ የባንዳነት ባህሪ ለአማራው የሰጡት መሰለኝ ። << ጉድ በል ጎንደር> > ይሄ አይነት ውሃ ሽቅብ አይነት ሲገጥመው መሆኑ ነው ። ምፀቱም ይሄው ነው ።
አማራ የውጭ ጠላት በመጣ ቁጥር ክተት ሥራዊት እየተባለ በራሱ ስንቅና ትጥቅ በባዶ እግሩ በመዝመት የአገሩን ዳር ድንበርና ወገኖቹን ከውጭ ወራሪ ጠላትና ከባርያ ፈንጋይ የዓረብ ነጋዴዎች ሲከላከልና ሲጠብቅ
መኖሩን ታሪክ ምስክር ነው።
አማራ ለአገሩ መንግሥትም ሆነ ለወገኑ ታማኝ፤ ከመሆኑ የተነሳ ለውጭ ጠላት ፈጽሞ የማይመችና የማይታለል በመሆኑ ይኸው አገራችን ኢትዮጵያ ዳር ድንበሯ ሳይደፈር አሁን ላለው ትውልድ እንድትደርስ ከፍተኛውን አስተዋጽዖ ያደረገ ኩሩና ጀግና ሕዝብ መሆኑን አይደለም ኢትዮጵያዊ፤ የዓለም ሕዝብ ያውቀዋል።
ኢትዮዽያዊ ጀግንነት ሀገሬን አላስነካም ብለው የአርበኝነቱን ቀንዲል አብርተው በታላቅ መስዋእትነት የሐበሻን የጀግንነት ተጋድሎ አቀጣጥለው ወራሪውን የኢጣሊያ ሰራዊት በተቆጣጠራት አዲስ አበባ ግምባር ለግምባር ገጥመው በጠላት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሰው ወደመጡበት እንድመለስ ተአማራዊ ህዝብ ነው። ስለአማራ አርበኝነት ለማውራት መሞከር አባይን በጭልፋ የሚሉት አይነት ነው።

አሁን ዛሬ ለእኛ ስለኢትዮጵያዊነት የሚሰብኩን ለትግራይ ሪፐብሪክ የተዋጉ ናቸው፡፡ ሶማሌ ኢትዮጵያን በወረረችበት ዘመን ከሶማሌ ጎን ኢትዮጵያን የወጉት ባንዶች ናቸው፡፡ መቋዲሾ ቢሮ ከፍተው በሱማሌ ፓስፖርት የታገሉን ናቸው ፡፡ ሌላም ሌላም … እንግዲህ የትግራይ ሪፐብሪክ ብሎ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚወጋ “ኢትዮጵያዊ ነኝ ” ፣ “አርበኛ ነኝ ተቆርቋሪ ነኝ” ሊል አይችልም፡፡

“ባንዳ እና ዘረኛ” (ይድነቃቸው ከበደ)



“ባንዳ እና ዘረኛ”

[[ ዶ/ር ቴዎድሮስ እንዳይመረጡ በአብዛኛው የሚደረገው ተቃውሞ በሥራቸው እንጂ ‘በብሔራቸው’ እንዳልሆነ ግልጽ ነው። የእሳቸውን ‘ብሔር’ መሠረተ አድርጉ የሚቃወም ቢኖሩ ያ ሰው ዘረኛ ነው። ለዘረኛ ደግሞ ‘ተክላይ’ ሲሆን የሚወገዝ፣ ‘ከበደ’ ከሆነ ደግሞ የሚወደስበት ምን አይነት የተለየ ሚዛን የለም ! ]


የዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የምረጡኝ ዘመቻ ተከትሎ በሃገር ውስጥ እና በውጪ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ነው። እሳቸውን በመደገፍ እና በመቃወም የሚደረገው እንቅስቃሴ በራሱ የሚበረታታ እና የሚደገፍ ነው። ይህ ማለት ግን በዘረኝነት እና በባንዳነት ደረጃ እዚህ እና እዚያ መስመር አስምሮ የሚደረገው ሰጣገባ ተገቢ ነው እያልኩ እንዳልሆነ ታሳቢ ይደረግልኝ።በምረጡኝ ዘመቻ ተፉካካሪ ባለበት አንዱን ከሌላ ማበላለጥ የምርጫ አንድ አካል ነው። እርግጥ ነው እሳቸው የሚወዳደሩት ከውጪ ሃገር ዜጋ ጋራ ነው። ይሁን እንጂ አብዛኛው የእሳቸውን መመረጥ የማይደግፍው ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖምን ከእንግሊዛዊ ዴቪድ ናባሮ ጋር በማወዳደር አይደለም።ዶ/ር ቴዎድሮስ በሃገር ውስጥ በሰሩት ሥራ ነው! ሥራቸው ደግሞ ምን እንደነበረ በእሳቸው ላይ ይቀርብ የነበረው ተቃውሞ እና ትችት መልስ ብሎ መመልከት ተገቢ ነው ። አብዛኛው ትችች እና ተቃውሞ እራሱን የቻለ በቂ ምክንያት አለዉ ! ይህን አሳማኝ ምክንያት ጠንቅቆ ካለመረዳት ወይም ለመረዳት አለመፈለግ ካልሆነ በስተቀር ።

እውነታው ይህ ሆኖ እያለ ፣ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ለWHO የሚያደርጉት የምረጡኝ ዘመቻ መቃወም በዘረኛነት እና በባንዳነት የሚያስፈጅ መሆኑ ሊረሳ የማይችል ትዝብት ውስጥ ይከታል። በተለይ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ደጋፊ ነን የሚሉ እራሳቸውን በዘውግ/በሔርተኝነት አጥረው እነሱን ከሚመስሉ ጋር ህብረት ፈጥረው ፣ ለፈጠሩት ህብረት ዘብ የሚቆሙ የጎሳ ፖለቲካ አራማጆች ናቸው። ይህ ከሆነ ደግሞ እነሱ እንደሚሉት ለዘረኛነት የሚቀረበው ማነው ?! ሌላው ደግሞ ለእኛ ለኢትዮጵያዊን በታሪካችን እንደ ሃገር ለባንዳነት ማን ይቀርብ ነበር ?! መልሱ ቀላል ነው። ነገር ግን ከትላንት የጋራ ታሪካችን በጎውን ነገር በይበልጥ አጎልብተን ፣ ስህተት የነበረውን ትምህርት ወስደንበት ዛሬ ላይ ተሽለን መገኘት የሁላችንም የጋራ ኃላፊነት ነው። ዘረኝነትን በመጠየፍ ፣ከዚህ ቆሻሻ ሃስተሳሰብ በመጽዳት የተሻለ ሆኖ መገኘት ለሥጋም ለነብስም እረፍት
ነው።

እባካችሁን ! እናተ የዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ደጋፊ ነን ባዮች፣ የሁላችንም በሆነችው ሃገራችን ላይ ዘረኝነትን በይፋ በማወጅ አንዱን ከሌላው ጋር ለመለያየት እና ለመከፋፈል መጥፎ መርዛቸውን አትርጩ ! ዶ/ር ቴዎድሮስ እንዳይመረጡ በአብዛኛው የሚደረገው ተቃውሞ በሥራቸው እንጂ ‘በብሔራቸው’ እንዳልሆነ ግልጽ ነው። ምን አልባት የእሳቸውን ‘ብሔር’ መሠረተ አድርጉ የሚቃወም ቢኖሩ አዎ ለእኔ ያ ሰው ዘረኛ ነው።
ለዘረኛ ደግሞ ‘ተክላይ’ ሲሆን የሚወገዝ፣ ‘ከበደ’ ከሆነ ደግሞ የሚወደስበት ምን አይነት የተለየ ሚዛን የለም።ሁለቱም ቆሻሻ የሆነውን ዘረኝነት መነሻ በማድረጋቸው ሊመከሩ ተዉ ይሄ ነገር አይጠቅምም ሊባሉ ይገባል። ምክር አልሰማ ያሉ እንደሆነ “ጨው ለራስ ስትል ጣፍጥ አለበለዚያ….” መባሉ ለምን ሆነና ። ወደ ጉዳያችን ስመለስ ዶ/ር ቴዎድሮስ እንዳይመረጡ መቃወም አንዳንዶቹ እንደ ሚሉት ‘መርህ’ አልባ አይደለም ! የዜጎች ሰብዓዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብት መሠረት ያደረገ ነው። ይህ ደግሞ ተቃውሞው እውነተኛ ‘መርህ’ እንዳለው ማሳያ ነው። መርህ ሲያምች የምንቀበለው ሣይሆን ሲቀር የምንተወው ተራ ነገር አይደለም። መርህ መሰረታዊ የሆነውን ሃቅ የሚደግፍ እንጂ በፍጹም የሚጻረር አይደለም፣ መርህ ፍርደ ገምድልነትን አይቀበለም ። መርህ አንድን ነገር ከሌላው
ተመዝኖ የሚደገፍበት ትክክለኛ ሚዛን ነው።

ሃሳቤን ሳጠቃልል ኢትዮጵያዊ ማንነት ክፍ አድርገን በኢትዮጵያዊነታችን እንድመቅ ፣ በጎሳ(በብሔር)
መከፋፈሉ ይብቃ! ከዚህ ቀደም እንደገለጽኩት ዘረኝነትን አጥብቄ እቃወማለሁ! እኔ በግሌ የሰው ወገን የሆን ሁሉ አንድ ነን ብዬ አምናለሁ ! የራሴን ምክንያታዊ ሃሳብ ለማቅረብ ወይም የሌላውን ሃሳብ በአመክንዮአዊ አመለካከት ለመሞገት፤ እኔ እና የእኔ ቤተሰቦች የምንናገረው ቋንቋ ፣ የምንከተለው ሐይማኖት፣እንዲሁም የቆዳ ቀለማችን ፈጽሞ መመዘኛ አይሆነኝም። አንድን ሰው በሃሳቡ ወይም በሥራው ለመቃወም ሆነ ለመደገፍ የነገሩ ጠቃሚነት ወይም ጎጂነት ብቻ መስፈርቱ ሆኖ ያገለግለኛል ። ዘረኝነት “ከቀለም ወይም ከዝርያ ልዩነት የተነሣ ራስን የተሻለ አድርጎ በመገመት ሌላውን መናቅ መጨቆን የበታች አድርጎ ማየት” እንደሆነ ይነገርለታል፤እንዲህ አይነቱ አጸያፊ ነገር የምጠየፈው ቆሻሻ ነው። ግን ! ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ለWHO የሚያደርጉት የምረጡኝ ዘመቻ መርህን መሰረት በማድረግ በምክንያት መቃወም “ባንዳ እና ዘረኛ ” ካስባለ አጋጣሚው መልካም ነው ። አዎ እሳቸው ለWHO የሚያደርጉት የምረጡኝ ዘመቻ እኔ አልደግፍም !

