Monday, October 3, 2016

“አማራው የራሱ ሬዲዮ ጣቢያ ካቋቋመ ኢሳትን ያዳከማል” የወቅቱ ነጠላ ዘፈን


“አማራው የራሱ ሬዲዮ ጣቢያ ካቋቋመ ኢሳትን ያዳከማል” የወቅቱ ነጠላ ዘፈን። ለምንድን ነው ኢሳት የሚዳከመው? ኢሳት የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ(OMN) ወይም የእስልምና አማኝ ወገኖቻችን ድምጽ ሬዲዮ ቢላል ብርድካስቲንግ ኔትወርክ (BBN) እና ሌሎችም በመቋቋማቸው ተዳከመ እንዴ? ለምንስ እነሱ ሲቋቋሙ ኢሳት ይዳከማል የሚል እሮሮ አልሰማንም? ለምንድን ነው ከምድረገጽ ሊጠፋ የተፈረደበት አማራ ልሳኑ እስከወዲያኛው እንዲዘጋ የሚፈለገው?
ኢሳት ቆሞ ያለው በአማራ ልጆች ገንዘብና ጉልበት ነው ማለት ነው? ከሆነ ታዲያ አማራው ለምን ከማዱ ተከለከለ? ለአማራ ምሁራንና የታሪክ ሰዎች የኢሳት ቢሮ ለምን ተዘጋባቸው? አማራ ትግሉን የአማራ ተጋድሎ በሉልኝ ሲል ኢሳት ለምን “የጎንደር፤የጎጃም አመጽ”
እያለ ያሳንሰዋል? ስለአኖሌ ሃውልት አደገኛነት ኢሳት ለምን የታሪክ ምሁራኖችን እየጋበዘ አያወያይም? ከኦሮሞ ንቅናቄ ጀምሮ ኢሳት ቪዥን ኢትዮጵያ ተብዬው ሁለት ጊዜ ምሁራንንና ፖለቲከኞችን እየጋበዘ ሲያወያይ በጎንደር ተቀስቅሶ በአማራ ክልሎች እየተካሄዱ ስላሉት ተጋድሎዎች ለምን ኢሳት ምሁራንንና ፖለቲከኞችን ጋብዞ አላወያየም?
በዚህ አካባቢ ይህን ያህል አማራዎች ተገደሉና ታሰሩ ከሚል የዘለለ የአማራ ፖለቲከኞችንም ሆነ ምሁራንን ጋብዞ የአማራውን ህዝብ እንዲቀሰቅሱ መቼ ተፈቀደላቸው? ሌላውና ዋነኛው ኢሳት ከተቋቋመ ጀምሮ አማራው በሃገሪቷ አራቱም ማእዘን በተለያዩ የጎሳ ጽንፈኞች በተለይም በቤኒሻንጉል እንደ አውሬ እየታደነ ዘግናኝ በሆነ መንገድ ሲጨፈጨፍ ኢሳቶች ለምን አትዘግቡም ሲባሉ “ህዝብ ለህዝብ ላለማጋጨት” ነው እያሉ ሲያላግጡብን የኖሩት ጸረ አማራ ደባቸው ነው።ብዙ ማለት ይቻላል፣ ኢሳት በአማራው ላይ የሚያደርገው አድሎ ብቻ አይደለም ጥርሱን ያገጥጥ ደባ። ለማንኛውም እኛ ኢሳትን ለማዳከም ሳይሆን ድምጹ ለታፈነው ምስኪኑ ወገናችን ድምጽ ለመሆን ነውና ተረጋጉ።ደሞስ ይህ ሬዲዮ ጣቢያ ስራችሁን ያቀልላችኋል እንጂ ለምን ይጎዳችኋል? በጤናማ ህሊና ካያችሁት።
ሰላምና ጤና ለምስኪኑ አማራው ወገኔ!!
ከፌስ ቡክ የተገኘ፣ ሰለሞን ደርዜ

No comments:

Post a Comment