የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ ወጣቶች ጉዳይ ምክትል ኃላፊን ጨምሮ ዘጠኝ ሰዎች የሽብር ክስ ተመሰረተባቸው
(በሰማያዊ ፓርቲ ብሄራዊ ሸንጎ የህዝብ ግንኙነት ንዑስ ኮሚቴ)
የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በ1996 ዓ/ም የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 35 ፣ 32/1/ሀ እና የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀፅ 4 ሥር ተላልፈዋል በሚል ክስ የመመረተባቸው ሲሆን አቃቢ ህግ በክሱ ላይ የአርበኞች ግንቦት 7 ድርጅት ውስጥ አባል በመሆን ከሀገር ውጭ ከሚገኙ የሽብር ቡድኑ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ግንኙነት በመፍጠርና ተልዕኮ በመቀበል በሀገር ውስጥ አባላትን በመመልመልና በማደራጀት የኢትዬጵያ መንግስት በትጥቅ ትግል በሀይል የመለወጥ የፖለቲካ ዓላማ በመያዝ የሀገሪቱን ሕገ- መንግስታዊ ፣ ፖለቲካዊ ፣ኢኮኖሚያዊ ና ማህበራዊ ተቋማትን ለመናድና ለማፈራረስ በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ቦታዎች ላይ አባላትን በመመልመልና በማደራጀት የሽብር ተግባር እንዲፈፀም ተልዕኮ በመስጠትና በመቀበል የሽብር ድርጅቱን አላማ ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ናቸው በማለት በክስ ዝርዝሩ ላይ ገልፀዋል።
በአቃቤ ህግ እንደተገለፀው ተከሳሾቹ አድራሻቸው አዲስ አበባ ሲሆን
1. ክንዱ መሐመድ አስፋው
2. መሐመድ ካሳ እብሬ
3. ደረጄ አያሌው ህብስቴ
4. ኤፍሬም ሰለሞን ለማ (የቀድሞው አንድነት የወጣቶች ጉዳይ ምክትል ኃላፊ (ከታች በምስል የሚታየው ))
5. አብርሃም ሰለሞን ከበደ ( የቀድሞው አንድነት አባል)
6. ጴጥሮስ ጉግሳ ለማ
7. ዘሪሁን አግዜ ካሳዬ
8. ተመስገን አልማው በላይ
9. ግሩም መርቅነህ ተገኑ ናቸው።
የአቃቤ ህግ ክስ እንደሚያሳየው ዳዊት ከሚባል የሽብር ቡድኑ አመራር ጋር በስልክና በዋትስ አፕ ግንኙነት በመፍጠር በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አካባቢዎች የነዳጅ ማደያዎችን ለማቃጠል ሲንቀሳቀሱ ተይዘዋል የሚል ነው።
No comments:
Post a Comment