(ይድነቃቸው ከበደ)

Sunday, May 21, 2017

የዉሸት የኢትዮጵያዊነት ፖለቲካ -(ምላሽ ለአቶ ኤፍሬም ማዴቦ) #ግርማ_ካሳ



የግንቦት ሰባት አመራር አቶ ኤፍሬም ማዴቦ የጻፉትን አንድ ጽሁፍ አነበብኩ። በአውስትራሊያ አካባቢ ስላደረጉት ጉብኝት የተወሰኑ ነገሮችን ጀባ ብለዉናል። ምን ያህል አሮፕላን ላይ ላይ እንደቆዩ፣ አቀባበሉ እንዴት እንደነበረ ወዘተረፈ ጽፈዋል። ብዙም እዚያ ላይ አላተኩሩም።
በጽሁፋቸው ወደ መጨረሻ አካባቢ አንዳንድ ያስገረመኝ ሀሳቦችን መወርወር ጀመሩ። ስለኢትዮጵያዊነት የጻፉት ልቤን ማረከው። “ትላልቅ የኢትዮጵያዊነት እሴቶች ተረስተዉ በአንዳንድ የፖለቲካ መድረኮች ላይ በአገር መዉደድ ስም ብሄረተኝነት እየተሰበከ ነዉ። ይህ አደገኛ ስብከት አገራችን የምትገኝበትን ሁኔታ በሚገባ ካለመረዳት፥ ከግድ የለሽነት፥ ለራስ ጥቅም ከመቆምና አገር ወዳድነትንና ብሄረተኛነትን ለያይቶ ካለማየት የሚመጣ በግዜ ካልታከሙት የማይድን በሽታ ነዉ” ሲሉ የዘረኝነትን መጠፎ ገጽታ ለማሳየት ሞክረዋል። የጻፉትን ሳነብ እኔ የጻፍኩት እስኪመስለኝ ድረስ “ትክክል ነው” እያልኩ ነበር ያነበብኩት።
“ብዙም አልቆየም፣ ወረድ ብዬ ጽሁፉን ማንበቤንን ስቀጥል “አይ አቶ ኤፍሬምና ግንቦት ሰባቶች” አልኩኝ። በጥሩ ጀመረው ነገሩን አበላሹት። የዘረኝነትን መጥፎነት በመናገር ጀምረው የለየለት ዘረኛ ሆኑብኝ።
አቶ ኤፍሬም ከሌላው ማህበረሰብ ነጥለው፣ በአማራ ስም በተደራጁትና የአማራ ብሄረተኝነት አቀንቃኝ በሆኑት ላይ ላይ ጠንካራና የሰላ ትችት ነው ያቀረቡት። “ከቅርብ ግዜ ጀምሮ በኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረኮች ላይ መሰማት የጀመረ አንድ እጅግ በጣም አደገኛ የሆነ ስብከት አለ . . እሱም የ“አማራዉ አማራ ሆኖ መደራጀት የአማራንም የኢትዮጵያንም ነፃነት ያፋጥናል” የሚለዉ ምንም አይነት መሠረት የሌለዉ ስብከት ነዉ” ይላሉ አቶ ኤፍሬም ። ሲያጠቃልሉም “ እዉነቱን እንናገር ከተባለ የአማራዉ በዘር መደራጀት በአንድ በኩል ህወሓት ከተቃዋሚዉ ጎራ የሚፈልገዉ ትልቁ ስጦታ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ የአማራዉ በዘር መደራጀት ኢትዮጵያ ከተጋረጡባት አደጋዎች ሁሉ ትልቁ ነዉ። ለዚህም ይመስለኛል የአማራዉን በዘር መደራጀት ከማንም በላይ አብዝቶ የሚኮንነዉ አማራዉ እራሱ የሆነዉ” ሲሉ በአማራ ስም መደራጀቱ ኮንነዋል።
ትችቱ ባልከፋ ነበር። በአማራ ስም በመደራጀቱ ዙሪያ ያለኝ አመለካከት የታወቀ ነው። ኦሮሞ፣ ትግሬ በሚል ስም መደራጀቱ ጥቅም እንደሌለው ስገልጽ እንደነበረው፣ አማራ ብሎ መደራጀቱ እንደማይመቸኝም በማስቀመጥ ደጋግሜ ጦምሪያለሁ። እንደ አገር የሚያዋጣን ትግሬ፣ አማራ፣ ኦሮሞ መባባል ሳይሆን ዘርና ቀለም ሳንለይ እንደ ኢትዮጵያዊ በአንድ ላይ መያይዝ እንደሆነና ፣ አሁን ያለው በዘር ላይ የተመሰረተ አወቃቀር መቀየር እንዳለበት ጽፊያለሁ።
አቶ ኤፍሬም ማዴቦና ድርጅታቸው ግንቦት ሰባት፣ በገሃድ ያሳዩን ነገር ቢኖር ግን አማራ ለሚባለው ማህበረሰብ አንድ መለኪያ፣ ለሌላው ደግሞ ሌላ መለኪያ እንዳላቸው ነው። ፈረንጆች double standards የሚሉት ማለት ነው። በአንድ ወገን ከለየላቸው በዘር ከተደራጁ ፣ ያዉም መገንጠልን ሲያቀንቅኑ ከነበሩ፣ ምን አልባትም አሁንም በልባቸው ከሚያቀነቅኑ፣ ድርጅቶች ጋር ጥምረት እየፈጠሩ፣ ዉሏቸው ሙሉ ለሙሉ ከነርሱ ጋር ሆኖ፣ አሁን ያለውን በዘር የተዋቀረ ፌዴራሊዝምን እየተቀበሉ፣ ኢትዮጵያዊነትን ሊሰብኩን መሞከራቸው ግብዝነታቸውን ነው የሚያሳየው። “ኦሮሞ ነን፣ ትግሬ ነን፣ ሶማሌ ነን፣ ሲዳማ ነን፣ አፋር ነን…” እያሉ ሌሎች በዘር ከተደራጁ ድርጅርቶች ጋር አብረው እየሰሩ፣ አማራ የሚባለው ማህበረሰብ ሲደራጅ ወደ ወገዛ መሄዳቸው አንደኛ ሰዎቹ መርህ የለሽ መሆናቸውን የሚያሳይ ሲሆን ሁለተኛ ጠባቸው ዘረኝነቱ ላይ ሳይሆን አማራ በሚባለው ማህበርሰብ ላይ እንደሆነ በግልጽ የሚያሳይ ነው።
በኔ እይታ፣ “ኢትዮጵያዊነት ነው አላማችን” ብለን ፣ በዘር የተደራጁ ሌሎቹን (ኦዴፍ፣ ኦነግ፣ ኦብነግ፣ ደሚት…) እያባበልን፣ በአማራ ስም የተደራጁት ላይ ጦርነት ማወጅ በራሱ ዘረኝነት ነው። በነገራችን ላይ አንዳንድ የአማራ ብሄረተኞች “ግንቦት ሰባት የአማራው ጠላት ነው” ብለው መጻፋቸው ትክክል ነበር ማለት ነው።
እርግጥ ነው አማራ የሚባለው ማህበረሰብ ኢትዮጵያዊነት ልቡ ዉስጥ ነው። ሆኖም ይሀ ማሀብረሰብ እኮ በአማራ ስም መደራጀት የጀመረው ወዶ ሳይሆን ተገዶ ነው። የሕልዉና ጉዳይ ሆኖበት ነው። “አማራ” እየተባለ የዘር ማጽዳት ወንጀል ሲፈጸመብት፣ አገር በዘር ተሸንሽና መሬቱ ሲወሰድበት፣ ለመኖር የግድ “ራሳችንን ማደራጀት አለብን” ብለው ተነሱ። የአማራ ማህበረሰብን ጥያቄ ባስተናገደ መልኩ ፣ ይሄን ማህበረሰብ ፣በማሳመን እና በማግባባት እንደ ድሮው በኢትዮጵያዊነት ማእቀፍ ውስጥ ትግሉን እንዲቀጥል ማግባባት ሲገባ፣ ዳግማዊ ሕወሃት በመሆን ይሄንን ማህበረሰብ በአደባባይ ነጥሎ መዝለፍ ነዉር ብቻ ሳይሆን አደርባይነት ነው።
ኢትዮጵያዊነት ማለት ሁሉንም በእኩል ማየት ማለት ነው። ከወቀሱ ሁሉንም፣ ከደገፉም ሁሉንም ነው። እንጅ እየለየን ለጊዜው የፖለቲካ ትርፍ ስለምናገኝበት ብቻ፣ ተመሳሳይ አካሄድ ያላቸውን ድርጅቶች፣ የተወሰኑትን ነቅፈን ሌሎችን ከደገፍን ኢትዮጵያዊነት ፖለቲካች የዉሸት ነው ማለት ነው።
በኔ እይታ ግንቦት ሰባት በኢትዮጵያዊነት ላይ የተንሸዋረረ አመለካከት ያለው በጣም አደገኛ የሆነ ድርጅት ነው። በብዙ መስፈርቶች ከሕወሃት ጋር የሚመሳሰል።
1. ሕወሃት ነጥሎ አንድን ማህበረሰብ(አማራ የሚባለውን) ያጠቃ እንደነበረ፣ ግንቦት ሰባትም ልክ እንደ ሕወሃት ይሄንኑ የአገራችን ማህበረሰብ ክፍል ነጥሎ እያጠቃና እየኮነነ ነው።
2. ሕወሃት ስልጣን ሲጨብጥ አጋፋሪዎቹ በሙሉ በዘር የተደራጁ ድርጅቶች እንደነበሩ፣ አሁንም ግንቦት ሰባት አጋፋሪዎቹ ሁሉም በዘር የተደራጁ ናቸው። (ደሚት፣ ኦዴፍ፣ የሲዳማ የአፋር ፣ ሰሞኑን ደግሞ የኦጋዴን ነጻ አውጭ ….)
3. ሕወሃት በዘር የተደራጁ ድርጅቶችን ሲሰበስብ፣ በአማራ ስም የተደራጀ ድርጅት እንዳልነበረ ፣ አሁንም ግንቦት ሰባት ሌሎች ዘሮች ሲሰበስብ በአማራ ስር ከተደራጁ ጋር ግን፣ እንኳን ሊሰራ እንደ ጠላት ነው የሚመለከታቸው። ( በቅርቡ ግንቦት ሰባትና ሶስት የዘር ድርጅቶች አቋቋሙት በተባለው ንቅናቄ እንደ ሞሬሽ ያሉ ድርጅቶች ተጠይቀው በዉይይቱ ለመሳተፍ ፍቃደኛ ሆነው የነበሩ ቢሆንም፣ ግንቦት ሰባት እነርሱ መኖር የለባቸውም በማለቱ የንቅናቄው አካል ሊሆኑ አልቻሉም)
4. ሕወሃት በሻእቢያ ይታገዝ እንደነበረው አሁንም ግንቦት ሰባት በሻእቢያ ቀሚስ ስር ቁጭ ብላ ቆሎና ፍርፋሪ እየተወረወረለት፣ ድርጅታዊ ነጻነቱን ተነፍጎ ያለ ድርጅት ነው።
5. ሕወሃት ስልጣን ከመጨበጡ በፊት ብዙ ተስፋ ለህዝብ ይሰጥ ነበር። ዴሞክራሲ እንደሚኖር ቃል ገብቶ ነበር። ግንቦት ሰባትም ልክ እንደ ሕወሃት ብዙ የተስፋ ቃል እየሰጠ ነው።
6. ሕወሃት አገሪቷ በዘር እንድትከፋፈል ያደረገ ነው። ግንቦት ሰባትም አሁን ያለው በዘር ላይ የተዋቀረ ፌዴራሊዝም እንዲቀጥል የሚፈለግ ነው።
7. ሕወሃት ኢትዮጵያን ወደብ አልባ ያደረገ፣ አሰብ የኤርትራ ናት የሚል አቋም ያለው ነው ። የግንቦት ሰባት አመራሮች ግን በቅንጅት ጊዜ ኢትዮጵያ የባህር በር ያስፈልጋታል የሚለውን አቋማቸዉን ትተወ፣ 180 ዲግሪ የፖለቲካ ጂምናስቲክ ሰርተው፣ የኢትዮጵያን የባህር አልባነት አምነው የተቀበሉ ናቸው።
8. ሕወሃት ሚስጥራዊ ድርጅት ነው። በውሸትና በሽፍጥ የተሞላ። የሚቆጣጠረዉንም ሜዲያ ለተራ የፕሮፖጋንዳ ፍጆታ የሚጠቀምበት። ግንቦት ሰባትም ግልጽነትና ተጠያቂነት የሌለበት፣ ኦዲት ተደርጎ የማያውቅ፣ አመራሮቹ የሚዋሹ፣ እንደ ኢሳት፣ ኢካዴፍ ያሉ ሜዲያዎችን በመጠቀም ተራ ፕሮፖጋንዳ የሚረጭ ድርጅት ነው።
እርግጥ ነው ሕወሃት እና ግንቦት ሰባት በጣም የሚለያቸው አንድ ነገር አለ። እርሱም ፣ ሕወሃቶች የወሬ ሰው አልነበሩም። ነፍጥ አንስተው፣ በየበረሃው በኮንጎ ጫማ ሜዳ ተራራዉን እያቋረጡ እየሞቱ፣ እየቆሰሉ፣ ተዋግተው ነው ደርግን የጣሉት። እነ ስዬ አብርሃ፣ እነ ጻድቃን ፣ እነ ሳሞራ፣ እነ አርከበ ..ሁሉም በረሃ ነበሩ። ግንቦት ስባቶች ግን በጎንደር በጎበዝ አለቃ የተደራጁ ወገኖች በአንዳንድ ቦታዎች የሚያደርጉትን ዉጊያ እየጠቀሱ “ግንቦት ሰባት ይሄን አደረገ “ከማለት ዉጭ፣ ያደረጉት ነገር የለም። መሪዎቻቸውም የት እንዳሉ፣ የት እንደሚኖሩ አገር ሁሉ የሚያወቀው ነው።
ታዲያ ከላይ በተጠቅሱት መስፈርቶች ግንቦት ሰባት ዳግማዊ ህወሃት ቢባል ስህተት ነውን ?
አበቃሁ !!!!

