Monday, October 17, 2016

የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግል በቅጥረኞች እና በአደርባዮች ኣይቀለበስም። ኢዴፓ ለስልጣን አሰፍስፏል።


የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግል በቅጥረኞች እና በአደርባዮች ኣይቀለበስም።
በተቃዋሚ ጭንብል በወያኔ ሚዲያዎች እየቀረቡ ሕዝብን ማዘናጋትና ማጭበርበር ሊበቃ ይገባል።እንደ ኢዴፓ ያሉ የልደቱ ኣይነት ታማኝ የወያኔ ባሪያዎች የሕዝብን ደም በመርገጥ ከወያኔ ስልጣን ለማግኘት ኣሰፍስፈዋል። ወያኔ መላወሻ ሲያጣ ሲጨንቀው አጣብቂኝ ውስጥ ሲገባ የተቃዋሚ ካባ ኣልብሶ የሕዝብ ኣዛኝ ኣስመስሎ የሚያመጣቸው እንደ ልደቱ ኣያሌው ኣይነዎቹ የፖለቲካ ቅጥረኞች ከሞት እንደማያድኑት ማወቅ ኣለበት።
ልደቱ ኣያሌው የወያኔ የጭንቅ ሰዓት ላይ በወያኔ ሚዲያዎች ማላዘኑን ወያኔ በሚያዘጋጃቸው ስብሰባዎች ላይ መጮኹን የለመደ የበግ ለምድ የለበሰ የወያነ ኣገልጋይ ቀበሮ መሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ያውቃል። የሕዝብን ድምጽ እና ትግል ለወያኔ ኣሳልፎ የሰጠና ሕዝብን ያስፈጀ ወንደና የወያኔ ሰላይ ቢኖር ልደቱና በታማኝ ተቃዋሚነት ተጠፍጥፎ የተሰራው ኢዴፓ የሚባለው ፓርቲ ነው።
ወያኔ ለጥቅሙ ስልጣን ሊሰጣቸው እየመለመላቸው መሆኑ ከተሰማ ስለቆየ የምንዋጋው ወያኔን ብቻ ሳይሆን በተቃዋሚ ጭንብል ያሉ እንደ ኢዴፓና ኣጋፋሪው ልደቱ ኣይነቶች ቅጥረኞች የስልጣን ጥመኞቹን ጭምር ነው።የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግል በቅጥረኞች እና በአደርባዮች ኣይቀለበስም።
Image may contain: 2 people , meme and text

No comments:

Post a Comment