Monday, March 27, 2017

የመንበረ ጸባኦት ቅ/ሥላሴ ካቴድራል ካህናትና ሠራተኞች፣ በአድመኛው ‘ምክትል አስተዳዳሪ’ የወገንተኝነት በደል እየታወኩ ነው




  • አንድን ብሔር ለይቶ በመጥራት፣ “ከካቴድራሉ አጸዳቸዋለሁ” እያለ ይዝታል፤
  • ጎይትኦምን በመመካት፥ በአድልዎ ለማዛወርና በጡረታ ለማግለል ይንቀሳቀሳል፤
  • ቆቡን በኮፍያ ለውጦ፥ ምንኵስናውንና ክህነቱን በሚያስነቅፍ ነውሩ ይታወቃል፤
  • ለሓላፊነት የሚያበቃ የአስተዳደር ብቃት ሳይኖረው፣ በተጽዕኖ የተመደበ ነው፤
*                    *                    *


ቅድስት ቤተ ክርስቲያን፣ የኹሉና በኹሉ ያለች አንዲት የመኾኗ ባሕርያት፣ በአንድ በኩል፣ አባላቷ፥ በዘር፣ በብሔር፣ በቀለም፣ በሀብት ወይም በሌሎች ከሚፈጸም አድሎአዊ አሠራር የመጠበቅ መብት እንዳላቸው ያመለክታል፡፡
የካህናትንና የሠራተኞችን መሠረታዊ መብቶችና ግዴታዎች የሚደነግገው ሕገ ቤተ ክርስቲያንም፥ አገልጋዮች፣ በሕግ ፊት እኩል ኾኖ የመታየት እንዲኹም፣ ደረጃቸው በሚፈቅድላቸው መጠን፣ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሚደረጉ መንፈሳዊ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ የመሳተፍ መብት እንዳላቸው ያረጋግጣል፡፡
ለተመደቡበት አገልግሎትና ሥራ ብቁ በኾነ የአእምሮና የአካል ጥንካሬ ዝግጁ ኾነው የመገኘት፤ ራሳቸውን ከሙስና እና አድሏዊ አሠራር ነጻ አድርገው ግብረ ገብነትንና ቅንነትን በማሳየት በሙሉ ኃይልና ችሎታ የመሥራት ግዴታ ያለባቸውን ያህል፤ በሥራ ጥራትና በታማኝነት በሚያበረክቱት ውጤት ብቁ ኾነው ሲገኙም፣ የደረጃና የደመወዝ ዕድገት የማግኘት መብት ይኖራቸዋል፡፡
አገልጋይ ካህናትና ልዩ ልዩ ሠራተኞች፣ እንደ አስፈላጊነቱ ከአንድ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ወደ ሌላ ቤተ ክርስቲያን ተዛውረው የመሥራት ግዴታ አለባቸው፤ በዕድሜ ጸጋ ከሥራቸው በጡረታ የሚገለሉበት የዕድሜ ገደብ 60 ዓመት ሲመላቸው ነው፤ ነገር ግን፣ ለሥራው ጠቃሚ ኾነው ሲገኙ ተጣርቶ ሊራዘምላቸው ይችላል፤ በተለይ የአብነት መምህራን፣ የመሥራት ኃይላቸው ሳይደክም በዕድሜ ገደብ ብቻ በጡረታ እንዳይገለሉ የሥራ መብታቸው የተጠበቀ ነው፡፡
አስተዳደራዊ በደል ሲፈጸምባቸው፣ ከቤተ ክርስቲያን የሥራ ጠባይ አንጻር ሥርዓቱን ጠብቀው ቅሬታ የማቅረብና ለአቀረቡት ቅሬታም ዳኝነት የማግኘት መብት አላቸው፡፡ አድማ ማድረግና እንዲደረግ የማነሣሣት ድርጊት፣ በአስተዳደርና ሃይማኖታዊ ቀኖና የሚያስጠይቅ ተግባር ሲኾን፤ እንደ ጥፋቱ ክብደትም ከሥራና ከሥልጣነ ክህነት የሚያሳግድ ሊኾን ይችላል፡፡
በጎሠኝነት ላይ በአተኮረ አድመኝነቱ የሚታወቀውን፣ አባ ገብረ ዮሐንስ ወልደ ሳሙኤልን ግን፣ ሕግና ደንቡ የሚገዛው አይመስልም፡፡ ጥፋቱ ሊመረመርና ከሥራና ከሥልጣነ ክህነቱ ሊታገድ ቀርቶ፣ ከአንዱ አጥቢያ ወደ ሌላው እየተዛወረ ለከፍተኛ ሹመት በቅቶአል፡፡ ባለፈው ታኅሣሥ፣ የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ምክትል አስተዳዳሪ የኾነበት መንገድ ይህን ያስረዳል፡፡

ቀደም ሲል እየተማረ እንዲያገለግል የተመደበው በታዕካ ነገሥት በኣታ ለማርያም ገዳም ነበር፡፡ ከአድመኝነቱና ከፋፋይነቱ የተነሣ በሊቀ ሊቃውንቱ አቤቱታ ሲቀርብበት ግን፣ ወደ መንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በቀዳሽነት ተዛውሯል፡፡ ብዙም ሳይቆይ ቄሰ ገበዝ ለመኾን ግን ጊዜ አልወሰደበትም፡፡ በግብዝናው፣ ከካህናትና ልዩ ልዩ ሠራተኞች ጋራ የነበረው ግንኙነት በግጭትና መቋሰል የተሞላ ኾኖ እያለ፣ ባለፈው ታኅሣሥ በምክትል አስተዳዳሪነት ተመድቧል፡፡

በአድማና በጎሰኝነት ካቴድራሉን የሚያውከው ‘ምክትል አስተዳዳሪ’፣ አባ ገብረ ዮሐንስ ወልደ ሳሙኤል
ለአስተዳደር የሚያበቃ ዕውቀትና ሞያ እንዲኹም፣ የማኅበረ ካህናትና ሠራተኞች ድጋፍና ተቀባይነት ሳይኖረው በምክትል አስተዳዳሪነት ሊመደብ የቻለው፥ አድልዎን፣ ወገንተኝነትንና ጥቅመኝነትን መሠረት አድርጎ በሕገ ወጥ ቅጥር፣ ዝውውር፣ ዕድገት፣ እግድና ስንብት ሀገረ ስብከቱን እያመሰው ከሚገኘው ሥራ አስኪያጁ ጎይትኦም ያይኑ ጋራ ባለው ልዩ ግንኙነት እንደኾነ ተገልጿል፡፡ ለምደባው፣ ከፓትርያርኩ የተሰጠ ማስረጃ ስለመኖሩ አልተረጋገጠም፡፡ የሥራ ድርሻውን በተመለከተም፣ ለማኅበረ ካህናትና ሠራተኞች የተገለጸላቸውና የተነበበላቸው ነገር የለም፡፡
አባ ገብረ ዮሐንስ ወልደ ሳሙኤል፣ በትምህርቱ የቅዳሴ መምህር እንደኾነ ቢናገርም፣ የሕዝብ ተሰጥኦ እንኳ በአግባቡ ለመቀበል የማይችል ነው፤ በመቅደሱ ውስጥም የከፋ የሥርዓት ጥሰት ይፈጽማል፡፡ በሥነ ምግባሩ፣ ከአንድ መነኰስ የማይጠበቅ፥ የመብልና የመጠጥ፣ አልባሳት እየቀያየሩ የመኵነስነስ ትዝህርት ይታይበታል፡፡ የምንኵስናውን ቆብ አውልቆ፣ በኮፍያ ራሱን ሰውሮ፣ በየመሸታው እንደሚሴስን በምስል ወደምፅ ማስረጃዎች የተረጋገጠ ነው፡፡ ለዚኽም ርኵስ ተግባሩ፣ የተቸገሩ የገጠር አብያተ ክርስቲያናትን እረዳለኹ፤ እያለ ከምእመናን ገንዘብ ይቀበላል፤ የሰበሰባቸውን ንዋያተ ቅድሳትና አልባሳት በመናኛ ዋጋ ሳይቀር ይሸጣል፡፡
በቅርቡ ደግሞ፣ ካህናትና ሠራተኞች በካቴድራሉ ተስማምተው እንዳያገለግሉ የማለያየትና “አንዱ ከሌላው እንዲታኮስ የማድረግ” የጎሰኝነት አድማ እየፈጸመ እንዳለ ተጠቁሟል፡፡ አንድ ወገንን ለይቶ ለማጥቃት በተነሣለት ዓላማም፣ “ጎንደሬዎችንና ወሎዬዎችን ከካቴድራሉ አጸዳቸዋለኹ፤” እያለ በየመሸታውና በየጎዳናው ሲዝት ሰንብቶ፣ ሰሞኑን ከደርዘን ያላነሱ “የአንድ ብሔር ተወላጅ” ካህናትን ስም ዝርዝር የያዘ ደብዳቤ ለሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት በ“ድብቅ” ማድረሱ ተመልክቷል፡፡
ደብዳቤው የካቴድራሉን ማኅተምና ቁጥር መያዙ የተገለጸ ሲኾን፣ ካህናቱ ወደ ሌላ አጥቢያ እንዲዛወሩ የሚጠይቅ ነው፤ ተብሏል፡፡ “ጽ/ቤቱን ንቆ እያታለለ በራሱ ቁጥር እየሰጠ ደብዳቤ ያወጣል፤” ያሉት ምንጮች፣ በካቴድራሉ አስተዳደር ዘንድ እንደማይታወቅ ተናግረዋል፡፡
በትውልዳቸውና በስማቸው እየጠቀሰ፣ “ከዚህ ካቴድራል ማጽዳት አለብን፤” እያለ የሚዝትባቸው ካህናት፣ በውስጥ አገልግሎቱም ኾነ በጽ/ቤት ሥራቸው ክፍተት የሌለባቸው፤ ብዙዎቹም ማስጠንቀቂያ ይኹን ቅጣት የማያውቁ፤ እንዲያውም ከራሳቸው አልፎ በተጓደለው ኹሉ እየሸፈኑ የሚሠሩ ትጉሃን አገልጋዮች መኾናቸው በመረጃው ተመልክቷል፡፡ ያለዕድሜአቸው በግፍ በጡረታ የተገለሉ ሠራተኞች እንዳሉና ጡረታ መውጣት ሲገባቸው ያልወጡ መኖራቸው ተጠቁሟል፤ “ትውልዳቸው ዕድሜአቸው” የኾነላቸው ናቸው፤ ይሏቸዋል፡፡
የምክትል አስተዳዳሪ ተብዬው አባ ገብረ ዮሐንስ አካሔድ፣ በአንድ በኩል፥ ነባሩንና ሞያተኛውን ካህንና ሠራተኛ ከካቴድራሉ እያስለቀቀ ሞያ ቢኖረውም ባይኖረውም በመሰሎቹ የመተካት ነው፤ በሌላ በኩል ደግሞ፣ ብልሹ ምግባሩንና አሠራሩን የሚቃወሙትን በዝውውርና በጡረታ ስም የማራቅ ነው፤ ይላሉ፣ ምንጮቹ፡፡ ይኸው እኵይነቱ፣ በካቴድራሉ የቄሰ ገበዝ እና ሊቀ ዲያቆን ምርጫ ወቅት ጭምር እንደታየ ተጠቅሷል፡፡
በአሠራሩ፣ የተሻለ ብቃት ያላቸው ዕጩዎች በጥቆማ ከተለዩ በኋላ በድምፅ ብልጫ እንደሚመረጡ እየታወቀ፣ ከፍተኛ ድምፅ ያገኙት ካህናት እርሱ የማይፈልጋቸው በመኾናቸው ብቻ፣ ድምፁ በአግባቡ አልተቆጠረም፤ በሚል ውጤቱን ውድቅ አድርጓል፡፡ በምትኩ፣ ካህናቱንና ሠራተኛውን በማሸማቀቅና በአድማ በመከፋፈል በድጋሚ በተካሔደው ምርጫ የፈለጋቸው እንዲመረጡ አድርጓል፡፡ “የጎሰኝነት አድመኝነቱ ግልጽ የወጣበት አጋጣሚ ነበር፤” ይላሉ ታዛቢዎች፡፡
በቃለ ዐዋዲው እንደተደነገገው፦ በሞያ፣ በሥራ ጥራት፣ በታማኝነት በሚመዘገብ ውጤት ለከፍተኛ ምደባ መብቃት መብት ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን አንዲት እንደመኾኗ፣ ተዛውሮ መሥራትም ኾነ በዕድሜ ገደቡ በጡረታ መገለል አግባብነት አለው፡፡ የአባ ገብረ ዮሐንስ ወልደ ሳሙኤልና ግብረ አበሮቹ፥ በወገንተኝነት ላይ ያተኮረና ሞያተኞችን የማሳደድ አካሔድ ግን፣ ግልጽ የወጣ አስተዳደራዊ በደል ነው!! ሳይታረም ከቀጠለ ደግሞ፣ ካቴድራሉን “መሪ የሌለው የታወረ ቤት” ሊያሰኘው እንደሚችል ግልጽ ነው፡፡ በረከታቸው ይድረሰንና እንደ አባ መዓዛ ቅዱሳን(በኋላ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል) ያሉት ታላላቅ አበው፣ በዚያው ሓላፊነት ተቀምጠው ለሠሩበት ካቴድራልም ኀፍረት ነው የሚኾነው፡፡
የቤተ ክህነታችን አስተዳደር፣ ከአድልዎና ወገንተኝነት ሙሉ በሙሉ ያልተላቀቀና የቤተ ክርስቲያናችንን ታላቅነትና ተሰሚነት ክፉኛ እየጎዳው መኾኑን፤ በምእመናን ላይም እምነት ማጣትንና ቅሬታን እያሳደረ መኾኑን በየቃለ ምዕዳናቸው ያሰሙን ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩም አስቸኳይ የእርምት ርምጃ ሊወሰዱበት ይገባል፤ ልዩ ሀገረ ስብከታቸው አዲስ አበባ፦ በዚኽ መሰሉ ምክንያታዊ ያልኾኑ ዝውውሮች፤ በደላላ መር የሠራተኛ ቅጥሮች፤ ወቅታዊ ባልኾነና ባልተጠና የደመወዝ ጭማሬ ጋራ በተያያዙ አስተዳዳራዊ ቀውሶች ውስጥ በመዘፈቁ፣ ቤተ ክርስቲያን ለውርደት፤ ካህናትና ሠራተኞች ለረኃብና እንግልት እየተዳረጉበት

No comments:

Post a Comment