Tuesday, October 31, 2017

ጭቆናን #በጭካኔ ማሸነፍ አይቻልም! — ስዩም ተሾመ

 

እኔ፣ ይህን ስርዓት የምነቅፈው፣ ሥራና አሰራሩን ዘወትር የምተቸው፣… ጠዋት ማታ የምፅፈው፣ የምናገረው፣ የማስበው፣ የዜጎች መብትና ነፃነት እንዲከበር ነው! “የአንድ ወገን የበላይነትና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የብዙሃኑ መብትና ነፃነት መጣስ የለበትም” ብዬ ስለማምን ነው። ይህ የአንዱ ብሔር ደጋፊ፣ የሌላው ብሔር ተቃዋሚ በመሆን ሳይሆን፣ “ሁሉም ሰው እንደ ሰው እኩል መብት፥ ነፃነትና ተጠቃሚነት ይገባዋል” የሚል ፅኑ እምነት ስላለኝ ነው። ነጋ ጠባ “የኦሮሞ ሕዝብ መብት ይከበር!” እያልኩ የምጮኸው የሕግ የበላይነት እንዲሰፍን እንጂ ሰሞኑን በኢሊባቡርና በመቱ፣ ዛሬ ደግሞ በነቀምት እንደሆነው፣ በተለይ የአማራና የትግራይ ተወላጆች መንገድ ላይ ተደፍተው እንዲቀሩ አይደለም።
የኦሮሚያ #አድማ_በተኝና የአከባቢው ፖሊሶች፣ የንፁሃን ዜጎች ሕይወትና ንብረት ሲጠፋ በቅርብ ርቀት ቆመው ሲመለከቱ ማየትን የመሰለ አሳፋሪ ነገር የለም። ይሄ የመጨረሻ ስሜት አልባነት ነው! የሞራል ዝቅጠት ነው! ለኦሮሞ ሕዝብ ሆነ ለክልሉ መንግስት ታላቅ ውርደት ነው! የኦሮሞ ሕዝብ መብትና ነፃነት የሚከበረው በፖለቲካዊ ስልትና የሞራል የበላይነት እንጂ በጭቃኔና ስርዓት-አልበኝነት አይደለም። ጭቆናን በጭካኔ ማሸነፍ አይቻልም።
 

የሰማያዊ ፓርቲ ሕዝባዊ ስብሰባና የባሕር ዳር እሥረኞቹ መለቀቅ


By ሳተናውOctober 30, 2017 16:26

 
የሰማያዊ ፓርቲ ሕዝባዊ ስብሰባ
ሰማያዊ ፓርቲ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከተጣለበት ጊዜ አንስቶ ላለፈው አንድ ዓመት የሚሆን ጊዜ የመጀመሪያዊን ሕዝባዊ ስብሰባ ትናንት አዲስ አበባ ላይ አካሂዷል።
ሰማያዊ ፓርቲ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከተጣለበት ጊዜ አንስቶ ላለፈው አንድ ዓመት የሚሆን ጊዜ የመጀመሪያዊን ሕዝባዊ ስብሰባ ትናንት አዲስ አበባ ላይ አካሂዷል።በመብራት ኃይል አዳራሽ ውስጥ በተካሄደው በዚህ ስብሰባ ላይ ቁጥሩ ከስምንት መቶ ያላነሰ ሰው መገኘቱን የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታነህ ባልቻ ማምሻውን ለቪኤኤ ገልፀዋል።


የፊታችን ዕሁድ፣ መስከረም 26/2010 ዓ.ም ከምኒሊክ አደባባይ ተነስቶ መስቀል አደባባይ ላይ የሚጠናቀቅ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያደርግም ሰማያዊ ፓርቲ አስታውቋል።
በሌላ በኩል ደግሞ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባለፈው ሐሙስ፣ ጥቅምት 16/2010 ዓ.ም. በዋለው ችሎት ባሕር ዳር ከተማ ላይ በነኀሴ 2ዐ1ዐ ዓ.ም. ተካሂዶ ከነበረውና ብዙ ጉዳይት ከደረበት ሰልፍ ጋር ተያይዞ በእሥር ላይ የነበሩ የሰማያዊ ፓርቲ የምዕራብ ጎጃም ዞን፣ በተለይ ደግሞ የፓርቲውን የባሕር ዳር ከተማ መሪዎች በነፃ ማሰናበቱ ታውቋል።
በፓርቲው መሪዎችና አባላት ላይ ለአሥራ አንድ ወራት ያህል ክሥ ሳይመሠረት መቆየቱን ለቪኦኤ የገለፁት የፓርቲው የባሕር ዳር ከተማ ሰብሳቢ አቶ ማሩ ዳኘው እና ምክትላቸው አቶ መልከሙ ታደሰ ክሡ ሲቀርብም ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ ከዕድሜ ልክ እሥራት እስ ሞት የሚያሰቀጣ የወንጀል ክሥ እንደነበር አመልክተዋል።

የትግሬ ነፍስ ከሌላው ይበልጣልን?


By ሳተናውOctober 30, 2017 17:02
    
ሙሉቀን ተስፋው
ሦስት ትግሬዎች ነቀምት ላይ መገደላቸውን ተከትሎ አገር ቁልቢጥ ሆናለች፤ ነገሩ በሦስት የሚቆም ቢሆን ባልከፋ! ገና ከአስቀያሚው ዘመን ዋዜማ ላይ መሆናችን ለፈርዖኖቹ አልታያቸውም፡፡
የኦሮሞን ወጣት በለው ጨርሰው እያለ የትግሬ ወታደር በአምቦ ሲገድል አላወገዙም፤ የዐማራ ስጋ በከማሽ የጅብ ቀለብ ሲሆን የትግሬ እስካልሆነ ድረስ ምንም አይደለም፡፡ በወልቃይትና ጠገዴ ዐማራን ገድለው በመኪና አስከሬን የሚጎትቱ እነዚህ አውሬዎች ዛሬ ሦስት ተጋሩዎች መሞታቸውን ተከትለው አገር ይያዝ ኡኡ እያሉ ነው፡፡ እኔ የማዝነው አንድ አስተዋይ ሽማግሌ በማጣታቸው ነው፤ መጪው ጊዜ የከፋ መሆኑን የሚነግራቸው፡፡
ግብዞቹ በጎንደር የእርቅ ኮንፍረንስ ለማካሔድ አስበናል እያሉን ነው፡፡ የወልቃይትና የራያ ዐማሮች ዐማራነታቸው ሳይከበር ዕርቅ አይደለም ከሚቀጥሉት መቶ ዓመታት በኋላ እንኳ የተገነባው የጥላቻ ግንብ መፍረስ የሚችል አይደለም፡፡ መቼም አይፈርስም! መጪው የዐማራ ትውልድ አባቱንና ወንድሙን ማን እንደገደለበት እርስቱን ማን እንደቀማው ከ‹ሀ ሁ› ፊደል ጋር እኩል እየቆጠረ ያድጋል፡፡ ከዚያ ትውልዱ በራሱ የሚያደርገውን ያውቃል፡፡



በተፈጠረው ችግር የአቶ ኃይለማርያም መንግስት ሥልጣን መልቀቅ ነበረበት – ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ በአገሪቱ ወቅታዊ ችግሮች ዙሪያ


     


