Tuesday, October 11, 2016

በኦሮሞ ህዝብና በአጋዚ ወታደሮች መካከል በተደረገው ጦርነት 38 የአጋዚ ወታደሮች መገደላቸውን በሻላ ወረዳ ምንጮች ይገልፃሉ።


በምስራቅ አርሲ ዞን በሻላ ወረዳ በኦሮሞ ህዝብና በአጋዚ ወታደሮች መካከል በተደረገው ጦርነት 38 የአጋዚ ወታደሮች መገደላቸውን ያካባቢው ምንጮች ይገልፃሉ። ሕወሓት ከገበሬዎች የደረሰበትን ከፍተኛ ጥቃት ለመሸፋፈን በመሞከር አንድ የአጋዚ ወታደርና አንድ የኦሮሚያ ፖሊስ መገደላቸውን ቢገልፅም እውነታው ግን ሕወሓት ከሚለው የማይገናኝ መሆኑን ምንጮች ይናገራሉ::
በቀደም ብቻ 3 ተገድለው አስክሬናቸው ውጪ ሜዳ ላይ አድሮ የተገኙ ወታደሮች መኖራቸውንም ጭምር ነው ምንጮች አክለው የገለፁት:: በግልፅ የሚታይ እውነታን ሸፋፍኖ የተጀመረውን ትግል ማደናቀፍ እንደማይቻልም ነው እነዚሁ ምንጮች ያሳሰቡት::
የአማራ ክልል በሆነችው አርማጭሆ ሳንጃ ከከተማዋ ወጣ ብሎ ብጭብጭቢት ላይ አንድ ኦራል የወያኔን አጋዚን የጫነ መኪና በውስጥ ባአርበኞች ጀግኖቻችን ሙሉ በሙሉ ሊደመሰስ ችሏል።

No comments:

Post a Comment