Saturday, March 11, 2017

የኢትዮጵያ መምህራን የስራ ማቆም አድማ አድማሱን እያሰፋ ነው



(ፎቶ ፋይል)
የለገሠ ወልደሃና ዘገባ
የህውሃት አገዛዝ ከሁሉ የተጣለ ነው ሰሞኑን ደግሞ ከዓመታት በፊት ጀምሮ የኢትዮጵያ መምህራንን አንሰተውት የነበረውን ጥያቄ እስከዛሬ ተዳፍኖ ቢቆይም ወቅቱን ጠብቆ ወደ ደባባይ ወጥቷል መምህራኑ የሚከፈላቸው ክፍያ ከወቅቱ የኑሮ ሁኔታ ጋር በማያያዝ ያነሱት የደመወዝ ጭማሪ ጥያቄ ለተቃውሞው መነሻ ቢሆንም ዋናው ምክንያት ግን የህወሓት አንባገነናዊ አገዛዝ ነው ፡፡
ከተጀመረ አንድ ሳምንት እንኳን ያልሞላው የመምህራኑ ተቃውሞ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙት መምህራን አድማዉን ተቀላቅለውታል የመምህራን አድማ ወደ ተቀናጀ ተቃዉሞ እየተቀየረ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ የመምህራኑን አድማ ተከትሎ ተማሪዎችም ተቃዉሞዉን እንደሚቀላቀሉ ይጠበቃል ፡፡
ከተለያየ ቦታው በተለያየ መንገድ ከሚደርሱኝ መረጃዎች መካከል አንደኛው እንደወረደ ፡፡
ሰላም ለገሰ! እንደምን አለህ ?
ይህን መረጃ ላካፍልህ ፈልጌ ነው።
በደቡብ ወሎ ወረኢሉ ወረዳ ውስጥ በተለያዩ ት/ቤቶች ከ4 ያላነሱ መምህራን ታስረዋል። አሁንም እየታሰሩ ነው እየታሰሩ ያሉት ደግሞ ሌሊት ነው። በዚህም የተነሳ መምህራኖች ማስተማራቸውን አቁመዋል። በተጨማሪም በወግዲ እና ከላላ ወረዳዎች ላይ ተመሳሳይ እስርና የስራ ማቆም አድማ በማድረግ ላይ ናቸው። የእስሩ ምክንያት (ወረኢሉ ወረዳ ወስጥ) በጥልቅ ተሃድሶ ስብሰባ ላይ መምህራኖች ከዚህ በፊት ያነሳናቸው ጥያቄዎች ለምን መልስ አልሰጣችሁንም (ከወልቃይት የማንነት ጥያቄ ጋር ተያይዞ ያለውን ጉዳይ) ብለው ሲጠይቁ በወቅቱ የነበረው አወያይ ስለዚህ ጉዳይ አላውቅም ብሎ ሲመልስ ተሳታፊው (የታሰረው) የማታቅ ከሆነ ለምን ትሰበስበናለህ በማለት ወጥረው ሲይዙት ረዕሰ መምህሩ (ካድሬው) ከወረዳ ጋር በመደዋወል ሌሊት እንዲታሰሩ አድርጓል። (በሌሎች አካባቢዎች የአለመግባባቱ መነሻ ከደመወዝ ጭማሪ ጋር የተያያዘ ቢሆን አሁን ግን ጥያቄው ከደመወዝ ጭማሪ አልፏል ይንን ለህዝብ አድርሰው። አመሰግናለሁ።

No comments:

Post a Comment