• በተፈጠረው ችግር የአቶ ኃይለማርያም መንግስት ሥልጣን መልቀቅ ነበረበት
• በየዞኑና በየወረዳው የሚፈጠረውን ግጭት የሚያነሳሱት ካድሬዎች ናቸው
• ህዝቡ የህግ ጥበቃ ያስፈልገዋል፤ አጥፊዎች በህግ መጠየቅ አለባቸው
• የኢትዮጵያ ህገ መንግስት ዶግማ አይደለም፤መከለስ ይችላል
አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተነሳው ሰላምና መረጋጋት ሰፍኗል በሚል ቢሆንም ግጭቱና አለመረጋጋቱ በየጊዜው እየተባባሰ ነው የመጣው። ለዚህ ምክንያቱ ምን ይመስልዎታል?
ህዝብ ጥያቄዎቹን በዝርዝር አቅርቦ፣ ይመለሱልኝ ሲል፣ ገዥው ፓርቲ በተቃራኒው ራሴን በጥልቀት እየገመገምኩ ነኝ ማለቱና ይሄም ከህዝብ ቀጥተኛ ጥያቄ ጋር የሚገናኝ አለመሆኑ ነው፡፡ ፓርቲው በራሱ ጣጣ ሲገማገም ሊኖር ይችላል፤ የእነሱ መገማገም ግን  የህዝቡን ጥያቄ መፍታት ማለት አይደለም፡፡ የህዝቡ ቀጥተኛ ጥያቄ እስካልተመለሰ ድረስ ደግሞ ጥያቄዎቹ በየጊዜው ተጨማሪ ገፅታ እየያዙ ነው የሚመጡት፡፡ በአሁኑ ጊዜ ቀድሞ በነበሩት ጥያቄዎች ላይ “የታሰሩ መሪዎቻችን ይፈቱ” የሚለውም ተጨምሮበታል፡፡ አሁን የህዝቡ ብሶት በላይ በላዩ እየተደራረበ ነው ያለው፡፡ የዚህ መጨረሻው ምን ይሆናል? ለሚለው ጥያቄ ግን ጊዜ የሚፈታው ጉዳይ ነው የሚሆነው፡፡
ገዥው ፓርቲ “ጥልቅ ተሃድሶ አደርጋለሁ” ሲል ምን ነበር  የተጠበቀው?
እንግዲህ አንዱ “አጠልቀዋለሁ” የሚለው የዲሞክራሲ ጉዳይ ነው፡፡ ዲሞክራሲን እያጠለቅን ነው ይላሉ፡፡ ነገር ግን እነሱ የሚሉት ዲሞክራሲና ዓለም የሚያውቀው እንዲሁም እኛ የምንታገልለት ለየቅል ናቸው፡፡ ምንም ግንኙነት የላቸውም፡፡ እነሱ ዲሞክራሲ የሚሉት፡- በማርክሲስት ሌኒኒስት ቀኖና የተቃኘ፣ በአንድ ፓርቲ የበላይነት ሁሉንም ፀጥ ለጥ አድርጎ፣ እኔን ብቻ ስሙ የሚለውን አስተሳሰብ ነው፡፡
እናንተ የምትሉት “ዲሞክራሲ” እና ኢህአዴግ የሚለው “ዲሞክራሲ” ትርጉሙ የተለያየው ከመቼ አንስቶ ነው? በፊትም አንስቶ ነው ወይስ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ?
አስታውሳለሁ፤ በሽግግር ወቅት ከእነሱ ጋር አብሬ ለመስራት በሞከርኩበት ወቅት አንዱ ወደ ፖሊቲካው ለማግባት መነሻ የሆነኝ፣ ኢህአዴግ የመደብለ ፓርቲ ስርአት አሰፍናለሁ የሚል ቃል በመግባቱ ነው፡፡ ነገር ግን በሂደት አቋማቸውን ቀይረው፣ የአንድ ፓርቲ የበላይነትና ፍጹማዊ አገዛዝን እውን ለማድረግ ነው የተንቀሳቀሱት። እነሱ አሁን የቻይናውን ኮሚኒስት ፓርቲ ሞዴል ለመከተል የሚፈልጉ ነው የሚመስለው፡፡ የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ላለፉት 70 ዓመታት በተግባሩ የብዙዎችን ይሁንታ ያገኘ ይመስላል፡፡ የቻይና እና የእኛ አገር ሁኔታ ግን ጨርሶ የተለያየ ነው። ቻይና አንድ ህዝብ ነው፡፡ “ይሄ ብሔር ያንን ጨቆነ፣ ተጨቋቆንን” የሚባል ነገር የለም፡፡ እነሱ በዚያ መነሻ በአንድ ፓርቲ ቢመሩ ምንም ላይሆን ይችላል፡፡ ኢህአዴግ ግን ለዚያ የሚበቃ ተክለ ሰውነት የለውም፡፡ የሃገሪቱ ሁኔታም ያንን በቀላሉ አይፈቅድም፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ፍላጎቶች አሉ፡፡ ያንን ማግባባት ያስፈልጋል፡፡ ከዚህ አንፃር አሁን እየተደረገ  ያለው ነገር ብዙም ተስፋ ሰጪ አይደለም፡፡
የመድብለ ፓርቲ ሥርአት የመመሥረት ተስፋ  ለምን የተዳፈነ  ይመስልዎታል?
እኔ ለረጅም ጊዜ አውጥቼ አውርጄ የደረስኩበት ዋናው ምክንያት፣ ደርግን ከስልጣን ማውረዳቸውን “የኢትዮጵያ ህዝብ  ሙሉ ለሙሉ  እንደ ውለታ ይቆጥርልናል” የሚል ሃሳብ ይዘው መነሳታቸው ነው፡፡ ህዝቡ እነሱን እንደ ነፃ አውጪ ቆጥሮ፣ ከማንም የፖለቲካ ፓርቲ ጋር ቢወዳደሩ፣ ማሸነፍ እንደሚችሉ አስበው  ነው የተነሱት፡፡ ወደ ተግባር ሲገቡ ነው ችግር የገጠማቸው፡፡ የመጀመሪያ ምርጫ ሲካሄድ በየቀበሌውና ወረዳው በእጅ በማውጣት ነበር፡፡ በዚያ ምርጫ ላይ ኢህአዴግ በአዲስ አበባም በክልሎችም በከፍተኛ ብልጫ ተሸንፎ ነበር። በተለይ በኦሮሚያ ኦነግ ነበር ያሸነፈው። ይሄ ምርጫ ለኢህአዴግ ከፍተኛ ምልክት ነበር ያሳየው። በወቅቱ “ዛሬ በእጅ በማውጣት ምርጫ ህዝብ እንዲህ ከጣለን በኮሮጆ ምርጫስ  ምን ሊያደርገን ይችላል?” በሚል  ግራ ተጋብተው ነበር። ይሄንን መነሻ አድርገውም ግምገማ አድርገዋል፡፡ እኛ በሽግግር መንግስቱ ውስጥ ገብተን የነበርነውንም በዚህ ምክንያት ማግለል ጀመሩ። በግልም በድርጅትም ላይ ነው ጥቃት መሰንዘር የጀመሩት። በሃዋሳ የሲዳማ አርነት ንቅናቄ መሥራች አቶ ወልደአማኑኤል ላይ  የግድያ ሙከራ ተደርጎባቸዋል፡፡ አቶ አሰፋ ጫቦና ፊታውራሪ መኮንን ዶሪ፤ የሽግግር መንግስቱን ብስራት ለህዝቡ እናሰማለን ብለው፣ ደብዳቤ ከጠ/ሚኒስትሩ ተፅፎላቸው፣ ወደ ጋሞ ጎፋ ሲሄዱ፣ መኪናቸው የድንጋይ ናዳ ወርዶበታል፡፡ እነዚህ (ኢህአዴጎች) ጠባያቸውን እየቀየሩ የመጡበት አጋጣሚዎችን ማሳያዎች ናቸው፡፡
የኢህአዴግ ትልቁ ችግር የርዕዮተ ዓለሙ መሰረት ነው፡፡ ይሄ ሲስተካከል ብቻ ነው መለወጥ የሚችሉት፡፡ ከማርክሲስት ሌኒኒስት አመለካከት ሲላቀቁ ነው ለውጥ የሚያመጡት፡፡ 21ኛው ክ/ዘመን ምን ይፈልጋል የሚለውን ሲያጤኑና ለውይይትና ክርክር በራቸውን ክፍት ሲያደርጉ ነው በራሳቸው ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉት። አለበለዚያ ግድብ ገደብን፣ ፎቅ ገነባን፣ መንገድ ሰራን ወዘተ — ብቻውን ፋይዳ  የለውም፡፡ የለውጥ ተስፋ የሚኖረው ውስጣቸውን በደንብ ሲፈትሹ  ነው፡፡ በመነጋገርና በመደራደር ማመን ሲጀምሩ ነው የሚለወጡት፡፡ ኢህአዴጎች፤ “እኛ ነን ለዚህች ሀገር ያለናት” የሚለውን መመፃደቃቸውን ትተው፣ “ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለሀገሩ በጎ ነገር ይመኛል” ብለው ማሰብ መጀመር  አለባቸው፡፡ “ባለፉት 26 ዓመታት የገነባነው ስርአት አሁንም የህዝብ ጥያቄን ማስቆም አልቻለም ወይም ምላሽ መስጠት አልቻለም” የሚለውን ግምገማ አድርገው፣ የፖለቲካ መስመራቸውን ቢፈትሹ  ሁነኛ መፍትሄ የሚገኝ ይመስለኛል፡፡
የዚህችን ሀገር  የወደፊት እጣ ፈንታ በመወሰን ረገድ የተቃዋሚዎች ድርሻ ምንድን ነው ይላሉ?