Saturday, May 20, 2017

የብሔር ፖለቲካ ጡዘት ከሰውነት እስከ አውሬነት ያደርሳል! -ስዩም ተሾመ



የሌላ ሀገር ዜጋን እየወደድን የሌላ ብሔር ተወላጅን እንጠላለን!
ስዩም ተሾመ
ስዩም ተሾመ
እስኪ አንድ ኢትዮጲያዊን ዝም ብላችሁ ታዘቡት። ወደ ቤተ-እምነት ሲሄድ “የሰው-ልጅ በአምላክ አምሳል የተፈጠረ ነው። ሰዎች እርስ-በእርስ ተዋደዱ፣ ጠላትህን እንደ ራስህ ውደድ፣…ወዘተ” የሚለውን ሃይማኖታዊ አስተምህሮት “አሜን” ይቀበላል። ወደ ትምህርት ቤት ሲሄድ ደግሞ ስለ ሰው ልጆች እኩልነት ይማራል። በሁሉም የትምህርት ደረጃ የታሪክና የሲቪክ መማሪያ መፅሃፍት ውስጥ በጥቁር-አሜሪካዊያን ላይ ስለደረሰው ባርነትና የጉልበት ብዝበዛ፣ በአፓርታይድ አገዛዝ ወቅት በጥቁር ደቡብ አፍሪካዊያን ላይ ስለተፈፀመው የዘር መድሎና ጭቆና፣…ወዘተ በሰፊው ያስተምራሉ። የግል ሆነ የመንግስት ሚዲያ ተቋማት ዘወትር “ዘር-ቀለም ሳንለይል…” እያሉ ዘወትር ይዘምራሉ።
አብዛኛው ኢትዮጲያዊ በተለያዩ የዓለም ሀገራት የቀድሞ ታሪክ ወይም ወቅታዊ ፖለቲካ በሰዎች ላይ ስለሚፈፀም የዘረኝነት መድልዎና መገለል፣ አስተዳደራዊ በደልና ጭቆና፣ ፖለቲካዊ እስራትና ግድያ፣…ወዘተ በየሚዲያው ይሰማል፣ በየትምህርት ቤቱ ይማራል፣ እርስ-በእርሱ ይወያያል፣ በጋራ ያወግዛል። በጦርነቶች ወይም በሽብር ጥቃቶች በሰዎች ላይ የሞትና አካል ጉዳቶች ሲደርሱ ሰብዓዊ ርህራሄ ይሰማዋል። ከማንም ቀድሞ ለተጎዱ ወገኖች የተሰማውን “ጥልቅ ሃዘን” በይፋ ይገልፃል።
ከዚህ በተጨማሪ፣ እያንዳንዱ ኢትዮጲያዊ በሀገሪቱ የቀድሞ ታሪክ ወይም በወቅታዊ ፖለቲካ አማካኝነት በዜጎች ላይ ስለተፈፀሙ በደሎች፣ ጭቆናዎች፣ አድልዎች፣ ግድያና እስራቶች ከቤተሰብ ወይም ከቅርብ ወዳጆቹ ጋር በግልፅ ይነጋገራል፥ ይወያያል፣ ይግባባል። በሌሎች ሰዎች ላይ የተፈፀሙ ታሪካዊና ፖለቲካዊ በደሎችና ጭቆናዎች በቤተሰቡ አባላት ወይም በወዳጆቹ ላይ እንዲፈፀም አይሻም።
እስካሁን ድረስ እንደተመለከትነው፣ አብዛኛው ኢትዮጲያዊ ለእሱ ቅርብ ከሆኑት የቤተሰብ አባላት ወይም ወዳጆች እና ሩቅ ካሉት የሌላ ሀገር ዜጎች ጋር ያለው ግንኙነትና አመለካከት በዋናነት በበጎ አመለካከትና በሰብዓዊነት የታነፀ ነው። ነገር ግን፣ ስለ ራሱ ሀገር የቀድሞ ታሪክና ወቅታዊ ፖለቲካ ውይይት ሲጀምር በአንድ ግዜ አቅሉን ይስታል። ስለኢትዮጲያ የቀድሞ ታሪክ ሆነ አሁን ስላለው ፖለቲካዊ ስርዓት የሚደረገው ውይይት ወዲያው “አማራ፣ ኦሮሞ፣ “ትግሬ”፣ ጉራጌ፣ ወላይታ፣ ሱማሌ፣….” እየተባባሉ መደናቆር ይጀመራል።
ታሪካዊ በደልና ጭቆና ወይም ፖለቲካዊ እስራትና ሞት በሌላ ሀገር ዜጋ ወይም በቤተሰባችን አባል ላይ ሲደርስ የነበረን ሰብዓዊነት እዚሁ ለሌላ ብሔር ተወላጅ የሀገራችን ዜጎች ሲሆን ከውስጣችን እንደ ጉም በኖ ይጠፋል። ለውጪ ሀገር ዜጋ የነበረን ሰብዓዊ አመለካከት ለሌላ ብሄር ተወላጅ ሲሆን ወደ ፖለቲካ ይቀየራል።
ለምሳሌ፣ ባለፈው አመት አንድ ወዳጄ “በጎንደር የሚኖሩ የትግራይ ብሔር ተወላጆች ከመኖሪያ ቄያቸው ተፈናቀሉ” በሚል አምርሮ ሲቃወም ነበር። በሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሪፖርት መሰረት በአማራ፣ ኦሮሚያና በደቡብ ክልል ከአራት ወር ባነሰ ግዜ ውስጥ 669 ሰዎች መገደላቸው ስነግረው “እነዚህ ፋብሪካ ለማቃጠል የወጡ ወንጀለኞች ናቸው” አለኝ። ይሄው ሰው ግን፣ ባለፈው በለንደን ከተማ በተፈፀመ የሽብር ጥቃት አንዲት የፓርላማ አባል መገደሏን እንደሰማ ጥቃቱን በማውገዝ ለተጎጂዎችና ለቤተሰቦቻቸው የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን ሲገልፅ ማንም አልቀደመውም። ታዲያ ይህ ወዳጄ ለውጪ ሀገር ዜጋ የነበረውን ሰብዓዊ አመለካከት ለሌላ ብሔር ተወላጅ ሲሆን በአንዴ ወደ ፖለቲካ ለምን ቀየረ?
በተመሣሣይ ስለ ሀገራችን የቀድሞ ታሪክና ወቅታዊ ፖለቲካ ሁኔታ ከውጪ ሀገር ዜጎች ጋር መወያያት እየቻልን የሌላ ብሔር ተወላጅ ከሆነ ኢትዮጲያዊ ዜጋ ጋር ግን መግባባት ቀርቶ መደማመጥ አንኳን አይቻልም። ለምሳሌ፣ ባለፈው ሳምንት ከአንድ ኢጣሊያናዊትና ኤርትራዊት ጋር ለመወያያት እድሉ ገጥሞኝ ነበር። ከኢጣላናዊቷ ጋር ስለ አደዋ ጦርነትና አፄ ሚኒሊክ በመግባባት ላይ የተመሰረተ ውይይት አድረገን። በተመሣሣይ፣ ከኤርትራዊቷ ጋር በኤርትራና በኢትዮጲያ ስላለው ፖለቲካዊ ሁኔታ በግልፅ ተወያየን። ወደ ሀገሬ ስመጣ ግን ስለ ኢትዮጲያ የቀድሞ ታሪክ ሆነ ስለ ወቅታዊ ፖለቲካ በግልፅ መወያያት አይቻልም። ስለ አደዋና አፄ ሚኒሊክ ከኢጣሊያን ዜጋ ጋር መወያያት ከቻልኩ ከአንድ የኦሮሞ ብሔር ተወላጅ ጋር መወያያትና መግባባት የሚሳነኝ ለምንድነው? ከኤርትራዊቷ ጋር ያደረኩትን ግልፅ ውይይት ከአንድ የትግራይ ተወላጅ ጋር ማድረግ የሚከብደኝ ለምንድነው? ከሌላ ሀገር ዜጋ የነበረን ግልፅ ውይይት ከሌላ ብሔር ተወላጅ ጋር ሲሆን በጭፍን ጥላቻ መደናቆር የሚሆነው ለምንድነው?
በአጠቃላይ፣ ከሌላ ሀገር ዜጋ ጋር በግልፅ እየተወያየን ከሌላ ብሔር ተወላጅ ጋር እንኮራረፋለን። ለሌላ ሀገር ዜጋ የነበረን ስብዓዊነት ለሌላ ብሔር ተወላጅ ሲሆን ፖለቲካ ይሆናል። የሌላ ሀገር ዜጋን እየወደድን የሌላ ብሔር ተወላጅን እንጠላለን። በቤተሰባችን አባላት ላይ ቀርቶ በሌላ ሀገር ዜጋ ላይ እንኳን እንዲደርስ የማንፈልገውን መጥፎ ነገር በሌላ ብሔር ተወላጅ ላይ ለማድረስ እንዝታለን። ለመሆኑ ለኢትዮጲያዊ ከሌላ ሀገር ዜጋ እና ከሀገሩ ልጅ ማን ይቀርበዋል?
የ“እኛ” እና “እነሱ” ፖለቲካ፡ ከሰብዓዊነት እስከ አውሬነት
