Saturday, March 18, 2017

ሰበር ዜና: የደሴ ማረሚያ ቤት ተሰበረ | በአካባቢው ከፍተኛ ተኩስ አለ | Updated



ደሴ ከተማ – ፎቶ ከፋይል
ከሙሉቀን ተስፋው
ዛሬ መጋቢት 9 ቀን 2009 ዓም ጠዋት የዐማራ ተጋድሎ የጎበዝ አለቆች የደሴን ማረሚያ ቤት ሰብረው እስረኞችን ማስወጣታቸውን ገለጹ። የደሴ ማረሚያ ቤት አካባቢ ከፍተኛ ተኩስ አለ።
አሁን በደረሰ መረጃ የደሴ ማረሚያ ቤት እንዲሰበር አግዘዋል የተባሉ የጥበቃ ሠራተኞች መታሰራቸው ታወቀ፤
ዛሬ መጋቢት 9 ቀን 2009 ዓ.ም ከእኩለ ሌሊት በኋላ የደሴ ማረሚያ ቤትን ተሰብሮ የተወሰኑ የግፍ እስረኞች ማምለጣቸውን ተከትሎ የጥበቃ አካላት ተኩስ ከፍተው ውጥረት ተፍጥሮ አርፍዷል፡፡ ከእስር ቤቱ ያመለጡት ሰዎች ቁጥር በትክክል እስካሁን ያልታወቀ ሲሆን ከተጋድሎው ጋር ተባባሪ ናቸው የተባሉ ተረኛ የጥበቃ ሠራተኞች መታሰራቸው ታውቋል፡፡ እስካሁን በደረሰን መረጃ መሠረት በሰው ሕይወት ላይ የደረሰ አደጋ የለም፡፡
ሆኖም በእስር ቤቱ ውስጥ ከአመለጡት ጋር አሲራችኋል የተባሉ የሕግ ታራሚዎች ለብቻ ተለይተው ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል ተብሏል፡፡
ዝርዝር መረጃዎችን እንደደረሰን እናሳውቃለን።

No comments:

Post a Comment