የተቃዋሚዎች ድርሻ ህዝብን ማደራጀት ነው፡፡ ያ የተደራጀ ህዝብ ጥያቄ ለመጠየቅ እስኪበቃ ድረስ አብሮ መስራት ነው ያለባቸው፡፡ አንድ የተደራጀ መሪ የሆነ አካል፣ በሌለበት ሁኔታ በአንድ ሀገር ውስጥ ስለ ለውጥ ማሰብ አይቻልም፡፡ የጎበዝ አለቃ ሁሉ ተነስቶ፣ የዘመነ መሳፍንት ሁኔታ ውስጥ እንግባ ካልተባለ በስተቀር የተደራጁ የፖለቲካ ኃይሎች ለህዝቡ አማራጩን ማሳየት አለባቸው። አሁን ከምንግዜውም በላይ ይሄ ነው በጥልቀት መካሄድ ያለበት፡፡ ዝም ብሎ የስርአት መውደቅ ብቻ አይደለም የሚታሰበው፤ በወደቀው ቦታ ማን ነው የሚተካው የሚለው መታሰብ አለበት፡፡ ይሄን ቦታ መተካት የሚችሉት የተደራጁ ኃይሎች ናቸው። የተደራጁ ኃይሎች ደግሞ የፖለቲካ ፓርቲዎች ናቸው፡፡ ይህን ነው የ21ኛው መቶ ክ/ዘመን ፖለቲካ የሚፈልገው፡፡
በሌላ በኩል ግን አመራሩን መረከብ የሚችል ጠንካራና ብቃት ያለው ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ የለም የሚሉ ወገኖች አሉ፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ የእርስዎ አስተያየት ምንድን ነው?
ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከህዝብ ጋር ተቀናጅተው፣ ብቃት ያለው እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ፣ እንቅፋት የሆነባቸው አሁን ያለው ሥርዓት ነው፡፡ በሌላ በኩል በከፍተኛ ሁኔታ መስዋዕትነት እየከፈሉ ያሉ ፓርቲዎች፣ በየእስር ቤቱ እየታጎሩ ያሉ የተቃዋሚ መሪዎች— ዕድሉን ቢያገኙ ሃገር የመምራት ሚናን አይወጡም ማለት የተንሸዋረረ አመለካከት ነው፡፡ የ97 ምርጫ እኮ ብዙ ነገር አሳይቶን ነው ያለፈው። በተፈጠረችው ክፍተት የፖለቲካ ፓርቲዎች 6 ወር ባልበለጠ እንቅስቃሴ ነው ብዙ ታሪክ የሰሩት። አሁንም በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት የፖለቲካ አመራሮች፣ ጨርሶ ብቃት የላቸውም የሚለው አመለካከት ስህተት ነው፡፡ ትንሽ ክፍተት ነው የሚፈለገው፡፡
እየተጎሳቆልንም፣ እየተሳደድንም ህዝቡን አደራጅተናል፡፡ ህዝቡ ነፃነቱን የሚያንፀባርቅበት መድረክ ቢፈጠርለት እኮ ብዙ መቀስቀስም አያስፈልገንም፡፡ ስለዚህ ተቃዋሚዎች የት አሉ? ምን ተቃዋሚ አለና? የሚባለው ነገር ጨለምተኛ አመለካከት ነው፡፡ ተቃዋሚዎች አሉ። እየጠበቁ ያሉት መልካም አጋጣሚን ብቻ ነው፡፡
አዲሱ ትውልድ ከሚፈልገው ለውጥ ጋር የሚጣጣም የፖለቲካ እንቅስቃሴ በተቃዋሚውም ሆነ በገዥው ፓርቲ ማምጣት አልተቻለም ብለው የሚያምኑ  ወገኖች አሉ፡፡ እርስዎ ምን ይላሉ?
እኔ አንድ ጥያቄ አለኝ፡፡ ይሄ የኢትዮጵያ አዲሱ ትውልድ፣ ከጨረቃ የወረደ ነው እንዴ? አይደለም። የፖለቲካ ትግል መዳረሻው ዲሞክራሲ ማስፈን ነው፤ ሌላ አይደለም፡፡ አዲሱ ትውልድም በራሱ መንገድ ተደራጅቶ መታገል ይችላል፡፡ እኛም በራሳችን እንታገላለን፡፡ በኔ እምነት ያለችው አንድ ሀገር ናት፡፡ ጥያቄውም አንድ ነው፤ እሱም የዲሞክራሲ ጥያቄ ነው፡፡ የቀረው ሁሉ ትርፍ ነው፡፡ ዝንጀሮ እንዳለችው፤ መጀመሪያ የመቀመጫዬን ነው ነገሩ፡፡ ዋናው ጉዳይ ዲሞክራሲያችንን በትክክለኛ ፈር ውስጥ ማስቀመጥ ነው፡፡ የዘመኑ ትውልድ ከዚህ ውጪ ምንም ሊያደርግ አይችልም፡፡ ተቆፍሮ የሚወጣ ነገር የለም፡፡ የተለየ ጥያቄም አይኖረውም፤ ሰው ሁሉ ሊግባባ የሚችለው በዲሞክራሲ ብቻ ነው፡፡ ዋናው የኔ አቋም፣ ሁሉም የየድርሻውን ያዋጣ ነው፡፡ እኛም ሆንን አዲሱ ትውልድ የምናዋጣው ተደማሪ ውጤት ለዚህች ሀገር መፍትሄ ያመጣል፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ብዙዎችን ስጋት ላይ የጣለ የድንበርና ብሄር ተኮር ግጭቶች እየተከሰቱ ነው? ይሄ አዝማሚያ ወዴት ያደርሰናል? መፍትሄውስ  ምንድን ነው?
የድንበር ጉዳይ ከሰው ልጅ ጋር አብሮ ያለ ጉዳይ ነው፡፡ መሬት ከሁሉም በላይ ዋጋ ያለው እሴት ሆኗል። አሁን የሚታየው አዝማሚያም ከመሬት መስፋፋት ጋር የተያያዘ ነው የሚመስለው። በሌላ በኩል ደግሞ ነገሩን ከብሄር ጉዳይ ጋር እያያያዙት፣ ሁኔታውን ውስብስብ እያደረጉት ነው፡፡ ይሄ  በእጅጉ የሚያሳዝን ነው፡፡ ለምሳሌ የሶማሌና የኦሮሞ ህዝብ፣ በወንድማማችነት አንዱ በሌላው ውስጥ መኖር የጀመረው በኢህአዴግ ዘመን አይደለም፡፡ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር ከተፈጠረችበት ጊዜ ጀምሮ ያለ ነው። በህዝቦች መካከል ድንበርን በመስመር ማስመር አይቻልም፡፡
በየዞኑና በየወረዳው የሚፈጠረውን ችግር የሚያነሳሱት ካድሬዎች ናቸው፡፡ ህዝቡ እርስ በእርሱ የተጋመደ፣ ለብዙ መቶ አመታት አብሮ የኖረ ነው፡፡ አሁን እየተፈጠረ ያለው ነገር፣ ለመናገርም የሚያሳፍር እብደት ነው፡፡ ልናፍርበት የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡ እኔ በዚህ ጉዳይ ላይ ምሬት ነው ያለብኝ፡፡ ለዚህም ነው ይሄ ሥርአት አገር ማስተዳደር አቅቶታል፤ ይበቃዋል የምለው፡፡ እንደ ሌላ ሀገር ቢሆን እኮ የአቶ ኃይለማርያም መንግስት፣ በዚህች ምክንያት በገዛ ፍቃዱ ስልጣን መልቀቅ ነበረበት፡፡ ለዘመናት አብሮ በኖረ ህዝብ ላይ ጥቃት የሚፈፀመው እኮ በአስተዳደሩ ውድቀት የተነሳ ነው፡፡ ህዝቡ የህግ ጥበቃ ያስፈልገዋል፡፡ አጥፊዎች በህግ መጠየቅ አለባቸው፡፡
እነዚህ ችግሮች በጊዜ መፍትሄ ካልተሰጣቸው ፌደራሊዝሙ አደጋ ላይ ይወድቃል የሚል ስጋት እየተስተጋባ ነው፡፡ የእርስዎ አስተያየት ምንድን ነው?
ፌደራሊዝም ለሀገሪቱ የአስተዳደር ጥያቄ ተገቢ ምላሽ ነው የሚል እምነት አለኝ፡፡ የተቸገርነው ፌደራሊዝምን ከዘረኝነት ጋር እያደባለቁ፤ ህዝብን እያናቆሩ ያሉ ወገኖች በመኖራቸው ነው፡፡ ይሄ ነው ትልቅ ስጋት ውስጥ እየከተተን ያለው፡፡ እኔ የፌደራሊዝም ሥርዓት ላይ ችግር የለብኝም፤ ነገር ግን አሁን ያለው የፌደራሊዝም ሁኔታ እንደገና መፈተሽ ይኖርበታል፡፡ “26 ዓመት ተሞክሯል፤ ምን ተገኘ?” የሚለው ተጠይቆ፣መከለስ ያስፈልጋል። የኢትዮጵያ ህገ መንግስት ዶግማ አይደለም፤ መከለስ ይችላል፡፡ አሜሪካኖች ህገ መንግስታቸውን ከ30 ጊዜ በላይ ከልሰው ነው፣ ጠንካራ ሥርዓት መገንባት የቻሉት፡፡

ለመሆኑ በብርሃን ጸዳል የተሽቆጠቆጠችው፤ ከሀገረ ቻይና እና ከብራዚል ጋር ዓለምዐቀፍ ተሸላሚዋ ዘመነኛዋ ትግራይ ግራጫ ጸጉር አላትን?


By ሳተናውOctober 30, 2017 23:32

 
ከሥርጉተ – ሥላሴ 31.10.2017 /ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ።/
„ … እንሆም፣ ሁሉ እሾህ ሞልቶበታል፣ ፊቱንም ሳማ ሸፍኖታል፣ የድንጋዩም ቅጥር ፈርሷል።
/ መጽሐፈ ምሳሌ ተግሣጽ ምዕራፍ 24 ከቁጥር 30 እስከ 31/“
እንደ በር።
ሥርጉተ ሥላሴ
ሥርጉተ ሥላሴ
በመጀመሪያ ጥናቱንና መቀነቱን 40 ዐመት ሙሉ በዕንባ ክርትት ለሚሉ ለኢትዮጵያ እናቶች እንዲሰጥልኝ አምላኬን እማጸነዋለሁ። በሥጋ የተለዩትንም ወገኖቼ ሰማዕትነታቸውን ፈጠሪዬ ይቀበልልኝ ዘንድም እማጸነዋለሁ።
በማስከትል … ወደ ዋናው ጉዳዬ ከመሄዴ በፊት ግን የአዋዜ አዘጋጅ ጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ የሰሞናቱን የአማራን የተደራጀና የታቀደ ጭፍጨፋ አስመልክቶ የሠራው ዜና እጅግ ውስጥን የተረጎመ፤ ሩቅ አሳቢና መንገድ ጠራጊ ዕድምታ ስለነበረ እጅግ አድርጌ ላመሰግነው ፈቀድኩኝ። ደፋር፤ ጥልቅ ትንታኔ ነው። ቅርብ – ከሩቅ ጥቃትን ያዋደደ ነው። ዓለም – ዓቀፋዊ ሰቅጣጭ የጭካኔ ዕውነታዎችን፤ ሁኔታዎችን በምልሰት የቃኘበት መንገዱ ብጡል ነው። አማራ እኮ ሐገር አልባነቱ ተውጆበታል። የከፈለው ደም ከንቱም ሆኗል። ስለሆነም የአዋዜ የንጽጽሩ የአምክንዮ አቅሙ አንቱ ነው። ለህሊና ቅድመ መሰናዶ ልዩ ተቋምም ነው። ለአማራ ሥነ – ልቦናዊ አኃቲነትም በኲራት ነው። አጭር ግን ልቅም ያለ፤ ልቁን የአማራን ዬዘር ጥፋት ትልም በጥልቀት የመረመረ፤ በስፋት ያስተዋለ፤ በውስጥነት የተቀበለ፤ የጉዳቱ ልክ በአትኩሮት እንዲታይ ፈር ቀያሽ የሆነ – መጸሐፍ ነው። ተባረክ! 

