Tuesday, October 18, 2016

ሃምሳ ሺህ ሕዝብ ከሚኖርባት ሰበታ በኣስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሽፋን ወደ ኣንድ ሺህ ዜጎች ታፈሱ።


ሃምሳ ሺህ ሕዝብ ከሚኖርባት ሰበታ በኣስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሽፋን ወደ ኣንድ ሺህ ዜጎች ታፈሱ።
የሕወሓት ቃል ኣቀባይ የሆነው ፋና ሚዲያ እንደገለጸው በተቃውሞ ላይ ተሳትፈዋል የተባሉ ከኣዲስ ኣበባ መውጫ ከምትገኘው ሰበታ ከተማ የሚኖሩ ኣንድ ሺህ የሚጠጉ ነዋሪዎች በወያኔ የጸጥታ ሃይል መታፈሳቸውን ተናግሯል። በቅርቡ በሰበታ ከተማ በተደረገ ተቃውሞ የተነሳ በተለያዩ ፋብሪካዎችና ድርጅቶች ላይ እርምጃ ወስደዋል ያላቸውን ነዋሪዎች በጥርጣሬ ታፍሰው እንደተወሰዱ የጁንታው ሚዲያ ገልጿል፤ በዛሬው እለት በኣዲስ ኣበባ የኢንቨስተሮች የሰላም ጉባዬ እየተደረገ እንደሆነ ዘገባው ኣያይዞ ተናግሯል።

No comments:

Post a Comment