Sunday, March 26, 2017

ጃንሆይ ከቤተመንግስት ወደ አራተኛው ክፍለ ጦር ስለተወሰዱባት ቮልስቫገን ተገኘች ።

   


ቮልሷ ተገኝታለች! !!!!!! ታርጋ ቁጥሯም 39762
ኢዮብ ዘለቀ
ከወራት በፊት ጃንሆይ ከቤተመንግስት ወደ አራተኛው ክፍለ ጦር ስለተወሰዱባት ቮልስቫገን መኪናን በተመለከተ አንዲት አጠር ያለጹሀፍ ስጽፍ እግረመንዴንም ይህቺ ታሪካዊ ቮልስ ቫገን በአሁን ስአት በማን እጅ ነች የሚል ሀሳብ አንስቼ ነበር ፤ ይህንን ተከትሎም የተለያዮ ሀሳቦች መንጸባረቃቸው ይታወሳል.. ..ብዙዋች አስተያየት ሰጭዎች ይህች ቮልስ በአሁን ሰአት የጋዜጠኛ ደረጄ ሀይሌ ንብረት ሆናለች ብለው አስተያየታቸውን ሲያሰፍሩ ሌሎች ደግም ይህ በፍጹም ከሀቅ የራቀ ነው ትክክለኛ መረጃ አይደለም በማለት ሀሳባቸውን ለማስቀመጥ ሞክረዋል ።
IMG_20170326_120321
እነዚህን የተምታቱ ሀሳቦች ለማስታረቅ ዛሬ ከከሰአት በኃላ ከሌሎች ጋዜጠኛች ጋር በመሆን አፍንጮ በር አካባቢ ወደሚገኘው የጄነራሉ ቤት አምራሁ ፤ በዛም ከባለቤታቸው ከ ወ/ሮ አፀደ ሀብተሚካኤል ጋር ጥሩ ጊዜ አሳለፍን ፤በዚህ ቆይታችን ስለታሪካኛው ቮልስ ብዙ ጨዋታዋችን አጫወቱኝ ፤ከጭውውታችን መሀል ያገኘሁትን እንደሚከተለው በአጭሩ አቅርቤዋለሁ ።ሌሎች ዘርዘር ያሉ ጽሁፎችን በሌላ ጽሁፍ እመለሳለሁ ።
*********************************************
እማማ አፀደ ከጀነራል ሉሉ ጋር በትዳር ለ 46 ዓመታት ኖረዋል፤ በእዚህ የረጅሙ ዘመን የትዳር ቆይታቸው እጅጉን ደስተኛ እንደነበሩ ይገልጻሉ ፤ ባለቤታቸው ጀነራል ሉሉ ለረጅም አመታት የቤተመንግስት የተሽከርካሪ ክፍል ሀላፊ ሆነው ሰርተዋል ከዚህም በተጨማሪም የጃንሆይ ሾፌርም ነበሩ ፤ የተለያዮ የሀገራት መሪዎች ወደ ኢትዮጵያ ብቅ ሲሉ ከአየር መንገድ ወደ ቤተመንግስት የሚያደርሱ ፤እንዲሁም ጉብኝታቸውን ጨርሰው ከሀገር ሲወጡ እስከ አየር ማረፊያ ድረስ የሚሸኙ ተመራጭ ሾፌር እኝህ ሰው ነበሩ ።
ጄነራል ሉሉ ታሪካዊቷን ቮልስ የገዟት በ1960 ዎቹ የነዳጅ ዋጋ ባልተለመደ መልኩ በመናሩ ነዳጅ ትቆጥበልኛለች በማለት ነበር ፤ በዚህም መሠረት ከሰኛ እስከ አርብ ከቤት ወደቤተመንግስት ፤ከቤተመንግስት ወደ ቤት ለመመላለስ ይህችን ቮልስ ለአመታት ተጠቅመዋል /ማርቼዲስ መኪናቸውን ከቅሜና እሁድ በቀር አይነኳትም ነበር/ እስከ 1967 ዓ.ም ድረሰ የጀነራሉና የቮልሷ ቁርኝት በዚህ መልኩ ቀጥሏል ።
1967 ዓ.ም ጃንሆይ ከስልጣን ሲወርዱ ደርጎች ጃንሆይን ከቤተመንግስት ወደ አራተኛው ክፍለ ጦር የወስዷቸው በአጋጣሚ በግቢው ውስጥ ቆማ በነበረችው በዚህች ታሪካዊት ቫልስ ነበር ፤ ይህቺ ቮልስ ጃንሆይን ካደረሰች በሁዋላ ወዲያውኑ ለጀነራሉ እንድትመለስ ተደርጔል ።
ሆኖም ግን ጃንሆይ ከወረዱ ከ 16 ቀን በሁዋላ ወታደሮች አፍንጮ በር አካባቢ በሚገኘው በጀነራል ሉሉ መኖሪያ በማምራት ጄነራሉንና ቮልሷን በቁጥጥር ስር አዋሉ ፤ጄነራሉ ለ8 አመታት ያህል ታስረው ከቀዮ በኃላ በነጻ የተለቀቁ ሲሆን ፤ የመኪናዋ እስራት ግን ለ20 አመታት ዘልቋል ።
እማማ አጸደ ከ 1983 ዓ.ም አንስቶ ለ3 አመታት ያህል በቤተመንግስት ጋራዥ በእስራት ላይ የነበረችውን የባለቤታቸውን መኪና ለማስመለስ ብዙ ደክመዋል ፤ ሁላም ላይ ድካማቸው እውን ሆነና ይህቺን ታሪካዊ መኪና በእጃቸው አስገብተዋል ፤ዛሬም ድረስ ይህች ቮልስ እሳቸው ጋር ትገኛለች ፤ እስከ እለተ ሞቴ ቮልሷ ከእጄ አትወጣም የሚል አቋምም አላቸው።
እማማ አፀደን ዛሬ እርጅና ተጫጭኖዋቸዋል በቤታቸው የሚገኙትን የባለቤታቸውን የተለያዮ አልባሳት፣ ሜዳሊያዋች እንዲሁም ከተለያዮ የሀገራት መሪዎች የተሸለሟቸውን ሽልማቶች ለሚመለከተው የመንግስት አካላት ለመስጠት ፍላጎት ቢኖረኝም የሚረከበኝ አካል አጣሁ እያሉ ነው ።

No comments:

Post a Comment