የሰው-ልጅ እርስ-በእርሱ የሚያደርገው ማህበራዊ ግንኙነት እና አንቅስቃሴ በዋናነት “እኛ” እና “እነሱ” በሚል እሳቤ ላይ የተመሰረተ ነው። በቋንቋ አጠቃቀማችን እና ትምህርት አሰጣጣችን መሰረት እያንዳንዱ ሰው ራሱን “እኛ” በሚል የቡድን እሳቤ ውስጥ ነው የሚመለከተው። ሌሎችን ደግሞ “እነሱ” በሚል የተፃራሪ ቡድን አባል አድርጎ የመመልከት ዝንባሌ አለ። ከዚህ በተጨማሪ፣ ይህ “እኛ” እና “እነሱ” የሚለው እሳቤ እንደ ሁኔታ የሚለያይ ነው። ለምሳሌ፣ “እኛ” ኢትዮጲያዊያን ከሆንን “እነሱ” ኢጣሊያዊያን፣ እንግሊዛዊያን፣ ኤርትራዊያን፣…ወዘተ፤ “እኛ” ኦሮሞ ከሆንን “እነሱ” አማራ፣ “ትግሬ”፣ ጉራጌ፣…ወዘተ፤ “እኛ” የአበበ ቤተሰቦች ከሆንን “እነሱ” የጫላ ቤተሰቦች፣ የሃጎስ ቤተሰቦች፣…ወዘተ ሊሆኑ ይችላሉ። በአጠቃላይ፣ “እኛ” እና “እነሱ” የሚለውን እሳቤ እንደ ሁኔታው በቤተሰብ፣ ብሔርና ሀገር ደረጃ ከፋፍሎ ማየት ይቻላል።
በሦስቱም ደረጃ “እኛ” እና “እነሱ” የሚለው አመለካከት የሚወሰነው በመካከላችን ካለው ግንኙነት አንፃር ነው። በዚህ መሰረት፣ ለአንድ ኢትዮጲያዊ የኢጣሊያኖችን ሃሳብና እንቅስቃሴ ማወቅና መገመት ከባድ ነው። ነገር ግን፣ የሁለቱ ሀገር ዜጎች በኢትዮጲያዊው ማህበራዊ ሕይወትና የዕለት-ከእለት እንቅስቃሴ ላይ ያላቸው ተፅዕኖ ውስን ነው። የኦሮሞዎች ሕይወት ከሌሎች ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ሃሳብና እንቅስቃሴ ጋር የተቆራኘ ስለሆነ አብዛኛው የኦሮሞ ሕዝብ ስለ አማራ፣ ትግራይ ወይም ጉራጌ ብሔር ተወላጆች ሃሳብና እንቅስቃሴ ማወቅና መገመት ይፈልጋል። ይሁን እንጂ፣ ሁሉም የኦሮሞ ብሔር ተወላጅ ከማንም በፊት የቤተሰቡንና የቅርብ ወዳጆቹን ሃሳብና እንቅስቃሴ በትክክል ማወቅና መገመት አለበት።
እያንዳንዱ ኢትዮጲያዊ በሕይወቱ ውስጥ ቀጥተኛ ግንኘነትና ተፅዕኖ ስላላቸው ቤተሰቦቹና የቅርብ ወዳጆቹ ሃሳብና እንቅስቃሴ በእርግጠኝነት ማወቅ ይችላል። እያንዳንዱ ኢትዮጲያዊ የቤተሰቡ አባላት ወይም የቅርብ ወዳጆቹ ከሆኑት “እነሱዎች” ጋር በቃላሉ መነጋገርና መግባባት ይችላል። ማህበራዊ ግንኙነቱም በውይይትና ሰብዓዊነት ላይ የተመሰረተ ይሆናል። ነገር ግን፣ እያንዳንዱ ኢትዮጲያዊ ስለ ሌላ ሀገር ዜጎች ሃሳብና እንቅስቃሴ በእርግጠኝነት ማወቅ አይችልም። ይሁን እንጂ፣ የውጪ ሀገር ዜጎች ከእሱ ጋር ያላቸው ግንኙነትና በዕለት-ከእለት ሕይወቱ ውስጥ ያላቸው ተፅዕኖ ውስን ነው። ስለዚህ፣ ሩቅ ያሉ የሌላ ሀገር ዜጎች “እነሱዎች” ጥሩ ሥራና ምግባር እንዳላቸው ይገምታል።
“Edmund Leach” የተባለው ምሁር፣ ቅርብ ባሉት “እነሱዎች” እና ሩቅ ባሉት “እነሱዎች” መካከል ሌላ ሦስተኛ “እነሱዎች” እንዳሉ ይገልፃል። እንደ እሱ አገላለፅ፣ ብዙውን ግዜ ሰዎች ስለ ከሦስተኛው “እነሱዎች” ጋር ያላቸው ግንኙነት በውይይት ላይ ያልተመሰረተና ለሌሎች ያላቸው አመለካከት ሰብዓዊነት የጎደለው ነው፡-
“But lying in between the remote Heavenly other and the close predictable other there is a third category which arouses quite a different kind of emotion. This is the other which is close at hand but unreliable. If anything in my immediate vicinity is out of my control, that thing becomes a source of fear. This is true of persons as well as objects. If Mr X is someone with whom I cannot communicate, then he is out of my control, and I begin to treat him as a wild animal rather than a fellow human being. He becomes a brute. His presence then generates anxiety, but his Jack of humanity releases me from all moral restraint: the triggered responses which might deter me from violence against my own kind no longer apply.” REITH LECTURES 1967: A Runaway World, Lecture 3: Ourselves and Others: 26 November 1967 – Radio 4
ከውጪ ሀገር ዜጋ ጋር በግልፅ መወያየትና መግባባት እንችላለን። ከእነሱ ጋር መወያየትና መግባባት ባንችል እንኳን የእነሱ ሃሳብና እንቅስቃሴ በእኛ ሕይወት ላይ የሚኖረው ተፅዕኖ ዝቅተኛ ስለሆነ ይህን ያህል አሳሳቢ አይደለም። ሆኖም ግን፣ በአንድ ሀገር ውስጥ አብረን እየኖርን እርስ-በእርስ መነጋገርና መግባባት ከተሳነን፤ የጠበቀ ማህበራዊ፥ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ግንኙነት እያለን አንዳችን የሌላችንን ሃሳብና እንቅስቃሴ ማወቅና መገመት ከተሳነን፣ እንደ ሰው ያለን ምክንያታዊ አስተሳሰብ ብቻ ሳይሆን ሰብዓዊ አመለካከታችን ከውስጣችን ይጠፋል። ከቤተሰቦቻችንና ጓደኞቻችን፣ ከጎጥ፣ ቀበሌ፣ ወረዳ፣ ዞንና ክልል ነዋሪዎች ጋራ የነበረን በውይይትና ምክንያታዊ ግንዛቤ ላይ የተመሰረተ አመለካከት፣ እንደ ሰው የነበረው ሰብዓዊነት ለሌላ ክልል ነዋሪዎች ወይም ብሔር ተወላጆች ሲሆን ከውስጣችን ተሟጥጦ ይጠፋል።
የሌላ ሀገር ዜጋን እንደ ሰብዓዊ ፍጡር እያየ፣ የሌላ ብሔር ተወላጅን ግን እንደ ዱር አውሬ አድኖ መግደል ይሻል። በእርግጥ ለአንዳንዶቻችሁ አገላለፁ በጣም የተጋነነ ሊመስላችሁ ይችላል። ነገር ግን፣ የራሱን ዝርያ እንደ አውሬ ወይም ጠላት አድኖ የሚገድል ፍጡር ቢኖር የሰው ልጅ ብቻ ነው። በጣም ውስን በሆኑ አጋጣሚዎች ካልሆነ በስተቀር ሌሎች እንስሳት የሚያድኑትና የሚገድሉት ሌላ የእንስሳት ዝርያን ነው። እንደ “Edmund Leach” አገላለፅ፣ የራሱን ዝርያ እንደ አውሬ ማደንና መግደል የሚሻው የሰው-ልጅ ብቻ ሲሆን ይህም

የዲሲ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን በሐራጅ የመሸጥ አደጋ ገጥሟታል

   


በዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ውስጥ የምትገኘውን ርዕሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በፍቅረ ንዋይ ያበዱ ካህናት በምዕመናን የተመረጠውን ህጋዊ የአስተዳደር ቦርድ (ሰበካ ጉባኤ) በአድማና በአመጽ ከተቆጣጠሩ ሁለት ዓመት ሊሞላቸው ነው። በአሁን ሰዓት ይህችን ቤተክርስቲያን በቁጥጥራቸው ስር ያደረጉ ለእግዚያብሔርንም ሆነ ለሰው ህግ የማይገዙ ጩሉሌዎች በጫካ ህግ በመጠቀም ሰብረው በመግባት የያዙትን በምዕመናን አንጡራ ሃብት የተገዛ ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚሰበስቡትን ገንዘብ በደሞዝና በተለያየ መንገድ ተከፋፍለው በማመናመን ለመንግሥት መከፈል የሚገባቸውን ግብር መክፈል ተስኗቸው ቤተክርስቲያኗን ከፍተኛ አደጋ ውስጥ ዳርገዋታል። አንዳንድ ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ምዕመናን እንደሚናገሩት ከሆነ በአሁኑ ጊዜ ዋሽንግተን ከተማ ውስጥ ለህንጻ ግንባታ የሚሆን ቦታ እጥረት ስላለ፣ ለመንግሥት የሚገባውን ግብር ባለመክፈል ቤተክርስቲያኗን በሃራጅ አሽጠው ገንዘቡን ለመቀራመት ነው ይላሉ።
በየሳምንቱ እሁድና በተለያየ ጊዜ ከምዕመናን የሚሰበስቡት በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በወቅቱ ግብር ሳይከፍሉ በመቅረታቸው መንግስት ለቤተክርስቲያኑ ማስጠንቀቂያ ማውጣቱ በአጠቃላይ በአሜሪካ ውስጥ ለሚገኙ የኢ/ተ/ተ/ቤ/ክ ምዕመናን እጅግ አሳፋሪና አንገት የሚያስደፋ ድርጊት ነው። በውንብድና ከሥልጣን የተወገደው ህጋዊው ቦርድ የቤተክርስቲያኑን አስተዳደር በአጥጋቢ ሁኔታ ሲያካሂድና የመንግሥትንም ግብር በወቅቱ ሲከፍል እንደነበር የሚታወቅ ነው።  በተለይ እንደ ዶክተር አክሊሉ ሐብቴ፣ አቶ ቢልልኝ ማንደፍሮና ሌሎችም አንቱ የተባሉና የኢትዮጵያ ሕዝብ አስተምሮ ለከፍተኛ ሥልጣንና ክብር ያበቃቸው ግለሰቦች እንዴት እንደዚህ ዓይነት ወራዳ ድርጊት ውስጥ እንደገቡ ብዙዎችን ግራ ያጋባ ጉዳይ ነው። እ.አ.አ. መስከረም 27 ቀን 2015 “በዶክተር አክሊሉ ሐብቴ የሚመሩት ጋጠወጦች የተዘጋ ቤተክርስቲያን ሰብረው ገቡ”በሚል ርዕሰ ተጠናቅሮ የነበረው ዜና ጉዳዩን ለማስታወስ ያህል እዚህ ላይ አቅርበንላችኋል። http://www.mereja.com/amharic/468218
የግብር አለመክፈል ጉዳይን አስመልክቶ የቤተክርስቲያኒቷ ህጋዊ የአሥተዳደር ቦርድ ያወጣውን መግለጫ ከዚህ በታች ይመልከቱ።
ከርዕስአድባራትደብረ ስላም ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ህጋዊ የባለአደራዎች ቦርድ የተሰጠ መግለጫ
ግንቦት ፲፩ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም./ MAY 19, 2017
ሰሞኑን በዋሽንግተን ዲሲ የመንግሥት ግበር ሰብሳቢ ጽሐፈት ቤት (IRS) በ1350 BUCHANN ST WASHINGTON DC  የምትገኘዋ የርዕሰ አድባራት ደብረሰላም ቅድስት ማርያም  ቤተክርስቲያን የንብረት ግብር (TAX) ለሦስት ተከታታይ ክፈያ ባለመከፈሉ የወጣውን እጅግ አስደንጋጭና አሳሳቢ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተመልክተነዋል። ምንም እንኳን ከተመክሯችን እንዲህ ዓይነቱ ነገር መከሰቱ የለመድነው ቢሆንም በጥቂት ራስ ወዳድና ኃላፊነት በጎደላቸው ግለሰቦች ምክንያት መላ ምዕመኑ ለ27 ዓመታት ባደረገው ያልተቋረጠ ድካምና መስዋዕትነት ለባለንብረትነት ያደረሳት ቤተ ክርስቲያን ለእንዲህ ዓይነቱ አደጋ ስትጋለጥ ማየት እንደማንኛውም ኃላፊነት የሚሰማው ወገን በእጅጉ አሳስቦናል።
ህግ በህገ ወጦች ተሽሮ፣ ፍቅርና ሰላም በራስ ወዳዶችና በረብሸኞች ታውኮ ፣ የተከበረው የቤተ ክርስቲያናችን አውደ ምህረት በጥቂት ካህናት አጋፋሪነት  በተነሳው አምባጓሮ ረክሶ፣ በብዙ ድካም የተገነባውን አድነታችን ልዩ ተልዕኮ ባላቸው ግለሰቦችና ቡድኖች እንዲበተን ተደርጎ፤ ህጋዊውን የባለ አደራዎች ቦርድ በጫካ ህግ አፍርሰውና እርስ በርስ ተመራርጠው የተዘጋ ቤተ ክርስቲያንን ሰብረው ገብተው ቤተ ክርስቲያኗን በጉልበት ከተቆጣጠሩት እነሆ 2 ዓምት ሊሞላቸው ጥቂት ወራት ነው የቀራቸው። በዚህ ጊዜ ውስጥ ከሚሊዮን ዶላር በላይ መሰብሰባቸውን ያወጁ ሲሆን ይህን የተጠየቀውን 40ሺ የማይሞላ የንብረት ግብር ለመክፈል አቅሙ እያላቸው እስከዛሬ ቀን ድረስ አለመክፈላቸው እጅግ ግራ ከማግባቱ ባሻገር ቤተ ክርስቲያናችን ምን ያህል ኃላፊነት በማይሰማቸውና ለሕዝበ ክርስቲያኑ ግድ በሌላቸው ግለሰቦች እጅ መውደቋ ከመቼውም ጊዜ በላይ ዛሬ ግልጽ ሆኗል።
ለመንግሥት የሚገባውን መክፈል እንደሚገባ በዓለማዊውም ሆነ በመንፋሳዊው እሳቤ ተገቢ መሆኑን የሚያጣው ስለማይኖር አለማወቅ እንዳልሆነ ለክርክር የሚቀርብ ጉዳይ አይደለም። አቅሙ ኑሮ ሁሉም ነገር ተመቻችቶ እያለ ለሦስት ተከታታይ ጊዜ የመንግሥትን ግብር አለመክፈልና የቤተ ክርስቲያናችንን ህልውና ለአደጋ ማጋለጥ፤ የቤተ ክርስቲያኗ ኃላፊዎች ነን ባዮች ንዝህላልነትና ቸልተኝነት ብቻ ነው ብሎ የሚታለፍ ሳይሆን፤ እነኝህ ግለሰቦች ምን ያህል ኃላፊነት የማይሰማቸው እንደሆኑና በራሳቸው ጥቅም ላይ ብቻ ያተኮሩ፣ ነገንና ትውልድን የማያስቡ፣ እምነታቸውን ለጊዚያዊና ለሥጋዊ ፍላጎታቸው መጠቀሚያ ከማድረግ አልፈው ለቤተ ክርስቲያኗ ምንም ራዕይ እንደሌላቸው የሚያረጋግጥ ክስተት ነው።  እንደዚህ ዓይነቱን ኃላፊነት የጎደለው ድርጊት ስናይ ለእኛ አዲስ አይደለም ትናንትም የሆነና  ወደፊትም ከዚህ በከፋ መልኩ የምናየው እንደሆነ እንገነዘባለን።  የተከበረችውን ታላቋን ደብራችን ለብዙዎች መመኪያና መጠጊያ ፣ ለታዳጊ ህፃናቶቻችን ተስፋ እንዳልነበረች ሁሉ ርካሽ ጥቅምና አሳፋሪ ተልዕኮን ለማሳካት ሲባል ያደረሱት በደል ቀላል እንዳልነበረ በከፍተኛ ቁጭትና ኃዘን የምናስታውሰው ነው።
ዛሬ ቤተ ክርስቲያኗን በሕገ ወጥ መንገድ ተቆጣጥረው በሳምንት 10ሺ ዶላር እያሰባሰቡና በሰበብ አስባቡ ምዕመናንን ያለማቋረጥ ተጨማሪ ገንዘብ እየለመኑ ባሉበት ሰዓት ይህንን ዋጋው እጅግ በጣም ትንሽ ነገር ግን አስፈላጊነቱ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ኃላፊነት መወጣት አቅቷቸው የቤተ ክርስቲያኗን አጠቃላይ ንብረት ለአደጋ ሊጋለጥ ቀን እየቆጣረ መሆኑን መስማት እጅጉን ያስደነግጣል። ገንዘብ ማሰባሰብ የዘወትር ሥራቸው ያደረጉት እነኝህ ግለሰቦች ግድግዳ እየቀባቡ ምዕመኑን ከመሸንገልና ምንም ዕርባናና ዋጋ ከሌለው መሞካሸትና መሸላለም በፊት እንዲህ ዓይነቱን ኃላፊነት መወጣት እንደሚገባ ማወቅ ነበረባቸው። ባለቀ ሰዓት ተነስቶ የሚደረግ ሽር ጉድ ጥንካሬን ሳይሆን ድክመትን ፣ ብስለትን ሳይሆን እርባና የለሽነትን፣ ኃላፊነትን ሳይሆን መረን የለቀቀ ግድየለሽነትንና ንቅዘትን ከማሳየት ሌላ ምንም ትርጉም የለውም።
ህጋዊው የባለአደራዎች ቦርድ ቤተ ክርስቲያኗን በሚያስተዳድርበት ወቅት እነሱ ሰበሰብን ከሚሉት ገንዘብ ያነሰ እየሰበሰበ፣ አገልጋይ ካህናቶችን ከየትኛውም ቤተ ክርስቲያን በተሻለ እየተንከባከበና ሁሉንም ኃላፊነቶችን በብቃት እየተወጣ የቤተ ክርስቲያኗን ዘላቂ ህልም  ለማሳካት ለህንፃ ማሰሪያ የሚሆን ብዙ ሚሊዮን ዶላር ተቀማጭ በማድረግ ይታወቃል።  ይህም በግልጽ በቤተ ክርስቲያኗ ድረ ገጽ WWW.DSKMARIAM.ORG ላይ የተቀመጠ በመሆኑ ማንም ሰው ሊያየውና ሊገነዘበው የሚችል ሀቅ ነው። ህጋዊው የባለ አደራዎች ቦርድ የህዝቡን ፍቅርና አመኔታ በንፁህ ሥራው  ያረጋገጠ ነበር እንጂ ዛሬ እንደምናየው ርካሽ በሆነ ጊዜያዊ ድለላ ወይንም የልጅ ሥራ በሚመስል የልደታ ድግስ አልነበረም።
በመጨረሻም 40ሺ ዶላር ለማይሞላ የመንግሥት ዕዳ ከ15ሚልዮን ዶላር በላይ የሚያወጣው  የቤተ ክርስቲያኗ ንብረት አደጋ ላይ እንዲወድቅ ማድረግ እጅግ አሳፋሪ፣ ምንም አመክንዮ የሌለውና ኃላፊነት የጎደለው ተግባር በመሆኑ ህጋዊው የባለ አደራዎች ቦርድ በጥብቅ ያወግዘዋል። እነኝህ ኃላፊነት የጎደላቸው አካላት ምንም ዓይነት ሰበብ ሳይደረድሩ ዛሬውኑ ይህንን ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ በጥብቅ እናሳስባለን። ማንኛውም ከህዝብ የሚሰበሰበው ዶላር በቀጥታ ለህዝብ ጠቀሜታ መዋል እንዳለበት እያስገነዘብን በዚህ ሳቢያ በቤተ ክርስቲያናችን ላይ ለሚደርሰውን ጉዳት ህጋዊ የባለ አደራዎች ቦርዱ በህግ እንደሚጠይቅ በአፅንዖት ያሳስባል።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
የርዕሰ አድባራት ደብራ ስላም ቅድስት ማርያም የባለአደራዎች ቦርድ

ዶክተር ደብረጽዮን ካለመንግስት ይሁንታ ቴዲ አፍሮን ቃለምልልስ እንዲደረግ ያደረጉ የኢቢሲ ሠራተኞች እንዲቀጡ አዘዙ




(ዘ-ሐበሻ) የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ካለመንግስት ኃላፊዎች እውቅና እና ይሁንታ ከቴዲ አፍሮ ጋር ቃለምልልስ ያደረጉ የኢቢሲ ሠራተኞች ላይ እርምጃ እንዲወሰድ መመሪያ አስተላለፉ::
የዘ-ሐበሻ ምንጮች እንዳስታወቁት ትናንት ሕወሓቱ ዶክተር ደብረጽዮን የኢቢሲን አስተዳደሮች በቴዲ አፍሮ ቃለምልልስ ዙሪያ ስብሰባ የተቀመጡ ሲሆን አርቲስቱን ቃለምልልስ እንዲደረግ ማን እንደፈቀደ እንዲመረመር አዘዋል:: ካለባለስልጣናት ይሁንታ ቃለምልልሱ መደረጉና ቃለምልልሱ ሳይተላለፍ በፊት ማስታወቂያ መለጠፉና በኋላም አለመተላለፉ መንግስትን አሳጥቶታል ያሉት ዶክተር ደብረጽዮን ቴዲ ቃለምልልስ ባይደረግ ኖሮ ይህ ሁሉ ውዥንበር አይፈጠርም ነበር ሲሉ በቁጣ መናገራቸውን ምንጮች ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል::
ደብረጽዮን ትናንት የኢቢሲን ማኔጅመንት የሰበሰቡት የመዝናኛ ክፍሉ ኃላፊ; ማስታወቂያውን በፌሰቡክና ዩቱብ በለቀቀው ሠራተኛና በጋዘጠኛ ብሩክ ላይ ቅጣት እንዲፈጸም ለማወጅ የነበረ ሲሆን ቃለምልልሱን ያደረገው ጋዜጠኛ ቀድሞ የሥራ መልቀቂያ በማስገባቱ ዶክተር ደብረጽዮን ምስጢር የሚያሾልክ አለ ማለት ነው በሚል በማኔጅመንቱ ላይ መጮሃቸውን ምንጮች አስታውቀዋል::

Friday, May 19, 2017

ተመራማሪ የሺወንድም ማሙዬ ከጎንደር የመጣ ዘመድ አሳድረሃል በሚል በማዕከላዊ እየተሰቃየ ነው፤



ሙሉቀን ተስፋው
አገዛዙ የዐማራ ወጣቶችን፣ ምሁራንና ፖለቲከኞችን በግፍ ማሰር ቀጥሎበታል፡፡ በየትኛውም አካባቢ የሚኖሩ የዐማራ ተወላጆች ሰበብ አስባብ እየተፈለገ በጂምላ እየታሠሩ በማዕከላዊ የቶርቸር ሰለባ ሆነዋል፡፡
ወጣቱ ምሁር የሺወንድም ማሙዬ በወያኔ የቶርቸር ሰለባ ከሆኑ የዐማራ ምሁራን አንዱ ነው፡፡ ጥር 12 ቀን 2009 ዓ.ም ጠዋት ከቤተ ክርስቲያን ደርሶ ሲመለስ በትግሬ ደኅንነቶች ተይዞ ወደ ማዕከላዊ ከገባ አራት ወራት አልፈውታል፡፡ ከአራት ጊዜ በላይ ፍርድ ቤት ቀርቧል፤ እስካሁን በማዕከላዊ ቶርቸር እየተፈጸመበት ነው፡፡
ተመራማሪ የሺወንድም ማሙዬ በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ በሜዲካል ቴክኖሎጅ የትምህርት ዘርፍ በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ የተመረቀ ሲሆን በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒዬም ሜዲካል ኮሌጅ ዲን በመሆን ያገለግል ነበር፡፡ የሺወንድም በበርካታ ዓለም አቀፍ የትምህርት ጆርናሎች ላይ ጥናታዊ ጽሑፎችን ያሳተመ ሲሆን በአሜሪካን አገር ከሚገኘው ሚቺጋን ዩንቨርሲቲ ጋር በመተባበር አንድ ለአገር የሚጠቅም ጥናት በማጠናቀቅ ላይ ነበር፡፡ ወጣቱ ተመራማሪ ወደ አሜሪካን ተጉዞ በሚቺጋን ዩንቨርሲቲ ጥናቱን ያቀረበ ሲሆን መጠናቀቅ የሚገባቸውን ጉዳዮች ለመጨረስ ወደ አገር ቤት በተመለሰ በ15ኛ ቀኑ ወደ ማዕከላዊ ገብቶ የቶርቸር ሰለባ የሆነው፡፡
ወጣቱ ተመራማሪ በማዕከላዊ ቀርቦበት የነበረው ክስ ‹‹ለዐማራ ታጋዮች የዩንቨርሲቲ ምግብ እንዲያገኙ አድርገሃል›› የሚል ቢሆንም የሺወንድም የተማሪዎች ዲን እንጅ የምግብ ክፍል ኃላፊ አለመሆኑን በማስረዳቱ ክሱም እንደማያስኬድ ሲታወቅ የክስ ጭብጡ ተቀይሯል፡፡ በተቀየረው ክስ ‹‹ከጎንደር የመጣ አሸባሪ አሳድረሃል›› በሚል አዲስ ፋይል ተከፍቶበት በቶርቸር መካከል ፍርድ ቤት እንደሚመላለስ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ወጣት ተመራማሪው የሺወንድም ከጎንደር የመጣ አብሮ አደግ መምህር ጓደኛውን የጥምቀት ዕለት አግኝቶት ከቤቱ አብረው ያደሩ ሲሆን መምህር ጓደኛውም እስካሁን አብሮ በማዕከላዊ በስቅይት ላይ ነው፡፡ የሺወንድምን ከእናቱ፣ ከእህቱና ከባለቤቱ ውጭ ማንም ሰው መጠየቅ አይችልም፡፡ በአራት ወራት ውስጥ በአማራነቱ ብዙ ስቃይና ሥነ ልቦናዊ ጉዳት ደርሶበታል፡፡ ከሚችጋን ዪንቨርሲቲ ጋር እየሠራው የነበረው ጥናታዊ ጽሑፍም ተቋርጧል፡፡

Thursday, May 18, 2017

በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒዬም ሜዲካል ኮሌጅ ዲን በማዕከላዊ እየተሰቃየ ነው



