Sunday, March 19, 2017

ፈይሳ ሌሊሳ የኒውዮርክ ግማሽ ማራቶንን አሸነፈ | የተለመደው ተቃውሞውን ለዓለም አሳየ

  





(ዘ-ሐበሻ) ከሪዮ ኦሎምፒክ ጀምሮ በተወዳደረባቸው ውድድሮች ሁሉ እጆቹን ወደላይ በማጣመር የኢትዮጵያን ሕዝብ ብሶት ለአለም የሚያሰማው ጀግናው አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ከደቂቃዎች በፊት በየተፈጸመውን የኒውዮርክ ግማሽ ማራቶን አሸነፈ:::
ፈይሳ ሌሊሳ ውድድሩን ለመጨረስ የፈጀበት ሰዓት 1:00:04 መሆኑም ታውቋል:: ከ20 ሺህ በላይ ሯጮች በተሳተፉበት በዚህ ውድድር ላይ ፈይሳ ውድድሩን አሸንፎ ሲገባ እጆቹን ወደላይ በማጣመር በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የሰብአዊ መብት ረገጣና ጭቆና ዳግም ለዓለም አሳይቷል::
አትሌት ፈይሳ በቅርቡ ቤተሰቡ ወደ አሜሪካ የመጡለት ሲሆን ሲያሸንፍ ልጆቹና ባለቤቱ እዚያው ኒውዮርክ አብረው ነበሩ:: የስፖርት ባለሙያዎች “ቤተሰቡ አጠገቡ መኖሩ ተጨማሪ ኃይል ሳይሰጠው አይቀርም ሲሉ” አስተያየት ሲሰጡ ተደምጧል:: በተወዳደረበት ውድድር ሁሉ ተቃውሞን ማሳየት እንደሚቀጥል ለውጭ ጋዜጠኞች መግለጹም አይዘነጋም:: “ለማም ሃገር ዜግነቴን ቀይሬ መሮጥ አልፈልግም” የሚለው ፈይሳ በመጪው ወር ኤፕሪል 23, 2017 ከሃገሩ ልጅ ቀነኒሳ በቀለ ጋር በለንደን የሚያደርገው ትንቅንቅ በጉጉት ይጠበቃል::

1 comment: