Tuesday, March 28, 2017

ግንቦት ሰባት የዚህን ያህል በህዝብ ላይ እቃቃ መጫወት ግን ለምን አስፈለገ ? አንሶ መገኘትስ ትርፉ ምንድን ነው ? (ኄኖክ የሺጥላ)

   


የአቶ አበበ ቦጋለን ቃለ መጠይቅ ከሰማሁ በኋላ ፥ ግንቦት ሰባት ውስጤ ነው የሚሉት እና እራሳቸውን በዲሲ ግብረ ሃይል ውስጥም አካተው በድርብ የግብረሃይሉን ስራ የሚሰሩት የግንቦት ሰባት ደጋፊዎች ትዝ ብለውኝ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ!
እነዚህ ልጆች እኮ የግንቦት ሰባት ጦር እያሉ ነበር የሚያወሩት። እነዚህ ልጆች ግንቦት ሰባት በአመራር ደረጃ በየ አገሩ ያሉ የአማራ ልሂቃን ናቸው ብለው ቪዲዮ ሰርተው እስከ መልቀቅ ደርሰዋል ። እነዚህ የዋህ እና አገራቸውን የሚወዱ ልጆች ከማንም በተሻለ መልኩ አንዳች ሳይሳሱ እኮ ነው ገንዘባቸውን ለዚህ ድርጅት የሚያዋጡት። እንደውም በቅርብ የማውቃቸው « እኔ ከድርጅቱ ጋር ያለኝን ልዩነት በገለጥኩ ሰዓት » አይንህ ለአፈር ከማለት አልፈው ወደ ድረ ገጥ ብቅ በማለት « አሁን ወያኔን እየተዋጋ ያለው ጦር የማን ጦር መሰለህ ? » እስከማለት ደርሰውም ነበር።
መሳይ መኮንን የዛሬ 2 አመት ገደማ ኤርትራ ደርሶ በመጣ ሰሞን ፥ የግንቦት ሰባት ጦር ይህንን ይመስላል በማለት ደጋግሞ በሲያትል ለሚገኘው ህዝብ ሲገልጥ ሰምቻለሁ። በጆሮዬ! የጦሩንም ኦዲዮ ቪዲዮ ሲያሳይ አይቻለሁ ፥ በአይኔ !
አርበኛ እና ታጋይ ብርሃኑ ነጋ ፥ አርበኛ እና ታጋይ ኤፍሬም ማዴቦ ፥ አርበኛ እና ታጋይ ታደሰ ብሩ ፥ አርበኛ እና ታጋይ ስንታየሁ ቸኮል ፥ አርበኛ እና ታጋይ አንዳርጋቸው ፅጌ ሁሉም የግንቦት ሰባት ጦር ሲሉ ሰምተናል። ማስረጃውም አለ! ታዲያ ዛሬ ከመሬት ተነስቶ ጦር አይደለም ሬዚዝታንስ አርሚ ነው ማለት ከምን የመጣ ነው ? ( ልዩነቱስ ምንድን ነው ? ) ሬዚስታንስ አርሚ ካልደረሱበት አይደርስብም ? ሬዚስታንስ አርሚ ምራቁን ከመረብ መልስ ተፍቶ « እስኪ ወንድ ከሆንህ ምራቄን እርገጣት » የሚል ነው ? ጦር ግን ሄዶ የተተፋውን ምራቅ የሚረግጥ ነው ? ምራቁ ሲረገጥ እሱ ቆዳ ጫማ ነው የለበሰው ስላለማለቱስ ምን ማረጋገጫ አለን ? ሰው ተደራጅቶ ሲቀልድ እንዴት ያስቃል ! እያዩ ፈንገስን ለመሆን ኤርትራ ድረስ መሄድ ለምን አስፈለገ ? እዛው ዲሲ ጣይቱ የባህል መአከል ኮሜዲውን ብታቀርቡ አለምዬ ጥሩ ሰው ነች እምቢም አትላችሁ!
እርግጥ አቶ ነአምን ዘለቀ ፥ ወያኔን ለመዋጋት አቅማችን አይፈቅድም ብለው ፍንጭ ሰጥተውን ነበር ፥ ምናልባት አቶ አበበ ቦጋላ ያንን ፍንጭ ቦግ እያደረጉት ይሆን ? የዚህን ያህል በህዝብ ላይ እቃቃ መጫወት ግን ለምን አስፈለገ ? የዚህን ያህል አንሶ መገኘትስ ትርፉ ምንድን ነው ?
ኄኖክ የሺጥላ

No comments:

Post a Comment