ተመራማሪ የሺወንድም ሹምዬ ከጎንደር የመጣ ዘመድ አሳድረሃል በሚል በማዕከላዊ እየተሰቃየ ነው፤ Brannamedia

አገዛዙ የዐማራ ወጣቶችን፣ ምሁራንና ፖለቲከኞችን በግፍ ማሰር ቀጥሎበታል፡፡ በየትኛውም አካባቢ የሚኖሩ የዐማራ ተወላጆች ሰበብ አስባብ እየተፈለገ በጂምላ እየታሠሩ በማዕከላዊ የቶርቸር ሰለባ ሆነዋል፡፡
ወጣቱ ምሁር የሺወንድም ሹምዬ በወያኔ የቶርቸር ሰለባ ከሆኑ የዐማራ ምሁራን አንዱ ነው፡፡ ጥር 12 ቀን 2009 ዓ.ም ጠዋት ከቤተ ክርስቲያን ደርሶ ሲመለስ በትግሬ ደኅንነቶች ተይዞ ወደ ማዕከላዊ ከገባ አራት ወራት አልፈውታል፡፡ ከአራት ጊዜ በላይ ፍርድ ቤት ቀርቧል፤ እስካሁን በማዕከላዊ ቶርቸር እየተፈጸመበት ነው፡፡
ተመራማሪ የሺወንድም ሹምዬ በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ በሜዲካል ቴክኖሎጅ የትምህርት ዘርፍ በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ የተመረቀ ሲሆን በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒዬም ሜዲካል ኮሌጅ ዲን በመሆን ያገለግል ነበር፡፡ የሺወንድም በበርካታ ዓለም አቀፍ የትምህርት ጆርናሎች ላይ ጥናታዊ ጽሑፎችን ያሳተመ ሲሆን  በአሜሪካን አገር ከሚገኘው ሚቺጋን ዩንቨርሲቲ ጋር በመተባበር አንድ ለአገር የሚጠቅም ጥናት በማጠናቀቅ ላይ ነበር፡፡ ወጣቱ ተመራማሪ ወደ አሜሪካን ተጉዞ በሚቺጋን ዩንቨርሲቲ ጥናቱን ያቀረበ ሲሆን መጠናቀቅ የሚገባቸውን ጉዳዮች ለመጨረስ ወደ አገር ቤት በተመለሰ በ15ኛ ቀኑ ወደ ማዕከላዊ ገብቶ የቶርቸር ሰለባ የሆነው፡፡
ወጣቱ ተመራማሪ በማዕከላዊ ቀርቦበት የነበረው ክስ ‹‹ለዐማራ ታጋዮች የዩንቨርሲቲ ምግብ እንዲያገኙ አድርገሃል›› የሚል ቢሆንም የሺወንድም የተማሪዎች ዲን እንጅ የምግብ ክፍል ኃላፊ አለመሆኑን በማስረዳቱ ክሱም እንደማያስኬድ ሲታወቅ የክስ ጭብጡ ተቀይሯል፡፡ በተቀየረው ክስ ‹‹ከጎንደር የመጣ አሸባሪ አሳድረሃል›› በሚል አዲስ ፋይል ተከፍቶበት በቶርቸር መካከል ፍርድ ቤት እንደሚመላለስ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ወጣት ተመራማሪው የሺወንድም ከጎንደር የመጣ አብሮ አደግ መምህር ጓደኛውን የጥምቀት ዕለት አግኝቶት ከቤቱ አብረው ያደሩ ሲሆን መምህር ጓደኛውም እስካሁን አብሮ በማዕከላዊ በስቅይት ላይ ነው፡፡ የሺወንድምን ከእናቱ፣ ከእህቱና ከባለቤቱ ውጭ ማንም ሰው መጠየቅ አይችልም፡፡ በአራት ወራት ውስጥ በአማራነቱ ብዙ ስቃይና ሥነ ልቦናዊ ጉዳት ደርሶበታል፡፡ ከሚችጋን ዪንቨርሲቲ ጋር እየሠራው የነበረው ጥናታዊ ጽሑፍም ተቋርጧል፡፡

ወያኔ በአዲስ አበባ ታክሲወች ላይ ያቀደው አደገኛ ሴራ ሲጋለጥ! – አስናቀው አበበ


By ሳተናውMay 18, 2017 06:47





 4  547  551
የግል ትምህርት ቤቶች የስለላ መዋቅር እየተዘረጋላቸው ነው
አዲስ የገንዘብ ማካበቻ ዘዴ ነው
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ባለስልጣን ቢሮ የከተማዋን ባለታክሲዎች ከስራ ውጪ ለማድረግ ያሴረው ውጥን እንደሚከተለው ነው…
የአ.አ. ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ባለስልጣን ቢሮ ከሚያዝያ 2009 ዓ.ም የመጨረሻ ሳምንት ጀምሮ እስከ 04/09/2009 ዓ.ም ድረስ በአጠቃላይ ለአፀደ ህፃናት እና ለ1ኛ/ደ/(ከ1-8) ት/ቤቶች በክፍያ ወደ ት/ቤት ለመሄድ እና ለመመለስ የተማሪዎች ትራንስፖርት ሰርቪስ/አገልግሎት እሰጣለሁ ብሏል፡፡ ለዚህም የፍላጎት መረጃ/Need assessment /ቅፅ ለሁሉም ት/ቤቶች በትኖ የተሞላውን መረጃ አሰባስቦ በቀጥታ ወደ ስራ እንደሚገባ ለየት/ቤቶች አሳውቋል፡፡ ይህ ድብቅና በተለይም ሁሉም የግል ት/ቤቶች ከተማሪ ወላጆች ጋር ስለፍላጎታቸው በቅርበት ያልተወያዩበት ጉዳይ መሆኑን ታውቆ ዋናው አላማውም የሚከተሉት ናቸው፡-
፨፨ መንግስት ገበያውን በብቸኝነት እና በበላይነት ተቆጣጥሮ በመቀጠል የእለት ኑሮአቸው እና ገቢያቸው ለተማሪዎች የትራንስፖርት ግልጋሎት በመስጠት የሚተዳደሩትን ባለታክሲዎች ሆን ተብሎ ለመጎድት
፨፨የከተማዋን ባለታክሲዎች በተለይም በአገልግሎት ቆይታቸው አርጅተዋል ተብለው ነገር ግን በአጭር ርቀትም ቢሆን እየሰሩ ያሉትን እና ሌሎችንም በትራንስፖርት ስምሪት ምድብ ውስጥ ገብተው መደበኛ አገልግሎት እየሰጡ
በተጨማሪ የእለት ኑሮን ለማሸነፍ ሲባል ጥዋትና ማታ ተማሪዎችን በኩንትራት ታክሲ የሚያመላልሱትን ከገበያ ለማስወጣት
፨፨ እንዲሁም በአሁኑ ሰዓት ወያኔ ተተኪ ትውሉዱን በሚፈልገው የሪወት አለም ቅኝት እንዲራመድ በመንግስት ት/ቤቶች ሙሉ ለሙሉ በሚባል ሁኔታ በየት/ቤቱ አንድ፡አንድ የአደረጃጀት ርዕሰ መ/ር ተብሎ ቅጥር በመፈፀም ዋና ተግባራቸው የድርጅት አባል ከመምህራን ፡ከአስተዳደር ሰራተኛውና ከተማሪዎች በመመልመል ርስበርስ አስተሳስሮ እንዲማቅቅ ያደረጉበትን ዘዴ ጠቀሜታ ስለሚያውቁት፡ነገር ግን በግል ት/ቤቶች ምንም አይነት መሠል መዋቅሮችን ስለማይከተሉ እና አመፅ ይኖራል ብሎ ስለሚያስብ፡የተማሪውን ስሜት፡ውሎና አቅጣጫ በቀላሉ ለመከታተል
፨፨ ወያኔ እያጣ የመጣውን የገንዘብ ገቢ መጠን ልክ በነጋዴው ማህበረሰብ ያለጥናት አዲስ የግብር ተመን ጥሎ ለመሠብሰብ ከሚኳትነው ተጨማሪ ዘዴም ነው ተብሏል፡፡
ለዘውትር አምደኛ ሪፖርተር እናመሰግናለን!
አስናቀው አበበ

ተስፋዬ ገ/አብ “የሚዲያ ያለህ” እያለ ነው!



ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
  • ለተስፋዬ ዕድል መስጠት ሬዲዮ RTLM መሆን ነው
የኢትዮጵያ ስም ሲጠራ፣ ከፍ ከፍ ሲል “የዘር ወባው” የሚነሳበት ተስፋዬ ገ/አብ አሜሪካ ገብቶ የሚያናግረው ሚዲያ በማጣቱ “በሚዲያ ረሃብ” እየተሰቃየ መሆኑ ተሰምቷል፡፡ በክፉም ይሁን በመልካም ከሚዲያ መገለል የማይወደው ተስፋዬ “ሻዕቢያን የሚያጋልጥ መጽሐፍ ጽፌአለሁና አናግሩኝ” እያለ በዳያስፖራ ያሉትን ሚዲያ እየለመነ፣ በራቸውን እያንኳኳ መሆኑ ተነግሯል – በተለይ የተንቀሳቃሽ ምስልና (TV and YouTube) የሬዲዮን፡፡ ዛጎል እንደዘገበው ከሆነ እስካሁን ዕድሉን የሰጠው የለም፡፡
ተስፋዬ ከዚህ በፊት እየጻፈ የሚያወጣቸው መጣጥፎች እንደዱሮው ተነባቢነት ካጡ ሰነባብተዋል፡፡ የኦሮሞም ጽንፈኞችም እንደፈለጉ ሲጠቀሙበትና እሱም በተራው ሲጠቀምባቸው ቆይቶ አሁን ከእርሱ “የተሻሉ” አግኝተው ትተውታል፡፡ በርካታ እርሱን የሚተኩ በዘረኝነት የተከተቡ የኦሮሞ ጽንፈኞች (ያውም እንደ ተስፋዬ “ሰልባጅ” ሳይሆኑ ኦሪጂናል ዘረኞች ስለተገኙ)፤ ሚዲያውንም እስከሚበቃቸው ስለተቆጣጠሩትና እርሱ የሚመጻደቅበትን ኦሮሚኛ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ያደረጉ በመሆናቸው ተስፋዬ “አሮጌ ስልቻ” ሆኗል፡፡ ከዚህም አልፎ ከአማርኛ ጋር ጨምረው ተስፋዬ ሲናገርም ሆነ ሲነገር የሚነስረውን እንግሊዝኛ አቀላጥፈው የሚያንበለብሉ በመሆናቸው ባሁኑ ጊዜ የተስፋዬ ዋጋ የተመጠጠ ሸንኮራ ወይም ፊልተሩ የቀረ የተጨሰ ሲጋራ ሆኗል፡፡ ከሁሉም በላይ የሚያሳዝነው ግን ዘመን ተገልብጦ አሁን የሚዲያ ባለቤት ሲሆኑ “ዝምታቸውን” አስጩኾ “የጡት ጉማጅ” ሃውልት ባለቤት ያደረጋቸውን “ወዳጅ” መዘንጋታቸው ነው፡፡
ተስፋዬ ግን ሞራል የሌለው በመሆኑ የትም ቢጠራ፣ የትም ተናገር ቢባል፣ … ያደርገዋል፡፡ ዓላማው የውይይት አጀንዳ መሆን ነው፡፡ በተለይ ሰሞኑን በድምጻዊ ቴዲ አፍሮ ኢትዮጵያዊነት አዲስ ቀለም አበጅቶ የአበባው ሕብረቀለማዊነት መታየት ስለጀመረ ይህንን ማፍረስ የተስፋዬ ተቀዳሚ ዓላማ እንደሚሆን የበፊት ታሪኩን መመልከት ብቻ በቂ ይሆናል፡፡
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ለተስፋዬ ዕድል ሰጥቶ ቃለምልልስ የሚያደርግለትን ሚዲያ የሩዋንዳውን ፍጅት እንዲቀጣጠል ካደረገው ሬዲዮ RTLM (Radio Télévision Libre des Mille Collines) ለይቶ እንደማያይ ግልጽ በሆነ ቋንቋ ለማስቀመጥ ይወዳል፡፡
በሩዋንዳ በተካሄደው የዘር ማጥፋት (ጄኖሳይ) በዋንኛነት ከሚጠቀሱት መካከል የሚዲያውን ኃይል በመጠቀም RTLM (Radio Télévision Libre des Mille Collines) በተሰኘው የሬዲዮ ማሰራጫ አማካኝነት የተነዛው የዘር ጥላቻ ተጠቃሽ ነው፡፡ ይህንን ተግባር ሲፈጽሙና ሁቱዎች በቱትሲዎች ላይ እንዲነሱ ያደረገውና ቱትሲዎችን “በረሮ” (“cockroaches”)  እያለ በመጥራት “እንዲገደሉ” በሬዲዮው አማካኝነት “ትዕዛዝ” ሲሰጥ የነበረው ፌሊሲዬን ካቡጋ (Félicien Kabuga) ዋነኛ ተጠቃሽ ነው፡፡ የሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ በሩዋንዳ ዘር ማጥፋት ዙሪያ ባደረገው ጥናት ካቡጋ እና የሬዲዮ ጣቢያው ልፈፋ ለ51ሺህ ሰዎች መገደል ቀጥተኛ ተጠያቂ አድርጓል፡፡ ይህም በአጠቃላይ ከተጨፈጨፉት ሰዎች ውስጥ 10በመቶ መሆኑን ጥናቱ ጠቁሟል፡፡
ተስፋዬ ማለት ካቡጋ ነው! መጽሐፎቹና መጣጥፎቹም RTLM ሬዲዮ ናቸው፡፡ ተስፋዬ በሚዲያ ረሃብ ጠውልጎ መሞት አለበት፡፡ ይልቅ የጻፋቸው መጽሐፎችና ያወጣቸው መጣጥፎች ለዜጎች መጨራረስ ምክንያት እንደሆኑ የራሱን ማስረጃዎች በመጥቀስ ለፍርድ የሚቀርብበት ሁኔታ ቢመቻች ነው ለአገርና ሕዝብ የሚበጀው፡፡ አሜሪካ ለዚህ ዓይነት ሕጋዊ አሠራር የተመቻቸች አገር ናት፤ በቅንጅት መንቀሳቀስ ብቻ ነው የሚያስፈልገው፡፡ ምናልባትም ወደ አሜሪካ መምጣቱ ሳያውቀው በአንገቱ ላይ ገመዱን እያጠበቀ እንዳይሆን! የመናገር ነጻነት ማለት ከተጠያቂነት ነጻ መሆን ማለት አይደለም!
ዛጎል ያወጣው ዜና እንዲህ ይነበባል፡፡
ኢትዮጵያዊነት ሲነሳ – ተስፋዬም ተነሳ
ተስፋዬ ሲያትል ግብቶ የሚዲያ ረሃብተኛ ሆነ!!
የጋዜጠኛ ማስታወሻ የሚለውንና “የግል የሚለውን ማስታወሻ” ገጣጥሞ ለንባብ ካበቃ በኋላ ዲያስፖራው አንግሶት ነበር። በፓልቶክ፣ በሬዲዮ፣ በ“ቲቪ/ዩቲብ” … በተለያዩ ሚዲያ አክተር ሆኖ ሙገሳ ጠግቧል። “የቡርቃ ዝምታ” በሚለው የፍጅት አቀጣጣይ መጽሃፉ ጥርስ የነከሱበት ከጅምሩ ቢቃወሙትም የሚሰማቸው አልነበረም። በኢትዮጵያኖች ሚዲያ፣ ኢትዮጵያ ላይ መርዝ እየረጨ ሲጨበጭብለት ያበዱ፣ የተቃጥሉና የተሟገቱ ብዙ ብለው እንደነበርና የሃሳብ መለያየት እስከሚከሰት ድረስ ግጭት ተነስቶም ነበር።
በደጋፊዎቹና ከልብ በሚጠሉት መካከል ያለውን ፍትጊያ “ኦሮሞን” በመንተራስና ግንቦት ሰባትን በ“መደገፍ” ያለፈው ተስፋዬ ገብረአብ (ገብረ እባብ አንዳንዶች እንደሚጠሩት)፣ በስደት ከሚኖርበት ኔዘርላንድስ የወጣበት መረጃ ሊስተባበል በማይችል መልኩ ከሚዲያና እንዳሻው ከሚዘንጥበት ማህበራዊ ገጾች ገፍትሮ እንደወረወረው በጊዜው ብዙ ተብሎበታል። የአሁኑ አመጣጡ ደግሞ ኢትዮጵያዊነት ሲነሳ መሆኑ አነጋግሪ ሆኗል።
በተለይም ከኤርትራው መሪ ኢሳያስ አፈወርቅ ጋር የሚያደርጋቸውን የጽሁፍ ምልልሶች ኮፒ በማደረግ የኔዘርላንዱ ነዋሪ ይፋ ካደረገው በኋላ፣ ካለፈው የቡርቃ ዝምታ መጽሃፉ ጋር ተያይዞ ሊከሰስ እንደሚገባው የሚጠይቁ ተነስተውበት ነበር። እነዚህን ሰዎች ጠቅሶ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ “ተስፋዬ ማለት ካቡጋ ነው፤ የቡርቃ ዝምታ ደግሞ የካቡጋ ሬዲዮ RTLM ነው” ብሏል። አያይዞም ያነጋገራቸውን ጠቅሶ “ሆላንዳዊው” ተስፋዬ እንደ ካቡጋ “ወደ አባት አገር” በመሄድ ከመሸሸጉ በፊት ውጤታማ ሥራ መሰራት ያለበት አሁን ነው ይላሉ” ሲል ዘግቦ “አክትቪስት ነን” ለሚሉት ሁሉ ህዝብን ለፍጅት በማነሳሳት ወንጀል እንዲከሰስ አሳስቦ ነበር። እንደተባለው ይሁን በሌላ ምክንያት ተስፋዬ አገሩ ገብቶ የኢንተርኔት ሱቅ በመክፈት ሲሰራ እንደነበር ከዚያው አካባቢ የመጡና የሚያውቁት ይናገራሉ። ተስፋዬ አስመራ እያለም ከሕገወጥ የሰው ዝውውር (human trafficking) ጋር በተያያዘ ታስሮ እንደነበርም ስለጉዳዩ የሚያውቁ አመልክተዋል።
ተስፋዬ በአሁኑ ሰዓት አሜሪካ ሲያትል ይገኛል። እዚያም ብዙ እንደሚቆይ ከመናገሩ ውጪ ከሻዕቢያ ጋር ስለመለያየቱ ያለው ነገር የለም። ይልቁኑም አሁን እያሳተመ ያለው ታሪክ የሻቢያን “ምስጢር” የሚያጋልጥ እንደሆነ መናገሩን ዜናውን ያቀበሉን ጠቁመዋል። ጥሩ የመጻፍና የመፈጠር ችሎታ ያለውን ተስፋዬን ኮሎኔል ከማል ገልቹ “የተወለድኩባትንና ያደኩባትን አርሲን ከኔ በላይ የሚያውቅ ሆኗል” ሲሉ አስተያየት እንደሰጡበት አይዘነጋም። ተስፋዬ አሁን እያሳተመ ያለው መጽሃፍ እንዲተዋወቅለት የኢትዮጵያኖችን ሚዲያና ለመጠቀም ቢፈልግም እንደፈለገው ሊሳካለት እንዳልቻለ በዚሁ ጉዳይ ያወያያቸው ለዛጎል አመልክተዋል።
ኢሳትን ለማስታወቂያነት ቢመርጥም እንዳልተሳካለት የጠቆሙት ምንጮች፣ ኢሳት ተስፋዬን ቃለ ምልልስ አድርጎ የመጽሃፉን ማስታወቂያ ከሰራ ከፍተኛ ተቃውሞ እንደሚነሳበት ገሃድ በመሆኑ ሊሳካለት እንደማይችል ተናገረዋል። ሌሎች የሚዲያ ተቋማትንም ለማነጋገር የሞከረ ሲሆን አንዳንዶቹ ጥያቄውን አንቀበልም ባይሉም እንደወትሮው እጃቸውን እንዳልዘረጉለት ነው የተሰማው።
በሌላም በኩል ኦነግን ሻቢያ እንዳፈራረሰው ሁሉንም አብጠርጥሮ የተናገረውን ሰናይን ለማስተባበብል ሆን ተብሎ የተዘጋጀና የሻዕቢያን እውቅና ያገኘ መጽሃፍ እንደሆነ ግምት ያላቸውም አሉ። ተስፋዬ ሻዕቢያን ሙሉ በሙሉ የሚያጋልጥ መጽሃፍ ለንባብ ካበቃ፣ የኤርትራን ምድር እንደማይረግጥ ግልጽ በመሆኑ “እመለሳለሁ” ማለቱ በመጽሃፉ ላይ ከወዲሁ ጥርጣሬን ፈጥሯል። ተስፋዬን በወጉ የሚረዱት እንዳሉት “አሁን ወቅቱ ኢትዮጵያዊነት የተነቃቃበት በመሆኑ ሃሳብ ለማስቀየርና ሌላ አጀንዳ ለማስቀመጥ ነው” ባይ ናቸው። በዚሁ መነሻ የሚዲያ ረሃቡን ማጠናከርና ፊት መንሳት አስፈላጊ እንደሆነ ያሰምሩበታል።