(ይድነቃቸው ከበደ)
–
አዋጁ የዴሞክራሲ መብት ሙሉ በሙሉ የሚገድብ ፣እንዲህም አገሪቷ በወታደራዊ ዕዝ እንድትመራ ያደረግ ከመሆኑ ባለፈ አዋጁን ተገን በማድረግ የዜጎች ሰብዓዊና ዴሞክራ መብት እየተጣሰ እንደሆነ በማሳሰብ ፣አዋጁ ሙሉ በሙሉ እንዲነሳ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪዎች እና የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራር እና አባላት ፣ አንዲሁም የተለያዩ ለጋሽ አገራት እየተጠየቁ የገኛሉ ። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የተወሰኑ ክልከላዎች በዛሬው ዕለት ተነስተዋል ። እነሱም ፦
–
1ኛ.ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማንኛውንም ሰው በቁጥጥር ስር ማዋል እና ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ብርበራ ማድርግ ተሽሯል ።
–
2ኛ.በሬዲዮ፣ ቴሌቪዥን፣ ጽሑፍ፣ ምስል፣ በፎቶ ግራፍ፣ ቴያትር እና በፊልም የሚተላለፉ መልዕክቶችን ለመቆጣጠር እና ለመገደብ የወጣው እገዳም ተሽሯል
–
3ኛ.የተዘረፉ ንብረቶች በመፈተሽ ለባለቤቶቹ እንዲመለሱ ማድረግ እና የመሳሰሉ እርምጃዎችም ተሽሯል፡፡
–
4ኛ.በመሰረተልማት፣ በፋብሪካዎች እና መስል ተቋማት አካባቢ ከምሽቱ 12 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12 ሰዓት ከተፈቀደለት ሰራተኛ በስተቀር ማንኛውንም እንዳይንቀሳቀስ የተላለፈው የሰዓት እላፊ ተሽሯል።
–
የፊታችን መጋቢት 28 ቀን 2009 ዓ.ም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የሚያበቃበት ቀን እንደሆነ ይጠበቃል ። በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምክንያት በተለያየ ፖሊሲ ጣቢያ ከ3 ወር በላይ ታስረው የነበሩ እስረኞች እየተፈቱ ነው። ይሁን እንጂ እስካሁን ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩ ፣የቀድሞ አንድነት ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ምክትል ኃላፊ የነበረው አቶ ዳንኤል ሺበሺ እና ጦማሪ እዮኤል ፍስሃ ይህ እንዲሁም፣ ሌሎች እስረኞች ይህ መረጃ ይፋ እስከሆነበት ጊዜ ድረስ በአስቸኳይ አዋጁ ምክንያት በእስር ላይ ይገኛሉ። ጋዜጠኛ አናኒያ ሶሪ ከሁለት ቀን በፊት ከእስር ተፈቷል ።
No comments:
Post a Comment