Monday, October 31, 2016

የንቀትና የሴራ ፖለቲካ ፣የሃሰትና የቅፈላ ፖለቲካ ቆሞ በሃገር ውስጥ የሚደረጉ ትግሎችን ሚና ሳንለይ በጋራ ልንደግፍ ይገባል።


Image may contain: text
የንቀትና የሴራ ፖለቲካ ፣የሃሰትና የቅፈላ ፖለቲካ ቆሞ በሃገር ውስጥ የሚደረጉ ትግሎችን ሚና ሳንለይ በጋራ ልንደግፍ ይገባል።

ኢትዮጵያውያን ላለፉት መቶዎች ፣ሺዎች ኣመታቶች ተፋቅረው ተከባብረው ተጋብተው ተዋልደው ለዛሬ ኣድርሰውናል። ዛሬ ላይ ሃገር ቤት ከሚገኘው ለነጻነቱና ለመብቱ ከሚታገለው ሕዝብ ይልቅ በመከፋፈል በዘረኝነት እና በትምክህት እየጦዘ ያለው ዲያስፖራው ነው። ይህ ዲያስፖራው የፈጠረው ኣጉል የበታችነት ስሜት የወለደው የጎሳ ፖለቲካ ክፍተት በመፍጠሩ ሕዝብ ነጻነቱንና መብቱን እንዳያስከብር እንቅፋት ከመሆኑም በላይ ለወያኔ የእፎይታ ጊዜ ሆኗል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ማሰብ የማይችሉ የኣጼዎቹ ስርዓት ናፋቂዎችም ሌላው ቤንዚሎች ናቸው።በዲያስፖራው ኣከባቢ የሚነዙ ጡዘቶች በሃገር ቤት ባለው ትግል ላይ ምናምን ይቸልሱበታል የሚለውን ፍራቻ ሰብረን ማለፍ በጣም ቀላል ነው። አንድነት – ፍቅር – ትእግስት – መከባበር – መደማመጥ – መተራረም
ደጋግመን የምንጮዀ ነገር ቢኖር በመላው ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የተጨቆኑ ሕዝቦች ለውጥ ይፈልጋሉ፤ ለለውጥ የሚደረገው ትግል ፈር ያዘ እንበርታ በተባለበት በዚህ የሕዝብ ድል በሚበሰርበት ኣዲስ ምእራፍ ተከፍቶ የእኩልነት ኢትዮጵያ በምትመሰረትበት ወቅት እኩይ ኣንደበታቸውን ይዘር ሴራቸውን የሚያቀረሹ ጥቂቶች ሰፊውን ሚዲያ ተቆጣጥለው ለሕዝቦች ዳግም ባርነት ልብ ሰባሪ ፖለቲካ በመቀሸር ላይ መገኘታቸው የለመለመን ተስፋ ኣቀጭጮ የወያኔን ስልጣን ከማጥበቅ ኣይለይም።
በማግለል በፍረጃ እና በኣልሳካም ባይነት የሚናውዘው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፖለቲካ በወያኔ ሃይሎች እጅ ሆኖ ሕዝብን እያመሰ ይገኛል፤ ለዚህ መፍትሄ የሚሆነው ሕዝባዊ ማኒፌስቶ የያዘ ኣጀንዳ ሲኖር ብቻ ነው። ሕዝባዊ ኣጀንዳ ባለለበት ብዙ ፖለቲከኞች እየተጋቡ ተፋተዋል ፖለቲካውን የቅፈላና የጭብጨባ ኣድርገውታል።እንዲሁም ከፖለቲካ የተገለሉ በሃገራቸው ጉዳይ እንዳይሳተፉ ስማቸው የሚጠፋ ኣካላት ከወያኔ ጋር በመተባበር የሚያሴሩት ተንኮል ትግሉ ወደ ኋላ እንዲጎተት ሲያደርገው ሕዝብ በፍራቻ እንዲርድ የፖለቲካ ውዥንብር እንዲፈጠር መንገድ ከፍቷል።
ለዚህ መፍትሄው ሁሉም ከትንሽ እስከ ትልቅ በሃገር ጉዳይ ስለሚያገባው በጋራ የተሳተፈበት ትልቅ ስራ በመስራት ትግሉን ወደ ድል ማሸጋገር ሲቻል ዋናው እና ሊተኮርበት የሚገባው ለውጥ ፈላጊውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ነጻ እናወጣሃለን ያሉ ሁሉ በጋራ ሊቆሙ ይገባል። በመከፋፈል በማግለል በማዋሰድ በመሳደብ በማንቋሸሽ ማንም ምንም የሚያተርፈው ሃቅ የለም። ሕዝቡን ተባብረን ተረባርበን ልንደግፍ ይገባል። የነጻ ኣውጪ ነን የሚሉ የለውጥ ሃዋርያ ነን የሚሉ ፖለቲከኛ ነን የሚሉ በመካከላቸው ያለው ግብግብ ለወያኔ የፕሮፓጋንዳ ስራ ታላቅ ኣስታውጾ ያደርጋል። የንቀትና የሴራ ፖለቲካ ቆሞ የሃሰትና የቅፈላ ፖለቲካ ቆሞ በሃገር ውስጥ የሚደረጉ ትግሎችን ሚና ሳንለይ በጋራ ልንደግፍ ይገባል። #ምንሊክሳልሳዊ

No comments:

Post a Comment