
ከአምስት ምዕተ ዓመታት በላይ የታሪክ ባለቤት የሆነችው ጠለምት በጎንደር ክ/ሃገር የምትገኝ አማርኛ ተናጋሪና የአማራ ባህልና ወግ የሚከተል ሕዝብ የሚኖርባት ስለመሆኑ በቀደምት የታሪክ መዛግብት ዉስጥ ሰፍሮ ይገኛል። የጠለምትን መልከዓ-ምድር አቀማመጥን ስንመለከት፤ በሰሜን ተከዜ ወንዝን ተከትሎ ትግራይ፤ ክ/ሃገርን በምሥራቅ እንዲሁ ተከዜን ወንዝን ተከትሎ ተንቤን አውራጃ(ትግራይ) እና ዋግ አውራጃ(ወሎን)፤ በምዕራብ ወልቃይትና ጠገዴ፤ በደቡብ በተፈጥሮ ሃብት የበለጸጉ በጎንደር ክፍለ-ሃገር የሚገኙ እንደ ሰንሰለት የተጠላለፉ የሰሜን ተራራዎች ጋር ይዋስናል።
የወያኔ አገዛዝ ተከዜን ወንዝ የተሻገረው “ታላቋን ትግራይ” ለመመሥረት ባቀደው እቅድ መሠረት፤ ለምና ወሃ-ገብ የሆኑትን የጎንደር ወረዳዎችን ወልቃይት፣ ጠገዴና ጠለምትን በተቆጣጠሩበት በ17 ዓመት የሽፍትነት ጊዜና ከ25ዓመት በፊት መላ ኢትዮጵያን በሃይል በመዳፉ ሥር ባሰገባበት ወቅት፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ይወያኔ ታጋይዮች የነበሩና ደጋፊዎቻችወን አምጥቶ በወልቃይት፣ በጠገዴና በጠለምት አስፍሮ ለዘመናት በጋራ አብሮ ይኖር የነበረን ሕዝብ እርስ በርሱ እንዲጋጭና እንዲጠላላ እያደረገ ይገኛል።
ወያኔ ካለፉት 25 ዓመታት ጀምሮ፤ የጠለምትን ሕዝብ በመዳፉ ሥር ካስገባ በኋላ፤ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን እንዲሁም የአማራን ሕዝብ ለማጥፋት ባለው እቅድ መሠረት፤
1ኛ) በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች ከትግራይ በማምጣት ኣስፍሯል።
2ኛ) ከ25,000 በላይ የሚሆኑ የኤርትራ ስደተኞችን በማይ ኣይኒና በኣዲሃሮሽ በተባሉ መንደሮች በማስፈር ለፖለቲካ ፍጆታ እየተጠቀመባቸው እንደሆነና ለዚሁም ማረጋገጫ የዛሬ ኣንድ ወር ገደማ የትግራይና የኤርትራ ባህላዊ ባንድ በጋራ በመሆን አመታዊ የህወሃት በዓል ላይ መጫወታቸዉንና በኤርትራና በትግራይ ህዝብ ላይ ምንም አይነት ልዩነት ኣለመኖሩንና አንድ ሕዝብ መሆኑን በግልፅ ባደባባይ መናገራቸው ላለሙት ዓላማ ገላጭ መሆኑን ያስረዳል።
ሰፋሪዎቹም ባአገሬው ሐዝብ ላይ ይህ ቀረሽ የማይባል ግፍና መከራ እየፈፀሙ ይገኛሉ። ተወልደው ባደጉበትና እትብታቸዉ በተቀበረብት አገር እንደ ሁለተኛ ዜጋ በመቆጠራቸው ግፍና መከራው ከሚገባው በላይ መሸከም ሲያቅታቸው በህወሃት ከተወሰደባቸው ህብት ንብረት የተረፈዉን እንኳን ለመውሰድ እድሉን ባለማግኘታቸው ሕይወታቸውን ለማትረፍ ሲሉ ስፍር ቁጥር የለላቸው ያገሬው ተወላጅ ባላባቶች ቀያቸዉን እየተዉ ወደ ጎረቤት አገር(ሱዳን)፥ወደ ጫካና ወደ ተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች ተሰደዋል። ያሠፈራቸውን ቅጥረኞችን በማስታጠቅ፤ በጠለምት ሕዝብ ላይ ወደር የሌለው ጭፍጨፋ (genocide) እና የዘር ማጥፋት (ethnic cleansing) በማያቋርጥ ሁኔታ አካሂዷል። እያካሄደም ነው።

ስለሆነም ጀግናው የጠለምት ሕዝብ ዛሬም እንደ ቀደምቱ ወያኔ የሸረበዉን ሴራ ለማክሸፍ “ጠለምት ጎንደር እንጂ ትግራይ አይደለችም፥ ሆናም አታውቅም” የሚለውን የጠለምት ታሪካዊ ምንነት አስረግጠህ ንገራቸው። ጠለምት የትግራይ ነው በሚል እነሱ ሊጠሩት ባስቡት የድጋፍ ሰልፍ ላይ በመገኘት እውቅና እንዳትሰጥዋቸው። ጀግናው የጠለምት ሕዝብ ሆይ! የትግራይ ነፃ አውጭ ግንባር (ወያኔ) አገዛዝን አሽቀንጥረህ በማጣል የአማራ ማንነትህንና የመሬት ባለቤትነትህን ለማስመለስ የጀምርከውን ትግል እንዳንተው ለአምራ ማንነቱንና የመሬት ባለቤትነቱን ለማስመለስና መብቱን ለማስከበር ዉድ ህይወቱን እየገበረ ካለው ጀግናው የወልቃት ጠገዴ እንቅስቃሴ ጋር በማቀናጀት ትግሉን አጠናክረህ ቀጥል። እኛም በውጭ የምንኖር የጠለምት፥ወልቃይትና፥ጠገዴ ተወላጆች በሙሉ በያለንበት በመሰባሰብና በመደራጀት፤ የትግራይ ነፃ አውጭ ግንባር (ወያኔ) በወገኖቻችን ላይ የሚያካሂደውን ጭፍጨፋ (genocide) እና የዘር ማጥፋት (ethnic cleansing) በማጋለጥና፤ ከወያኔ ጨቋኝ አገዛዝ ቀንበር ነፃ ለመውጣት የምታደርጉትን ትግል በማንኛው መልክ ለመርዳት እስከመጨረሻው ድረስ ከጎናችሁ መሆናችንን ለማረጋገጥ እንወዳለን።
የጠለምት፥ወልቃይትና የጠገዴ የማንነት ጥያቄ በሃቀኛ የሕዝብ ትግል ይረጋገጣል!
የኢትዮጵያ እንድነት ለዘላለም በክብር ይኑር!!
No comments:
Post a Comment