Friday, October 14, 2016

ሻእቢያ በኣስመራ ወያኔ በኣዲስ ኣበባ ተቃዋሚ ፓርቲዎችንና የለውጥ ሃይሎችን እየበጠበጡ ነው። – ፈንቅል ኣባቄራ


ሻእቢያ በኣስመራ ወያኔ በኣዲስ ኣበባ ተቃዋሚ ፓርቲዎችንና የለውጥ ሃይሎችን እየበጠበጡ ነው። – ፈንቅል ኣባቄራ
ባኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ ለማምጣት በርካታ ተቃዋሚዎችና የለውጥ ሃይሎችን በማቀናጀት ከፍተኛ ተጋድሎ እያደረጉ የሚገኙ ቢሆንም በተለያዩ የፖለቲካ ሴራዎች በኣስመራና ኣዲስ ኣበባ ያሉ የሻእቢያና የወያኔ ሰርጎገቦችን በማስገባት ከፍተኛ የሆነ የማፈራረስ ኣደጋ በፓርቲዎች ላይ እየተደረገ መሆኑ ታውቋል።
ከኣስመራ እና ኣውሮፓ ዬተገኙ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በሻእቢያ ሴራ በዶ\ር ብርሃኑ ነጋ በሚመራ በግንቦት ሰባትና በኣቶ መዓዛው ጌጡ በሚመራው ኣርበኞች ግንባር መካከል ከፍተኛ የሆነ ግብግብ መፈጠሩ ሲታወቅ ይህን ተከትሎ በኣውሮፓና በኣሜሪካ የሚኖሩ የግንቦት ሰባት ከፍተኛ ኣመራሮች ወደ አስመራ ማቅናታቸው ታውቋል።የኣርበኞች ግንባር ኣመራሮች ግንቦት ሰባት ሃያ የሚሆኑ ወታደሮች ሳይኖረው ኣርበኞች ግንባርን ማዘዝም ሆነ መዋሃድ ኣይችልም ውህደቱ ካለፍላጎት የመጣ ሲሆን በኣናሳ ፓርቲ ልንመራ ኣንችልም ግንቦት ሰባት በፕሮፓጋንዳ የገዘፈ ኣንድም ስራ ያልሰራ ድርጅት ነው በማለት የሚናገሩት የኣርበኞች ግንባር ሰዎች ዶ\ር ብርሓኑ ነጋ ድርጅቶችን እየበጠበጠ ስለሆነ ከስልጣን እንዲወርድ ሲሉ ውህደቱንም መምራት ያለበት በርካታ ወታደሮች ያሉት ኣርበኞች ግንባር በመሆኑ ይህ ካልሆነ ግን ውህደቱ መፍረስ ኣለበት የሰራውም ስራ የለም ሲሉ ምሬታቸውን ያሰማሉ።
በኣለም ኣቀፍ ደረጃ የኣርበኞች ግንባር ድጋፍ ኮሚቴ በተለያዩ ሚዲያዎች እንደሚናገረው ግንቦት ሰባት የተባለው ድርጅት ራሱን በፕሮፓጋንዳ ኣግዝፎ ምንም ሳይሰራ ትግሉን እያዳከመ ነው ሲሉ ይከሳሉ። በተጨማሪም ግንቦት ሰባት ጠንካራና ለሀገር ተቆርቋሪ የሆኑ ታጋዮችን በሻእቢያ ደህንነቶች እያሳፈነ ወደ ወህኒ ሲያስወረውር ሌሎችን ደሞ በቁም እስር ላይ እንዲሆኑ ኣድርጓል ሲሉ የኣስመራ ኣርበኞች ግንባር ኣመራሮችን ጠቅሰው ይናገራሉ።
በኣስመራ የተከሰተው ችግር ኣሁንም ሳይፈታ በእንጥልጥል ላይ ሲሆን የኣርበኞች ግንባር ኣመራሮችና ታጋዮች የግንቦት ሰባትን ተግባር የማይዋጥላቸውና ኣስፈላጊ ነው ሲሉ ይገልጻሉ።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ በኣዲስ ኣበባ የሚገኘው የሰማያዊ ፓርቲ በሰርጎ ገብና እስር ቤት ተሃድሶ በወሰዶ ኣባላት እየታመሰ መሆኑን ሰሙኑን የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ፥ የፓርቲው ገጽ እንዳለው ሰማያዊ ፓርቲን ለማፍረስ ወያኔ ሰባ ኣምስት ሰርጎገቦችን ሰብስቦ ጠቅላላ ጉባዬ በማድረግ የዕለቱ ጉባኤ አካሔድ አስቂኝ እና ህገወጥነቱ የሚጀምረው የጉባኤው አባላት ያልሆኑ በማን ጋባዥነት እንደመጡ የማይታወቁ ግለሰቦች የጉባዔው አባላትን ቀድመው ቦታ ይዘዋል፡፡ ጉባኤው ሕገ ወጥ ቢሆንም በቦታው ተገኝቶ የሚደረገውን ለማየት የተገኙ የጠቅላላ ጉባዔ አባላት በቦታው ሲደርሱ የጉባኤው አጋፋሪ የነበሩ ግለሰቦች አስቀድመው በወሰኑት መሰረት ወደ ጉባዔው እንዲገቡ የማይፈልጓቸውን አባላት በመደባደብ ጭምር ለማስቀረትና ይህ ካልሆነላቸው ግን “ተጨማሪ ኃይል ይምጣልን” እያሉ ፖሊስን እያዘዙ በመጠቆም የጉባዔ አባላትን ለማስደብደብ ሞክረዋል፡፡ ይህንን ትንቅንቅ አልፈው ወደ ተዘረጋው የሸራ ድንኳን የገቡ አባላት ከጧቱ ሁለት ሰዓት ጀምሮ ይካሔዳል የተባለ ጉባኤ እስከ ፭ ሰዓት ተኩል ድረስ የሚከፍተው በጥፋቱ የፍጥጫ መድረክ አድርገውት ቆይተዋል፡፡ ፓርቲው ይገልጻል የፓርቲዉን ማብራሪያ ይህ ነው ፣ 
በኢትዮጵያ የተነሳውን የለውጥ ማእበል ይመሩብኛል ብሎ የፈራቸውን የፖለቲካ ድርጅቶች ከኣባቱ ሻእቢያ ጋር ሆኖ መበጥበጥ የያዘው ወያኔ በከፍተኛ የፖለቲካ በሽታ ውስጥ በመሆኑ ከሞት ለማምለጥ ሲል የሚሰራቸው ተንኮሎችና ሴራዎች በሕዝብ ሃይል ወደ ሞት እያጣደፉት ነው። ፈንቅል ኣባቄራ

No comments:

Post a Comment