
በአርበኛ ጎቤ እግር ተተክቶ ጦሩን ሲመራ የነበረው አርበኛ ሻንቆ ‹‹የመሪያችን ሞት በሚገባ ተበቅለናል፤ ተጋድሎአችን እስከ ያለምንም ጥርጥር ያሸንፋል›› ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡ የዐማራው ጦር የተማረከውን ወታደር ጨምሮ የ14 ወታደሮችን ሙሉ ትጥቅ የማረከ ሲሆን ከባለፈው ወር ወዲህ የተገኘ ታላቅ ወታደራዊ ድል እንደሆነ ተገልጧል፡፡
የዐማራ አርበኞችን ለማጥቃት የመጣው ጦር መሣሪያውን በዱር እየጣለ ወደ አቅራቢያ ከተማ የሸሸ ሲሆን የአካባቢው ገበሬዎች በዱር የወዳደቀ ብዙ መሣሪያ እየያዙ እንደሄዱም ለማወቅ ተችሏል፡፡
(ማሳሰቢያ፤ በአርበኞቹ ጥያቄ መሠረት ጦርነቱ የተካሔደበትን ቦታ ከመግለጽ ተቆጥበናል)
የዐማራ ተጋድሎ ያሸንፋል//
No comments:
Post a Comment