Sunday, March 19, 2017

የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገሥት መንግስት ባለ ሙሉ ስልጣን አልጋ ወራሽ ወሰንሰገድ ወዳጆ ጎበና ዳጨ (አቻምየለህ ታምሩ)

    


17352101_1405378942817384_2454853912304545886_n 17264172_1405378506150761_636814000572663224_n
የODF አመራር አባል የሆነው «ፕሮፌሰር» ሌንጮ ባቲ በኢሳት ቀርቦ «ልጅ እያሱ ሊነግስ ያልቻለው አበሾች ወይንም በሱ አባባል አቢሲኒያንስ ኦሮሞ በኢትዮጵያ ላይ እንዲነግስ ስለማይፈልጉ ነው» ብሎን ነበር። ከሰሞኑ ደግሞ ይህንን የሌንጮን ንግግር አንዱ ደቀመዝሙር ነጥቆ «ልጅ እያሱ ያልነገሰው ኦሮሞ ስለሆነ ነው» ሲል ደገመው። ይገርማል። ዘመኑ የካድሬ ሆነ። አንዱ የተናገረውን የሚደግም እንጂ የሚመረምር፤ አጣርቶ የሚናገር ጠፋ!
የዘር ፖለቲከኞች ተከታዮች የሚሽቀዳደሙት የዘራቸው አባል የሆነ ፖለቲከኛ የተናገረውን ለማስተጋባት እንጂ ሰለተናገረው ነገር እውነትነት መረጃና ማስረጃ አፈላልጎ ለማጣራት አይደለም። ባለፈው ሰሞን አንዷ እዚህ ፌስቡክ ላይ በሰራችው ቪዲዮ «ምኒልክ ጡት ቆርጧል» ያሏትን ይዛ፤ የእናቴን ጡት ምኒልክ ስለቆረጠው ጡት ሳልጠባ ነው ያደግሁት አለች። ይህንን የተናገረችው ልጅ እድሜዋ 25 አይሞላም። ለዚች ልጅ ምኒልክ ካረፉ 103 ዓመታቸው መሆኑን እንኳ አላስተማሯትም።
ከታች የሚታየው ምስል የወሰንደገድ ወዳጆ ጎበና ዳጨ ፎቶ ነው። ወሰንሰገድ ወዳጆች ጎበና ዳጨ የታዋቂው የኦሮሞ ተወላጅ ኢትዮጵያዊ ጀኔራል የጎበና ዳጨ የልጅ ልጅ ነው። ወሰንሰገድ ወዳጆች ጎበና ዳጨ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገሥት መንግስት ባለ ሙሉ ስልጣን አልጋ ወራሽ እንዲሆን በዳግማዊ አጤ ምኒልክ ተመርጦ ነበር። ግን ሞት ቀደመውና ዳግማዊ አጤ ምኒልክን ተክቶ በዙፋናቸው ሊቀመጥ አልቻለም። ወሰንሰደግ እንደሞተ ራስ መኮነን ለመንበሩ ታጩ። ራስ መኮነንም ሞቱ። ራስ መኮነን ሲሞቱ ልጅ እያሱ ታጩ። ልብ በሉ! ከእያሱ በፊት የዳግማዊ አጤ ምኒልክ አልጋ ወራሽ ሆኖ የተመረጠው የጎባና ዳጨ ልጅ የደጃዝማች ወዳጆ ጎበና ልጅ ወሰን ሰገድ ኦሮሞ ነበር። አባቱ ደጃዝማች ወዳጆ ጎበና ደግሞ የሀድያ ገዢ የነበሩ ሲሆን በሀድያ ላይ የተሾሙት በአባታቸው በራስ ጎበና ዳጨ ደጃዝማች ተብለው ነበር። በፕሮፌሰር ሌንጮ እምነት ልጅ እያሉም ኦሮሞ ነው።
እንደ ሌንጮ ባቲ ንግግር በኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት ወንበር ላይ ኦሮሞ እንዲነግስ ካልተፈለገ እንዴት ብለው «አበሻው» ዳግማዊ አጤ ምኒልክ «ኦሮሞዎችን» ልጅ እያሱንና የደጃዝማች ወዳጆ ጎበናን ልጅ ወሰንሰገድ ጎበናን አልጋ ወራሻቸው አድርገው መረጧቸው? ብለን ጠይቀን መልስ ያጣንበት ሁኔታ ነው ያለው 🙂

No comments:

Post a Comment