በወያኔ እስር ቤት የሚገኙት የፖለቲካ እስረኞቹ አቶ በቀለ ገርባ አቶ ደጀኔ ጣፋ የረሃብ አድማ ጀመሩ።
በቂልንጦ ማረሚያ ቤት የሚገኙ የእስረኛ ቤተሰቦች ታሳሪ ቤተሰቦቻቸውን አግኝተው ምግብ ማቀበል እንዳልቻሉና ሲያገኟቸውም ማረሚያ ቤቱ ውስጥ ከፍተኛ ችግር ስላለባቸው ችግራቸው እስኪፈታ ምግብ እንደማይቀበሏቸው እንደነገሯቸው ለአሜሪካ ድምጽ ገለጹ።የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ ልጅ ወ/ት ቦንቱ በቀለና የፓርቲው ዋና ፀሐፊ አቶ ደጀኔ ጣፋ ባለቤት ወ/ሮ አሰለፈች ሙላት ዛሬ ወስደውት የነበረውን ስንቅ ይዘውት ወደቤት እንደተመለሱ ሲናገሩ የሕግ ጠበቃቸው ደግሞ ደንበኞቻቸውን ማግኘት እንዳልቻሉ ተናግረዋል። VOA
የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ እና የፓርቲው ፀሐፊ አቶ ደጀኔ ጣፋ ቤተሰቦች እስረኛ ቤተሰቦቻቸው በማርሚያ ቤቱ ውስጥ ለእስረኛ የሚሰጥ መብት ለእነሱ ስለተነፈጋቸው ማረሚያ ቤቱ መብታቸውን እሲያከብርና ውሳኔ እስኪሰጣቸው ምግብ እንደማይቀበሉ እንደነገሯቸው ተናገሩ።
No comments:
Post a Comment