ወይ አረናዎች! – ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው



  
By ሳተናውOctober 31, 2017 05:48

 
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
የከዚህ ቀደሙን ትተን ሰሞኑን በኢሉባቡር፣ በቤንሻንጉል ጉምዝ፣ አስቀድሞም በሱማሌ ክልል በበርካታ የአማራና የኦሮሞ ተወላጆች ላይ ጥቃት ሲፈጸም “ዘር ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ነው!” ያላሉና ያላወገዙ፣ ያልተቃወሙ፣ ያልጮሁ፣ ሐዘን ያልተቀመጡ አረናዎች ትናንትና ጀግና ጀግና የነቀምት ወጣቶች በሦስት የወያኔ ሰላዮች ላይ ተገቢ እርምጃ መውሰዳቸውን ተከትሎ ከአሜሪካ ድምፅ እስከ ማኅበራዊው የብዙኃን መገናኛ ድረስ የብዙኃን መገናኛውን ወረው ይዘው ጥቁር በጥቁር ለብሰው ሙሾ እያወረዱ መራራ ሐዘን ተቀምጠዋል፡፡
በዚህ አሳፋሪ ተግባራቹህ እጅግ በጣም እናዝናለን! ይሄ ጠባብነትና ኢፍትሐዊነት ያወረው ድድብናቹህ ብዙ ዋጋ እንደሚያስከፍላቹህ መቸ እንደሚገባቹህ አላውቅም፡፡ ይሄ ድርጊታቹህና አስተሳሰባቹህ “ትግሬ የወያኔ ሰላዮች የፈለጉትን እያደረጉ ኦሮሞን በአማራ፣ ጉምዝን በአማራ….. ላይ እያነሣሡ ያጨፋጭፉ፣ ሥራቸውን እንቅፋት ሳያጋጥማቸው ይሥሩ! ለምን ይነኩብናል?” ማለታቹህ እንደሆነ ይገባቹሀል?
ትግሬ ስለሆኑ ብቻ ምንም ዓይነት ወንጀልና ግፍ ቢፈጽሙም መጠየቅና የሚገባቸውን ቅጣት ማግኘት የለባቸውም ማለት ነው? እኮ ለምን? እንዴት ነው ግን የምታስቡት? ለመሆኑ ጤነኞችስ ናቹህ? እንዴት ብትደፍሩን ነው ግን እንዲህ የታሰባቹህ? እንዴት ደናቁርት ብትሆኑ ነው ግን እንዲህ ያለ የደነቆረ፣ እጅግ ጠባብና ዘረኛ አስተሳሰብ ይዛቹህ እራሳቹህን ለአንድነት፣ ለእኩልነት፣ ለፍትሕ በሚታገልና በቆመ የፖለቲካ ፓርቲ ስም ስትጠሩ የማታፍሩት??? አንድነት እኩልነት ፍትሕ… የሚገባቹህና ለዚህም የቆማቹህ ቢሆን ኖሮ በነቀምት ወጣቶች የተወሰደውን ፍትሐዊ እርምጃ ታደንቁ፣ ትደግፉ ነበር እንጅ አሁን እያደረጋቹህ ያላቹህትን ነገር ፈጽሞ ባላደረጋቹህ ነበር! የነዚህን ሕዝባዊ ፍትሐዊ እርምጃ ለተወሰደባቸው የወያኔ ሰላዮችን ተግባር ደግፋቹሀልና፣ ተባባሪዎችም ናቹህና ነገ እናንተም ላይ ሕዝባዊ የሆነ ፍትሐዊ እርምጃ በተመሳሳይ መልኩ ይፈጸማል!!! ጠብቁ!!!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
amsalugkidan@gmail.com

አይነኬ የህወሓት ጀነራሎች!!! በኮንትሮባንድ የሰከሩ፣የደም ገንዘብ!!!


     
      
ክፍልአንድ | / ፂዩን ዘማርያም

ላንባው ተነቃነቀ!!!

የሳኦል መንግሥት ወደቀ!!!


‹‹በፊት በፊት እኛን መመርመር አይቻልም” ያሉ የዘመናችን የመንግስት ተቋማትን አይተናል፡፡ ይሄ እንግዲህ የፖለቲካ አይነኬዎች መፈጠራቸውን ያረጋግጥልናል፡፡ መሬት የዘረፉ እጃቸውን ቸብ ቸብ ተደርገው፣ ተቀጡ ተብለው ወዲያው ይለቀቃሉ፡፡ አንድ ሞባይል የመነተፈ ግን አደገኛ ቦዘኔ ተብሎ ከ2 ዓመት በላይ ይታሰራል፡፡ የፖለቲካ ኃይልና የዘረፋ ኃይል ውህደቱ ከፍተኛ ነው፡፡ “ይሄ የኔ ሰው ነው፤ አትንካው” የሚባልበት የአይነኬዎች ስርአት ነው የምለው ከዚህ አንፃር ነው፡፡›› ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ

የህወኃት የጦር አበጋዝ  መንግስት፣“ይሄ የኔ ዘር ነው፤ አትንካው” የሚለውን ወያኔ የኢትዩጵያ ህዝብ ከስሩ መንግሎ መጣል በሃገር የመኖርና ያለመኖር የህልውና ጥያቄ ነው፡፡ ዘውጌኛ የትግራይ፣የሶማሌ ወዘተ ጠባብ ብሄረተኛነት በሰፊ ኢትዩጵያዊ ብሄረተኛነት መተካት አለበት፡፡ በሕወሓት በተቀናበረው ሴራ፣ የሱማሌ የጦር አበጋዞች በኦሮሞ ህዝብ ላይ ያደረሱት አደጋ፣ የሞት፣ የስደት፣ የመፈናቀል፣ የእርስ በእርስ ጦርነት ጥቃቶች አብሮ በኖረው ህዝብ ዘንድ ጥቁር ጠባሳ ጥሎ ያልፋል፡፡ የወያኔ የፖለቲካ ሴራ ተጋልጦ የሱማሌና የኦሮማ ህዝብ አብረው ይኖራሉ፡፡ የህወኃት ጄነራሎች እነ ጄነራል አብርሃም ወልዴ (ካርተር) በሱማሌ ክልል ውስጥ ስውር መሪዎች በመሆን፣ አብዲ ኢሊ በመሾም  ልዩ የፖሊስ ኃይል በማደራጀት የፖለቲካ አይነኬዎች በመፍጠር  ከሱማሌ የጦር አበጋዞች ጋር ሽርክና መስርተዋል፡፡ የኢኮኖሚ ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ በኮንትሮባንድ ንግድ በተለይም በጮት፣ ማእድን ኃብት፣ የቁም እንሰሳትን ወዘተ በድንበር ዘለል ንግድ በማካሄድ የውጪ ምንዛሪ ዶላር በማከማቸት የሃገሪቱን ኢኮኖሚ ተቆጣጥረዋል፡፡ ለዘመናት አብረው የኖሩትን የሱማሌና የኦሮሞ ህዝብ በማጣላት ከሱማሌ ክልል የኦሮሞ ተወላጆችን በብዙ መቶ ሽህ የሚቆጠር ህዝብ ከኖረበት ቀየ እንዲፈናቀል አድርገዋል፡፡ በኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ የእንቢተኝነት ትግልን ለማኮላሸት ህወኃት የጠነሰሰው ሴራ በመሆኑ የመከላከያ ሠራዊቱ ጣልቃ አልገባም፣ እንዲውም ከፍተኛ የኦህዴድ አመራሮች ከግድያ ሙከራ አምልጠዋል፡፡  የህወኃት በትረ ሥልጣኑን የማቆየት አንዱን ብሄር ከሌላው በማጋጨት በተለይም የአማራና የኦሮሞ ህዝብን በማጣላት ስልቱ ከሽፎበታል፡፡ በዚህም የተነሳ የህወኃት የጦር አበጋዞች መንግሥት በምድረ ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የሱማሌ የጦር አበጋዞች መንግስት በመፈልፈል የአናሳ ብሄራት ህብረት በመፍጠር፣ ለልዩ ፖሊስ ኃይል መሣሪያ በማሳታጠቅ የኦሮሞ ህዝብ ላይ በማዝመት ታሪክ ይቅር የማይለው በደል በመፈጸም ላይ ይገኛሉ፡፡ በሌሎችም የኢትዩጵያ ክልሎች ተመሳሳይ የጦር አበጋዞች መንግስት፣ በህወኃት መፈጠራቸው አይቀሬ ነው፡፡
{1} የጦር አበጋዝ ማለት የግል ወታደራዊ ኃይል በማደራጀት፣ ለግል ጥቅም ስልጣንና ኃብትን የሚያካብት ተዋናይ ሲሆን በአንድ ሃገር፣ያለው መንግስትና መንግስታዊ መዋቅሮች ጠንካራ ባልሆነበት አካባቢ የሚፈለፈል የጦር አበጋዝ ነው፡፡(ማኪንሌይ፣2007)‘Warlord’ is a term which used to describe a specific period of China’s history but which has re-emerged as a label during the last three decades (MacKinlay, 2007). The definition of a warlord differ, but most authors agree that a Warlord is an actor who accumulate power and wealth for private means by using military force in an environment where the formal state has little or no control (Reno, 1998, MacKinlay, 2007). በኢትዮጵያ ወታደራዊው መንግስት ሲዳከምና በየቦታው ከአማፂያን ጋር ጦርነት ሲገጥም ድንበር ላይ ያሉ ግዛቶች የሚያገናኛቸው መስረተ ልምት መንገድ፣ ባቡር ወዘተ ያልዘመነ በመሆኑ ምክንያት የመንግስት ሥልጣንና ኃላፊነት እየተዳከመ ሲሄድ ቀየው በአካባቢው በሚገኙ የጎሳ የጦር አበጋዞች (የጎበዝ አለቃዎች) ህወኃት፣ሻብያ፣ኦነግ ወዘተ ቁጥጥር ስር ወደቀ፡፡ በዚህም መሠረት በኢትዩጵያ ታሪክ ከ1960 እስከ ከ2010ዓ/ም እስካሁን ያለው አገዛዝ የወያኔ ‹‹ዘመነ-ጦር አበጋዞች  መንግስት›› እንደ አሸን የተፈለፈሉበት ዘመን  እንደሆነ ጥናታዊ ፁሁፉ ያስረዳል፡፡
2} ‹‹የፖለቲካ የማንነት ጥያቄ›› Identities Politics
በአፍሪካ የዘመነ-ጦር አበጋዞች ‹‹የማንነት ጥያቄ›› ዘውጌ ብሄረተኛነት ፅንሰ ሃሳብ ዋነኛና አንገብጋቢ የፖለቲካ ጥያቄ የሆነው ለዚህ ነው፡፡ ዘውጌ ብሄረተኛነት፣‹‹በማህበራዊ ጭብጦች ላይ ሳይሆን፣ በዝርያ፣ በወገን መመሳሰል ላይ የተመሠረተ ብሄርተኛነት››ነው፡፡ (አንዳርጋቸው ፅጌ ገፅ310) በዘመነ-ጦር አበጋዞች በጎሳ፣ በነገድ፣ በዘር፣ በዘውግ፣ በክልል (የደም ግንኙነት፣ የዘር ሃረግ፣ የቌንቌ፣ ወዘተ) ላይ የተከለሉና የተመሠረቱ አንድ ዘርን  በውትድርና በማሠልጠን፣ በማደራጀትና ተዋጊዎች በመመልመልና በሌሎች ዘሮች ላይ በማስነሳት፣የፖለቲካ ሥልጣን ለመጨበጥ የማንነት ጥያቄን ሽሮ መብሊያቸው አደረጉት፡፡ ማርክሲዝም ሌኒኒዝም፣ ማኦይዝም ቀመስ የሆኑ የጦር አበጋዞች በስመ ሶሻሊዝም የብሄር ብሄረሰብን ጥያቄ በማራገብ የጀሌውን ደቀ መዝሙር ህሊና አጠቡት፡፡ የጦር አበጋዞቹ እልፍ አእላፍ ገበሬዎችን በወታደርነት በመመልመልና አንዱን ዘር በሌላው ዘር ላይ ጥላቻ በመቀስቀስ፣ የራሳቸውን ታማኝ ጦር ማደራጀት ቻሉ፡፡ የጦር አበጋዞቹ  የማንነት ጥያቄ ኢንተርፕሬነር ፈላስፎች ሆኑ፡፡

አፈትልኮ የወጣ መረጃ፦ “ስዩም ተሾመን ጨምሮ ሁለት ፀሃፊዎችን ለመግደል ታቅዷል!”



  
By ሳተናውOctober 31, 2017 07:33

 
ስዩም ተሾመ
ስዩም ተሾመ
ይህ “ከከፍተኛ የደህንነት ኃላፊዎች አፈትልኮ ወጣ” የተባለው መረጃ ለመጀመሪያ ግዜ የደረሰኝ ባለፈው ሳምንት ሲሆን የስልክ ቃለ ምልልስ ይህን ማያያዣ (Link) በመጫን ማዳመጥ ይቻላል። በተደጋጋሚ እንዲህ ያለ የማስጠንቀቂያና ማስፈራሪያ ስለሚደርሰኝ ብዙም ትኩረት አልሰጠሁትም። ባለፈው ሳምንት መረጃውን ያደረሰኝ ግለሰብ ትላንትም በድጋሜ ከአሜሪካ በቀጥታ የስልክ መስመር ደውሎ ስለሁኔታው በዝርዝር ገለፆልኛል። ከግለሰቡ ጋር ያደረኩትን የስልክ ቃለ ምልልስ ቀድቼዋለሁ። ሁለተኛውን የስልክ ቃለ ምልልስ ይህን ማያያዣ (Link) በመጫን ማዳመጥ ይቻላል፡፡
ከላይ የቀረቡት የስልክ ቃለ ምልልሶች የድምፅ ጥራታቸው ዝቅተኛ በመሆኑ የቃለ ምልልሱን ዋና ሃሳብ እንደሚከተለው በአጭሩ እገልፃለሁ። ከላይ የተጠቀሰው ግለሰብ ከከፍተኛ የደህንነት ኃላፊዎች እና የኢህአዴግ ባለስልጣናት ጋር ቅርበት እንዳለው ይናገራል። ለምሳሌ፣ ከውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ፣ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም፣ ሬድዋን ሁሴን እና ከከፍተኛ የደህንነት ሃላፊዎች ጋር በአካል ተገናኝቶ እንደሚወያይ ገልጿል፡፡ ይህ ውስጥ አዋቂ እንደሚለው፣ በሀገሪቱ ወቅታዊ ፖለቲካ ላይ ንቁ ተሳትፎ የሚያደርጉ፣ እኔን ጨምሮ በሦስት ፀሃፊዎች ላይ “መወገድ አለባቸው” የሚል ትዕዛዝ መተላለፉን ገልጿል። ከላይ ከተጠቀሰው ግለሰብ በተጨማሪ፣ ለደህንነት ሰዎች ቅርበት ያላቸው ሌሎች ጓደኞቼ “ስዩም ተሾመ መወገድ አለበት” የሚለው ውሳኔ መተላለፉን እንደሰሙ በመጠቆም ስጋታቸውን ገልፀውልኛል።
ይህን ከመስማቴ በፊት፣ ትላንት ጠዋት ብዙ የፌስቡክ ጏደኞቼ ከአሉላ_ሰለሞን ገፅ ላይ የተወሰደ ምስል ልከውልኝ ነበር። ከታች እንደሚታየው አቶ አሉላ ሰለሞን እኔ እንድታሰር በይፋ ጥሪ አቅርቧል። ውስጥ አዋቂው “ከአሉላ ሰለሞን ጋር እንዴት ስዩም ተሾመ ይወገድ ትላለህ” ብሎ ለረጅም ሰዓት እንደተከራከረው በመግለፅ ከፅሁፉ በስተጀርባ ያለውን እውነታ፣ በተለይ የአቶ አሉላ ሰለሞን የፖለቲካ አቋም በግልፅ ያሳያል፡፡ በዚህ መሠረት፣ አቶ አሉላ ሰለሞን እንደ እኔ የተለየ አቋምና አመለካከት የሚያራምዱ ግለሰቦችን ያለምንም ጥፋትና ማስረጃ እንዲታሰሩ በይፋ ጥሪ ከማቅረብ ጀምሮ ያለፍርድ “መገደል አለባቸው” ብሎ እንደሚከራከር ለማወቅ ተችሏል፡፡ በዚህም ህግ በሰፈነበት አሜሪካን ሀገር ተቀምጦ በኢትዮጲያኖች ላይ የሽብር ወንጀል እንዲፈፀም ጥሪና ቅስቀሳ እያደረገ እንደመሆኑ በህግ ሊጠየቅ ይገባል፡፡

የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በቀለ ገርባን በሰበብ በእስር ለማቆየት የጻፈው ደብዳቤ

የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በቀለ ገርባን በሰበብ በእስር ለማቆየት የጻፈው ደብዳቤ

          
      
(ዘ-ሐበሻ) የተከሰሱበትን የሽብር ወንጀል በውጭ ሆነው እንዲከታተሉ በዋስ እንዲወጡ የተወሰነላቸው አቶ በቀለ ገርባ ይህ ዘገባ እስከተሰራጨበት ጊዜ ድረስ አልተፈቱም:: ለዋስትና የሚሆነ 30 ሺህ ብር ወዲያውኑ የተከፈለ ቢሆንም የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ለምን እስካሁን እንዳልፈታቸው ሰበብ የያዘ ደብዳቤ ለፍርድ ቤት ጽፏል::
ደብዳቤው ይኸው:-

66

ንግስት ይርጋ በማረሚያ ቤቱ ኃላፊዎች ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣት ገለፀች


Filed under|


ከኢትዮጵያ ሰብ አዊ መብቶች ፕሮጀክት
በእነ ንግስት ይርጋ የክስ መዝገብ ብይን ለመስጠት በሚል በድጋሜ ቀጠሮ ተሰጥቷል
የቃሊቲ ማረሚያ ቤት የፍ/ቤት ትዕዛዝ አላከበረም ተብሏል
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት የሽብር ክስ የቀረበባቸውን የእነ ንግስት ይርጋ የክስ መዝገብ የአቃቤ ህግ ማስረጃን መርምሮ ተከሳሾች የቀረበባቸውን የወንጀል ክስ መከላከል ያስፈልጋቸዋል ወይስ መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነጻ ሊሰናበቱ ይገባል የሚለውን ብይን ለማሰማት ለዛሬ ጥቅምት 21/2010 ዓ.ም ቀጠሮ ይዞ የነበር ቢሆንም፣ ዳኞች መዝገቡን መርምሮ ለመስራት ተጨማሪ ጊዜ ያስፈልገናል በሚል በድጋሜ ቀጠሮ ሰጥተዋል፡፡
አክቲቪስት ንግስት ይርጋን ጨምሮ ስድስት ተከሳሾችን የያዘው የእነ ንግስት ይርጋ መዝገብ ነሐሴ 12/2009 ዓ.ም ለብይን በሚል ቀጠሮ ከተያዘ በኋላ ብይኑ አልደረሰም በሚል ለዛሬ ተላልፎ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ሆኖም ግን ዛሬም መዝገቡ ተመርምሮ ብይኑ ባለመሰራቱ ለሁለተኛ ጊዜ ለህዳር 01/2010 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡
በሌላ በኩል ቃሊቲ ማ/ቤት የምትገኘው አክቲቪስት ንግስት ይርጋ በእስር ቤት የጥየቃ ሰዓትና የጠያቂ ገደብ ተጥሎብኛል የሚሉና ሌሎች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች አቤቱታ አቅርባ ይህ እንዲስተካከል ፍ/ቤቱ ለቃሊቲ ማ/ቤት አስተዳደር ትዕዛዝ ሰጥቶ የነበር ቢሆንም ማ/ቤቱ ትዕዛዝን አለማክበሩ ተገልጹዋል፡፡
‹‹ሐምሌ 21/2009 ዓ.ም ፍ/ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቶልኝ ነበር፡፡ ሆኖም ማ/ቤት አስተዳደሩ የፍ/ቤቱን ትዕዛዝ አክብሮ መብቶቼን ባለማክበሩ በድጋሜ ነሃሴ 12/2009 ዓ.ም አቤቱታ አቅርቤ፣ ለዛሬ ማ/ቤት አስተዳደር ለምን ትዕዛዙን እንዳላከበረ መልስ እንዲሰጥ ታዝዞ ነበር፡፡ ይባስ ብሎ በማ/ቤቱ አስተዳደር ቢሮ እየተጠራሁ ‹አንቺ ማን ስለሆንሽ ነው ማ/ቤቱን የምትከሽው፣ አንቺ ከማን ትበልጫለሽ እየተባልሁ ማስጠንቀቂያ እየተሰጠኝ ነው›› በማለት ንግስት ይርጋ ስላለው ሁኔታ አቤቱታ አሰምታለች፡፡
ሌሎችም ተከሳሾች አቤቱታ እንዳላቸው ቢገልጹም ፍ/ቤቱ አቤቱታቸውን በጽሁፍ ካቀረቡ ብቻ እንደሚቀበላቸው በመግለጽ እንዳይይገሩ ከልክሏል፡፡
ፍ/ቤቱ የቃሊቲ ማ/ቤት አስተዳደር ቀደም ሲል በንግስት ይርጋ አቤቱታ ላይ የተላለፈውን የፍ/ቤቱን ትዕዛዝ ለምን እንዳላከበረ በቀጣይ ቀጠሮ ቀርቦ እንዲያስረዳ በድጋሜ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡


Monday, October 30, 2017

የወያኔ “ዕዉራን” ምሁራን የሚጠነስሱት ሴራ


ቢንያም ሙሉጌታ ከኖርዌ




የወያኔ ህወሃት ባለስልጣናት የኛ የሚሏቸውን የትግራይ ምሁራንና ካድሬዎቻቸውን
ብቻ ለይተው ለመጥቀም እንዲሁም ሌላኛውን ለመጉዳትና ለማሸማቀቅ ላለፉት 26
ዓመታት በሁሉም ኢትዩጵያዊ መታወቂያ ላይ ዘር እንዲጠቀስ በማድረግ ከፍተኛ
የሆነ አገርን የማፍረሻ ቫይረስ ሲረጩ ቆይተዋል።
ይህ ህወሃት ወያኔ የረጨው የዘር ቫይረስ የትግራይ ህዝብ ሙሉ በሙሉ
እንደተስማማው እርግጠኛ መሆን ባይቻልም ነገር ግን ትግራይ ውስጥ ምንም
አይነት ተቃውሞ የማይሰማው አንዳንድ የትግራይ ፀሀፊዎች እንደሚሉት በትግራይ
ብዙ ጭቆና አለ በትግራይ የሌለውና የጠፋው ጭቆናውን የሚያጋልጥ ነው እያሉ
ሲሉ እንሰማለን። ሆኖም ግን ሌላው ኢትዩጵያዊ በወያኔ ህወሀት ቀንበር ተጭኖበት
ሲገደል ሲታሰር ብዙ በደል ሲፈፀምበት የትግራይ ህዝብና ምሁራን ዝምታ የተለመደ
ነው።
ህወሀት ወያኔ በመታወቅያ ወረቀት ላይ የጠመደው የዘር ፈንጂ ሌላውን ኢትዮጵያዊ
እያጠፋ እየበታተነ እየከፋፈለ እንዳለ የትግራይን ህዝብና ሙሁራን እንደሚያቁ
ግልፅ ነው። ገዢው ፓርቲ ኢትዩጵያን በዘር የመከፋፈል ክፉ አጀንዳ ብዙዎችን ዋጋ
አስከፍሏል። በቅርብ ግዜያት እንኳን ብዙ ታዝበናል። በጉራ ፈርዳ የአማራ
ተፈናቃዮች ከ20 ዓመታት በላይ ከኖሩበት መሬታቸው አማራ ስለሆናችሁ በዚህ ክልል
መኖር አትችሉም ተብለው ተፈናቅለዋል እንዲሁም በኦሮሚያ እና ሶማሊያ አካባቢ
ህወሀት ወያኔ ሆን ብሎና አቅዶ የእርስበርስ ግጭት በመፍጠር በሁለቱም
አካባቢዎች የሚገኝ በብዙ ሺህ የሚቆጠር ዚጎቻችን ህይወታቸውን ንብረታቸውን
አጥተዋል። ለዘመናት ከኖሩበት የመኖርያ አካባቢያቸውም ተሰደዋል።
ወያኔ ህወሀት እንደዚህ የመሳሰሉ የእርስ በእርስ ግጭቶችን በብዙ ኢትዩጵያ
አካባቢዎች ላይ ተግባራዊ አድርጓል እያደረገም ነው። አሁን ግን ግጭቱም በማንና
ለምን እንደሚፈፀም ሁሉም ኢትዩጵያዊ ጠንቅቆ ተረድቶታል። ይህ አምባገነን ገዢ
በሀገሪቱ ላይ ያለው የህዝቦች አንድነት፣ሰላም እና መግባባት እንዲቀጥል ፈፅሞ
አይሻም። ለምሳሌ በኦርቶዶክስ ሀይማኖት በየገዳማቱ ላይ እያደረሰ ያለው ጥቃት እና
በሀይማኖቱ መሪዎች መካከል በጳጳሳቱ እንዲሁም በሊቀ ጳጳሳቱ ብሎም በሲኖዶሱ
መካከል ሰርጎ በመግባት ሀይማኖቱን ለማበጣበጥ እና ለመከፋፈል ባደረገው
እንቅስቃሴ አሁንም ድረስ ህዝበ ክርስቲያኑን እንዳሳዘነ እና እንዳስቆጣ ይገኛል።
በየእምነት ተቋማቱ ውስጥ ወያኔ እጁን በማስገባት ችግር ፈጣሪዎቹ እነሱ
መሆናቸው እየታወቀ መፍትሔ አፈላላጊ አካል ነን ብለውም ከፊት የሚቆሙት
ራሳቸው ናቸው። በኢትዩጵያዊው ሙስሊሙ ህብረተሰብ ውስጥ አክራሪነትንና
ሽብረተኛነትን ለመዋጋት በሚል የይስሙላ ፖሊሲ ነድፈው ሙስሊም ህብረተሰብን
ለመከፋፈል ለመበታተን ለማጋጨት ብዙ ደክመዋል። በእነዚህና መሰል ብዙ
ቀውሶች ወቅት ከትግራይ ተወላጅ ሙሁራን የአገዛዙን የተዛባ ፍትህ የሚያወግዝ
ድምፅ እረጭ ፀጥ ማለቱ ያሳዝናል። ከፋሺስት ወራሪ ጦር ኢትዩጵያ ሀገራቸው
ለመታደግ የተዋደቁት ቀደምት የትግራይ ተወላጆች አጥንት ይወቅሳቸዋል። የፈሰሰ
የደማቸውም ጩኽትም ከተኙበት ወያኔያዊ አዚም ያነቃቸው ዘንድ እመኛለሁ።
አምባገነኑ የትግራይ ወያኔ በሀገራችን ኢትዮጵያ ላይ ያለው ግልፅ የሆነ ደባ ከዚህ
በኋላ ሊቆም ይገባል። ሀገሪቱን እንደነ ዮጎዝላቪያ፣ሶማሊያ፣ሩዋንዳ እና ሶሪያ
ለመበታተን አንግቦ የተነሳውን አጀንዳ ማስቆም የግድ ነው። ይህንን አምባገነን
ሰይጣናዊ ስርዓት በጊዜ ካለመወገዱ የተነሳ ለአዲሱ እና ተተኪው ትውልድ ተሻጋሪ
ጥፋትና ቀውስ ፈፅሟል። በአማራው፣በጋምቤላው በኦሮሞው በአፋሩ በተቀረው
ኢትዮጵያዊ ላይ እያነጣጠረ በመፈፀም ላይ የሚገኘው ጥቃት ፈተናውና መዘዙ
ውሎ አድሮ የኋላ ኋላ ለራሱ ለትግራዮም ተወላጅ መትረፉ የማይቀር ነው።
የኢትዮጵያ መከራ እንዳያበቃ በማድረግ እና የህወሀት ወያኔ መሪዎችን እድሜ
የሚያረዝመው ዘረኝነት ህሊናቸውን ያሳወራቸው የትግራይ ዕዉራንምሁራን
የሚጠነስሱት ሴራ የበለጠ ሀገሪቱን ወደ ውስብስብ ችግር ውስጥ እየከተተ ይገኛል።
እነዚሁ ህጋዊ የሆኑ ዘራፊ ቡድኖች የሀገሪቱ ሀብት ምዝበራ ላይ በዋና ተጠቃሚ
ስለሆኑ ስለሚፈጠረው ቀውስ እና ስለ ነገይቱ ኢትዮጵያ ምንም አይገዳቸውም።
እነርሱ የሚረጩት መርዝ ብዙ ታማሚዎችንም አፍርቷል። ዛሬም ህልማቸው መዋለ
ንዋይ ብቻ ነው። መዝረፍ ማድከም ባዶ ማድረግ አላማቸው ነው። የትግራይ ህዝብ
ከወያኔ ጋር አብረው ኢትዮጵያዊነትን የሚያፈርሱ ዘረኝነትን የሚያስፋፉ
በመሆናቸው ታሪክ ይፋረዳቸዋል።
በአሁን ወቅት ገዢው ፓርቲ ከግብር አበሮቹ ጋር በመሆን ኢትዮጵያዊነት ትርጉመ
ቢስ ደረጃ ያደረሱት መስሎ ቢሰማቸውም፤ ኢትዮጵያዊነት ግን በደም ውስጥ ያለ
የማይቀየር ማንነት ነው። በህወሀት ወያኔ እና በትግራይ ዕዉራን ምሁራን ጥምረት
የሚመራው የዘር ማጥፋትና ኢትዮጵያዊነትን ማፅዳት ዘመቻ የረዘመ ዘመን
ያስቆጠረ መሆኑ ግልፅ ቢሆንም፤ገና የትጥቅ ትግል ሲጀምር ኢትዮጵያዊነትን
ማዳከም አማራውን እና ኦሮሞውን በማጣላት ማህበራዊ ህይወቱንም ማናጋት
አጀንዳው ነበር። ይህንን በሀገሪቱ ላይ ለ26 ዓመት በአምባገነንነትና በዘረኝነት
ስልጣንን ለብቻው በመያዝ የሚገዛው ወንበዴ ቡድን ማንና ምን እንደሆነ
ኢትዮጵያዊ የሆነ ሁሉ ጠንቅቆ ስለተረዳው በተባበረ ክንድና በአንድ ኢትዯጵያዊት
የሚያምን ሁሉ ከፊት ለፊቱ ያለውን ሀገር አድኑን ተጋድሎ እየተባበረ ወያኔ ህወሀትን
የሚማርክበት ዕዉራንምሁራን ትግራዮችን የሚስቆምበት ወሳኙ ጊዜ አሁን
ነው።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!