Friday, March 17, 2017

የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎችና ክለቡ ቆሼ አካባቢ አደጋ የደረሰባቸውን ወገኖች ያሉበት ቦታ ሄደው አጽናኑ




በዛሬው እለት የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ፣ የደጋፊዎች ማህበር እንዲሁም ደጋፊዎች ባዋጡት የገንዘብና የቁሳቁስ እርዳታ የክለቡ ስራ አሰኪያጅ ፡ የደጋፊ ማህበር የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ፣ የጽህፈት ቤት ሰራተኞች እና ከአምስት መቶ በላይ ደጋፊዎች በተገኙበት ሰሞኑን በተለምዶ ቆሼ አካባቢ ተብሎ በሚጠራው ሰፈር አደጋ የደረሰባቸውን ወገኖቻችንን የተለያዩ ምግቦች፣ ውሀ፣ በርካታ አልባሳት እና የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን በቦታው ድረስ በመገኘት ለተቋቋመው ኮሚቴ ያበረከቱ ሲሆን በየሀዘን ቤቱም በመገኘት ለሟች ቤተሰቦች መጽናናትን በመመኘት በአካባቢውም የሀዘን መግለጫ ባነር በመስቀል እና የጧፍ በማብራት ስነስርዓት በማካሄድ ተመልሰዋል፡፡
በቀጣይም የቤት ቁሳቁሶችን እና አልባሳትን በዋናው የደጋፊዎች ማህበር ጽ/ቤት በማምጣት ተሰብስቦ የተጎዱት ወገኖች ጋር መሄድ እንደሚቻል የደጋፊ ማህበር ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሰለሞን ታምራት ገልጸዋል፡፡
ለተጎዱ ወገኖቻችንን መጽናናትን እንመኛለን፡፡
የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ጽ/ቤት እና ደጋፊዎች ማህበር፡፡

No comments:

Post a Comment