የዐማራ የጎበዝ አለቆች ሕብረት ተጋድሎ ወደ ሕዝባዊ ንቅናቄ ሊያድግ ነው፤
በተለያዩ አካባቢዎች ያነጋገርናቸው የጎበዝ አለቆች የወያኔ መንግሥት በዐማራው ሕዝብ ላይ የሚያደርሰው ጥቃት ተጠናክሮ በመቀጠሉ በተበታተነ መልኩ በየአካባቢው ሲደረግ የነበረው ሕዝባዊ ተጋድሎ ድርጅታዊ መዋቅር የያዘ ሕዝባዊ ንቅናቄ ሊሆን ነው ብለዋል፡፡ የጎበዝ አለቆቹ ሕብረት የመሠረቱት የሕዝባዊ ንቅናቄ ትግል በቅርብ ይፋ እንደሚደረግም አክለው ገልጸዋል፡፡
‹‹ወሳኙ›› በመባል የሚታወቀው የጎበዝ አለቃ ‹‹ሕይወታቸውን ለመስጠት ዝግጁ ከሆኑ ወጣቶች ጋር በአንድ ላይ መክረንበታል፡፡ በማንነታችን ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ለመመከት የእኛን መስዋእትነት ይጠይቃል፤ በተለያዩ አካባቢዎች ካሉ የጎበዝ አለቆች ጥምረት ጋር መክረንበታል›› ሲል ዛሬ ጥቅምት 17 ቀን 2009 ዓ.ም. አረጋግጦልናል፡፡ ወሳኙ ያለበትን ቦታ ዕቅድም በድፍረት የተናገረ ቢሆንም ለጥንቃቄ ሲባል ቦታዎቹን ይፋ አለማድረግ መርጠናል፡፡ ‹‹ፈላሻው›› በመባል የሚታወቀው ሌላው የጎበዝ አለቃ ደግሞ ‹‹ወያኔ በዐማራው ላይ እያደረሰው ያለው ጥፋት ምንም ዓይነት መሻሻል አላሳየም፤ የማንነት ጥያቄ ያቀረቡ የወልቃይት ጠገዴ ዐማራ ኮሚቴዎችን ጥያቄያቸውን ከመፍታት ይልቅ እያሳደደ ማሳር ሥራየ ብሎ ይዞታል፡፡ የዐማራ ወጣት ለበለጠው ተጋድሎ መዘጋጀት አለበት፡፡ ሁሉም የዐማራ ወጣት እንደ አንድ መነሳት አለበት፡፡ ወጣቱ ዛሬ ወይም ነገ ለሚደረግ ጥሪ ዝግጁ ሆኖ መጠበቅ አለበት፡፡ ከሕዝባችን ላይ የተጣለውን ጭቆና ለመገርሰስ የእኛ መስዋትነት የግድ ብሏል›› ሲል አብራርቷል፡፡
የጎበዝ አለቆቹ በሰሜን ጎንደር የኮማድ ፖስት የሚባለው የወያኔ አገዛዝ የገበሬውን ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ መፍጠሩንና በርካታ ወጣቶችን ማሰሩን አውስተዋል፡፡ በምስራቅ ጎጃም በጎንቻ ሲሦእነሴ ጉንደወይን ከተማ የሁለት ወያኔዎች ንብረት የሆነ ዓለም ሆቴል የተባለን ለማቃጠል አስባችኋል በሚል ሳጅን ምናሉ የተባለ ቅጥረኛ የዐማራ ወጣችን ዛሬ ማሰሩን የጎበዝ አለቆቹ ጨምረው ተናግረዋል፡፡ ሳጅን ምናሉ እና ተመሳሳይ ወንጅል እየፈጸሙ ያሉ ቅጥረኞች ከዐማራ ሕዝብ ጎን እንዲቆሙም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በባሕር ዳር ዙሪያ ወረዳ የአበባ እርሻ ባለንብረቶች ዐማራ የሆኑ የድርጅቱን ሠራቶች የሁለት ወር ደመወዝ ካለመክፈላቸውም በተጨማሪ ሠራተኞችን ያለ አግባብ ማንገላታታቸው በኋላ የእጃቸውን እንደሚያገኙም አሰጠንቅቀዋል፡፡ የአበባ እርሻ ጥበቃ ሠራተኞች በገበሬዎች ላይ ምንም ዓይነት እርምጃ እንዳይወስዱ አሳስበዋል፡፡
No comments:
Post a Comment